#ሮሜዎና_ዡልዬት
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
የካፑሌ ፡ ሚስት (የዡልዬት እናት)
ወዴት ፡ ነው ፡ ያለሽው ፡ ልጄ ፡ ተነሣሽ ፡ ወይ ?
#ዡልዬት።
ይኸው ፡ ተነሣሁኝ ፡ ምነው ፡ እናቴ ሆይ ?
(ለብቻዋ ፡ ቀስ ብላ)
ምን ፡ ነካት ፡ እናቴ ፡ እንዲህ ፡ ጧት ፡ ተነሥታ ፈልጋኝ አታውቅም በማለዳ መጥታ ።
(የካፑሌ ሚስት ' ወደልጅዋ፡ወደ፡ዡልዬት መኝታ' ቤት፡ገባች
#የካፑሌ_ሚስት ።
ዐፈር ፡ አስመሰለሽ ፡ የቲባልት ፡ ሐዘን ፡
ያስፈልጋል ፡ ልጄ ፡ ማሰብ ፡ ማመዛዘን '
እንባ ፡ ቢያፈሱለት ፡ ቢያለቅሱለት በጣም
ሰው ፡ አንዴ ከሞተ ተመልሶ ፡ አይመጣም
ሐዘን ፡ የሚያስረሳ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ወሬ
ይዤ ፡ ወዳንቺ ፡ ዘንድ ፡ መጥቻለሁ' ዛሬ "
#ዡልዬት ።
እናቴ ፡ ንገሪኝ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ያለ ፡ ነው ?
#የካፑሌ_ሚስት ።
በቲባልት ፡ መሞት ፡ በብዙ ፡ ያዘነው ፡
ልብሽ ፡ እንዲጽናና ፡ በጣም ፡ በማሰቡ ፡
መልካሙ ፡ አባትሽ ፡ አላረፈም ፡ ልቡ ፤
በዚሁ ፡ ምክንያት ፡ ሳይውልም ፡ ሳያድር ፡
ቈርጧል ለጥሩ ባል ኀሙስ አንቺን ሊድር
ባልሽ ፡ የሚሆነው ቆንዦ ነው ፡ ጌታ ሰው
በዘርም ፡ በገንዘብ ፡ ምንም ፡የማያንሰው !
እንዲያውም ፡ ገልጨ ፡ ልንገርሽ ፡ ካሁኑ ፤
መልካሙ ፡ፓሪስ ፡ ነው ፡ ወጣት ፡ መኰንኑ
#ዡልዬት ።
እናቴ ፡ ሆይ ፡ምነው ፡ በፊት ፡ ሳንማከር ፡
እንደ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ እንዲህ ያለ ፡ ነገር
አስቀድመን ፡ እኛ ፡ ተጫጭተን ፡ በደንቡ፡
ሳላውቀው ሳያውቀኝ ፡በፍጥነት ፡ ተጋቡ !
እንዴት ፡ ትላላችሁ ፡ እንዲህ ፡ በችኰላ ?
አሁንም ፡ በቶሎ ፡ ፈልጉለት ፡ መላ'
እኔ ፡ አልችልምና ፡ ለማግባት ፡ በቶሎ ፤
አባቴን 'ንገሪው ፡ እንደ ፡ ምንም ፡ ብሎ
ቃል ቢኖር ምናልባት ለፓሪስ የሰጠው
አንድ' ዘዴ ፡ ፈጥሮ ፡ ቶሎ ፡እንዲለውጠው
#የካፑሌ_ሚስት ።
አፍሽን ፡ አታጥፊ ፡ ምክንያት ፡ አታምጪ '
ያለቀ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ ዐርፈሽ ፡ ተቀመጪ ።
#ዡልዬት ።
አድምጪኝ ፡ እናቴ ፡ እንግዲያውስ ፡ ስሚ
አባቴም ፡ አይልፋ ፡ አንቺም ፡ ኣትድከሚ'
የመጣ ፡ ቢመጣ ፡ መቼም ፡ቢሆን ደግሞ
እኔ ፡ አላገባም ፡ ፓሪስን ፡ ፈጽሞ ።
#የካፑሌ_ሚስት ።
አልገባም ፡ ጨርሼ ፡ እኔ ፡ በዚህ ፡ ጣጣ ፤
ንገሪው ፡ ላባትሽ ፡ ይኸው ፡ወዲህ ፡ መጣ
#ካፑሌ ፡ (ገባ)
ምነው ፡ ምን ሆናችሁ ? በይ ልመለስ ሄጄ
ታዲያስ ፡ ነገርሻት ፡ ወይ ነገሩን ፡ ለልጄ ?
#የካፑሌ_ሚስት ።
እኔ ፡ ከሷ'ጋራ ፡ አልችልም ፡ ክርክር ፤
ትችል ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡አስረዳት ፡ በምክር ።
#ካፑሌ ።
እስቲ ፡ እኮ ፡ ንገሪኝ ፡ ምንድነው ፡ ነገሩ ፡
አሁን ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ደርሶ ፡ ግርግሩ ።
#የካፑሌ_ሚስት
ትችል ፡ ትመስላለህ አንተ ፡ ደግሞ ፡ ደርሶ
የምሥራች ፡ « እንቢ» ፡ ብላለች ፡ ጨርሶ ፡
የመጣ ፡ ቢመጣ ፡ ይልቁንም ፡ ደግሞ ፡
አላገባም ፡ አለች ፡ ፓሪስን ፡ ፈጽሞ ።
#ካፑሌ ።
እግራችንን ፡ ስማ ፡ እኛን ፡ አመስግና ፡
በትልቅ ፡ ደስታ ፡ መቀበል 'ቀረና ፡
እንቢ ፡ አለች ፡ ብትይኝ ጆሮዬም ፡ አይሰማ
እስቲ ፡ ልስማው ፡ እኔ ፡ ትናገረው ፡ ደግማ
#ዡልዬት ።
ለክፋት ፡ አይደለም ፡ አትቈጣ ፡ አባቴ ።
#ካፑሌ ።
እረግ ፡ የኛ ፡ ሕፃን ፡ ትንሿ ፡ ማሚቴ ፡
የማነሽ ፡ ለዛ ፡ ቢስ ፡ የማነሽ ፡ ወልጋዳ ፤
የማነሽ ፡ አመዳም ፡ የማነሽ ፡ ገዳዳ'
ባለወግ ፡ አድርገን እኛ ፡ ነን ያጠፋን ፡
ብታውቂው ፡ ባታውቂው ኧረ ምን ፡ አለፋን
በግድ፡ ነው ፡ እንጂ፡ በኅይል ፡ የምንድር ፡
መች ፡ ያስፈልግና ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ንግግር
ነገ ፡ በማለዳ ፡ ተዘጋጅተሽ ፡ ውጪ ፣
ከተክሊሉ ፡ ቦታ ፡ ዐውቀሽ ' እንድትመጪ,
ታዛዤ ፡ ነሽና ፡ የወለድኩሽ ፡ ልጄ ፣
እኔ ፡ እድርሻለሁ ፡ በኀይል' አስገድጄ ፤
ለወግ ፡ መጠየቄ ፡ ቅብጠት ፡ነው ፡ አብጄ
እስከዚያ ፡ ድረስ ፡ ግን ፡ በፊቴ ፡ አትለፊ ፤
ዐይንሽን ፡ አልየው ፡ ካጠገቤ ፡ ጥፊ ።
#ዡልዬት ።
ነገሩን ፡ ላስረዳህ ፡ አባቴ ፡ አድምጠኝ ፤
ጋብቻው ፡ ፈጠነ ፡ ጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ስጠኝ
#ካፑሌ ።
ነገርሽ እሬት ነው ፡ መሪር ነው ፡ ኮምጣጣ
ካፍሽ ፡ ካንደበትሽ ፡ አንድ ፡ቃል፡ አይውጣ'
ሴት ልጅ እንቢ፡ብትል፡አለው አንድ አገባብ
መች ተሠርቶ ያውቃል እንዲህ፡ያለ ጥጋብ
ዘሩ ፡ የታወቀ ነዉ መልኩ ፡ የሚያኰራ ፡
ገንዘብ ፡ የተረፈው ፡ ስሙ ፡ የተጠራ፡
ደኅና ፡ ባል ፡ ፈልጎ ፡ በስንት ፡ መከራ፡
አባቷ ፡ ሲያመጣ ፡ ወዲያ ፡ ወዲህ ፡ ዞሮ '
ከቤት ፡ ተወዝፋ ፡ የኛ ፡ ሴት ፡ ወይዘሮ ፡
እኔ ፡ ባል ፡ አልሻም ፡ ትላለች ፡ ሞጋጌ ፤
መካን ፡ ሰው ፡ ይሻላል ከመውለድ ፡ ባለጌ
ጥኀጋብሽ ፡ ነው ፡ እኮ ደሜን ፡ የሚያፈላው ፤
ምኑ ፡ ነው ፡ እባክሽ ፡ፓሪስ ፡ የሚጠላው ?
ያለባል ፡ ለመኖር ፡ ከሆንሽ ፡
የምትወጂ ፡
ምን ፡ ቸገረኝ፡ እኔ ፡ ወደ ፡ ገዳም ፡ሂጂ ፡
ነገር ፡ ግን ፡ ከሆነ ፡ ማግባትሽ ፡ የማይቀር ፡
የመረጥኩልሽን ፡ ይገባሻል ፡ ማፍቀር ፡
ያላንድ ፡ ክርክር ፡ ያላንድ ፡ ቅሬታ ፡
ፈቃዴን ፡ መቀበል ፡ አለብሽ ፡ ግዴታ ።
የምትይ ፡ ከሆነ ፡ የኔን ፡ ፈቃድ ፡ እንቢ ፡
ከዛሬ ፡ ጀምረሽ ፡ ሂጂ ፡ ገደል ፡ ግቢ ፤
ዐይንሽን ፡ አልየው ፡ በዚህ ፡ በኔ ፡ ግቢ ።
የካፑሌ ፡ ሚስት ።
ቀስ ፡ ብሎ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ አባት ፡ ከመከረ ፡
አንተም ፡ አበዛኸው ፡ ነገርህ ፡ ከረረ ።
ካፑሌ ።
አትግቢ ፡ ፈጽሞ ፡ አንቺ ፡ በኔ ፡ ሥራ ፤
ሂጂ ፡ ወደ ፡ ጓዳ ፡ ከሴቶቹ ፡ ጋራ ፡
ቀኑን ፡ ሙሉ ፡ ባሳብ ፡ ሌሊቱን ፡ በሕልሜ ፡
ባል ፡ ስፈልግላት ፡ በመኖር ፡ ደክሜ ፡
በስንት 'ዐይነት ፡ ዘዴ ፡ እኔ ፡ ተጣጥሬ፡ .
እግዚአብሔር ረድቶኝ ፡ ይኸውና ፡ ዛሬ ፡
የሚሆን ፡ ሰው ፡ ባገኝ ፡ ጨዋ ፡ባለገንዘብ፡
እሜቴ ፡ ፈጠሩ ፡ ሠላሳ ፡ ሺሕ፡ ሰበብ ።
ስሚኝ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ልንገርሽ ፡ ካሁኑ፤
እሱን ፡ ካላገባሽ ፡ ታዘቢኝ ፡ በውኑ
የትም ፡ ትሄጃለሽ ፡ አብርሬሽ፡ ከቤቴ፤
እርሜን ፡ አወጣለሁ ፡ ቆርጬሽ ፡ ካንጀቴ
ልጅና ፡ አባት ፡ ሆነን ፡ መኖራችን ፡ ቀርቶ ፡
ክጄሽ ፡ ትሄጃለሽ ፡ አልምርሽም ፡ ከቶ ፡
ስለዚህ ፡ አስቢ፡ ከልብሽ ፡ ምከሪ፤
የሚከተለውን ፡ ተመልክተሽ ፡ ፍሪ'
ካሁኑ ፡ ጀምረሽ ፡ በነገሩ፡ ሥጊ፤
ቃሌ ፡ አይታጠፍም ፡ ኋላ ፡ ልብ ፡ አድርጊ
(ካፑሌ "ከቤት " ወጥቶ ሄደ)
#ዡልዬት ።
እባክሽ ፡ እናቴ ፡ ለልጅሽ ፡ እዘኚ፤
ባይሆን ፡እንኳን ፡ አንቺ ፡ ከኔ ፡ ወገን ፡ ሁኚ'
ቀኑ ፡ ረዘም ፡ ይበል ጥቂት ፡ ጊዜ ስጡኝ፤
አሳቤን ፡ ሳታውቁ ፡ በከንቱ ፡ አትቁጡኝ ።
ግዴታ፡ ካልሆነ' በጣም ' ካልቸረኝ፡
እንቢ ፡ አልልምና ፡ ምክንያት ፡ ካልኖረኝ ።
#የካፑሌ_ሚስት ።
ዕዳሽን ፡ በጨርቅሽ ፡ እንደምትፈልጊ '
አንቺ ፡ እንደ ፡ ፈቃድሽ 'እንዳሻሽ አድርጊ ።
(እናቷም' ወጥታ ሄደች)
#ዡልዬት ።
ርጂኝ ፡ አንቺ ፡ እባክሽ ፡ ምከሪኝ ፡
#ሞግዚቴ ፤
ምስጢር፡ ተካፋዬ፡አንቺ፡ነሽ ፡እናቴ '
የኛን ተክሊል ማንም አይችልም፡ሊያፈርሰው፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ድብቅ ፡ ነው አያውቅም፡ማንም፡ሰው፡
እባክሽ ፡ ምከሪኝ ፡ ዘዴ ፡ አታጭምና ፤
ጨነቀኝ ፡ ጠበበኝ'አገኘኝ ፡ ፈተና ።
#ሞግዚት ።
ቃሌን ፡ ብትሰሚ ፡ ተራዬን ፡ ልናገር ፤
ሮሜዎ ፡ ሰው ፡ ገድሎ ፡ ተሰደደ ፡ ካገር፡
ልትኖሩ ፡ ከሆነ ፡ ለብቻ ፡ ለብቻ ፡
በዚሁ ፡ ይፈርሳል ፡ የናንተ ፡ ጋብቻ ፡
በዚሁ ፡ ላይ ፡ ደግሞ ፡ አባትሽ ፡ ላባቱ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
የካፑሌ ፡ ሚስት (የዡልዬት እናት)
ወዴት ፡ ነው ፡ ያለሽው ፡ ልጄ ፡ ተነሣሽ ፡ ወይ ?
#ዡልዬት።
ይኸው ፡ ተነሣሁኝ ፡ ምነው ፡ እናቴ ሆይ ?
(ለብቻዋ ፡ ቀስ ብላ)
ምን ፡ ነካት ፡ እናቴ ፡ እንዲህ ፡ ጧት ፡ ተነሥታ ፈልጋኝ አታውቅም በማለዳ መጥታ ።
(የካፑሌ ሚስት ' ወደልጅዋ፡ወደ፡ዡልዬት መኝታ' ቤት፡ገባች
#የካፑሌ_ሚስት ።
ዐፈር ፡ አስመሰለሽ ፡ የቲባልት ፡ ሐዘን ፡
ያስፈልጋል ፡ ልጄ ፡ ማሰብ ፡ ማመዛዘን '
እንባ ፡ ቢያፈሱለት ፡ ቢያለቅሱለት በጣም
ሰው ፡ አንዴ ከሞተ ተመልሶ ፡ አይመጣም
ሐዘን ፡ የሚያስረሳ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ወሬ
ይዤ ፡ ወዳንቺ ፡ ዘንድ ፡ መጥቻለሁ' ዛሬ "
#ዡልዬት ።
እናቴ ፡ ንገሪኝ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ያለ ፡ ነው ?
#የካፑሌ_ሚስት ።
በቲባልት ፡ መሞት ፡ በብዙ ፡ ያዘነው ፡
ልብሽ ፡ እንዲጽናና ፡ በጣም ፡ በማሰቡ ፡
መልካሙ ፡ አባትሽ ፡ አላረፈም ፡ ልቡ ፤
በዚሁ ፡ ምክንያት ፡ ሳይውልም ፡ ሳያድር ፡
ቈርጧል ለጥሩ ባል ኀሙስ አንቺን ሊድር
ባልሽ ፡ የሚሆነው ቆንዦ ነው ፡ ጌታ ሰው
በዘርም ፡ በገንዘብ ፡ ምንም ፡የማያንሰው !
እንዲያውም ፡ ገልጨ ፡ ልንገርሽ ፡ ካሁኑ ፤
መልካሙ ፡ፓሪስ ፡ ነው ፡ ወጣት ፡ መኰንኑ
#ዡልዬት ።
እናቴ ፡ ሆይ ፡ምነው ፡ በፊት ፡ ሳንማከር ፡
እንደ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ እንዲህ ያለ ፡ ነገር
አስቀድመን ፡ እኛ ፡ ተጫጭተን ፡ በደንቡ፡
ሳላውቀው ሳያውቀኝ ፡በፍጥነት ፡ ተጋቡ !
እንዴት ፡ ትላላችሁ ፡ እንዲህ ፡ በችኰላ ?
አሁንም ፡ በቶሎ ፡ ፈልጉለት ፡ መላ'
እኔ ፡ አልችልምና ፡ ለማግባት ፡ በቶሎ ፤
አባቴን 'ንገሪው ፡ እንደ ፡ ምንም ፡ ብሎ
ቃል ቢኖር ምናልባት ለፓሪስ የሰጠው
አንድ' ዘዴ ፡ ፈጥሮ ፡ ቶሎ ፡እንዲለውጠው
#የካፑሌ_ሚስት ።
አፍሽን ፡ አታጥፊ ፡ ምክንያት ፡ አታምጪ '
ያለቀ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ ዐርፈሽ ፡ ተቀመጪ ።
#ዡልዬት ።
አድምጪኝ ፡ እናቴ ፡ እንግዲያውስ ፡ ስሚ
አባቴም ፡ አይልፋ ፡ አንቺም ፡ ኣትድከሚ'
የመጣ ፡ ቢመጣ ፡ መቼም ፡ቢሆን ደግሞ
እኔ ፡ አላገባም ፡ ፓሪስን ፡ ፈጽሞ ።
#የካፑሌ_ሚስት ።
አልገባም ፡ ጨርሼ ፡ እኔ ፡ በዚህ ፡ ጣጣ ፤
ንገሪው ፡ ላባትሽ ፡ ይኸው ፡ወዲህ ፡ መጣ
#ካፑሌ ፡ (ገባ)
ምነው ፡ ምን ሆናችሁ ? በይ ልመለስ ሄጄ
ታዲያስ ፡ ነገርሻት ፡ ወይ ነገሩን ፡ ለልጄ ?
#የካፑሌ_ሚስት ።
እኔ ፡ ከሷ'ጋራ ፡ አልችልም ፡ ክርክር ፤
ትችል ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡አስረዳት ፡ በምክር ።
#ካፑሌ ።
እስቲ ፡ እኮ ፡ ንገሪኝ ፡ ምንድነው ፡ ነገሩ ፡
አሁን ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ደርሶ ፡ ግርግሩ ።
#የካፑሌ_ሚስት
ትችል ፡ ትመስላለህ አንተ ፡ ደግሞ ፡ ደርሶ
የምሥራች ፡ « እንቢ» ፡ ብላለች ፡ ጨርሶ ፡
የመጣ ፡ ቢመጣ ፡ ይልቁንም ፡ ደግሞ ፡
አላገባም ፡ አለች ፡ ፓሪስን ፡ ፈጽሞ ።
#ካፑሌ ።
እግራችንን ፡ ስማ ፡ እኛን ፡ አመስግና ፡
በትልቅ ፡ ደስታ ፡ መቀበል 'ቀረና ፡
እንቢ ፡ አለች ፡ ብትይኝ ጆሮዬም ፡ አይሰማ
እስቲ ፡ ልስማው ፡ እኔ ፡ ትናገረው ፡ ደግማ
#ዡልዬት ።
ለክፋት ፡ አይደለም ፡ አትቈጣ ፡ አባቴ ።
#ካፑሌ ።
እረግ ፡ የኛ ፡ ሕፃን ፡ ትንሿ ፡ ማሚቴ ፡
የማነሽ ፡ ለዛ ፡ ቢስ ፡ የማነሽ ፡ ወልጋዳ ፤
የማነሽ ፡ አመዳም ፡ የማነሽ ፡ ገዳዳ'
ባለወግ ፡ አድርገን እኛ ፡ ነን ያጠፋን ፡
ብታውቂው ፡ ባታውቂው ኧረ ምን ፡ አለፋን
በግድ፡ ነው ፡ እንጂ፡ በኅይል ፡ የምንድር ፡
መች ፡ ያስፈልግና ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ንግግር
ነገ ፡ በማለዳ ፡ ተዘጋጅተሽ ፡ ውጪ ፣
ከተክሊሉ ፡ ቦታ ፡ ዐውቀሽ ' እንድትመጪ,
ታዛዤ ፡ ነሽና ፡ የወለድኩሽ ፡ ልጄ ፣
እኔ ፡ እድርሻለሁ ፡ በኀይል' አስገድጄ ፤
ለወግ ፡ መጠየቄ ፡ ቅብጠት ፡ነው ፡ አብጄ
እስከዚያ ፡ ድረስ ፡ ግን ፡ በፊቴ ፡ አትለፊ ፤
ዐይንሽን ፡ አልየው ፡ ካጠገቤ ፡ ጥፊ ።
#ዡልዬት ።
ነገሩን ፡ ላስረዳህ ፡ አባቴ ፡ አድምጠኝ ፤
ጋብቻው ፡ ፈጠነ ፡ ጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ስጠኝ
#ካፑሌ ።
ነገርሽ እሬት ነው ፡ መሪር ነው ፡ ኮምጣጣ
ካፍሽ ፡ ካንደበትሽ ፡ አንድ ፡ቃል፡ አይውጣ'
ሴት ልጅ እንቢ፡ብትል፡አለው አንድ አገባብ
መች ተሠርቶ ያውቃል እንዲህ፡ያለ ጥጋብ
ዘሩ ፡ የታወቀ ነዉ መልኩ ፡ የሚያኰራ ፡
ገንዘብ ፡ የተረፈው ፡ ስሙ ፡ የተጠራ፡
ደኅና ፡ ባል ፡ ፈልጎ ፡ በስንት ፡ መከራ፡
አባቷ ፡ ሲያመጣ ፡ ወዲያ ፡ ወዲህ ፡ ዞሮ '
ከቤት ፡ ተወዝፋ ፡ የኛ ፡ ሴት ፡ ወይዘሮ ፡
እኔ ፡ ባል ፡ አልሻም ፡ ትላለች ፡ ሞጋጌ ፤
መካን ፡ ሰው ፡ ይሻላል ከመውለድ ፡ ባለጌ
ጥኀጋብሽ ፡ ነው ፡ እኮ ደሜን ፡ የሚያፈላው ፤
ምኑ ፡ ነው ፡ እባክሽ ፡ፓሪስ ፡ የሚጠላው ?
ያለባል ፡ ለመኖር ፡ ከሆንሽ ፡
የምትወጂ ፡
ምን ፡ ቸገረኝ፡ እኔ ፡ ወደ ፡ ገዳም ፡ሂጂ ፡
ነገር ፡ ግን ፡ ከሆነ ፡ ማግባትሽ ፡ የማይቀር ፡
የመረጥኩልሽን ፡ ይገባሻል ፡ ማፍቀር ፡
ያላንድ ፡ ክርክር ፡ ያላንድ ፡ ቅሬታ ፡
ፈቃዴን ፡ መቀበል ፡ አለብሽ ፡ ግዴታ ።
የምትይ ፡ ከሆነ ፡ የኔን ፡ ፈቃድ ፡ እንቢ ፡
ከዛሬ ፡ ጀምረሽ ፡ ሂጂ ፡ ገደል ፡ ግቢ ፤
ዐይንሽን ፡ አልየው ፡ በዚህ ፡ በኔ ፡ ግቢ ።
የካፑሌ ፡ ሚስት ።
ቀስ ፡ ብሎ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ አባት ፡ ከመከረ ፡
አንተም ፡ አበዛኸው ፡ ነገርህ ፡ ከረረ ።
ካፑሌ ።
አትግቢ ፡ ፈጽሞ ፡ አንቺ ፡ በኔ ፡ ሥራ ፤
ሂጂ ፡ ወደ ፡ ጓዳ ፡ ከሴቶቹ ፡ ጋራ ፡
ቀኑን ፡ ሙሉ ፡ ባሳብ ፡ ሌሊቱን ፡ በሕልሜ ፡
ባል ፡ ስፈልግላት ፡ በመኖር ፡ ደክሜ ፡
በስንት 'ዐይነት ፡ ዘዴ ፡ እኔ ፡ ተጣጥሬ፡ .
እግዚአብሔር ረድቶኝ ፡ ይኸውና ፡ ዛሬ ፡
የሚሆን ፡ ሰው ፡ ባገኝ ፡ ጨዋ ፡ባለገንዘብ፡
እሜቴ ፡ ፈጠሩ ፡ ሠላሳ ፡ ሺሕ፡ ሰበብ ።
ስሚኝ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ልንገርሽ ፡ ካሁኑ፤
እሱን ፡ ካላገባሽ ፡ ታዘቢኝ ፡ በውኑ
የትም ፡ ትሄጃለሽ ፡ አብርሬሽ፡ ከቤቴ፤
እርሜን ፡ አወጣለሁ ፡ ቆርጬሽ ፡ ካንጀቴ
ልጅና ፡ አባት ፡ ሆነን ፡ መኖራችን ፡ ቀርቶ ፡
ክጄሽ ፡ ትሄጃለሽ ፡ አልምርሽም ፡ ከቶ ፡
ስለዚህ ፡ አስቢ፡ ከልብሽ ፡ ምከሪ፤
የሚከተለውን ፡ ተመልክተሽ ፡ ፍሪ'
ካሁኑ ፡ ጀምረሽ ፡ በነገሩ፡ ሥጊ፤
ቃሌ ፡ አይታጠፍም ፡ ኋላ ፡ ልብ ፡ አድርጊ
(ካፑሌ "ከቤት " ወጥቶ ሄደ)
#ዡልዬት ።
እባክሽ ፡ እናቴ ፡ ለልጅሽ ፡ እዘኚ፤
ባይሆን ፡እንኳን ፡ አንቺ ፡ ከኔ ፡ ወገን ፡ ሁኚ'
ቀኑ ፡ ረዘም ፡ ይበል ጥቂት ፡ ጊዜ ስጡኝ፤
አሳቤን ፡ ሳታውቁ ፡ በከንቱ ፡ አትቁጡኝ ።
ግዴታ፡ ካልሆነ' በጣም ' ካልቸረኝ፡
እንቢ ፡ አልልምና ፡ ምክንያት ፡ ካልኖረኝ ።
#የካፑሌ_ሚስት ።
ዕዳሽን ፡ በጨርቅሽ ፡ እንደምትፈልጊ '
አንቺ ፡ እንደ ፡ ፈቃድሽ 'እንዳሻሽ አድርጊ ።
(እናቷም' ወጥታ ሄደች)
#ዡልዬት ።
ርጂኝ ፡ አንቺ ፡ እባክሽ ፡ ምከሪኝ ፡
#ሞግዚቴ ፤
ምስጢር፡ ተካፋዬ፡አንቺ፡ነሽ ፡እናቴ '
የኛን ተክሊል ማንም አይችልም፡ሊያፈርሰው፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ድብቅ ፡ ነው አያውቅም፡ማንም፡ሰው፡
እባክሽ ፡ ምከሪኝ ፡ ዘዴ ፡ አታጭምና ፤
ጨነቀኝ ፡ ጠበበኝ'አገኘኝ ፡ ፈተና ።
#ሞግዚት ።
ቃሌን ፡ ብትሰሚ ፡ ተራዬን ፡ ልናገር ፤
ሮሜዎ ፡ ሰው ፡ ገድሎ ፡ ተሰደደ ፡ ካገር፡
ልትኖሩ ፡ ከሆነ ፡ ለብቻ ፡ ለብቻ ፡
በዚሁ ፡ ይፈርሳል ፡ የናንተ ፡ ጋብቻ ፡
በዚሁ ፡ ላይ ፡ ደግሞ ፡ አባትሽ ፡ ላባቱ
👍1