አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
479 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_ስምንት


#በሜሪ_ፈለቀ

ጥቁርና ነጭ አይደሉ? ቢሆንም የከዳሁት ልቡ አንደኛውን ሲሄድ ህመሜን ደምሬ ልታመም ወስኜ ዛሬ አብሬው ጠፋሁ። እኔ የጊዜ ዑደትን ማስላት ምን ሊረባኝ ያልኖርኩባትን ነገ ትቶኝ ይሄዳል ብዬ ዛሬዬን ልብከንከን? ኤፍሬምን በተመለከተ ከነገ እውነት የዛሬ ስሜቴ ልክ ነው። ከእርሱ ጋር አንድ ቀን ዘልአለም ነው አንድ አይደለም። ከእርሱ ጋር አንድ ቀን ዘለዓለም ነው። ዘለዓለም
ደግሞ ውሱን አይደለም፡፡ ዛሬ ዘለዓለም ናት! ስለዚህ ከርሱ ጋር ዘለዓለም መኖር ምርጫዬ ሆነ፡፡

"ደህና እደሪ" ሲለኝ ፀጉሩን እንደዳበሱት ህፃን አንቀላፋሁ።

"እወድሻለሁ" ያለኝ ቃል በጆሮዬ ለብዙ ዘለዓለም ቀናት ተንቆረቆረ።

ዘለዓለም ጥግ ኣልባ ነውና ዛሬ ለኔ ያለው ስሜት ጥግ አልባ ነው። ያንን ብቻ አምናለሁ። ነገ ስለመለያየቴ መርሳት ፈለግኩ፡፡ዘለዓለም ከእርሱ ጋር አለሁና! እስከሁሌው እቅፍ ውስጥ ብኖር
ብዬ ሳሳሁ። ጠዋት ተመልሰን ስለየው የመጨረሻዬ እንደሆነ እያወቅኩ ነበር በስስት የሳምኩት።እናም "ደህና ዋይልኝ" ሲለኝ ቀጥሎ ሊፈጠር ስለሚችለው ክስተት ሳላስብ ከደህና በላይ ሆንኩ፡፡ ከእርሱ ተለይቼ ብዙም ሳልቆይ አያሌው ደወለልኝ። እመኑኝ ኤፍሬምን ላለማጣት እናትና ወንድሜን አያስከፍለኝ
እንጂ ምንም አደርግ ነበር፡፡ አሁን ግን
ተመሳቅሏል፡፡እውነቱን ብነግረውም አብሮኝ ስለመዝለቁ ዋስትና
የለኝም፡፡

“ምን ብታቀምሺው ነው? ንግስቴን አመስግናት ሲለኝ እንኳን ያላፈረኝ?" አለኝ፡፡ ዝም አልኩት፡፡

“ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ላግኝሽ?" ብሎ ቀጠረኝ:: በድኔን እየጎተትኩ
ደረስኩ። ብሩን በቦርሳ በካሽ ሰጠኝ:: የማይሆን ነገር ባስብ በበርዬ ያስፈራራኝን ደገመልኝ።ከአንድ ሰዓት በኋላ እንደሚፈርምለት እየፈነጠዘ ነግሮኝ ተለያየን።ታክሲ ይዤ እየሄድኩ በመስኮቱ
አሻግሬ አያለሁ።ታክሲው ጎን የቤት መኪና አየሁ ውስጡ የነበሩት ሰዎች ትኩረቴን ሳቡት።አያሌውን የኤፍሬም እናት።አልተሳሳትኩም፡፡ ከንፈር ለከንፈር እየተሳሳሙ ነው ያየሁት።በደስታ
የሰከሩ ይመስላሉ፡፡ እናትየው የፋብሪካው ድርሻ እንዲሽጥ መወትወታቸው የተለየ ምክንያት ሊኖረው
እንደሚችል እንዴት አልጠረጠርኩም? የማደርገው ጠፋኝ፡፡

ቢሮው እያለከለኩ ስደርስ ብዙም አልዘገየሁም። የማደርገው ነገር የሚያመጣውን ቀውስ ማሰብ አልፈለግኩም፡፡ ሊፈርም
ያዘጋጃቸውን ሰነዶች እንደያዘ ኤፍሬም ፈዞ ያየኛል። የሆነውን አንድ በአንድ ነገርኩት። ገንዘቡን ለአያሌው ጠረጴዛው ላይ አስቀመጥኩለት።

"እኔጋ የሚቀርህን ገንዘብ እመልስልሃለሁ፡፡" ብዬው ስወጣ
ለመጨረሻ ጊዜ የኤፍሬምን ፊት አየሁት:: ደንዝዟል።ለመጨረሻ ጊዜ ይህን አለ፡፡

"ያ ሁሉ ለክፍያ ነበር?"

ኤፍሬም ድጋሚ ሊያየኝ እንደማይፈልግ የስንብት በሚመስል የመጨረሻ መልዕክቱ በስልክ አሳውቆኛል: ህይወት አስጠላኝ፣ እማዬና በርዬ እኔን ማባበል ስለቻቸው።በርዬ መፅሀፉን
የሚያሳትምለት አሳታሚ ድርጅት አጊንቶ ከስድስት ወር በኋላ ታተመለት:: ርዕሱ 'ምርጫ አልባ ምርጫ መሆኑን ያወቅኩት
ልናስመርቅ ስንሰናዳ ነው:: ሁሉ ነገር ቢያስጠላኝም የበርዬ ህልም መሳካቱ በተወሰነ መልኩ የደስታ ምንጭ ሆኖልኛል።መደበቂያዬ መፅሀፍ ማንበብ ሆኗል፡፡ ከማይገፋ የብቸኝነት ወራት በኋላ በርዬ ሱፍ ለብሶ፣ እኔ የሀበሻ ቀሚስ ለብሼ የመፅሀፉ ምረቃ ዝግጅት ላይ ከመታደማችን በፊት እማዬጋ
ሄድን፡፡ በደስታ አነባች:: መገኘት ባትችልም በልጆቿ ደስታ በማያባራ እንባ ታጠበች። ይህቺን ቀን እውን ለማድረግ ብዙ አልፌያለሁ እና አብሪያት አለቀስኩ፡፡

አዳራሽ ውስጥ ስንገባ ሰዓት ገና ቢሆንም ወዲህ ወዲያ የሚሉ
ሰዎች ነበሩ፡፡

"ሩካ?" የሰማሁትን ድምፅ ማመን አቅቶኝ ዞርኩ፡፡ ኤፍሬም የበርዬ መፅሀፍ ምረቃ ላይ ምን ይሰራል? አላችሁ? እኔም
ራሴን እንዲያ ከጠየቅኩ በኋላ ወዲያው
እስካሁን ያላስተዋልኩትን ነገር አስታወስኩ፡፡ የመፅሀፉ ሽፋን ላይ
አሳታሚና አከፋፋይ ተብሎ የተፃፈው የኤፍሬም ድርጅት ስም ነው።

"ወይዬ” አልኩት የምለው ጠፍቶኝ፡፡ በርዬ ዊልቸሩን እየገፋ አጠገቤ ሲደርስ ፍፁም በወዳጅነት መንፈስ ተቀላልደው አልፎን ሄደ፡፡ እንደትንግርት የሚሆነውን ከማየት ውጪ ምርጫ አልሰጡኝም:: በርዬ አልፎኝ ከሄደ በኋላ በአይኑ ጠቀሰኝ፡፡ እንዴትና የት ተግባቡ

“ይሄን መፅሀፍ ካነበብኩ በኋላ እንደገና ላውቅሽ እንደሚገባ ወሰንኩ።ኤፍሬም!!" አለኝ እጁን እየዘረጋልኝ፡፡

"ረቂቅ" አልኩት እጄ ሳላዘው ሊጨብጠው እየተዘረጋ።

።።።።።።።።
እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው።ያንተ ግራ የኔ ቀኝ ነው 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ ። እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል።እንደኔ አቋቋም ደግሞ የኔ ትክክል ይሆናል። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ።የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራው ስዳኝህ እቀሽማለው።
።።።

#በረከት

እሷ ዋሸኸኝ ነው የምትለኝ፡፡ እኔ ደግሞ አልነገርኳትም እንጂ ዋሸኋት ብዬ አላሰብኩም ወይም እንደዛ ማመን አልፈልግም።በእርግጥ ያልነገርኳት አለመነገር የሚችል አልያም ባይነገርም
በእኔ እና በሷ ግንኙነት ሂደት ለውጥ የማይፈጥር ዝባዝንኬ ሆኖ አልነበረም
እሷን እስከማጣት የሚስቀጣኝ ሊሆን
እንደሚችል አውቅ ነበር።ግን ማወቅ ከባድ አይደለም መኖር እንጂ! ያወቁትን ሁሉ መኖር የሚቻል ቢሆን ኖሮ ይህች ዓለም ከብዙ ስህተቶችና ጥፋቶች በተረፈች ነበር። ምክንያቱም የማይረቡ የምንላቸውን ጭምር አብዛኛዎቹ ጥፋቶች ባለማወቅ የሚደረጉ አይደሉም።

"ይቅርታ ውዴ! አንቺን ለመጉዳት ብዬ ያደረግኩት ምንም ነገር የለም። እመኚኝ፡፡" ብዬ የስልኬ መልዕክት መፃፊያ ሳጥን ውስጥ ካሰፈርኩ በኋላ ስልኩን አቀበልኳት::

“ታዲያ ለምን ዋሽኸኝ? ያን ሁላ ጊዜ ስንፃፃፍ ላንተ ጨዋታ ነበረ? እያሾፍክብኝ ነበር?" እኔ ከፃፍኩላት ስር ይሄን ፅፋ
ስልኩን መለሰችልኝ፡፡ በኖርኩባቸው የሃያ ሰባት ዓመት የዕድሜዬ ቁጥር ልክ ብዙዎች በተለያየ ምክንያት ሲያዝኑ እና ሲሰበሩ አይቼ አውቃለሁ። እሷ ላይ በማነበው ልክ ፊት ላይ የተገለጠ መሰበር አስተውዬ ማወቄን እጠራጠራለሁ፡፡ ምክንያቱ እኔ መሆኔ ደግሞ በሰባት ዓመቴ ወድቄ የተሰበረ እጄ ሲታከም ከተሰማኝ ህመም በላይ ያማል።

“በፍፁም አልነበረም:: የፃፍኩልሽን እያንዳንዷን ቃል እና ስሜት
ከልቤ ነው ያልኩሽ! የፃፍሽልኝ እያንዳንዱ ቃል ደግሞ በዘመኔ ሁሉ እየመነዘርኩት ደስታን የምሸምትበት ሀብቴ ነው ።
ስለሚቀጥለው ግንኙነታችን ልብሽ የሚልሽን አድርጊ ስላለፈው
ግን እመኚኝ የተሰማሽም የተሰማኝም እውነት ነበር። በዛሬው ጥርጣሬሽ ትናንትናችንን አታርክሺው ይሄን ፅፌ አቀበልኳት።አንብባ ስትጨርስ መልስ መፃፍ ጀመረች፡፡ ስልኩን መልሳ
ስታቀብለኝ ግን ምንም የተፃፈ መልዕክት የለዉም፡፡ ልቧን በቃላት ማስፈር የተሰማትን ስሜት ማቅለል ሆነባት የተወችው መሰለኝ።

ሩካ እና ኤፍሬም በእኔና በማርቲ መሃከል የተከወነውን የስልክ መቀባበል እንዳላስተዋለ ለማስመሰል ለቡና ቁርስነት የቀረበው ፈንድሻ ላይ ራሳቸውን ጠምደዋል፡፡ሁላችንም በፀጥታ
ሀሳቦቻችንን እያላመጥን መሰለኝ ሩካ ቡናውን ፉት ስትል
ፉፉፉፉፉፉትታዋ እንኳን አንድ ጠረጴዛ ለከበብነው አራት ሰዎች ከጊቢ ውጪ ለሚያልፍ ሂያጅ የ'ቡና ጠጡልኝ መልዕክት ይነግራል፡፡

"አቦል ልድገማችሁ?" የሚለው የሳራ ድምፅ (ሩካ ከሶስት ወር በፊት የቀጠረቻት በእድሜ ገፋ ያለች የቤት ሰራተኛችን ናት፡፡
👍2😁1