የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.7K subscribers
8.91K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#አስቸኳይ_ጥሪ
#ለሁሉም_ሚዲያዎች
#ረቡዕ_ሐምሌ_14 #ከቀኑ_09_ሰዓት

በአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የፀደቀ 20,000 ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ የወንጌል አማኞችን ለሚወክለው ካውንስል ተሰጥቶ ነበር። ነገር ግን ካውንስሉ ቦታውን እንዳይወስድ የሚሰሩ አካላት ተፈጥረዋል። ይህ ለምን ሆነ መፍትሄውስ ምንድን ነው? Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ

በመሆኑም ይሄንን እና ሌሎች ከወንጌላውያን አብያተ ርክስቲያናት ላይ የተወረሱ ቦታዎችን አስመልክቶ የፊታችን ረቡዕ ሐምሌ 14/2013ዓ.ም ከቀኑ 09:00 ሰዓት በካውንስሉ ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ እና በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።

ስለሆነም ጉዳዩ የሁሉም ወንጌላውያን ስለሆነ ሁላችሁም የመንፈሳዊ ሚዲያዎች እና ጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ የምትፈልጉ ማንኛውም የሚዲያ አካል በጽ/ቤቱ እንድትገኙ በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።

ተጨማሪ ማብራሪያው ይመልከቱ https://www.youtube.com/watch?v=KKPYeDXFVuM
#ቀን_አስር ፲/10 #ረቡዕ

" ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፥ በዕቃ ውስጥ ባለውም ደም ንከሩት፥ በዕቃውም ውስጥ ካለው ደም ሁለቱን መቃኖችና ጉበኑን እርጩ፤ ከእናንተም አንድ ሰው ከቤቱ ደጅ እስኪነጋ ድረስ አይውጣ።"
(ኦሪት ዘጸአት 12:22)

እስራኤላዊያን በግብፅ ሳሉ የበራቸው መቃን ላይ የጠቦት ደም በመቀባት የሞት መለአክን አምልጠዋል ፤ እኛ የአዲስ ኪዳን ነዋሪዎችን ግን ከከበበን የዘለአለም ሞት የሚያስመልጠን የክርስቶስ ደም ነዉ፡፡

#ምህረት_ኢተፋ
ደሙ በመቃኔ ላይ ስለተቀባ
ደሙ በጉበኔ ላይ ስለተቀባ
ሞት አለፈ ሄደ እራቀ ከእኔ ጋር
የጌታዬን ደም አይቶ
የኢየሱሴን ደም አይቶ (፪x)
ሞት አለፈ ፣ ሞት አለፈ ሄደ ከእኔ ርቆ

የሞት መልአክት አያስፈራኝ
ተሸፍኛለሁ አያገኘኝ (፪x)
ዙሪያዬ ከደሙ ታጥሯል
ያን ቅጥር አልፎ እንዴት ይገባል (፪x)

መልካም ቀን!