ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አመራሮች እና በስሩ የሚገኙ ሕብረቶች መሪዎች በጋራ በመሆን በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
መግለጫን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚደንት ዶክተር ጣሰው ገብሬ ሲሆኑ ከትንቢተ ኢርሚያስ 29 ፡7 ላይ “በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።” የሚለውን ክፍል አንስተው ምንም እንኳን ምርኮኞች ባንሆንም ስለሀገራችን ኢትዮጵያ መጸለይ አለብን በማለት ተናገረዋል።
በመቀጠልም ዝርዝር መግለጫው የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ የሆኑት ቄስ ደረጄ ጀንበሩ በጽሁፍ አቅርበዋል።
በጽሁፍ የቀረበው መግለጫም በቅድሚያ እስከ ዛሬ ድረስ የረዳንን እግዚአብሔርን የሚያመሰግን ሲሆን ከዛም በመቀጠል ለሀገራችን ሰላም የተለያዩ አካላት ማድረግ የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ የሚያቀርብ ነው።
በመግለጫውም ፡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች በሙሉ ግጭትን ለማስወገድ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ፣ በማንኛውም ምክንያት ተለያይተው የቆዩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ይቅርታ በማድረግ እና ይቅርታን በመቀበል አዲሱን አመት እንዲቀላቀሉ ፣ በማህበራዊ ሚድያ የሚሰሩ አካላት አስታራቂ እና የፍቅር ቃል በማስተላለፍ እንዲተጉ ፣ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶች ከጎጂ እንቅስቃሴ በመራቅ ለሀገራቸው አስተማማኝ ሰላም እና ለነገው ብሩሕ ተስፋ ሲሉ በትጋት እንዲሰሩ እና የሀገራቸውን ደህንነት እንዲጠብቁ እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች በጋራ በመሆን ጉዳይ የሚመለከታቸውን በሙሉ በመምከር እና በማበረታታት ለሀገራችን ሰላም እንዲተጉ ጥሪ ቀርቧል።
ከዚህም በተጨማሪ ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚገኙ የወንጌል አማኝ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሐምሌ 30 - ነሀሴ 2 ፤ 2017 ዓ.ም ስለ ሀገራችን ዘላቂ ሰላም እና ስለ ሕዝባችን አንድነት በጾም እና በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት እንዲሆኑ ካውስንሉ ጾም እና ጸሎት አውጇል።
በወንጌል አማኞች ልማድ በሆነው የጳጉሜ ጸሎት ላይም የወንጌል አማኞች ሀገራቸውን በእግዚአብሔር ፊት በጾም እና በጸሎት ይዘው እንዲቀርቡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

❤2