የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.7K subscribers
8.91K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቀን_አንድ ፩/1 (የመጀመሪያ ቀን) ሰኞ

" #በነጻነት_ልንኖር_ክርስቶስ_ነጻነት_አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።" (ወደ ገላትያ ሰዎች 5:1)

ክርስቶስ በሞቱና ትንሳኤዉ ከህግ ቁጥጥርና አድርግ አታድርግ ከሚል ስርአት ወደ ጸጋዉ ሕይወት ነጻ አዉጥቶናል ፡፡

በእርግጥ ሕጉ የሚታዘዙትን (የሚፈፅሙትን) ቢያጸድቃቸዉም የሰዉ ልጅ በሙሉ ግን በፍፅምና ሕጉን መጠበቅ ተስኖት የኃጢአት ባሪያ ሁኖ ሕይወቱን መርቷል ፡፡ ኢየሱስ ግን ራሱ በመስቀል የሁላችንን ኃጢያት ሁኖ ተሰቅሎልን በሕግ ከመጽደቅ ያለ ስራ በፀጋዉ ወደ መፅደቅ ነፃነት ወሰደን ፡፡
#ክርስቶስ_በሕግ_ሳይሆን_በጸጋዉ_አጽድቆናል ፡፡ ከዘላለም ሞትና ፍርድ ነፃ አዉጥቶናል