ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
🅰"አልፋና ዖሜጋ"♎️
👳‍♂ሙሐመዳውያን "እየሱስ እራሱን አምላክ ብሎ የጠራበትን ቦታ ከመፅሐፍ ቅዱስ ቃል በቃል አሳዩን? አንዳች ጥቅስ ታመጡ ዘንድ #አይቻላችሁም!" በማለት መፎከር ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል። ይሁና ጥያቄውን እንኳ እንደ ጥያቄ ብንመዝነው🔍 ወዳቂ መሆኑ ብቻ ሳይሆን "ተንጋለው ቢተፉ ተመልሶ ካ ፉ!"🤦‍♂ እንደሚለው ያገሬ ሰው እራሳቸው ላይ መልሶ ጉድን እንደሚያፈላ አለማወቃቸው ነው።
👉 መቼም ይህንን ከዚህም በፊት አነሳስተነዋልና የዛሬ መፃፅፌን ይህንን ሙግት በመድገም አላንዛዛም። ይሁንና መቼም ነገሩ ለአቅመ ጥያቄም ባይደርስ🤷‍♂ መልስን ሁሌም መመለስ፤ እውነትን ዘወትር መግለጥ💡 ልምዱ የሆነው ሕዝበ ክርስትያን እንካችሁ እያለ ካንድም ሁለት ከሁለትም ሦስት ከሦስትም አራት ቦታን መዥረጥ እያረገ ጀባ ሲል ኖሯል። ይሁንና አውቆ የተኛን እንዲሉ አሻፈረን ሲሉ ይስተዋላል። ዛሬም ይህችን መከተቤ አቶ ዲዳትና👳‍♂ የእርሳቸው የገደል ማሚቶ የሆኑ የኛዎቹ እውቀት አጠር ምላስ ረዘም👳‍♀ ተሳስቶ አሳሳቾች በተለይ በራዕይ መፅሐፍ ላይ ያሉትን ሦስት ጥቅሳት እየሱስ አደለም "#አልፋናዖሜጋ" የተባለው በማለት አይን ያወጣን የአርዮሳዊያን መሰል ትምህርትን ድሮም በተነገረ አሁንም ባለ በሚመጣም እውነት ላቀልም ነው።
እንግዲህ ይህ የራዕይ መፅሐፍ ሙግት እንዲህ በማለት ያትቱታል፦
፩, "ይህ ራዕይ የተሰጠው ከአብ ነውና ማንኛውም ነገር በመፅሐፉ ያለ ምንጩና እኔነቱ የአብና የአብ ብቻ ነው።"
፪, ሲብስም "አልፋና ኦሜጋ ነኝ!" ያለው እራሱ አብ ነው("ያለውና የሚመጣው ጌታ አምላክ")።
፫, ብቻ ምን አለፋን ተወደ መደምደሚያው "ምንም እንኳ እየሱስ 'አልፋና ዖሜጋ' ነኝ ቢል እንኳ በል📢 የተባለውን እንጂ የራሱን ማንነት የሚገልፅ አንዳች ይል ዘንድ መልእክተኛ ብቻ ስለሆነ አይችልምም አላለምም" ይሉናል።😳😳🤔🤔
👉እንግዲህ እስቲ ሌላውን ትተን በራዕይ መፅሐፍ 1 ላይ እንኳ ያለውን ብንተነትን በቂ ስለሚመስለኝ ይህንኑ እንደሚከተለው አስነብባለሁ።
ስንጀምር ይህ መፅሐፍ ሊሆን ያለውን እግዚአብሄር(ይህ የስላሴን የመጀመሪያ አካል "አብን" ማሳየቱን ልብ ይለዋል) ለእየሱስ ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ #መግለጡን፤ ወልድም ይህንን መልአኩን ልኮ ለሐርያው ዮሐንስ #ማመልከቱን፤ ሐዋርያውም ለሰባቱ አብያተ ክርስትያናት በመልዕክተኞች #እንደሰደደ እናያለን።
እንግዲህ ነገሩ እዚ ላይ ነው እሚጀምረው። እዚጋር ነው እንግዲህ ድሮም ቢሆን የእየሱስ ከአባቱ ከአብ ጋር ያለው የልጅና የአባትነት ሕብረት በሚገለጥበት ዘላለማዊ ፍፁም #መታዘዝ(በፈቃዱ) ያልገባቸው መሐመዳውያን😲 ግራ መጋባት የሚጀምሩት። እየሱስ ፈቃዱን በፍፁም መታዘዝ(#perfectobedience) የሚናገረውን የሚያደርገውንም ሁሉን ፈቃዱን #በራሱ ለአብ በማስገዛት የአብን እውቀትና ፈቃድ ይፈፅም ዘንድ ያለው። ይህ ነው እንግዲ የመጀመሪያው የሁለቱ ሕብረት። ይህ ማለት ግን ከአብ የመጣው እውቀት ልክ መልዐኩ ከእየሱስ ተቀብሎ ለሐዋርያው ዮሐንስ እንደሚገልጥ በሶስተኛ ሰውና እራሱን #እኔ እያለ ሳይጠራ እንደሚያቀብል ተራ የመልእክት ተዋረድ አካል ነው ማለት አይደለም‼️ይህም መፅሐፉን መጀመርያና መጨረሻ #ብቻ ሳይሆን #ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ላነበበ እየሱስ ራሱን ብቻና ብቻ የሚወክልን ንግግር ሲያደርግ ትዕይንት ሲከውን እንመለከታለን። ስለዚህም የአብን ፈቃድና እውቀት ሲፈፅምና ሲናገር በተመሳሳይ መልኩ አብ የልጁን ማንነት ልጁ በአባቱ ግልጠት እራሱ የሚያቀውን ይናገር ዘንድ ሰቶታል ማለት ነው።🔑 ይህንንም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14፥21-24 ማበብ ጠቃሚ ነው። እየሱስ "የላከኝ የአብ ቃል ነው" እያለ፤ እዛው "ቃሌን" ብሎ ሲጀምር፤ የሚገልጠው የተሰጠውን የላከውን እንደሆነ እያወሳ #ራሴን እገልጥለታለሁ ሲል እናያለን። ይህ ማለት አብና ወልድ አንድ አካል ናቸው ማለት ሳይሆን #በምንነት #ሁለቱ #ከአንድ እንደሚቀዱ ያስተውላል።ይህንን ጠልቀን በየጥቅሱ እንተነትናለን።
እንደው ለመጠየቅ ያህል መሐመዳውያን ቁጥር አንድን ሲያነቡ "ለባሪያዎቹ...በመልአኩ ልኮ" የሚሉት ቃላት የሚያሳዩት #ባለቤት ማነው?
መቼም መልአክን የሚልክ ባርያም እንሆንለት ዘንድ የተገባው ማን እንደሆን ግልፅ ነው።🤔😁😁😁
ቁጥር ሁለትን በመዝለል መሮጥ🏃‍♂ የሁሌም ልማዳቸው ነው። ግና ሁለትን ቢያዮአት ኖሮ መፅሐፉ ስለምን እንደሚያወራ ይገባቸው ነበር።💡 በቁጥር ሁለት ላይ ለእግዚአብሄር ቃል፣ ለእየሱስም ምስክርነትና ላየው ሁሉ ነገር እንደተፃፈ በእርግጥ ያስረዳል❗️ ይህ ማለት ይህ መፅሐፍ ሦስት ነገሮችን ይዞል ማለት ነው 1⃣ የእግዚአብሄርን ቃል፣ 2⃣የእየሱስን ምስክርነትና 3⃣መልአኩ ያሳየውን። ስለዚህ እየሱስ ተራ መልዕክት አስተላላፊ ቢሆን ኖሮ እንዴት የራሱን ምስክርነት ያወራል?🤔 ግን ነገሩ እንደዛ ስላልሆነ አብን በማክበሩ አብ ደግሞ እርሱ በፊት በነበረ ክብሩ ያከብረው ዘንድ ይሁን ያለውን #የራሱን ምስክርነት ሲያቀርብ እናያለን። ለዚነው ተዋረዱ እነሱ እንዳሰቡት #አደለም ያልነው።
ቁጥር አራት የሚናገረው ስለሰላምታ ቢሆንም ግልፅ ያለ #የስላሴን አስተምሮ የሚያሳይ ለቀጣይም ቁጥሮች ማጣቀሻን #ፍንጭ የሚሰጥ ትልቅ ቁጥር ነው።
ሰላምታው ከአብ(ካለው ከነበረው ከሚመጣ)፣ ከሰባቱ መናፍስት(ከመንፈስ ቅዱስ፤ ይህን በ3፥1,4፥5,5፥6 ላይ መመልከት ይቻላል...ሰባት ብዛትን ሳይሆን ፍፅምናን የሚያሳይ ሲሆን ከነዚ ውጭ ያሉ ሰባት መልአክት ወዘተ የሚሉ ክፍሎች እስካልተፃፈ ድረስ ይህንን ሐረግ አይወክሉም)ና ከወልድ(ከእየሱስ) ነው የመጣው። #ፍንጩንም እንደሚከተለው አትታለሁ፦
ማነው የታመነ ምስክር? #እየሱስ
" ከሙታን በኩር? #እየሱስ....
" ኃጥያታችንን በደሙ ያጠበ? #እየሱስ
" ለአምላኩና ለአባቱ ካህናትያረገን? #እየሱስ
" ከደመና ጋር እሚመጣ? #እየሱስ
" የተወጋ የተወጋውም ውጉም ሲመጣ የሚታይ? #እየሱስ(ዮሐ19፥37) ...
ስለዚህ ይህንን ይዘን ታች ቁጥር 8 ላይ ስንደርስ ይኃው ሲገለፅ የነበረ ማንነት እኔ እንዲ ነኝ ብሎ ይናገራል፦ " ያለውና የሚመጣውም ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ #አልፋናዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።"
🤔እናም "ማነው ይህን የሚለው?" #እየሱስ "ስለማ?" ከላይ ጀምሮ የተጠቀሰው ማንነት እርሱ ብቻ ስለሆነ #ስለራሱ ነዋ እሚለው።
"እንዴት ተልኮ ነው እንጂ ስለ ራሱማ አደለም!" ታድያ እኔ ብሎ ስለ አብ ብቻ ከሆነ እሚያወራው ለምን በቁጥር 18 ላይ "ሞቼ ነበርሁ..." እያለ ያወራል ወገንመችና የትነው አብ የሞተው እናስብ እንጂ‼️