ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
Forwarded from ለምን አልሰለምኩም? (Naol Jigy)
 በ አላህ ስሞች ዙሪያ "ሙግት"

የ እስልምና መፅሓፍቶች፣ አላህ 99 ስሞች እንዳለው ይነግሩናል።

Bukhari Vol. 3, Book 50, Hadith 894
Narrated Abu Huraira:

Allah's Messenger (ﷺ) said, "Allah has ninety-nine names, i.e. one-hundred minus one, and whoever knows them will go to Paradise."
አቡ ሁረይራ የዘገበው ሓዲዝ ነው፦ የ አላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፣ " አላህ 99 *ስሞች* አሉት ፤ መቶ ሲቀነስ አንድ። ሁሉንም የሚያውቅ ሰው ወደ ገነት ይግባል።

በ Sahih Muslim – Book 35 Hadith 6476 ላይ፤ ከላይ ባነበብነው ሓዲዝ ላይ ጨምሮ እንዲህ ይላል። " አላህ የሚታወቀው በ ጎዶሎ ቁጥር (odd number) ስለሆነ (አንድ ስለሆነ) ጎዶሎ ቁጥርን ይወዳል።"

ጥያቄያችን፦
 1.በ 99ኙ የ አላህ ስሞች ውስጥ "አላህ" የሚልው አልተካተተም። ስለዚህ " አላህ" ከተጨመረበት 99 ሳይሆን 100 ይሆናል። ስለዚህ ከላይ "አላህ 99 ስም አለው" " አላህ የሚወደው ጐዶሉ ቁጥርን ነው" የሚሉ ሓዲዞች ውድቅ ሆኑ ማለት ነው።

2. አይ! "አላህ" የሚለውን አይጨምርም ካላቹ ፣ታዲያ "አላህ"  የሚለው 'ስም' ካልሆነ ምንድን ነው??

3.  አይደለም! 99ኙ ስሞች ለ ፍጡርም ያገለግላሉ፤ ስለዚህ መግለጫ ብቻ ናቸው ('አላህ' ከሚለው ስም ይለያሉ)ካላቹ ደግሞ፣ በ ምሳሌ ብንወስድ ከ 99ኙ ስሞች አንዱ  الْخَالِقُ "አል ኻሊቅ" "ፈጣሪ"  የሚል እንውሰድ። ስለዚህ ፍጡር ሆኖ ፈጣሪ አለ ልትሉን ነው??

4.አይ! ለ ፍጡር አንጠቀማቸውም፣ ካላቹ፤፦ እየሱስ ከ 99ኙ የ አላህ ስሞች በ ብዙ እራሱን ጠርቷል። ስለዚህ እየሱስ ፍጡር ነው ብላቹ የምትሟገቱት ሙግት ውድቅ ይሆናል ማለት ነው። ለምሳሌ፤ ከ 99ኙ የ አላህ ስሞች፦
A. "አል አዋሉ" እና "አል አኺሩ" "የ መጀመሪያ፣ የ መጨረሻ" الأوَّلُ እና الآخِرُ "the beginning and the end" አሉ። ቁርአንም እንዲህ ይላል * ሱራ 57:3

እርሱ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ፣ ግልፅም ስውርም ነው፤ እርሱም ነገርን ሁሉ ዐዋቂ ነው።
He is #the #First and #the #Last, the Ascendant and the Intimate, and He is, of all things, Knowing.

እየሱስም እንዲህ ብሏል

(የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 1)
----------
17፤ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ። አትፍራ፤ #ፊተኛውና #መጨረሻው #ሕያውም እኔ ነኝ፥

18፤ #ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።

B. An-noor النُّورُ The light ሌላ የ አላህ ስም ነው
 
እየሱስም በ ዮሓኒስ 14:6 " ..እኔ ብርሃን ነኝ" " The light"። ልብ በሉ "Al-' ወይም " The" የሚለው definite article ለ አላህም ለ እየሱስም ተጠቅሟል። ይሄ ደግሞ ዝም ብሎ ለተራ ሰው የምንጠቀምው ሳይሆን "ልዩ" መሆናቸውን የሚገልፅ ነው።

C. الباعث አል-ባእዝ "ትንሳኤ" "The resurrection" ወይም "The Resurrector" ወይም  "አዲስ ሕይወት ሰጪ"
እየሱስም በዚህ ስም ተጠርቷል፦

" ኢየሱስም። #ትንሣኤና #ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤"
(የዮሐንስ ወንጌል 11:25)

" ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን #አስነሣዋለሁ።"...The Resurrector!!
(የዮሐንስ ወንጌል 6:54)

ስለዚህ "የ አላህ ስሞች ለ ፍጡር አንጠቀምም" በሚለው ሙግት ከሄድን እየሱስ በ አላህ ስም ስለተጠራ #እየሱስ ፍጡር ሳይሆን #ፈጣሪ ነው ማለት ነው።


 "እየሱስ ዬት ጋር ነው 'እኔ አምላክ ነኝ' ያለው??" ለምትሉ ሙስሊሞች መልሱ ከላይ እንዳነበባችሁት ነው እንላለን!!
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
1
እስልምና እየሱስ አልሞተም ይላልን??

ክፍል አንድ

መፅሓፍ ቅዱሳችን በማያሸማ መልኩና በታሪክ በታጀበ አገላለፅ እየሱስ እንደሞተ፣ ከሙታንም እንደተነሳ አስተምሮናል። እየሱስም በራሱ አንደበት ተናግሯል።

." እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥"በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት #ከኢየሩሳሌም ጀምሮ #በአሕዛብ #ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።"
(የሉቃስ ወንጌል 24:46-47)

" #ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።"
(የዮሐንስ ራእይ 1:18)

" በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። #ሞቶ_የነበረው_ሕያውም_የሆነው_ፊተኛውና_መጨረሻው እንዲህ ይላል።"
(የዮሐንስ ራእይ 2:8)

ሙሐመዳውያን ይህንን በ መፅሓፍ ቅዱስ አልፎም በ ሴኪውላር ታሪክ ውስጥ ተዐማኒነቱ የተረጋገጠለትን ክስተት በተቃራኒው ለመሟገት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ለመሆኑ የእስልምና  ትምህርት በ እየሱስ ሞት ላይ ያለው አቋም ሙስሊሙ ሕብረተሰብ እንደሚያስበው በማያከራክር መልኩ "አለመሞቱን" ነውን??


ሱራቱ አሊ ኢምራን (3):55

አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ ዒሳ ሆይ! እኔ #ወሳጂህ፣ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፤ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ፤*** እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ፥ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፤ ከዚያም መመለሻችሁ ወደኔ ነዉ፤ በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ።

إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى ُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَىَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَجَاعِلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوكَ فَوْقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ ۖ ثُمَّ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ
በዚህ ክፍል ላይ በ አማርኛው "ወሳጂ" ተብሎ የተተረጎመው"َ مُتَوَفِّيكَ" (mutawaffika, ሙታዋፊካ) የሚል ቃል ሲሆን፣ "ወፋት wafat" (ሞት, death") ከሚል ቃል የመጣና ትክክለኛ ትርጉሙ "እንዲሞት ማድረግ" "መግደል" ነው። "ወሳጂ" ተብሎ የተተረጎመበት ምክኒያት ቃሉ አንዳንዴ "በ እንቅልፍ ውስጥ ወደ ላይ መውሰድ" ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በ "እንቅልፍ ውስጥ" የሚለውን ትርጉም ለመስጠት ግዴታ አረፍተ ነገሩ ውስጥ "እንቅልፍ" የሚል መኖር አለበት። አለበለዚያ ቃሉ ሁል ጊዜ ነፍስ ላለው ነገር ለማገልገል ሲገባ ትርጉሙ "እንዲሞት ማድረግ" ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ የዚህ ሱራ (3:55) ትክክለኛው ትርጉም ኢሳ( እየሱስ) እንዲሞት መደረጉን ያሳያል።

ለምሳሌ ያህል ይህንን ክፍል፣ "መሞት" ብሎ የተረጎሙ የ ቁረአን ትርጉሞችን እንመልከት

ዩሱፍ አሊ የመጀመሪያ ትርጉም (ሳይከለስ)
አለህ ባለ ጊዜ አስታውስ " #እንድትሞት አደርገሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው

ሼር አሊ ትርጉም
Remember the time when ALLAH said' `O Jesus, I will cause thee to #die a
natural death and will raise thee to Myself,
አለህ ባለ ጊዜ አስታውስ " #እንድትሞት አደርገሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው"

ኻሊፋ ትርጉም
Thus, GOD said, "O Jesus, I am terminating your life, raising you to Me,
አላህም አለው:"እየሱስ ሆይ፣ሕይወትህን እቋጨለው፣ከዚያም ወደኔ አነሳሃለው

ፓልመር ትርጉም
When God said, 'O Jesus! I will make Thee #die and take Thee up again to me
 አላህም አለ፣"እየሱስ ሆይ #እንድትሞት አደርገሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው"

ሮድዌል ትርጉም
 Remember when God said, "O Jesus! verily I will cause thee to #die, and will take thee up to myself
አለህ ባለ ጊዜ አስታውስ " #እንድትሞት አደርግሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው

ሴይል ትርጉም
When God said, o Jesus, verily I will cause thee to #die, and I will take thee up unto me,
አለህ ባለ ጊዜ አስታውስ " #እንድትሞት አደርግሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው

ማውላና ሙሓመድ አሊ ትርጉም
When Allah said: O Jesus, I will cause thee to #die and exalt thee
አላህ ባለ ጊዜ አሥታውስ፣"#እንድትሞት አደርግሀለው ከዛም ከፍ አደርገሃለው

ሸቢር አህመድ ትርጉም
”O Jesus! I will cause you to die of natural causes and I will exalt you in honor
"እየሱስ ሆይ #እንድትሞት አደርግሃለው ከዚያም በክብር አነሳሃለው።"

ሙሓመድ አሰድ ትርጉም
“Lo! God said: “O Jesus! Verily, I shall cause thee to die, and shall exalt thee unto Me
አላህም አለ፣"እየሱስ ሆይ #እንድትሞት አደርገሀለው ከዛም ወደኔ አነሳሃለው"

የሚገርመው ነገር ሱራ 3:55ን "ወሳጂ" ብሎ የሚቶረጉሙ ምሁራን ሳይቀሩ፣ "ወፋት" የሚለውን ቃል በ ሌሎች የ ቁረአን ጥቅሶች፣ "ሞት" ብሎ ተርጉሞውታል። የ እየሱስ ነገር ላይ ሲደርሱ ግን "መውሰድ" እንደሆነ አድርገው ተርጉመውታል።

ከታች የተዘረዘሩ የ ቁረአን ጥቅሶች ሁሉ "ወፋት" የሚለውን ቃል የተጠቀሙ ሲሆኑ #በሁሉም የ ቁርአን ትርጉሞች #ሞት ተብሎ ተተርጉሟል።

2:234፣ 2:240፣ 3:193፣ 4:15፣4:97፣ 6:61፣7:37፣ 7:126፣ 8:50፣ 10:46፣ 10:104፣ 12:101፣ 13:40,
16:28፣ 16:32፣ 16:70፣ 39:42፣ 40:67፣ 40:77፣ 47:27
 
ምሳሌ

2:234
وَٱلَّذِينَ يُتَوَفَّوْنَ مِنكُمْ وَيَذَرُونَ أَزْوَٰجًا يَتَرَبَّصْنَ بِأَنفُسِهِنَّ أَرْبَعَةَ أَشْهُرٍ وَعَشْرًا ۖ فَإِذَا بَلَغْنَ..

እነዚያም ከናንተ ውስጥ #የሚሞቱና('ዩታዋፋውና'    يُتَوَفَّوْنَ) ሚስቶችን የሚተዉ (ሚስቶቻቸው) በነፍሶቻቸው አራት ወሮች ከዐስር (ቀናት ከጋብቻ) ይታገሱ፡፡

3:193
 
رَّبَّنَآ إِنَّنَا سَمِعْنَا مُنَادِيًا يُنَادِى لِلْإِيمَٰنِ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِرَبِّكُمْ فَـَٔامَنَّا ۚ رَبَّنَا فَٱغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّـَٔاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ ٱلْأَبْرَارِ
ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፤ አመንንም፤ ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፤ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፤ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር #ግደለን( وَتَوَفَّنَا ዋታዋፋና)
ክፍል ሁለት ቀጥለህ አንብብ..
@Jesuscrucified