የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.7K subscribers
8.91K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቀን_ሁለት ፪/2 ማክሰኞ

" ... #የልጁም_የኢየሱስ_ክርስቶስ_ደም_ከኃጢአት_ሁሉ_ያነጻናል።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7)

ከአዳም ጀምሮ የሰዉ ልጅን ባሪያ አርጎ ሲገዛ የነበረዉ ፣ ወደማይፈልግበት የሚነዳዉ ትልቁ የሰዉ ልጅ ጠላት ኃጢያት ነበር ፡፡ ኃጢያት ደግሞ የሚሰራ ብቻ ሳይሆን የሰዉ ማንነት ሆኖ ሰዉን ከአምላኩ አጣልቶ ከወንድሙ አባልቶ የሰዉ ልጆችን ሁሉ በምድር ያልተገባ ሕይወት እንዲኖሩ የሚያስገድድ ሀይል ነበር ፡፡
የሰዉ ልጆች በዘመናቸዉ ከጥንት ጀምሮ ከዚህ ጨቋኝ ገዢ ለመላቀቅ ቢያስቡም የሚቻልና የሚዘለቅ አልነበረም ፡፡ አምላክም ፍጡሩን ስለሚወድ ከዚህ እንዲወጡ የተለያየ መንገድ ሲያዘጋጅላቸዉ እንደነበር መፀሀፍ ቅዱስ ይነግረናል ፡፡ ይሁን እንጂ የሰዉ ልጆች አምላክ የሰጣቸዉን ህግ ለመጠበቅ ሲጣጣሩ ነገር ግን ሳይችሉ ደግሞም መስዋት በማቅረብ ለኃጢአታቸዉ ስርየት ደም ሲያፈሱ እንደነበር ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል ፡፡

ይህም ሆኖ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልተቻለም ፡፡ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ስለ ሰዋች ሁሉ ኃጢያት መስቀል ላይ ሰዋዉ ፡፡ ልጁም ኢየሱስ ስለኛ ታዞ በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰልን ይህንንም ደም ይዞ ስለኛ ዘወትር ሊማልድ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ አሁን በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ ባፈሰሰዉ ደም ኃጢያታቸዉን ሊያነጻ ስለኛ በአብ ዘንድ ጠበቃ ሆኖ ተቀምጧል ፡፡

የኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያድናል ፡፡ ወንድሜ ፥ በኃጢያት ዉስጥ አለህ ፣ ማንነትህ ኃጢያት ነዉ ? እንግዲያዉስ ኃጢአትህን ሁሉ ሊያነፃ ወደሚችል ወደ ኢየሱስ ተመለስ ፡፡

ማመሳከሪያ ጥቅስ ፦
" የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:34)