የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.7K subscribers
8.91K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቀን_አንድ ፩/1 (የመጀመሪያ ቀን) ሰኞ

" #በነጻነት_ልንኖር_ክርስቶስ_ነጻነት_አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።" (ወደ ገላትያ ሰዎች 5:1)

ክርስቶስ በሞቱና ትንሳኤዉ ከህግ ቁጥጥርና አድርግ አታድርግ ከሚል ስርአት ወደ ጸጋዉ ሕይወት ነጻ አዉጥቶናል ፡፡

በእርግጥ ሕጉ የሚታዘዙትን (የሚፈፅሙትን) ቢያጸድቃቸዉም የሰዉ ልጅ በሙሉ ግን በፍፅምና ሕጉን መጠበቅ ተስኖት የኃጢአት ባሪያ ሁኖ ሕይወቱን መርቷል ፡፡ ኢየሱስ ግን ራሱ በመስቀል የሁላችንን ኃጢያት ሁኖ ተሰቅሎልን በሕግ ከመጽደቅ ያለ ስራ በፀጋዉ ወደ መፅደቅ ነፃነት ወሰደን ፡፡
#ክርስቶስ_በሕግ_ሳይሆን_በጸጋዉ_አጽድቆናል ፡፡ ከዘላለም ሞትና ፍርድ ነፃ አዉጥቶናል
#ቀን_ሁለት ፪/2 ማክሰኞ

" ... #የልጁም_የኢየሱስ_ክርስቶስ_ደም_ከኃጢአት_ሁሉ_ያነጻናል።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7)

ከአዳም ጀምሮ የሰዉ ልጅን ባሪያ አርጎ ሲገዛ የነበረዉ ፣ ወደማይፈልግበት የሚነዳዉ ትልቁ የሰዉ ልጅ ጠላት ኃጢያት ነበር ፡፡ ኃጢያት ደግሞ የሚሰራ ብቻ ሳይሆን የሰዉ ማንነት ሆኖ ሰዉን ከአምላኩ አጣልቶ ከወንድሙ አባልቶ የሰዉ ልጆችን ሁሉ በምድር ያልተገባ ሕይወት እንዲኖሩ የሚያስገድድ ሀይል ነበር ፡፡
የሰዉ ልጆች በዘመናቸዉ ከጥንት ጀምሮ ከዚህ ጨቋኝ ገዢ ለመላቀቅ ቢያስቡም የሚቻልና የሚዘለቅ አልነበረም ፡፡ አምላክም ፍጡሩን ስለሚወድ ከዚህ እንዲወጡ የተለያየ መንገድ ሲያዘጋጅላቸዉ እንደነበር መፀሀፍ ቅዱስ ይነግረናል ፡፡ ይሁን እንጂ የሰዉ ልጆች አምላክ የሰጣቸዉን ህግ ለመጠበቅ ሲጣጣሩ ነገር ግን ሳይችሉ ደግሞም መስዋት በማቅረብ ለኃጢአታቸዉ ስርየት ደም ሲያፈሱ እንደነበር ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል ፡፡

ይህም ሆኖ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልተቻለም ፡፡ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ስለ ሰዋች ሁሉ ኃጢያት መስቀል ላይ ሰዋዉ ፡፡ ልጁም ኢየሱስ ስለኛ ታዞ በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰልን ይህንንም ደም ይዞ ስለኛ ዘወትር ሊማልድ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ አሁን በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ ባፈሰሰዉ ደም ኃጢያታቸዉን ሊያነጻ ስለኛ በአብ ዘንድ ጠበቃ ሆኖ ተቀምጧል ፡፡

የኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያድናል ፡፡ ወንድሜ ፥ በኃጢያት ዉስጥ አለህ ፣ ማንነትህ ኃጢያት ነዉ ? እንግዲያዉስ ኃጢአትህን ሁሉ ሊያነፃ ወደሚችል ወደ ኢየሱስ ተመለስ ፡፡

ማመሳከሪያ ጥቅስ ፦
" የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:34)
#ቀን_አምስት ፭/5 አርብ

" እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል። "
(ወደ ዕብራውያን 9:28)

በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምነን ለዳንን እኛ ፦ በአብ ዘንድ ሁልጊዜ የሚታይልን ዘራችን ፣ ቋንቋችን ፣ የትምህርት ደረጃችን ፣ የሀብት መጠናችን ፣ የጤና ሁኔታችን ሳይሆን ስለኛ እንደተሰቀለ ያመነዉ ክርስቶስ ነዉ ፡፡ እሱ ደግሞ በእግዚአብሔር አብ ፊት ቅዱስ መስዕዋትና ለእኛ ጠበቃ ነዉ ፡፡

መስቀሉን ስናስብ ፍቅሩን እናስታዉስ ፤
መስቀሉን ስናይ የተከፈለልንን አንርሳ ፤
ይህ ሁሉ ስቃይ ፣ ይህ ሁሉ መከራ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የደረሰዉ እኛን ከዘላለም ፍርድ ለማዉጣት ስለኛም በአብ ፊት በፍፅምና ለመታየት ነዉ ፡፡

#መልካም_ቀን
👍1
#ቀን_ሶስት ፫/3 ረቡዕ

" አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ #በክርስቶስ_ኢየሱስ_ሆናችሁ_በክርስቶስ_ደም_ቀርባችኋል ።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:13)

ሰዋች ሁላ በኃጢአታችን ምክንያት የቁጣ ልጆች የነበርን ሲሆን ከእግዚአብሔር ክብር ርቀን በመከራ በሀዘን እንኖር ነበር ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ በደላችንና ስለ መተላለፋችን ባፈሰሰልን ደም ወደ እግዚአብሔር ክብር መቅረብ ሆነልን ይህም ሳይበቃ የእግዚአብሔር ወራሽ አደረገን ደግሞም እግዚአብሔርን እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብርም እየለወጠን ልጆቹ አደረገን፡፡

ድሮ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለእርሱ ሕዝቦች ባዳ ሁነን እንኖር ነበር አሁን ግን ቤተኛ ብሎም ልጆች ሁነናል ፡፡

እዩት ኢየሱስን መስቀሉ ማማሩ
ለተመራመረዉ ብዙ ነዉ ሚስጥሩ !

በእዉነት ለሰዉ ልጆች በመስቀል ላይ የተሰራዉ ስራ ከመረዳት ያለፈና የሰዉ ልጅ ታሪክን ላንዴና ለመጨረሻ የቀየረ ስራ ነዉ ፡፡ በመስቀል ላይ በክርስቶስ ያየነዉ ፍቅር ለስፋቱ ድንበር ፣ ለጥልቀቱ መድረሻ የሌለዉ እጅግ በጣም ሰፊ የሆነ ነዉ ፡፡
#ቀን_አራት ፬/4 ሀሙስ

" የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ #ከአቤልም_ደም_ይልቅ_የሚሻለውን_ወደሚናገር_ወደ_መርጨት_ደም_ደርሳችኋል ።"
(ወደ ዕብራውያን 12:24)

በመስቀል ላይ የፈሰሰልን ደም ተራ የአንድ ሰዉ ደም ብቻ አይደለም በመስቀል ላይ የፈሰሰዉ ደም አምላክ ሰዉ ሁኖ ስለኛ መተላለፍና በደል የከፈለዉ ዋጋ እንጂ ፡፡ ይህ ደም እንደ ዋዛ ፈሶም የቀረ ደም አይደለም ይልቁንስ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር
ስለ ምህረት ፣ ይቅርታ ስለኛ የሚጮህ ነዉ ፡፡

" አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። "
(ኦሪት ዘፍጥረት 4:10)

በእርግጥ ቃየን ወንድሙ አቤልን ሲገለዉ የአቤል ደም ስለ ራሱ ፍትህ ወደ እግዚአብሔር ይጮህ ነበር በመስቀል ላይ ስለኔና ስለናንተ የፈሰሰዉ የንጉሳችን ኢየሱስ ደም ግን ስለ ራሱ ሳይሆን ስለኛ ምህረትና ይቅርታ ዘወትር ይጮኸል ፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ከአቤል ይልቅ ለሚጮኸዉ ደም እንዴት ምህረቱን በኢየሱስ በኩል ለህዝቡ አይሰጥ???!
#ቀን_ስድስት ፮/6 ቅዳሜ

" ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:14-15)


እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ጊዜ ህዝቡን ከስጋ ሞት ሊያድን ሙሴን የነሀሱን እባብ በመስቀል ላይ እንዲሰቅል አደረገ ፡፡ ያንን የተሰቀለ እባብ ያየ ሁላ ከስጋዉ ሞት ይድን ነበር ፡፡ በእርግጥ በመስቀል ላይ የተሰቀለዉ እባብ የሚወክለዉ እርግማንንን ሀጢያትን ክፋትን በደልን ነበር ፡፡

በሚሻለዉ በአዲሱ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ህዝቡን ከስጋዊ ሞት ሳይሆን ከስጋ ሞት ከሚከፋዉ ዘላለማዊ ሞት ሊያድን አንድያ ልጁን በመስቀል ላይ እንዲሞት ወሰነ ፡፡ ኃጢያት የማያዉቀዉንም ቅዱስ ልጁን በመስቀል ላይ ስለሁላችን በደል ኃጢያት አርጎ ስለኛ ክፋት እኛን ለማዳን ሰቀለዉ ፡፡


ማጣቀሻ

(ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ 21)

6፤ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ እባቦችን ሰደደ፥ ሕዝቡንም ነደፉ፤ ከእስራኤልም ብዙ ሰዎች ሞቱ።

7፤ ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው። በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ስለ ተናገርን በድለናል፤ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን አሉት።

8፤ ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን። እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፤ የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው።

9፤ ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ 5:21

እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።
መልካም ቀን!
#ቀን_እሑድ ፯/7 እሁድ

" በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።"
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2:14)

ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰዉ ልጆች ሁሉ በደል ሲሰቀል ከኛ ላይ ያልገፈፈልን ነገር አልነበረም ፡፡ የዘላለም ሞታችንን ፣ አበሳችንን መከራችንን ስቃያችንን እንዲሁም በበደላችን ምክንያት የነበረብንን የዕዳ ጽሕፈት አንድ ሳያስቀር በሱ በማመናችን ብቻ አስወገደልን ፡፡ ክብር ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን፡፡

መልካም ሰንበት!
#ቀን_ስምንት ፰/8 #ሰኞ

#ሞት_ጥፋት_እልቂት_ከሀገራችን_ይወገድ !

" ሙሴም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠርቶ አላቸው። በየቤታችሁ ጠቦት ምረጡ፥ ወስዳችሁም ለፋሲካ እረዱት።"
(ኦሪት ዘጸአት 12:21)

በብሉይ ኪዳን የሞት መለአክን በር መቃን ላይ የጠቦት ደም በመቀባት አምልጠዋል ፤ እኛ የአዲስ ኪዳን ነዋሪዎች ግን በእኛ ላይ ያለዉ ከዘለአለም ሞት የሚያስመልጠን የክርስቶስ ደም በእኛ ላይ አለ፡፡

ደሙ በመቃኔ ላይ ስለተቀባ
ደሙ በጉበኔ ላይ ስለተቀባ
ሞት አለፈ ሄደ እራቀ ከእኔ ጋር
የጌታዬን ደም አይቶ
የኢየሱሴን ደም አይቶ (፪x)
ሞት አለፈ ፣ ሞት አለፈ
ሄደ ከእኔ ርቆ

መልካም ቀን !
#ቀን_ዘጠኝ ፱/9 #ማክሰኞ

" በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።"
(የዮሐንስ ራእይ 5:12)

ክብር
ክብር
ክብር
ክብር
መስዋዕት ሆኖ ላዳነን ለጌቶች ጌታ ለነገስታት ንጉስ ኢየሱስ ይሁን ፡፡



መልካም ቀን !
#ቀን_አስር ፲/10 #ረቡዕ

" ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፥ በዕቃ ውስጥ ባለውም ደም ንከሩት፥ በዕቃውም ውስጥ ካለው ደም ሁለቱን መቃኖችና ጉበኑን እርጩ፤ ከእናንተም አንድ ሰው ከቤቱ ደጅ እስኪነጋ ድረስ አይውጣ።"
(ኦሪት ዘጸአት 12:22)

እስራኤላዊያን በግብፅ ሳሉ የበራቸው መቃን ላይ የጠቦት ደም በመቀባት የሞት መለአክን አምልጠዋል ፤ እኛ የአዲስ ኪዳን ነዋሪዎችን ግን ከከበበን የዘለአለም ሞት የሚያስመልጠን የክርስቶስ ደም ነዉ፡፡

#ምህረት_ኢተፋ
ደሙ በመቃኔ ላይ ስለተቀባ
ደሙ በጉበኔ ላይ ስለተቀባ
ሞት አለፈ ሄደ እራቀ ከእኔ ጋር
የጌታዬን ደም አይቶ
የኢየሱሴን ደም አይቶ (፪x)
ሞት አለፈ ፣ ሞት አለፈ ሄደ ከእኔ ርቆ

የሞት መልአክት አያስፈራኝ
ተሸፍኛለሁ አያገኘኝ (፪x)
ዙሪያዬ ከደሙ ታጥሯል
ያን ቅጥር አልፎ እንዴት ይገባል (፪x)

መልካም ቀን!
በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በደቡብ አዲስ አበባ ክላስተር ጽ/ቤት የተዘጋጀ ኮንፍራንስ
በእለቱ የእግዚአብሔር ቃል ይሰበካል / ለበሽተኞችና የተለያየ ችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች ይፀለያል / ይምጡ ሌሎችንም ያጋብዙ!
#ቀን ፡- ሰኞ ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም
#ቦታ፡- በሊቪንግ ክራይስት ኢንተርናሽናል ቸርች
#ሰዓት፡- ጠዋት ከ3፡00 – 7፡00
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የምትገኙ የካውንስሉ አባላት እንደዚሁም በሊቪንግ ክራይስት ኢንተርናሽናል ቸርች ያላቹህ ቅዱሳን በሙሉ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል፡፡
#አድራሻ፡-ከመብራት ሃይል ወደ ጋርመንት ሲሄዱ ያለ የመጀመሪያው ገላን ሕንፃ 4ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ፡- +251910915858 / +251911419667
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/Evangelical MEDIA/Council
ዩትዩብ፦ https://youtu.be/Uq8OHBV327w
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1👎1
በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በደቡብ አዲስ አበባ ክላስተር ጽ/ቤት የተዘጋጀ ኮንፍራንስ
በእለቱ የእግዚአብሔር ቃል ይሰበካል / ለበሽተኞችና የተለያየ ችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች ይፀለያል / ይምጡ ሌሎችንም ያጋብዙ!
#ቀን ፡- ሰኞ ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም
#ቦታ፡- በሊቪንግ ክራይስት ኢንተርናሽናል ቸርች
#ሰዓት፡- ጠዋት ከ3፡00 – 7፡00
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የምትገኙ የካውንስሉ አባላት እንደዚሁም በሊቪንግ ክራይስት ኢንተርናሽናል ቸርች ያላቹህ ቅዱሳን በሙሉ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል፡፡
#አድራሻ፡-ከመብራት ሃይል ወደ ጋርመንት ሲሄዱ ያለ የመጀመሪያው ገላን ሕንፃ 4ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ፡- +251910915858 / +251911419667
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/Evangelical MEDIA/Council
ዩትዩብ፦ https://youtu.be/Uq8OHBV327w
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃♂️🏃♀️🏃♂️🏃♂️
ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።
#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።
ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።
#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?
#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።
ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?
#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።
ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።
ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ
ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ" #አሜን መልዕክታችን ነው።
ምንጭ- The Christian News
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/7294xQsv7BI
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
2👍1👎1