የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
8.95K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቀን_አስር ፲/10 #ረቡዕ

" ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፥ በዕቃ ውስጥ ባለውም ደም ንከሩት፥ በዕቃውም ውስጥ ካለው ደም ሁለቱን መቃኖችና ጉበኑን እርጩ፤ ከእናንተም አንድ ሰው ከቤቱ ደጅ እስኪነጋ ድረስ አይውጣ።"
(ኦሪት ዘጸአት 12:22)

እስራኤላዊያን በግብፅ ሳሉ የበራቸው መቃን ላይ የጠቦት ደም በመቀባት የሞት መለአክን አምልጠዋል ፤ እኛ የአዲስ ኪዳን ነዋሪዎችን ግን ከከበበን የዘለአለም ሞት የሚያስመልጠን የክርስቶስ ደም ነዉ፡፡

#ምህረት_ኢተፋ
ደሙ በመቃኔ ላይ ስለተቀባ
ደሙ በጉበኔ ላይ ስለተቀባ
ሞት አለፈ ሄደ እራቀ ከእኔ ጋር
የጌታዬን ደም አይቶ
የኢየሱሴን ደም አይቶ (፪x)
ሞት አለፈ ፣ ሞት አለፈ ሄደ ከእኔ ርቆ

የሞት መልአክት አያስፈራኝ
ተሸፍኛለሁ አያገኘኝ (፪x)
ዙሪያዬ ከደሙ ታጥሯል
ያን ቅጥር አልፎ እንዴት ይገባል (፪x)

መልካም ቀን!