አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_ዘጠኝ


#አባ_ሎራ
ለምን ፡ ታስባለህ ፡ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ነገር ፤
ብላሽ ፡ ሰው ፡ አትሁን ፡ ሲመክሩህ ፡ ተመከር ,እንደ ፡ ሴት ፡ አታልቅስ ፡ እንዳውሬ ፡ አትቈጣ
እንደ፡እብድ፡አትበሳጭ ፥ ከሰው፡ ግብር፡ አትውጣ
ትመስለኝ ፡ ነበረ ፡ በውነቱ ፡ ጠንካራ ፤
ሰው ፡ ለምን ፡ ይረባል ፡ ካልቻለ ፡ መከራ
መቀጣት ፡ ከወደድህ ፡ በገዛ ፡ እጅህ ፡ ሞተህ ፡
ስለምን ፡ ገደልከው ፡ ቲባልትን ፡ ተዋግተህ ?
በገዛ ፡ እጅህ ፡ ብትሞት ፡ ባለማመዛዘን ፡
መግደልህ ፡ እኮ ፡ ነው ሚስትህን ፡ በሐዘን '
ለዚህ ፡ ነው ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ ኅሊናና ፡ አእምሮ ፡
ከእግዜር ፡ የተሰጠ ፡ ለሰው ፡ ልጅ ፡ ተፈጥሮ'
ዡልዬት ፡ ጠልታኛለች ፡ ብለህ ፡ ስትሠጋ፡
ሰው ፡ ልካ ፡ ጠራችህ ምሕረትን ፡ አድርጋ
ቲባልት ፡ ሊገድልህ ፡ ቢመጣ ፡ ደንፍቶ ፡
በገዛ ፡ ጥጋቡ ፡ ወደቀ ፡ ተወግቶ "
ባንተም የሞት ቅጣት ሊወድቅ የነበረው
በስደት ፡ ለውጦ ፡ መስፍናችን ፡ ሻረው '
ብትመለከተው : በውነቱ ፡ የት ፡ አለ ፤
እንዳንተ ፡ የቀናው ፡ በጣም ፡ የታደለ ፡
ተጠንቀቅ ፡ በውነቱ ፡ ልጄ ፡ በጣም ፡ ሥጋ
ሳታውቀው ፡ ብትቀር ፡ የደስታን ፡ ዋጋ ፡
ኑሮህ ፡ይበላሻል ፡ አለመጠን ፡ ፍራ ፡
ምን ፡ጊዜም ፡ አይለቅህ ፡ ጭንቅና ፡ መከራ ።
ሚስትህን ምከራት ፡ እንዳትሞት ፡ አልቅሳ
መምሸቱ፡ነውና፡ በል ቶሎ ፡ ተነሣ፡
ነገ ፡ ግን ፡ ለመሄድ ፡ ልብህ ፡ይሰናዳ ፤
ውጣ ፡ ከቬሮና ፡ ሌሊት ፡ በማለዳ
ተዛውረህ ተቀመጥ ፡ ሄደህ ፡ ወደ ፡ ማንቱ
እኛ ፡ ጊዜ ፡ አግኝተን ፡ ሲመቸን ፡ ሰዓቱ ፡
ወገኖቻችሁን ፡ በምክር ፡ አስታርቀን ፡
ጋብቻችሁንም ፡ በገሃድ ፡ ኣስታውቀን ፡ .
ላንተም ፡ ከመስፍኑ ፡ ምሕረትን ፡ ጠይቀን
እንጣጣራለን ፡ ቶሎ ፡ እንድትመለስ
እግዜር ፡ይጠብቅህ በል እስከዚያ ፡ ድረስ
አሁን ፡ ወደ ፡ ዡልዬት ፡ በቶሎ ሂድ ፡ ተነሥ

የካፑሌ ሚስት #ካፑሌ #ፓሪስ

#ፓሪስ
ጉዳዩ ዘገየ ፡ በመዋል' በማደር ፤
ታዲያስ እንዴት ፡ ሆነ ፡የጋብቻው ፡ ነገር ?

#ካፑሌ
ነገሩን ፡ ለዡልዬት ፡ ሳልነግር ፡ መቅረቴ ፡
ወድጄን ፡ አይደለም ፡ እንዲህ ፡ መዘግየቴ
በቲባልት ፡ መሞት ፡ አዝናለች ፡ በብርቱ ፤
ታፈቅረው ፡ ነበረ ፡ ከልቧ ፡ በውነቱ ፡
ስለዚህ ፡ ሐዘኑ ፡ ጥቂት ፡ ሳይረሳ ፡
አልቻልኩም ፡ ጕዳዩን ፡ ለጊዜው ፡ ላነሣ ፡
አድርግልኝና ፡ ከልብህ ፡ ይቅርታ ፤
እኔ ፡ እጨርሳለሁ ፡ ነገሩን ፡ አንድ ፡ አፍታ

#ፓሪስ
እውነት ፡ ነው ሐዘኑ ፈጽሞ ፡ አልተመቸም
ተስማምተንበታል ይህን ጕዳይ ፡ መቼም
እሷም እንቢ እንዳትል ፡ እናንተ ፡ አስቡበት

#የካፑሌሚስት _ ።
ግድ የለም ሠርጋችሁ ይሆናል በፍጥነት

#ካፑሌ
ፓሪስ ሆይ አትሥጋ አይዞህ ይህን ጕዳይ
መሄድ ፡ ትችላለህ ፡ ጥለኸው ፡ በኔ ፡ ላይ
እንዴት ፡ ትወጣለች ፡ ከኔ ፡ ፈቃድ ፡ ልጄ ፤
ያቀረብኩላትን ፡ መርጬ ፡ ወድጄ
ያላንድ ፡ ቅሬታ ፡ አለባት ፡ መቀበል ፤
እንዲያውም ፡ እንፍጠን ፡ ዛሬ ነገ ፡ አንበል
በይ ፡ ፍጠኝ ፡ ሚስቴ ፡ ወደ ፡ ልጅሽ ፡ ሂጂ
በዘዴ ፡ በርጋታ፡ነገሩን አስረጂ ፡
መልካሙ ፡ ልጃችን 'ፓሪስ ፡ አንቺን ፡ ወዶ ፡
እኔም ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ አባትሽም ፡ ፈቅዶ ፡
ይኸው ፡ በዚህ መሰሞን ሊያገባሽ ፡ ነውና
ተዘጋጂ፡ በያት ፡ በሙሉ ፡ ልቡና '
በል ፡ አንተም ፡ ንገረኝ ፡ እንደምትፈልገው
ሰርጉ ፡ እንዲፈጸም ለመቼ እናድርገው ?

#ፓሪስ
እንደ ፡ እኔ ፡ ሰርጋችን ፡ የራቀ ፡ ከሚሆን ፡
ቢፈጸም ፡ ይሻላል ፡ አሁን ፡ በዚህ ፡ ሰሞን

#ካፑሌ
እንግዲያው መልካም ነው ባጭር እንደግስ
ተክሊሉም ፡ ይፈጸም ፡ በሚመጣው ፡ ኀሙስ ፡
ጃጃታ ፡ አላበዛም ብዙም ፡ ሰው ፡ አልጠራ ፤
ልጄን ፡ እድራለሁ ፡ ብዬም ፡ አላወራ ፡
ሐዘን ፡ ስለ ፡ ሆነ ፡ቲባልት፡ በመሞቱ ፡
ቅር ፡ ያሰኛልና ፤ ዘመድ ፡ በጥቂቱ ፡
በድብቅ ፡ እንጥራ ፡ ነገር ሳናበዛ ፤
እንደዚህ 'ብናደርግ ፡ ወሬው ፡ ሳይነዛ ፡
ጉዳያችን'ያልቃል፡ያግር፡ ሰው ፡ ሳይሰማ ፤
እንግዲህ ፡ መልካም ፡ ነው ፤ በዚሁ 'እንስማማ ።

#ፓሪስ
እኔም ፡ እስማማለሁ ፡ ይሁን ፡ በዚሁ ፡ ቀን
በሉ ፡ እስከዚያው፡ድረስ፡እግዜር፡ይጠብቀን ። (ሄዳ).

#ካፑሌ ፡ (ለሚስቱ )
እንደዚህ ፡ ያለ ፡ ባል ፡ ትልቅ ፡ ሰው ፡ የበቃ
ቢሄዱ ፡ አይገኝም ፡ እግር ፡ እስቲነቃ ፡
በይ ፡ ቶሎ ፡ ፍጠኚ ፡ ወደ ፡ ልጅሽ ፡ ሂጂ ፤
ነገ ፡ ጧት ፡ አሳቧን ፡ ልቧን ፡ አዘጋጂ ።

#ሮሜዎና #ዡልዬት ፡ (በዥልዬት ' መኝታ ፡ ቤት) ።

#ዡልዬት
አይዞህ፡አትቸኵል ፡ አልነጋም ፡ ሌሊቱ ፤
ቁጭ ፡ በል ፡እናውጋ ፡ ገና ፡ ነው ፡ ሰዓቱ ፡
ተመልከት ጨለማ መሬቱን
ሲሸፍን ፡
የሰማናትም ፡ ወፍ ፡ አሁን ፡ ስትዘፍን ፡
ዞትር ፡ ልማዴ ፡ ነው ፡ ሌሊቱ ፡ ሳይነጋ ፡
መጮህ ፡ ትወዳለች ፡ እመነኝ ፡ አትሥጋ

#ሮሜዎ
ይህች ፡ የንጋት ፡ ወፍ ፡ ነች ፡ አሁን ፡ የጮኸችው ፤
ትክክል ፡ ይታያል ፡ ዡልዬት ፡ ተመልከችው
ሰማይ ወገግ፡ አለ ፡ ያው በምሥራቅ በኩል ፤
ሰዓቱ ፡ ደረሰ ፡ እንግዴህ ፡ ልቸኵል ፡
በቬሮና ፡ አድሬ ፡ ቢያገኙኝ ፡ ሳልወጣ ፡
መስፍኑ ፡ ፈርደዋል ፡ በሞት ፡ እንድቀጣ ፡
ልዳን ፡ ያልኩ ፡ እንደሆን ፡ ሕይወቴን ፡ ወድጄ ፡
መሄድ ፡ ይገባኛል ፡ አሁን ፡ ተሰድጄ ።

#ዡልዬት
እኔ ፡ መች ፡ አጣሁት ፡ ይህ ፡ ያሁኑ ፡ ብርሃን ፡
የሰማይ ፡ ፋና ፡ ነው ፡ የኮከብ ፡ ውጋጋን
ሌሊት ፡ በጨለማ ፡ ሳይነጋ ፡ ሌሊቱ ፡
ለምን ፡ ትሄዳለህ ፡ አሁን ፡ ወደ ፡ ማንቱ ፡
አይዞህ ፡ እንጫወት ሌቱ ፡ አልነጋም ፡ ገና
ጊዜ ፡ አለን ፡ እስኪታይ ፡ የንጋቱ ፡ ፋና ።

#ሮሜዎ
ዘፈኑ ፡ ሲወጣ ፡ አልሰማንም ፡ ካፍ
አልነጋም ፡ ሌሊቱ ፡ አልጮኸችም ፡ ወፍ፡
ይህም ፡ በሰማይ ላይ የሚታይ ፡ ውጋጋን አይደለም ፡ የመጣ ፡ ከፀሓይዋ ፡ ብርሃን ፡
ብለን ፡ እንካደው ፤ አምኜ፡ ልቀበል !
ሳልወጣ ፡ ይያዙኝ ፡ ተይዤም ፡ ልገደል "
ካንቺ ፡ ተለይቼ ፡ የሐዘን ፡ ኵነኔ ፡
ከሚያገኘኝ፡ መሞት ፡ እመርጣለሁ ፡ እኔ ።
አልፈራም ፡ ፈጽሞ ፡ በሞት ልቀጣ
ዡልዬት ፡ ከፈቀደች ፡ የፈለገው ፡ ይምጣ ፡
ወፎች አልተንጫጩም ሌሊቱም ፡ አልነጋ
ዡልዬት ጨዋታ አምጪ እንግዴህ እናውጋ፡

#ዡልዬት
እኔ ፡ ብዬ ፡ ነበር ፡ ገና ፡ ነው ፡ ሌሊቱ፤
አሁን ፡ ገና ፡ታየኝ ፡ ትክክል ፡ መንጋቱ ፡
ንጋት ፡ ነው ፡ የመጣው ፡ ሂድ ፡ ቶሎ ፡ ተነሣ፤
አምልጠህ ፡ ሽሽ ፡ ቶሎ ፡ ብረር ፡ በግሥገሣ ፡
እየው ፡ ተመልከተው ፡ የንጋት ፡ ወገግታ፤
ጨለማውን ቀዶ፡ ሄደ ፡ እየበረታ ፡
አስተውለው ፡ መሬቱ ፡ ሲታየን ፡ ተገልጦ ፤
አሞኘችኝ፡ ወፏ ድምፅዋ ፡ ተለውጦ ፡
ፍጠን ፡ ቶሎ ውጣ እየው፡እንደ፡ ነጋ ፤
ተነሥ ፡ ቶሎ ፡ ጥፋ፤ አይንካህ ፡ አደጋ ።

#ሞግዚት
እናትሽ ፡ ነቅተዋል' እመቤቴ ፡ ዕወቂ፤
መንጋቱ ፡ ነውና ' በጣም' ተጠንቀቂ "
ደኅና ሰንብት ፡ ልበል ፡ እኔው ፡ አስቀድሜ
እንግዴህ ፡ ደኅና'ሁን'ሮሜዎ ፡ ወንድሜ ።

#ሮሜዎ
ዡልዬት ደኅና ሁኝ ፡ ደኅና ሰንብች ፡ ፍቅሬ

#ዡልዬት
አደራ ፡ እንዳገኘው ፡ እኔ ፡ ያንተን ፡ ወሬ ፡
ሁል ፡ ጊዜ ጻፍልኝ ፡ መሆንህን ፡ ጤና ፤
መቼ ፡ እንደማገኝህ ፡ አላውቀውምና ።

#ሮሜዎ
መቼም ፡ ቢሆን ፡ ካንቺ ፡ አይለይም ፡ ልቤ
እጽፍልሻለሁ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡