አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስራ_ሁለት

#ሞግዚት
ሞታለች ፡ ሞታለች ፡ ጕድ ፡ ነው ፡ የሚያስደንቅ ,

#የካፑሌ_ሚስት
ምን ፡መድኀኒት ላምጣ ወዴት ስፍራ ሄጄ

#ካፑሌ
ቆዩ፡እስቲ፡እኔ፡ልያት፡ የታለች፡ ቀዝቃዛ ፡ (እየዳበሳት).
ፈጽማ ፡ ሞታለች ፡ በምን ፡ ጕዴ በዛ
ሌሊት፡ በጨለማ ፡ ፀሓይዋ፡ ሳትወጣ ፡
ልጄ ፡ አበባዬ ፡ ወድቃለች ፡ ተቋርጣ ።

#ሞግዚት
የተረገመ ፡ ነው ፡ አወይ ፡ የዛሬው ቀን ፤

#የካፑሌ_ሚስት
ምነው ፡ ብንቀበር ፡ ሁላችንም ፡ አልቀን !

#ካፑሌ
ምንም ፡ አልናገር' ምላሴ 'ታሰረ
ልሳኔ ፡ በሐዘን 'ተቁልፎ ፡ ቀረ ።
(አባ ' ሎራና 'ፓሪስ ' በሙዚቃ ገቡ ።)

#አባ_ሎራ
ወደ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን እንሂድ ፍጠኑ
ሙሽራዋን ጥሩ እናንተም ቶሎ'ኑ ።

#ካፑሌ
ጉድ ሆነናል ዛሬ ይተዉ አባቴ
ጕድ ፡ ለማየት ፡ ኖሯል ፡ የቈየች ፡ ሕይወቴ
እኔ ፡ ወዴት ፡ ልድረስ ፡ የት ፡ አባቴ ፡ ልግባ
ሞተች ፡ ተቀጠፈች ፡ ልጄ ፡ የኔ ፡ ኣበባ ።
እናቷ ፡ ሳታስብ ፡ ኣባቷ ፡ ሳይሰማ ፡
ሞት ፡ የሚባል ፡ ሌባ ፡ ሌሊት በለጨለማ
ለካ ፡ ከቤታችን ፡ ገብቶ ፡ ተደብቆ ፡
ይዟት ፡ ሄዶ ፡ ኖሯል ፡ ልጃችንን ፡ ሰርቆ ፤
እንዴት ፡ ጉድ፡ ሆነናል ፡ እንዲህ ፡ ተደግሶ
ሰርጓ ሐዘን ፡ ሆነ ደስታችን ለቅሶ ።

#ፓሪስ
እኔ ፡ ዕድለ ፡ ቢሱ፡ እንዴት፡ ያለ ፡ መርዶ፡
እንዴት ፡ ያለ ፡ሐዘን ፡ ጠበቀኝ ፡ ተወልዶ

#የካፑሌ_ሚስት
የተረገመ ፡ ነው ፡ አወይ ፡ የዛሬ ፡ ቀን
ቀረን ፡ እኮ ፡ ሰዎች ፡ እንደዚህ ፡ ተሳቀን ፡
ያይኖቼ ፡ ማረፊያ ብትኖረኝ አንዲት ፡ ልጅ
ያንድ ፡ ቀን 'ደስታ' ለማየት'ስዘጋጅ፡
ለማን ኣቤት ልበል ፡ ሞት ፡ ይዞብኝ ፡ ሄደ
ሆዴ ተቃጠለ አንጀቴ ፡ ነደደ

#አባ_ሎራ "
ይብቃ ፡ ለሐዘኑ ፡ አድርጉለት ፡ መጠን ፤
አስቡ ፡ ይችን 'ልጅ' እግዜር ፡ ነው' የሰጠን
አሁንም ፡እግዚአብሔር ወሰዳት መልሶ :
ሐዘናችሁ ፡ አይሁን ፡ ያረመኔ ፡ ለቅሶ ፡
ቀረባት ፡ ብላችሁ ፡ የመሬት ፡ ደስታ ፡
ጸጸታችሁ ፡ አይሁን ፡ በጣም ፡ የበረታ ፡
የመሬት ፡ ደስታ ፡ ምንም ፡ የለው ፡ ዋጋ ፤
ይልቅ አይበልጥም ወይ የሰማይቤት ጸጋ፡
ከሚያልፍ ፡ዓለም ወጥታ፡ ከዘለዓለም ቤቷ
መተላለፍ፡ ነው ፡ በሰላም ፡ መግባቷ ፡
መሆኑ ፡ ቀረና፡ ሰርጓ በመሬት ላይ፤
ብርሃን ፡ ወዳለበት፡ሄደች፡ ወደ ፡ ሰማይ ፡
እናድርጋት ፡ ስንል ፡ ምድራዊት ፡ ሙሽራ ፡
አይሆናትም ፡ ብሎ ፡ የመሬት ፡ መከራ ፡
ሺሕ ፡ ጊዜ ፡ የላቀ ፡ ደስታ፡ አዘጋጅቶ ፡
እግዚአብሔር ፡ ወሰዳት ፡በፈቃዱ ፡ ጠርቶ
የሰርግ ልብሷን ለብሳ እንዳማረች በክብር
በሉ ፡ ያዟትና ፡ እንሂድ ፡ መቃብር ።

#ሮሜዎ ። (በተሰደደበት ፡ አገር 'ሆኖ)
መሠረት ፡ ቢኖረው ፡ የኔ ፡ ሕልም፡ ዛሬ ፡
አገኝ ፡ ይመስለኛል ፡ ደስ የሚያሰኝ ፡ ወሬ
ዡልዬት ፡ ስትመጣ ፡ ስታገኘኝ ፡ ሞቼ ፡
አልቅሳ ፡ ስትስመኝ ፡ እኔ ፡ ተዘርግቼ ።
ኋላም ፡ በሷ ፡ ትንፋሽ ፡ ሕይወቴን ፡ አድሼ
ከሞት ፡ ተነሥቼ ፡ አየሁኝ ፡ ነግሼ ።
በጣም ፡ ደስ ፡ ብሎኛል ፡ ዛሬ ጧት፡ጀምሮ
ሰላም ፡ ይሰማኛል ፡ የመንፈስ ፡ የአእምሮ
(ቤልሻጥር ቦት ጫማ አድርጎ፡ መጣ)
ቤልሻጥር ፡ጐበዙ፡ እንኳን ፡ ገባህ ፡ ደኅና'
ምን ወሬ ይዘህ መጣህ ዛሬ ከቤሮና ?
ዡልዬት ደኅናነች ወይ አባቴስ እንዴት ነው ?
እሷ ፡ ደኅና፡ ብትሆን ፡ግድ የለም የቀረው
ዡልዬት ፡እንደ ፡ምን ነች ? አሁንም አድሼ
ልጠይቅህ ፡ በጣም ሺሕ ፡ ጊዜ ፡ መልሼ

#ቤልሻጥር
ደኅና ፡ ነች ፡ ልበልህ ፡ አልነካትም ፡ ዐፈር
እንደሌላው ፡ ፍጥረት ፡ መሬት ፡ ሳትቀበር
ከመቃብሩ ፡ ቤት፡ ሠርተው ፡ አባቷ
ካዘጋጁት ፡ ገብታ ፡ እግሮቿም ፡ እጆቿ ፡
ታስረው ፡ ሳትገነዝ ፡ በማዕርግ ፡ ተንጋላ ፡
ተኝታ ፡ ኣየናት ፡ ያንቀላፋች ፡ መስላ ።
እንዲህ ፡ በጌትነት ፡ ዡልዬት ፡ ተቀበረች ፤
በቃ ፡ የሷ፡ ነገር ፡ እንደ ፡ ዘበት ፡ ቀረች ።
ነፍሷ ፡ ግን ወደ እግዜር ዐረገች ወደ ላይ
ዐርፋ ፡ ከዚህ ዓለም ወጣች ፡ ወደ ሰማይ

#ሮሜዎ ። (በድንጋጤ ፊቱ ተለወጠ)
ምን ፡ አገኛትና ? በምን ፡ የተነሣ ?

#ቤልሻጥር
ጧት፡ ባልጋዋ ፡ ላይ ፡ በድን ሆና ሬሳ፡
ተገኘች ፡ ከእንቅልፍ፡ ሳትነቃ ፡ ሞታ ፤

#ሮሜዎ
እንደዚህ ፡ ከሆነ 'የዡልዬት ፡ ሁኔታ ፡
ደግ ፡ ነው መልካም ፡ ነው ፤ ብዕር፡ቀለም፡ኣምጣ፡
ፈረሶች ፡ ተከራይ ፈጥነህ መንደር ፡ውጣ
ማንም ሰው ሳያየኝ ማንም ሰው ሳይሰማ
መሄዴ' ነውና ፡ ሌሊት ፡ በጨለማ ።

#ቤልሻጥር
እባክህ ፡ ጌታዬ ፡ ፊትህ ፡ ተለወጠ ፤
ደምህም ፡ ጠቈረ ፡ ልቤ ፡ ደነገጠ '
ቻለው ፡ ሐዘንህን ፡ ከትዕግሥት ፡ ጋራ

#ሮሜዎ
አትሥጋ ፡ ግድ የለም ፡ ቤልሻጥር አትፍራ
የማይሆን አይሆንም የሚሆን ፡ ይሆናል !

ይልቅ ፡ቶሎ ፡ ፍጠን ፡ ጊዜው ፡ ያልፍብናል
(ቤልሻጥር ሄደ፤ ሮሜዎ'ብቻውን) »
እንገናኛለን ፡ ዥልዬት ፡ ዛሬ ፡ ማታ ፤
ወዳንቺ ፡ ለመድረስ ፡ ቶሎ ፡ በደስታ ፡
መንገዱን ፡ መፈለግ ፡ አለብኝ ፡ ግዴታ ፡
መድኀኒት ፡ የሚሸጥ ፡ አንድ ፡ ጎረቤቴ ፡
መኖሩን ፡ ዐውቃለሁ ፥ እኔ ፡ በሕይወቴ ፡
አይቼ ፡ አላውቅም ፡ ችግረኛ ፡ እንደ ፡ እሱ
ሁል ፡ ጊዜ ፡ ያደፈ፡ ቀዳዳ ፡ ነው ፡ ልብሱ ፡
የተጐዳ ፡ ሰው ፡ ነው ፡ ድህነት ፡ ያጠቃው
ሰውነቱ ፡ ከስቷል ፡ የመደብር ፡ ዕቃው ፡
አሮጌ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ቈሻሻ ፡ ሰባራ ፤
ተጠርጎ ፡ የማያውቅ ፡ የለበሰ ፡ ዐቧራ ።
ከሱቁ ፡ ስገባ ኔም አስተውዬ
እሱን ፡ባየሁ ቍጥር አሰብኩ እንዲህ ብዬ
በማንቱ ፡ ከተማ ፡ ለሰው ፡ መርዝ ፡ የሸጠ
በምንም ፡ አኳኋን ፡ አውጥቶ ፡ የሰጠ ፡
ምንም ፡ እንኳ፡ የሚያዝ ፡ በሞት ፡ እንዲቀጣ ፡
ኀይለኛ ፡ ዐዋጅ ፡ ቢኖር ፡ ተጽፎ ፡ የወጣ ፡
መርዝ ፡ የሚፈልግ ፡ ሰው ፡ ብዙ ፡ ገንዘብ ፡ ሰጥቶ ፡
ይህን ችግረኛ፡ ቢጠይቀው ፡ መጥቶ ፡
አይጠረጠርም : እንቢ ፡ እንደማይለው ፤
ስለዚህ ፡ ጠርቼ ፡ እስቲ ፡ ልሞክረው ፡
አንተ ፡ መድኀኒት ፡ ሽያጭ፡ እባክህ ፡ ወዲህ ፡ ና ።

#መድኀኒት_ሽያጭ
ምነው ፡ ሮሜዎ አይዶለም ወይ ፡ ደኅና ?

#ሮሜዎ
ሰው ፡ አንተን ይሻሃል ባጣ ፡ ጊዜ ፡ ጤና፡
አንድ ፡ ነገር ፡ አሁን ፡ ልንገርህ ፡አድምጠኝ
ቶሎ ፡ የሚገድል ፡ ብርቱ ፡ መርዝ ፡ ስጠኝ፡
አርባ ፡ ዱካ ፡ ልስጥህ ለመርዝህም ዋጋ
አንተም ፡ ትሆናለህ ፡ በዚህ ፡ ባለጸጋ ፡
አንተን ፡ ለመሰለ ፡ በጣም ፡ ለተጐዳ ፡
ይህ ፡ ብዙ ፡ ገንዘብ ነው በጣም የሚረዳ

#መድኅኒት ፡ ሽያጭ ።
ኀይለኛ ፡ መርዝ አለኝ በመደብሬ ውስጥ
ግን ፡ ባዋጅ ፡ ክልክል ነው፡ለማንም፡ እንዳልሸጥ ።

#ሮሜዎ
ሞኝ ፡ ነህ ፡ መሰለኝ ፡ ዐዋጅ ፡ብሎ ፡ ጣጣ
ራብ ፡ ለገደለህ ፡ ዐጥንትህ ' ለወጣ'
ላንተ ፡ ምን ' ጠቀመህ ይልቅ ስጠኝ' ቶሎ
ድኽነት ፡ ይታያል ፡ በመልክህ ፡ ተሥሎ'
ጒዳት ፡ አቈራምዶ፡ ችግር ፡ ያሸነፈህ

💫ይቀጥላል💫
👍1