#እኔ_ጠላሻለሁ፣
እንደ ጫማ ሽታ
ልክ እንደ በሽታ
ጌታ በባርያው ላይ እንደ ሚበረታ
#እኔ_ጠላሻለሁ፣
እንደ ረጅም መንገድ
ለሀብታም እንደ መስገድ
ከጠጡ በኋላ እንደ መንገዳገድ
#እኔ_ጠላሻለሁ፣
ገንዘብ እንደ ማጣት
ዳገት እንደ መውጣት
ከያዘ እንደ ማይለቅ እንደ ጨካኝ ቅጣት
#እኔ_ጠላሻለሁ፣
ልክ እንደ መልከስከስ
እምነት እንደ ማርከስ
ማስቲካ እያኘኩ ምላስ እንደ መንከስ
እኔ ጠላሻለሁ . . . (ወዘተ )
አሁን ግን ፈራሁኝ ጀመርኩኝ መብሰልሰል ጠላሁሽ ያበዛሁ
#ወድጄሽ ነው መሰል፡፡
🔘እዮብ
🔘