የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.7K subscribers
8.91K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቀን_አምስት ፭/5 አርብ

" እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል። "
(ወደ ዕብራውያን 9:28)

በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምነን ለዳንን እኛ ፦ በአብ ዘንድ ሁልጊዜ የሚታይልን ዘራችን ፣ ቋንቋችን ፣ የትምህርት ደረጃችን ፣ የሀብት መጠናችን ፣ የጤና ሁኔታችን ሳይሆን ስለኛ እንደተሰቀለ ያመነዉ ክርስቶስ ነዉ ፡፡ እሱ ደግሞ በእግዚአብሔር አብ ፊት ቅዱስ መስዕዋትና ለእኛ ጠበቃ ነዉ ፡፡

መስቀሉን ስናስብ ፍቅሩን እናስታዉስ ፤
መስቀሉን ስናይ የተከፈለልንን አንርሳ ፤
ይህ ሁሉ ስቃይ ፣ ይህ ሁሉ መከራ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የደረሰዉ እኛን ከዘላለም ፍርድ ለማዉጣት ስለኛም በአብ ፊት በፍፅምና ለመታየት ነዉ ፡፡

#መልካም_ቀን
👍1