#እኔ_እና_አንቺ
ሒሳብ ፣ ስሌት ፣ ቀመር
ስሜት ፣ እውነት ፣ ፍቅር
አንድ እኔ ማንነት . . .
ዜሮ አንቺነትሽን ቆሞ ይጠብቃል
ከዜሮ ማንነት ዕጥፍ ይሠንቃል።
( የት ነሽ ብዙነቴ . . . ?)
ዕወቂኝ ልወቅሽ ፤ በድንቅ ሕገ ሐሳብ
0ጥልቂኝ፣ ታጠቂኝ ፤ በመዋሐድ ሒሳብ።
ዜሮ ነሽ አንድ ነኝ ፤
በዕብሮነት መንገድ
ነይ አብረን እንገኝ።
የሕይወት ውብ እውነት ፣ የሙሉነት ምስጢር
አንድ ከዜሮ ጋር ፣ ሲቆም ሲሰባጠር።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
ሒሳብ ፣ ስሌት ፣ ቀመር
ስሜት ፣ እውነት ፣ ፍቅር
አንድ እኔ ማንነት . . .
ዜሮ አንቺነትሽን ቆሞ ይጠብቃል
ከዜሮ ማንነት ዕጥፍ ይሠንቃል።
( የት ነሽ ብዙነቴ . . . ?)
ዕወቂኝ ልወቅሽ ፤ በድንቅ ሕገ ሐሳብ
0ጥልቂኝ፣ ታጠቂኝ ፤ በመዋሐድ ሒሳብ።
ዜሮ ነሽ አንድ ነኝ ፤
በዕብሮነት መንገድ
ነይ አብረን እንገኝ።
የሕይወት ውብ እውነት ፣ የሙሉነት ምስጢር
አንድ ከዜሮ ጋር ፣ ሲቆም ሲሰባጠር።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
👍3❤1