አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
502 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እኔ_አንዳንዴ_ስሰጥ

ኑሮ ለገረፈው ፤ በችግር አለንጋ
በረሃብ ጠውልጎ፤ እጁን ለዘረጋ
በመከራ ስለት፤ ጎኑን ለተወጋ
ለዚህ ብሶተኛ፤
ለዚህ ጉዳተኛ፤
ጥቂት ልመፀውት፤ ከኪሴ እገባለሁ
ከብሮች መካከል፤ብሮች አወጣለሁ
አምስት ብርአውጥቼ፤ልሰጠው እልና
እኒህ አምስት ብሮች፤ ይበዙብኝና
አራቱን ለመስጠት፤ጥቂት ሳሰላስል
'ለእኔ አይበዛብኝም ለእሱ ይበዛል' ስል
ሶሥት ብር ለመስጠት፤ውሳኔ ደርሼ
'ጎዶሎ አይሰጥም፤ እልና መልሼ
በሁለት ብሮች ላይ፤ፍርዴን እሰጣለሁ
ፍርዴን ግን መልሼ፤ እከልሰዋለሁ
ሁለት ብር ከምሰጥ፤ ለመንገድ ልመና፤
አንዳንድ እንካፈል፤ ብዬ እወስንና
'አንድ ብር ብሰጠው፤ለዚህ ብሶኛ
ሆላ ቢጠጣበቸፈት፤ እያልኩ አስብና
ያችን አንድ ብርም፤ ኪሴ እከታታለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ!" ብዬው እሄዳለው