ለምን አልሰለምኩም?
2.91K subscribers
51 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ዒሳ ወፍ ፈጥሯልን?

በቴሌግራም ሰፈር ስዘዋወር "ኢሳ ወፍ ፈጥሯልን?" በሚል ርእስ የተጻፈች መጣጥፍ አየሁ፡፡ የጽሑፉ ዓላማ ኢሳን እንደ ኢየሱስ የሚቆጥሩና የእርሱን አምላክነት በቁርአን ለማረጋገጥ የሚዳዳቸው ወገኖች ለሚያነሱት ሙግት ምላሽ ለመስጠት ታስቦ ይመስላል፡፡

ሱረቱል አሊ-ኢምራን 3 ፥49
ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ (ይላልም)፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡»

ጸሐፊው ቃላትን በመሰነጣጠቅ ኢሳ እንዳልፈጠረና ከጭቃ በተሠራችው የወፍ ቅርጽ ላይ እፍ ሲልባት አላህ ወፍ እንድትሆን እንዳደረገለት ማሳየትና የሞጋቾቹን ሙግት ስሁት ለማድረግ ተጣጥሯል፡፡ የፈጣሪውን ባለቤትነት ለአላህ ሰጥቷል፡፡ በኢሳና በሙሳ የተሠሩ ተአምራቶችን ለንጽጽር ተጠቅሟል፡፡ ሙግቱ ለሌላ ሙግት ጋባዥና የጠራ ባይሆንም እርሱን ይቆይ፡፡ በተጠቀሰው የቁርአን ታሪክ ላይ ያለው ጥያቄ እንደተባለው ፈጥሯል አልፈጠረም የሚለው ሳይሆን መለኮታዊ መገለጥነቱ ላይ ነው፡፡ መለኮታዊ መገለጥ መሆኑ ላይ የሚነሳውን ጥያቄ ፈች ጽሑፍ ሆኖ ግን አላገኘሁትም፡፡

በአጭሩ ቁርአን መለኮታዊ መገለጥ አይደለም፡፡ ለዚህ የምዕራፍ ስያሜ መለኮታዊ መገለጥ አለመሆኑን ገላጩ ብርሃን ወገግ በማድረግ እዚህ ነኝ ማለት ይጀምራል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ 49 ኛው አንቀጽ እንደ ቀትር ፀሐይ ነገሩን ያደምቀዋል፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ኢሳን በተመለከተ ተገለጠልኝ ያሉትንና ያስተላለፉትን አንዱንም በመለኮታዊ መገለጥ አለመቀበላቸው በዚህ ይጋለጣል፡፡ በእርሳቸው ዘመን የነበሩ ሞጋቾቻቸው ይሉት እንደ ነበር በጀሯቼው ይነበብላቸው ከነበረው የወሰዱትን ነው ተገለጠልኝ ብለው በተለያየ ምክንያት ይከተላቸው ለነበረው ሕዝብ ያስተጋቡ የነበረው፡፡ ቁርአን ጀሯቼው ሞልቶ ሲፈስ የተከተበ ነው ማለት ነው፡፡

ሱረቱል አል-ፉርቃን 25 ፡ 4-5
እነዚያም የካዱት ይህ (ቁርኣን ሙሐመድ) የቀጠፈው በእርሱም ላይ ሌሎች ሕዝቦች ያገዙት የኾነ ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም አሉ፡፡ በእርግጥም በደልንና እብለትን ሠሩ፡፡ አሉም «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናት፡፡ አስጻፋት፡፡ እርሷም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች፡፡»

እንዲህ ከሆነ ከየትኛው መጽሐፍ ላይ እንደ ተነበበላቼውና እነማን እንዳነበቡላቸው ማስረጃህን አምጣው ትሉኝ ይሆናል፡፡ አዎን መካ ውስጥና መዲና በነቢዩ ሙሐመድ ዙሪያና እርሳቸው ጋር ይገናኙ የነበሩ ክርስቲያን የሚባሉ ሰዎች እንደ ነበሩ ቁርአን ይተርካል፡፡ ለዚህ የዚህኛውን የቁርአን አንቀጽ ተፍሲሮች መመርመር ያቻላል፡-

ሱረቱል አን-ነህል 16 ፡ 103
እነርሱም «እርሱን (ቁርኣንን) የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ የዚያ ወደርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐጀም ነው፡፡ ይህ (ቁርአን) ግን ግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ ነው፡፡

ከየትኛው መጽሐፍ ለሚለው ደግሞ የሚከተለውን የአዲስ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍ የሆነውን የቶማስ ወንጌልን ድርሳን ላስነብባችሁ፡-

Gospel of Infancy Thomas 2 : 4-7
'But when a Jew saw what Jesus was doing while playing on the sabbath day, he immediately went off and told Joseph, Jesus' father: "See here, your boy is at the ford and "has taken mud and fashioned twelve birds with it," and so has violated the sabbath." So, Joseph went there, and as soon as he spotted him, he shouted, "Why are you doing what's not permitted on the sabbath?" "'But Jesus simply clapped his hands and shouted to the sparrows: "Be off, flyaway, and remember me, you who are now alive!" And the sparrows took off and flew away noisily." 'The Jews watched with amazement, then left the scene to report to their leaders what they had seen Jesus doing.

ታዲያ የትኛው ነው መለኮታዊ መገለጡ? ነቢዩ ሙሐመድ ከጠገበው ጀሯቼው የተናገሩት እንጂ ከመለኮታዊ መገለጥ የተቀበሉት አይደለም፡፡ እና ውድ ሙስሊም እህቶችና ወንድሞች ምን እንዳመናችሁ፣ ምን ላይ እንደቆማችሁ፣ ወዴት እየሔዳችሁ እንዳላችሁ አሁን ቆም ብላችሁ የምታስቡበት ሰዓት አይመስላችሁም? አምላኬ የውስጥ ዐይናችሁን ይክፈተው!
ሱና ነውና!
ከሰሞኑ በፈረንሳይ የሆነውን መቼም ሁላችን ያየነው ነው። እንዲያው ብዙም ሳንል(ለግዜው ማለቴ ነው) አንድን ሐዲስ ላስነብባችሁና ይህንን መሐመድ ላይ እንዲህና እንዲያ አላችሁ ብሎ በስለት ዘንጥሎ መጣልን እንዴትና ከየት እንደተማሩት ላስታውሳችሁ(ህልቆ መሳፋርት መረጃ ማምጣት ቢቻልም ለግዜው ይበቃል)። በዛውም መሐመድ አበጀህ ማለታቸውን ሳንዘነጋው። ነገሩንም ቅቡል ያደርገዋል ሱና ነውና!

"አብደላ ኢብን አባስ እንደዘገቡት
አንድ አይነስውር የነበረ ሰው ነብዮን የምታንቋሽሽና ስለእርሳቸው መጥፎ ነገርን የምትናገር እናት-ባርያ ነበረችው። እርሱም ይህንን እንዳታደርግ ከለከላት እርሷ ግን አላቆመችም። ነቀፋት ግን እርሷ ይህን ልምዷን አልተወችም። አንድ ምሽት ነብዮን ልትተችና ልታንቋሽሻቸው ጀመረች። እናም እርሱ ጬቤ አፈፋ አድርጎ ከሆድቃዋ ቀበቀበው አጥልቆም ተጫነው፤ ሞተችም። በእግሮቿ መሃል የገባም ልጅ ከርሷ በወጣም ደም ተጥለቀለቀ። ሲነጋም ነብይ ስለሁኔታው ተነገራቸው.......
እርሱም በነብዮ ፊት ተቀመጠ እንዲህም አለ: የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔ አሳዳሪዋ ነኝ፤ እርሷም እርሶን ታንቋሽሽና ትተች ነበረ። ከለከልኳት አላቆመችም፤ ነቀፋኳትም፤ ነገር ግን ይህንን ልማዷን አላቆመችም። ከርሷም እንቁ የመሰሉ ሁለት ልጆችን አፍርቻለሁ አጋሬም ነበረች። ትላንት ምሽት ክፉ ልትናገርዎና ልታንቋሽሽዎ ጀመረች። እናም እኔ ጬቤ አፈፋ አድርጌ ከሆድቃዋ ቀበቀብኩት አጥልቄም እስክገላት ተጫንኩት፤
ይሄኔ ነብዮ:- 'ምስክር ሁኑ ምንም አይነት የደም ካሳ አይከፈልም።' አሉ።"

ሱና አቡ ዳውድ 4361

"Narrated Abdullah Ibn Abbas:

'A blind man had a slave-mother who used to abuse the Prophet (ﷺ) and disparage him. He forbade her but she did not stop. He rebuked her but she did not give up her habit. One night she began to slander the Prophet (ﷺ) and abuse him. So he took a dagger, placed it on her belly, pressed it, and killed her. A child who came between her legs was smeared with the blood that was there. When the morning came, the Prophet (ﷺ) was informed about it........

He sat before the Prophet (ﷺ) and said: Messenger of Allah! I am her master; she used to abuse you and disparage you. I forbade her, but she did not stop, and I rebuked her, but she did not abandon her habit. I have two sons like pearls from her, and she was my companion. Last night she began to abuse and disparage you. So I took a dagger, put it on her belly and pressed it till I killed her.

Thereupon the Prophet (ﷺ) said: Oh be witness, no retaliation is payable for her blood."

Sunan Abi Dawud 4361
In-book : Book 40, Hadith 11
English translation : Book 39, Hadith 4348
Abu Dawood

ተመከቱ እንግዲህ አንድን "የልጆቹን እናት" የሆነችን ባርያውን፣ አንድን "ነብይ" ተናገርሽ ብሎ በአሰቃቂ ሁኔታ መግደል፤ ገዳይንም አበጀህ ማለት ውሉ ምን ይሆን?
እና እስልምና ምንድር ነበር ያልከው ጃል?

@Jesuscrucified
ፍቅር እንደዚህ ነው፤

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥10

ሐዋርያው አንድን ነገር ተረድቷል፤ አምላክ ሲሆን ሳለ ይህን እንደመቀማት ሳይቆጥር የአባቱን ፈቃድ ራሱን በመስጠት እንደ ባርያ ተገኝቶ ከወነ። ይህም እኔ ባልወደድሁት ጊዜ፣ እነሆ ነገሬን ከነገሩ ላርቅ በምሻ ወቅት፣ የቁጣ ልጅ ሳለሁ እኔ እድን ዘንድ የእርሱም ወንድም የአባቱም ልጅ እባል ዘንድ፤ በዘመኑ ፍፃሜ ከርሱ ጋር እርሱን እያየው፤ በታላቅነቱ እንደልቀቱ፤ በክብሩ እንደ ክብረቱ፤ በምስጋናው እንደ አምልኮቱ በህልውናው እኖር ዘንድ ነው። ዛሬ ለኔ የተዋረደው ጌታዬ አምላክ ሲሆን ስጋ የሆነው ፍቅሩን፤ ያተገባኝን ለኔ ያለውን ፍቅር ይገልጥልኝ በዛም እውነት አርነት እወጣ ዘንድ ነው።
ከዚህ በላይ ሚወደኝ ፣ ሚወድሽ፣ ሚወድክ ማን አለ?

ለኃጥኡ እሚሞት በእውነት ይገኝ ይሆንን?

ፍቅር እንደዚህ ነው! እርሱ ቃል ሰው ሆኖልሀል!

አምላክ ሲሆን ሳለ ፍቅር ግድ ቢለው እርሱ እየሱስ ለመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ!

ይህ ፍቅር ከገባህ ቀን አይለፍህ ሰአታትም፥ እየሱስ ይወድሀል። እየሱስ ይወድሻል።

ከኃጥያት አበሳ ነፃ የሚያወጣህን ጌታ እመን ፍቅሩንም ተቀበል።
እነሆ ጊዜው አሁን ነው።

ፍ ቅ ር እንደዚህ ነው።

“This is love: not that we loved God, but that he loved us and sent his Son as an atoning sacrifice for our sins.”
— 1Jn 4፥10

@Jesuscrucified
ለምን አልሰለምኩም? pinned «ፍቅር እንደዚህ ነው፤ “ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥10 ሐዋርያው አንድን ነገር ተረድቷል፤ አምላክ ሲሆን ሳለ ይህን እንደመቀማት ሳይቆጥር የአባቱን ፈቃድ ራሱን በመስጠት እንደ ባርያ ተገኝቶ ከወነ። ይህም እኔ ባልወደድሁት ጊዜ፣ እነሆ…»
ሙስሊም ወገኖቻችን ብዙ ጊዜ ክርስቶስ ያስተማረው በአረማይክ ቋንቋ ስለነበረ የአረማይክ ወንጌል አምጡ ይሉናል፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው ቁርአን መልእክተኞች ሁሉ በገዛ ቋንቋቸው እንጂ በሌሎች ቋንቋዎች አልተላኩም በማለት ስለሚናገር ነው፡-

“ከመልክተኛ ማንኛውንም፤ ለነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም፤ አላህም የሚሻውን ያጠማል፤ የሚሻውንም ያቀናል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።” (ሱረቱ ኢብራሂም 14፡4)

ነገር ግን ቁርአን ለዒሳ “ኢንጂል” የተባለ መጽሐፍ እንደተሰጠው ይናገራል፡-

“በፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲሆን፣ አስከተልን፤ ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሣጭ ሲሆን ሰጠነው።” (ሱረቱ አል-ማኢዳህ 5፡46)

“ኢንጂል” የሚለው ቃል Εὐαγγέλιον “ኤዋንጌሊዮን” ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ መሆኑን ሊቃውንት ይስማማሉ፡፡ ስለዚህ መልእክተኞች ሁሉ በገዛ ሕዝባቸው ቋንቋ ብቻ ተልከው ከነበሩ ለዒሳ ተሰጠ የተባለው መጽሐፍ ቋንቋው ግሪክኛ ሊሆን እንዴት ቻለ? የቁርአን ደራሲ መልእክተኞች በገዛ ቋንቋቸው ብቻ እንደተላኩ ተናግሮ ካበቃ በኋላ በግሪክ ቋንቋ የተጻፈ መጽሐፍ ለዒሳ እንደተሰጠው መናገሩ የአይሁድን ቋንቋ ባለማወቁ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ እንዲህ ያለ የተምታታ ጽሑፍ በዘላለማዊነት በፈጣረ ዘንድ እንደነበረ ማመን መታወር ነው!
የሱራ 9፡31 ሁለት መሠረታዊ ችግሮች

“ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለዉን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፤ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው።” (ሱረቱ አል-ተውባህ 9፡31)

የመጀመርያው የዚህ ጥቅስ ችግር እስላማዊ አስተምህሮን በመጻረር ኢየሱስ አምላክ መሆኑን መናገሩ ነው፡፡ የአማርኛና ብዙ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ከላይ በሚገኘው መንገድ “የመርየም ልጅ አልመሲሕ” የሚለውን “ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን” ከሚለው ጋር በመደመር ቢተረጉሙትም የአረብኛው ጽሑፍ “አልመሲሕ” የሚለውን ከአላህ በኋላ በማምጣት “ወ” (እና) በሚል መስተጻምር ያያይዛቸዋል፡-

اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِنْ دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ
“አትተኸዙ አሕባረሁም ወ ሩህባነሁም አርባባን ሚን ዱኒ አላሂ ወ አል-መሲሐ ኢብነ መርየም …”

ቀጥተኛው ትርጉም “ከአላህና ከአልመሲሕ የመርየም ልጅ ሌላ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን ጌቶች አድርገው ያዙ…” የሚል ነው፡፡ ለዋናው የአረብኛ ንባብ ሃቀኛ መሆን የፈለጉ አንዳንድ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች በዚህ ጉዳይ የተፈተኑ ይመስላሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በአረብኛው ጥቅስ ውስጥ የማይታይ የኮማ ስርዓተ ነጥብ በመጠቀም ለማስተካከል ሞክረዋል፡-

They have taken their doctors of law and their monks for lords besides Allah, AND (also) the Messiah son of Marium… (Shakir)

They take their doctors and their monks for lords rather than God, AND the Messiah the son of Mary… (Palmer)

They take their priests and their monks for [their] lords, besides God, AND Christ the son of Mary… (Sale)

ይህ የቁርአን ጥቅስ ክርስቲያኖች ከአላህ እና ከመሲሑ ውጪ ሌሎችን ማምለክ የማይገባቸው ሆነው ሳሉ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን ያመልካሉ በማለት ወቀሳ ያቀርባል፤ ስለዚህ በጥቅሱ መሠረት ኢየሱስ አምልኮ የተገባው አምላክ ነው፡፡

ሙስሊም ሰባኪያን ይህንን እውነታ ለማስተባበል “መሲሐ” የሚለው حَ በፈትሃ ስለተጻፈ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት ሳይሆን ተሳቢ በመሆኑ ከሊቃውንትና መነኮሳት ጋር መቆጠር አለበት ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይህ አጻጻፍ በቀዳሚያን ማኑስክሪፕቶች ውስጥ ያልነበረ ሲሆን ከጊዜ በኋላ የተጨመረ ነው፡፡ ጥንታዊው የአረብኛ አጻጻፍ አናባቢ ነቁጦች (diacritical marks) ስላልነበረው ከጊዜ በኋላ የተጨመረ ምልክት በመጠቀም መሞገት አሳማኝ አይደለም፡፡ የቁርአን ደራሲ ይህንን ችግር ለማስወገድ ቢፈልግ ኖሮ በቀዳሚያን ማኑስክሪፕቶች መሠረት ክርስቶስ አምላክ መሆኑን በሚያረጋግጥ መንገድ ሐሳቡን ከመግለፅ ይልቅ አላህና መሲሑን ነጣጥሎ “አልመሲሕ” የሚለውን ቃል “ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን..” ከሚለው በፊት ወይም በኋላ ማስቀመጥ ይችል ነበር፤ ነገር ግን አላደረገውም፡፡

ሁለተኛው የዚህ ጥቅስ ችግር ክርስቲያኖች የሃይማኖት አባቶቻቸውን እንደሚያመልኩ በሐሰት መክሰሱ ነው፡፡ በሙሐመድ ዘመን የነበሩ ሰዎች ይህንን ችግር በመረዳት “ክርስቲያኖች ሊቃውንትና መነኮሳትን አያመልኩም እኮ” በማለት ሙሐመድን ለማረም እንደሞከሩ እስላማዊ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ የሙሐመድ ምላሽ የነበረው “አይሁድና ክርስቲያኖች ረበናትና መነኮሳት የተፈቀደውን ሲከለክሏቸው ወይም የተከለከለውን ሲፈቅዱላቸው ይታዘዟቸዋል፤ ይህ አምልኮ ነው” የሚል ነበር፡፡ (Tafsir Ibn Kathir (Abridged), 2000, Volume 4, pp. 409-410)

የተፈቀደውን የሚከለክልና የተከለከለውን የሚፈቅድን ሰው መታዘዝ አምልኮ ከተባለ በቁርአን መሠረት ዒሳ የተከለከለውን የመፍቀድ ሥልጣን እንዳለውና የእርሱን ትዕዛዛት መከተል አስፈላጊ መሆኑ ስለተነገረ በተዘዋዋሪ ቁርአን ኢየሱስን ማምለክ ትክክል መሆኑን ያረጋግጣል ማለት ነው!

“ከተዉራትም ከኔ በፊት ያልለዉን ያረጋገጥሁ ስሆን የዚያንም በናንተ ላይ እርም የተደረገዉን ከፊል ለናንተ #እፈቅድ_ዘንድ፥ (መጣኋችሁ) ከጌታችሁም በሆነ ታምር መጣሁዋችሁ አላህንም ፍሩ፤ #ታዘዙኝም።” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3:50)

እንደ እስልምና አስተምህሮ ሁሉ ነገር የተምታታበት አስተምህሮ በምድር ላይ ይገኝ ይሆን?
አዲስ ጽሑፍ ያንብቡ
ተመሳሳዮቹ ወንጌላት ተጻራሪ ወይስ ተሰባጣሪ?
http://www.ewnetlehulu.org/am/synoptic-gospels/
እግረ መንገዴን ቴሌግራም ገብቼ የሰዎችን ውይይት እየሰማሁ፣ አንድ የሙስሊሞች ግሩፕ ውስጥ አንዱ ክርስቲያን ልጅ ስለ እዮብ 33:4 ጠቅሶ መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ መሆኑን እንደሚያሳይ ይነግረዋል። ክፍሉ እንዲህ ይላል:
"4፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።"

ከዛ፣ ሙስሊሙ ልጅ፣ የግሪክ ሰፕቱያጅንቱ እንደዛ አያሳይም። የአረፍተ ነገሩ ባለቤት "እግዚያብሄር" ነው የሚለው። ስለዚህ የእግዚያብሔር መንፈስ ነው እንጂ መንፈሱ እግዚያብሔር አይደለም ይለዋል። probably ልጁ ከኡዝታዞቹ የሰማውን ነው እንጂ ቋንቋውን አያውቅም። ለማንኛውም ክፍሉን እንመልከት።

Job 33:4
[4]πνεῦμα θεῖον τὸ ποιῆσάν με πνοὴ δὲ παντοκράτορος ἡ διδάσκουσά με

ክፍሉን ከግሪኩ በቀጥታ ሲተረጎም "Divine spirit made me መሎኮታዊው መንፈስ ሰራኝ πνεῦμα θεῖον τὸ ποιῆσάν με" ይሆናል። ምክኒያቱም

1. θεῖον የሚለው ቃል "እግዚያብሄር" አይደለም። መሃል ላይ ያለችው iota "ῖ" ትርጉሙን ትለውጠዋለች። ትርጉሙም "መለኮት" ወይም ደግሞ "አማልክት gods" ማለት ነው። ከአውዱ የምንረዳው ግን ብዛትን ሳይሆን ስለ አንዱ መለኮት ስለሆን ትርጉሙ መለኮት ይሆናል ማለት ነው።

2. θεῖον ግዑዝ ፆታ ነው። እግዚያብሔር ግን θεος ሲሆን፣ ግራማቲካሊ ማስኩሊን ፆታ ነው። የመለኮት masculine gender ደግሞ θεῖος ነው። እዚህ ክፍል ላይ ግን አጨራረሱ ተቀይሮ θεῖον የሆነው፣ መንፈስ፣ የሚለው የግሪክ ቃል πνεῦμα በተፈጥሮ grammatically neuter ወይም ግዑዝ ስለሆነ ነው። ስለዚህ፣ "መለኮት" የሚለው ቃል በግሪክ ሰዋሰዋዊ ህግ የዓረፍተ ነገሩን ባለ ቤት ሲገልፅ በ case, gender, number መመሳሰል ስላለበት ወደ ግዑዝ ተቀይሯል። ይህ ማለት #መንፈስ የአረፍተ ነገሩ ባለ ቤት እንጂ ገላጭ አለመሆኑን ያሳያል። ስለዚህ የሙስሊሞቹ ሙግት ውድቅ ነው ማለት ነው። የአማርኛ መፅሐፍ ቅዱሳችንም የትርጉም ጉድለት እንዳለበት ማወቁ አይከፋም።

መልካም ቀን!!

@Jesuscrucified
በነገራችን ላይ ዮሐንስ 10:30 ላይ "እኔ እና አብ አንድ ነን" የሚለውን ሙስሊሞች ግሪኩን ሲጠቃቅሱት እያየሁ ነው። heis, hen, mia የሚለውን ትርጉም ሲሰጡት አይቻለው። የአላማ አንድነት፣ የህላዌ አንድነት...ምናምን። እንዲህ አይነት ትርጉም በአጭሩ በዘመናዊው ቋንቋ "ሳክስ" ይባላል።😊 ከዬትኛውም ተአማኒ ግሪክ ኤግዝጄስስ ሙግትህን ማስደገፍ አትችልም። እነኚህ ቃላቶች ትርጉማቸው "አንድ" ማለት ሲሆን በግሪክ ግራማቲካል ፆታ ብቻ ነው የሚለያቸው። እሱም እንደ adjective ከመጡ ከሚገልፁት ባለቤት ጋር ለመስማማት ነው፣ except in few exceptions። አንዱ እንዲህ አይነት exception ምሳሌ፣ እራሱ ዮሐንስ 10:30 ነው። በዚህ ክፍል ላይ፣ ግሪኩ "ኤጎ ካይ ሆ ፓቴር #ሄን ኤስሜን" ይላል። 'ኤጎ' ማለት እኔ ሲሆን 'ፓቴር' ማለት ደግሞ አብ ማለት ነው። ሁለቱም masculine gender ናቸው። ስለዚህ፣ በኖርማል ግራማቲካል ሕግ ቀጥሎ መምጣት የነበረበት "ሄስ"(masculine) እንጂ "ሄን"(neuter) መሆን አልነበረበትም። ነገር ግን፣ እንደ ታላቁ ስኮላር ሮበርትሰን "Word pictures of the NT" ፣ #ሄን የተጠቀመበት ምክንያት አብ እና ወልድ አንድ አካል አለመሆናቸውን ለማሳየት እና እንዲያውም በEssence አንድ መሆናቸውን ለማሳየት እንደሆነ ፅፏል።
ዮሓኒስ ደግሞ ቴዎሎጂካል መልዕክቱን ለማስረዳት፣ አንዳንዴ የሰዋ ሰው ህጎችን እንደሚጠመዝዝ የታወቀ ነው። ለምሳሌ፣ Dr. T.Cowden Laughling በ1902 የPHD dissertationኑን በራዕይ መፅሃፍ ውስጥ ዮሓኒስ እንዴት አድርጎ ግራመር እንደተጠቀመ የሚያጠና The Solecism of the Apocalypse ብሎ የፃፈውን ደስ የሚል ጥናት ማየት ይቻላል።

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Concerning the worship of Christ in light of Koine Greek. ሁሉም ሰው ይስማው።
🎙 Naol
ሰሞኑን ሙስሊሞች ነብዩ ተሰደቡ ብለው የሰደበውን ሰውዬ መግደል የሚፈልጉት ከማን ተምረው ነው? መልሱ: the prophet himself!
Sunan Abu Dawud 4361
Fiker
Dawit Getachew
Christ died for us!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Did Matthew compose his gospel only in Hebrew?
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጥበብ ፍጡር ተብላለችን? ክርስቶስ እንዴት ጥበብ ተባለ?
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለወልድ ሕይወት ተሰጥቶታል ማለት ካለመኖር ወደ መኖር ማለት ነውን? And what does the Koine Greek say?
እውነት አላህ የቁርኣን ጠባቂ ነው ተብሏልን? The Islamic Dilemma

ሙስሊሞች ከሚያነሱት ሙግቶች አንዱ፣ ቀጥሎ ያለው ነው:

"መፅሐፍ ቅዱስ የተበረዘው ሰዎች ጠባቂዎቹ ስለተባሉ ሲሆን የቁርአን ጠባቂ ግን አላህ ነው ተብሏል።"

የሚጠቅሱትም ሱራ ይሄ ነው: ሱራ 15:9

إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ

እኛ "ቁርኣንን" እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡

ነገር ግን እዚህ ላይ "ቁራኣን" ተብሎ የተተረጎመው - "አል-ዚክራ" የሚል ቃል እንጂ ቁርአን አይደለም

ዚክር- ማለት "reminder- ማስታወሻ፣ admonition- ምክር" ማለት ነው።

ታድያ መፅሐፍ ቅዱስ ዚክር አልተባለምን? መልሱ ተብሏል ነው።

ሱራ 21:48

وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ

ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን (ወዚክራ) በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡

ሱራ 16:43

وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِي إِلَيْهِمْ ۚ فَاسْأَلُوا أَهْلَ #الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

ከአንተም በፊት ወደእነሱ ወሕይን (ራእይን) የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ #የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡

በዚህ ክፍል ላይ أَهْل الذِّكْرِ (አህላል-ዚክሪ) የሚለውን- የዕውቀትን ባለቤቶች ብለው ተርጉሞውታል። ኢብኑ ከሢር ግን በተፍሲራቸው አህለል ዚክር ማለት "the people of the previous Books" " የቀድሞ መጽሓፍት ባለቤቶች" ማለት እንደሆነ አስቀምጧል ።

ስለዚህ ለሙሴ የወረደውና ከቁርኣን በፊት የወረዱት መፅሓፍት "ዚክር" ከሆኑ፣ ሙግቱ ቀጥሎ ያለው ይሆናል:

1- አላህ ዚክሩን ያወረድነው እኛው ነን፣ እኛው ጠባቂዎቹ ነን ካለ እና ተውራት ዚክር ከሆነ፣ ተውራት ተበርዟል ካልን አላህ ውሸታም መሆኑ ነው። ምክኒያቱም አልጠበቀውማ።

2- አይ፣ ተውራት አልተበረዘም ከተባለም፣ አላህ ውሸታም ይሆናል። ምክኒያቱም ፔንታቱክ የምንላቸው ወይም "ተውራት" ውስጥ እግዚአብሔር ያስተማረው የቁርአን ተቃራኒ ናቸው።

ለምሳሌ: ዘጸአት 4

23 እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤ ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ ትለዋለህ።

እንደ ቁርአን ትምህርት ግን አላህ ባሪያ እንጂ ልጅ የለውም!

3- አይ፣ ኦሪት ከተውራት ይለያል አልተጠበቀም ወይም አሁን ላይ ተውራት ጠፍቷል ከተባለም፣ አላህ መጀመሪያ ያወረደውን ዚክር አሁንም መጠበቅ አልቻለም ማለት ነው።

Hence, Islamic Dilemma! Damned if you do, damned if you don't!😄
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ዚክር ለጠየቃችሁት ሙግት።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በፍጥረታት አለም ውስጥ አንድ አካል ሆኖ ሁለት የተለያዩ ምንነት (Nature) ያላቸው ምሳሌዎች እውነት የሉምን? ክርስቶስ ሁለት Nature ስላለው Opposing ምንነት ነውን?