አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
480 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_አንድ


#በሜሪ_ፈለቀ

ሁሌም ዛሬ ላይ ቆመህ ሁለት ምርጫ አለክ ትናንት ወይም ነገ ትዝታ ወይም ተስፋ!
።።።።።
#ረቂቅ

ከወንድምና ከህሊና የቱ ይበልጣል? ወይም ከእናት እና ከህሊና?
እሺ ከነገና ከህሊና ?ህሊና እንጀራ ይሆናል?

የህሊና ንፅህና ለነፍስ ምግብ ይሆን ይሆናል። በነፍስ እርካታ ስጋ ይጠግባል እንዴ? ነፍስ ጠገበች ብሎስ ሆድ ይጠግባል?
ኸረ እንደውም ነፍስ ስጋ ውስጥ ነው የምታድረው። ማደሪያዋ የህልውና ጥያቄ ውስጥ ሲገባ ነፍስም ህልውናዋ አጠያያቂ ነው።በእጅ አዙር እንጀራ ትፈልጋለች።በእርግጥ ነፍስ ለማደሪያነት
የቱን ትመርጣለች? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ይሆናል። ስጋን ወይስ ከስጋ ከተለየች በኋላ የምታድርበት መኖሪያዋን?ሀይማኖተኛ ወይም የሞራል ሰው ሆኜ አይደለም ይህን
መዘላበዴ እንደው ከፀፀት ለመዳን ታክል እንጂ፡፡

ከዚህ ሁሉ ውዝግብ በፊት ለመልስ ሳትቸኩሉ ራሴን ላስተዋውቃችሁ።

ስሜ ረቂቅ ነው:: በእርግጠኝነት የእኔን ስም እናቴ እንጂ መላዕክት አላወጡትም

እድሜዬ አስራ ሰባት ዓመት
የማልቆጥራቸው
ነው:: (በእርግጥ ከመኖር ከማልቆጥራቸው ሰባት የቀነስኳቸው ዓመታት አሉ እንተዋወቅና ከመኖር ከቆጠራችሁት ደምሩበት፡፡)

የስራ ሁኔታ ገንዘብ ብቻ ላላቸው ድሀ ወንዶች ደስታና ሳቅን መለገስ (በእርግጥ ማማለልም አለበት። መተኛትም።)

የአገልግሎት ዘመን ከንቱ፡፡

ዛሬ የተለየ ጉዳይ ገጥሞኛል፡፡ የኢትዮጵያ አማርኛ ፊልሞች ላይ ብቻ ያሉ ዓይነት ታሪኮች የሚመስል ስራ ነው።ስራው አንድ
ጋግርታም ሰውዬ ማማለል።
ኤፍሬም ይባላል።ለየት የሚያደርገው እርሱ ለመማለልም ለመሳቅ ፍቃደኛ አይደለም።የአባቱ ጓደኛ የሆነ አያሌው የሚባል ሰው ነው።እንዳማልለው የቀጠረኝ፡፡ ክፍያው አምስት መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር ነው።

አፌዛችሁ አይደል? እኔም የሰማሁኝ ሰዓት በፌዝ ስቄ ነበር።በትክክል ኤፍሬምን ማማለል ብቻውኝን በቂ አይደለም።አብሮ መተኛትም ይሄን ብር አያስገኝም።

ነገርየው በደንብ ፌዝ የሚመስለው ዋናውን ዓላማ ስታውቁት ነው።
ኤፍሬም የተለያዩ ሴክተሮች ያሉት ትልቅ ኩባንያ ባለቤት ነው።

አዲስ አበባ ውስጥ የኩባንያውን ስም ከተለያዩ ምርቶችና አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ መስማት እንደ አንዱ
የቤተስባችሁ ስም የተለመደ ነው። ብነግራችሁ ታውቁታላችሁ እኮ! አቶ አያሌው የቆዳ ውጤቶች፣ ከብት ማደለቢያ፣ ማተሚያ ቤት እና በተጨማሪም የኤፍሬም አባትና አቶ አያሌው (የአባቱ ጓደኛ) በሼር ይሰሩት የነበረ አሁን ለኤፍሬም የተላለፈ ትልቅ
የሳሙና ፋብሪካ በኩባንያው ስር እንደሚጠቃለል ዘረዘረልኝ፡፡
እንግዲህ ኤፍሬምን በእጅ በእግሩ ገብቶ የፋብሪካውን ሼር ለአያሌው እንዲሸጥ ማሳመን ነው ስራዬ፡፡ የሆነ ቧልት ነገር
አለው አይደል? እኔም ያልኩት እንደዛ ነው፡፡

እንዴት ብታስበው ነው ይሄን ያህል ከባድ ውሳኔ ላስወስነው እንደምችል ያስብከው?" ነበር የጠየቅኩት።

ያንቺ ስራ እንዲወድሽ ማድረግ ብቻ ነው:: ሰውየው ከወደደሽ፣
እንኳን በንብረቱ በነፍሱ ይደራደርልሻል:: ለሚስቱ እንደዛ ነበር::" ነበር ያለኝ አያሌው፡፡

ሰውየው(አቶ አያሌው) አንቱ ለማለት የሆነ ቀላል ነገር ስላለው
አንቱ ማለት ከብዶኝ ነው አንተ የምለው እንጂ አንተ የሚሉት ሰውስ አልነበረም።

"ማንም ምራቁን የሚውጥልሽ ቆንጆ ነሽ፣ ተግባቢ ነሽ፣ በምንም ምክንያት ይሁን ተግባብተሽዋል።" ቀጠለ።


ሰውየው ማወቅ ስላለብኝ የኤፍሬም ባህርያትና ይጠቅምሻል ያለኝን የቤተሰቡን እና የኤፍሬምን ያለፈ ታሪኮች ነገረኝ፡
አያሌው ሂሳብ ክፍለ ጊዜ ላይ ብቻ የፃፍኩትን ቁጥር መጠን ብር ሳይጠራልኝም በፊት ኤፍሬምን ለመጥበስ አስቤ ነበር።ተጨማሪ ስራ ስለተደረበልኝ የመሳካት እድሉ የእስራኤሎችን የተስፋይቱ ምድር ከንዓን ያህል ሩቅ እንደሆነ ቢሰማኝም
እያወሩላት እያዩዋት፣ እየተዋጉላት
አርባ ዓመት እንደመባተል፣ ዘምረውላት ሳይኖሩባት ምድረ በዳ
እንደመቅለጥ) ባይሳካልኝ የምጎዳው ነገር የለም ከዚህ በፊት እንደነበረኝ አይነት ሽግግር ወደ ሌላ ሀብታም ቀን መሰስ ብዬ እገባለሁ፡፡ ቢሳካልኝ ደግሞ ፐ! መሞከር ከምንም ይሻላል።

“ሁሌም ቢሆን ደግሞ የአዳም ድክመቱ ሄዋን ናት! አይደል?

ቆዩማ ስራዬን ከመጀመሬ በፊት ኤፍሬምን እና ቤተሰቡን
እንዴት እንዳወቅኳቸው ልንገራችሁ:: ከአስማማው ጋር አንድ ትልቅ የሀብታሞች እና የቦርጫሞች እራት ላይ ታደምኩ።
አስማማው የሆነች ሴትዮ ባል፣ የእኔ ስም የሌለው ነገሬ ነው።
እናስ አብሬው ምን እያደረግኩ እንደሆነ ከጠየቃችሁኝ የስራ ልምድ እየደመርኩ ነዋ! ቅምጡ ነኝ! ለስራዬ ተገቢውን ክፍያ ይከፍለኛል አንዳንዶች ያው ሽርሙጥና ነው ልትሉት ትችላላችሁ። እኔ አልስማማም:: ሽርሙጥና የሚሆነው ከተለያየ ወንድ ክፍያ ሲገኝበት ነው የሚመስለኝ።እኔ ቢያንስ በአንዴ

ከተለያየ ወንድ ጋር አልሆንም።በአንድም ቀን ይሂድ በአንድ ዓመት አንዱ
ካልሄደ ሌላ አልጠብስም።

እየሽረሞጥኩ እንዳይመስለኝ ደሞ እንደ እነዚህ ያሉ ዝግጅቶችን ጨምሮ
የሰውየው የተለያየ የቀን እንቅስቃሴዎች ውስጥ ጥልቅ እላለሁ።

ለነገሩ የፈለጋችሁትን በሉት ጉዳዬ አይደለም፡፡ ድንግል ናት ብላችሁኝም ቢሆን ኖሮ ለድንግልናዬ የአንድ ቀን
ቀለብ አትሰፍሩልኝም። አልያም ለክብሬ ብላችሁ የአንድ ወር የቤት ኪራይ አትከፍሉልኝም ነበር። ለምግባሬ የፈለጋችሁን ስድብ ብትለጥፉበትም ነፍስ ገለመሌ ህሊና ቅብርጥሶ እያልኩ
ባልፈላሰፍም ለስጋዬ መደበኛ የእለት ፍላጎቱን እየሞላሁለት ነው። የእለት መደበኛ ፍላጎቴ ምን መሰላችሁ? ወንድሜና እናቴ ናቸው።

ከአስማማው ጋር የታደምኩበት እራት የኤፍሬም ሽንጣም ስም ያለው ድርጅት ዓመታዊ ሪፓርት እና የአዲስ በጀት ዓመት አንኳር እቅዶች የሚወሱበት ስብሰባ ነገር ነው።

ጠቅላላው የድርጅቱ ሰራተኞችን እና ድርሻ ተጋሪዎችን እንዲሁም አጋር ድርጅት ሀላፊዎችን ያሰባሰበ እራት ነበር፡፡

ሁሉንም የኤፍሬምን ቤተሰቦች ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋቸው እዛ
ነው። አያሌውንም አይቼው ነበር። ወሬያቸው፣ አለባበሳቸው፣ቄንጣቸው፣ ሳቃቸው፣ የሚያጨሱት ፒፓ አህ! ይጨንቃሉ።
ሁሉም ነገራቸው ቄንጥ ስለሚበዛበት ለበጣ ይመስላል፡፡ ሰው ሳመሳቅ ቄንጥ እያበጀ ይስቃል? እነርሱን ለመምሰል አስማማው የገዛልኝ ሰውነቴን አጣብቆ እግሬ ድረስ የዘለቀው ቀሚስ
ጨንቆኛል፡፡ ከዚህ ስብስብ ወጥቶ ማጨስ አምሮኛል።

“ዓለምሽን አሳየሁሽ አይደል?" አለኝ አስማማው:: ዓለሜ ይህቺን ታክል ጠባብ አለመሆኗን ላስረዳው ባስብም፣ ለእንደአስማማው አይነት ሰው ይሄ አይነገርም ብነግረውም አይገባውም
_ የሚገርማችሁ አብዛኛዎቹ የአዲስ አበባ ሀብታሞች በአንድ ፋብሪካ ተመርተው የተተፉ እስኪመስሉ ድረስ

የሚያመሳስላቸው ነገር ይበዛል። ቦርጫቸው፣ ሳቃቸው፣ ክፍት
አፍነታቸው፣ ከእውቀትና ከምግባር ነፃ መሆናቸው፣ ሴት መውደዳቸው
በገንዘባቸው የማይገዙት ነገር እንደሌለ
ማመናቸው..... ኸረ ብዙ ነገራቸው ይመሳሰላል። አስማማው
ስለተሰበሰቡት ሰዎች ማንነት የሚደሰኩረው ዲስኩር ከምግቡ
ይልቅ ሆዴን ነፋኝ፡፡ ወሬውን ሳያስመልሰኝ በፊት ማቆም ፈልጌ ስለ ሲደመር
አንገብጋቢው ጉዳዬ ስለነበር ርዕስ ቀየርኩ።

“ብሩን አስገባህልኝ?" አልኩት::

"ረቂቅ ብር ካስገባሁልሽ እኮ ገና አስራ አምስት ቀን አልሆነም::" ግን እንደ እሱ ዓይነት ደርዘን ደነዝ ሀብታሞች ስለሚያወጡት ገንዘብ ማማረር ከጀመሩ መሄጃቸው መድረሱን ከስራ ልምዴ
አውቃለሁ፡፡ ሲጀመር ሰሞን ገንዘብ እስኪጠየቁ አይጠብቁም።

ራሴ ተነጥፌልሽ ተራመጂብኝ ማለት ነው የሚቀራቸው።ከወራት በኋላ ወይ ሌላ
👍4😁41
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_ሁለት


#በሜሪ_ፈለቀ


..."ያምሃል እንዴ?” ብዬው ተነስቼ አጠገቡ ያለ መኪና ላይ ደገፍ አልኩ።

"በእርግጥ ያመኛል። ቆየሁ ካመመኝ፡፡ ሶስት ዓመት!!" በእጁ የተገባደደ የውስኪ ጠርሙስ እንደያዘ ከመኪናው ወጣ፡፡
ኤፍሬም ነው! የድርጅቱ ሀላፊ ተብሎ ለታዳሚው ገለፃ ሲጠርቅ አይቼው ነበር።

"ሰክረሃል::" አልኩት መንገዳገዱን እና አፉ መተሳሰሩን አይቼ።

“ሰክሬያለሁ፡፡ ነገር አስክሮኛል፡፡ ጥንቅቅ
ብዬ ከሰከርኩ ሶስት ዓመቴ!" እርሱ መድረክ ላይ ፅዋ ሲያነሳለት እንዳየሁት አስማማው ደግሞ እንዳስፋልኝ ከሶስት ዓመት በፊት ከመሞቷ አስቀድሞ እንደነፍሱ የሚያፈቅራት ሚስቱ የድርጅቱ
ምክትል አስተዳደር ነበረች። እየደጋገመ የሚያሰምረው ሶስት ዓመት የሚስቱ ሞት ጊዜ መሆኑ ወዲያው ስለገባኝ ዝምታን
መረጥኩ፡፡ መኪናው ውስጥ ገብቶ ለመንዳት ሲሞክር ሁለቴ ከግንድ ጋር ተጋጨ፡፡ በሶስተኛው የተጋጨው ከመኪና ጋር ስለነበር አካባቢው በመኪና ጩኸት ተደበላለቀ።ምን አስቤ ነበር? ዘልዬ መኪናውን ከፈትኩና እንዲጠጋልኝ ነገርኩት።

"ምን ልትሆኚ?" አለኝ:: የመኪናዎቹን እሪታ ተከትሎ እየተሯሯጡ የሚመጡትን
የሆቴሉን ጠባቂዎች ሲያይ ለመጠጋት እያመነታ።

"ላድርስህ? ፓሊስ ጣቢያ ታድራለህ?" መለስኩለት።

እንግዲህ ኤፍሬምን ያወቅኩት እንዲህ ነው።እቤቱ ካደረስኩት በኋላ ከኋላ ወንበር ያስቀመጥኩት ቦርሳዬን ሲያቀብለኝ ቦርሳው ተበተነ፡፡ በርዬ (ወንድሜ ነው) ግዢ ያለኝ መፅሀፍ መኪናው ውስጥ መውደቁን አላየሁም ነበር። እቤቴ ስደርስ በርዬ የጠየቀኝ

የመጀመሪያ ጥያቄ መፅሀፉን ነው:: እንደጣልኩትም የገባኝ የዛኔ ነው።

በርዬ

በረከት ነው:: ታላቅ ወንድሜ ነው:: መራመድም መናገርም አይችልም:: በዊልቸር ይሄዳል፣ በምልክት ይናገራል ወይም ሀሳቡን በፅሁፍ ይገልፃል፡፡ ከኔ ጋር ግን ይሄን ሁሉ ማድረግ ሳይጠበቅበት በዓይኑ ብቻ እረዳዋለሁ። በዛ መፅሀፍ ሰበብ በነገታው ኤፍሬም ቢሮ ተገኘሁ:: መፅሀፉን እያገላበጠ እየሳመ እንባ ቀረሽ አኳኋን ሲሆን ከመደንገጥ በላይ ተሰምቶኛል።

"ከየት አገኘሽው? ፈልጌ ያጣሁት ስራዋ ነው::" አለኝ።

“የወንድሜ የመፅሀፍ ደንበኛ ነው ያገኘልኝ። ገበያ ላይ የለም::"
መለስኩለት፡፡

የምትፈልጊውን ያህል ገንዘብ ልስጥሽ እና መፅሀፉን ተይልኝ::" አለኝ፡፡

እሺ አትልማ?"

ኸረ እሺ እላለሁ::" ሲለኝ ሳቄ መጣ።

እናንተ ሀብታሞች ግን በገንዘብ ልዋጭ የማታገኙት ነገር እንደሌለ ነው አይደል የምታስቡት?" አልኩት፡፡

“እንደዛ ማለቴ እንኳን አልነበረም::” አለ የውስጡ ቅሬታ ፊቱ ላይ እያሳበቀ፡፡

"ብትልስ ማን ይሰማሃል?"

ጠረጴዛው ላይ ያለውን የሚስቱን ፎቶ አዙሮ አሳየኝ፡፡ መፅሀፉ የሟች ሚስቱ ከመጋባታቸው በፊት የፃፈችው የመጀመሪያ ድርሰቷ ነው፡፡ እሷ በህይወት እያለች በድጋሚ ሊያሳትሙት እቅድ እንደነበራቸውና በቸልተኝነቱ ምንም ቅጂ ለራሱ እንዳላስቀረ ነገረኝ፡፡ ስነግራችሁ በጣም ከማዘኔ የተነሳ መፅሀፉን ትቼለት ልሄድ ሁሉ አስቤ ነበር፡፡ ማታ በመኪና ሳደርሰው መንገዱን ሙሉ ከሶስት ዓመት በፊት ስለሞተችው ሚስቱ ነበር ሲያወራልኝ የነበረው። ለበርዬ መፅሀፉን ስሰጠው የተከሰተውን ነገር ነገርኩት:: ስላልሰጠሁት እየተቆጣኝ መልሼ መፅሀፉን ለኤፍሬም እንድሰጠው ለመነኝ፡፡ ቢሮው ድጋሚ ተከሰትኩ ማለት አይደል? መፅሀፉን ስሰጠው ወንበሩ ላይ ቁጭ ብድግ ሰራ። የሚለው ጠፋው።

"በነፃማ አልሰጠሁህም።" አልኩት።

"የፈለግሽውን ያህል... ......

"የክፍያውን ይዘትና መጠን ምሳ እየጋበዝከኝ እንደራደራለን።"

ስለው ፊቱን አፈሰሰው።

"ምሳው በሌላ ነገር ይቀየርልኝ::"

እንደውም ምሳ ሰዓት ደርሷል ስለው ትናንት እንዳደረገው የተተለተለ ቁምጣዬንና ሰፊ ሸሚዜን አየው።ግድ የለሽ አለባበሴ እንዳልተመቸው ስለገባኝ ሳቄ መጣ፡፡

ለምሳ ተያይዘን ስንወጣ አቶ አያሌውና የኤፍሬም እናት(ቄንጠኛ አለባበስ የምትለብስ ዘመናዊ ሴት ናት፡፡) ወደ ህንፃው ሲገቡ ተገናኘን፡፡ ጓደኛው
እንደሆንኩኝ አስተዋወቃቸው።

"በእረፍት ጊዜህ የት ታሳልፋለህ?" አልኩት ምግብ አዝዘን እስኪቀርብ እየጠበቅን፡፡

"የመቃብር ቦታ!!"

"እየቀለድክ?"

“እየቀለድኩ አይደለም:: የሊዲያ መቃብር ቦታ ነው እረፍት የሚስማኝ፡፡” ሊዲያ ሟች ሚስቱ ናት፡፡

ምሳ ልንበላ (እኔ እየበላሁ እሱ እያወራ ማለት ይቀላል)
የተቀመጥነውን አንድ ሰዓት ከአስራ ስድስት ደቂቃ አንድ ሰዓት ከሰባት ደቂቃ ስላሊዲያ ሲያወራ፣ ስምንቱን ደቂቃ ሲጎርስና ሲያላምጥ፣የቀረውን አንድ ደቂቃ በረዥሙ ተንፍሶ ተለያየን መፅሃፉን ልሰጠው ብንገናኝም ከአስማማው ጋር
ስለተለያየን ተረኛ አሰሪዬ ሊሆን
እንደሚችል አሰብኩ፡፡ ቢሆንም
ከማውቃቸው ሀብታሞች የተለየ ነገር ስለሆነ የተለየ መንገድ ተጠቅሜ ካልሆነ በቀር ይሄን ጋግርታም ሰው መጥበስ ቀላል እንደማይሆን ገብቶኛል።ከትንፋሹ ጋር ስሟን የሚተነፍሰውን ሟች ሚስቱን ሀዘን ማደብዘዝ የባሰ ከባድ መሆኑም ገብቶኛል፡፡ ቢሆንም መሞከሩ አይከፋም! ሙከራዬን ለመጀመር በቀናት
ልዩነት ለሶስተኛ ጊዜ የቢሮ ስርዓት ያልተከተለ አለባበሴን በሳቅና በሰለቸው ፊት የሚያጉረጠርጡ ሰራተኞቹን አልፌ
ኤፍሬም ቢሮ ገባሁ።

"አንተ ሴክሬተሪክ ግን አካሏ ሁሉ ከምላስ ነው እንዴ የተሰራው? ያለቀጠሮ፣ ያለ አለባበስ...... ቂቂ ቢሪቂቂ ስትል ነው
አልፌያት የገባሁት::" አንደኛው ወንበር ላይ ተቀመጥኩ፡፡

ደህና አደርሽ....?" አለኝ ስሜን ከሰላምታው አስከትሎ ሊጠራ ከጭንቅላቱ ጓዳ እየበረበረ።

"ረቂቅ...."

እሺ ረቂቅ ምን ልታዘዝ?" በተቀመጠበት በትህትና አናገረኝ፡፡

“ዝም ብዬ ሳስበው በአንድ ምሳ መፅሀፍ መቀየር የሚያዋጣኝ አልመሰለኝም::" ምን እንደምለው እቅድ አልነበረኝም።

"ምሳ አብሮ መብላት አይሁን እንጂ የጠየቅሽኝን እከፍላለሁ"

እራትም ቢሆን ይመቸኛል::" መለስኩለት፡፡ ፍቅፍቅ ብሎ ሳቀ።

"በቁም ነገር ምን ላድርግልሽ?" ትህትናው ማስደንገጡ!

"እራት ልጋብዝህ:: ሂሳብ ክፈል::"

ቀልድ አይፈጅም:: አሁንም ሳቀ።

"በቃ?" አለኝ ሳቁ ከፊቱ ሳይጠፋ፡፡

ፈገግታህ ከደመናት መሀል ብቅ ያለች ፀሀይን ያስንቃል::"

"ፈዛዛ ነው እንደማለት?"

"ሀዘንን ይገፋል እንደማለት" ይሄ የማማለያ ጥበቤ አልነበረም።ከልቤ ነው:: የሚስቱን ፎቶ አይቶ ፈገግ አለ እና "እሺ በሁለት ነገር ከተስማማን እራት እንበላለን።" አለኝ።

"አንዱ መቼም ህጋዊ ልብስ ልበሺ የሚል መሆን አለበት።ከአስተያየቱ የምለብሳቸው አለባበሶች እንደሚዘገንነው ገብቶኛል።

“እሱን ሶስተኛ አድርጊው::" አለኝ እየሳቀ፡፡

"ሁለቱን ንገረኝ፡፡"

"አንደኛ በቀደም ለምሳ መጣሽ፤ ዛሬ ደግሞ ለእራት፤ ነገ ለቁርስ እንደማትመለሺ እርግጠኛ አድርጊኝ፡፡ ሁለተኛ እና ዋነኛው ነገር እባክሽ በምንም ምክንያት ቢሮዬ ተመልሰሽ አትምጪ"
እሱን እራት እየጋበዝከኝ እንደራደራለን።"

ቀለል ያለ ቀሚስ ለብሼ ቦታውና የምግብ ምርጫው በኔ ተወስኖ
ከኤፍሬም ጋር እራት ታደመን፡፡ በአብዛኛው ምን እንዳወራን ባልነግራችሁም ታውቁት የለ?ሊዲያ! በርዬ ስለ ሊዲያ መፅሃፎች የተወሰነ ነገር አውርቶኝ ስለነበረ ትንሽም ቢሆን ስሜት የሚሰጥ መግባባት ተግባባን!

መፅሀፎቿን አንብበሻቸዋል ማለት ነው?
እስቲ ስለእርሷ የምታስቢውን ንገሪኝ" አለኝ በሚያንሰፈስፍ ጉጉት፡፡ አንብቤው
ቢሆንና ባወራው ተመኘሁ::

እውይ እኔ እንኳን መፅሃፍ ማንበብ አልወድም! ወንድሜ ነው
የሚያነበው: የሚቀረው መፅሃፍ የለም:: ሁሉንም መፅሃፎቿን
👍5
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_ሶስት


#በሜሪ_ፈለቀ

"ስለዚህ ቢያንስ አንድ ጊዜ ወይ ቢሮህ እመጣለሁ ወይ ቁርስ እንበላለና"

በእርግጥ ለምን እንደሆነ በማይገባኝ ምክንያት ወንድ ልጅ ሲናደድ እና እልህ ሲይዘው ደስ ይለኛል። ኤፍሬምን ግን
ማናደድ ፈልጌ አልነበረም።ምርጫ ስላልሰጠኝ እንጂ፡፡ ይኸው ነወ። በሚቀጥለው ቀን የማላውቀውን ስልክ ጥሪ አስተናገድኩ፡፡አያሌው! ኤፍሬም ሚስቱ በሞተች በሶስት ዓመት
ውስጥ ቁጭ ብሎ አብሯት ምሳ እራት የበላ፣ ፈገግ ሲልላት የታየ ብቸኛዋ ሴት መሆኔን ነገረኝ፡፡

አሁን በአንድ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪ የተለየ ምክንያት ኤፍሬምን ለመጥበስ ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አድርጌ መሞከር
ስላለብኝ አጭር ጅንስ ቁምጣ ወደ አንድ ጎኑ ባዘነበለ ሰፊ አላባሽ፣ በሸራ ጫማ አድርጌ ኤፍሬም ቢሮ በድጋሚ መጣሁላችሁ።
ሃሃሃ እንኳን ኤፍሬም እናንተ እንኳን ኤጭ! አላችሁ አይደል?
ቅዳሜ ስለነበር ማንም ይኖራል ብዬ አልገመትኩም ነበር።ፀሀፊው የሆነ ነገር እየተወራጨች ብላኛለች “ኢር ፎን
ሰክቻለሁ። አልፌያት ገባሁ። ኤፍሬም
ስብስባ ላይ ነው:: ከአያሌው ጋር ተያየን፡፡

"ይቅርታ!! ስትጨርስ እጠብቅሃለሁ::” ብዬው ወጣሁ።

ምናልባትም ከግማሽ ሰዓት በኋላ ስብሰባቸው አልቆ ሲወጡ ፀሃፊውን ጨምሮ እዛ ከነበሩት ሰራተኞቹ ጋር ከዚህ በፊት በግልምጫ እንዳልሸኙኝ ሁሉ እንደሚተዋወቅ ሰው እየቀደድን
ስለነበር መውጣታቸውን ያወቅኩት ሰራተኞቹ እየተወለካከፉ ወደየስራቸው ሲዞሩ ነበር፡

“ምን እያደረግሽ ነው? ይሄ ለእኔ ከስራ ቦታዬ በላይ ነው።ልረበሽበት አልፈልግም::” አለኝ ኤፍሬም ቢሮው እንደገባን እየተበሳጨ።

በቅዳሜ ምድር ያንተ ቢሮ መግባት ሲገርመኝ ሰራቸኞቹን ሁሉ ትጠገርራቸዋለህ?"

"ረቂቅ ቁርስ እንብላ ልትዪኝ አይደለም አይደል የመጣሽው?"

ኸረ አይደለም፡፡ ቅዳሜህን አውሰኝ ልልህ አስቤ ነው አመጣጤስ፡፡ ቁርስ ካልበላህ ግን እሱንም ያካትታል::"

'ምን እያሰብሽ ነው?"

'ምን እንደምናደርግበት? እርግጠኛ አይደለሁም ግን ውለህ
እንደማታውቀው አይነት አዋዋል አስውልሃለሁ:: እና ትወደዋለህ አታስብ፡፡” መለስኩለት:: አውቄ ስጠም እንጂ ምን
እንደጠየቀኝ ገብቶኛል:: እየተበሰጫጨ ኮቱን አንስቶ እየደረበ ለመሄድ ተሰናዳ፡፡

ረቂቅ ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም። ነይ መፅሀፉን እሰጥሻለሁ።" አለኝ፡፡

ሆ! በአንድ መፅሀፍ ጦስ አሳሬን ልጨልጥ?" መኪናውን እየነዳ
ብቻውን ያወራል፡፡ ሳቄ መጥቷል። መበሳጨቱ ደግሞ ሲያምር፡፡

'ሀያ አራት ሰዓትህን ብቻ ስጠኝ፡፡ ሙሉ ቅዳሜን" ደጋግሜ እጠይቀዋለሁ። አይመልስልኝም።ብቻውን ያወራል። ሆ! ይላል እየደጋገመ።

ቁርስ መብላት እፈልጋለሁ።" አልኩት ለሶስተኛ ጊዜ፡፡

"ቢሮ ሰዎች ይጠብቁኛል፡፡ መፅሀፉን ይዘሽ ስንለያይ ትበያለሽ አለኝ በመጨረሻ።

"ሂሳብ ማን ሊከፍል? ታካብዳለህ እንዴ ልትፋታኝ አይደል?"

ከፈለግከሽ የቁርስሽን ሂሳብ እሰጥሻለሁ።" ንዴት ድምፁን እያጎረነነው።

"ያለአጃቢ? ደስ አይልም! አንተ ግን አንድ ቀን ብዙ መሆኑ ነው? እንኳን ለሰው ለእንቅልፍ ይሰጥ የለ? ብቻዬን
እለፈልፋለሁ። አይመልስልኝም። የመኪናውን በር ከፈትኩት እና አንድ እግሬን አስወጣሁ ቀጥዬ "ልወርድ ነው።" አልኩት።
መኪናውን ሲጢጢጥ አድርጎ አቆመው።

"አነቅከኝ::" አልኩት እኔ ዱለቴን እየበላሁ እሱ እያየኝ፡፡ ግራ ገብቶት አየኝ፡፡ የምሬን ነው ከመጠቅለሌ ጀምሮ እስከምጎርስ
በዓይኑ ምግቡን ይሸኘዋል፡፡

ከምግቡ ጋር እኮ አብረህ ገባህ!"

"አስቤው አልነበረም::" አለኝ ንዴቱ በረድ እያለለት።

"የቁርስ ምርጫህ ምንድነው?"

"የምግብ ምርጫ የለኝም::

"የቀለም ምርጫ ግን ይኖርሃል።"

"የለኝም::"


"እሺ ኮከብህ ምንድነው?"

"አላውቀውም::"

"ቆይ እሺ ጎደኛ ምናምን እንኳን የለህም?"

"ከሊዲያ ሌላ ጓደኛ ኖሮኝ አያውቅም። ጓደኝነት ላይ እንኳን ጥሩ ነኝ ብዬ አላስብም::" አለኝ በቁርጥሽን እወቂ አይነት፡፡

"እሱን እኔ ላረጋግጥልህ እችላለሁ:: አስቀያሚ ጓደኛ ነህ!"

ውጪ እንድጠብቀው ቢነግረኝም እስከመኝታ ቤቱ ተከተልኩት::
መፅሀፉን ከሰጠኝ በኋላም ምንም እንዳልነካ ቢያስጠነቅቀኝም ወደ ሳሎን ገባሁ።ሶፋው ላይ ከተደረደሩት አሻንጉሊቶች መሀል አንዱን ከማንሳቴ ኤፍሬም ከየት መጣ ሳልለው መነጨቀኝ እና ቦታው መለሰው።አስደንግጦኛል።

ይቅርታ!" አለኝ መልሶ።

የእርሷ እጅ፣ የእርሷ ጠረን፣ የእርሷ ምስል...... ሁሉም ነገር እሷ ራሱ ህያው ሆና ያለችው እዚህ ቤት ነው።እዚህ
ቤት ፍቅሬ አልሞተችም።የሳቅነው፣ ያለቀስነው፣ የተላፋነው፣የተጣላነው. እዚህ ቤት ነው።ሁሉም ነገር እንደ ዛሬ ትኩስ ህልውና አለው።እሷ ከሞተች በኋላ የቤቱቀለም አልተቀየረም።
የቤቱ እቃ አልተቀየረም።ሁሉም እሷ እንዳስቀመጠችው ነው።ማንም እዚህ ቤት ሲገባ ጠረኗን የተሻማኝ፣ ትዝታዋን የተጋራኝ ስለሚመስለኝ ለማንም ሰው እንዲገባ ፈቅጄ አላውቅም።" አለኝ
በተሰበረ ልብ፡፡

በቋሚነት የሚኖረው እናቱ ቤት መሆኑን ሚስቱ ስትናፍቀውና ሲከፋው እዚህ ቤት እንደሚመጣ ነገረኝ፡፡ ከልቤ አዘንኩለት ብቻ አደለም ሀዘኑን አጋባብኝ።

ቢሮ ሰዎች ቀጥሪያለሁ። እንሂድ" አለኝ የእኔን ተረጋግቶ የመሬቱ ምንጣፍ ላይ መቀመጥ ሲያይ እንድወጣለት ፈልጎ፡፡

"ሁሌም ዛሬ ላይ ቆመህ ሁለት ምርጫ አለህ:: ትናንት ወይም ነገ፤ ትዝታ ወይም ተስፋ!” አልኩት፡፡ አንዳንዴ እንደ አዋቂ ያደርገኝ የለ? የበርዬ እህት አይደለሁ?

"ከሊዲያ ጋር የኖርኳቸው አምስት ዓመታት ትዝታ ብቻ አይደሉም።ነፍስ ያላቸው ስንቆች ናቸው።"መለሰልኝ።

"የሚወዱትን ማጣት ምን ያህል እንደሚከብድ አውቃለሁ::"

"የእኔን ያህል አይገባሽም::"

ሁላችንም የራሳችን ስቃይ ሌላውን ያልጎበኘ ህመም እንዳለው ነው የሚገባን፡፡" እያወራሁት ከሱ በባሰ እኔ ታመምኩ። እንባዬ መጣ፡፡

"ገና በዘጠኝ ዓመቴ አባቴ አንገቱን በገመድ አንጠልጥሎ ሲሞት
በዓይኔ አይቼዋለሁ::" ይሄን ከተናገርኩ በኋላ ከኤፍሬም መለየት አማረኝ፡፡ተነስቼ መኪናው ውስጥ ገባሁ፡፡ ምንም
ሳንነጋገር ብዙ ተጓዝን: የረቀቀችው ረቂቅ ይህቺ ነኝ፡፡እንደጎርፍ የሚግተለተል ሳቅና ልፍለፋዬ በአንዴ የሚደፈርስ ትንሽ ቢራቢሮ፡፡

"እዚህጋ አውርደኝ።" አልኩ ድንገት ማጨስ ስላማረኝ።አቆመልኝ፡፡ መረበሼ ረብሾታል፡፡ዝምታዬ ጨንቆታል።
ያስቀመጥኩትን መፅሀፍ አቀበለኝ፡፡

"ያንተ ይሁን። በመፅሀፍ አሳብቤም ቢሮ አልመጣብህም።"ያልኩት እውነቴን ነው:: ፊትለፊት ያገኘሁት ሱቅ ገብቼ
ሲጋራዬን እዛው መማግ ጀመርኩ።

የማስታውሳቸው የልጅነት ቀኖቼ ላይ ሁሉም ልክ ነበር፡፡ እማዬ ደከመኝ ሳትል በምቾት የምታኖረን ልጆቿ እኔና በርዬ

አባታችን ልጆቹን እና ሚስቱን የሚወድ ጎበዝ ሰካራም፧ በርዬ ከውልደቱ ጀምሮ መራመድም መናገርም የማይችል ታላቅ
ወንድሜ፤ እማዬ ሁሉንም ምንም ጉድለት እንደሌለ፣ በርዬም ጤነኛ፣ ባሏም በየእለቱ የማይሰክር እና ሁሉ እንደሞላለት ታስመስለው ነበር፡፡ ልጅነቴ እንዳላስተውል አድርጎኝ ይሆን
የጎደለ ስንጥር የኑሮ ክፍተት አይታየኝም ነበር፡፡ በእርግጥ ማገናዘብ የምችልበት እድሜዬ ላይም ቢሆን ቅንጡ ኑሮ
ባይባልም የተደላደለ ነበር ኑሯችን፡፡ አንድ ቀን ግን ልክነት አበቃ:: እማዬ አንድ ቅዳሜ በርዬንና እኔን እንዲጠብቅ ለአባዬ
ጥላለት ሸመታ ወደ ገበያ ሄደች፡፡ በምን አጋጣሚ ዘወር እንዳለ በርዬ እየተሳበ የተለኮሰ ሲሊንደር አጠገብ ደርሶ እሳት እግሩን አቃጠለው፡፡ በርዬ በአባዬ ቸልተኝነት እንዳልተቃጠለ እኔ ምስክሩ ነበርኩ፡፡ እኔና አባዬ የምናደርገው
👍2🔥21
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_አራት


#በሜሪ_ፈለቀ

እማዬ የተወሰነውን ለበርዬ መታከሚያ ገንዘብ ቤታችንን አስይዛ ከባንክ እንደተበደረች ያወቅኩት። በርዩንም ከብዙ ገንዘብ ግፍገፋ በኋላ ምንም ሊረዱት ባይችሉም የማሰብ ክህሎቱ ከጤነኛ ሰው በብዙ የላቀ በመሆኑ መማሩ መጨረሻውን እንዲቀይርለት
አክስቴና ባሏ እዛው ትምህርት አስጀመሩት፡፡

የተፈጠረውን ሁሉ ተቀብለን መኖር በጀመርንበት ሰዓት ግን የባሰ ምስቅልቅል ተተካ፡፡ አስረኛ ክፍል ማትሪክ ተፈትኜ
ውጤት መጣብኝ (ለመፈተን ያህል
እንጂ አልሰራሁም፡፡) እማዬ ብቻ በምታውቀው ዓመታት ያስቆጠረ
ታሪክ በርዬን ውጪ ሀገር ልካ ለማሳከሚያ ብር አንሷት ከምትሰራበት መስሪያ ቤት ባነሳችው ገንዘብ ጦስ የተነሳ ከዓመታት በኋላ ተረጋግጦ የመስሪያ ቤቱን ገንዘብ በመመዝበር
የአስር ዓመት እስራት ተፈርዶባት ዘብጥያ ወረደች፡፡ ይሄኔን የተፈጠረውን ሲያውቅ በርዬ ከውጪ ሀገር ትምህርቱን ትቶ
መጣ። እንዳንዴ እሱ ባይመለስ ኖሮ ብቻዬን ምን ዓይነት ቀንኀሊኖረኝ እንደሚችል ሳስብ ደስታ የራቀው ኑሮ የሚኖረኝ የነበረ ይመስለኛል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በተለይ መኖር ቋጥኝ መግፋት
የሚሆንብኝ ሰዓት ላይ እሱ ባይኖር አንድ ሀሳብ ይቀልልኝ እንደነበር አስባለሁ፡፡ ወዲያው ግን ይሄን ማሰቤንም እንዲህ
በማሰቤ ራሴንም እጠላዋለሁ፡፡

የአስራ ሰባት ዓመት ሴት፣ ወጣት፤ በአምስት ዓመት የሚበልጣት በዊልቸር የሚገፋ ወንድም ያላት፣አባቷ የሞተባት፣ እናቷ የታሰረችባት ረቂቅ ሆንኩ፡፡

“ቅዳሜ የቀረውን አስራ ስድስት ሰዓት ምን በመስራት እንደምንጀምረው ምሳ እየበላን እንደራደር?" አለኝ ኤፍሬም
አጠገቤ ደርሶ:: አላመንኩትም፡፡ ደስ ያለኝ በየትኛው ምክንያት እንደሆነ ሳይገባኝ ተጠመጠምኩበት፡፡ የለበሰውን ሙሉ
ልብስ ቡቲክ ገብተን አስቀይሬው ነበር ቀኑን የጀመርነው::
እነዚህ ለቅዳሜ ያፀደቅናቸው ህጎች ናቸው። ስልክ መዝጋት፣
ስለሊዲያ አለማውራት፣ ስለአባቴ አለመጠየቅ፣ ከዛሬዋ ቅዳሜ
ውጪ ሌላ ቀን የለም ብሎ ማመን፡ ትናንትንም ነገንም ረስቶ ደስ መሰኘት፡፡ ከላይ የዘረዘርኩላችሁ ለሁለት ያፀደቅነውን ነው።ለብቻዬ ግን ሊረሳው የማይችለው ቀን ልሰጠው ምያለሁ።

“ማጨስ እንዴት ጀመርሽ? በጓደኛ ተፅኖ?"

"አይደለም። ምነው? ሴት ልጅ ስታጨስ ውበቷ ይቀንስብኛል ከሚሉት ጎራ ነህ?"

ላይ ተቀምጦ እስክነቃ እየጠበቀኝ ነበር፡፡

"እኔ እንኳን ከማንነት ጋር አላያይዘውም፡፡ ከጤና አንፃር ግን ባታደርጊው እመርጣለሁ::" አለኝ እና በድርድር ቅዳሜ
እስኪያልቅ ሶስት ሲጋራ ብቻ ላጨስ
ተስማማን፡፡ እኔ የማውቃቸው አብዛኛው ባለገንዘብ ወንዶች ገበጣ ሲጫወቱ እንዳላደጉ ሆቢህ ምንድነው?” ሲባሉ ጎልፍ፣ የበረዶ ሸርተቴ፣ራግቢ ምናምን ማለት ይዳዳቸዋል።ኤፍሬም ከጠረጴዛ ቴኒስ እና ከሊዲያ ውጪ የሚወደውን ነገር እንኳን አያውቀውም፡፡ቅዳሜን አሰከርናት። ቅዳሜን አሳበድናት፡፡ ቅዳሜ ምትሀት ነገር ነበረች።

እሁድ ጠዋት ሆቴል አልጋ ላይ ስነቃ ኤፍሬም ተነስቶ ወንበር ላይ ተቀምጦ እስክነቃ እየጠበቀኝ ነበር።መፀፀቱ እንዲገባኝ ብዙ ሊነግረኝ አልተገባውም።
ፀጥታው ብዙ እሪታ ነበረው።ወትሮም ፀጥታ እጠላለሁ።በጆሮዬ የምሰማው ድምፅ ሲጠፋ የምትጮህ ነፍሴን መስማት እፈራለሁ እስካልተኛሁ መለፍለፍ እመርጣለሁ።ዛሬ ግን ዝም አልኩ። ለምንድነው የምከተለው?ያለምንም ቃል ልውውጥ የሚያደርገውን የማደርገው ለምንድነው?

ለምንድነው? ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተጣጥቤ ለባበስኩ።ቁርስ
ቀርቦ እየበላን ፀጥታው ጮኸብኝ።

"ብሎን እንደጠፋበት ሰዓት ሰሪ አደፈጥን እኮ!" አልኩት።ሁለታችንም ምግቡ ላይ አቀረቀርን እንጂ በተገቢው እየተመገብን አልነበረም።

"አንቺ ግን ምንም አይመስልሽም አይደል?" አለኝ በትዝብት አይነት።

"የምልህ ግራ ገብቶኝ እንጂ ፀፀት ላይ እንደጣድኩህ ገብቶኛል።በሆነ ነገር ማለቃቀስ መፍትሄ ያመጣል ብዬ ስለማላስብ አላላዝንም::" ያልኩት ከልቤ እንጂ እየኮነንኩት አልነበረም።
አልመለሰልኝም ፀጥ አለኝ።

"መጥፎ እንዲሰማህ ስላደረግኩህ ይቅርታ በጣም!" አልኩት።አሁንም አልመለሰልኝም። ልሂድ?' አላልኩትም:: ምንድነው ሀሳብሽ?” አላለኝም:: መኪናውን ነድቶ መቃብር ስፍራ ደረስን፡፡
ቃል ወጣው፡፡

"መጣሁ!"

ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ መታገስ አቃተኝ። ተከተልኩት።አላየኝም:: ያየሁት ነገር የምቋቋመው አይነት አልነበረም፡፡
እንደምትሰማው ሁሉ፣ እንደምታየው ሁሉ፤ እንደምታባብለው ሁሉ መቃብሯ ላይ አቅሉን እየሳተ ያወራል፤ ያለቅሳል፤
ይጠይቃል፤ ይመልሳል። ብዙም እርምጃ ባልራቀ ርቀት በእንባዬ አጅበዋለሁ። የሷ የነበረውን ገላ ለሌላ ሰው ስላጋራባት ይቅርታ ይለምናታል፣ተነስታ እንድትወቅሰውና የፀፀት ወላፈኑ
እንዲበርድ ይማፀናታል፡፡ እግሬን አላዘዝኩትም:: በደመ ነፍስ
እየተጓዝኩ ታክሲ ይዤ እቤቴ ደረስኩ፡፡ ማጨስ አይደለም ያማረኝ ማልቀስ!! በርዬ እንዳየኝ ገብቶታል። እቅፉን ዘረጋልኝ።እንደ ህፃን ድምፅ አውጥቼ አለቀስኩ። ለበርዬ የሆነውን ሁሉ ነገርኩት።ቀጥዬ ያደረኩት አያሌውን ማግኘት ነበር።

ኤፍሬምን ካሁን በኋላ ላገኘው አልፈልግም።" አልኩት ለአያሌው ደውዬ እንዳገኘሁት።

ማንም በሱ ቦታ ቢሆን በመጀመርያ ቀን ሊሰማው የሚችለው እንደዚህ ነው።"

"አይደለም።" መለስኩለት።

"እየገፋሽ ያለሽው ገንዘብ ይታይሻል ረቂቅ? እንደ ' ቦሊ ቦል' ከአንዱ ወንድ እጅ ወደሌላው መንጠር አልሰለቸሽም? " እውነቱን ነው ሰልችቶኛል።ነገር ግን ኤፍሬም የሚስቱ መቃብር ላይ የሆነው መሆን በገንዘብ ለመደራደር ይከብዳል። በተቀመጠበት ትቼው ወደቤቴ ተመለስኩ።

ለቀናት እቤት አርፌ ተቀመጥኩ።እንኳን ለእማዬ የማስረው ስንቅ እቤት ውስጥ እንኳን የሚበስል ነገር እያለቀብኝ ነው።ባንክ ያለችኝን አራት መቶ ብር አውጥቼ ምን ምን እንደማደረግ አቀድኩ። አስማማው ጋር ወይም አንዱ በፊት የማውቀው ሰው ጋር ልደውል ባስብም ሳስበው ገና ሰለቸኝ። ሁሌ ችግር ማውራት እንኳን የሚሰሙኝን ወንዶች እኔን እንዴት ወንድ እና ገንዘብ ዘውድና ጎፈር እንደሆኑብኝ ልንገራችሁ።የምነግራችሁ ጅማሬዬን እንጂ ሰበቤን አይደለም። ምክንያቱም ወንድን ለገንዘቡ ብላ የምትተኛ ከንቱ ለመሆን የትኛውም ሰበብ እና ምክንያት ሚዛን የሚደፋ አይደለም።

#ያኔ

አባቷ የሞተባት፣ እናቷ ስንቅ የሚያስፈልጋት እስረኛ፣ ወንድሟ
መፅሀፍ ማሳተም የሚመኝ በዊልቸር ሂያጅ ዲዳ የሆነባት ረቂቅን የሆንኩ ጊዜ፤ አንድ ሆቴል አስተናጋጅ ሆኜ በማገኛት
ገንዘብ ልንኖር ስዳክር በርዬ ሲያለቅስ ያየሁት ጊዜ፤ በርዬ ስራ ፍለጋ በፀሀይ እጁ እስኪርድ ዊልቸሩን እየገፋ ውሎ እጁ ተልጦ ያየሁት ጊዜ ፤ በርዬ መፅሀፉን ሊያሳትም አሳታሚ ፍለጋ ሲዞር ዉሎ አፍንጫውን ነስሮት የገባ ጊዜ እንደምንም አጠራቅሜ የበርዬን መፅሀፍ ላሳትምለት ቃል የገባሁ ጊዜ እማዬ ልንጠይቃት ስንሄድ እያለቀስኩ ልጆቼን አላይም ብላ አልወጣም ያለችን ጊዜ ፤ እማዬ ሲጋራ እንዳስገባላት የጠየቀችኝ
ጊዜ ፤ የወደደኝ የመሰለኝ ፍቅረኛዬን
ከሌላ ሴት ጋር ያየሁት ጊዜ ከእነዚህ በአንዱ ጊዜ ወይም በሁሉም ጊዜ ምንም ለማድረግ ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ ከአንድ ሀብታም ባለሚስት ጋር ሆቴል ሲመጣ ተቀራረብን። ባለትዳር መሆኑን ሳይደብቀኝ ቁንጅናዬ እንዳማለለው ነገረኝ፡ ስለሰማሁት የታክሲ አምስት መቶ ብር (የመስተንግዶ ደሞዜን) ሰጠኝ፡፡ ስለተሳምኩለት የወር አስቤዛ
አደረገልኝ፡፡ ስለወጣሁለት የቸገረኝን እንድነግረው ሊያሟላልኝ ማለልኝ። የጠገበኝ ሲመስለው ሄደ:: ሌላ ተመሳሳይ ሰው ለመድኩ። በርዬ መማር የሚፈልገውን ኮምፒውተር ሳይንስ
መማር ጀመረ።
👍7🔥1
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_አምስት


#በሜሪ_ፈለቀ

እኔ ወደ ህይወቱ ብቅ ማለቴን አክሎ ነገረኝ።

እናቱ በግልፅ “ስራህን ከቁስልህ መደበቂያ አድርገኸዋል። ያንተን
ድርቅናና የሟች ሚስትህን ትዝታ ማስታመም እየሰለቸኝ ነው::"
ብለውት ልቡ መድቀቁን ሲነግረኝ ግን ያቺ ከቀናት በፊት ሊያያት እንደማይፈልግ ሲሆንባት ለነበረችው ረቂቅ እየተናገረ አይመስልም።

"በዚህ ከቀጠልኩ እነርሱ እንደሚፈሩት ከዓመታት በኋላ የድርጅቱንም ሆነ የቤተሰባችንን ህልውና አደጋ ላይ ልጥለው እንደምችል ማሰቤ ይባስ ውጥንቅጥ ውስጥ ይከተኛል::" ሲለኝ
ይሄን ሀሳብ ለጥዝጠዛ ለማመቻቸት ወሳኙ ጊዜ መሆኑን አሳሰበኝ።

"ጥቅሙ የሚያመዝን ከሆነ ለምን በቤተሰቦችህ ሀሳብ አትስማማም?"

"አንደኛ አሳማኝ አይደለም፡፡ በግሌ ከማስተዳድራቸው ዘርፎች
በላይ ፋብሪካው ትርፋማ እየሆነ በመጣበት ወቅት በተለይ የእማዬ እንዲሸጥ መወትወት አልዋጥልህ ነው ያለኝ፡፡ ሁለተኛኀአባዬ ያስረከበኝን ምንም
ነገር ማብዛት እንጂ ማጉደል አልፈልግም።

መቃብሩ ጋር ጥዬው የሄድኩ ዕለት ራሱን ስቶ ሀኪም ቤት ገብቶ ነበር፡፡ ማረፍ እንዳለበት በሀኪም ስለታዘዘ ለወንድሙ
ውክልና ፈርሞለት እረፍት መሆኑን እና ላይደውልልኝ ከራሱ ጋር ብዙ ቢሟገትም ቀኖቹ አላልቅ ብለውት አማራጭ ሲያጣ
እነደደወለልኝ ሳይደብቅ ነገረኝ።

አሁን ጓደኝነቴን አምነህ ብትቀበል ነው የሚያዋጣህ።"

"ምን ያህል “ኮስት ያደርገኛል?"

እንነጋገርበታለን::" አልኩት:: ፈገግ አለ፡፡ መስማማቱ ነው።

"ስለሴት ልጅ የምትወደውን ሶስት ነገሯን ንገረኝ እስቲ?" አልኩት እራት መብላት ጨርሰን ወደ ቤት እየሸኘኝ፡፡ ጠዋት
ወደ ላንጋኖ ልንሄድ ተቀጣጥረናል።

"እናትነቷን"

ሶስት ነው ያልኩህ::"

"እኔ ስለሴት ልጅ ይሄ የምለው የተለየ ነገር አልወድም። ራሷን ስትሆን፣ የራሷ እምነት ፣ የራሷ ፋሽን፣ የራሷ ኩራት! በቃ
የራሷ ነገር ሲኖራት ራሷን ስትሆን ደስ ትለኛለች:: የሰው ልጅ ምርጥ እየሆነ የሚመስለኝ ራሱን ወደ መሆን ሲያድግ ነው።"

“ለምሳሌ?"

“ለምሳሌ እንዳንቺ!! እራት ቀጥሬሽ ቁምጣ በቲሸርት ለብሰሽ
ትመጫለሽ" አለኝ ቁምጣዬን እያየ::" ቤዚካሊይ የራስሽ የሆነውን ነገር ሰው ለማስደሰት ብለሽ አትቀይሪውም::"

"በቻይንኛ ወድጄሻለሁ እንደማለት”

ባህሪሽ ደስ ይለኛል ማለት በቻይንኛ ወድጄሻለሁ እንደማለት መሆኑን አላውቅም ነበር።" ፈገግ አለ።"አንቺስ?"

"እኔ ምን?"

"አባትነቱን"

"ሶስት ነው ያልኩሽ?" አለ እየተንፈቀፈቀ::

"ባክህ የወንድ ሁሉ ተምሳሌቴ ወንድሜ ነው፡፡ ዓይንህን ብቻ አይቶ ጥልቅ ስሜትህ የሚገባው አይነት ነው። የወንድ መለኪያዬ እሱ ነው።

ወዲያው ስልኬ ጠራ። አያሌው ነው። ኤፍሬምን ቀና ብዬ አየሁት። አንሺው፣ ችግር የለውም::” እንደማለት ምልክት
አሳየኝ፡፡ ለኔ ግን የገባኝ፡፡ 'አምንሻለሁ እንዳለኝ ነበር:: አነሳሁት።

"እድል ካንቺ ጋር የሆነች ይመስላል፡፡ ተጠቀሚባት:: እንደሌሎቹ
ወንዶች አጣጥሞሽ ሲበቃው ከነድህነትሽ ጥሎሽ እንዲሄድ
አትፍቀጂለት" አለኝ፡

፡መልስ ሳልሰጠው ዘጋሁት።

"ምን እያሰብክ ነው?" አልኩት ላንጋኖ ሀይቁ ዳር አሸዋው ላይ እንደተቀመጥን፡፡ እኩለ ለሊት ሆኗል፡፡ ከመጣን ሶስተኛ ቀናችን ነው።

"አንቺን" አለኝ፡፡ በኤፍሬም ድምፅ ይሄን መስማት ብዙ ነገር ነበር፡፡

"እቀፈኝ!"

ግን እንደዛ አላደረገም:: ከአጠገቤ ተነስቶ ከጀርባዬ በኩል እግሮቹ
መሃል አድርጎኝ ተቀመጠ። በግዙፍ ሰውነቱ ሙሉ ውስጡ ደበቀኝ። ከብዙ ክፋቶች የተጠበቅኩ መሰለኝ፡፡ አንገቴ ስር የሚሰማኝ ሞቅታ ትንፋሹ እጠብቅሻለሁ፣ አለሁልሽ' ያለኝ
መሰለኝ፡፡ የማንም ወንድ ገላ በዚህ መጠን ናፍቆኝ ማወቁን እጠራጠራለሁ
"እንግባ?" ከማለቱ እኔ ተነስቻለሁ። ገብቶታል።እንደህፃን ልጅ ብድግ አድርጎ ከመሬት አንስቶ እንደታቀፈኝ አልጋው ጋረሸ አደረሰኝ።

መች ነው እንዲህ ለሱ የተሰማኝ? ከዛሬ በፊት በነበሩት ቀናት?፣ከአዲስ አበባ ስንመጣ እግሮቹ ላይ እንቅልፌን ተኝቼ መኪና ሲነዳ?፣ ሀይቁ ውስጥ ስንዋኝ?፣ የጠረጴዛ ቴኒስ ስንጫወት?፣
ቼዝ ሲያለማምደኝ?፣ ካንፋየር አጠገብ እራት እየበላን ውስኪ ስንጠጣ? ክፍላችን ውስጥ በድሮ ሙዚቃ የድሮ ዳንስ ስንደንስ?እግሩ ስር አስቀምጦኝ ፀጉሬን ሲያበጥርልኝ ካርታ ተጫውተን አሸንፌው በውርርዱ አዝሎኝ ጊቢውን ዞር በአንዱ ወይም በሁሉም ሰዓት የተለየ ስሜት ተሰምቶኛል።

ቁርስ መብላት ደስ የሚለኝ ፍርፍር በሻይ ነው::" አለኝ ጠዋት እቅፉ ውስጥ እንዳለሁ።

"ፍርፍር? ፍርፍር? ስጋ ሳይኖረው?"

ቢኖረው ጥሩ! ባይኖረውም ከሌላ ምግብ ፍርፍር ምርጫዬ ነው:" አለኝ ከአልጋው ለመነሳት ያቀፈኝን እጁን በቀስታ እያነሳ።

"እንቆይ? እንደዚህ ትንሽ እንቆይ? አቅፈኸኝ ትንሽ እንተኛ?" አልኩት:: ተመልሶ አጥብቆ አቅፎኝ ተኛ።

መታቀፍ የተለየ ትርጉም እና ስሜት የሚሰጠኝ ነገር ነው። ለአቃፊው የምሰጠው ዋጋ የትርጉሙን ልኬት የሚያወጣና የሚያወርደው ቢሆንም ያቀፈኝ ሰው ስሜቴን ብነግረው ባልነግረውም ያጋባሁበት እነደሆነ ነው የሚሰማኝ።ባቀፈኝ ቅፅበት ሸክሜን የተጋራልኝ፣ ካለሁበት ትርምስ የደበቀኝ ነው የሚመስለኝ፡፡ ይሄን ትርጉም በትክክል የሚያሟላልኝ የእማዬና
የበርዬ እቅፍ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ተሰምቶኝ በማያውቅ ልክ የኤፍሬም።


ከሶስት ቀናት በኋላ ከራሴ እውነት ጋር መላተም ጀመርኩ::አያሌው እቤት ድረስ መጥቶ አስር ሺህ ብር አስቀምጦልኝ
መሄዱን በርዬ ነገረኝ፡፡

"እሺ ልመልስለት:: ከዛስ? ከዛ ምን እንብላ? ከዛ ለእማዬ ምን
እንሰርላት? ከዛ ገንዘብ ፍለጋ የማልወደው ገላ ላይ ልጣድ?
ንገረኛ?" ብሩን መልሺለት ስላለኝ ነው በርዬ ላይ የምጮኸው።ለኤፍሬም እውነቱን እንድነግረው ሲወተውተኝ፡፡
በርዬ አቀረቀረ:: አድርጌው እንደማላውቅ
ሁሉ ለገንዘባቸው ከምተኛላቸው ወንዶች ጋር መሆን ቀፋፊ ነገር ሆነብኝ፡፡

ከኤፍሬም ጋር የስራሁትን ፍቅር ማርከስ መሰለኝ፡፡ የሆነ ልክ ከኤፍሬም ጋር ከተኛሁ በኋላ ገላዬ የተቀደሰ ነገር መሰለኝ፡፡ ያንን ማርከስ መሰለኝ፡፡ በእርግጥ ኤፍሬምን ገንዘብ ብጠይቀው
ይከለክለኝ ነበር? አይከለክለኝም ይሆናል፡፡ በግልፅ ምክንያት
የአያሌውን ገንዘብ ብመልስለት ለኤፍሬም እውነቱን እንደሚነግረው አስፈራርቶኛል፡፡ በድብቅ ምክንያቴ ግን ኤፍሬም ጋር ያለኝ ነገር ከዚህ በፊት ከማውቃቸው ወንዶች ጋር እንደነበረኝ ስራ እንደሆነ እንዲሰማኝና እንዲቀልብኝ
አልፈለግኩም:: ሌላው አማራጭ ግን እንደገሃነም አስፈሪ ነው፡፡እውነቱን መናገር! ለኤፍሬም የቀረብኩህ ተከፍሎኝ ነውኀልበለው? ከዛስ? ጥሎኝ ሲሄድ ትርፌ ምንድነው? ፊልም ላይ
ብቻ ነው ይሄ የሚሰራው:: አባዬ ራሱን ያጠፋው የቤተሰቡን ምስቅልቅል መሸከም ስለከበደው ነበር:: ያንን የተሸናፊ ፊቱን ልረሳው አልችልም፡፡ እኔ እማዬንና በርዬን የራሳቸው ጉዳይ ብዬ
ህሊናን መምረጥ አልችልም።የኔ ህሊና
ንፅህና የቤት ኪራያችንን አይከፍልም ወይም የበርዬን ትምህርት ቤት ክፍያ
አያጠናቅቅም አልያም ለእማዬ ስንቅ አይሆንም።ህሊና በአገልግል አይቆጠርም።

ከኤፍሬም ጋር ሳንገናኝ የዋልንበት ቀን ጠፋ። እቤት ከማድርበት ከኤፍሬም ጋር የማድርበት ቀን በለጠ፡፡ ሀኪም ያዘዘለትን ሀያ የእረፍት ቀን አረፍንበት። አብሬው አሳለፍኩ፡ እሱ በትክክል ምን እንደሚሰማው ግን አሁንም ማወቅ አልቻልኩም:: ከነዚህ ቀናት በኋላ አሁን ጥያቄዬ ህሊና ብቻ አይደለም ኤፍሬምን ማጣት ማሰብ ያስፈራኝ ጀምሯል። ኤፍሬም ሊዲያ የሞተችበት
ረቡዕ ዕለት ሁሌም መቃብሯጋ እንደሚሄድ ስለማውቅ
👍61🔥1
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_ስድስት


#በሜሪ_ፈለቀ

“ወንድ ልጅ! ስራ አልናፈቀህም ማለት እኮ ፍቅር አስይዤሃለሁ ማለት ነው።" አልኩት እንደመደነስ እያደረገኝ።

"አልወጣኝም::" አለ በሁኔታዬ ፈገግ እያለ፡፡

"ጉረኛ!! አታምንም አይደል?"

ስራ በጀመረባቸው ቀናት ለየት ያለ የምሳ ግብዣ ላይ አብሬው እንድሄድ ጋበዘኝ፡፡ ከአንድ ባለሀብት ጋር የንግድ ድርድር ነው።የባለሀብቱን ሚስት ተከትዬ መፀዳጃ ቤት ገባሁ:: ኤፍሬም
የገዛልኝ ቀሚስ ፕሮቶኮላም አድርጎኛል፡፡ እንደዛ የለበስኩት እርሱ በሰጠኝ ክብር ልክም ባይሆን የሚገባውን ላደርግላት
ስለፈለግኩ ነው:: የወንዶቹ ወሬ እንደኔ ካሰለቻት ከሰውየው ሚስት ጋር ቀላል ወሬዎች ተጫወትን። ከኔ የባሰች ለፍላፊ
ነገር ስለነበረች በደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር አወራችኝ፡፡ ወደ ጠረጴዛው ስመለስ የወንዶቹ ድርድር ቀልቤን ሳበው:: ባለሀብቱ ከነኤፍሬም የእንስሳት ማደለቢያ ማዕከል ወደውጪ የከብት ስጋ ለመላክ ነው በሚያዋጣቸው ድርሻ የሚደራደሩት፡፡ ሰውየው የሚያዋጣኝ ስድሳ አምስት በመቶ ድርሻ ሲኖረኝ ነው ብሎ ግግም አለ፡፡ የተቀረው ሰላሳ አምስት በመቶ ድርሻ የኛ ሊሆን
ማለት ነው። (ቡፍፍ! የኛ አልኩ እንዴ? እኔ ከስሙኝ ብዙ አወራ የለ? ባልስማ እለፉኝ፡፡) ኤፍሬም ሲያቅማማ አየሁት፡፡

የኛ ድርጅት አያዋጣውም።አርባ አምስት በሃምሳ አምስት ካዋጣህ መቀጠል እንችላለን፡፡" አልኩኝ ጣልቃ ገብቼ፡፡ ኤፍሬም ዘወር ብሎ የተናገርኩትን ባለማመን አየኝ፡፡

"እመነኝ እሺ ያዋጣዋል፡፡" አልኩት በጆሮው።

"እመቤት አንቺ የገባሽ አልመሰለኝም።" አለ ባለሃብቱ እንደማፌዝ እያደረገው።

“ምኑ ነው የገባኝ ያልመሰለህ? መልካም እንግዲህ፡፡ ሀሳብህን ከቀየርክ ደውልልን።" ብዬው ተነሳሁ:: ኤፍሬም ግራ በመጋባት ተከተለኝ። ሰውየው እየተበሳጨ ጠረጴዛውን ከነረተ በኋላ "እሺ ተቀመጡ!!" አለ።

"ምንድነበር ያደረግሽው?" አለኝ ኤፍሬም ተፈራርመው ከሆቴሉ ወጥተን መኪና ውስጥ እየገባን።

“ከሚስቱ ጋር የሴቶች ወሬ አውርተን ነበር። ብታያት ከኔ የባሰች ቀዳዳ ናት! ለባሏ በጣም አንገብጋቢ ድርድር መሆኑን ፣የሚወዳት ልጁን ልደት ትቶ እንደአምላክ ቀጠሮ የማይሰረዝ
ያለው ምሳ ላይ መምጣቱን ምናምን ነገረችኝ፡፡ አንተ ግን እንዴት አመንከኝ?

"አላውቅልሽም:: ሁሌም ሳምንሽ ከራሴ ጋር አልማከርም::" አለኝ እየገረመው አፍጥጦብኝ፡፡

ቆይ ግን የምር እስከምንድነው የተማርሽው?" አለኝ ለጥያቄው ተገቢ ይሆናል ያለውን ቃል እየመረጠ።

እውይ! አራተኛ ክፍል ሳይንስ መፅሃፍ ላይ እባብ በከለር አይቼ ደንብሬ እንደቀረሁ ነው::" መለስኩለት፡፡

'የምር? የምር ንገሪኝ?" አለኝ እየሳቀ፡፡ እስከ አስር መማሬን እና ውጤት ቢመጣልኝም ለመማር እንዳልተመቸኝ ነገርኩት።ገብቶት ይመስለኛል '
ለምን?” ብሎ አላጨናነቀኝም!

"የጭንቅላትሽ ከፍታ እኮ። ግን ማትሪክት የመንጣብሽ አይመሰልም።ብሎኝ የሽቶ እቃ እያቀበለኝ ቅድም ነው የገዛሁልሽ አለኝ።ሽቶውን ከፍቼ እያሸተትኩት ዝም ብዬ አየሁት፡፡

"አንተ ግን በእናትህ እመን ፍቅር ይዞሃል አይደል?" አልመለሰልኝም።ዝም ብሎ ብቻ ሳመኝ።

እስከማስታውሰው ማታ ደህና እደሪልኝ እንዲለኝ ጠዋት ደህና ዋይልኝ እንዲለኘሸ ስልኩን በናፍቆት የጠበቅኩትን ሰው
አላስታውስም፡፡ ኤፍሬም ሳይደውል ያረፈደ ቀን በእንቅልፍ ልቡ የእናቱን ጡት እንደሚፈልግ ህፃን ያንሰፈስፈኛል።
በስህተት ደህና ዋይልኝ ያላለኝ ቀን ቀኔ ደህና ቀኔ ደህና አይሆንልኝም የሆነ እሁድ ቀን ጠዋት ስልኩን እንደዘጋው ከሊ.ዲ.ያ ጋር ይኖር የነበረበት
ቤት ለመሄድ ታክሲ ተሳፈርኩ፡፡

እንዴት እዚህ መሆኔን አወቅሽ?" አለኝ የአጥሩን በር እየከፈተ።

"ደበረኝ አላልከኝም? ሲደብርህ ከዚህ ቤትና ከኔ ውጪ የትም እባክ መሄጃ እንደሌለህ አውቃለሁኣ።” መለስኩለት፡፡ አቀፈኝ።ወዲያውኑ ለቤተክርስቲያን የለበስኩትን ረዥም ቀሚስና ነጠላ
በጥያቄ እየሆኑ።

ዛሬ የዓመቷ ኪዳነ-ምህረት ናት፡፡”
ስለውም ጥያቄውን የጨረሰ አልመሰለም።


"ባክህ የእግዜር ሰው ሆኜ አይደለም። እማዬ ስለምታደርገው ነው::" አልኩት። ቤተክርስቲያን ሄደን አረፈድን። አመሻሹን
የሊዲያን አትክልቶች መኮትኮት ልምድ ስለነበረው ወደ ቤት ተመለስን። አበቦቿን የሚነካበት መንገድ ቅጠል ሳይሆን
የእርሷን ሰውነት እየነካ ነው የሚመስለው። እዛው ቤት ሳሎኑ ውስጥ ፍራሽ አንጥፈን አደርን ጠዋት እንዳልረብሸው ተጠንቅቄ ተነስቼ የእርሱን ሸሚዝ ብቻ ለብሼ ፍርፍር አበሰልኩለት።ሲነቃ የሚደሰት ነው የመሰለኝ።የተፈጠረው ግን ተቃራኒው ነው።አበደብኝ!የእርሷን ቦታ ለመተካት ያሰብኩት እራሴን እንደምን ቆጥሬው እንደሆነ አፈጠጠብኝ።

"እኔ እንዳልደርስበት የምትጠብቀው የህይወትህ ክፍል እንዳለ ይገባኛል እኮ የቀረብኩህ ስለመሰለኝ እንጂ እኔ ለሷ ያለህን ፍቅርና ዋጋ አከብርልሃለሁ:: ግን አበዛኸው....." አልኩት ትቼው ልሄድ እየለባበስኩ።

"ለሷ ልሰጣት የሚገባኝን የፍቅር ልክ አንቺ አትነግሪኝም::" አለኝ
ልሄድ መነሳቴ እንኳን ግድ ሳይለው።
ኡኡቴ እንደምትሉ አውቃለሁ። እኔም ማነኝ ብዬ እንዳስብኩ እንጃ! ሳይገባኝ ግን በሟች ሚስቱ ቀናሁ። ወደቤቴ
እንደሄድኩ ስልኬን አጠፋሁ።
የተፈጠረውን ለበርዬ ነገርኩት። የሚያባብለኝ ነበር የመሰለኝ፡፡
እሱ ግን ያለማቋረጥ ሳቀ፡፡ ከልቡ ሳቀ፡፡

"ምን ያስገለፍጥሃል? አሁን ይሄ ምን የሚያስቅ ነገር አለው?"

ፍቅር ይዞሻል!" አለኝ አንዳንዴ እንደሚያደርገው አንደታላቅ ወንድም እያየኝ፡፡

የማደርገው ሳይገባኝ ከበርዬ መፅሃፍቶች ውስጥ የሊዲያን መፅሀፍት ለይቼ አንዱን ማንበብ ጀመርኩ፡፡ በርዬ ይፅፋል። እኔ
አነባለሁ። በመሃል እናወራለን፡፡

ከሁለት ቀን በኋላ ስልኬን ስከፍተው ኤፍሬም ስምንት የይቅርታ መልዕክት ልኮልኛል። ደወልኩለት፡፡

"ላግኝሽ?"

“አሪፍ ምክንያት ካቀረብክ?"

ካንቺ ጋር መሆን ደስ ስለሚያሰኘኝ!"

“ቀሽም ምክንያት"

"ይህን አይደል መስማት የምትፈልጊው? አዎን ካንቺ ፍቅር

"እሺ ይቅርታ ልጠይቅሽ ስለምፈልግ

"ጭራሽ የወረደ ምክንያት"

"እሺ ስለናፈቅሽኝ"

"የት እንገናኝ?"

"ቢሮ ነኝ ነይና አብረን ምሳ እንወጣለን።"

"ቢሮ?"

አዎን!"

ሳየው ምን ያህል እንደናፈቀኝ ገባኝ፡፡ ስስመው በሩን እንኳን ያለመዝጋቴን ያወቅኩት ፀሃፊው ስትገባ ነው።ምሳ በልተን እቤቱ ይዞኝ ሄደ።እቃዎቹን በአዲስ እቃ ቀይሯቸዋል።
የቤቱንም ቀለም ቀይሮታል፡፡

"እርግጠኛ ነህ?" አልኩት በመገረም እያየሁት።

"እንደዚህ እርግጠኛ የሆንኩበት ነገር የለም::" መለሰልኝ።

"ይህን አይደል መስማት የምትፈልጊው? አዎን ካንቺ ፍቅር ይዞኛል።" አለኝ ከመቀመጣችን፡፡

ከንፈሩን ያለማቋረጥ ሳምኩት፡፡ ምክንያቱም ዝም እንዲለኝ ፈለግኩ።ገና መናገር እንደለመደ ህፃን እየቦረቀ ነው።
የሚያወራው። ድንገት መሳሙን አቁሞ "ሩካ?" አለኝ፡፡ ጥሪው ውስጥ ምንድነው አብሬ የሰማሁት? ልቤን ምን አስደለቀው? ሰውነቴን ምን አሞቀው?

"ወይዬ?"

“አንቺ ለኔ ከፈጣሪ እንደተላከ መላዕክ በመጥፎ ሰዓቶቼ ሁሉ ከጎኔ አገኝሻለሁ፣ እያስቀየምኩሽ እንኳን ትረጂኛለሽ:፡ እኔ ግን ላንቺ ጥሩ ጓደኛሽ እንኳን አይደለሁም::"

“በምን ምክንያት?" አልኩት፡፡

"ስላንቺ የማውቀው አንድ ነገር ቢኖር ለመኖር እንድጓጓ እንዳደረግሽኝ ብቻ ነው።"


"ታዲያ መላዕክ እኮ ጥሩም መጥፎም ቀን የለውም፡፡ አንተ ደስተኛ እንድትሆንልኝ ብቻ ከሆነስ የታዘዝኩት?" ይሄን በአፌ ልበለው እንጂ በእርግጥ
ለምን ስለራሴ እንዳልነገርኩት
ምክንያቴን
👍7
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_ሰባት


#በሜሪ_ፈለቀ


ድጋሚ አንቺን ባጣ የሚተርፍ ልብ አይኖረንም።” አለኝ ቀጠለና፡፡ አሁን ራሴን ጠላሁት። ረቂቅ መሆኔን ተፀየፍኩት።
የእማዬ እና የአባዬ ልጅ፣ የበርዬ እህት መሆኔን አምርሬ ጠላሁት።ከእውነት መደበቅ አማረኝ ከእርሱ የተሻለ መደበቂያ ደግሞ የለኝም።

"ዝም ብለህ ሳመኝ!" አልኩት የሽሚዙን አንገትጌ በሁለት እጄ ይዤ። ከንፈሮቹ እስከዛሬ እንደሳምኳቸው ከንፈሮች ስጋ ብቻ አይደሉም፡፡ ስመውኝ ለልቤ የሚደምሩት ሀሴት አላቸው።
ለነፍሴ ሹክ የሚሏት ጥፍጥና አላቸው:: እጆቹ እያንዳንዱን የሰውነት አካሌን ሲነኩ ሰውነቱን መናፈቅ ብቻ አይደለም
የሚፈጥሩት ነፍሴ እንኳን ማቃሰቷ ይገባኛል።የገባኝ ነገር ከሌሎች ወንዶች ጋር ያደረግኩትን ወሲብ አይደለም ከኤፍሬም ጋር ያደረግኩት። ፍቅር ነው የሰራነው። ኤፍሬም እንደሌሎቹ
ወንዶች ስጋዬን ብቻ አይደለም የሚወስበው ነፍሴንም በስጋዬ
ቅኝት ውስጥ ያወሳስባታል።

"ንግስቴ ነሽ!" ይለኛል ሲያቆላጵሰኝ፡፡ እርሱ የሰጠኝን ክብር ማንም ወንድ ሰጥቶኝ አያውቅም።ያላስገባኝ የህይወቱ ክፍል የለም። ስራው፣ ቤተሰቡ፣ ቤቱ: በኩራት ከጎኑ ይዞኝ ሲዞር የምር ንግስቱ እንደሆንኩ ይሰማኛል፡፡ በማይገባኝ የስራ ጉዳይ እንኳን ሊያደርግ ያሰበውን ያማክረኛል።

እማዬና ዘሪሁን ከአያሌው ጋር አብረው ሊያፈነዱኝ ነው።"
አለኝ አንድ ማታ እቅፉ ውስጥ አድርጎኝ ዓይን ዓይኔን እያየ፡፡

"ለምን?" አልኩት ለመጠየቅ ያህል እንጂ አያሌው እናትየውና ወንድሙ እንደሚደግፉት በተደጋጋሚ ነግሮኛል።

"ምንም በማይዋጥልኝ ምክንያት የዚህ ፋብሪካ ድርሻ መሸጥ የቤተሰቡን ሰላም በጥብጦታል። እማዬን ላስቀይማት
አልፈልግም።" አለኝ። ኤፍሬም እናቱና አባቱ ተፋተው አሁን እማዬ የሚላቸው እንጀራ እናቱ ናቸው ያሳደጓት።በጣም ስለሚወዳቸው በስህተት እንኳን እንዲከፉበት አይፈልግም።ከወላጅ እናት በላይ ተንከባክበው እንዳሳደጉት አውርቶኛል። እርሱም ወላጅ እናቱን ከስንት አንዴ ከመጠየቅ ያለፈ ግድ የለውም።እማዬ የሚለው የእንጅራ እናቱን ነው።ወንድሜ የሚለውም የአባቱ ልጅ ሳይሆን የእንጀራ እናቱ ልጅ ነው።

"አባትህ ቢሆኑ ባንተ ቦታ ምን ይወስኑ ነበር?"

"በእርግጠኝነት አባዬ ቤተሰቡን ሳያማክር ምንም አይነት ትልቅ ውሳኔ አይወስንም። በተለይ እማዬን፡፡ አባዬም ቢሆን በዚህ
ጉዳይ መስማማቱን እጠራጠራለሁ።" ሲያስረዳኝ በቅንነት እና በፍቅር ነው።

አልፈልግም::" አለኝ፡፡ ኤፍሬም እናቱና አባቱ ተፋተው አሁን እማዬ የሚላቸው እንጀራ እናቱ ናቸው ያሳደጉት። በጣም
ስለሚወዳቸው በስህተት እንኳን እንዲከፉበት አይፈልግም::
ከወላጅ እናት በላይ ተንከባክበው እንዳሳደጉት አውርቶኛል። እርሱም ወላጅ እናቱን ከስንት አንዴ ከመጠየቅ ያለፈ ግድ የለውም:: እማዬ የሚለው እንጀራ እናቱን ነው። ወንድሜ
የሚለውም የአባቱ ልጅ ሳይሆን የእንጀራ እናቱ ልጅ ነው።

"አባትህ ቢሆኑ ባንተ ቦታ ምን ይወስኑ ነበር?"


"በእርግጠኝነት አባዬ ቤተሰቡን ሳያማክር ምንም አይነት ትልቅ ውሳኔ አይወስንም። በተለይ እማዬን፡፡ አባዬም ቢሆን ግን በዚህ ጉዳይ መስማማቱን እጠራጠራለሁ።" ሲያስረዳኝ በቅንነት እና በፍቅር ነው።

አንዳንዴ በገንዘብ የማትገዛቸውና የማታስተካክላቸው ነገሮች
አሉ::" አልኩት።

ሩካዬ እኔ ቤተሰቤንና ቁስን ለንፅፅር የማቀርብ ቀሽም ሰው አይደለሁም።ብቻ ምክንያታዊ አይደሉም አልተዋጠልኝም::"
ተጨንቆ ሳየው አሳዘነኝ።

"ዛሬ እኔጋ ነው አይደል የምታድሪው?" አለኝ፡፡

"አሪፍ ምክንያት ካቀረብክ!”

"ሱሴ.....ስለማፈቅርሽ"

አያሌው በተደጋጋሚ እየደወለ ብዙ ጊዜ መፍጀቴን ይነግረኛል::
ስራ ቢሰጥሽ ፍቅር ታደሪያለሽ እንዴ?” እያለ ይዘባበታል፡፡ሲያሻው በውስጡ ብታፈገፍጊ ለኤፍሬም እውነቱን እነግረዋለው።የሚል አንድምታ ያለው ማስፈራርያ ይቦጠለቃል።በተጨማሪ ሌላ አስር ሺ ብር እቤት አስቀምጦልኛል።
መቀበሉም አለመቀበሉም ለውጥ ስላልነበረው አስቀመጥኩት። አያሌው እኔን ሲነተርክ፣ እኔ በኤፍሬም ፍቅር፣
በህሊናዬ እና በምኖረው እውነት ተወጥሬ፣ ኤፍሬም በቤተሰቡ ንዝንዝ እና ከኔጋር በጀመረው አዲስ ፍቅር ሲዋከብ ሶስት ወራት አለፉ።

ሩካዬ? አግቢኝ!” ያለኝ ማታ ስሜቴ ተደበላለቀ። ደስታና ሀዘን፣ተስፋና ፀፀት ውስጤ ተሳከረ፡፡ አልመለስኩለትም።

"ሱሴ የኔ ሁኚልኝ!" ደገመው። ዝምታዬን ደገምኩት።

'የኔ መሆን አትፈልጊም? አታፈቅሪኝም?"

“እሱማ አፈቅርሃለሁ።"

"እሱማ ምን?"

"ጊዜ ስጠኝ ኤፊ" አልኩት አፌ እንዳመጣልኝ እንጂ ጊዜ
ከማወሳሰብ አልፎ የሚፈታው የኔ ጉዳይ እንደሌለ አውቃለሁ።

"የፈለግሽውን ያህል ጊዜ ውሰጂና አስቢበት።የመጨረሻው መልስሽ ብቻ እሺ ይሁን።" አለኝ፡፡ ዓይኔ በእንባ መሞላቱ አስደነገጠው።

"ደስ የሚልሽ ነበር የመሰለኝ!" አለ ቅር እየተሰኘ፡

"ደስ ብሎኝ ነው! አንተ ለኔ የምትገባ ሰው አልነበርክም። ይሄ ክብር የሚገባኝ ሴት አይደለሁም።" እንባዬን ከዚህ በላይ ማቆም አልቻልኩም።ሳይገባው አባበለኝ።

"ኤፍዬ በናትህ ከእቅፍህ አታስወጣኝ! እቀፈኝ!" አልኩት። እቅፉ ውስጥ ተደብቄ እንቅልፍ ወሰደኝ። ብቸኛው ሰላም የማገኝበት ቦታዬ ከእውነታው የምሸሽበት ዋሻዬ ፍረዱኝ እስኪ ምን ነበር ማድረግ የነበረብኝ? እውነቱን መንገር አትሉኝም?

ጠዋት ስራ ከመሄዱ በፊት የሰራሁለትን
ቁርስ እየበላ ስለአያሌው ድርሻ ጉዳይ አነሳልኝ።

"ሌሎቹ ዘርፎች ትርፍ ስለቀነሱ ገበያው ላይ እያተረፈ ያለ ፋብሪካ ድርሻ መሸጥ ምኑ ነው የሚያሳምነው?" አለኝ ከኔ ሀሳብ እየፈለገ።

"ምናልባት ብዙ ያሳደደ አንድ አይዝም እንዳይሆንብህ ብለው ይሆናል" መለስኩለት። ሊጎርስ ያዘጋጀውን ሰሀኑ ላይ መልሶ እያፈጠጠብኝ "አንቺም በመሸጡ ትስማሚያለሽ?" አለኝ፡፡

“በመጠኑ!"

"አሳምኚኝ!!" አለኝ ምንም ክፋትና እልህ
በሌለበት አንደበት።

“አንደኛ ፋብሪካው የጋራ ነው።ምንም ውሳኔ የራስህ ብቻ የማይሆንበት። የቀሩት ዘርፎች ግን የግልህ ናቸው:: በራስህ እጅ ብቻ ያለ ነገር ዋስትናው የተሻለ ነው። ባንተ ብቻ የሚተዳደር
ያላነሰ ንግድ እያለ አንድ ፋብሪካ ውስጥ ላለህ ድርሻ እንዲህ ከቤተሰብ ጋር የመቃረኛ ነጥብ እስኪሆን ድረስ ትልቅ ጉዳይ መሆኑ የሚዋጥ አደለም
ሁለተኛ በአጭር ጊዜ እንደታዘብኩት
የግልህ የሆኑት ዘርፎች ሶስት ዓመት ሙሉ ምንም ለውጥና እድሳት አልተደረገባቸውም፡፡ ላድርግም ብትል
በዛ ያለ ገንዘብ ያስፈልግሃል::ያን ደግሞ ፋብሪካው ውስጥ ያለህን ድርሻ ሸጠህ ካልተጠቀምክ በቀር አቅም ያንስሃል።”

“እሱ ይህን ያህል ገንዘብ ፕሮፖዝ ሲያደርግልኝ የወደፊትትርፉን አስልቶ አይመስልሽም?"

"ይሆናል።ትርፍና ኪሳራውን ሳያመዛዝን እንደማይወስን ግልፅ ነው።ያንተ ድርጅቶችም ቢሆኑ አባትህና ሊዲያ
በሚያስተዳድሩባቸው ዓመታት እጅግ ትርፋማ የነበሩ ናቸው።አሁንም በትንሽ ጥረት ወደ ቀድሞ ቦታቸው የማይመለሱበት ምክንያት አይታየኝም::"

"እደግመዋለሁ የጭንቅላትሽ ምጥቀት እኮ ማትሪክ የመጣብሽ አትመስይም::" አለኝ ወደ ቁርሱ እየተመለሰ። ቀጠል አድርጎ
"አሁንም አይዋጥልኝም፡፡ ከነሱ ግን ያንቺ ምክንያት የተሻለ አሳማኝ ነው::"

ከዚህ በኋላ ለተከታታይ ቀናት ይሄን ጉዳይ ሳናነሳ ነግቶ የመሸ ቀን አልነበረም፡፡ ከቤት እናቱና ወንድሙ ስለሚጨቀጭቁት መጥቶ የሚተነፍሰው እኔጋ ነው።

እኔም እየጨቀጨቅኩት እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡

“ሩካዬ በዚህ ጉዳይ ካሁን በኋላ ካንቺም ከቤተሰቤም ጋር መጨቃጨቅ አልፈልግም::" አለኝ የሆነ ቀን
እያደረሰኝ፡፡ ደስ አላለኝም:: የኔና
👍7
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_ስምንት


#በሜሪ_ፈለቀ

ጥቁርና ነጭ አይደሉ? ቢሆንም የከዳሁት ልቡ አንደኛውን ሲሄድ ህመሜን ደምሬ ልታመም ወስኜ ዛሬ አብሬው ጠፋሁ። እኔ የጊዜ ዑደትን ማስላት ምን ሊረባኝ ያልኖርኩባትን ነገ ትቶኝ ይሄዳል ብዬ ዛሬዬን ልብከንከን? ኤፍሬምን በተመለከተ ከነገ እውነት የዛሬ ስሜቴ ልክ ነው። ከእርሱ ጋር አንድ ቀን ዘልአለም ነው አንድ አይደለም። ከእርሱ ጋር አንድ ቀን ዘለዓለም ነው። ዘለዓለም
ደግሞ ውሱን አይደለም፡፡ ዛሬ ዘለዓለም ናት! ስለዚህ ከርሱ ጋር ዘለዓለም መኖር ምርጫዬ ሆነ፡፡

"ደህና እደሪ" ሲለኝ ፀጉሩን እንደዳበሱት ህፃን አንቀላፋሁ።

"እወድሻለሁ" ያለኝ ቃል በጆሮዬ ለብዙ ዘለዓለም ቀናት ተንቆረቆረ።

ዘለዓለም ጥግ ኣልባ ነውና ዛሬ ለኔ ያለው ስሜት ጥግ አልባ ነው። ያንን ብቻ አምናለሁ። ነገ ስለመለያየቴ መርሳት ፈለግኩ፡፡ዘለዓለም ከእርሱ ጋር አለሁና! እስከሁሌው እቅፍ ውስጥ ብኖር
ብዬ ሳሳሁ። ጠዋት ተመልሰን ስለየው የመጨረሻዬ እንደሆነ እያወቅኩ ነበር በስስት የሳምኩት።እናም "ደህና ዋይልኝ" ሲለኝ ቀጥሎ ሊፈጠር ስለሚችለው ክስተት ሳላስብ ከደህና በላይ ሆንኩ፡፡ ከእርሱ ተለይቼ ብዙም ሳልቆይ አያሌው ደወለልኝ። እመኑኝ ኤፍሬምን ላለማጣት እናትና ወንድሜን አያስከፍለኝ
እንጂ ምንም አደርግ ነበር፡፡ አሁን ግን
ተመሳቅሏል፡፡እውነቱን ብነግረውም አብሮኝ ስለመዝለቁ ዋስትና
የለኝም፡፡

“ምን ብታቀምሺው ነው? ንግስቴን አመስግናት ሲለኝ እንኳን ያላፈረኝ?" አለኝ፡፡ ዝም አልኩት፡፡

“ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ላግኝሽ?" ብሎ ቀጠረኝ:: በድኔን እየጎተትኩ
ደረስኩ። ብሩን በቦርሳ በካሽ ሰጠኝ:: የማይሆን ነገር ባስብ በበርዬ ያስፈራራኝን ደገመልኝ።ከአንድ ሰዓት በኋላ እንደሚፈርምለት እየፈነጠዘ ነግሮኝ ተለያየን።ታክሲ ይዤ እየሄድኩ በመስኮቱ
አሻግሬ አያለሁ።ታክሲው ጎን የቤት መኪና አየሁ ውስጡ የነበሩት ሰዎች ትኩረቴን ሳቡት።አያሌውን የኤፍሬም እናት።አልተሳሳትኩም፡፡ ከንፈር ለከንፈር እየተሳሳሙ ነው ያየሁት።በደስታ
የሰከሩ ይመስላሉ፡፡ እናትየው የፋብሪካው ድርሻ እንዲሽጥ መወትወታቸው የተለየ ምክንያት ሊኖረው
እንደሚችል እንዴት አልጠረጠርኩም? የማደርገው ጠፋኝ፡፡

ቢሮው እያለከለኩ ስደርስ ብዙም አልዘገየሁም። የማደርገው ነገር የሚያመጣውን ቀውስ ማሰብ አልፈለግኩም፡፡ ሊፈርም
ያዘጋጃቸውን ሰነዶች እንደያዘ ኤፍሬም ፈዞ ያየኛል። የሆነውን አንድ በአንድ ነገርኩት። ገንዘቡን ለአያሌው ጠረጴዛው ላይ አስቀመጥኩለት።

"እኔጋ የሚቀርህን ገንዘብ እመልስልሃለሁ፡፡" ብዬው ስወጣ
ለመጨረሻ ጊዜ የኤፍሬምን ፊት አየሁት:: ደንዝዟል።ለመጨረሻ ጊዜ ይህን አለ፡፡

"ያ ሁሉ ለክፍያ ነበር?"

ኤፍሬም ድጋሚ ሊያየኝ እንደማይፈልግ የስንብት በሚመስል የመጨረሻ መልዕክቱ በስልክ አሳውቆኛል: ህይወት አስጠላኝ፣ እማዬና በርዬ እኔን ማባበል ስለቻቸው።በርዬ መፅሀፉን
የሚያሳትምለት አሳታሚ ድርጅት አጊንቶ ከስድስት ወር በኋላ ታተመለት:: ርዕሱ 'ምርጫ አልባ ምርጫ መሆኑን ያወቅኩት
ልናስመርቅ ስንሰናዳ ነው:: ሁሉ ነገር ቢያስጠላኝም የበርዬ ህልም መሳካቱ በተወሰነ መልኩ የደስታ ምንጭ ሆኖልኛል።መደበቂያዬ መፅሀፍ ማንበብ ሆኗል፡፡ ከማይገፋ የብቸኝነት ወራት በኋላ በርዬ ሱፍ ለብሶ፣ እኔ የሀበሻ ቀሚስ ለብሼ የመፅሀፉ ምረቃ ዝግጅት ላይ ከመታደማችን በፊት እማዬጋ
ሄድን፡፡ በደስታ አነባች:: መገኘት ባትችልም በልጆቿ ደስታ በማያባራ እንባ ታጠበች። ይህቺን ቀን እውን ለማድረግ ብዙ አልፌያለሁ እና አብሪያት አለቀስኩ፡፡

አዳራሽ ውስጥ ስንገባ ሰዓት ገና ቢሆንም ወዲህ ወዲያ የሚሉ
ሰዎች ነበሩ፡፡

"ሩካ?" የሰማሁትን ድምፅ ማመን አቅቶኝ ዞርኩ፡፡ ኤፍሬም የበርዬ መፅሀፍ ምረቃ ላይ ምን ይሰራል? አላችሁ? እኔም
ራሴን እንዲያ ከጠየቅኩ በኋላ ወዲያው
እስካሁን ያላስተዋልኩትን ነገር አስታወስኩ፡፡ የመፅሀፉ ሽፋን ላይ
አሳታሚና አከፋፋይ ተብሎ የተፃፈው የኤፍሬም ድርጅት ስም ነው።

"ወይዬ” አልኩት የምለው ጠፍቶኝ፡፡ በርዬ ዊልቸሩን እየገፋ አጠገቤ ሲደርስ ፍፁም በወዳጅነት መንፈስ ተቀላልደው አልፎን ሄደ፡፡ እንደትንግርት የሚሆነውን ከማየት ውጪ ምርጫ አልሰጡኝም:: በርዬ አልፎኝ ከሄደ በኋላ በአይኑ ጠቀሰኝ፡፡ እንዴትና የት ተግባቡ

“ይሄን መፅሀፍ ካነበብኩ በኋላ እንደገና ላውቅሽ እንደሚገባ ወሰንኩ።ኤፍሬም!!" አለኝ እጁን እየዘረጋልኝ፡፡

"ረቂቅ" አልኩት እጄ ሳላዘው ሊጨብጠው እየተዘረጋ።

።።።።።።።።
እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው።ያንተ ግራ የኔ ቀኝ ነው 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ ። እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል።እንደኔ አቋቋም ደግሞ የኔ ትክክል ይሆናል። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ።የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራው ስዳኝህ እቀሽማለው።
።።።

#በረከት

እሷ ዋሸኸኝ ነው የምትለኝ፡፡ እኔ ደግሞ አልነገርኳትም እንጂ ዋሸኋት ብዬ አላሰብኩም ወይም እንደዛ ማመን አልፈልግም።በእርግጥ ያልነገርኳት አለመነገር የሚችል አልያም ባይነገርም
በእኔ እና በሷ ግንኙነት ሂደት ለውጥ የማይፈጥር ዝባዝንኬ ሆኖ አልነበረም
እሷን እስከማጣት የሚስቀጣኝ ሊሆን
እንደሚችል አውቅ ነበር።ግን ማወቅ ከባድ አይደለም መኖር እንጂ! ያወቁትን ሁሉ መኖር የሚቻል ቢሆን ኖሮ ይህች ዓለም ከብዙ ስህተቶችና ጥፋቶች በተረፈች ነበር። ምክንያቱም የማይረቡ የምንላቸውን ጭምር አብዛኛዎቹ ጥፋቶች ባለማወቅ የሚደረጉ አይደሉም።

"ይቅርታ ውዴ! አንቺን ለመጉዳት ብዬ ያደረግኩት ምንም ነገር የለም። እመኚኝ፡፡" ብዬ የስልኬ መልዕክት መፃፊያ ሳጥን ውስጥ ካሰፈርኩ በኋላ ስልኩን አቀበልኳት::

“ታዲያ ለምን ዋሽኸኝ? ያን ሁላ ጊዜ ስንፃፃፍ ላንተ ጨዋታ ነበረ? እያሾፍክብኝ ነበር?" እኔ ከፃፍኩላት ስር ይሄን ፅፋ
ስልኩን መለሰችልኝ፡፡ በኖርኩባቸው የሃያ ሰባት ዓመት የዕድሜዬ ቁጥር ልክ ብዙዎች በተለያየ ምክንያት ሲያዝኑ እና ሲሰበሩ አይቼ አውቃለሁ። እሷ ላይ በማነበው ልክ ፊት ላይ የተገለጠ መሰበር አስተውዬ ማወቄን እጠራጠራለሁ፡፡ ምክንያቱ እኔ መሆኔ ደግሞ በሰባት ዓመቴ ወድቄ የተሰበረ እጄ ሲታከም ከተሰማኝ ህመም በላይ ያማል።

“በፍፁም አልነበረም:: የፃፍኩልሽን እያንዳንዷን ቃል እና ስሜት
ከልቤ ነው ያልኩሽ! የፃፍሽልኝ እያንዳንዱ ቃል ደግሞ በዘመኔ ሁሉ እየመነዘርኩት ደስታን የምሸምትበት ሀብቴ ነው ።
ስለሚቀጥለው ግንኙነታችን ልብሽ የሚልሽን አድርጊ ስላለፈው
ግን እመኚኝ የተሰማሽም የተሰማኝም እውነት ነበር። በዛሬው ጥርጣሬሽ ትናንትናችንን አታርክሺው ይሄን ፅፌ አቀበልኳት።አንብባ ስትጨርስ መልስ መፃፍ ጀመረች፡፡ ስልኩን መልሳ
ስታቀብለኝ ግን ምንም የተፃፈ መልዕክት የለዉም፡፡ ልቧን በቃላት ማስፈር የተሰማትን ስሜት ማቅለል ሆነባት የተወችው መሰለኝ።

ሩካ እና ኤፍሬም በእኔና በማርቲ መሃከል የተከወነውን የስልክ መቀባበል እንዳላስተዋለ ለማስመሰል ለቡና ቁርስነት የቀረበው ፈንድሻ ላይ ራሳቸውን ጠምደዋል፡፡ሁላችንም በፀጥታ
ሀሳቦቻችንን እያላመጥን መሰለኝ ሩካ ቡናውን ፉት ስትል
ፉፉፉፉፉፉትታዋ እንኳን አንድ ጠረጴዛ ለከበብነው አራት ሰዎች ከጊቢ ውጪ ለሚያልፍ ሂያጅ የ'ቡና ጠጡልኝ መልዕክት ይነግራል፡፡

"አቦል ልድገማችሁ?" የሚለው የሳራ ድምፅ (ሩካ ከሶስት ወር በፊት የቀጠረቻት በእድሜ ገፋ ያለች የቤት ሰራተኛችን ናት፡፡
👍2😁1
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በሜሪ_ፈለቀ

"ከዛሬ በፊት ነግሬሽ ቢሆን ኖሮ ምንድን ነበር የሚፈጠረው?ከነጉድለቴ ትወጂኝስ ነበር?" አስቀድሜ ስልኬ ላይ ፅፌው ልሰጣት ሳመነታ የነበረውን አቀበልኳት
አቀበልኳት: አንብባው ቀና ስትል ያፈጠጠባት ዓይኔን ቀለበችው:: በዝቅተኛ ግን በቁጣ ድምፅ "ማድረግ የነበረብህ ያን ነበር፡፡ ግድ ሊልህ የሚገባው ነገር የእኔ ስሜት ለውጥ ወይም ውሳኔዬ ሳይሆን ያንተ ሀቀኝነት ነበር። ታውቃለህ? በእውነተኛ
ታሪክ ላይ የተመሰረተ ልብ-ወለድ መፃፍ ትክክለኛ ተስዕጦህ ነው:: በእኔና ባንተ መሃከል የነበረው ነገር ላንተ እንደዛ ነበር::
አንዷን ገፀ-ባህሪህን እንደምታዋራት እና እንደምታስወራት ያህል የምትዝናናበት ልብ-ወለድ!!" ብላኝ ስልኬን ከጠረጴዛው
አጋጭታ አስቀምጣ ወደ ውጪ ወጣች:: እየሆነ የነበረውን እየተከታተሉ እንደነበር በሚያሳብቅባቸው አኳኋን ሩካ እና
ኤፍሬም ተከታትለው ወደ ሳሎን ብቅ አሉ፡፡ ኤፍሬም በ'አይዞህ!'
ባይነት ትከሻዬን ጨበጥ አድርጎ ማርቲን ያረፈችበት ሆቴል ሊያደርሳት ተከትሏት ወደ ውጪ ወጣ፡፡

"ያልጠበቅከው ነገር አልነበረም የተፈጠረው:: ለእርሷም ዱብ-ዕዳ ነው የሆነባት፡፡ ጊዜ ስጣትና የሚሆነውን እንጠብቅ፡፡" አለችኝ ሩካ የከፋኝ ሲመስላት ሁሌ እንደምታደርገው በሁለቱ
እጆቿ ጉልበቴን ተደግፋ እግሬ ስር ቁጢጥ ብላ የተሰማኝን ለመረዳት ዓይን ዓይኔን እያየች፡፡ ላስረዳት ከምፍጨረጨረው በላይ ቀድማ የእኔን ህመም በራሴው
እንደምትታመምልኝ ስለማውቅ መልስ ልሰጣት አልደከምኩም።ፀጉሮቿ መካከል ጣቶቼን ሰድጄ የራስ ቅሏን ቆዳ እየነካካሁ
ደቂቃዎች አለፉ። ጉልበቴ ላይ ግንባሯን ደፍታ ሳላወራ ሰማችኝ፡፡ ሳላስረዳት ገባኋት፡፡ እንባዬ በዓይኔ ባይገነፍልም
ማልቀሴን አየችው። ሩካ ናታ! ግነት የለውም፡፡ እንደውም አልገለፅኳትም። ሩካ የሌላ ሰው ስሜት የራሱን ያህል በተጠጋጋ ቅርበት የሚሰማት ለነፍስ የቀረበች ፍጡር ናት!

በረከትን ሆኜ በምተውነው ራሴን ካወቅኩበት ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን ባለ መደበኛ የየዕለት የኑሮ ተውኔት ውስጥ በጉልህ የደመቁ ሶስት ሴቶች የሀሳቤን አቅጣጫ ፈቃዴን እያዛቡ ያንዥዋዥውታል። እማዬ ሩካ እና ማርቲ።

እማዬ ያው እማዬ ናት።ለእኔ ለልጇ ብላ አስር የዘመኗ ቁጥር በእስር ቤት እየተቆረጠመባት ያለች እናቴ! በየቱም ድርጊቴ የከፈለችልኝን መስዋዕትነት ጥቂት ሽራፊ እንኳን ላካክስላት
እንደማልችል ሳስብ ከንቱነቴ ይገንብኛል፡፡ ማድረግ የምችለው ብቸኛ ነገር የእማዬ ፊት ላይ ለሚታይ የፈገግታ ፍንጣቂ
ምክንያት ለመሆን ቢያቅተኝ እንኳን ቢያንስ በጉንጫ ላይ ለሚወርድ አንዲት የእንባ ዘለላዋ ምክንያት ላለመሆን
መፍጨርጨር ነው።

ረቂቅ ታናሽ እህቴ ናት፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍቅረኛዋ በሚጠራት ቁልምጫ ሩካ እያልኩ ነው የምጠራት:: ብቸኛዋ
እህቴ! ስለሩካ ማብራራት ቀላልም ከባድም የሚሆንበት ምክንያት ብዙ ነው። ልክ ለመሰላት ነገር የማታመነታ ቆራጥ መሆኗን ባመንኩ ልቤ በየደማቅ አበባው ተዟዙራ መዓዛውን ቀስማ
የማትረካ ቀልቃላ ቀለማም ቢራቢሮ ትመስለኛለች፡፡ ብዙም ሳይቆይ ውስብስብ የሆነች ጭምት ትሆንብኛለች
በጭምትነቷ ሳልረጋ ስስና ተሰባሪ ትሆንብኛለች።ሩካ የህይወቴም የመፅሐፌም ዋና ገፀ ባህሪ ናት! መፅሐፍ መፃፌን ነገርኳችሁ? ከወራት በፊት አንድ መፅሐፍ ፅፌ ለንባብ
አብቅቻለሁ። ለስነ ጥበባዊ ውበቱ መጠነኛ ቅብ ከመጨመሬ ውጪ ሙሉ ለሙሉ የሩካ ታሪክ ነው:: ርዕሱ "ምርጫ አልባምርጫ!!! የተሰኘ ነው:: የመጨረሻዋ ሴት ማርቲ የተከሰተችው በዚህ መፅሐፍ ሰበብ ነው፡፡

ስለእነርሱ ማንነት ከምፅፍላችሁ ቀድሞ የተውኔቱን ያልሰነበተ ትዕይንት የማርቲ
ልብ የተሰበረበትን ገፅ እንደምትፈልጉ አውቃለሁ። ምን አስቸኮላችሁ? ልክ ነበርክ ወይም ተሳስተሃል ብሎ ለመፍረድ ምን ከዳኝነታችሁ በፊት እኔን ማወቁ ለፍርዱ አይረዳችሁም ብላችሁ
ነው? ይመስለኛል። ለነገሩ እኔም ብሆን ያደረግኩትን ያደረገው ሌላ ሰው ቢሆን የፍርድ ወንበሬ ላይ ለመሰየም እጣደፍ ነበር::የፍርድ አንቀፅን በመዶሻ ድለቃ አጅቦ ማንበብ ከባድ የሚሆነው
የተፈራጅ እግርን ተውሶ በቆመበት ማጥ መቆም ሲቻል ነው።ነገር ግን የእኔ የልክነት ጥግ' ነው ብዬ ያመንኩበት የግሌ እውነት ለእናንተም የልክነት ጣሪያ መሆን አለበት ብዬ እናንተን በተሳሳች ሂሳብ መዳኘት ከቂልነቴ ባሻግር የጠበበ
የሀሳብ ምህዳሬን ገልቦ አደባባይ ማስጣት ይመስለኛል።

እኔ የቆምኩበትን ጫማስ “ስህተት ብላችሁ ለመዳኘት ለመሆኑ
የእናንተ ልክ በየትኛው ሚዛንና በማን ዳኝነት ተሰፍሮ ነው ልክነቱ የተረጋገጠው?

አይደለም ለሌላ ሰው ለራሳችን እንኳን “ልክ ነው ያልነውን እምነታችንን ጊዜ አላንጓለለብንም? የዛሬ ምናምን ዓመት በፊት የልክነት ጫፍ የመሰለን በጠበበም ወይ በሰፋ አስተሳሰባችን ሳቢያ ዛሬ አልተቀየረም? እንዴት ነው በጊዜ፣ በመረዳታችን መጠን፣ በቦታና በበሽቃጣ የህይወት ክስተቶች እንደማይቀየር
ዋስትና በሌለን ልክነት ሌላውን በስህተት የምንዳኘው?

የኔ ስህተት ውስጥ ተዘፍቆ ላገኘሁት ሰው ከመዳኘቴ በፊት የዝፍቀቱን ሰበብ መረዳቱ ይቀል አልነበር? ምክንያቱ ደግሞ
የእኔ ልክ የልክ ጣሪያ ሊሆን አይችልም፡፡ የሆነ ቦታ.... የሆነ ጊዜ.....ለሆነ ሰው ስህተቱ ሊሆን ይችላል፡፡

እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው። ያንተ ግራ የኔ ቀኝ ነው። ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ፡፡
እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል። እንደ እኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን
ጫማ መዋስ አለብኝ፡፡ የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ፡፡

እግሬን አውሻችሁ የዳከርኩበትን ስትዳክሩት አሁን ካለሁበት
የጊዜ ካብ ወራትን ወደኋላ ንጄ አፍ ውስጥ እየጣፈጠ የሚሟሟ
ግን እንዳያልቅ እንደሚሳሱለት፤ ያልቃል ብለው ማጣጣሙን እንዳይተውት ጥፍጥናው እንደሚያባብል ጣፋጭ ከረሜላ የሚጣፍጠውን የኑሮ ተውኔቴን ገፅ ላስነብባችሁ። እዚህ የጊዜ
ካብ ላይ ለማማረር ምክንያቶቼ የሚዘቅጡብኝ፤ የመጀመሪያ መፅሐፌን ለንባብ ያበቃሁ፤ የከበቡኝ ሰዎች የተደላደለ ቀን የሚያልፉበት፤ እማዬ በደስታ ያነባችበት እና የመፅሐፌን
አንባቢ አስተያየት በኢሜሌ እያነበብኩ ተስፋዬን የምስቅል በረከት ነበርኩ። በኤፍሬም ማተሚያ ቤት አማካኝነት
ማስታወቂያ ተሰርቶለት ስለነበር መፅሐፌ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደራሽነቱ ሰፊ ሆኖ ነበር፡፡ በመፅሐፌ ቀደምት ገፆች አንዱ ገፅ ላይ በተፃፈው የኢሜል አድራሻዬ የሚደርሱኝን የአንባቢያን
አስተያየት ማንበብ የሚደፍነው የስሜት ሽንቁር አለው፡፡

አንዳንዶቹ እንደዚህኛው ቦታ ላይ ታሪኩ እንደዚህ ባይሆን:መጨረሻው እንደዚህ ቢሆን የሚሉ ናቸው:: እንዲህና እንዲያ
ቢሆን የተባሉትን መልዕክቶች ስጨምቃቸው እኔ ከፃፍኩት በአንድ መስመር የማይገናኝ ሌላ ታሪክ እንደሚሆን እያሰብኩ ፈገግ እላለሁ። አብዛኛዎቻችን ስናነብ ደራሲው
ያሰበውን ሳይሆን እኛ የምናስበውን ቢፅፍልን እንፈልጋለን፡፡በተዘዋዋሪ የመፅሃፉ ደራሲ ራሳችን መሆን ነው የምንሻው::ለፃፈልኝ በሙሉ በምስጋና ብመልስም ጥያቄዎቹን ከራሴ ህይወት እውነታ ጋር እያዛመድኩ ለራሴ እመልሳለሁ::

'የምንትስ ገፀ ባህሪ ታሪክ መጨረሻው አልታወቀም:: ሲሉኝ
በእውነተኛው ዓለም መጨረሻቸው ያልተቋጨ ወይ ያልታወቀ
ታሪክ ባለቤቶች ብዙ አይደሉ? እላለሁ አባቴና ሰራተኛችን ሙሉ የነበራቸው ድብቅ ፍቅር መጨረሻው ምን
ነበር? እማዬ ወደ ስራ ሩካ
👍4
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_አስር


#በሜሪ_ፈለቀ

...የእውነታው ኑሯችን ለፍፁምነት የተጠጋጋ እንኳን አይደለም፡፡በመፅሐፌ ውስጥ ፍፅምናን ለምን ይጠብቃሉ? መፅሐፌ የሀሳቤና የኑራችን ግልባጭ እንጂ እነርሱ የሚመኙት የ'ቢሆን ዓለም ሊሆን እንዴት ይችል ነበር?

በአንዱ ቀን እንደተለመደው ኢሜሌን ስከፍት ረዥም ሀተታ ያለው መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ማርቲ ነበረች፡፡ ስለመፅሃፉ ይዘት
ተያያዥ ሀሳቦች ከተነተነች በኋላ ስለተሰማት ስሜት የፃፈችው ጭብጥ መልዕክቱ እንዲህ የሚል ነበር።

ታሪኬን ነግሬህ የፃፍከው እስኪመስለኝ ያለፍኩትን መንገድ እና የተሰማኝን ስሜት ነው የፃፍከው:: ወንድ ሆነህ እንዲህ የሴትን ጥልቅ ስሜት መፃፍህ እስገርሞኛል፡፡ መፅሐፍህን እያነበብኩኝ
የምታውቀኝ የምታውቀኝ አይነት ነበር የሚሰማኝ። በቅርቡ ከሀገር ቤት የመጣች ጓደኛዬ ገዝታልኝ ከመጣቻቸው አዳዲስ መፅሐፍት ውስጥ አንዱ ምርጫ አልባ ምርጫ ነበር፡፡ ይሄን መልዕክት ስፅፍልህ መፅሐፍህን ለሶስተኛ ጊዜ አንብቤዋለሁ::"የሚል ነበር። ተመሳሳይ አስተያየት አንብቤ ባውቅም አንድም ይሄኛው ጥልቀት ያለው ትንተና የተካተተበት መሆኑ ሁለትም ማብራራት በማልችለው ምክንያት ከሌሎቹ ተመሳሳይ መልስ አልመለስኩም። ይሄ መልዕክት ከፊደላቱና ከሀሳቡ በተጨማሪ መንፈስ ነበረው:: አውስትራሊያ ሆና የፃፈችበትን ስሜት አዲስ መንፈስ አጋብቶብኛል።

"ውድ ማርታ ስለመፅሐፌ ለፃፍሻቸው ውብ ሙገሳዎች ከልቤ አመሰግናለሁ። በፃፍሽልኝ መልዕክት ስለመፅሐፍት ያለሽን ሰፊ ግንዛቤ ማወቅ በመቻሌ ምክንያት ያንቺን አድናቆት ማግኘት
ከፍ ያለ ደስታ አለው። ያንቺ የኑሮ መንገድ ከየትኛው የመፅሐፉ ታሪክ ጋር እንደተመሳሰለ ባላውቅም ከፃፍኩት ታሪክ ውስጥ በአንዱ ተመሳሳይ ጉዳት እንኳን ተጎድተሽ ከነበር ላለፍሽው
ሀዘን አዝናለሁ:: አንዳንዴ የተሰማሽን መተንፈስ ከፈለግሽ እና ይረዳኛል ብለሽ ካሰብሽ ፃፊልኝ፡፡ በድጋሚ አመሰግናለሁ::" ብዬ መለስኩላት:: የእኔና የማርቲ እውቂያ የጀመረው በእነዚህ
የመልዕክት ልውውጦች ነበር፡፡ በተደጋጋሚ ከተፃፃፍን በኋላ የብዕር ጓደኛሞች ለመሆን ተስማምተን በየቀኑ መፃፃፍ ቀጠልን፡፡ በቀን ሁለቴ... ሶስቴ... አራቴ አምስቴ...መቁጠር አቆምን፡፡ ያወቅኳት መሰለኝ፡፡ ያወቀችኝ መሰላት።በየሰዓቱ ስለምታደርገው ጥቃቅን ነገር ሳይቀር ከፎቶዎቿ ጋር
እያያያዘች ትፅፍልኛለች:: ከሁለት
የዘለለ ልኬላት ባላውቅም ፤ አዋዋሌን በሙሉ ባልፅፍላትም ለፃፈችልኝ ቁጥር
ያህል ጊዜ መልስ እፅፍላታለሁ፡፡ በጠዋት ዓይኖቼን ስገልጥ ማየት የምመኘው የእርሷን መልዕክት ሆነ። በሆነ ምክንያት ሳትፅፍልኝ ካረፈደች ስጋቴ እያንዳንዷን ደቂቃ የመላ ምት ቁልል እየደረመሰ ሊያሳብደኝ ይደርሳል፡፡ ምክንያቱም ለማርቲ ምንም ጥቅምም ሆነ ዕውቀት የማይደምርላት ዝባዝንኬ ሳይቀር ስፅፍላት በዊልቸር እንደምሄድ እና መናገር እንደማልችል ፅፌላት አላውቅም:: አታውቅም! ማርቲ ስልክ ደውላ ድምፄን መስማት ሳትፈልግ ቀርታ ወይም ምስሌን እያየች ልታወራኝ
ሳትጨቀጭቀኝ እረስታ አልነበረም አጋጣሚው ያልተፈጠረው፡፡ለቀናት እስከመኮራረፍ ያደረሰን ምክንያት ሆኖ ያውቃል፡፡በደሌን የምትቆልልብኝ የምሰጣትን ቀሽም ምክንያት ሁሉ
ስታምነኝ ነው። በእርግጥ በሆነኛው ቀን በስካይፒ ካላየሁህ ብላ ከልቧ ስላመረረች የሚከሰተውን ለመቀበል
ራሴን አሳምኜ ኮምፒተሬ ፊት ተቀምጬላትም ነበር፡፡ በሚቆራረጠው ኔትወርክ ምክንያት ከሰከንዶች የዘለለ መተያየት አልቻልንምና በቅን ልቧ ኔትወርኩ ብልሹ ስለነበር ድምፄን መስማት አለመቻሏን እንጂ
ዲዳነቴን አልተጠራጠረችም።

ለእንደኔ ዓይነት ሰው ይሄን እድል ማን ይሰጠው ነበር? ማርቲስ ብትሆን እውነቱን ብታውቅ የሰጠችኝን ፍቅርና ያሳየችኝን ህልም መሰል ቀን ትሰጠኝ ነበር? ምንም መጨረሻው ከህልም
መንቃት ዓይነት ቢሆንም እነዚህን ቃላት ማጣጣም የተለየ ነገር ነበረው፡፡ እና ለምን ብዬ እውነቱን ነግሪያት የደስታ ቀኔን
ላሳጥር? እንኳን ለመፈቀር መብቃት እንደሙሉ ሰው መታየት የሚናፍቀኝ ሰው ነኝ፡፡ በየመንገዱ የሚያየኝ ሰው አንዳች አሳዛኝ ገር እንደተመለከተ ከንፈሩን ሲመጥልኝ ስበግን የኖርኳቸው ዓመታት ጥቂት አይደሉምና በፍቅር መቆለጳጰስ ይቅርብኝ ማለት አልችልም ነበር፡፡ አንዳንዶች አፍ አውጥተው ይሄን
የመሰለ ልጅ... “እግዜር ለራሱ የሰራውን ያሳምራል:: የመሳሰሉ አሳማሚ አባባሎች ሲሉ እየሰማሁ የገፋሁት ቀን ጥቂት
አይደለምና ከማርቲ ፍቅር እውነቱን ነግሪያት የሚመጣውን መቀበል መምረጥ አይቻለኝም።

ቤክዬ ልይህ ስልህ ስትከለክለኝ እኮ አስቀያሚ ነህ ብዬ ደምድሜ ነበር፡፡ የላክልኝን ፎቶዎች እንኳን መጠራጠር ጀምሬ መፅሐፍህ ጀርባ ላይ ካለው ጉርድ ፎቶህ ጋር ስንቴ እንዳመሳሰልኳቸው
ባየህ!" ብላ ፅፋልኝ ነበር በዚያው ዕለት:: የፃፍኩላትን በሙሉ ባላምንበትም ደግማ እንተያይ ወይም ልደውልልህ እያለች
እንዳትጨቃጨቀኝ ፍቅር ከሚታየው ሳይሆን ከልብ መዋሃድ ጋር ብቻ መሆኑን በውብ ቃላትና ገለፃ አንዳንዴም በሚያሳምን ምሳሌ እያጣቀስኩ እፅፍለታለሁ። በእርግጠኝነት ያላመነችኝ
እንኳን ቢሆን ለትክክለኛው ምክንያት የቀረበ ግምት

አይኖራትም ነበር፡፡ ጉረኛ፣ ኩራተኛ፣ ቀብራራ፣ በራሱ የሚተማመን፣ የተረጋጋ...... ልታየኝና ልትሰማኝ አለመፈለጌን የምታመኃኝባቸው ፀባዮቼ ናቸው።

የምትዋሸው ወይ የምትደብቀው ታሪክህ የምታፍርበት ነው::ትላለች የኔዋ ረቂቅ:: ምናልባት ደግሞ የምትወደውን ነገር
የሚያሳጣህ ሊሆንም ይችላል። በእርግጥ እኔ የደበቅኳት ታሪኬን
ሳይሆን ተፈጥሮዬን ነው። እኔ በረከት ነኝ፡፡ መራመድም መናገርም የማልችል በረከት ለመሆን ያበረከትኩት አንዳችም
ጠጠር የለም:: ከአባዬ እና ከእማዬ ለመወለድ የሩካ ወንድም ለመሆን የኔ ፈቃድና ምኞት አይደለም:: የሆንኩትን ሆኜ ለመፈጠሬ የእኔ አስተዋፅኦ
ባዶ ነበር። ግንሳ? ፈቅጄ ባልመረጥኩት አፈጣጠሬ ጉድለት ሳቢያ ቀኖቼ ጎዶሎ ሆነውብኝ ነው ለመደበቅ የተገደድኩት።

ከአሁን ወደ ኋላ ንጄ ካስነበብኳችሁ ጣፋጭ ገፅ ወደ ፊት የጊዜን ካብ ስደረድር የኑሮን ጥፍጥና ለማጎምዘዝ ጊዜው የንስር ክንፍ ተውሶ ይንደረደር ነበር፡፡ እነዚህ ገዖች ጉራማይሌ ስሜት
የታጨቀባቸው ነበሩ።

"አንተ? ማታ እስኪሪብቶህን አገንፍለህ ነው እንዴ ያደርከው?"

"አንቺ ባለጌ ታላቅሽ እኮ ነኝ፡፡ አፍሽን አትክፈቺ!" እላታለሁ በእጆቼ ምልክት የእውነት እያፈርኳት፡፡ ክትክት ብላ በማፈሬ ትስቅብኛለች፡፡ ያሳፈረኝ የእርሷ ንግግር ብቻ አይደለም። ያለችው
እውነት መሆኑም ተደምሮ እንጂ፡፡
ከእንቅልፌ ከባነንኩ በኋላ ለማስታወስ ስሞክር ያልተከሰተልኝ መልክ ያላት ሴት ፈዛዛ የወይን ጠጅ ቀለም ያለው ስስ ቀሚስ ለብሳ የአልጋዬ ጠርዝ ላይ ተቀምጣ ስታጫውተኝ ነው ያደረችው:: ቁልጭ ብሎ ቅርፀ ምስሏ ባይታወሰኝም ቆንጆ እንደሆነች ይታሰበኛል።....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍5
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_አስራ_አንድ (የመጨረሻ ክፍል)


#በሜሪ_ፈለቀ

....በቀኝ እጅዋ የሌባ ጣት እንደመዳበስ ትነካካኛለች ምኔጋ እንደነካችኝ እንደነበረም ማስታወስ አልቻልኩም። ከእንቅልፌ ስባንን ጠዋት ሆኖ ሩካ ልትቀሰቅሰኝ በሬን እያንኳኳች ነበር። ከላዬ ተገፎ ከግማሽ በላዩ መሬት በተነጠፈ የልጋ ልብሴ አንሶላዬን እየሸፈንኩ እንድትገባ ነገርኳት
ይሄኔ ገብታ ነው “እስኪሪብቶህን
አገነፈልክ የምትለኝ።

“ተነስ እሺ አሁን ቁርስ እንብላ!"

“ማርቲ ልትመጣ ነው!" አልኳት የሚያስጮኃት አጀንዳ መሆኑን
ባውቅም እንደዚህ የምትዘል አልመሰለኝም ነበር፡፡ ጭንቀቴ
ወዲያው ጨንቋት ፈንጠዝያዋን ትታ ሀሳብ የገባት መሰለች::

"መቼ ነው የምትመጣው?" አለችኝ ማጥኛ ጠረጴዛዬ ጠርዝ ላይ
በግማሽ መቀመጫዋ እየተቀመጠች

“ከስድስት ቀን በኋላ! እና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም፡፡የማብድ እየመሰለኝ ነው:: የምትመጣው እኔን ብላ ነው።ያንቺንም ሰርግ ለመታደም ነው:: ሳትመጣ እውነቱን ብነግራት
አትመጣም:: ጭራሽ ዓይኗን ላላየው ነው:: መጥታ እውነቱን ስታየው ልትጠላኝ እንደምትችልም አውቃለሁ፡፡ የቱን መምረጥ እንዳለብኝ መወሰን አቃተኝ::” ከገለፅኩት ስሜቴ በላይ በጥልቀት
ምን እንደሚሰማኝ ሩካ እንደሚገባት አውቃለሁ።

“በርዬ በእውነተኛነት ስለመቆም ካንተ የተሻለ ልምዱ የለኝም፡፡የፍቅር ግንኙነትን አስመልክቶ ግን የተሻለ ልምድ ሳይኖረኝ
አይቀርም ነገሮችን ለመረዳትም ሆነ ለማስረዳት በአካል መገናኘትና በርቀት መነጋገር የትየለሌ ልዩነት አለው እስክትመጣ አፍህን ሰብስበህ ስትመጣ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር ለመቀየር ወይም ለመቀበል ራስህን ብታዘጋጅ የተሻለ ይመስለኛል።" አለችኝ ጭንቀቴን ልታቀልልኝ እየሞከረች።ያለችውን ቀላል አድርጋ ትበለው እንጂ ሊገጥመኝ የሚችለውን አስባ እንደፈራችልኝ አውቅባታለሁ፡፡ ልቤ እንዳይሰበር
ፈርታልኛለች:: እንዳልጨነቃት ስታስመስል አሁንም አሁንም ግንባሯን ታሻሻለች። አንዱ ከአንዱ የማይያያዝ ወሬ
ትዘላብዳለች፡፡ ቁርሴን ሰርታ አብልታኝ ስለማያገባኝ ሁሉ ነገር ዘባርቃልኝ ከቤት ወጣች፡፡

ማርቲ የረቂቅ ሰርግ መድረሱን ስታውቅ ለመምጣት መወሰኗን ስትነግረኝ ላስቆማት ብችል ደስ ባለኝ፡፡ በየትኛውም ጨዋታዬ ስለሩካ አለመጥቀስ የማልችለው ነገር ነውና ታውቃታለች:: ሩካ
እኔ ሳላውቅ ነበር መጀመሪያ የፃፈችላትና የተዋወቁት፡፡ በስልክም የተወሰኑ ቀናት አውርተዋል። የማውቃት የማውቃት
ይመስለኛል፡፡ ትለኝ ነበር ማርቲ ስለ እህቴ ስትፅፍልኝ። በምን ፍጥነት ተወዳጅተው መቆለጳጰስ እንደጀመሩ ግራ ያጋቡኝ
የሩካን የሙሽራ ቀሚስ በጋራ እንደመረጡ ሩካ የነገረችኝ ጊዜ
ነበር፡፡ በስካይፒ እንደሚያወሩ ያወቅኩት ስለማርቲ ቁንጅና የምትነግረኝ ቀን ነው:: በስምንት ወራት ውስጥ ከማርቲ ጋር
የተቆራኘንበትን ጥብቀት እያሰብኩ ወደ መኝታ ቤቴ ስገባ ሳራ አንሶላዎቼን እየቀየረችልኝ ነበር። ዊልቸሬን ወደ ጠረጴዛዬ አስጠግቼ ኮንፒውተሬን ከፈትኩ፡፡ የማርቲን መልዕክት ፍለጋ።
የሳራ ዓይኖች ትከሻዬን ስለተጫኑኝ ለማራገፍ ቀና አልኩ።አልተሳሳትኩም:: የቀየረቻቸውን የቆሸሹ አንሶላዎች በእጇ ይዛ ቆማ ዓይኗን ጭናብኛለች፡፡ በጥያቄ አየኋት።

"አንሶላዎቹን ላጥባቸው ነው::" አለችኝ በቃሏ። አስተያየቷን ደምሬ ስሰማት ልትነግረኝ የፈለገችው አንሶላዎቹ የረጠቡበትን ምክንያት እንዳወቀች ነው የመሰለኝ፡፡ የማብሸቅ ዓይነት ፈገግታ
እያሳየችኝ ክፍሌን ለቃ ወጣች።

ስድስት ቀን እንዲህ አጭር ነው? በእንዲህ ያለ ውዝግብ ቀናት ውስጥ
ጊዜው የብርሃንን ፍጥነት ይዋሳል ፣ እሷ ልታገኘኝ ስለጓጓች ረዘመብኝ አለችኝ።እኔ ግን መገናኘታችን የሚጎትተው መዘዝ ፍራቻ ስለቆነደደኝ እንዲረዝም ብመኝም አጠረብኝ። እንዲህ የተወዛገበ ቀን ለራሴ እፈጥርለታለሁ ብየ አስቤ አላውቅም።

መምጫዋ ቀን ደረሰ:: እናም ሩካ እና ኤፍሬም አጅበውኝ እየጠበቅኳት ነው።
ከፍርሃቴ የተነሳ ልቤን የምተፋት
እስኪመስለኝ እየደለቀች ነው።እጆቼ እየተንቀጠቀጠ እና እያላባቸው የዊልቸሬን መደገፊያ በወጉ መንተራስ እቅቷቸዋል፡፡የለበስኩትን ስስ ሸሚዝ ማውለቅ እስኪያሰኘኝ እየሞቀኝ ነው፡፡
ሩካና ኤፍሬም ሀሳቤን በጭንቅ ከተሞላው ጥበቃዬ ለማሸሽ
ጨዋታ ይፈጥራሉ። ስለሰርጋቸው ጣጣ
ይነግሩኛል፡፡አልሰማቸውም ወይም ደግሞ ብሰማም አይስበኝም፡፡ በጭንቅላቴ ውስጥ እዚህም እዛም እኳትናለሁ።

“ብቻህን ብትቀበለኝ ነው ደስ የሚለኝ፡፡ እንዳገኘሁህ ሰው አየኝ አላየኝ ሳልል እስክጠግብህ ልስምህ ነው የምፈልገው::"ትናንትና ማታ ከፃፈችልኝ መሃል አሰብኩ፡፡

“የምትጠብቂው ዓይነት ሰው ሆኜ ባታገኚኝስ?" ብዬ መልሼ ፅፌላታለሁ።

'የምጠብቀው ዓይነት የለኝም:: የማውቀው ፍቅረኛ ነው ያለኝ፡፡
ጥቃቅን ልዩነቶች አያሳስቡኝም::" ነበር መልሳ የፃፈችልኝ፡፡

ትንፋሼ ቀጥ ልትል ትንሽ ሲቀራት ሻንጣዋን እየጎተተች ዓይኗን
በፍለጋ እያቅበዘበዘች ብቅ አለች:: ዊልቸሬን ወደኋላ አዙሬ መመለስ ነበር ያሰብኩት።ኤፍሬም ትከሻዬን ጨበጥ ጨበጥ ሲያደርገኝ ለመረጋጋት መጣር ጀመርኩ።በአንድ እይታ አወቅኳት፡፡ አቅራቢያዬ ሆናም ፍለጋዋን አላቆመችም። ሩካን አይታት ለፈገግታ ለማሸሽ የጀመረችውን ከንፈሯን ጨርሳ
ሙሉ ፈገግታ ከማሳየቷ በፊት አየችኝ። ከንፈሯን ሰበሰበችው።እኔ እንዴት ነው
ያልኩት? ፈገግኩ?አፈጠጥኩባት? ዓይኔን አሸሁ? የሆንኩትን እንጃ ብቻ
ድንጋጤዋ አቃዠኝ፡፡ ረቂቅ ብዙ ቅርቢያ እንዳለው ሰው ተጠመጠመችባት:: ማርቲ ደርቃ ቀርታለች፡፡ ዓይኗ ከዊልቸሬ
ላይ አልተነቀለም ነበር፡፡ ልቅረባት ልራቃት እያሰብኩበት ባልነበረበት ደቂቃ ኤፍሬም ዊልቸሬን ገፍቶ እግሯ ስር አደረሰው እና ለሰላምታ እጁን ዘረጋላት፡፡

"ኤፍሬም! የሩካ እጮኛ ነኝ! ስላንቺ ብዙ ሰምቻለሁ። እንኳን ደህና መጣሽ!" ለዘረጋላት እጅ አፀፋ እጁን እየዘረጋች
የተናገረውን የሰማችው አልመሰለኝም:: ፈዝዛ እያየችኝ ነው።ፈገግ አልኩ መሰለኝ። ከዛም እጄን ዘረጋሁላት በዘገምተኛ ሂደት ከኤፍሬም እጅ ያላቀቀችውን እጇን ሰዳ ጨበጠችኝ፡፡

"እንዴ? አትሳሳሙም እንዴ?" አለች ሩካ ምንም ያልተከሰተ እያስመሰለች፡፡ ጉንጬን ልትስመኝ ዝቅ አለች፡፡ አዟዙሬ
አቀበልኳት፡፡ ለተወሰነ ሰከንድ የሚያሳብድ ዓይነት ረጭታ ሆነ።

"እንንቀሳቀስ አይደል? የተቀረውን ናፍቆታችሁን እቤት ትወጡታላችሁ።" አለች አሁንም ሩካ ቶሎ ተሽቀዳድማ
አንደኛውን ሻንጣ ለመግፋት እየተሰናዳች፡፡ ሌላኛውን ሻንጣ
ኤፍሬም ያዘ፡፡ ዊልቸሬን ለመንቀሳቀስ አዞርኩ፡፡ ማርቲ እስከአሁን ዓይኗ ከእኔ ላይ አልተነቀለም።

"አይይ እኔ እንኳን ሆቴል ሄጄ ትንሽ ባርፍ ሳይሻለኝ አይቀርም።" አለች በደከመ ድምፅ:: በእርግጥ እቅዳችን እቤት
ከነሩካ ጋር ምሳ በልተን አብረን ወደ ሆቴሏ መሄድ ነበር። እኔ ማለቷ የጠበቅኩት ስለነበር ብዙም አልገረመኝም፡፡

“ኸረ በጭራሽ! እቤት ላንቺ ተብሎ ምሳ ተዘጋጅቷል፡፡ ሻወር መውሰድ ከፈለግሽም እቤት ትተጣጠቢያለሽ!" አለቻት ሩካ።መልስ ሳትመልስ ወደ መኪናችን ተከተለችን። ከዊልቸሬ ወደ
መኪና ለመግባት ተደግፌ ስነሳና ተንፏቅቄ ስቀመጥ እንደ ተዓምር አፍጥጣ እያየችኝ ነበር፡፡

ይሄ አቃጣሪ ጊዜ ህይወቴን ጣእም አልባ ሊያደርገው እንደሚናድ ድንጋይ ካብ ተንደርድሮ አሁን ላይ ደረሰ። ማርቲ ምሳ አብራን ከታደመች በኋላ ወደ ሆቴሏ ከሄደች ሁለት ቀን አለፈ።ላልቆጠርኩት ያህል ጊዜ ፃፍኩላት። ለአንዱም አልመለሰችልኝም።ሆቴሏንም መልቀቋን አረጋገጥኩ ኢትዬጵያ ውስጥ ልትጠይቀው የምትችለው ዘመድ እንደሌላት አውቃለሁ። ወይ ወደ ሃገሯ ተመልሳለች
👍4