ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
Audio
ለምን አልሰለምኩም??
" በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5:10)
ሕፃኑዋ አይሻን ብቻ ነው ወይስ ሕፃን ወንዶችንም?

ከዚህ በፊት እንዳየነው፣ ሙሓመድ አይሻ ገና የወር አበባዋን ማየት ሳትጀምር በ 9 አመቷ ከሱ ጋራ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንድትፈፅም እንዳደረጋት አይተናል።

ሳሂህ አል ቡኻሪ 7:62:163
ፈትሁ አል ባሪ ቅጽ 13  ገፅ 143
 
ለተከታዮቹም ሕፃን ልጅን እንዲያገቡ ይመክራቸው ነበር

-ሳሂህ ሙስሊም 3460

ይህ የሚያሳየው፣ ነብዩ ከ ኖርማል ሰው በተቃራኒ ለ ጋብቻና ለ ግብረ ስጋ ግንኙነት አእምሮው አመቺ አድርጎ የሚያስበው #ሕፀናትን ነው።

ከዚህም የተነሳ ከታች ያሉትን ሓዲዞች ሳነብ አይምሮዬ ውስጥ ጥያቄ መፈጠር ጀመረ። ነብዩ ሙሓመድ ሕፃን #ወንዶችንም በዚው አይን አይተው ይሁን??

አንባቢው ይፍረድ

አል አዳብ አል ሙፍራድ አል-ቡኻሪ ሓዲዝ 1183

"...ነብዩም..አሉ "ትንሹ ልጅ የት አለ? እስኪ ጥሩት። ሓሳንም እየሮጠ መጥቶ ነብዩ ሙሓመድ ላይ ዘሎ ተቀመጠ።ከዛም እጁን ፂሙ ውስጥ ማስኬድ ጀመረ፤ ነብዩም የ ልጁን አፍ ከፍቶ #ምላሱን_አፉ_ውስጥ _ከተተ። እንዲህም አለ " ኦ አላህ ሆይ፣ ልጁን እወደዋለው አንተም ውደደው፣ እሱንም የሚወዱ ይወደዱ።"
"...He sat down and wrapped himself in his garment. Then he said, 'Where is the little one? Call the little one to me.' Hasan came running and jumped into his lap. Then he put his hand in his beard. Then the Prophet, may Allah bless him and grant him peace, opened his mouth and put his tongue in his mouth. Then he said, O Allah, I love him, so love him and the one who loves him!'"

ከታች ተፅፎ ላሉት ቃላቶች ይቅርታ እጠይቃለው። ነገር ግን ቃሉ የ ሓዲዙ ነው፣ የኔ አይደለም። ምንም ማድረግ አልችልም።

ሙስናድ አሕማድ 16245

Mua’wiya said "I saw the prophet sucking on the tongue or the lips of Al-Hassan son of Ali, may the prayers of Allah be upon him. For no tongue or lips that the prophet sucked on will be tormented (by hell fire).

ሙአዊያ ዘግቦታል፦"ነብዩ ሙሓመድ የ አል ሓሳን #ምላስ/ከንፈር #ሲጠቡ አይቼያለው። ምክኒያቱም ነብዩ የጠቡት ከንፈር ወይም ምላስ በ ጀሃነም እሳት አይቃጠልምና።"

ልብ በሉ፣ ነብዩ እራሱ፣ ነፍሱ ወዴት እንደምትሔድ (ጀነት ወይስ ጀሃነም) አያውቅም ነበር : በተጨማሪም ማንም ሰው ነፍሱ የሚትሔድበትን ስለማያውቅ "ጀነት እገባለው" ብሎ መናገር እንደማይችል ሌሎች ሓዲዞች ግልፅ ናቸው።
-Sahih al-Bukhari Book 58, Number 266
-Tafsir Ibn Kathir-sura 46:9

ከላይ ያነበብነው ሓዲዝ ላይ ግን በ ነብዩ የተጠባ ምላስ ወይም ከንፈር  ጀሃንም አይገባም ይላል። እንደዛ ከሆነ ሓዲዞቹ አይጋጩምን??የ ነብዩ ከንፈር ገነት የሚያስገባ ከሆነ ለምን ሌሎች ተከታዮች እንዳሉ ከነብዩ ጋር ይህንን ድርጊት አልፈፀሙም??

ነው ወይስ ጉዳዩ ሌላ ነው?? ለ አንባቢው ትቼዋለው።
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
👍1
የምስል ማስረጃ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 በዚህም ዘመን የነብዩ ሱና ተብሎ በአንዳንድ ሙስሊሞች ዘንድ ጀነት እንዲገቡ በሚል የወንድ ህፃናትን ምላስ በትላልቅ ሰዎች ያስጠባሉ፡፡
የአሕመድ ዲዳት አስደንጋጭ ቅጥፈቶች 👉 http://www.ewnetlehulu.org/am/our-answers/deedat_lies/
የ አይሻ ቤት ወይስ የ አይሸ ቀሚስ?

እውቀት አልባውን ሙስሊም ሰብስቦ ሲያስጨፍር የሚውል አንድ 'ጥንጥ' ጭንቅላት የተሸከመ ሕይወቱን ሙሉ ሲንከራተት ያሳለፈና ምን ማመን እንዳለበት እንኳን የማያውቅ አንድ 'ኡስታዝ ነውም ይሉታል'፣ አለ። ልክ በራሱ አጥንቶ እንዳመጣ ሰው፣ ነብዩ ሙሓመድ 'የ አይሻ #ቀሚስ ውስጥ ካልሆነኩ ወሒ(መገለጥ) አይመጣልኝም' ብሎ የተናገሩትን፣ "የ አይሻ #ቤት" ማለት ነው ብሎ ሙግቱን አቅርቧል።ክርስቲያኖችም ይህንን መረዳት ያልቻሉበት ምክኒያት ከ ጎግል ስለሚጎረግሩት እንጂ እውቀት ስላላቸው እንዳልሆነ ተናግሯል። የሚገርመው ነገር ግን ይህ ሰው ሙግቱን ቃል በ ቃል 'Answering Christianity' ከተሰኘ ድሕረ ገፅ  በ 'ኦሳማ አብዱላህ' ከተፃፈው አርቲክል እና 'አቡአልራብ' የሚባል ሰው ከፃፈው አርቲክል ኮፒ ፔስት ማድረጉ እጅጉን ፈገግ የሚያደርግ ነው። "ሌባ እናት ልጇን አታምንም" ይሉ ይለ?

ሳሂህ አል ቡኻሪ መፅሓፍ 51 ሓዲሥ 16

ነብዩ እንዲህ ብሏል "...ወሒ(መገለጥ) በ አይሻ ቀሚስ(ሠውብ 'ثوب') ውስጥ(في) ካለሆነ በ ሌሎች ሴቶች ቀሚስ ውስጥ አይመጣልኝም።"
فدار إليها فكلمته فقال لها ‏ ‏لا تؤذيني في ‏ ‏عائشة ‏ ‏فإن الوحي لم يأتني وأنا في ثوب امرأة إلا ‏ ‏عائشة.

ሳሂህ ሙስሊም መፅሓፍ 31 ሓዲዝ 5907

زَوْجَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم وَعُثْمَانَ حَدَّثَاهُ أَنَّ أَبَا بَكْرٍ اسْتَأْذَنَ عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَهُوَ مُضْطَجِعٌ عَلَى ِرَاشِهِ لاَبِسٌ ِرْطَ عَائِشَةَ
Abu Bakr requested permission from the prophet to enter when the prophet was lying down on Aisha’s #bed wearing her #garment (mirt)
"አቡ በከር ነብዩ ወዳሉበት ክፍል ለመግባት ፍቃድ ጠየቀ። ነብዩም በ አይሻ #ፍራሽ ላይ የሷን #ቀሚስ(mirt) ለብሶ ጋደም ብሎ ነበር።"

ነብዩ በ እርግጥ የሴት ልብስ እንደሚለብሱና መገለጥም በሱ ውስጥ እንደሚመጣላቸው መናገራቸው ግልፅ ነው። እነኚህ የሙሃመድ "ጠባቂያን" ግን ይህንን የሚያክል አሳፋሪ ድርጊት ለመሸፈን የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም።

የ ሙስሊም ነኝ ባዩ ሙግት እንዲህ የሚል ነው፦

"ሠውብ” ثَوْب የሚለው ቃል በብዙ ይመጣል፦
“ሂጃብ” حِجَاب “መጋረጃ”፣“ፊራሽ” فِرَٰش ምንጣፍ”፣“ሊሃፍ” لِحَاف “ፍራሽ”“በይት” بَيْت “ቤት”
“ሊባሥ” لِبَاس “ልብስ......ይህንን ካየን ነብያችን”ﷺ”፦ “ከማናቸውም ሴቶች ልብስ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ በስተቀር” ሲሉ ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” #ፍራሽ ወይም #ቤት ማለታቸው እንደሆነ እሙንና ቅቡል ነው..."

ይሄ ሙግት በጣም የወረደ መሆኑን ላስነብባቹ።

1. ነብዩ "ለበሱ" የተባለው " ሠውብ" ብቻ አይደለም። "ሚርት" ተብሏል።ትርጉሞቹን እንመልከት

ሠውብ፦ ከ ዲክሺነሪ
ثَوْب
apparel
- clothes worn on a special occasion
(ልዩ የሆነ ቀን ላይ የሚለበስ ልብስ)
- clothes; dress(ልብስ፣ቀሚስ)

2. "ሚርት"
 እውነት ሓዲዙ የሚነግረን ነብዩ መገለጥ ይመጣልኛል ያሉት የ አይሻ #ቤት ወይም #ፍራሽ ላይ እንጂ የሷ ቀሚስ ውስጥ አይደለምን?

ከ ላይ እንዳነበብነው፣ ሳሂህ ሙስሊም 5907 እንዲህ ይላል፦
"አቡ በከር ነብዩ ወዳሉበት ክፍል ለመግባት ፍቃድ ጠየቀ። ነብዩም በ አይሻ #ፍራሽ فِرَاشِهِ ላይ የሷን #ቀሚስ(ሚርት) ለብሶ ጋደም ብሎ ነበር።"

ልብ በሉ፣ በዚህ ሓዲዝ ላይ በ ግልፅ "ፍራሽ" እና "ልብስ" ሁለት የተለያዩ ቃላቶች ሆኖ ተቀምጧል።
A. ነብዩ ምን ላይ ነው የተኙት? መልሱ፦ የ አይሻ ፍራሽ
B. ነብዩ ምን ለብሶ ነበር?፦ የ አይሻ ቀሚስ

ስለዚህ በ ሌሎች ሓዲሣት ውስጥ ነብዩ "በ አይሻ ቤት ውስጥ እንጂ በሌሎች ሶቶች ቤት ውስጥ መገለጥ አይመጣልኝም (ሙስነድ አህመድ መጽሐፍ 6 ሐዲስ 293") ብለው እንደተናገሩ ተደረጎ የተፃፉ፣ ነብዩ የ አይሻ ልብስ አይለብሱም ማለት አይደለም። ይልቁንስ ከላይ ባነበብነው ሓዲሥ መሠረት "በ አይሻ ቤት ውስጥ የሷን ቀሚስ ለብሶ" ማለት ነው እንጂ።

በተጨማሪም "ሚርት" የሚለበሰው በ ሴቶች #ብቻ መሆኑን የ ሙስሊሞች መፃሕፍት መስክሯል። ምሳሌ፦

ፈትሁል ባሪ፣ የ ሳሂህ አልቡካሪ ማብራሪያ (ኢማም ኢብን ሓጀር አል አስቀላኒ) ቅጽ 2፤
Volume 2፦ The Book of Prayer Times; Chapter of Dawn Prayer

"..'ሚርት' ተብሎ የሚጠራ ልብስ በ ሴቶች #ብቻ የሚለበስ ነው" ይላል።

#የሴት_ልብስ_መልበስ_በ_ሓዲሣት_ህግ

ሱናን አቡ ዳውድ 4098
Narrated AbuHurayrah:

The Messenger of Allah (ﷺ) cursed the man who dressed like a woman and the woman who dressed like a man. (Sahih)
حَدَّثَنَا زُهَيْرُ بْنُ حَرْبٍ، حَدَّثَنَا أَبُو عَامِرٍ، عَنْ سُلَيْمَانَ بْنِ بِلاَلٍ، عَنْ سُهَيْلٍ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ لَعَنَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الرَّجُلَ يَلْبَسُ لِبْسَةَ الْمَرْأَةِ وَالْمَرْأَةَ تَلْبَسُ لِبْسَةَ الرَّجُلِ ‏.‏
:  (  صحيح   (الألباني)
"ነብዩ እንዲህ ብሏል፦ 'የ ሴት ልብስ(እንደሴት) የሚለብስ  ወንድ ወይም የ ወንድ ልብስ የምትለብስ ሴት #የተረገመ/ች ነው/ናት"

መደምደሚያ:

ነብዩ የሴት ልብስ ይለብሱ ስለ ነበረ እራሳቸው በተናገሩት ንግግር መሠረት #የተረገሙ ናቸው ማለት ነው!! አከተመ።

ነብዩ ለ እርግማናቸው የሞተውን ክርስቶስ ለመቀበል ሁለተኛ እድል አይሰጣቸውም። ይህን ፅሁፍ የምታነብ ሙስሊም ግን ማምለጥ ትችላለህ። የሞተልህን ክርስቶስ ተቀበል!!!

 " እንግዲህ። በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:24)
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
🅰"አልፋና ዖሜጋ"♎️
👳‍♂ሙሐመዳውያን "እየሱስ እራሱን አምላክ ብሎ የጠራበትን ቦታ ከመፅሐፍ ቅዱስ ቃል በቃል አሳዩን? አንዳች ጥቅስ ታመጡ ዘንድ #አይቻላችሁም!" በማለት መፎከር ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል። ይሁና ጥያቄውን እንኳ እንደ ጥያቄ ብንመዝነው🔍 ወዳቂ መሆኑ ብቻ ሳይሆን "ተንጋለው ቢተፉ ተመልሶ ካ ፉ!"🤦‍♂ እንደሚለው ያገሬ ሰው እራሳቸው ላይ መልሶ ጉድን እንደሚያፈላ አለማወቃቸው ነው።
👉 መቼም ይህንን ከዚህም በፊት አነሳስተነዋልና የዛሬ መፃፅፌን ይህንን ሙግት በመድገም አላንዛዛም። ይሁንና መቼም ነገሩ ለአቅመ ጥያቄም ባይደርስ🤷‍♂ መልስን ሁሌም መመለስ፤ እውነትን ዘወትር መግለጥ💡 ልምዱ የሆነው ሕዝበ ክርስትያን እንካችሁ እያለ ካንድም ሁለት ከሁለትም ሦስት ከሦስትም አራት ቦታን መዥረጥ እያረገ ጀባ ሲል ኖሯል። ይሁንና አውቆ የተኛን እንዲሉ አሻፈረን ሲሉ ይስተዋላል። ዛሬም ይህችን መከተቤ አቶ ዲዳትና👳‍♂ የእርሳቸው የገደል ማሚቶ የሆኑ የኛዎቹ እውቀት አጠር ምላስ ረዘም👳‍♀ ተሳስቶ አሳሳቾች በተለይ በራዕይ መፅሐፍ ላይ ያሉትን ሦስት ጥቅሳት እየሱስ አደለም "#አልፋናዖሜጋ" የተባለው በማለት አይን ያወጣን የአርዮሳዊያን መሰል ትምህርትን ድሮም በተነገረ አሁንም ባለ በሚመጣም እውነት ላቀልም ነው።
እንግዲህ ይህ የራዕይ መፅሐፍ ሙግት እንዲህ በማለት ያትቱታል፦
፩, "ይህ ራዕይ የተሰጠው ከአብ ነውና ማንኛውም ነገር በመፅሐፉ ያለ ምንጩና እኔነቱ የአብና የአብ ብቻ ነው።"
፪, ሲብስም "አልፋና ኦሜጋ ነኝ!" ያለው እራሱ አብ ነው("ያለውና የሚመጣው ጌታ አምላክ")።
፫, ብቻ ምን አለፋን ተወደ መደምደሚያው "ምንም እንኳ እየሱስ 'አልፋና ዖሜጋ' ነኝ ቢል እንኳ በል📢 የተባለውን እንጂ የራሱን ማንነት የሚገልፅ አንዳች ይል ዘንድ መልእክተኛ ብቻ ስለሆነ አይችልምም አላለምም" ይሉናል።😳😳🤔🤔
👉እንግዲህ እስቲ ሌላውን ትተን በራዕይ መፅሐፍ 1 ላይ እንኳ ያለውን ብንተነትን በቂ ስለሚመስለኝ ይህንኑ እንደሚከተለው አስነብባለሁ።
ስንጀምር ይህ መፅሐፍ ሊሆን ያለውን እግዚአብሄር(ይህ የስላሴን የመጀመሪያ አካል "አብን" ማሳየቱን ልብ ይለዋል) ለእየሱስ ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ #መግለጡን፤ ወልድም ይህንን መልአኩን ልኮ ለሐርያው ዮሐንስ #ማመልከቱን፤ ሐዋርያውም ለሰባቱ አብያተ ክርስትያናት በመልዕክተኞች #እንደሰደደ እናያለን።
እንግዲህ ነገሩ እዚ ላይ ነው እሚጀምረው። እዚጋር ነው እንግዲህ ድሮም ቢሆን የእየሱስ ከአባቱ ከአብ ጋር ያለው የልጅና የአባትነት ሕብረት በሚገለጥበት ዘላለማዊ ፍፁም #መታዘዝ(በፈቃዱ) ያልገባቸው መሐመዳውያን😲 ግራ መጋባት የሚጀምሩት። እየሱስ ፈቃዱን በፍፁም መታዘዝ(#perfectobedience) የሚናገረውን የሚያደርገውንም ሁሉን ፈቃዱን #በራሱ ለአብ በማስገዛት የአብን እውቀትና ፈቃድ ይፈፅም ዘንድ ያለው። ይህ ነው እንግዲ የመጀመሪያው የሁለቱ ሕብረት። ይህ ማለት ግን ከአብ የመጣው እውቀት ልክ መልዐኩ ከእየሱስ ተቀብሎ ለሐዋርያው ዮሐንስ እንደሚገልጥ በሶስተኛ ሰውና እራሱን #እኔ እያለ ሳይጠራ እንደሚያቀብል ተራ የመልእክት ተዋረድ አካል ነው ማለት አይደለም‼️ይህም መፅሐፉን መጀመርያና መጨረሻ #ብቻ ሳይሆን #ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ላነበበ እየሱስ ራሱን ብቻና ብቻ የሚወክልን ንግግር ሲያደርግ ትዕይንት ሲከውን እንመለከታለን። ስለዚህም የአብን ፈቃድና እውቀት ሲፈፅምና ሲናገር በተመሳሳይ መልኩ አብ የልጁን ማንነት ልጁ በአባቱ ግልጠት እራሱ የሚያቀውን ይናገር ዘንድ ሰቶታል ማለት ነው።🔑 ይህንንም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14፥21-24 ማበብ ጠቃሚ ነው። እየሱስ "የላከኝ የአብ ቃል ነው" እያለ፤ እዛው "ቃሌን" ብሎ ሲጀምር፤ የሚገልጠው የተሰጠውን የላከውን እንደሆነ እያወሳ #ራሴን እገልጥለታለሁ ሲል እናያለን። ይህ ማለት አብና ወልድ አንድ አካል ናቸው ማለት ሳይሆን #በምንነት #ሁለቱ #ከአንድ እንደሚቀዱ ያስተውላል።ይህንን ጠልቀን በየጥቅሱ እንተነትናለን።
እንደው ለመጠየቅ ያህል መሐመዳውያን ቁጥር አንድን ሲያነቡ "ለባሪያዎቹ...በመልአኩ ልኮ" የሚሉት ቃላት የሚያሳዩት #ባለቤት ማነው?
መቼም መልአክን የሚልክ ባርያም እንሆንለት ዘንድ የተገባው ማን እንደሆን ግልፅ ነው።🤔😁😁😁
ቁጥር ሁለትን በመዝለል መሮጥ🏃‍♂ የሁሌም ልማዳቸው ነው። ግና ሁለትን ቢያዮአት ኖሮ መፅሐፉ ስለምን እንደሚያወራ ይገባቸው ነበር።💡 በቁጥር ሁለት ላይ ለእግዚአብሄር ቃል፣ ለእየሱስም ምስክርነትና ላየው ሁሉ ነገር እንደተፃፈ በእርግጥ ያስረዳል❗️ ይህ ማለት ይህ መፅሐፍ ሦስት ነገሮችን ይዞል ማለት ነው 1⃣ የእግዚአብሄርን ቃል፣ 2⃣የእየሱስን ምስክርነትና 3⃣መልአኩ ያሳየውን። ስለዚህ እየሱስ ተራ መልዕክት አስተላላፊ ቢሆን ኖሮ እንዴት የራሱን ምስክርነት ያወራል?🤔 ግን ነገሩ እንደዛ ስላልሆነ አብን በማክበሩ አብ ደግሞ እርሱ በፊት በነበረ ክብሩ ያከብረው ዘንድ ይሁን ያለውን #የራሱን ምስክርነት ሲያቀርብ እናያለን። ለዚነው ተዋረዱ እነሱ እንዳሰቡት #አደለም ያልነው።
ቁጥር አራት የሚናገረው ስለሰላምታ ቢሆንም ግልፅ ያለ #የስላሴን አስተምሮ የሚያሳይ ለቀጣይም ቁጥሮች ማጣቀሻን #ፍንጭ የሚሰጥ ትልቅ ቁጥር ነው።
ሰላምታው ከአብ(ካለው ከነበረው ከሚመጣ)፣ ከሰባቱ መናፍስት(ከመንፈስ ቅዱስ፤ ይህን በ3፥1,4፥5,5፥6 ላይ መመልከት ይቻላል...ሰባት ብዛትን ሳይሆን ፍፅምናን የሚያሳይ ሲሆን ከነዚ ውጭ ያሉ ሰባት መልአክት ወዘተ የሚሉ ክፍሎች እስካልተፃፈ ድረስ ይህንን ሐረግ አይወክሉም)ና ከወልድ(ከእየሱስ) ነው የመጣው። #ፍንጩንም እንደሚከተለው አትታለሁ፦
ማነው የታመነ ምስክር? #እየሱስ
" ከሙታን በኩር? #እየሱስ....
" ኃጥያታችንን በደሙ ያጠበ? #እየሱስ
" ለአምላኩና ለአባቱ ካህናትያረገን? #እየሱስ
" ከደመና ጋር እሚመጣ? #እየሱስ
" የተወጋ የተወጋውም ውጉም ሲመጣ የሚታይ? #እየሱስ(ዮሐ19፥37) ...
ስለዚህ ይህንን ይዘን ታች ቁጥር 8 ላይ ስንደርስ ይኃው ሲገለፅ የነበረ ማንነት እኔ እንዲ ነኝ ብሎ ይናገራል፦ " ያለውና የሚመጣውም ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ #አልፋናዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።"
🤔እናም "ማነው ይህን የሚለው?" #እየሱስ "ስለማ?" ከላይ ጀምሮ የተጠቀሰው ማንነት እርሱ ብቻ ስለሆነ #ስለራሱ ነዋ እሚለው።
"እንዴት ተልኮ ነው እንጂ ስለ ራሱማ አደለም!" ታድያ እኔ ብሎ ስለ አብ ብቻ ከሆነ እሚያወራው ለምን በቁጥር 18 ላይ "ሞቼ ነበርሁ..." እያለ ያወራል ወገንመችና የትነው አብ የሞተው እናስብ እንጂ‼️
በተጨማሪም እቁጥር 6 ላይ ሐዋርያው ለዚህ ለተወጋው ጌታ ለአምላኩና ለአባቱ ካህናት እንድንሆን ላደረገን፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን የሚለው ተሳስቶ ይመስላችኃል?
ስንቀጥልም ሞቼ ነበርሁ ካለ በኃላ ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ነኝ ማለት ምን ማለት ነው ወገን⁉️
"እንዴት ባንዴ ሁለት አካላት ያለውና የነበረው የሚመጣውም ይባላል?" ካላችሁ ሐዋርያው ዮሐንስ በወንጌሉ መግቢያ እንዳደረገው በተመሳሳይ አውድ አንድን #ምንነት ለሁለት #አካለት ሲጠቀም ነው እንዲህ ያለው❗️ መልሳችን ነው። 👉ማጠናከርያ ከዚሁ መፅሐፍ ሳንወጣ በምዕራፍ 4፥8 ላይ በዙፋኑ ለተቀመጠው(ለአብ) የሰገዱትና ያመሰገኑት እንስሳት በምዕራፋ 5፥9-14 ላይ ከ24ቱ ሽማግሌዎችና ከአእላፋት መላእክትም ጋር "ባለጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል።" ያሉለት የታረደው #በግ(እየሱስ) ጨምረው በቁጥር 13 ላይ እየሰገዱ ልክ ለአብ በሰጡት ክብር #ለበጉም #ይሁን ሲሉ ለሁለት ማንነት ያለን አንድን ምንነት ለማሳየት አይደለምን?
....................🙏🙏🙏...............
" እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:32)
🙏አርነት በእውነት ይሆንላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው🙏🙏🙏
📌
"ሁለቱ ማንነቶች"
ልዩ ክፍል
🐐 "ፍየል ወዲ ቅዝምዝም ወድያ!"↔️
"ሁለቱ ማንነቶች!" በሚል ርዕስ ተከታታይ #፬ ክፍሎችን ማድረሴ ይታወሳል። ይኽውም በእስልምና ውስጥ ካሉ ኃጥያቶች ሁሉ የከፋው ማሻረክ ወይም #ማጋራት እንደሆነ እየነገሩን በዛው በእስልምና መዛግብት አላህን ብቻ ሳይሆን ሙሐመድንም ማምለክ እንደሚገባን፤ ተጋሪ አድርጎ ማቅረቡን ነበር ያተትኩት። ይህንንም ለሙሐመድ👳‍♂ መገዛት፣ ሙሐመድን መታዘዝ፣ ሙሐመድን መከተልንና ሙሐመድን መውደድን አንስተን እንደ ማስረጃ ዱያለሁ። ይህችም #ልዩ ክፍል ቃል በገባሁት መሰረት በበለጠ ዳሰሳ🔦🔍 ከመመለሴ በፊት ለማስታወሻም ለማርከሻም😉 ትሆን ዘንድ እንካችሁ ያልኳት ቅንጭብ ናት።📝
"በእውነት ሙሐመድን👳‍♂ መገዛት፣መታዘዝ ፣ መከተልና መውደድ ለሌላውም መልእክተኛ የሚደረግ አይደለም ወይ?"🤔 ባለፈውም እንደከተብኩት "ምኑን ከምኑ አገናኘኽው?" ካላችሁኝ የዘረዘርኳቸው🗞 መሰረታዊ ልዩነቶችን መለስ ብሎ መቃኘት ሙግቱም ያልገባው😴 ደጋግሞ በሰከነ🧐 አእምሮ ማየት መልካም ነው። አልያ "አይ መታዘዝ፣ መገዛት ወዘተ ለሌሎቹም የምንሰጠው ነውና ምን አዲስ ነገር አለ?"🤷‍♂ ብሎ መመለስ ሙግቱ እዚ መልሱ እዚያ፤ ፍየል ወዲ ቅዝምዝም ወድያ ማለት ነው። ይሁንና በመዛግብቱ መሐመድን መታዘዝ፣ መገዛት፣ መከተልም ሆነ መውደድ ከሌላው የሚለይበትን ነጥብ በነጥብ በድጋሚ እነሆ፦
👉 ስለ መታዘዝና ለሙሐመድ ፍርድ ስለ መገዛት ስናወራ ከሌላው እኮ እንደሚለይ 📚ኢቡኑ ካቲር በምዕራፍ 4፡65 ላይ የሰጠውን ማብራራያና የጥቅሱን "መገለጥ" ስናይ አንድም ሙሐመድን #በፍፁምመታዘዝ መታዘዝን አማኝ ለመባል የሚጠይቅ ሁለትም አንድምታው የመሐመድን ፍርድ ያልተስማማውን ሰው በቅፅበት ጭንቅላቱን ያስቀላን አንድምታ እያነበብን እንዴት ነው ከሌላው ጋር አንድ ነው እምንለው ጃል?🤔 አላህስ ይህን አስከትሎ ካልታዘዝክ ዋ! ያለው ለማነው? የቱስ መልዕክተኛ ነው እንዲህ ባለ መገዛት ተገዙት የተባለው ጭንቅላትስ #የተቀላለት?
👉 ታዘዙኝ ተከተሉኝ ሲል ሙሐመድ ዝም ብሎ አይደለም ንፅፅርን አቅርቦ እንጂ! ይኽውም #ተራን መከተል መታዘዝን ሳይሆን #ክርስትያኖች #እየሱስን #ይከተሉትና #ይታዘዙት #በነበረበት #ልክ፣ ጠርዝና ሙላት ነው እኮ ነው የሚሉን ኢብኑ አባስ ለምዕራፍ 3፥31-32 በሰጡት ማብራርያ። መቼም ሙሐመድ ከኔ በፊት ነበሩ እንዳላቸው የእስልምና ነብያት ሳይሆን አምላክ አድርገው ክርስትያኖች እየሱስን እንደያዙት ያዙኝ ማለት ቀጥታ አምልኩኝ ካልሆነ ምንድነው?🤦‍♂
👉 ሙሐመድ እኮ ውደዱኝ፤ ለኔ ያላችሁ ፍቅር ለዘላለማችሁ ወሳኝ ነው ያለው አሁንም በ ሳሂህ አል ቡካሪ ቅፅ 1 መፅሀፍ 2 ሀዲዝ ቁጥር 15 እና 16፣ ሳሂህ ሙስሊም መፅሀፍ 001 ሀዲዝ ቁጥር 70 እና 71 #ከሰውዘር ሁሉ በላይ እንዳለ ለምን እንዘነጋለን ጎበዝ?
- በመጨረሻም "መታዘዝ ማለት ማምለክ አይደለም!" ለሚል #ልክነው፤ እኛስ መች አልን እንደዛ? ነገር ግን ከትልቅ ምስጋና ጋር በዚህ የሚስማማና "ይህን የሚል ሐሰተኛ ነው!" የሚል ሙስሊም ካለ ካለበት ግዜ አንስቶ ሙስሊም አደለሁም ስላለ እጃችንን ዘርግተን እንቀነለዋለን። እንዴት ካላችሁ እንዲህ፦
🖊 አንድን የሐይማኖት አባት የሚሉትን መስማትና መታዘዝ እርሳቸውን #ማምለክ አደለም።
🖊 አይ መታዘዝና ያሉትን ማድረግ ማምለክ ነው! ያለ የተፋለሰን ሐሳብ #ተናግሯል
🖊 የተፋለሰን ሐሳብ የተናገረ #ስህተተኛ ነው።
📌 ሲጠቀለል ሙሐመድ(ኢብኑ ካቲር ለምዕራፍ 9፡31 በዘገበው ላይ) "መታዘዝና ሊቃውንቶች ያሉትን ማድረግ ማምለክ ማለት ነው።" ካለ ከላይ ባለው ዝርዝር መሰረት የተፋለሰን ሐሳብ ተናግሯል። እናም #ሙሐመድ "#ስህተተኛና የተፋለሰን ነገር #ተናጋሪ ነው!" የሚለውን ስለሚያረጋግጥልን እናመሰግናለን።🤓
.................//................
" እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:32)
🙏አርነት በእውነት ይሆንላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው🙏🙏🙏
የቁርአን ጸሐፊ ስለ ክርስቲያናዊ ነገረ መለኮት የነበሩት የተሳሳቱ አመለካከቶች
👇
ብዙ ሙስሊም ወገኖች የኢየሱስን አምላክነት ለመቀበል የሚቸገሩት የእግዚአብሔርን ሥሉስ አሐዳዊነት መረዳት ስለሚሳናቸው ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ሥሉስ አሐዳዊነት ለመረዳት የሚቸገሩት ደግሞ በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመርያው እስልምና ስለ ፈጣሪ አንድነት ያለው አመለካከት ነው፡፡ እስልምና ስለ ፈጣሪ አንድነት ያለው ግንዛቤ ፈጣሪ በአካልም በመለኮትም ሌጣ አንድ (Monadic) እንደሆነ ሲሆን ይህ እምነት “ነጠላ አሃዳዊነት” (Unitarian Monotheism) ይሰኛል፡፡ የእስልምና ነጠላ አሃዳዊነት እምነት በፈጣሪ ማንነት ውስጥ ምንም ዓይነት ብዝሐነት መኖሩንና መኖር መቻሉን የሚክድ በመሆኑ ብዙ ሙስሊሞች እግዚአብሔር በመለኮታዊ ባሕርዩ አንድ ሆኖ በሦስት አካላት የተገለጠ መሆኑን የሚያስተምረውን የክርስትናን ትምህርት እንደ መድብለ አማልክታዊነት እንዲቆጥሩት አድርጓቸዋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ስለ እግዚአብሔር አንድነት የሚናገሩትን ጥቅሶች የሚተረጉሙት በዚሁ የነጠላ አሃዳዊነት አመለካከት መሠረት ሲሆን የእግዚአብሔርን ሥሉስ አሐዳዊነት ለመረዳት በእጅጉ ይቸገራሉ፡፡ ኢየሱስ አምላክ መሆኑንና ደግሞም የእግዚአብሔር ልጅ መባሉን ሲሰሙ ግራ የሚጋቡት በዚህ ምክንያት ነው፡፡ “ኢየሱስ አምላክ ከሆነ እንዴት የአምላክ ልጅ ሊሆን ይችላል? እንዴት ወደ እግዚአብሔር ሊጸልይ ይችላል? እንዴት በእግዚአብሔር የተላከ ሊሆን ይችላል? ወዘተ.” በማለትም ይጠይቃሉ፡፡

ሁለተኛውና ዋነኛው ምክንያት ደግሞ የቁርአን ጸሐፊ ክርስቲያኖች በሦስት አማልክት የሚያምኑ በማስመሰል መናገሩ ነው፡፡ ቁርአን ሱራ 4፡171 ላይ ለክርስቲያኖች “(አማልክት) ሦስት ናቸው አትበሉ” የሚል መልእክት ያስትላልፋል፡፡ ነገር ግን ክርስቲያኖች በየትኛውም ዘመን “አማልክት ሦስት ናቸው” በማለት አምነው አያውቁም፡፡ ትክክለኛው የክርስትና አስተምህሮ አንድ አምላክ ብቻ እንዳለና ይህ አንዱ አምላክ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የተሰኙ ሦስት አካላት እንዳሉት የሚናገር ነው፡፡ የቁርአን ጸሐፊ “አንዱ አምላክ ሦስት አካላት አሉት አትበሉ” ቢል ኖሮ በእርግጥም ክርስትያናዊውን አስተምህሮ የሚመለከት አባባል በሆነ ነበር፡፡ ቁርአን የነቀፈው ይህ አስተምህሮ ለክርስትና ባዕድ በመሆኑ ይህ ትምህርት በክርስትና ውስጥ እንደሚገኝ በማስመሰል የተናገረው ሰው ሀሰተኛ ነው፡፡ የቁርአን ጸሐፊ የሥላሴን አስተምህሮ በትክክል ያቀረበበት አንድም ጥቅስ የለም፡፡ ሦስቱን የሥላሴ አካላት፣ ማለትም አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስን በጋራ አንድም ጊዜ አልጠቀሰም፡፡ ከዚህ በተፃራሪ ተከታዩን ጥቅስ በመጻፍ ሙስሊሞችን ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ የመራ መልዕክት አስተላልፏል፡- “አላህም፡- የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ አንተ ለሰዎቹ፡- እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን? በሚለው ጊዜ (አስታውስ)፤ ጥራት ይገባህ፤ ለኔ ተገቢዬ ያልሆነን ነገር ማለት ለኔ አይገባኝም፤ ብዬው እንደሆነም እርግጥ አውቀኸዋል፤ በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፤ ግን አንተ ዘንድ ያለውን አላውቅም፤ አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህና ይላል” (ሱራ 5፡116)፡፡

ይህ ጥቅስ በዕለተ ቂያማ (በፍርድ ቀን) በአላህና በዒሳ መካከል የሚደረግ ምልልስ እንደሆነ ሙስሊሞች ያምናሉ፡፡ የቁርአን ጸሐፊ መንፈስ ቅዱስ የሥላሴ አካል መሆኑ በክርስቲያኖች መታመኑን የጠቀሰበት ቦታ ባለመኖሩ ብዙሙስሊሞች ከዚህ ጥቅስ በመነሳት ሥላሴ ማለት አላህ፣ ማርያምና ኢየሱስ እንደሆኑ ያስባሉ፡፡ በዚህ ዘመንየሚገኙት አንዳንድ ሙስሊም ምሑራን አሸማቃቂ የሆነውን ይህንን የቁርአን ስሁት መረዳት አለባብሶ ለማለፍ የተለያዩ ትርጉሞችን ለመስጠት ሙከራዎችን ቢያደርጉም ጥንታዊያን ሙስሊም ሊቃውንት ይህ ጥቅስ ስለ ሥላሴ የሚናገር መሆኑን በጽሑፎቻቸው አስፍረዋል፤ በዚህ ዘመን የሚገኙት ብዙ ሙስሊሞችም ተመሳሳይ አመለካከት ያንፀባርቃሉ፡፡1 ለመጽሐፍ ቅዱስና ለክርስትና ሥነመለኮት መሠረታዊ እውቀት የጎደለው ሰው ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ክርስቲያን ሥላሴ ማለት አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ያውቃል፡፡ ክርስቲያኖች ኢየሱስና ማርያም ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች እንደሆኑ አያምኑም፡፡ ነገር ግን አንዱና ብቸኛው አምላክ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ የተሰኙ ሦስት አካላት እንዳሉት ያምናሉ፡፡

የሥላሴን ትምህርት እንደተገነዘቡ የሚናገሩ ቀላል ቁጥር የሌላቸው ሙስሊም ወገኖች ደግሞ አስተምህሮውን ከሰባሊዮስ አመለካከት ጋር ሲያምታቱት ይስተዋላሉ፡፡ ሰባሊዮስ እግዚአብሔር ነጠላ አካል ብቻ እንዳለው ነገር ግን ራሱን እየለዋወጠ እንደገለጠ ያስተማረ በሦስተኛው ክፍለ ዘመን የኖረ ሰው ነበር፡፡2 ሱራ 4፡171 ላይ ከተጻፈው ጋር በሚጣረስ ሁኔታ የቁርአን ጸሐፊ ተከታዩን ሐሳብ ይናገራል፡- “እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፤ አልመሲሕም አለ፦ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፤ እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት፤ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡” (5፡72)

መጽሐፍ ቅዱስ መሲሁ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን በበርካታ ስፍራዎች ላይ ይናገራል፡፡ (ዮሐንስ 1፡1፣ 20፡28 ሮሜ 9፡5፣ ቲቶ 2፡13፣ ዕብራውያን 1፡8-10)፡፡ ከላይ በተቀመጠው የቁርአን ጥቅስ ውስጥ ክርስቲያኖች “አላህ የመርየም ልጅ አልመሲህ ነው” እንደሚሉ ተነግሯል፡፡ “አላህ” የሚለው እግዚአብሔርን ለማመልከት የገባ የአረብኛ ቃል ነው ብንል “ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው” ማለት እና “እግዚአብሔር ክርስቶስ ነው” ማለት ከፍተኛ የሆነ ልዩነት አላቸው፡፡ በክርስትና አስተምህሮ መሠረት እግዚአብሔር በመለኮቱ ፍጹም አንድ ቢሆንም ነገር ግን በአካል ነጠላ ስላልሆነ ለአብ እና ለመንፈስ ቅዱስ እውቅናን በመንፈግ “እግዚአብሔር ክርስቶስ ነው” የሚለው አባባል ከክርስትና ትምህርት ጋር የሚጣጣም አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም ምንም አይነት ድጋፍ የለውም፡፡ የአብ እና የመንፈስ ቅዱስን ህልውና በመካድ ኢየሱስ ብቸኛው የእግዚአብሔር አካል እንደሆነ የሚያስተምረው ትምህርት ነቢዩ መሐመድ ከመወለዳቸው ከሦስት ክፍለ ዘመናት በፊት በቤተ ክርስቲያን ተወግዟል፡፡ መሐመድ “ነቢይ” ተብለው በምድረ አረብ ከመነሳታቸው በፊት የተጻፉ ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን መናገር ትክክል መሆኑን ነገር ግን እግዚአብሔር ኢየሱስ መሆኑን መናገር ስህተት መሆኑን የሚገልፁ ክርስቲያናዊ ጽሑፎች አሉ፡፡👇
የቁርአን ጸሐፊ ስለ ሥላሴ አስተምህሮ ያለው የተሳሳተ አመለካከት በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም፡፡ እስኪ ተከታዩን ጥቅስ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፡- “እነዚያ አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፤ ከአምላክም አንድ አምላክ እንጅ ሌላ የለም፤ ከሚሉትም ነገር ባይከለከሉ፣ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል” (5፡73)፡፡ በክርስትና አስተምህሮ መሠረት እግዚአብሔር የሦስት ሦስተኛ ሳይሆን በሦስት አካላት የሚኖር አንድ አምላክ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በስፋት እንደምንመለከተው ለዚህ አስተምህሮ ከበቂ በላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች አሉ፡፡ በየትኛውም ዘመን ክርስትያኖች እግዚአብሔር የሦስት ሦስተኛ እንደሆነ አምነው አያውቁም፡፡ ምናልባት ከላይ በተጠቀሰው የቁርአን ቃል ውስጥ አላህ የተባለው እግዚአብሔር አብን ለማመልከት ከሆነ፤ በሥላሴ ውስጥ እግዚአብሔር አብ መጀመርያ እንጂ ሦስተኛ አይደለም፡፡ ክርስቲያኖች የሥላሴን አካላት ሲጠሩ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በማለት አብን ያስቀድማሉ (ማቴ 28፡19)፡፡ የቁርአን ጸሐፊ ስለ ክርስትና አስተምህሮ ምንም ዕውቀት የሌለው ሰው መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

የቁርአን ጸሐፊ ስለ ክርስትና አስተምህሮ ምንም ፍንጭ ያልነበረው ሰው መሆኑ የተጋለጠበት ሌላው አጋጣሚ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ለማስተባበል በሞከረበት ወቅት ነው፡፡ ሱራ 23፡91 እንዲህ ይነበባል፡- “አላህ ምንም ልጅን አልያዘም (አልወለደም)፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም…” እንዲሁም ሱራ 9፡30 ላይ ጸሐፊው ስለ ክርስቲያኖች በእርግማን የታጀበ ንግግር ይናገራል፡- “አይሁድ ዑዘይር የአላህ ልጅ ነዉ፣ አለች፤ ክርስቲያኖችም አልመሲሕ የአላህ ልጅ ነዉ አሉ፤ ይህ በአፎቻቸዉ (የሚናገሩት) ቃላቸው ነው፤ የነዚያን ከነሱ በፊት የካዱትን ሰዎች ቃል ያመሳስላሉ፤ አላህ ያጥፋቸዉ (ከእዉነት) እንዴት ይመለሳሉ!” የቁርአን ጸሐፊ አላህ ልጅ አለመውለዱን ሲናገር ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድን ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ሱራ 6፡101 ላይ “ለርሱ ሚስት የሌለችው ሲሆን እንዴት ልጅ ይኖረዋል?” በማለት ከተናገረው መረዳት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ሱራ 72፡3 ላይ “…ሚስትንም ልጅንም አልያዘም” ይላል፡፡ ብዙ ሙስሊሞች “ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው” የሚለውን ንግግር ሲሰሙ ወደ አዕምሯቸው የሚመጣው ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ የሚለው የተሳሳተ ግንዛቤ በመሆኑ ይህ ንግግር አይዋጥላቸውም፡፡ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የሚለው አባባል በእርሱና በእግዚአብሔር አብ መካከል ያለውን ዘላለማዊ ሕብረት ለማመልከት የሚያገለግል መንፈሳዊ አገላለጽ እንጂ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድን የሚያመለክት አይደለም፡፡ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለውን ንግግር በእጅጉ ይቃወማሉ፤ ለመስማትም ይጸየፋሉ፡፡

ማጠቃለያ
የቁርአን ጸሐፊ ክርስቲያናዊ አስተምህሮዎችን በትክክል ማቅረብ አለመቻሉ መገለጡ ሁሉን አዋቂ ከሆነው አምላክ ዘንድ እንዳልመጣለትና ውሱን ከሆነው አእምሮው ያመነጫቸው ስለመሆኑ ጥሩ ማስረጃ ነው፡፡ እውነተኛው አምላክ አማሬ ኩሉ በመሆኑ እንዲህ ያሉ ስህተቶችን ሊሠራ አይችልም፡፡ ሙስሊም ወገኖቻችን በእንዲህ ያሉ ስህተቶች የተሞላውን ቁርአንን ከመከተል ይልቅ እውነተኛ ወደሆነው ቃለ እግዚአብሔር ወደ መጽሐፍ ቅዱስተመልሳችሁ የዘለዓለምን ሕይወት ታገኙ ዘንድ ጥሪ እናደርግላችኋለን፡፡ የልብ ዓይኖቻችሁ ተከፍተው የእውነትንብርሃን ታዩ ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ይርዳችሁ!

ኦንላይን ለማንበብ 👇👇👇

http://www.ewnetlehulu.org/am/who-is-god/01-2/
እስልምና እየሱስ አልሞተም ይላልን??

ክፍል አንድ

መፅሓፍ ቅዱሳችን በማያሸማ መልኩና በታሪክ በታጀበ አገላለፅ እየሱስ እንደሞተ፣ ከሙታንም እንደተነሳ አስተምሮናል። እየሱስም በራሱ አንደበት ተናግሯል።

." እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥"በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት #ከኢየሩሳሌም ጀምሮ #በአሕዛብ #ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።"
(የሉቃስ ወንጌል 24:46-47)

" #ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።"
(የዮሐንስ ራእይ 1:18)

" በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። #ሞቶ_የነበረው_ሕያውም_የሆነው_ፊተኛውና_መጨረሻው እንዲህ ይላል።"
(የዮሐንስ ራእይ 2:8)

ሙሐመዳውያን ይህንን በ መፅሓፍ ቅዱስ አልፎም በ ሴኪውላር ታሪክ ውስጥ ተዐማኒነቱ የተረጋገጠለትን ክስተት በተቃራኒው ለመሟገት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ለመሆኑ የእስልምና  ትምህርት በ እየሱስ ሞት ላይ ያለው አቋም ሙስሊሙ ሕብረተሰብ እንደሚያስበው በማያከራክር መልኩ "አለመሞቱን" ነውን??


ሱራቱ አሊ ኢምራን (3):55

አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ ዒሳ ሆይ! እኔ #ወሳጂህ፣ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፤ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ፤*** እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ፥ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፤ ከዚያም መመለሻችሁ ወደኔ ነዉ፤ በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ።

إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى ُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَىَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَجَاعِلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوكَ فَوْقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ ۖ ثُمَّ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ
በዚህ ክፍል ላይ በ አማርኛው "ወሳጂ" ተብሎ የተተረጎመው"َ مُتَوَفِّيكَ" (mutawaffika, ሙታዋፊካ) የሚል ቃል ሲሆን፣ "ወፋት wafat" (ሞት, death") ከሚል ቃል የመጣና ትክክለኛ ትርጉሙ "እንዲሞት ማድረግ" "መግደል" ነው። "ወሳጂ" ተብሎ የተተረጎመበት ምክኒያት ቃሉ አንዳንዴ "በ እንቅልፍ ውስጥ ወደ ላይ መውሰድ" ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በ "እንቅልፍ ውስጥ" የሚለውን ትርጉም ለመስጠት ግዴታ አረፍተ ነገሩ ውስጥ "እንቅልፍ" የሚል መኖር አለበት። አለበለዚያ ቃሉ ሁል ጊዜ ነፍስ ላለው ነገር ለማገልገል ሲገባ ትርጉሙ "እንዲሞት ማድረግ" ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ የዚህ ሱራ (3:55) ትክክለኛው ትርጉም ኢሳ( እየሱስ) እንዲሞት መደረጉን ያሳያል።

ለምሳሌ ያህል ይህንን ክፍል፣ "መሞት" ብሎ የተረጎሙ የ ቁረአን ትርጉሞችን እንመልከት

ዩሱፍ አሊ የመጀመሪያ ትርጉም (ሳይከለስ)
አለህ ባለ ጊዜ አስታውስ " #እንድትሞት አደርገሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው

ሼር አሊ ትርጉም
Remember the time when ALLAH said' `O Jesus, I will cause thee to #die a
natural death and will raise thee to Myself,
አለህ ባለ ጊዜ አስታውስ " #እንድትሞት አደርገሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው"

ኻሊፋ ትርጉም
Thus, GOD said, "O Jesus, I am terminating your life, raising you to Me,
አላህም አለው:"እየሱስ ሆይ፣ሕይወትህን እቋጨለው፣ከዚያም ወደኔ አነሳሃለው

ፓልመር ትርጉም
When God said, 'O Jesus! I will make Thee #die and take Thee up again to me
 አላህም አለ፣"እየሱስ ሆይ #እንድትሞት አደርገሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው"

ሮድዌል ትርጉም
 Remember when God said, "O Jesus! verily I will cause thee to #die, and will take thee up to myself
አለህ ባለ ጊዜ አስታውስ " #እንድትሞት አደርግሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው

ሴይል ትርጉም
When God said, o Jesus, verily I will cause thee to #die, and I will take thee up unto me,
አለህ ባለ ጊዜ አስታውስ " #እንድትሞት አደርግሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው

ማውላና ሙሓመድ አሊ ትርጉም
When Allah said: O Jesus, I will cause thee to #die and exalt thee
አላህ ባለ ጊዜ አሥታውስ፣"#እንድትሞት አደርግሀለው ከዛም ከፍ አደርገሃለው

ሸቢር አህመድ ትርጉም
”O Jesus! I will cause you to die of natural causes and I will exalt you in honor
"እየሱስ ሆይ #እንድትሞት አደርግሃለው ከዚያም በክብር አነሳሃለው።"

ሙሓመድ አሰድ ትርጉም
“Lo! God said: “O Jesus! Verily, I shall cause thee to die, and shall exalt thee unto Me
አላህም አለ፣"እየሱስ ሆይ #እንድትሞት አደርገሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው"

የሚገርመው ነገር ሱራ 3:55ን "ወሳጂ" ብሎ የሚቶረጉሙ ምሁራን ሳይቀሩ፣ "ወፋት" የሚለውን ቃል በ ሌሎች የ ቁረአን ጥቅሶች፣ "ሞት" ብሎ ተርጉሞውታል። የ እየሱስ ነገር ላይ ሲደርሱ ግን "መውሰድ" እንደሆነ አድርገው ተርጉመውታል።

ከታች የተዘረዘሩ የ ቁረአን ጥቅሶች ሁሉ "ወፋት" የሚለውን ቃል የተጠቀሙ ሲሆኑ #በሁሉም የ ቁርአን ትርጉሞች #ሞት ተብሎ ተተርጉሟል።

2:234፣ 2:240፣ 3:193፣ 4:15፣4:97፣ 6:61፣7:37፣ 7:126፣ 8:50፣ 10:46፣ 10:104፣ 12:101፣ 13:40,
16:28፣ 16:32፣ 16:70፣ 39:42፣ 40:67፣ 40:77፣ 47:27
 
ምሳሌ

2:234
وَٱلَّذِينَ يُتَوَفَّوْنَ مِنكُمْ وَيَذَرُونَ أَزْوَٰجًا يَتَرَبَّصْنَ بِأَنفُسِهِنَّ أَرْبَعَةَ أَشْهُرٍ وَعَشْرًا ۖ فَإِذَا بَلَغْنَ..

እነዚያም ከናንተ ውስጥ #የሚሞቱና('ዩታዋፋውና'    يُتَوَفَّوْنَ) ሚስቶችን የሚተዉ (ሚስቶቻቸው) በነፍሶቻቸው አራት ወሮች ከዐስር (ቀናት ከጋብቻ) ይታገሱ፡፡

3:193
 
رَّبَّنَآ إِنَّنَا سَمِعْنَا مُنَادِيًا يُنَادِى لِلْإِيمَٰنِ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِرَبِّكُمْ فَـَٔامَنَّا ۚ رَبَّنَا فَٱغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّـَٔاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ ٱلْأَبْرَارِ
ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፤ አመንንም፤ ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፤ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፤ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር #ግደለን( وَتَوَفَّنَا ዋታዋፋና)
ክፍል ሁለት ቀጥለህ አንብብ..
@Jesuscrucified
ክፍል ሁለት
 በ አረብኛ " موت" (መውት፣ Mawt) የሚል ቃል ለ "ሞት" የሚጠቀሙት ሲሆን ቃሉም በማያከራክር መልኩ "ሞት Death" ማለት ነው። ሌላ ትርጉምም የለውም።

የሚገርመው ነገር ለነብዩ የቅርብ ዘመድና ተከታይ እንዲውም የ ቁረአን ምሁር የነበሩት "ኢብኑ አባስ" ይህንን ቃል ("መውት")ለ እየሱስ ተጠቅሟል። "ሙታዋፊካ" የሚለው ቃል "ሙሚቱካ" (እንዲሞት ማድረግ) እንደሆነ ግልፅ አድርጓል።

عَنْ اِبْن عَبَّاس , قَوْله : إِنِّي مُتَوَفِّيك يَقُول : إِنِّي مُمِيتك
ኢብኑ አባስ "ሙታዋፊካ"የሚለውን "ሙሚቱካ" "እንዲሞት ማድረግ" ብሎ ዘግቧል።
reference
  1. ተፍሲር አልተበሪ በ ሱራ 3:55 ( http://www.altafsir.com/Tafasir) ላይ በ አረብኛ ማግኘት ይቻላል።
   2. ሳሂህ አልቡኻሪ  ኪታቡል ተፍሲር በ ሱረቱል ማኢዳህ ስር (5:110) Arabic

ስለዚህ በማያከራክር መልኩ አላህ "እየሱስ የተባለውን"  #ኢሳ፣ ወደላይ ሲወስድ መጀመሪያ እንዲሞት ፈቅዶ ከ ሞተ በኋላ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ነገር የ እስልምና መፅሓፍቶችስ ምን ይላሉ?

የ አልተበሪ ታሪክ ቅጽ 4 ገጽ 123

According to Ibn Humayd- Ibn Ishaq- an impeccable authority- Wahb b. Munabbih al-Yamani: GOD ALLOWED JESUS, THE SON OF MARY, TO DIE AT THREE O'CLOCK IN THE DAY; then He took him unto himself.

"ኢብን ሁመይድ ከ ኢብኑ ኢሻቅ እንደዘገበው (ዘገባውም በጣም ታማኝ ወይም ከማያከራክር ስልጣን impeccable) አላህ የ መሪያም ልጅ ኢሳን(ኢየሱስ) ከ ቀኑ በ 3 ሰአት ላይ #እንዲሞት አደረገ። ከዛም ወደላይ አነሳው።"
(ተፍሲር አል ተበሪ ሱራ 3:55 ላይም ይመልከቱ)

ስለዚህ በ እየሱስ ሞትና ትንሳአ ዙሪያ ግራ የተጋባው ከ 600 አመታት በኋላ የመጣው  እሥልምና ነው እንጂ ክርስትና አይደለም።

ስለ ሱራ 4:157ስ?

"እኛ የአላህን መልክተኛ የመሬምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸው (ረገምናቸው)፤ አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትምም ግን ለነሱ ተመሰለ እነዚያም በርሱ ነገር የተለያዩት፣ ከርሱ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፤ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፤ በእርግጥም አልገደሉትም"
-ሱራ 4:157

በዚህ ሱራ ላይ እየሱስን አልገደሉትም የተባሉት አይሁዶች ናቸው። አይሁዶች እየሱስን አልገደሉትም ይላል እንጂ እየሱስ ጭራሹን አልሞተም የሚል የት አለ?? አይሁዶች አልገደሉትም ማለትስ ሮማውያን አልገደሉትም ማለት ነውን?? አይሁዶች እየሱስን ለ ክስ አቅርቧል ግን የ ስቅለቱን ስነ ስርአት የፈፀሙት የ ሮም ወታደሮች ናቸው።

" በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች( ሮማዊው ጲላጦስ) ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ።..."
(የማቴዎስ ወንጌል 27:27-40)

"ለነሱ ተመሰለ" የሚለውስ

እዚህ አያ ላይ (4:157) "ተመሰለ" የሚለው ምን እንደሆነ ኦሪጅናል ቋንቋ ውስጥ የለም፤ ነብዩም አንድም ቦታ " በ ኢሳ ሌላ ሰው ተመሰለ" አላሉም። ቁርአኑ ግልጽ አይደለም። ይልቁንስ ምሳሌ ላሳያቹ፦

 ሱረቱ አል አንፈል 8:17
"አልገደልኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው፤ (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም፤ ግን አላህ ወረወረ፤ (ወደ ዓይኖቻቸው አደረሰው)፤ ለአማኞችም ከርሱ የሆነን መልካም ጸጋ ለመስጠት (ይህን አደረገ)። አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነውና።"

ይህ ክፍል የሚያወራው ሙስሊሞች በጦርነት ውስጥ ስለገደሏቸው ሰዎች ነው። አላህ እያለ ያለው ምንም እንኳን ሙስሊሞች በራሳቸው ጦር ጠላቶቻቸውን ወግቶ ቢገድሉም፣ እነኚህን ጠላቶቻቸውን የገደሉት እነሱ እንዳልሆኑና አላህ እንደሆነ ነው። አገላለፁም እንዲህ ነው
"አልገደልኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው፤ (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም፤ ግን አላህ ወረወረ፤.."

ልክ በዚህ አይን ሱራ 4:157 ላይ ስለ እየሱስ ስናነብ፣ "አልገደሉትም አልሰቀሉትም" ሲል በ እየሱስ ላይ ግድያው አልተፈፀመም ማለት ሳይሆን "አላህ እየሱስ እንዲሞት ማድረጉን" ለመግለፅ መጠቀሙን እንደሆነ እንረዳለን።

አከተመ!!


(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ 15)
----------
3፤ እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥

4፤ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥

5፤ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ፤

6፤ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል፤

7፤ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ፤

8፤ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ።
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
እስላማዊ አጣብቂኝ
መጽሐፍ ቅዱስ ከተበረዘ ቁርኣን ዋሽቷል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ካልተበረዘ ቁርኣን የፈጣሪ መጽሐፍ አይደለም! 👇👇👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/the-holy-bible/islamic_dilemma/
"ሁለቱ ማንነቶች"
ክፍል ፭
👉 በእስካሁኑ ጉዞችን ሙሐመድ እንዴት አምልኩኝ እንዳለ አላህም እንዴት ራሱን ከመሐመድ ጋር ተጋሪ አድርጎ በመፅሐፉ እንዳቀረበ ቃኝተናል። በዛሬው ክፍል ፭ ቅኝታችንም ሙሐመድ እንዴት ከአምልኩኝ ጥያቄ ባለፈ መልኩ በእስልምና መዛግብት እንደተሳለ #እንደተመለከም እናያለን።
👉በሱረቱል አል ፈትህ(48) ቁጥር ዘጠኝ ላይ አንድ ለሙስሊም ወገኖች ሁሉ አስደንጋጭና በዘመናት ለማስተካከል ቢሞክሩም ያልተሳካላቸውን አያ እንመለከታለን። ይህንን #ከሻኪር ቁርአን ላይ በእንግሊዝ አፍ ያለውን ለማሳያ ተጠቅሜአለሁ፦
Surah Al-Fath, Verse 9:
لِّتُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُ وَتُسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

That you may believe in Allah and His Apostle and may aid him and revere him; and (that) you may declare His glory, morning and evening.
(English - Shakir)
እንግዲህ በዝህች አንድ ጥቅስ ውስጥ አላህ እንዲህ ይላል "በአላህና በመልእክተኛው እመኑ እርዱትም፤ ፍሩትም ክብሩንም ሌት ተቀን አውጁ!" ይህ ትርጉም ነው እንግዲ አጨቃጫቂው።
ይህን ሙግት የሚያነብ ሰው ሁሉ ልብ ይለው ዘንድ እሚገባው አረብኛ አለማወቅ ወይም ማወቅ ለዚህ አያ ቀጥተኛ ትርጉም ምንነት ግድ አለመሆኑን ነው። ለምን ቢባል ከላይ የሰጠሁት ትርጉም የኔ ፈጠራ አለመሆኑን ስተነትን ግልጥ ይሆናል። እንግዲ እንደተለመደው አላህንና መልእክተኛውን #እመኑ በሚል ትእዛዝ ይጀምርና #እርዱትም(Tu'azziruh በአረብኛው)፣ #ፍሩትም(Tuwaqqiruh) እና ክብሩን ሁሌም #አውጁ (አምልኩትም, Tusabbihuh) ይላል። የሻኪር ቁርአን ይህንን ነው ቃል በቃል አለምንም ጭማሬ ቁጭ ያደረገው። ሌሎቹ ግን (አማረኛውንም ጨምሮ) #የሌለውን በመጨረሻው ትእዛዝ ላይ "አላህን" የሚል ይጨምሩበታል።
ጥያቄ 🤔ለምንድነው ሻኪር ቀጥታ የተረጎመው? ለምንድነውስ ሌሎቹ ይህንን የጨመሩበት?(ሲያስቡት ስለማያዋጣ ነው ወይስ እውን ስላለ?)
🤔የመጀመሪያው ትእዛዝ ሙሐመድን ያማከለ ከሆነ አለምንም ማስረጃ ሦስተኛው እርሱን አይደለም ማለት ምን ማለት ነው?
ለማንቻውም ይህ አያ ላይ ያሉ ሦስቱም ትእዛዛት ለሙሐመድ እንደሚውሉና እንደዋሉ ለማሳየት 📚የኢብን #አባስን ተፍሲር ማየት በቂ ነው። ኢብን አባስ በተፍሲራቸው ፍሩትንና ክብርን ስጡትን በቀጥታ ከእርዱት ቀጥሎ በማስገባት ቀጥሎም ወደ አላህ ቀንና ለሊት ፀልዮ በሚል ፍቺ ያሳርጉታል።
በእውነቱ ሦስቱም ለአንድ ማንነት መጠቀም እማይመስል ሆኖ የታያቸው ሰዎች ይህንን ለማስታረቅ ነው የመጀመሪያ ሁለቱን ለሙሐመድ ከሰጡ በኋላ ክብር ስጡ እሚለው ጋር ሲደርሱ ለአላህ ያሉት። ሦስቱም ለአላህ እንዳይሆን ደሞ መቼም አላህ በሰይፍ እሚጠብቀው እና እሚረዳው አያስፈልግም። ስለዚ ያው በቅድሙ መንገድ መሄድን መረጡ። ግን በምን ማስረጃ እና ከምን ተነስተው ይህንን አፀደቁ?
💡 እውነታው ግን ኢብኑ አባስ እንደፈሰሩት ሻኪርም እንደ ተረጎመው ሶስቱም ትዕዛዛት ያማከሉት ሙሐመድን ነው።ለዚነው ከሰዋስዋዊ ሙግት በዘለለ ለሙሐመድ ክብር መስጠት #ቁርአናዊ ነው የምንለው። አያችሁ እንዴት አላህ እንኳ ሙሐመድ ክብር እንደሚገባው ሲመሰክር?
ይቀጥላል......
.................//................
" እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:32)
🙏አርነት በእውነት ይሆንላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው!🙏🙏🙏
“ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።” 1ጴጥ. 3፡15

የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ያለ ተግዳሮት የኖረችበት ዘመን የለም፡፡ በየዘመናቱ የነበሩት ተግዳሮቶች አንድ መልክ ባይኖራቸውም ነገር ግን አንድ ዓላማና ግብ ያላቸው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ እርሱም ቤተ ክርስቲያንን ማዳክም ብሎም ማጥፋት ነው፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ዘመናት የኖሩት ክርስቲያኖች መሠረታዊውን የክርስትና አስተምሕሮ ከውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች ተከላክሎ በማቆየቱ ረገድ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል፡፡

የምንኖረው መንፈሳዊ ውጊያ ባለበት ዓለም ውስጥ ነው፡፡ ውጊያው ደግሞ የሚደረገው በሰዎች አዕምሮ ውስጥ ነው፡፡ ይህንን ውጊያ ለማሸነፍ የተዘጋጀንና የታጠቅን መሆን ያስፈልገናል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ስለ ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት ታሪካዊ አመጣጥና መጽሐፍ ቅዱሳዊነት መሠረታዊ ግንዛቤን ማስጨበጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ 1ቆሮ 10፡4-6 ላይ በተናገረው መሠረት በእግዚአብሔር ሐሳብ ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን የሰውን ሐሳብ በማፍረስ አዕምሮን ሁሉ ለክርስቶስ እንዴት መማረክ እንደምንችል ክርስቲያናዊውን መንገድ ያመላክታል፡፡ አንባቢያንም ስለ ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት የበለጠ ጥናት እንዲያደርጉ እንደሚያነሳሳና አቅጣጫን እንደሚጠቁም ይታመናል።

በወንድም ኑረዲን የተዘጋጀውን ይህንን ግሩም ጽሑፍ ያንብቡ👇👇👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/forchristians/apologia/