የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.7K subscribers
8.91K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቀን_አራት ፬/4 ሀሙስ

" የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ #ከአቤልም_ደም_ይልቅ_የሚሻለውን_ወደሚናገር_ወደ_መርጨት_ደም_ደርሳችኋል ።"
(ወደ ዕብራውያን 12:24)

በመስቀል ላይ የፈሰሰልን ደም ተራ የአንድ ሰዉ ደም ብቻ አይደለም በመስቀል ላይ የፈሰሰዉ ደም አምላክ ሰዉ ሁኖ ስለኛ መተላለፍና በደል የከፈለዉ ዋጋ እንጂ ፡፡ ይህ ደም እንደ ዋዛ ፈሶም የቀረ ደም አይደለም ይልቁንስ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር
ስለ ምህረት ፣ ይቅርታ ስለኛ የሚጮህ ነዉ ፡፡

" አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። "
(ኦሪት ዘፍጥረት 4:10)

በእርግጥ ቃየን ወንድሙ አቤልን ሲገለዉ የአቤል ደም ስለ ራሱ ፍትህ ወደ እግዚአብሔር ይጮህ ነበር በመስቀል ላይ ስለኔና ስለናንተ የፈሰሰዉ የንጉሳችን ኢየሱስ ደም ግን ስለ ራሱ ሳይሆን ስለኛ ምህረትና ይቅርታ ዘወትር ይጮኸል ፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ከአቤል ይልቅ ለሚጮኸዉ ደም እንዴት ምህረቱን በኢየሱስ በኩል ለህዝቡ አይሰጥ???!