የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.7K subscribers
8.91K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንሰል መገለጫ ሰጠ።

ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ ወደ ምድራችን የሚመጡ የንስሐ ግቡ ሐልዕክቶች ሰለሆኑ ባላፈው ዓመት ታላቅ የአገራዊ ንስሃ ጊዜን በአደባባይ አከናውነናል። ይህንን ንስሃ መቀጠል ስለታመነበት የአገራዊ ንስሃ የሚያስተባብር ግብረ ኃይል በወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ይሁንታ ተቋቁሞ ተግባሮቹን በተሻለ መንገድ ለመወጣት በመሥራት ላይ ይገኛል።

ስለዚህ ፦

1.ከሚያዝያ 6 እስከ 11/2017 ዓ.ም ከሰኞ- ቅዳሜ በሉት የህማማቱ ሳምንት በመላው አገሪቱ ባሉ ማህበር ምዕመናን ቢቻልም በከተሞች አመቺ በሆኑ በተመረጡ አብያተክርስቲያናት በአንድነት በመሰባሰብ የኑዛዜና የንስሐ ቀናቶች እንዲሆኑ።

2. ከሚያዝያ 19 እስከ ግንቦት 17/2017 ዓ.ም ባሉት ሳምንታት ኑዛዜ ያደረግንባቸው ጉዳዮችን ወደ ፍሬ እንዲመጡ በየአጥቢያው የንስሐ አቅጣጫዎች የትምህርት እና ንስሃውን ከሕይወት ጋር የምሰናዛምድባቸው ጊዜያቶች እንዲሆኑ።

3.ግንቦት 24 ቀን 2017ዓ.ም በሁሉም ከተሞችና አካባቢዎች የማጠቃለያ የንሰሐ ጊዜ መሪዎች በየክልሎቻቸው የካውንስል እና የኀብረቶች አደረጃጀቶች እንዲያደርጉና በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ለአገር አቀፉ የማጠቃለያ የንስሐ ጊዜ ከልሉን የሚወክሉ መሪዎችን ወክለውና በክልሉ ቤተክርስቲያን መለኮታዊ ሥልጣን ጸልየውላቸው ወደ አዲስ አበባ እንዲልኩ።

4.ከግንቦት 25 አስከ 27 2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ከመላው ኢትዮጵያ ክልሎች እና ከዲያስፖራ በክልሎች ቤተክርስቲያን መለኮታዊ ሰልጣን በሚወከሉ መሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ማጠቃለያውን በተወከሉ መሪዎች የንስሐ ጊዜ በማድረግ የንሰሐ ማጠቃለያ እንዲሆን ታቅዷል።

በመላው ኢትዮጵያ እና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የወንጌላውያን አማኞች ሁሉ በዚህ በወጣው ፕሮግራም መስረት አሰተባባሪ ግብር ኃይል በልዩ ልዩ መገናኛ ዘዴዎች በሚያሰራጫቸው የንስሐ አቅጣጫዎች እና የኑዛዜ የጸሎት ርዕሶች አየታገዛቸሁ የንስሐ ጊዜውን አብረን በጋራ እንድናከናውን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

“ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ጕበኞችን በቅጥርሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንና ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምታሳስቡ፥ ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ።”ትንቢተ ኢሳይያስ 62፥6-7

ልዑል አግዚአብሔር አገራችንን ኢትዮጵያን ይባርክ!!

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ከርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ

መጋቢት 3/2017 ዓ.ም #ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🙏10👍53🔥2
📅 ማክሰኞ | ሚያዝያ 7 | 2017 ዓ፡ም
የንስሐ ጸሎት ርዕስ
የሕይወት ቀደም አገልግሎት ተጠያቂነት
ዝርዝር የንስሐ የጸሎት ርዕሶች
1. በውስጣችን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተስሎ የነበረውን ክርስቶስን ገሸሽ ስላደረግንበት ውድቀታችን
2. የክርስቶስ አምላክነቱና ጌትነቱ፣ እንዲሁም ፍቅሩና ምሕረቱ፣ ደግሞም ቤዛነቱና መሥዋዕታዊ ሞቱ ዳግመኛ በልባችን ማዕከላዊ ሥፍራ ላይ እንዲቀመጡ የጌታን ምሕረትና ዕርዳታውን እየለመንን እንጸልያለን፡፡
3. ቃሉን እና ፈቃደ-እግዚአብሔርን ያቃለልንበትን ፣ ደግሞም የዚህ ዓለምን ነገሮች ከሁሉ ያስቀደምንበትን የተበለሻሸውን ሕይወታችንን እያሰብን በፊቱ ንስሐ እየገባን እንጸልያለን፡፡
4. ጸጋውን ያክፋፋንበትንም ሆነ ዕውነተኞችና ደጋግ የጸጋው መጋቢ ያልሆንንበትን ልምምዳችንን በጌታ ፊት እያሰብን የንስሐ ጸሎትን እንጸልያለን፡፤
5. ሊከተሉን ያሉ ነገሮችን ስላስቀደምንበት መንገዳችን በጌታ ፊት ንስሐ እየገባን እንጸልያለን፡፡


https://youtu.be/-obGnDZOxSw?si=ac5j-3zxyhmBDHBb

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍2311🙏3
📅 ረቡዕ | ሚያዝያ 8 | 2017 ዓ፡ም
የንስሐ ጸሎት ርዕስ
የሕይወት ቀደም አገልግሎት ተጠያቂነት
1. በሥልጣን ሽሚያ ሰበብ በተነሡ ግጭቶች በምድራችን ላይ ስለ ፈሰሰው ደም፣ ስለ ተቀጠፉቱ
ነፍሶች፣ ስለ ተፈጸሙ የጅምላ ግድያዎች ንስሐ እየገባን እንጸልያለን፡፡
2. በምድራችን ላይ ያለች የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንም የጨውነት እና የብርሃንነት ሚናዋን በአግባቡ
ስላልተወጣችበት እና የፖለቲካ ሰዎች መጠቀሚያ ስለሆነችበት ሁኔታ በጌታ ፊት ንስሐ እየገባን
አንጸልያለን፡፡
3. በምድሪቱ ላይ ከጥንት እስከ ዛሬ ድረስ ስለሚፈጸሙ የፍርድ መዛባቶች እና የፍትሕ መታጣቶች
በጌታ ፊት ንስሐ እየገባን እንጸልያለን፡፡
4. በምድሪቱ ላይ ስለሚፈጸሙ ምግባረ ብልሹነት፣ ሙሰኝነትና ሌብነትና ዝርፊያ በጌታ ፊት ንስሐ
እየገባን እንጸልያለን፡፡
https://youtu.be/5qxLYnw0sB4?si=uCpjegKdZH276HGo

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍157🔥2
የንስሐ ጸሎት ርእሶች
📅 ሐሙስ | ሚያዝያ 9 | 2017 ዓ፡ም
1. የእግዚአብሔር መንግሥትን ምንነት በሙላት ስላልተረዳንበትና ለመንግሥቱም በሚሆን ተጠያቂነት ረገድ ወድቀን ስለምንታይበት ሁኔታ
2. ከውስጣዊ ነገሮች ይልቅ በውጫዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ስለምናደርግበት፣ በዚህም ደግሞ ከእግዚአብሔር አሳብና ፈቃድ ጋር መተላለፍ ስለ ተፈጠረበት ሁኔታ በጌታ ፊት ንስሐ እየገባን እንጸልያለን፡፡
3. የመንፈስን አንድነት እና ኅብረት በፍቅር ስላልጠበቅንበት ሁኔታ በጌታ ፊት የንስሐ ጸሎትን እንጸልያለን፡፡
4. እርስ በርስ ስለምንከፋፈልበትና በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንኳ ብዙ ቡድኖችን ስለምንፈጥርበት
መከፋፈላችን እና መቧደናችን በጌታ ፊት የንስሐ ጸሎትን እንጸልያለን፡፡
https://youtu.be/5qxLYnw0sB4?si=uCpjegKdZH276HGo

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🙏128👍3
#ጥብቅ_ማሳሰቢያ

ከሶስት አመት በፊት March 18/2022 የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አውጥቶት የነበረውን መግለጫ አሁን እንደተሰጠ በማድረግ በማህበራዊ ሚዳያዎች ላይ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ። ይህንን በማስመልከት
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተ_ክርስቲያናት_ካውንስል ጥብቅ ማሳሰብያ አስተላልፏል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🙏288👍8🔥4😢3
#የኢትዮጲያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተ_ክርስቲያናት_ካውንስል
#4ኛ_መደበኛ_ጠቅላላ_ጉባዔ
በአዲስ አበባ ጉዲና ቱምሳ ሁለገብ ማሰልጠኛ ማዕከል በይፋ ተጀመሯል፡፡


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
6👍1
#የኢትዮጲያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተ_ክርስቲያናት_ካውንስል
#4ኛ_መደበኛ_ጠቅላላ_ጉባዔ
በአዲስ አበባ ጉዲና ቱምሳ ሁለገብ ማሰልጠኛ ማዕከል


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
👍2014👎1🙏1
በአሜሪካን ኮሎራዶ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የዉይይት እና የአንድነት ጊዜ አካሄደ።

ሚያዚያ 25 ቀን 2017ዓ/ም በተካሄደዉ የዉይይት መድረክ በኮሎራዶ የሚገኙ የካዉንስሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ልዩ ልዩ የሚንስትሪ አገልጋዮች በዉይይት መድረኩ ተሳትፈዋል።

በኮሎራዶ የካዉንስሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ጌታቸው ታደሰ በእለቱ የእንኳን ደህና መጣቹ መልዕክት በማስተላለፍ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዉ የካውንስሉ አመሰራረት እና ጠቃሚነቱን በመግለፅ አብራርተዋል።

የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን በዋና ፀሃፊነት እያገለገሉ የሚገኙት ዶ/ር አድያምሰገድ ወልደማርያም የካዉንስሉ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ፥ ዓላማ ፥ ራዕይ እንዲሁም ቀጣይ ተግባራቶችን ለአባላቱ  በዘርዝር አቅርብዋል። ካዉንስሉ በአሜሪካ እና በአለም አቀፍ ሊሰሩ የታሰቡ ስራዎችን በማብራራት በኮሎራዶ ከሚገኙ አብያተክርስቲያናት እና ህብረት ጋር አሁንም ለመስራት ዝግጁ እንደ ሆኑ አስረድተዋል። በዚህም ከካውንስሉ ጋር በመተባበር አብረን ታላቁን ተልዕኮ በፍቅር እና በአንድነት እናገልግል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

መጋቢ ያሬድ ፀጋዬ ምክትል ዋና ፀሐፊ ሲሆኑ የካውንስሉ የትኩረት መስክ ፣ ሚዲያ ፣ የአባለት መብትና ግዴታ ዙሪያ በተመለከተ ማብራሪያ ሰተዋል።

በመጨረሻም ከአባል ቤተ እምነቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ሰፊ ማብራሪያ ተሰቶባቸዉ ስብሰባዉ ተጠናቋል።

#ሪፖርተር_ብንያም_ሱፋ

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
👍71
የዘማሪ አስፋው መለስ ስድስተኛው አልበም በተመለከተ ጋዜጣዊ መገለጫ ተሰጠ።

ሰኔ 24/2017 ዓ.ም የዘማሪ መጋቢ አሰፋው መለሰ ስድስተኛውን "አንተን አልጣ እንጂ" በሚል ርዕሰ የተዘጋጀው ሐምሌ 6 ቀን የሚመረቀውን አልበም በተመለከተ በሳሮማሪያ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል ።


ይህ የመዝሙር አልበም በማቴዎስ ወንጌል 6፥31 ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ነው። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይም “በ20 ዓመታት የአገልግሎት ጊዜዬ በማግኘትም በማጣትም ጌታን ብቻ አላጣውትም።” ሲል መጋቢ ዘማሪ አስፋው ተነግሯል።

የዘማሪ አስፋው መለሰ ስድስተኛ አልበም 2 አመታትን እንደፈጀ የተገለፀ ሲሆን በውስጡም 11 መዝሙሮችን መያዙ ተነግሯል።

ዘማሪ አስፋው "ብዙ ዘመን ራራህልኝ"፡ "በጅምር አይቀርም የኔ ነገር"፡ "ትላንት ዛሬ አይደለም"፡ "የሩቅ ህልሞቼ" እና "ይሁን" ከዚህ በፊት ለወንጌል አማኞች ያደረሳቸው የዝማሬ አልበሞች ናቸው።

አልበሙም ሐምሌ 6/2017 ዓ.ም በልደታ ጉባኤ አግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የወንጌል አማኞች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እንደሚመረቅ እና ዝማሬዎቹም ሐምሌ 6 በፓስተር አስፋው መለሰ ክራይስት ግሎሪ ዩቲዩብ ገጹ ላይ እንደሚለቀቅ ተገልጿል ።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
10🔥5
የጌጃ ቃለ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ለ 43ተኛ ጊዜ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ሰኔ 21/10/2017 ዓ.ም የጌጃ ቃለ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ የረጅም ዓመት ልምድ ያለውና በዘርፉም በርካታ ተማሪዎችን እያሰለጠነ የሚገኝ ተቋም ነው። በተካሄደው የምርቃት መርሀግብር ላይም የተመራቂ ቤተሰቦች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና አገልጋዮች ተገኝተዋል።

የጌጃ ቃለ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ በዲግሪ መርሀግብር የሰለጠኑ 24 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ካለፈው አመት ጀምሮ በተግባራዊ ስነ መለኮት የማስተርስ መርሀግብር የጀመረ መሆኑንና የአሁኖቹ ተመራቂዎች በስነ መለኮት እና ስነ አመራር መሰልጠናቸውም ተገልጿል።

የጌጃ ቃለ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ከተለያዩ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት የመጡ ተማሪዎችን በይፋ ባስመረቀበት ቀን የጌጃ ቃለ ሕይወት ሀ መዘምራን በዝማሬ አገልግለዋል።

የጌጃ ቃለ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ አካዳሚክ ዲን የሆኑት መጋቢ መስፍን ካሳ በበኩላቸው በማስተርስ የተግባራዊ ስነ መለኮት እንዲሁም በዲግሪ መርሀ ግብር ደግሞ በስነ መለኮት እና በስነ አመራር ተማሪዎችን እያሰለጠነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

መረጃውን ከኮሚሽኑ የሚዲያ ክፍል አገኘነው

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
2🔥1
በአማሪካ ውርጃን የሚቃወሙ ብድኖች በውርጃ አማካኝነት ሕይወታቸውን ያጡ ከ390,000 በላይ ልጆችን በማሰብ የዳይፐር እደላ አደረጉ።


የውርጃ ተቃውሚ የሆኑት ቡድኖች በጋራ በመሆን ከ390,000 በላይ ዳይፐሮችን ለወላጆች አድለዋል። ይህም የሆነው ሕይወትን የማክበር ፕሮግራም በተካሄደበት ጊዜ ነበር።


“Students for life of America” እና “Everylife”ን የመሳሰሉ የውርጃ ተቃዋሚ ቡድኖች በካፕቶል በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነውን ዳይፐር የማደል የማደል እንቅስቃሴ አካሂደዋል።


ይህም የሆነው በሀገሪቱ ውርጃን የመከልከል ምርጫ ለግዛት አስተዳደሮች ከተሰጠ አንድ አመት በሞላበት ጊዜ ነው። የተደረገው እንቅስቃሴ ዓላማው በውርጃ አማካኝነት ምን ያህል ልጆች ሕይወታቸውን እንዳጡ ለማስገንዘብ ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓትም እናቶችን ፣ ካለጊዜያቸውን የተወለዱ ሕጻናት እና ቤተሰቦችን ማገዝ ነው።


ፕላንድ ፓረንትሁድ የተሰኘው በአሜሪካ ግንባር ቀደም የውርጃ ማዕከል በ2022 እና በ2023 ስለ ሰራው ስራ ሲናገር 393,715 ልጆችን ማስወረዱን አሳውቆ ነበር።

በውርጃ አማካኝነት ሕይወታቸውን የሚያጡ ልጆች ቁጥርም በፈረንጆቹ 2024 መጨመሩን ቡድኖቹ ያነሳሉ።
መረጃውን ከሲቢኤን ሊውስ አገኘነው።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
1
በአርባ ምንጭ ልማት ቃ/ሕ /ቤ/ክ የመዘመራን ስልጠና ተሰጠ።

ከሰኔ 13 እስከ 15/ 2017 ዓ/ም በደቡብ ምዕራብ ቀጠና በአርባ ምንጭ ዙሪያ የህብረት ልማት የቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤ/ክ ለዝማሬ እና ለሙዚቃ አገልጋዮች መሠረታዊ ሥልጠና ተሰጥቷል ።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የአጥቢያዋ አዳራሽ የድምጽ ማስተጋባት ችግር ለአገልግሎቶች እንቅፋት እየሆነ በማስቸገሩ ሙያዊ ምክር እና አስፈላጊው የአኮስቲክ ሥራ እንዲጀመር ተደርጎ፣ በዕሁድ አምልኮ ለዚሁ ሥራ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤ/ክ የወጣቶች አገልግሎት የሙዚቃና አምልኮ ክፍል ብሔራዊ አስተባባሪ የሆኑት ወ/ም ረታ ጳውሎስ ይህ አይነቱ ስልጠና እና የአዳራሽ የድምጽ ችግር ማስተካከያዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን ገልጸው በየቀጠና ያሉ አጥቢዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አድርገዋል።

መረጃውን ከአገልግሎት ክፍሉ አገኘነው
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
8
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባ እና አካባቢው ክልል የልጆች አስተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ።


ሰኔ 21/2017 ዓ.ም በገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ በተካሄደው ስልጠና ላይ በክልሉ ከሚገኙ 98 አጥቢያዎች የተወጣጡ 350 የልጆች አስተማሪዎች ተገኝተዋል።

የዝማሬ እና የጸሎት ጊዜ የተደረገ ሲሆን ነብይ ብስራት የእግዚአብሔር ቃል በማቅረብ ጸሎት አድርገዋል።

በመቀጠልም የክልሉ የወጣቶቸ አገልግሎት ክፍል ሀላፊ የሆኑት መጋቢ ኤልያስ አየለ አዲሱ የልጆች ማስተማርያ መጸሃፍ ጠቃሚነቱን አጽንኦት በመስጠት በመናገር በቀጣይ ክልሉ በልጆች አገልግሎት ላይ ሊያከናውናቸው የታሰበውን ተናግረዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነው።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
8👍6