ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ክፍል ሁለት
 በ አረብኛ " موت" (መውት፣ Mawt) የሚል ቃል ለ "ሞት" የሚጠቀሙት ሲሆን ቃሉም በማያከራክር መልኩ "ሞት Death" ማለት ነው። ሌላ ትርጉምም የለውም።

የሚገርመው ነገር ለነብዩ የቅርብ ዘመድና ተከታይ እንዲውም የ ቁረአን ምሁር የነበሩት "ኢብኑ አባስ" ይህንን ቃል ("መውት")ለ እየሱስ ተጠቅሟል። "ሙታዋፊካ" የሚለው ቃል "ሙሚቱካ" (እንዲሞት ማድረግ) እንደሆነ ግልፅ አድርጓል።

عَنْ اِبْن عَبَّاس , قَوْله : إِنِّي مُتَوَفِّيك يَقُول : إِنِّي مُمِيتك
ኢብኑ አባስ "ሙታዋፊካ"የሚለውን "ሙሚቱካ" "እንዲሞት ማድረግ" ብሎ ዘግቧል።
reference
  1. ተፍሲር አልተበሪ በ ሱራ 3:55 ( http://www.altafsir.com/Tafasir) ላይ በ አረብኛ ማግኘት ይቻላል።
   2. ሳሂህ አልቡኻሪ  ኪታቡል ተፍሲር በ ሱረቱል ማኢዳህ ስር (5:110) Arabic

ስለዚህ በማያከራክር መልኩ አላህ "እየሱስ የተባለውን"  #ኢሳ፣ ወደላይ ሲወስድ መጀመሪያ እንዲሞት ፈቅዶ ከ ሞተ በኋላ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ነገር የ እስልምና መፅሓፍቶችስ ምን ይላሉ?

የ አልተበሪ ታሪክ ቅጽ 4 ገጽ 123

According to Ibn Humayd- Ibn Ishaq- an impeccable authority- Wahb b. Munabbih al-Yamani: GOD ALLOWED JESUS, THE SON OF MARY, TO DIE AT THREE O'CLOCK IN THE DAY; then He took him unto himself.

"ኢብን ሁመይድ ከ ኢብኑ ኢሻቅ እንደዘገበው (ዘገባውም በጣም ታማኝ ወይም ከማያከራክር ስልጣን impeccable) አላህ የ መሪያም ልጅ ኢሳን(ኢየሱስ) ከ ቀኑ በ 3 ሰአት ላይ #እንዲሞት አደረገ። ከዛም ወደላይ አነሳው።"
(ተፍሲር አል ተበሪ ሱራ 3:55 ላይም ይመልከቱ)

ስለዚህ በ እየሱስ ሞትና ትንሳአ ዙሪያ ግራ የተጋባው ከ 600 አመታት በኋላ የመጣው  እሥልምና ነው እንጂ ክርስትና አይደለም።

ስለ ሱራ 4:157ስ?

"እኛ የአላህን መልክተኛ የመሬምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸው (ረገምናቸው)፤ አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትምም ግን ለነሱ ተመሰለ እነዚያም በርሱ ነገር የተለያዩት፣ ከርሱ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፤ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፤ በእርግጥም አልገደሉትም"
-ሱራ 4:157

በዚህ ሱራ ላይ እየሱስን አልገደሉትም የተባሉት አይሁዶች ናቸው። አይሁዶች እየሱስን አልገደሉትም ይላል እንጂ እየሱስ ጭራሹን አልሞተም የሚል የት አለ?? አይሁዶች አልገደሉትም ማለትስ ሮማውያን አልገደሉትም ማለት ነውን?? አይሁዶች እየሱስን ለ ክስ አቅርቧል ግን የ ስቅለቱን ስነ ስርአት የፈፀሙት የ ሮም ወታደሮች ናቸው።

" በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች( ሮማዊው ጲላጦስ) ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ።..."
(የማቴዎስ ወንጌል 27:27-40)

"ለነሱ ተመሰለ" የሚለውስ

እዚህ አያ ላይ (4:157) "ተመሰለ" የሚለው ምን እንደሆነ ኦሪጅናል ቋንቋ ውስጥ የለም፤ ነብዩም አንድም ቦታ " በ ኢሳ ሌላ ሰው ተመሰለ" አላሉም። ቁርአኑ ግልጽ አይደለም። ይልቁንስ ምሳሌ ላሳያቹ፦

 ሱረቱ አል አንፈል 8:17
"አልገደልኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው፤ (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም፤ ግን አላህ ወረወረ፤ (ወደ ዓይኖቻቸው አደረሰው)፤ ለአማኞችም ከርሱ የሆነን መልካም ጸጋ ለመስጠት (ይህን አደረገ)። አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነውና።"

ይህ ክፍል የሚያወራው ሙስሊሞች በጦርነት ውስጥ ስለገደሏቸው ሰዎች ነው። አላህ እያለ ያለው ምንም እንኳን ሙስሊሞች በራሳቸው ጦር ጠላቶቻቸውን ወግቶ ቢገድሉም፣ እነኚህን ጠላቶቻቸውን የገደሉት እነሱ እንዳልሆኑና አላህ እንደሆነ ነው። አገላለፁም እንዲህ ነው
"አልገደልኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው፤ (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም፤ ግን አላህ ወረወረ፤.."

ልክ በዚህ አይን ሱራ 4:157 ላይ ስለ እየሱስ ስናነብ፣ "አልገደሉትም አልሰቀሉትም" ሲል በ እየሱስ ላይ ግድያው አልተፈፀመም ማለት ሳይሆን "አላህ እየሱስ እንዲሞት ማድረጉን" ለመግለፅ መጠቀሙን እንደሆነ እንረዳለን።

አከተመ!!


(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ 15)
----------
3፤ እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥

4፤ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥

5፤ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ፤

6፤ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል፤

7፤ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ፤

8፤ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ።
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
ስለ ኢየሱስ መሞት

ሰሞኑን ደግሞ የሕያ የተባለው አብዱል ከዚህ በፊት ጓደኛው ወሒድ ሞክሮት የነበረውን ሙግት አምጥቶ ስለ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ግራ መጋባቱን እና አለማወቁን አሳይቶናል። የ Basiledes እና ሌሎች Gnostic የተባሉትን አስተምህሮት እንደ ሙግት ማቅረቡ አስቂኝ ሆኖ ሳለ በዚህ ጉዳይ ላይ ለጓደኛው የጻፍነውን አለማንበቡ ደግሞ ignorant ያደርገዋል። ባሲለደስ የጻፈው መጽሐፍ አንድም አሁን የለም። ያለው በearly church fathers መጻሕፍት ውስጥ ስለ እሱ የተጻፉ ጥቂት ስንኞች ብቻ ናቸው። እነኚህ ኖስቲኮች ደቀ መዛሙርትም አልነበሩም። ለማንኛውም ለሙግቶቹ ከዚህ በፊት መልስ ሰጥተናል። አሁን ግን፣ እሱ ታማኝ ካልሆኑ የኖስቲኮች ሙግት ይሆኑኛል በሚል ሐሳብ ኢየሱስ አልሞተም ብሎ ከተጠቀማቸው፣ እኛ ደግሞ #ከእስልምና ታማኝ ምንጮች #ኢየሱስ_ሞቶ_ከሞትም_ተነስቷል የሚል ቃል እናስነብበዋለን።

የ አልጠበሪ ታሪክ ቅጽ 4 ገጽ 123

According to Ibn Humayd- Ibn Ishaq- an impeccable authority- Wahb b. Munabbih al-Yamani: GOD ALLOWED JESUS, THE SON OF MARY, TO DIE AT THREE O'CLOCK IN THE DAY; then He took him unto himself.

"ኢብን ሁመይድ ከ ኢብኑ ኢሻቅ እንደዘገበው (ዘገባውም በጣም ታማኝ ወይም ከማያከራክር ስልጣን impeccable) አላህ የ መሪያም ልጅ ዒሳን (ኢየሱስ) ከ ቀኑ በ 3 ሰአት ላይ #እንዲሞት አደረገ። ከዛም ወደላይ አነሳው።"
(ተፍሲር አል ጦበሪ ሱራ 3:55 ላይም ይመልከቱ)

ስለዚህ በ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ዙሪያ ግራ የተጋባው ከ 600 አመታት በኋላ የመጣው እስልምና ነው እንጂ ክርስትና አይደለም።
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified