አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮሜዎና_ዡልዬት

#ክፍል_አምስት

ከተሸንፍክማ ' በጕንጮቿ ፡ ቅላት '
በወገቧ ቅጥነት፡ በደረቷ፡ ሙላት'
አበድኩ ፡ ካልክማ፡ ለጥርሶቿ 'ንጣት '
ለባቷ፡ አቀራረጽ ለጠጕርዋ ፡ቀለም ፡
ፍቅርህ ፡ ባይንህ ፡ ላይ ፡ነው፤ በልብህ ፡ አይደለም ይቅር በለኝ፡ልጄ፡ ባሁኑ ፡ ወቀሣ
ለዚች ፡ ከንፈህላት፡ ያችን ' ስትረሳ ፡
አመዛዘንኩና' ሠጋሁ፡ ኣስተውዬ '
ይችንም ፡ እንደዚያች' ትረሳለህ ፡ ብዬ ።

#ሮሜዎ
አባቴ ፡ በፍጹም ፡ ይህን ፡ አይጠርጥሩ፤
የዚችና ፡ የዚያች ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ነገሩ
በምን ፡ ቃል ፡ ልናገር ፡ ይህን ፡ ለማሳመን
በግሪክ ፡ በሮማ ፡ በጥንታዊው ፡ ዘመን ፡
ያነቡ፡ እንደ'ነበር' የእንስሳውን ፡ ሞራ ፡
ይችሉ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ አባቴ ፡ አባ፡ ሎራ '
እርስዎም ፡ እንደዚሁ፡ የልቤን ፡ ብራና፡
በጥበብ ፡ አውጥተው ፡ገልጠው፡ያንቡና '
የወረት ፡ ምልክት ፡ ቢያገኙ፡ በውስጡ '
ያን ፡ ጊዜ 'ይገባል ፡ ቢንቁኝ ፡ ቢቈጡ ።

#አባ_ሎራ
መልካም ነው አመንኩህ ፡ግን ከዚህ ፡ በኋላ
አንድ ፡ ነገር ፡ አለ ፡ የሚያስቸግር ፡ ሌላ ፤
ካፑሌና ፡ ሞንታግ ፡ የናንተ ፡ አባቶች ፡ .
ወገኖቻቸውን ፡ ጨምረው ፡ ጠላቶች ፡
ባላንጦች ፡ ቂመኞች ፡ ደመኞች ፡ ሲሆኑ ፤
በየመንገዱ ፡ ላይ ፡ እንዳውሬ ፡ እያደኑ ፡
አንዱ ፡ አንዱን ፡ ሲገድለው ፡ ባይኑ ፡ ሲያየው፡ብቻ
እንዴት ፡ ሊፈጸም ፡ ነው ፡ የናንተ ፡ ጋብቻ ? .
ይኖሩ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ዘወትር ፡ በዘመቻ ፡
ዘለዓለም ፡ ለውጊያ ፡ ለጠብ ፡ ተሰልፈው ፡
ለቄስ ፡ ላስታራቂ ፡ ለዳኛ ፡ አሸንፈው ።

#ሮሜዎ
ይኸው፡አባቴ ሆይ ይህ ነው፡ ዋናው ነገር
በዚህ ፡ ላይ ፡ ይገባል ፡ በብዙ ፡ መማከር ፡
እውነት፡ ነው ፡ ቢኖሩ፡ ዘለዓለም ፡እነሱ፡
በጠብ ፡ ባምባጓሮ ፡ ደም ፡ እያፈሰሱ ፡
ለፍርድ ፡ ቢያስቸግሩ የቄስ ፡ ቃል ፡ ባይሰሙ ፡
እኔና ፡ ዡልዬት ፡ ግን ፡ንጹሕ ፡ ነን ፡ ከቂሙ፡
አለ ፡ ወይ ፡ አባቴ ፡ በሃይማኖት ፡ መንገድ
የሚከለክል ፡ ሕግ ፡ እኛ ፡ እንዳንዋደድ ፡
እንግዲህ ፡ አባቴ ፡ ይህንን ፡ ካወቁ ፡
ዘዴውን ፡ ለማግኘት ፡ እርስዎም ፡ ይጨነቁ ፡ቤተ ሰቦቻችን ወሬውን ፡ ሳይሰሙ
ተክሊሉን ፡ በምስጢር ፡ እርስዎ፡ ይፈጽሙ ።

#አባ_ሎራ
ይህንን ፡ ታልህማ ፡ ዘዴ ፡ ጠፍቶ ፡ ለርቁ ፡
ካህንም ፡ አልቀረም ፡ አብሮ ፡ መጨነቁ ፡
ለሁለቱ ፡ ወገን ፡ ሰላምን ፡ መልሶ ፡
ያባቶቻችሁን ፡ ክፉ ፡ ቂም ፡ ደምስሶ ፡
ስለታቸው ፡ ዘወትር ፡ የሰው ፡ ደም ፡ ከማፍሰስ ፡
እንዲቆም ፡ ለማድረግ ፡ ትንሽ ፡ እንዲታገሥ ፡
ለሻምላ ፥ ለጩቤ ፥ ለሰይፍ ፡ ለጐራዴ ፡
ከዚህ ፡ የተሻለ ፡ መች ፡ ይገኛል ፡ ዘዴ ።
የናንተ ፡ ጋብቻ ፡ ይህን ፡ ቂም ፡ አብርዶ ፤
ዕርቅ ፡ ይመሠረታል ፡ ሰላምን ፡ አውርዶ ።

#ሮሜዎ
እንግዴህ፡ አባቴ ፡ እንፍጠን ፡ በቶሎ ፡
ተክሊሉ ፡ ይፈጸም ፡ በዛሬ ፡ቀን ፡ ውሎ ፡
ጊዜና ሰዓቱን ፡ ካልተሻማን ፡ በጣም :
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ዕንቅፋት ፡ አያጣም

#አባ_ሎራ
እንግዲያው ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ኑና ፡ ባሥር ፡ ሰዓት፡
ትፈጽማላችሁ ጋብቻችሁን በስራት

#የዡዬየት_ሞግዚትና #ሮሚዎ

#ሞግዚት
መልሱን ፡ ተቀብለሽ ፡ እንድትመጪ ' ብላ
ልካኝ' እመቤቴ ፡ በቶሎ ፡ አስቸኵላ '
ይኸው ፡ መጥቻለሁ፡ መልሱን ፡ ለመቀበል ፤
ቸኩያለሁና ፡ ንገረኝ፡ ቶሎ ፡ በል ።

#ሮሜዎ
ምላሴ 'ያሞግስ ፡ አፌም ፡ ያመስግናት ፤
በውነት' ያንቺ ፡ እመቤት ፡ የተባረከች ፡ ናት
ዐመሏ ' ጠባይዋ ፡ በለጠ ' ከመልኳ፤
ቃሏን ፡ ፈጸመችው ፡ አንቺን ፡ በመላኳ
ዥሮቼ ፡ ተከፍተው 'እሰማለሁና፡
እንግዴህ ፡ ንገሪኝ የዡልዬትን ፡ ዜና ።

#ሞግዚት
ለተነጋገርነው ፡ ትናንትና ፡ ማታ ፡
እንድትልክብኝ' ያሳብህን ፡ ሁኔታ ፡
በመጠበቅ ፡ ላይ ፡ ነኝ ፡ አስታውቀኝ ፡ በቶሎ ፤
በዪና፡ ንገሪው ፤እንደዚህ ፡ ነው፡ ብሎ ፡
አሳቡን ፡ ሲነግርሽ ፡ ተቀብለሽ ፡ አምጪ፡
ብላኝ ' መጥቻለሁ ።

#ሮሜዎ
መልሴን ፡ ስትሰጪ '
እንግዲያው ፡ ንገሪያት ፡ ሮሜዎ ፡ ከልቡ ፡
ይወድሻል ፡ ብለሽ ፡ መንፈሱም ፡ አሳቡ ፡
ወዳንቺ ፡ ነው ፡ በያት ፡ ንገሪያት ፡ አደራ ፤
እስቲ ፡ ልለምንሽ ፡ እባክሽ ፡ ሳልፈራ ፡
እኔ ፡ እንደምወዳት፡ እንደዚሁም ፡ እሷ'
ትወደኝ ፡ እንደሆን ፡ ዡልዬት፡ በመንፈሷ፡
ታውቂዋለሽና ፡ እባክሽ ፡ ንገሪኝ ፡
አሳቧን ፡ ጠባይዋን 'እንዳውቀው ፡
ምከሪኝ ።

#ሞግዚት
ምንም ፡ አልደብቅህ ፡ ልንገርህ ፡ ካንዠቴ
አንተን ፡ ስታፈቅር ፡ ዝልዬት ፡ እመቤቴ'
እመነኝ ፡ ልንገርህ ፡ በውነት ፡ ከልቧ' ነው
የመስፍኑ ዘመድ፡ፓሪስ የሚባለው፡
ሊያገባት፡ ፈልጎ ፡ መሞቱ ፡ ነው ፡ ደክሞ ፡
ጨርሳ ፡ አትወደውም፡ እሷ ፡ ግን ፡ ፈጽሞ
አታንሡ፡ትላለች ፡ የሱን ፡ ስም ፡ ከፊቴ ፤
ትቈጣለችና ፡ ስቈይ ፡ እመቤቴ ፡
ልመለስ ፡ እባክህ ፡ መልሱን ፡ ስጠኝና ፤

#ሮሜዎ
አቀርብልሻለሁ'በሰፊው ፡ ምስጋና ።
እንደዚህ ' በዪና ፡ መልሱንም ፡ ንገሪያት ፤
ከቀትር ፡ በኋላ ፡ ዛሬ ፡ ባሥር ፡ ሰዓት ፡
አባ 'ሎራ፡ ድረስ ፡ አስፈቅዳ ፡ ትምጣ፤
ተናዘን ፡ ተባርከን ፡ የተክሊሉን ፡ጣጣ፡
ደብቀው ፡ በሙሉ ፡ ሊፈጽሙ፡ ቄሱ ፡
ተስማምተናል ፡ በያት ፡ ዛሬ ፡ ሊጨርሱ ።

#አባ_ሎራ #ዡልዬት #ሮሜዎ

#አባ_ሎራ
የናንተ ፡ ጋብቻ ፡ ፍጻሜው ፡ እንዲያምር ፡
ፈጣሪ ፡ ጸጋውን ፡ ምሕረቱን ፡ ይጨምር ።

#ሮሜዎ
አሳቤ ' ሞላልኝ ፡ እንግዲህ ፡ አባቴ ፡
ይህ ፡ ብቻ፡ ነበረ ፡ የቀረኝ ፡ ምኞቴ ።
ከሷ'ጋራ ፡ መጥቼ ፡ ቀርበን ፡ ከመንበሩ፡
ሥራቱን ፡ ከሞላን ፡ አለቀ ፡ ነገሩ ፡
እንግዲህ ፡ ግድ ፡ የለም የመጣ ፡ ቢመጣ

#አባ_ሎራ
ልጄ ፡ ሆይ ፡ ብዙ ነው የዚህ ዓለም ፡ ጣጣ
ለደስታ ፡ ሐዘን ፡ ለማር ፡ አለው ፡ እሬት ፤
ጠፊ ፡ ካጥፊው ፡ ጋራ ፡ ይኖራል ፡ በመሬት
ስለዚህ ፡እግዚአብሔር መጥፎውን ፡ አርቆ
ልጄ ፡ ያኑራችሁ ፡ በሰላም ፡ ጠብቆ ።

(ዡልዩት ፡ መጣች) ።

ፍቅሯንና ፡ ጌጧን ፡ በልቧ ፡ ሸፍና ፡
አልማዟ ፡ ማስተዋል ፡ ወርቋ ፡ ትሕትና ፡
ምስጢሯን ፡ ባሳቧ ፡ በጥበብ ፡ ሰውራ ፡
ይኸው ፡ መጣችልን ፡ መልካሟ ፡ ሙሽራ

#ዡልዬት
ሰላም ፡ ለርስዎ ፡ ይሁን ፡ ኣባቴ ፡ አባ ሎራ

#አባ_ሎራ
ደኅና ፡ ነሽ ወይ? ልጄ። ወጣት ፡ ሴት ፡ ወይዘሮ ፤
መልካም ፡ ጊዜ ፡ መጣሽ ፡ ልክ ፡ በቀጠሮ

#ዡልዬት
አመሰግናለሁ ፡ ለኔም ፡ ለሮሜዎ ፡
አባቴ ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ በመቸገርዎ ።

#ሮሜዎ
እንዳንቺ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ በፍቅር ፡ ተሳስረው
ለመጡ ፡ ወጣቶች ፡ ሥራቱን ፡ አክብረው
ፍቅራቸውን ፡ ባርኮ ፡ በእጁ ፡ ሊቀድሰው ፡
ምን ፡ ጊዜም ፡ ሥራው ፡ ነው ፡ ካህን ፡ የሆነ ፡ሰው።

#አባ_ሎራ
እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ ካህን ፡ ይጠብቃል ፤
እውነት ፡ ነው ፡ ሮሜዎ ፡ የተናገረው ፡ ቃል'
ከቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ እንግባና ፡ በሉ ፡
ሳይዘገይ ፡ በቶሎ ፡ ይፈጸም ፡ ተክሊሉ ።

(ቤተ ፡ ክርስቲያን'ገቡ)

(#በቬሮና #ከተማ' #መንገድ) •

#ሜርኩቲዎ #ቤንቮሊዎ ፡ አንድ ፡ የእልፍኝ #አሽከር

#ቤንቮሊዎ
ሜርኩቲዎ ፡ እንሂድ ፡ የካፑሌ ፡ ሰዎች ፡
ይጠፉ ፡ አይመስለኝም በነዚህ መንደሮች
ድንገት ፡ ብንገናኝ ፡ ኋላ ፡ ጠብ ፡ ይነሣል ፤
ደግሞ ፡ ጠብ ሲነሣ ፡ ጸጥታ ፡ ይፈርሳል ፡
ብንሸሽ ፡ ይሻላል ፡ ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ ጣጣ ።

#ሜርኩቲዎ
እነሱም ፡ አስበው ፡
👍1
#መንገድ_እንይ

ወደፊት ስንሄድ...
መንገዳችን ደሞ፤ወደ ኋላ ይሄዳል
መድረሻ ብናጣም
መንገዱ ርቆናል
ወደ ወጣንበት ፥ መመለስ ይከብዳል።
በየ መንገዱ ላይ ...
እየተጠላለፍን ፥ እየተገፋፋን
ወደ ፊት ስንጎዝ
መንገድ ወደኋላ ፥ ተጉዞ ሲያለፋን
“እግር እንይ" ብለን
እግር እግር ስናይ : መንገድ እንዳይጠፋን
እስቲ መንገድ እንይ!
እግሮችን እያየን ፥ መከተሉን እንተው
መንገድ ወደ ኋላ
እየሔደብን ነው
ወደ ፊት እየሔድን ፥ የምንጎተተው፡፡
እስቲ መንገድ እንይ!
የሚከተሉ አይኖች ፥ ከእግሮች ይነቀሉ
ትክክል መንገድ ላይ
ትክክል ያልሆኑ ፣ እርምጃዎች አሉ።
#መንገድ

የመኼድ ርዝመት በዕርምጃ ስኬት
የሕይወትም ዳና በመሥመሩ ልኬት

ከተነጻጸረ . . .!
ይመተራል ዕድሜ ፣ ይሰበዛል ታሪክ
ይፍታታል ትርጓሜ ፣ በተጓዙበት ልክ።

ዕርምጃ - ፩
ዕንቅፋት በበዛው በጠባብ ጎዳና
ዐይነ ስውር ተጓዥ በእዝነ ልቦና ፣
ያለ መሪ ጒዞ በሐሳብ በትሩ
ያለመደናቀፍ ፣ መድረስ ከመንበሩ።

ዕርምጃ – ፪
በፍሥሓ ጕዝጓዝ ፣ በተደላደለ
የሚደነቃቀፍ ፣ ማየት ያልታደለ
ትላንቱን የረሳ ፣ በነግ አልባ ጕዘት
በለኮሰው እሳት ፣ ያልወጣ ከፍዘት።

እንግዲኽ . . .
በመንገድ ርቀት በ'ርምጃችን ዕድሜ
ከምንም መጀመር . . .
ያልጀመሩት ጉዞ የለም ፍጻሜ።

ለቅጽበት አይተሺኝ
በድኔን ዳብሰሺኝ
ያንቀላፋው ልቤን
ነክተሽ ብታነቂው።

እስኪ አኹን ምን ነበር . . . ?!
በምኞት ሠቀቀን ያ'ላንቺ ከምኖር
አንድ'ዜ ዳብሰሽኝ ዘላ'ለም ብቀበር።

እስኪ ምን አለበት . . . ?!
ፍቅርሽን ሰጥተሺኝ ፣
ሞትን ብንቅበት
ትንሣኤን ባውቅበት።

እስኪ ምን አለበት . . . ?!
ዘመኑን በሙሉ ባክኖ እንደኖረ
የመናፈቅ ዕድሜው በፍቅር ተሻረ።
( . . . የሚል ገድል ታሪክ . . . )
(. . . ተጽፎ ቢተረክ . . .)
እስኪ ምን አለበት . . .?!

ድንገት ተከስተሽ ፣
ፍካት ባጣው ቤቴ ፣ ሣቅሽን ብትዘሪበት
ብለሽ ብትነግሪያቸው ሕያውነት ቅጽበት።