አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮሜዎና_ዡልዬት

#ክፍል_አምስት

ከተሸንፍክማ ' በጕንጮቿ ፡ ቅላት '
በወገቧ ቅጥነት፡ በደረቷ፡ ሙላት'
አበድኩ ፡ ካልክማ፡ ለጥርሶቿ 'ንጣት '
ለባቷ፡ አቀራረጽ ለጠጕርዋ ፡ቀለም ፡
ፍቅርህ ፡ ባይንህ ፡ ላይ ፡ነው፤ በልብህ ፡ አይደለም ይቅር በለኝ፡ልጄ፡ ባሁኑ ፡ ወቀሣ
ለዚች ፡ ከንፈህላት፡ ያችን ' ስትረሳ ፡
አመዛዘንኩና' ሠጋሁ፡ ኣስተውዬ '
ይችንም ፡ እንደዚያች' ትረሳለህ ፡ ብዬ ።

#ሮሜዎ
አባቴ ፡ በፍጹም ፡ ይህን ፡ አይጠርጥሩ፤
የዚችና ፡ የዚያች ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ነገሩ
በምን ፡ ቃል ፡ ልናገር ፡ ይህን ፡ ለማሳመን
በግሪክ ፡ በሮማ ፡ በጥንታዊው ፡ ዘመን ፡
ያነቡ፡ እንደ'ነበር' የእንስሳውን ፡ ሞራ ፡
ይችሉ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ አባቴ ፡ አባ፡ ሎራ '
እርስዎም ፡ እንደዚሁ፡ የልቤን ፡ ብራና፡
በጥበብ ፡ አውጥተው ፡ገልጠው፡ያንቡና '
የወረት ፡ ምልክት ፡ ቢያገኙ፡ በውስጡ '
ያን ፡ ጊዜ 'ይገባል ፡ ቢንቁኝ ፡ ቢቈጡ ።

#አባ_ሎራ
መልካም ነው አመንኩህ ፡ግን ከዚህ ፡ በኋላ
አንድ ፡ ነገር ፡ አለ ፡ የሚያስቸግር ፡ ሌላ ፤
ካፑሌና ፡ ሞንታግ ፡ የናንተ ፡ አባቶች ፡ .
ወገኖቻቸውን ፡ ጨምረው ፡ ጠላቶች ፡
ባላንጦች ፡ ቂመኞች ፡ ደመኞች ፡ ሲሆኑ ፤
በየመንገዱ ፡ ላይ ፡ እንዳውሬ ፡ እያደኑ ፡
አንዱ ፡ አንዱን ፡ ሲገድለው ፡ ባይኑ ፡ ሲያየው፡ብቻ
እንዴት ፡ ሊፈጸም ፡ ነው ፡ የናንተ ፡ ጋብቻ ? .
ይኖሩ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ዘወትር ፡ በዘመቻ ፡
ዘለዓለም ፡ ለውጊያ ፡ ለጠብ ፡ ተሰልፈው ፡
ለቄስ ፡ ላስታራቂ ፡ ለዳኛ ፡ አሸንፈው ።

#ሮሜዎ
ይኸው፡አባቴ ሆይ ይህ ነው፡ ዋናው ነገር
በዚህ ፡ ላይ ፡ ይገባል ፡ በብዙ ፡ መማከር ፡
እውነት፡ ነው ፡ ቢኖሩ፡ ዘለዓለም ፡እነሱ፡
በጠብ ፡ ባምባጓሮ ፡ ደም ፡ እያፈሰሱ ፡
ለፍርድ ፡ ቢያስቸግሩ የቄስ ፡ ቃል ፡ ባይሰሙ ፡
እኔና ፡ ዡልዬት ፡ ግን ፡ንጹሕ ፡ ነን ፡ ከቂሙ፡
አለ ፡ ወይ ፡ አባቴ ፡ በሃይማኖት ፡ መንገድ
የሚከለክል ፡ ሕግ ፡ እኛ ፡ እንዳንዋደድ ፡
እንግዲህ ፡ አባቴ ፡ ይህንን ፡ ካወቁ ፡
ዘዴውን ፡ ለማግኘት ፡ እርስዎም ፡ ይጨነቁ ፡ቤተ ሰቦቻችን ወሬውን ፡ ሳይሰሙ
ተክሊሉን ፡ በምስጢር ፡ እርስዎ፡ ይፈጽሙ ።

#አባ_ሎራ
ይህንን ፡ ታልህማ ፡ ዘዴ ፡ ጠፍቶ ፡ ለርቁ ፡
ካህንም ፡ አልቀረም ፡ አብሮ ፡ መጨነቁ ፡
ለሁለቱ ፡ ወገን ፡ ሰላምን ፡ መልሶ ፡
ያባቶቻችሁን ፡ ክፉ ፡ ቂም ፡ ደምስሶ ፡
ስለታቸው ፡ ዘወትር ፡ የሰው ፡ ደም ፡ ከማፍሰስ ፡
እንዲቆም ፡ ለማድረግ ፡ ትንሽ ፡ እንዲታገሥ ፡
ለሻምላ ፥ ለጩቤ ፥ ለሰይፍ ፡ ለጐራዴ ፡
ከዚህ ፡ የተሻለ ፡ መች ፡ ይገኛል ፡ ዘዴ ።
የናንተ ፡ ጋብቻ ፡ ይህን ፡ ቂም ፡ አብርዶ ፤
ዕርቅ ፡ ይመሠረታል ፡ ሰላምን ፡ አውርዶ ።

#ሮሜዎ
እንግዴህ፡ አባቴ ፡ እንፍጠን ፡ በቶሎ ፡
ተክሊሉ ፡ ይፈጸም ፡ በዛሬ ፡ቀን ፡ ውሎ ፡
ጊዜና ሰዓቱን ፡ ካልተሻማን ፡ በጣም :
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ዕንቅፋት ፡ አያጣም

#አባ_ሎራ
እንግዲያው ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ኑና ፡ ባሥር ፡ ሰዓት፡
ትፈጽማላችሁ ጋብቻችሁን በስራት

#የዡዬየት_ሞግዚትና #ሮሚዎ

#ሞግዚት
መልሱን ፡ ተቀብለሽ ፡ እንድትመጪ ' ብላ
ልካኝ' እመቤቴ ፡ በቶሎ ፡ አስቸኵላ '
ይኸው ፡ መጥቻለሁ፡ መልሱን ፡ ለመቀበል ፤
ቸኩያለሁና ፡ ንገረኝ፡ ቶሎ ፡ በል ።

#ሮሜዎ
ምላሴ 'ያሞግስ ፡ አፌም ፡ ያመስግናት ፤
በውነት' ያንቺ ፡ እመቤት ፡ የተባረከች ፡ ናት
ዐመሏ ' ጠባይዋ ፡ በለጠ ' ከመልኳ፤
ቃሏን ፡ ፈጸመችው ፡ አንቺን ፡ በመላኳ
ዥሮቼ ፡ ተከፍተው 'እሰማለሁና፡
እንግዴህ ፡ ንገሪኝ የዡልዬትን ፡ ዜና ።

#ሞግዚት
ለተነጋገርነው ፡ ትናንትና ፡ ማታ ፡
እንድትልክብኝ' ያሳብህን ፡ ሁኔታ ፡
በመጠበቅ ፡ ላይ ፡ ነኝ ፡ አስታውቀኝ ፡ በቶሎ ፤
በዪና፡ ንገሪው ፤እንደዚህ ፡ ነው፡ ብሎ ፡
አሳቡን ፡ ሲነግርሽ ፡ ተቀብለሽ ፡ አምጪ፡
ብላኝ ' መጥቻለሁ ።

#ሮሜዎ
መልሴን ፡ ስትሰጪ '
እንግዲያው ፡ ንገሪያት ፡ ሮሜዎ ፡ ከልቡ ፡
ይወድሻል ፡ ብለሽ ፡ መንፈሱም ፡ አሳቡ ፡
ወዳንቺ ፡ ነው ፡ በያት ፡ ንገሪያት ፡ አደራ ፤
እስቲ ፡ ልለምንሽ ፡ እባክሽ ፡ ሳልፈራ ፡
እኔ ፡ እንደምወዳት፡ እንደዚሁም ፡ እሷ'
ትወደኝ ፡ እንደሆን ፡ ዡልዬት፡ በመንፈሷ፡
ታውቂዋለሽና ፡ እባክሽ ፡ ንገሪኝ ፡
አሳቧን ፡ ጠባይዋን 'እንዳውቀው ፡
ምከሪኝ ።

#ሞግዚት
ምንም ፡ አልደብቅህ ፡ ልንገርህ ፡ ካንዠቴ
አንተን ፡ ስታፈቅር ፡ ዝልዬት ፡ እመቤቴ'
እመነኝ ፡ ልንገርህ ፡ በውነት ፡ ከልቧ' ነው
የመስፍኑ ዘመድ፡ፓሪስ የሚባለው፡
ሊያገባት፡ ፈልጎ ፡ መሞቱ ፡ ነው ፡ ደክሞ ፡
ጨርሳ ፡ አትወደውም፡ እሷ ፡ ግን ፡ ፈጽሞ
አታንሡ፡ትላለች ፡ የሱን ፡ ስም ፡ ከፊቴ ፤
ትቈጣለችና ፡ ስቈይ ፡ እመቤቴ ፡
ልመለስ ፡ እባክህ ፡ መልሱን ፡ ስጠኝና ፤

#ሮሜዎ
አቀርብልሻለሁ'በሰፊው ፡ ምስጋና ።
እንደዚህ ' በዪና ፡ መልሱንም ፡ ንገሪያት ፤
ከቀትር ፡ በኋላ ፡ ዛሬ ፡ ባሥር ፡ ሰዓት ፡
አባ 'ሎራ፡ ድረስ ፡ አስፈቅዳ ፡ ትምጣ፤
ተናዘን ፡ ተባርከን ፡ የተክሊሉን ፡ጣጣ፡
ደብቀው ፡ በሙሉ ፡ ሊፈጽሙ፡ ቄሱ ፡
ተስማምተናል ፡ በያት ፡ ዛሬ ፡ ሊጨርሱ ።

#አባ_ሎራ #ዡልዬት #ሮሜዎ

#አባ_ሎራ
የናንተ ፡ ጋብቻ ፡ ፍጻሜው ፡ እንዲያምር ፡
ፈጣሪ ፡ ጸጋውን ፡ ምሕረቱን ፡ ይጨምር ።

#ሮሜዎ
አሳቤ ' ሞላልኝ ፡ እንግዲህ ፡ አባቴ ፡
ይህ ፡ ብቻ፡ ነበረ ፡ የቀረኝ ፡ ምኞቴ ።
ከሷ'ጋራ ፡ መጥቼ ፡ ቀርበን ፡ ከመንበሩ፡
ሥራቱን ፡ ከሞላን ፡ አለቀ ፡ ነገሩ ፡
እንግዲህ ፡ ግድ ፡ የለም የመጣ ፡ ቢመጣ

#አባ_ሎራ
ልጄ ፡ ሆይ ፡ ብዙ ነው የዚህ ዓለም ፡ ጣጣ
ለደስታ ፡ ሐዘን ፡ ለማር ፡ አለው ፡ እሬት ፤
ጠፊ ፡ ካጥፊው ፡ ጋራ ፡ ይኖራል ፡ በመሬት
ስለዚህ ፡እግዚአብሔር መጥፎውን ፡ አርቆ
ልጄ ፡ ያኑራችሁ ፡ በሰላም ፡ ጠብቆ ።

(ዡልዩት ፡ መጣች) ።

ፍቅሯንና ፡ ጌጧን ፡ በልቧ ፡ ሸፍና ፡
አልማዟ ፡ ማስተዋል ፡ ወርቋ ፡ ትሕትና ፡
ምስጢሯን ፡ ባሳቧ ፡ በጥበብ ፡ ሰውራ ፡
ይኸው ፡ መጣችልን ፡ መልካሟ ፡ ሙሽራ

#ዡልዬት
ሰላም ፡ ለርስዎ ፡ ይሁን ፡ ኣባቴ ፡ አባ ሎራ

#አባ_ሎራ
ደኅና ፡ ነሽ ወይ? ልጄ። ወጣት ፡ ሴት ፡ ወይዘሮ ፤
መልካም ፡ ጊዜ ፡ መጣሽ ፡ ልክ ፡ በቀጠሮ

#ዡልዬት
አመሰግናለሁ ፡ ለኔም ፡ ለሮሜዎ ፡
አባቴ ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ በመቸገርዎ ።

#ሮሜዎ
እንዳንቺ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ በፍቅር ፡ ተሳስረው
ለመጡ ፡ ወጣቶች ፡ ሥራቱን ፡ አክብረው
ፍቅራቸውን ፡ ባርኮ ፡ በእጁ ፡ ሊቀድሰው ፡
ምን ፡ ጊዜም ፡ ሥራው ፡ ነው ፡ ካህን ፡ የሆነ ፡ሰው።

#አባ_ሎራ
እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ ካህን ፡ ይጠብቃል ፤
እውነት ፡ ነው ፡ ሮሜዎ ፡ የተናገረው ፡ ቃል'
ከቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ እንግባና ፡ በሉ ፡
ሳይዘገይ ፡ በቶሎ ፡ ይፈጸም ፡ ተክሊሉ ።

(ቤተ ፡ ክርስቲያን'ገቡ)

(#በቬሮና #ከተማ' #መንገድ) •

#ሜርኩቲዎ #ቤንቮሊዎ ፡ አንድ ፡ የእልፍኝ #አሽከር

#ቤንቮሊዎ
ሜርኩቲዎ ፡ እንሂድ ፡ የካፑሌ ፡ ሰዎች ፡
ይጠፉ ፡ አይመስለኝም በነዚህ መንደሮች
ድንገት ፡ ብንገናኝ ፡ ኋላ ፡ ጠብ ፡ ይነሣል ፤
ደግሞ ፡ ጠብ ሲነሣ ፡ ጸጥታ ፡ ይፈርሳል ፡
ብንሸሽ ፡ ይሻላል ፡ ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ ጣጣ ።

#ሜርኩቲዎ
እነሱም ፡ አስበው ፡
👍1
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_ሰባት

#ቤንቮሊዎ
ጠቡን ፡ የጀመረው ፡ ክፉ ፡ ቃል ፡ ተናግሮ
ይኸው ፡ ቲባልት ፡ ነው ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፤
ከሱ ፡ በቀር ፡ ዛሬ ፡ ጠብ ፡ ያነሣ ፡ የለም ።
እኔና ፡ ሜርኩቲዎን ፡ ሰደበን ፡ ሳንሰድበው
ሮሜዎ ፡ ደረሰ ፡ ድንገት ፡ ሳናስበው ።
እሱም ፡ በደግነት ፡ ቃሉን ፡ አለስልሶ ፡
ልዑል ፡ የሰጡትን ያዋጅ ፡ ቃል ፡ ኣስታውሶ ፡
ቲባልትን ፡ ለመነው ፡ ጠብ ፡ እንዳያነሣ ፤
መቼም ፡ መጥቷልና ፡ እሱ ፡ ግን ፡ ላበሳ ፡
በእልህ ፡ እንቢ ፡ ብሎ ስድቡን ፡ ሲቀጥል
ከሜርኩቲዎ ፡ ጋራ ፡ ተማረሩ ፡ በጥል ፤
ሻምላ ፡ ቢማዘዙ ፡ ቶሎ ፡ መገላገል ፡
አሰብንና ፡ ገባን ፡ ከነሱ ፡ መካከል ።
እኔና ፡ ሮሜዎ ፡ ስንገላግላቸው ፡
ሜርኩቲዎን ለመውጋት ቲባልት ተመቸው
እኛም ፡ አላየንም ሜርኩቲዎን ፡ ሲወጋው
ኋላ ፡ ግን ፡ አየነው ፡ ቁስሉን ፡ ከነ አደጋው
ከሽሸ ፡ በኋላ ፡ ቲባልት ፡ እንደ ፡ ገና ፡
ቢመጣ ፡ ሮሜዎ ፡ ነዶት ፡ ነበርና ፤
ደሙን ፡ ለመበቀል ፡ በንዴት ፡ ተነሥቶ ፡
ከቲባልት ፡ ጋራ ፡ በቅጽበት ፡ ተዋግቶ ፡
ወዲያው በደቂቃ ውጊያው በጣም ሲግል
እኔም ፡ ሳያደርሰኝ ፡ ችዬ ፡ ሳልገላግል ፡
ቲባልት ፡ ቆሰለና ፡ በፍጥነት ፡ ወደቀ ፥
ሮሜዎም ፡ ሸሸና ፡ በዚሁ ፡ አለቀ ፤
ከተናገርኩትም ፡ ከውነቱ ፡ የራቀ ፡
ውሸት ፡ ቢገኝብኝ ፡ ተደርጎ ፡ ምርመራ ፡
ይድረስብኝ ፡ በኔ ፡ የቅጣት ፡ መከራ ።

የካፑሌ ፡ ሚስት (መጣች)

መሠረት ፡ የለውም ፡ ምስክርነቱ ፤
ከእውነተኛው ፡ ነገር ፡ ይበልጣል ፡ ሐሰቱ '
ይህንን ፡ ቢናገር ፡ እያስመሰለ ፡ እሱ ፡
የሞንታግ ወገን ነው ልዑል ሆይ አይርሱ!
በፍርድ ሮሜዎ ፡ ይሙት ፡ ነው ፡ የምለው

#መስፍን
ሮሜዎ ፡ ቲባልትን ፡ ወግቶ ፡ ከገደለው ፡
እናንተ ፡ ስለሱ ፡ ፍርድ ፡ ስጥ ፡ ስትሉ ፡
የሜርኩቲዎን ፡ ደም ፡ ማን ይክፈለኝ ፡ለኔ
ዘመዴ ፡ ነው ፡ እኮ ፥ ሥጋዬ ፡ወገኔ ።

#ሞንታግ
ልዑል ፡ሆይ ሜርኩቲዎን ቲባልት ገደለው
ዐዋጁ 'ቲባልትን ፡ ይሙት' ነው ' የሚለው
ስለዚህ ፡ ቢያስቡት ፡ አሁን ፡ የኔ ፡ ልጅ ፤
ቲባልትን ሲገድለው ፡ዐዋጅ ፈጸመ ፡ እንጅ
ሌላ ፡ ምን ፡ ጨመረ ፡ እስቲ ምን አጠፋ ?

#መስፍን
ሞንታግ ምሕረት አለ ብለህ ፡ እንዳትለፋ፡
ሮሜዎ ፡ በፍጥነት ፡ ዛሬ ፡ ካገር ፡ ይውጣ
ጠባችሁ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ይኸው ዞሮ ፡ መጣ
በናንተ ፡ ምክንያት ፡ የሞተው ፡ ደጉ ፡ ሰው
ሥጋዬ ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ ደሙ ፡ የፈሰሰው ፡
በሰጠሁት ፡ ዐዋጅ ፡ ራሴ ፡ ወስኜ ፡
እገኛለሁ ፡ እኔ ፡ ጨካኝ ፡ ቀጭ ፡ ሆኜ፡
የፍርዴንም ፡ ሥራ ፡ በቅጣት ፡ ስሠራ ፡
ይቅርታ ፡ የለኝም ፡ ለማንም ፡ አልራራ ።
አማላጅ ፡ ልመና ፡ ጸጸትና ፡ ለቅሶ ፡
ፍርዴን ፡ ሊመልሱት ፡ አይችሉም ፡ ጨርሶ
ስማ ፡ ልጅህ ፡ ዛሬ ፡ የኔን ፡ ትእዛዝ ፡ ሽሮ ፡
የተገኘ ፡ እንደሆን ፡ በከተማው ፡ አድሮ ፡
ዛሬ ፡ ከቬሮና ፡ በፍጥነት ፡ ካልወጣ '
ዕወቀው ' ያለፍርድ' በሞት እንዲቀጣ ።

#ዡልዬትና#ሞግዚቷ ፡ (በቤታቸው) "

#ዡልዬት
እኔና ፡ ሮሜዎ ፡ ዕድላችን ፡ ክፉ ፤
ይደንቃል ፡ ሰርጋችን ፡ እንደዚህ ፡ ማለፉ፡
ሰርጉ አልነበረም ወይ የሰው ፡ልጅ ደስታ
እኛ ፡ ግን ፡ምስኪኖች በዚህ ፡ ሁሉ ፈንታ፡
መሥጋትና ፡ መፍራት ፡ ያባት የናት ፡ ቁጣ
ሆነና ፡ ተገኘ ፡ የተሰጠን ፡ ዕጣ ።
አልገሠግሥ ፡ አለ ፡ ጊዜና ፡ ሰዓቱ ፤
ምነው ፡ የዛሬ ፡ ቀን ፡ ደከመ ፡ ፍጥነቱ ?
ሰዓቱም ፡ ለገመ ፡ ዳተኛ ፡ መሆኑ ፡
ሮሜዎን ፡ ስጠብቅ ፡ አልመሽ ፡አለኝ ፡ ቀኑ
ደግሞ ፡ ሞግዚቴ ፡ ነች ፡ ዋና ፡ ጥፋተኛ ፤
ምነው ፡ ሆነችብኝ ፡ እንደዚህ ፡ ዳተኛ ?
በፊት ፡ ደኅንነቱን ፡ ነግራኝ ፡ ተመልሳ ፡
መሄድ ፡ ትችል ፡ ነበር ዳግም ፡ በግሥገሣ
ሌሊቱ ፡ ሲጨልም ፡ ጨረቃ ፡ ሳትወጣ ፡
ንገሪው ፡ አልኩና ፡ ሮሜዎ ፡ እንዲመጣ '
ብልካት ፡ እንሆ ፡ ቀረች ፡ እዚያው ፡ ቀልጣ
እባክህ ፡ ጨለማ ፡ ፍጠን ፡ በቶሎ ፡ ና ፤
ካልመሸ ፡ ሮሜዎ ፡ ደፍሮ ፡ አይመጣምና
ሌሊቱ' ይተካ ፡ የቀን ፡ ብርሃን ፡ ሄዶ፤
ሮሜዎን ወደ እኔ እንዲያስገባው ፡ ጋርዶ።
ቀኑ ፡ እየደከመ ፡ ብርሃን ፡ እየሸሸ ፡
ፀሓይ ፡ እየጠፋች ፡ ሰዓቱ ፡ እየመሸ ፡
አንተ ፡ ከባድ ፡ ጽልመት፡የሌሊት ፡ ጨለማ
ፈጥነህ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ አትሁን ፡ ደካማ ።
ገሥግሠህ ፡ ሸፍናት ፡ ዓለምን ፡ በጥላ ፤
ጥላህ ፡ ለሮሜዎ ፡ ይሁነው ፡ ከለላ '
ፀሓይም ፡ ጥለቂ ፤ ብርሃንን ፡ አትስጪ ፤
ኮከብ ፡ ተሰወሪ ፡ ጨረቃም ፡ አትውጪ'
ካለም ፡ ገለል ፡ በሉ ፡ ብርሃንና ፡ ፋና ፡
ብርሃን ፡ እሱ፡ ራሱ ፡ ሮሜዎ ፡ ነውና ፡
ያቻት ወዲህ መጣች ብቅ አለች ሞግዚቴ
ደርሳ እስክትነግረኝ ፡ ወሬውን ፡ ከፊቴ ፡
ቸኩያለሁ ፡ በጣም ፡ እንዴት ፡ ያለ ፡ ወሬ ፡
ይዘሽልኝ ፡ መጣሽ ፡ ሞግዚቴ ፡ ሆይ ፡ ዛሬ ?
ምነው ፡ ምን ፡ ሆነሻል ፡ ፊትሽ ፡ ተለወጠ ?

#ሞግዚት
አዬ 'ከንቱ ፡ ነገር ፡ በቃ ፡ ተቈረጠ'
ባጭር ፡ ተቀጠፈ ' ያን ፡ መሳይ ፡ መኰንን
አዬ ፡ጉድ አዬ ፡ ጉድ! ጠላሁ ሰው መሆንን

#ዡልዬት
አሁን ፡ ባሁን 'ሄደሽ ፡ ከኔ ዘንድ ፡ ከወጣሽ'
ምን ፡ዐይነት ፡ኀዘን ነው ይዘሽው የመጣሽ

#ሞግዚት
አወይ 'ሮሜዎ 'ቲባልት ፡ መልካሙ ፡ ሰው፡
እንደ ፡ፋሲካ ፡ በግ ፡ ደሙ ፡ የፈሰሰው ።

#ዡልዬት
ሐዘኑን ' ሰምቼ ፡ ልቤ ፡ ሳይመታ፡
መናገር' አቃተሽ ፡ አፍሽ ፡ አመነታ '
ሮሜዎ ፡ ሞተ፡ ወይ ? ሞቶም ፡እንደ ፡ ሆነ
ንገሪኝ ፡ ምላስሽ ፡ እየሸፋፈነ ፡
ሳይደብቅ ፡ ገልጦልኝ ፡ መርዶውን ፡ ልረዳ
ልቤም ፡ ተሠንጥቆ ፡ በሐዘን ፡ ይፈንዳ ።

#ሞግዚት
ቍስሉንም ፡ አየሁት ፡ በጣም ፡ ያሳዝናል ፤
ሐኪም 'አይጠሩለት ፡ ሞቶ፡ ምን ፡ ይሆናል
ምንም' ትንፋሽ የለው አልፋለች ፡ ሕይወቱ፡
ደሙ ፡ ይመነጫል ፡ ቆስሎ ' ከደረቱ ፤
ከሞተ 'ቁይቷል ደርቋል ፡ ሰውነቱ "
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ሥራ መቼም ፡ አልተሠራም
ዥልዬት ፡ የዛሬ ፡ ጉድ ፡ ይቅር ፡ አይወራም
ቲባልት ! ሮሜዎ ! አየሁ ፡ ደሙ ፡ ፈሶ :
ልብሱ ፡ ተበክሎ ፡ መሬቱም ፡ ርሶ ።

#ዡልዬት
ቲባልት ! ሮሜዎ ! ሁለቱንም ፡ ጠርተሽ ፡
ከምታስጨንቂኝ ፡ ንገሪኝ ፡ ለይተሽ '
ሮሜዎ ፡ ባሌ ፡ ነው ፡ ቲባልት ፡ ዘመዴ ፤
የቱ ፡ ነው ፡ የሞተው ፡ ተጨነቀ ፡ ሆዴ
ባለም ፡ ላይ ፡ ከሌሉ ፡ እነዚህ ፡ ሁለቱ ፡
መታከት ፡ ነውና ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ ከንቱ ፡
የምጽኣት ፡ ቀን ፡ ይሁን ፡ መለከት ፡ ይነፋ ፤
አሁን ፡ ተደምስሶ ፍጥረተ ዓለም ፡ ይጥፋ፡
ባሕር ፡ ጫካ ፥ ገደል ፥ ጅረትም ፡ ተራራ ፡
ፍጡር ፡ እዬዬ ፥ በል ፡ አልቅስ ፡ ከኔ ፡ ጋራ

#ሞግዚት
ሟቹ ፡ ቲባልት ፡ ነው ፡ ካለም ፡ ላይ ፡ የሄደ
ገዳዩ ፡ ሮሜዎ ፡ ካገር ፡ተሰደደ ።

#ዡልዬት
ሮሜዎ ፡ ቲባልትን ፡ ብትዪኝ ፡ ገደለው ፡
አይችልም ፡ መንፈሴ ፡ አምኖ ፡ ሊቀበለው

💫ይቀጥላል💫
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_ስምንት


#ሞግዚት
የተሠራውን ፡ ጉድ ፡ እንግዲህ ፡ ዕወቂው
እርገሚው ፡ ሮሜዎን ፡ ከልብሽም ፡ ናቂው
በቀልሽን ፡ ቂምሽን ፡ አድርጊው ፡ የጸና ፤
በውነቱ ፡ ሮሜዎ ፡ ሰው ፡ አይደለምና ።
አብነት ፡ ይሁንሽ ፡ ይህ ፡ መጥፎ ፡ ደመኛ
ሰውን ፡ አትመኝ ፡ እንግዲህ ፡ ዳግመኛ ፡
ፍቅሩም ፡ደግነቱም ፍሬ ቢስ ፡ ነው ፡ ከንቱ
ፈጽሞ ፡ ሰው ፡ የለም መጥፎ ፡ነው ፡ ሰዓቱ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ነገር ፡ ሮሜዎ ፡ ሲሠራ ፡
ማነው ፡ የሚታመን ? ማነው ፡ ባለአደራ ?

#ዡልዬት
ምንም ፡ አልተገኘ ፡ የሚበጀኝ ፡ ለኔ ፤
ሁለት ፡ ስለት ፡ ያለው ፡ ሰይፍ ፡ ነው ፡ ኀዘኔ
ቲባልት ፡ ባይሞት ኖሮ ሮሜዎ ፡ ይሞታል፤
ቲባልት ፡ ባይሸነፍ ፡ ሮሜዎ ፡ ይረታል!
ሮሜዎን ፡ ከልብሽ ፡ ትይኛለሽ ፡ ጥዪው ፤
ምነው ልቤን ገብተሽ መርምረሽ ብታዪው
ለኔም ፡ገዳይ ፡ ቢሆን ፡ ለናቴም ፡ ላባቴ ፡
ሮሜዎን ፡ ለመጥላት አይችልም ፡አንጀቴ
ቲባልትም ፡መጥፎ ነህ ፡ሮሜዎም አትረባ
መሪር ፡ ነው ፡ ከናንተ ፡ የሚተርፈኝ ፡ እንባ
ባሌ ፡ ካገር' ወጣ ፤ቲባልት ፡ ሞተ ፡ በፊት፤
ሐዘኔ ፡ ዐጓጕል ፡ የሌለው ፡ መድኀኒት ፡
እንደ ምን ፡ አድርጌ ደግሞስ ፡ እስከ መቼ
እኖራለሁ ፡ እኔ ፡ እናንተን ፡ አጥቼ ፡
ከቲባልት ፡ መሞት ፡ ሮሜዎ ፡ ስደቱ ፡
ከሮሜዎ ፡ ስደት ፡ ቲባልት ፡ መሞቱ ፡
ቢሆን ፡ ምን ፡ ቸግረው ፡ ሐዘኔ ፡ በተራ ፤
ለማንኛው ፡ ላልቅስ ፡ ወይ ፡ የኔ ፡ መከራ !
ዛሬ ፡ በሠርጌ ፡ ቀን ፡ ደስ ፡ብሎኝ ፡ መዋሌ
ቀረና ፡ ሰው ፡ ገድሎ ፡ እንዲሰደድ ፡ ባሌ '
ቲባልትም ፡ እንዲሞት ፡ አድርጎ ፡ ዕድሌ ፡
ሐዘን ፡ ከሆነ ፡ ለኔ ፡ የደገሰው ፡
ልቤ ፡ ሳያደላ ፡ እንባዬን ፡ ላፍስሰው ።

#ሞግዚት
በእውነት፡ሴት ልጅ ባሏን፡ከወደደች አይቀር
እንዳንች ፡ አድርጎ ፡ ነው ከልቡና ማፍቀር
ከልብ ፡ አዘንኩልሽ ፡ በጣሙን ፡ አድርጌ ፤
አለበት ፡ ገብቼ ፡ ሮሜዎን ፡ ፈልጌ ፡ .
እኔ ፡ አመጣዋለሁ ፡ እንባሽን ፡ አድርቂው
እመኝታ ፡ ቤትሽ ፡ ግቢና ፡ ጠብቂው ።
በስደተኛነት ፡ ሳይሄድ ፡ ነገ ፡ ርቆ ፡
ተሰነባበቱ ፡ ይምጣ ፡ ተደብቆ ።

#ዡልዬት
መልካም ፡ ነው ፡ ሞግዚቴ ፡ሙሽራ ፡ ሲገባ
አጊጦ ፡ ታጅቦ ፡ በዘፈን ፡ ባበባ ፡
በወግ ፡ በማዕርግ ፡ ባለም ፡ በደስታ ፡
በክብር ፡ ነበረ ፡ በብዙ ፡ እልልታ ፤
ሌሊት ፡ ጨለማውን ፡ ከለላው ፡ አድርጎ ፡
የኔ ፡ ሙሽራ ፡ ግን ፡ ይግባ ፡ ተሸሽጎ ።
እንቢ ፡ ብሎ ፡ እንዳይቀር ፡ጠርተሽ ፡ ስታመጪው
እንቺ ፡ ለምልክት ፡ቀለበቴን ፡ ስጪው ፡
(ቀለበቷን ፡ ሰጠቻት)

#አባ_ሎራ (ባባ ሎራ ፡ ቤት)
ሮሜዎ ፡ ብቅ ፡ በል ፡ውጣ ፡ ከጨለማ ፤
የፍርዱን ፡ ቃል ፡ ይዤ ፡ መጣሁ ልጄ ስማ

#ሮሜዎ
ሳልሰማው ፡ ቢዘገይ ፡ ይሻለኝ ፡ ነበረ ፤
ፍርዱ ፡ ምን ፡ ዐይነት ነው ? ልቤ ፡ ተሸበረ

#አባ_ሎራ
መስፍኑ ፡ ፈቀደ ፡ በቀላል ፡ ሊቀጣ ፤
የሞት ፡ ፍርድ ፡ ቀርቶ ፡ካገር ፡ እንድትወጣ

#ሮሜዎ
ጨካኝ ፡ ቅጣት ፡ እንጂ ፡ ከሞትም ፡ የከፋ
ይህ ፍርድ መሪር ነው ያስቈርጣል ፡ ተስፋ
ዥልዬት ፡ ካለችበት ፡ ከተማ ፡ ወጥቼ ፡
ስደተኛ ፡ ሆኜ ፡ አገሬንም ፡ ትቼ ፡
የምኖረው ፡ ኑሮ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ይገፋል ፣
ቀኑና ፡ ሰዓቱ ፡ ደቂቃው ፡ መች ፡ ያልፋል ፡
እንዴት ፡ እችላለሁ ፡ ዡልዬትን ፡ ለመርሳት
ሲኦል ፡ ነው ፡ ኵነኔ ፡ ሞት ፡ገሃነመ ፡ እሳት

#አባ_ሎራ
ደስታህ ፡ ቀረና ፡ በማመስገን ፡ ፈንታ ፡
ለምን ፡ ትረሳለህ ፡ የእግዜርን ፡ ውለታ ፡
ዐዋጁ ፡ የሚያዘው ፡ የሞት፡ ቅጣት ፡ ነበር'
ለምን ፡ አታስብም ፡ ይህን ፡ ትልቅ ፡ ነገር ፡
ሄደህ ፡ ብትቀመጥ ፡ በማንቱ ፡ ከተማ ፡
አገሩ ፡ ጥሩ ፡ ነው ፡ በጣም ፡ የሚስማማ
ልጄ ሆይ ፡ ቅጣቱ ፡ በጣም ፡ የቀለለ ፡
ጥሩ ፡ ነው ፡ ሺ ፡ ጊዜ ፡ ከሞት ፡ የተሻለ ።

#ሮሜዎ
ያስቡት ፡ አባቴ ፡ ነገሩን ፡ ያስተውሉት ፤
ምኑን ፡ ነው እርስዎ ቀላል ነው ፡ የሚሉት

#አባ_ሎራ
ብስጭት ፡ አታብዛ ፡ በጣም ፡ አትናደድ ፤
ከመሞት ፡ ይሻላል ፡ ሺ ፡ ጊዜ ፡ መሰደድ
ልጄ ፡ ዓለም ፡ሰፊ ፡ ነች ወጥተህ ከቬሮና
የትም ፡ ሄደህ ፡ መኖር ፡ ትችላለህና ።

#ሮሜዎ
ወጥቼ ፡ ከሄድኩኝ ፡ እኔ ፡ ከቬሮና ፡
ውሸት ፡ ነው ፡ አባቴ ፡ ምን ፡ዓለም ፡ አለና፡
ሕይወት ፡ ነው ፡ አይበሉት የምኖረው ኑሮ
ዓለም ፡ እዚህ ፡ ቀረ ፡ ከሚስቴ ጋር አብሮ'
ሰው ነህ እንስሳ ዕንጨት አበባና ፡ቅጠል ፡
ፀሐይ ፡ ተከልሎ ፡ አየር ፡ ሳይቀበል ፡
የኖረ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ ይሞታል ፡ ይደርቃል፤
ለኔም ፡ እንደዚህ ነው ፡ ስደት የሚሉ፡ ቃል
አገሬ ፡ ንብረቴ ፡ አየሬ ፡ ፀሓዬ ፡
ዓለሜ ፡ ትንፋሼ ፡ ሕይወቴ ፡ ሰማዬ ፡
የነበረችውን ፡ ዝልዬትን ፡ አጥቼ ፡
እሷ ፡ ካለችበት ፡ ከተማ ፡ ወጥቼ ፡
መሄዴ ፡ ከሆነ ፡ እሷም ፡ ከኔ ፡ ርቃ ፡
ነጣጥለው ፡ ከለዩን ፡ የኔ ፡ ነገር ፡ በቃ ።
ሕይወቴም ፡ ኑሮዬም ፡ ሞተ ፡ ተበላሸ ፤
ደስታ ፡ ተለየኝ ፡ ከኔ ፡ ርቆ ፡ ሸሸ ፡
እንግዲህ ፡ መቆሜ ፡ ለምንም ፡ አይበጅ ፤
ይህን ፡ኑሮ ፡አይበሉት መናወዝ ነው እንጅ
ፍርድ ፡ ማሻሻያ ፡ የተባለው ፡ ዘዴ ፡
ከመርዝም ፡ ይብሳል ፡ ከጦር ፡ ከጐራዴ '
ስደት ፡ የሚሉ ፡ ቃል ፡ ጨለማ ነው ፡ ገደል
እኔን ፡ አስጨንቆ ፡ መጣ ፡ ለመግደል ።

#አባ_ሎራ
እረ ፡ ስማኝ ፡ ልጄ ፡ ምክሬንም ፡ ተቀበል ፡
ሞትና ፡ መሰደድ ፡ እኩል ፡ ነው ፡ አትበል

#ሮሜዎ
ተመልሰው ፡ ስደት ፡ ወደሚባለው ፡ ቃል ፡
ሊመጡ ፡ ነውና ፡ አባቴ ፡ ይበቃል ፡
ምን ፡ አደከመዎት ፡ በቃ በዚህ ፡ ዓለም ፡
እኔን ፡ የሚያጥናና ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ የለም
ከሞት ፡ የባሰ ፡ ነው ፡ የመከራ ፡ ጭቃ ፤
የሮሜዎ ፡ ነገር ፡ ተከተተ ፡ በቃ ።

#አባ_ሎራ
ዐውቃለሁ ፡ እንዲሆን ፡ ስደትህ ፡ መራራ ፤
ግን ፡ መድኀኒት ፡ አለው ለዚህ ፡ ለመከራ'
ዕረፍት ፡ እንድታገኝ ፡ ባሳብ ፡ በኅሊና ፡
የደረሰብህን ፡ ጭንቅህን ፡ እርሳና ፡
ልብህን ፡ መልሰው ፡ ወደ ፡ ፍልስፍና ።

#ሮሜዎ
ዡልዬትን ፡ ፈጥሮልኝ ካልሰጠኝ ፡ አምጥቶ
የመስፍኑን ፡ ብይን ፡ በጥበብ ፡ አጥፍቶ ፡
እኔን ፡ ካላዳነኝ ፡ የርስዎ ፡ ፍልስፍና ፡
ለምንም ፡ አይበጀኝ ፤ የለውም ፡ ርባና ።
(የዡልዬት'ሞግዚት'ከደጅ'ሆና'በር መታች)

#አባ_ሎራ
ተነሣ ፡ ሮሜዎ ፡ ግባ ፡ ወደ ፡ ጓዳ ፤
ስማ ፡ በር ፡ ይመታል ፡ መጣብን ፡ እንግዳ
ተደበቅ ፡ በቶሎ ፡ ጥግ ፡ ይዘህ ወደ ፡ ጐን
ይይዙሃልና ፡ ያገኙህ ፡ እንደሆን ።
(በሩ ይመታል)

#ሮሜዎ
በስደት ፡ ከሆነ ፡ እኔ ፡ የምቀጣ ፡
ምን ፡ ያስጨንቀኛል ፡ የፈቀደው ፡ ይምጣ

#አባ ፡ ሎራ ።
ለምን ፡ ትሆናለህ ፡ አንተ ፡እንደዚህ ፡ ደረቅ
እባክህ ፡ ግባና ፡ በቶሎ ፡ ተደበቅ ፡ (ሮሜዎ ሄደ)
እንዲህ ፡ ባሁን ፡ ሰዓት ፡ የመጣ ፡ በማታ ፡
ማነው ፡ በጨለማ ፡ በሬን ፡ የሚመታ ?

#ሞግዚት
መጥቻለሁና ፡ ልካኝ ፡ እመቤቴ ፤
የዡልዬት ፡ ሞግዚት ፡ ነኝ ያስገቡኝ ፡ አባቴ

#አባ ፡ ሎራ ።
እንኳን ፡ ደኅና መጣሽ ፡ ነይ ግቢ ወዳጄ፤
(ከፍተውላት ገባች)

#ሞግዚት
ሮሜዎን ፡ አጣሁት ፡ ብፈልገው ፡ ሄጄ ።
ይንገሩኝ ፡ አባቴ ፡ ከመሸ ፡ አሁን ፡ ማታ
አይተው ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ ያለበትን ፡ ቦታ ፡

#አባ ፡ ሎራ ።
በሐዘኑ ፡ ሰክሮ ፡ ያለቅሳል
👍1
፡ ተጨንቆ ፤
ያውልሽ ፡ ከጓዳ ፡ እመሬት ፡ ላይ ፡ ወድቆ

#ሞግዚት
ዠልዬት ፡ እመቤቴም ፡ በዚሁ ፡ ሁኔታ ፡
ስታለቅስ ፡ ዋለች ፡ ይኸው ፡ እስከ ፡ ማታ ፡
ጥሩልኝ ፡ አባቴ ፡ መልክቴን ፡ ልንገረው ።
ሮሜዎ ፡ (ከጓዳ ' ወጣ) ።
ዡልዬት ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ነች?መልካም ፡ የነበረው
ልቧ ፡ ተለውጦ ፡ ባደረግሁት ፡ ነገር ፡
አልጠላችኝም ፡ ወይ ? ምላስሽ ፡ ይናገር ፡
ልብሽ ፡ አይደብቀኝ ፡ ንገሪኝ ፡ አትፍሪ ፤
ያየሽውን ፡ ሁሉ ፡ አስተካክለሽ ፡ አውሪ ።
በሠራሁት ፡ ሥራ ፡ ፍቅራችን ፡ መጥፋቱ ፡
እንግዴህ ፡ ወደ ፡ ፊት ፡ ተቀብሮ ፡ መቅረቱ
እርግጥ፡አይደለም ፡ ወይ ? እንዴት፡ ነው ፡መንፈሷ ፤
እኔን ፡ ስታነሣ ፡ ምን ፡ ትላለች ፡ እሷ ።

#ሞግዚት
በሐዘን ፡ ተጨንቃ ፡ ከማልቀስ ፡ በስተቀር ፡
ክፉም ፡ ሆነ ፡ በጎ ፡ ምንም ፡ አትናገር ፡
ቲባልት ሮሜዎ ! አዬ ፡ ጕድ ፡ እያለች ፡
እንባዋን ፡ በማፍሰስ ፡ ቀኑን ፡ሙሉ ፡ ዋለች
ሐዘኗ ፡ ግን ፡ ሆኗል፡ አለመጠን ፡ ብርቱ ፥
ከመሄድህ ፡ በፊት ፡ ተሰነባበቱ ፤
እንሂድ ፡ በቶሎ ፡ መሸብን ፡ ሰዓቱ ።

#ሮሜዎ
ገላዬን ፡ ብወጋ ፡ እስቲ ፡ ከምን ፡ ቦታ ፡
መሞት እንደምችል በቅጽበት ፡ አንዳፍታ
ብልኅ ፡ ነዎትና ፡ ጥበብን ፡ መርማሪ ፤
ተምረው ፡ እንደሆን ፡ ያከላትን ፡ ባሕሪ ፡
በፍጥነት ፡ ይንገሩኝ ፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ፤
የት ፡ ነው የሰው ነፍሱ ያለችበት ፡ ስፍራ ?
አድርጊያለሁና ፡ ጸጸቷን ፡ መራራ '
ሐዘኔ ፡ጥልቅ ፡ ነው ፡ አልችልም ፡ ልጥናና
በገዛ ፡ እጄ ፡ ልሞት ፡ ቁርጫለሁና ። (ሰይፉን መዘዘ።)

💫ይቀጥላል💫
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_ዘጠኝ


#አባ_ሎራ
ለምን ፡ ታስባለህ ፡ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ነገር ፤
ብላሽ ፡ ሰው ፡ አትሁን ፡ ሲመክሩህ ፡ ተመከር ,እንደ ፡ ሴት ፡ አታልቅስ ፡ እንዳውሬ ፡ አትቈጣ
እንደ፡እብድ፡አትበሳጭ ፥ ከሰው፡ ግብር፡ አትውጣ
ትመስለኝ ፡ ነበረ ፡ በውነቱ ፡ ጠንካራ ፤
ሰው ፡ ለምን ፡ ይረባል ፡ ካልቻለ ፡ መከራ
መቀጣት ፡ ከወደድህ ፡ በገዛ ፡ እጅህ ፡ ሞተህ ፡
ስለምን ፡ ገደልከው ፡ ቲባልትን ፡ ተዋግተህ ?
በገዛ ፡ እጅህ ፡ ብትሞት ፡ ባለማመዛዘን ፡
መግደልህ ፡ እኮ ፡ ነው ሚስትህን ፡ በሐዘን '
ለዚህ ፡ ነው ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ ኅሊናና ፡ አእምሮ ፡
ከእግዜር ፡ የተሰጠ ፡ ለሰው ፡ ልጅ ፡ ተፈጥሮ'
ዡልዬት ፡ ጠልታኛለች ፡ ብለህ ፡ ስትሠጋ፡
ሰው ፡ ልካ ፡ ጠራችህ ምሕረትን ፡ አድርጋ
ቲባልት ፡ ሊገድልህ ፡ ቢመጣ ፡ ደንፍቶ ፡
በገዛ ፡ ጥጋቡ ፡ ወደቀ ፡ ተወግቶ "
ባንተም የሞት ቅጣት ሊወድቅ የነበረው
በስደት ፡ ለውጦ ፡ መስፍናችን ፡ ሻረው '
ብትመለከተው : በውነቱ ፡ የት ፡ አለ ፤
እንዳንተ ፡ የቀናው ፡ በጣም ፡ የታደለ ፡
ተጠንቀቅ ፡ በውነቱ ፡ ልጄ ፡ በጣም ፡ ሥጋ
ሳታውቀው ፡ ብትቀር ፡ የደስታን ፡ ዋጋ ፡
ኑሮህ ፡ይበላሻል ፡ አለመጠን ፡ ፍራ ፡
ምን ፡ጊዜም ፡ አይለቅህ ፡ ጭንቅና ፡ መከራ ።
ሚስትህን ምከራት ፡ እንዳትሞት ፡ አልቅሳ
መምሸቱ፡ነውና፡ በል ቶሎ ፡ ተነሣ፡
ነገ ፡ ግን ፡ ለመሄድ ፡ ልብህ ፡ይሰናዳ ፤
ውጣ ፡ ከቬሮና ፡ ሌሊት ፡ በማለዳ
ተዛውረህ ተቀመጥ ፡ ሄደህ ፡ ወደ ፡ ማንቱ
እኛ ፡ ጊዜ ፡ አግኝተን ፡ ሲመቸን ፡ ሰዓቱ ፡
ወገኖቻችሁን ፡ በምክር ፡ አስታርቀን ፡
ጋብቻችሁንም ፡ በገሃድ ፡ ኣስታውቀን ፡ .
ላንተም ፡ ከመስፍኑ ፡ ምሕረትን ፡ ጠይቀን
እንጣጣራለን ፡ ቶሎ ፡ እንድትመለስ
እግዜር ፡ይጠብቅህ በል እስከዚያ ፡ ድረስ
አሁን ፡ ወደ ፡ ዡልዬት ፡ በቶሎ ሂድ ፡ ተነሥ

የካፑሌ ሚስት #ካፑሌ #ፓሪስ

#ፓሪስ
ጉዳዩ ዘገየ ፡ በመዋል' በማደር ፤
ታዲያስ እንዴት ፡ ሆነ ፡የጋብቻው ፡ ነገር ?

#ካፑሌ
ነገሩን ፡ ለዡልዬት ፡ ሳልነግር ፡ መቅረቴ ፡
ወድጄን ፡ አይደለም ፡ እንዲህ ፡ መዘግየቴ
በቲባልት ፡ መሞት ፡ አዝናለች ፡ በብርቱ ፤
ታፈቅረው ፡ ነበረ ፡ ከልቧ ፡ በውነቱ ፡
ስለዚህ ፡ ሐዘኑ ፡ ጥቂት ፡ ሳይረሳ ፡
አልቻልኩም ፡ ጕዳዩን ፡ ለጊዜው ፡ ላነሣ ፡
አድርግልኝና ፡ ከልብህ ፡ ይቅርታ ፤
እኔ ፡ እጨርሳለሁ ፡ ነገሩን ፡ አንድ ፡ አፍታ

#ፓሪስ
እውነት ፡ ነው ሐዘኑ ፈጽሞ ፡ አልተመቸም
ተስማምተንበታል ይህን ጕዳይ ፡ መቼም
እሷም እንቢ እንዳትል ፡ እናንተ ፡ አስቡበት

#የካፑሌሚስት _ ።
ግድ የለም ሠርጋችሁ ይሆናል በፍጥነት

#ካፑሌ
ፓሪስ ሆይ አትሥጋ አይዞህ ይህን ጕዳይ
መሄድ ፡ ትችላለህ ፡ ጥለኸው ፡ በኔ ፡ ላይ
እንዴት ፡ ትወጣለች ፡ ከኔ ፡ ፈቃድ ፡ ልጄ ፤
ያቀረብኩላትን ፡ መርጬ ፡ ወድጄ
ያላንድ ፡ ቅሬታ ፡ አለባት ፡ መቀበል ፤
እንዲያውም ፡ እንፍጠን ፡ ዛሬ ነገ ፡ አንበል
በይ ፡ ፍጠኝ ፡ ሚስቴ ፡ ወደ ፡ ልጅሽ ፡ ሂጂ
በዘዴ ፡ በርጋታ፡ነገሩን አስረጂ ፡
መልካሙ ፡ ልጃችን 'ፓሪስ ፡ አንቺን ፡ ወዶ ፡
እኔም ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ አባትሽም ፡ ፈቅዶ ፡
ይኸው ፡ በዚህ መሰሞን ሊያገባሽ ፡ ነውና
ተዘጋጂ፡ በያት ፡ በሙሉ ፡ ልቡና '
በል ፡ አንተም ፡ ንገረኝ ፡ እንደምትፈልገው
ሰርጉ ፡ እንዲፈጸም ለመቼ እናድርገው ?

#ፓሪስ
እንደ ፡ እኔ ፡ ሰርጋችን ፡ የራቀ ፡ ከሚሆን ፡
ቢፈጸም ፡ ይሻላል ፡ አሁን ፡ በዚህ ፡ ሰሞን

#ካፑሌ
እንግዲያው መልካም ነው ባጭር እንደግስ
ተክሊሉም ፡ ይፈጸም ፡ በሚመጣው ፡ ኀሙስ ፡
ጃጃታ ፡ አላበዛም ብዙም ፡ ሰው ፡ አልጠራ ፤
ልጄን ፡ እድራለሁ ፡ ብዬም ፡ አላወራ ፡
ሐዘን ፡ ስለ ፡ ሆነ ፡ቲባልት፡ በመሞቱ ፡
ቅር ፡ ያሰኛልና ፤ ዘመድ ፡ በጥቂቱ ፡
በድብቅ ፡ እንጥራ ፡ ነገር ሳናበዛ ፤
እንደዚህ 'ብናደርግ ፡ ወሬው ፡ ሳይነዛ ፡
ጉዳያችን'ያልቃል፡ያግር፡ ሰው ፡ ሳይሰማ ፤
እንግዲህ ፡ መልካም ፡ ነው ፤ በዚሁ 'እንስማማ ።

#ፓሪስ
እኔም ፡ እስማማለሁ ፡ ይሁን ፡ በዚሁ ፡ ቀን
በሉ ፡ እስከዚያው፡ድረስ፡እግዜር፡ይጠብቀን ። (ሄዳ).

#ካፑሌ ፡ (ለሚስቱ )
እንደዚህ ፡ ያለ ፡ ባል ፡ ትልቅ ፡ ሰው ፡ የበቃ
ቢሄዱ ፡ አይገኝም ፡ እግር ፡ እስቲነቃ ፡
በይ ፡ ቶሎ ፡ ፍጠኚ ፡ ወደ ፡ ልጅሽ ፡ ሂጂ ፤
ነገ ፡ ጧት ፡ አሳቧን ፡ ልቧን ፡ አዘጋጂ ።

#ሮሜዎና #ዡልዬት ፡ (በዥልዬት ' መኝታ ፡ ቤት) ።

#ዡልዬት
አይዞህ፡አትቸኵል ፡ አልነጋም ፡ ሌሊቱ ፤
ቁጭ ፡ በል ፡እናውጋ ፡ ገና ፡ ነው ፡ ሰዓቱ ፡
ተመልከት ጨለማ መሬቱን
ሲሸፍን ፡
የሰማናትም ፡ ወፍ ፡ አሁን ፡ ስትዘፍን ፡
ዞትር ፡ ልማዴ ፡ ነው ፡ ሌሊቱ ፡ ሳይነጋ ፡
መጮህ ፡ ትወዳለች ፡ እመነኝ ፡ አትሥጋ

#ሮሜዎ
ይህች ፡ የንጋት ፡ ወፍ ፡ ነች ፡ አሁን ፡ የጮኸችው ፤
ትክክል ፡ ይታያል ፡ ዡልዬት ፡ ተመልከችው
ሰማይ ወገግ፡ አለ ፡ ያው በምሥራቅ በኩል ፤
ሰዓቱ ፡ ደረሰ ፡ እንግዴህ ፡ ልቸኵል ፡
በቬሮና ፡ አድሬ ፡ ቢያገኙኝ ፡ ሳልወጣ ፡
መስፍኑ ፡ ፈርደዋል ፡ በሞት ፡ እንድቀጣ ፡
ልዳን ፡ ያልኩ ፡ እንደሆን ፡ ሕይወቴን ፡ ወድጄ ፡
መሄድ ፡ ይገባኛል ፡ አሁን ፡ ተሰድጄ ።

#ዡልዬት
እኔ ፡ መች ፡ አጣሁት ፡ ይህ ፡ ያሁኑ ፡ ብርሃን ፡
የሰማይ ፡ ፋና ፡ ነው ፡ የኮከብ ፡ ውጋጋን
ሌሊት ፡ በጨለማ ፡ ሳይነጋ ፡ ሌሊቱ ፡
ለምን ፡ ትሄዳለህ ፡ አሁን ፡ ወደ ፡ ማንቱ ፡
አይዞህ ፡ እንጫወት ሌቱ ፡ አልነጋም ፡ ገና
ጊዜ ፡ አለን ፡ እስኪታይ ፡ የንጋቱ ፡ ፋና ።

#ሮሜዎ
ዘፈኑ ፡ ሲወጣ ፡ አልሰማንም ፡ ካፍ
አልነጋም ፡ ሌሊቱ ፡ አልጮኸችም ፡ ወፍ፡
ይህም ፡ በሰማይ ላይ የሚታይ ፡ ውጋጋን አይደለም ፡ የመጣ ፡ ከፀሓይዋ ፡ ብርሃን ፡
ብለን ፡ እንካደው ፤ አምኜ፡ ልቀበል !
ሳልወጣ ፡ ይያዙኝ ፡ ተይዤም ፡ ልገደል "
ካንቺ ፡ ተለይቼ ፡ የሐዘን ፡ ኵነኔ ፡
ከሚያገኘኝ፡ መሞት ፡ እመርጣለሁ ፡ እኔ ።
አልፈራም ፡ ፈጽሞ ፡ በሞት ልቀጣ
ዡልዬት ፡ ከፈቀደች ፡ የፈለገው ፡ ይምጣ ፡
ወፎች አልተንጫጩም ሌሊቱም ፡ አልነጋ
ዡልዬት ጨዋታ አምጪ እንግዴህ እናውጋ፡

#ዡልዬት
እኔ ፡ ብዬ ፡ ነበር ፡ ገና ፡ ነው ፡ ሌሊቱ፤
አሁን ፡ ገና ፡ታየኝ ፡ ትክክል ፡ መንጋቱ ፡
ንጋት ፡ ነው ፡ የመጣው ፡ ሂድ ፡ ቶሎ ፡ ተነሣ፤
አምልጠህ ፡ ሽሽ ፡ ቶሎ ፡ ብረር ፡ በግሥገሣ ፡
እየው ፡ ተመልከተው ፡ የንጋት ፡ ወገግታ፤
ጨለማውን ቀዶ፡ ሄደ ፡ እየበረታ ፡
አስተውለው ፡ መሬቱ ፡ ሲታየን ፡ ተገልጦ ፤
አሞኘችኝ፡ ወፏ ድምፅዋ ፡ ተለውጦ ፡
ፍጠን ፡ ቶሎ ውጣ እየው፡እንደ፡ ነጋ ፤
ተነሥ ፡ ቶሎ ፡ ጥፋ፤ አይንካህ ፡ አደጋ ።

#ሞግዚት
እናትሽ ፡ ነቅተዋል' እመቤቴ ፡ ዕወቂ፤
መንጋቱ ፡ ነውና ' በጣም' ተጠንቀቂ "
ደኅና ሰንብት ፡ ልበል ፡ እኔው ፡ አስቀድሜ
እንግዴህ ፡ ደኅና'ሁን'ሮሜዎ ፡ ወንድሜ ።

#ሮሜዎ
ዡልዬት ደኅና ሁኝ ፡ ደኅና ሰንብች ፡ ፍቅሬ

#ዡልዬት
አደራ ፡ እንዳገኘው ፡ እኔ ፡ ያንተን ፡ ወሬ ፡
ሁል ፡ ጊዜ ጻፍልኝ ፡ መሆንህን ፡ ጤና ፤
መቼ ፡ እንደማገኝህ ፡ አላውቀውምና ።

#ሮሜዎ
መቼም ፡ ቢሆን ፡ ካንቺ ፡ አይለይም ፡ ልቤ
እጽፍልሻለሁ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስር


የካፑሌ ፡ ሚስት (የዡልዬት እናት)
ወዴት ፡ ነው ፡ ያለሽው ፡ ልጄ ፡ ተነሣሽ ፡ ወይ ?

#ዡልዬት
ይኸው ፡ ተነሣሁኝ ፡ ምነው ፡ እናቴ ሆይ ?
(ለብቻዋ ፡ ቀስ ብላ)
ምን ፡ ነካት ፡ እናቴ ፡ እንዲህ ፡ ጧት ፡ ተነሥታ ፈልጋኝ አታውቅም በማለዳ መጥታ ።
(የካፑሌ ሚስት ' ወደልጅዋ፡ወደ፡ዡልዬት መኝታ' ቤት፡ገባች

#የካፑሌ_ሚስት
ዐፈር ፡ አስመሰለሽ ፡ የቲባልት ፡ ሐዘን ፡
ያስፈልጋል ፡ ልጄ ፡ ማሰብ ፡ ማመዛዘን '
እንባ ፡ ቢያፈሱለት ፡ ቢያለቅሱለት በጣም
ሰው ፡ አንዴ ከሞተ ተመልሶ ፡ አይመጣም
ሐዘን ፡ የሚያስረሳ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ወሬ
ይዤ ፡ ወዳንቺ ፡ ዘንድ ፡ መጥቻለሁ' ዛሬ "

#ዡልዬት
እናቴ ፡ ንገሪኝ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ያለ ፡ ነው ?

#የካፑሌ_ሚስት
በቲባልት ፡ መሞት ፡ በብዙ ፡ ያዘነው ፡
ልብሽ ፡ እንዲጽናና ፡ በጣም ፡ በማሰቡ ፡
መልካሙ ፡ አባትሽ ፡ አላረፈም ፡ ልቡ ፤
በዚሁ ፡ ምክንያት ፡ ሳይውልም ፡ ሳያድር ፡
ቈርጧል ለጥሩ ባል ኀሙስ አንቺን ሊድር
ባልሽ ፡ የሚሆነው ቆንዦ ነው ፡ ጌታ ሰው
በዘርም ፡ በገንዘብ ፡ ምንም ፡የማያንሰው !
እንዲያውም ፡ ገልጨ ፡ ልንገርሽ ፡ ካሁኑ ፤
መልካሙ ፡ፓሪስ ፡ ነው ፡ ወጣት ፡ መኰንኑ

#ዡልዬት
እናቴ ፡ ሆይ ፡ምነው ፡ በፊት ፡ ሳንማከር ፡
እንደ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ እንዲህ ያለ ፡ ነገር
አስቀድመን ፡ እኛ ፡ ተጫጭተን ፡ በደንቡ፡
ሳላውቀው ሳያውቀኝ ፡በፍጥነት ፡ ተጋቡ !
እንዴት ፡ ትላላችሁ ፡ እንዲህ ፡ በችኰላ ?
አሁንም ፡ በቶሎ ፡ ፈልጉለት ፡ መላ'
እኔ ፡ አልችልምና ፡ ለማግባት ፡ በቶሎ ፤
አባቴን 'ንገሪው ፡ እንደ ፡ ምንም ፡ ብሎ
ቃል ቢኖር ምናልባት ለፓሪስ የሰጠው
አንድ' ዘዴ ፡ ፈጥሮ ፡ ቶሎ ፡እንዲለውጠው

#የካፑሌ_ሚስት
አፍሽን ፡ አታጥፊ ፡ ምክንያት ፡ አታምጪ '
ያለቀ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ ዐርፈሽ ፡ ተቀመጪ ።

#ዡልዬት
አድምጪኝ ፡ እናቴ ፡ እንግዲያውስ ፡ ስሚ
አባቴም ፡ አይልፋ ፡ አንቺም ፡ ኣትድከሚ'
የመጣ ፡ ቢመጣ ፡ መቼም ፡ቢሆን ደግሞ
እኔ ፡ አላገባም ፡ ፓሪስን ፡ ፈጽሞ ።

#የካፑሌ_ሚስት
አልገባም ፡ ጨርሼ ፡ እኔ ፡ በዚህ ፡ ጣጣ ፤
ንገሪው ፡ ላባትሽ ፡ ይኸው ፡ወዲህ ፡ መጣ

#ካፑሌ ፡ (ገባ)
ምነው ፡ ምን ሆናችሁ ? በይ ልመለስ ሄጄ
ታዲያስ ፡ ነገርሻት ፡ ወይ ነገሩን ፡ ለልጄ ?

#የካፑሌ_ሚስት
እኔ ፡ ከሷ'ጋራ ፡ አልችልም ፡ ክርክር ፤
ትችል ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡አስረዳት ፡ በምክር ።

#ካፑሌ
እስቲ ፡ እኮ ፡ ንገሪኝ ፡ ምንድነው ፡ ነገሩ ፡
አሁን ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ደርሶ ፡ ግርግሩ ።

#የካፑሌ_ሚስት
ትችል ፡ ትመስላለህ አንተ ፡ ደግሞ ፡ ደርሶ
የምሥራች ፡ « እንቢ» ፡ ብላለች ፡ ጨርሶ ፡
የመጣ ፡ ቢመጣ ፡ ይልቁንም ፡ ደግሞ ፡
አላገባም ፡ አለች ፡ ፓሪስን ፡ ፈጽሞ ።

#ካፑሌ
እግራችንን ፡ ስማ ፡ እኛን ፡ አመስግና ፡
በትልቅ ፡ ደስታ ፡ መቀበል 'ቀረና ፡
እንቢ ፡ አለች ፡ ብትይኝ ጆሮዬም ፡ አይሰማ
እስቲ ፡ ልስማው ፡ እኔ ፡ ትናገረው ፡ ደግማ

#ዡልዬት
ለክፋት ፡ አይደለም ፡ አትቈጣ ፡ አባቴ ።

#ካፑሌ
እረግ ፡ የኛ ፡ ሕፃን ፡ ትንሿ ፡ ማሚቴ ፡
የማነሽ ፡ ለዛ ፡ ቢስ ፡ የማነሽ ፡ ወልጋዳ ፤
የማነሽ ፡ አመዳም ፡ የማነሽ ፡ ገዳዳ'
ባለወግ ፡ አድርገን እኛ ፡ ነን ያጠፋን ፡
ብታውቂው ፡ ባታውቂው ኧረ ምን ፡ አለፋን
በግድ፡ ነው ፡ እንጂ፡ በኅይል ፡ የምንድር ፡
መች ፡ ያስፈልግና ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ንግግር
ነገ ፡ በማለዳ ፡ ተዘጋጅተሽ ፡ ውጪ ፣
ከተክሊሉ ፡ ቦታ ፡ ዐውቀሽ ' እንድትመጪ,
ታዛዤ ፡ ነሽና ፡ የወለድኩሽ ፡ ልጄ ፣
እኔ ፡ እድርሻለሁ ፡ በኀይል' አስገድጄ ፤
ለወግ ፡ መጠየቄ ፡ ቅብጠት ፡ነው ፡ አብጄ
እስከዚያ ፡ ድረስ ፡ ግን ፡ በፊቴ ፡ አትለፊ ፤
ዐይንሽን ፡ አልየው ፡ ካጠገቤ ፡ ጥፊ ።

#ዡልዬት
ነገሩን ፡ ላስረዳህ ፡ አባቴ ፡ አድምጠኝ ፤
ጋብቻው ፡ ፈጠነ ፡ ጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ስጠኝ

#ካፑሌ
ነገርሽ እሬት ነው ፡ መሪር ነው ፡ ኮምጣጣ
ካፍሽ ፡ ካንደበትሽ ፡ አንድ ፡ቃል፡ አይውጣ'
ሴት ልጅ እንቢ፡ብትል፡አለው አንድ አገባብ
መች ተሠርቶ ያውቃል እንዲህ፡ያለ ጥጋብ
ዘሩ ፡ የታወቀ ነዉ መልኩ ፡ የሚያኰራ ፡
ገንዘብ ፡ የተረፈው ፡ ስሙ ፡ የተጠራ፡
ደኅና ፡ ባል ፡ ፈልጎ ፡ በስንት ፡ መከራ፡
አባቷ ፡ ሲያመጣ ፡ ወዲያ ፡ ወዲህ ፡ ዞሮ '
ከቤት ፡ ተወዝፋ ፡ የኛ ፡ ሴት ፡ ወይዘሮ ፡
እኔ ፡ ባል ፡ አልሻም ፡ ትላለች ፡ ሞጋጌ ፤
መካን ፡ ሰው ፡ ይሻላል ከመውለድ ፡ ባለጌ
ጥኀጋብሽ ፡ ነው ፡ እኮ ደሜን ፡ የሚያፈላው ፤
ምኑ ፡ ነው ፡ እባክሽ ፡ፓሪስ ፡ የሚጠላው ?
ያለባል ፡ ለመኖር ፡ ከሆንሽ ፡
የምትወጂ ፡
ምን ፡ ቸገረኝ፡ እኔ ፡ ወደ ፡ ገዳም ፡ሂጂ ፡
ነገር ፡ ግን ፡ ከሆነ ፡ ማግባትሽ ፡ የማይቀር ፡
የመረጥኩልሽን ፡ ይገባሻል ፡ ማፍቀር ፡
ያላንድ ፡ ክርክር ፡ ያላንድ ፡ ቅሬታ ፡
ፈቃዴን ፡ መቀበል ፡ አለብሽ ፡ ግዴታ ።
የምትይ ፡ ከሆነ ፡ የኔን ፡ ፈቃድ ፡ እንቢ ፡
ከዛሬ ፡ ጀምረሽ ፡ ሂጂ ፡ ገደል ፡ ግቢ ፤
ዐይንሽን ፡ አልየው ፡ በዚህ ፡ በኔ ፡ ግቢ ።
የካፑሌ ፡ ሚስት ።
ቀስ ፡ ብሎ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ አባት ፡ ከመከረ ፡
አንተም ፡ አበዛኸው ፡ ነገርህ ፡ ከረረ ።
ካፑሌ ።
አትግቢ ፡ ፈጽሞ ፡ አንቺ ፡ በኔ ፡ ሥራ ፤
ሂጂ ፡ ወደ ፡ ጓዳ ፡ ከሴቶቹ ፡ ጋራ ፡
ቀኑን ፡ ሙሉ ፡ ባሳብ ፡ ሌሊቱን ፡ በሕልሜ ፡
ባል ፡ ስፈልግላት ፡ በመኖር ፡ ደክሜ ፡
በስንት 'ዐይነት ፡ ዘዴ ፡ እኔ ፡ ተጣጥሬ፡ .
እግዚአብሔር ረድቶኝ ፡ ይኸውና ፡ ዛሬ ፡
የሚሆን ፡ ሰው ፡ ባገኝ ፡ ጨዋ ፡ባለገንዘብ፡
እሜቴ ፡ ፈጠሩ ፡ ሠላሳ ፡ ሺሕ፡ ሰበብ ።
ስሚኝ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ልንገርሽ ፡ ካሁኑ፤
እሱን ፡ ካላገባሽ ፡ ታዘቢኝ ፡ በውኑ
የትም ፡ ትሄጃለሽ ፡ አብርሬሽ፡ ከቤቴ፤
እርሜን ፡ አወጣለሁ ፡ ቆርጬሽ ፡ ካንጀቴ
ልጅና ፡ አባት ፡ ሆነን ፡ መኖራችን ፡ ቀርቶ ፡
ክጄሽ ፡ ትሄጃለሽ ፡ አልምርሽም ፡ ከቶ ፡
ስለዚህ ፡ አስቢ፡ ከልብሽ ፡ ምከሪ፤
የሚከተለውን ፡ ተመልክተሽ ፡ ፍሪ'
ካሁኑ ፡ ጀምረሽ ፡ በነገሩ፡ ሥጊ፤
ቃሌ ፡ አይታጠፍም ፡ ኋላ ፡ ልብ ፡ አድርጊ
(ካፑሌ "ከቤት " ወጥቶ ሄደ)

#ዡልዬት
እባክሽ ፡ እናቴ ፡ ለልጅሽ ፡ እዘኚ፤
ባይሆን ፡እንኳን ፡ አንቺ ፡ ከኔ ፡ ወገን ፡ ሁኚ'
ቀኑ ፡ ረዘም ፡ ይበል ጥቂት ፡ ጊዜ ስጡኝ፤
አሳቤን ፡ ሳታውቁ ፡ በከንቱ ፡ አትቁጡኝ ።

ግዴታ፡ ካልሆነ' በጣም ' ካልቸረኝ፡
እንቢ ፡ አልልምና ፡ ምክንያት ፡ ካልኖረኝ ።

#የካፑሌ_ሚስት
ዕዳሽን ፡ በጨርቅሽ ፡ እንደምትፈልጊ '
አንቺ ፡ እንደ ፡ ፈቃድሽ 'እንዳሻሽ አድርጊ ።
(እናቷም' ወጥታ ሄደች)

#ዡልዬት
ርጂኝ ፡ አንቺ ፡ እባክሽ ፡ ምከሪኝ ፡

#ሞግዚቴ
ምስጢር፡ ተካፋዬ፡አንቺ፡ነሽ ፡እናቴ '
የኛን ተክሊል ማንም አይችልም፡ሊያፈርሰው፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ድብቅ ፡ ነው አያውቅም፡ማንም፡ሰው፡
እባክሽ ፡ ምከሪኝ ፡ ዘዴ ፡ አታጭምና ፤
ጨነቀኝ ፡ ጠበበኝ'አገኘኝ ፡ ፈተና ።

#ሞግዚት
ቃሌን ፡ ብትሰሚ ፡ ተራዬን ፡ ልናገር ፤
ሮሜዎ ፡ ሰው ፡ ገድሎ ፡ ተሰደደ ፡ ካገር፡
ልትኖሩ ፡ ከሆነ ፡ ለብቻ ፡ ለብቻ ፡
በዚሁ ፡ ይፈርሳል ፡ የናንተ ፡ ጋብቻ ፡
በዚሁ ፡ ላይ ፡ ደግሞ ፡ አባትሽ ፡ ላባቱ
👍1
ቂመኛ ፡ ነውና 'ደመኛ ፡ ጠላቱ ፤
ዕርቅ ፡ይኖራል ፡ ማለት ፡ መጓጓት ፡ ነው ፡ ከንቱ ።
ስለዚህ ፡ ፓሪስን ፡ እሺ ፡ ብለሽ ፡ አግቢ ፤
ሮሜዎን ፡ በልብሽ ፡ በቃሽ ፡ አታስቢ '
ደግሞስ ፡ ምንና፡ ምን ፡ እነዚህ ፡ ሁለቱ ፤
ፓሪስ ፡ የላቀ ፡ ነው ፡ በውበት ፡ በሀብቱ ፡
በዘር፡ በጌትነት'ይበልጣል' በሁሉ ፤
ደግሞስ ፡ ከዚህ ፡ በላይ፡ ሕግስ ፡ ቢሆን ፡
በድብቅ ፡ የሆነው ፡ አይረጋም ፡ተክሊሉ ።

#ዡልየት
እውነት ፡ ካንጀት ነው ወይ ፡ የምትናገሪ ?

#ሞግዚት
ከልቤ ፡ መሆኑን ፡ አትጠራጠሪ ።

#ዡልዬት
መልካም ፡ ነው በይ ሄደሽ ንገሪያት ለናቴ
መሄዴ ፡ ነውና ፡ በፍጥነት ፡ መውጣቴ ፡
ወደ ፡ አባ ፡ ሎራ ፡ ዘንድ በፍጥነት ፡ ደርሼ
እመጣለሁ፡በያት፡አሁን፡ተመልሼ ። (ሞግዚት ' ሄደች) "

(#ዡልዬት ብቻዋን) •
ለማ ፡ ልናገረው ፡ ምስጢሬን ፡ ገልጩ፡
ወደ ፡ አባ ፡ ሎራ ፡ ዘንድ ፡ ልሂድ ፡ እንጂ ፡
ከካህናቶች ፡ ዘንድ ፡ ቢበጅም ፡ ቢከፋ፡
የነፍስ ፡ መድኀኒት፡ ምን ጊዜም ፡ አይጠፋ

💫ይቀጥላል💫
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስራ_ሁለት

#ዡልየት
ወደ ፡ አባ " ሎራ ፡ ዘንድ ፡ ደርሼ ፡ ነበረ ፤
ምክራቸው ፡ ገሠጸኝ ልቢ ፡ ተሰበረ ፡
ያንተን ፡ ያባቴን ፡ ቃል ፡ ልፈጽም ፡ ፈቅጄ ፡
የምጠላውን ፡ ሰው ፡ ስላንተ ፡ መድጄ፡
ፓሪስን ፡ ላገባ ፡ ሆኛለሁ ፡ ዝግጁ
ሰርጌ ፡ ይሰናዳ ፡ ሁሉንም ፡ አብጁ
ደግሞም ብለውኛል አጥብቀው በብርቱ
« ምሕረቱን ፡ ለምኚ፡ ወድቀሽ ፡ ከጕልበቱ
(ተንበረከከች)
ንዴት ፡ አይግባችሁ ፡ በኔ ፡ የተነሣ ፤
ያለፈው ፡ ጥፋቴ ፡ እንግዴህ ፡ ይረሳ፡
የሰላም ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ያለም ፡ የደስታ ፡
ለኔም ፡ ለልጃችሁ ፡ አድርጉ ፡ ይቅርታ ።

#ካፑሌ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ካህን ፡ እግዜር ፡ የባረከው
ምክሩ ፡ ንግግሩ ፡ ለሰው ፡ የሚሰብከው ፡
ከጻድቅ ፡ የመጣ ፡ ንጹሕ ፡ በመሆኑ ፡
ጠልቆ ፡ ልብ ፡ ይገባል ያጠግባል ፡ በውኑ
እስቲ ፡ አሁን ፡ ባሁን እንደ ፡ ምን ፡ አድርጎ
መልሶ ፡ ላከልኝ ፡ አንቺን ፡ ወደ ፡ በጎ ።
(ከተንበረከከችበት ቦታ'ያስነሣታል )

ተነሺ ፡ ከመሬት ፡ ይብቃ ፡ አትንበርከኪ ፡
ምክሩን ፡ መከተልሽ ፡ አንቺም ፡ ተባረኪ ።
(ወዴ ፡ ሚስቱ' መለስ ' ብሎ)
እንግዴህ ፡ ይፋጠን ፡ ይቀጥል ፡ ድግሡ፤
አሽከሮቹ ፡ ሁሉ ፡ በሌሊት ፡ ይነሡ ፡
ተክሊሉ ፡ እንዲፈጸም ፡ ነገ ፡ በማለዳ ፡
ማንኛውም ፡ ነገር ፡ ዛሬ ፡ ይሰናዳ ።
(በካፑሌ ፡ ቤት ጧት) ,

#ካፑሌ
ሰዎቼ ፡ ተኝተው ፡ ሳይነሡ ፡ ካልጋ ፡
ወፎቹ ፡ ተንጫጩ ፡ ይኸው ፡ ሌቱ ፡ ነጋ ፡
ተነሡ፡ረፈደ፡እሳቱን ፡ አንድዱ፤
መብሉን ፥ መጠጡን ፥ በቶሎ ፡ አሰናዱ ።

የዡልዬት ፡ ሞግዚት'
ርስዎ ፡ ዛሬ ፡ ሌሊት ፡ ጨርሰው ፡ ሳይትኙ
ቁጭ ፡ ብለው ፡ ነጋ ፡ ሥራውን ፡ ሲቃኙ፡
በጣም መልካም ነበር አሁን ጥቂት ቢያርፉ

#ካፑሌ
አታስቡ ፡ ለኔ ፡ ይልቅ ፡ አትስነፉ ፡
አያሸንፈኝም ፡ ዱሮም ፡ ቢሆን ፡ እንቅልፍ ፡
መብልና ፡ መጠጥ ፡ ደኅና ፡ የሚያሳልፍ ፡
ወዴት፡አገኝ፡ ይሆን ፡ የሠለጠነ ፡ ሰው ፤
ምንም ፡ ሳይዘጋጅ ፡ አንዱንም ፡ ሳንይዘው
ስትተራመሱ ፡ እንዲሁ ፡ በከንቱ ፡
የሙሽራው ፡ መምጫ ፡ ደረሰ ፡ ሰዓቱ ፡
ዕቃ ፡ ማነሱ፡ ነው ፡ አንዱም ፡ የሚያውከው ፡
(አሽከሮቹ'ገቡ' በያይነቱ፡ ዕቃ ፡ ይዘው)»
ምንድነው'ደግሞ አንተ ይህ የተሸከምከው ?

#አሽከር
የጠቦት፡ ሥጋ ነው፡ ለጥብስ ፡ የታረደ

#ካፑሌ
በል ፡ፍጠን ፡ ቶሎ ፡ በል ፡ ሰዓቱ ፡ ረፈደ ።

#የካፑሌ_ሚስት
ከምን ጊዜ ነጋ አለፈ ሌሊቱ ካፑሌ
አንቺን ፡ አይጠብቅም ፡ ጊዜና ፡ ሰዓቱ
ሙሽራው ይመጣል አንዱን ሳትጨብጨው።
የሚያስፈልገውን ፡ ለወጥ ፡ ቤቱ ፡ ስጪው
አለዚያ ፡ ሲቸኵል ፡ ይበላሻል ፡ ወጡ!
አንችም ፡ ቶሎ ፡ ልበሽ ፡ ሰርገኞች ፡ ሳይመጡ ።

#የካፑሌ_ሚስት
ዡልዬት ሳትነሣ እኔም ልብሴን ሳልለብስ ፡
በጣም ፡ ያስደንቃል ፡ የሰዓቱ ፡ መድረስ ፡
እመጣለሁ ፡ ብሏል ፡ ፓሪስ ፡ በሙዚቃ ፡
እንግዴህ ፡ ዡልዬትም ፡መተኛቷ ፡ ይብቃ።
(ሞግዚቷ ፡ ገባች)
እንዴት ፡ ረፈደ ፡ በጣም ፡ ያስገርማል ፤
ሰርገኞቹ ፡ መጡ ፡ ሙዚቃው ፡ ይሰማል !
እባክሽ ፡ ፍጠኚ ፡ ቶሎ ፡ በይ ፡ አስነሻት ፤
ገላዋን ፡ ትታጠብ ፡ ልብሷንም ፡ አልብሻት
ቶሎ ፡ እንደ ፡ ጨረሰች ፡ ለብሳና ፡ አጊጣ ፡
አብራችሁ ፡ ካንቺ ጋር ወደኛ እንድትመጣ
እኔም ፡ ሰርገኞቹን ፡ እስከዚያ ፡ ልቀበል ፤
አሽከር ፡ በሩን ፡ ክፈት እባክህ ፡ ቶሎ ፡ በል

በዡልዬት ፡ መኝታ ፡ ቤት ።

#ሞግዚት ፡ (ዡልዬትን፡ትቀሰቅሳለች) •
ተነሺ ፡ ረፈደ ፡ ዡልዬት ፡ እመቤቴ ፤
ተነሺ ፡ ይሉሻል ፡ እናትሽ ፡ እሜቴ ፡
ሰርገኞች ፡ ሲመጡ ፡ ሙዚቃ ፡ ሲሰማ
አትንቀሳቀስም ፡ እሷ ፡ ግን ፡ ፈጽማ ፤
ምነው ፡ ምን ሆንሽብኝ ተነሺ እንጂ ቶሎ
አንቺን ፡ ይጠብቃል ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ቸኩሎ
(ገልጣ' ታያታለች) •
እኔ ፡ ጠፋሁ ፡ ዛሬ ፡ ያለትንፋሽ ፡ ቀርታ ፡
ገላዋ ፡ ቀዝቅዟል ፡ እመቤቴ ፡ ሞታ፡
እረ ፡ ትልቅ ፡ጉድ፡ ነው ፡ ኑ፡ ቶሎ ፡ድረሱ !

#የካፑሌ_ሚስት
ማነው ይህን ያኽል የሚጮኸው እሱ ?

#ሞግዚት
አሁን ፡ በገደለኝ ፡ መሬት ፡ እኔን ፡ ውጦ ።

#የካፑሌ ፡ ሚስት ።
አትጩሂ ፡ እባክሽ ፡ እንግዳ ፡ ተቀምጦ ።

#ሞግዚት
ልጅዎን ፡ ያስተውሏት ፡ በመኝታ ፡ ቤቷ ፤

#የካፑሌ_ሚስት (ግባች) •
ስለምን፡ነው ፡ እስካሁን ፡ አለመነሣቷ ?
ልጄ ፡ ዡልዬት ፡ ተነሽ ፡ ዐይንሽን ፡ ግለጪ
አባቷን ጥሩልኝ ፡ በቶሎ ፡ ከውጪ
ልጄን ፡ ምን፡ አገኛት ፥ ሞታለች ፡ ጨርሶ ።

#ካፑሌ ፡ (ገባ) «
እንግዲህ ፡ መንጫጫት ይወዳሉ ፡ ደርሶ
ዡልዬት አትመጣም ወይ ሙሽራው ሲጠብቅ

💫ይቀጥላል💫
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስራ_ሁለት

#ሞግዚት
ሞታለች ፡ ሞታለች ፡ ጕድ ፡ ነው ፡ የሚያስደንቅ ,

#የካፑሌ_ሚስት
ምን ፡መድኀኒት ላምጣ ወዴት ስፍራ ሄጄ

#ካፑሌ
ቆዩ፡እስቲ፡እኔ፡ልያት፡ የታለች፡ ቀዝቃዛ ፡ (እየዳበሳት).
ፈጽማ ፡ ሞታለች ፡ በምን ፡ ጕዴ በዛ
ሌሊት፡ በጨለማ ፡ ፀሓይዋ፡ ሳትወጣ ፡
ልጄ ፡ አበባዬ ፡ ወድቃለች ፡ ተቋርጣ ።

#ሞግዚት
የተረገመ ፡ ነው ፡ አወይ ፡ የዛሬው ቀን ፤

#የካፑሌ_ሚስት
ምነው ፡ ብንቀበር ፡ ሁላችንም ፡ አልቀን !

#ካፑሌ
ምንም ፡ አልናገር' ምላሴ 'ታሰረ
ልሳኔ ፡ በሐዘን 'ተቁልፎ ፡ ቀረ ።
(አባ ' ሎራና 'ፓሪስ ' በሙዚቃ ገቡ ።)

#አባ_ሎራ
ወደ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን እንሂድ ፍጠኑ
ሙሽራዋን ጥሩ እናንተም ቶሎ'ኑ ።

#ካፑሌ
ጉድ ሆነናል ዛሬ ይተዉ አባቴ
ጕድ ፡ ለማየት ፡ ኖሯል ፡ የቈየች ፡ ሕይወቴ
እኔ ፡ ወዴት ፡ ልድረስ ፡ የት ፡ አባቴ ፡ ልግባ
ሞተች ፡ ተቀጠፈች ፡ ልጄ ፡ የኔ ፡ ኣበባ ።
እናቷ ፡ ሳታስብ ፡ ኣባቷ ፡ ሳይሰማ ፡
ሞት ፡ የሚባል ፡ ሌባ ፡ ሌሊት በለጨለማ
ለካ ፡ ከቤታችን ፡ ገብቶ ፡ ተደብቆ ፡
ይዟት ፡ ሄዶ ፡ ኖሯል ፡ ልጃችንን ፡ ሰርቆ ፤
እንዴት ፡ ጉድ፡ ሆነናል ፡ እንዲህ ፡ ተደግሶ
ሰርጓ ሐዘን ፡ ሆነ ደስታችን ለቅሶ ።

#ፓሪስ
እኔ ፡ ዕድለ ፡ ቢሱ፡ እንዴት፡ ያለ ፡ መርዶ፡
እንዴት ፡ ያለ ፡ሐዘን ፡ ጠበቀኝ ፡ ተወልዶ

#የካፑሌ_ሚስት
የተረገመ ፡ ነው ፡ አወይ ፡ የዛሬ ፡ ቀን
ቀረን ፡ እኮ ፡ ሰዎች ፡ እንደዚህ ፡ ተሳቀን ፡
ያይኖቼ ፡ ማረፊያ ብትኖረኝ አንዲት ፡ ልጅ
ያንድ ፡ ቀን 'ደስታ' ለማየት'ስዘጋጅ፡
ለማን ኣቤት ልበል ፡ ሞት ፡ ይዞብኝ ፡ ሄደ
ሆዴ ተቃጠለ አንጀቴ ፡ ነደደ

#አባ_ሎራ "
ይብቃ ፡ ለሐዘኑ ፡ አድርጉለት ፡ መጠን ፤
አስቡ ፡ ይችን 'ልጅ' እግዜር ፡ ነው' የሰጠን
አሁንም ፡እግዚአብሔር ወሰዳት መልሶ :
ሐዘናችሁ ፡ አይሁን ፡ ያረመኔ ፡ ለቅሶ ፡
ቀረባት ፡ ብላችሁ ፡ የመሬት ፡ ደስታ ፡
ጸጸታችሁ ፡ አይሁን ፡ በጣም ፡ የበረታ ፡
የመሬት ፡ ደስታ ፡ ምንም ፡ የለው ፡ ዋጋ ፤
ይልቅ አይበልጥም ወይ የሰማይቤት ጸጋ፡
ከሚያልፍ ፡ዓለም ወጥታ፡ ከዘለዓለም ቤቷ
መተላለፍ፡ ነው ፡ በሰላም ፡ መግባቷ ፡
መሆኑ ፡ ቀረና፡ ሰርጓ በመሬት ላይ፤
ብርሃን ፡ ወዳለበት፡ሄደች፡ ወደ ፡ ሰማይ ፡
እናድርጋት ፡ ስንል ፡ ምድራዊት ፡ ሙሽራ ፡
አይሆናትም ፡ ብሎ ፡ የመሬት ፡ መከራ ፡
ሺሕ ፡ ጊዜ ፡ የላቀ ፡ ደስታ፡ አዘጋጅቶ ፡
እግዚአብሔር ፡ ወሰዳት ፡በፈቃዱ ፡ ጠርቶ
የሰርግ ልብሷን ለብሳ እንዳማረች በክብር
በሉ ፡ ያዟትና ፡ እንሂድ ፡ መቃብር ።

#ሮሜዎ ። (በተሰደደበት ፡ አገር 'ሆኖ)
መሠረት ፡ ቢኖረው ፡ የኔ ፡ ሕልም፡ ዛሬ ፡
አገኝ ፡ ይመስለኛል ፡ ደስ የሚያሰኝ ፡ ወሬ
ዡልዬት ፡ ስትመጣ ፡ ስታገኘኝ ፡ ሞቼ ፡
አልቅሳ ፡ ስትስመኝ ፡ እኔ ፡ ተዘርግቼ ።
ኋላም ፡ በሷ ፡ ትንፋሽ ፡ ሕይወቴን ፡ አድሼ
ከሞት ፡ ተነሥቼ ፡ አየሁኝ ፡ ነግሼ ።
በጣም ፡ ደስ ፡ ብሎኛል ፡ ዛሬ ጧት፡ጀምሮ
ሰላም ፡ ይሰማኛል ፡ የመንፈስ ፡ የአእምሮ
(ቤልሻጥር ቦት ጫማ አድርጎ፡ መጣ)
ቤልሻጥር ፡ጐበዙ፡ እንኳን ፡ ገባህ ፡ ደኅና'
ምን ወሬ ይዘህ መጣህ ዛሬ ከቤሮና ?
ዡልዬት ደኅናነች ወይ አባቴስ እንዴት ነው ?
እሷ ፡ ደኅና፡ ብትሆን ፡ግድ የለም የቀረው
ዡልዬት ፡እንደ ፡ምን ነች ? አሁንም አድሼ
ልጠይቅህ ፡ በጣም ሺሕ ፡ ጊዜ ፡ መልሼ

#ቤልሻጥር
ደኅና ፡ ነች ፡ ልበልህ ፡ አልነካትም ፡ ዐፈር
እንደሌላው ፡ ፍጥረት ፡ መሬት ፡ ሳትቀበር
ከመቃብሩ ፡ ቤት፡ ሠርተው ፡ አባቷ
ካዘጋጁት ፡ ገብታ ፡ እግሮቿም ፡ እጆቿ ፡
ታስረው ፡ ሳትገነዝ ፡ በማዕርግ ፡ ተንጋላ ፡
ተኝታ ፡ ኣየናት ፡ ያንቀላፋች ፡ መስላ ።
እንዲህ ፡ በጌትነት ፡ ዡልዬት ፡ ተቀበረች ፤
በቃ ፡ የሷ፡ ነገር ፡ እንደ ፡ ዘበት ፡ ቀረች ።
ነፍሷ ፡ ግን ወደ እግዜር ዐረገች ወደ ላይ
ዐርፋ ፡ ከዚህ ዓለም ወጣች ፡ ወደ ሰማይ

#ሮሜዎ ። (በድንጋጤ ፊቱ ተለወጠ)
ምን ፡ አገኛትና ? በምን ፡ የተነሣ ?

#ቤልሻጥር
ጧት፡ ባልጋዋ ፡ ላይ ፡ በድን ሆና ሬሳ፡
ተገኘች ፡ ከእንቅልፍ፡ ሳትነቃ ፡ ሞታ ፤

#ሮሜዎ
እንደዚህ ፡ ከሆነ 'የዡልዬት ፡ ሁኔታ ፡
ደግ ፡ ነው መልካም ፡ ነው ፤ ብዕር፡ቀለም፡ኣምጣ፡
ፈረሶች ፡ ተከራይ ፈጥነህ መንደር ፡ውጣ
ማንም ሰው ሳያየኝ ማንም ሰው ሳይሰማ
መሄዴ' ነውና ፡ ሌሊት ፡ በጨለማ ።

#ቤልሻጥር
እባክህ ፡ ጌታዬ ፡ ፊትህ ፡ ተለወጠ ፤
ደምህም ፡ ጠቈረ ፡ ልቤ ፡ ደነገጠ '
ቻለው ፡ ሐዘንህን ፡ ከትዕግሥት ፡ ጋራ

#ሮሜዎ
አትሥጋ ፡ ግድ የለም ፡ ቤልሻጥር አትፍራ
የማይሆን አይሆንም የሚሆን ፡ ይሆናል !

ይልቅ ፡ቶሎ ፡ ፍጠን ፡ ጊዜው ፡ ያልፍብናል
(ቤልሻጥር ሄደ፤ ሮሜዎ'ብቻውን) »
እንገናኛለን ፡ ዥልዬት ፡ ዛሬ ፡ ማታ ፤
ወዳንቺ ፡ ለመድረስ ፡ ቶሎ ፡ በደስታ ፡
መንገዱን ፡ መፈለግ ፡ አለብኝ ፡ ግዴታ ፡
መድኀኒት ፡ የሚሸጥ ፡ አንድ ፡ ጎረቤቴ ፡
መኖሩን ፡ ዐውቃለሁ ፥ እኔ ፡ በሕይወቴ ፡
አይቼ ፡ አላውቅም ፡ ችግረኛ ፡ እንደ ፡ እሱ
ሁል ፡ ጊዜ ፡ ያደፈ፡ ቀዳዳ ፡ ነው ፡ ልብሱ ፡
የተጐዳ ፡ ሰው ፡ ነው ፡ ድህነት ፡ ያጠቃው
ሰውነቱ ፡ ከስቷል ፡ የመደብር ፡ ዕቃው ፡
አሮጌ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ቈሻሻ ፡ ሰባራ ፤
ተጠርጎ ፡ የማያውቅ ፡ የለበሰ ፡ ዐቧራ ።
ከሱቁ ፡ ስገባ ኔም አስተውዬ
እሱን ፡ባየሁ ቍጥር አሰብኩ እንዲህ ብዬ
በማንቱ ፡ ከተማ ፡ ለሰው ፡ መርዝ ፡ የሸጠ
በምንም ፡ አኳኋን ፡ አውጥቶ ፡ የሰጠ ፡
ምንም ፡ እንኳ፡ የሚያዝ ፡ በሞት ፡ እንዲቀጣ ፡
ኀይለኛ ፡ ዐዋጅ ፡ ቢኖር ፡ ተጽፎ ፡ የወጣ ፡
መርዝ ፡ የሚፈልግ ፡ ሰው ፡ ብዙ ፡ ገንዘብ ፡ ሰጥቶ ፡
ይህን ችግረኛ፡ ቢጠይቀው ፡ መጥቶ ፡
አይጠረጠርም : እንቢ ፡ እንደማይለው ፤
ስለዚህ ፡ ጠርቼ ፡ እስቲ ፡ ልሞክረው ፡
አንተ ፡ መድኀኒት ፡ ሽያጭ፡ እባክህ ፡ ወዲህ ፡ ና ።

#መድኀኒት_ሽያጭ
ምነው ፡ ሮሜዎ አይዶለም ወይ ፡ ደኅና ?

#ሮሜዎ
ሰው ፡ አንተን ይሻሃል ባጣ ፡ ጊዜ ፡ ጤና፡
አንድ ፡ ነገር ፡ አሁን ፡ ልንገርህ ፡አድምጠኝ
ቶሎ ፡ የሚገድል ፡ ብርቱ ፡ መርዝ ፡ ስጠኝ፡
አርባ ፡ ዱካ ፡ ልስጥህ ለመርዝህም ዋጋ
አንተም ፡ ትሆናለህ ፡ በዚህ ፡ ባለጸጋ ፡
አንተን ፡ ለመሰለ ፡ በጣም ፡ ለተጐዳ ፡
ይህ ፡ ብዙ ፡ ገንዘብ ነው በጣም የሚረዳ

#መድኅኒት ፡ ሽያጭ ።
ኀይለኛ ፡ መርዝ አለኝ በመደብሬ ውስጥ
ግን ፡ ባዋጅ ፡ ክልክል ነው፡ለማንም፡ እንዳልሸጥ ።

#ሮሜዎ
ሞኝ ፡ ነህ ፡ መሰለኝ ፡ ዐዋጅ ፡ብሎ ፡ ጣጣ
ራብ ፡ ለገደለህ ፡ ዐጥንትህ ' ለወጣ'
ላንተ ፡ ምን ' ጠቀመህ ይልቅ ስጠኝ' ቶሎ
ድኽነት ፡ ይታያል ፡ በመልክህ ፡ ተሥሎ'
ጒዳት ፡ አቈራምዶ፡ ችግር ፡ ያሸነፈህ

💫ይቀጥላል💫
👍1