#ቀን_ሶስት ፫/3 ረቡዕ
" አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ #በክርስቶስ_ኢየሱስ_ሆናችሁ_በክርስቶስ_ደም_ቀርባችኋል ።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:13)
ሰዋች ሁላ በኃጢአታችን ምክንያት የቁጣ ልጆች የነበርን ሲሆን ከእግዚአብሔር ክብር ርቀን በመከራ በሀዘን እንኖር ነበር ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ በደላችንና ስለ መተላለፋችን ባፈሰሰልን ደም ወደ እግዚአብሔር ክብር መቅረብ ሆነልን ይህም ሳይበቃ የእግዚአብሔር ወራሽ አደረገን ደግሞም እግዚአብሔርን እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብርም እየለወጠን ልጆቹ አደረገን፡፡
ድሮ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለእርሱ ሕዝቦች ባዳ ሁነን እንኖር ነበር አሁን ግን ቤተኛ ብሎም ልጆች ሁነናል ፡፡
እዩት ኢየሱስን መስቀሉ ማማሩ
ለተመራመረዉ ብዙ ነዉ ሚስጥሩ !
በእዉነት ለሰዉ ልጆች በመስቀል ላይ የተሰራዉ ስራ ከመረዳት ያለፈና የሰዉ ልጅ ታሪክን ላንዴና ለመጨረሻ የቀየረ ስራ ነዉ ፡፡ በመስቀል ላይ በክርስቶስ ያየነዉ ፍቅር ለስፋቱ ድንበር ፣ ለጥልቀቱ መድረሻ የሌለዉ እጅግ በጣም ሰፊ የሆነ ነዉ ፡፡