የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.18K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#እግዚአብሔር_መፅናናትን_እንዲያበዛላችሁ_ፀሎታችን_ነዉ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ እና በአከባቢዉ ማህበረሰብ ላይ በደረሰዉ የጎርፍ አደጋ በህይወት እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት እጅግ ማዘናችንን እንገልጻለን።

በትላንትናው እለት በጣለው ከፍተኛ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ህይወታቸውን ላጡ እና ንብረቶቻቸው ለወደመባቸው አካላት ካውንስሉ መጽናናትን ይመኛል።

ስለሆነም ሁላችሁም የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል አባላት ቤተእምነቶች፤ ሚኒስትሪዎች እና አገልጋዮች በሙሉ ከሴሚናሪው እና ጉዳት ከደረሰባቸው አካላት ጉን በጸሎታችሁ እና ልዩ ልዩ ድጋፍ በማድረግ አብራችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ለኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና ለተጎጂ ቤተሰቦች እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲያበዛላችሁ ፀሎታችን ነዉ።

1 ተሰ. 4፥13-18

ቄስ ደረጀ ጀምበሩ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ጠቅላይ ፀሐፊ
#እግዚአብሔር_በአደጋው_ህይወታቸውን_ላጡ_ቤተሰቦች_መጽናናት_ይስጣቸው

ነሃሴ 11/2013ዓ.ም በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ ላይ በደረሰው አደጋ የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ህብረት እጅግ ማዘኑን እገልጻለሁ።

የተፈጠረው አደጋ አሳዛኝ ቢሆንም ለምን ሆነ አንልም ይልቁንም በመላው አለም የምትገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ በአደጋው የተጎዱ ቤተሰቦችን ልናጽናናቸው እና ከጎናቸው ልንሆን ይገባል።

የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በተቻለን መጠን አንድነታችንን ለመግለጽ 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) ድጋፍ የምናደርግ ሲሆን ሌሎቻችን በሀገር ውስጥም ይሁን ከሀአገር ውጪ የምትገኙ ይህንን አደጋ የሰማቹ በተቀመጡ ድጋፍ የማድረጊያ አማራጮች በመጠቀም ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ጭምር ትልቅ ስራ የሰራች እና ለብዙዎች በረከት የሆነች ቤተክርስቲያን ነች።

እግዚአብሔር በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናት ይስጣቸው እያልኩኝ ለሚደርሰው ማንኛውም ነገር ጸሎት አስፈላጊ ስለሆነ ሁላችንም በጸሎታችን እናስባቸው።

እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባረክ። አመሰግናለው

መጋቢ እሸቱ ወርቄ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ቦርድ አባል እና የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝደንት
ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃♂️🏃♀️🏃♂️🏃♂️
ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።
#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።
ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።
#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?
#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።
ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?
#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።
ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።
ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ"
#አሜን መልዕክታችን ነው።
ምንጭ- The Christian News
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/7294xQsv7BI
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
2👍1👎1