ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
📌እስልምና ቀልድ ነው📌

🌅ፀሃይ የምትወጣው በ ሰይጣን ቀንድ ታጅባ ነውንን??🌅

ሙስሊሞች ነብዩ ሙሓመድ ጠቢብ እንደሆኑና ማንም ሊደርስባቸው እንዳይማይችል ይሰብኩናል። ከዚህ ቀጥሎ ያለው ሓዲዝ ግን በተቃራኒው እሳቸው ያስቀመጡልን ትምህርት ጥበብ ሳይሆን  "ቀልድ" መሆኑን ግልጥ አድርጎ ያሳየናል።

ሙዋታ መሊክ መፅሓፍ 15 ሓዲዝ 44

ያህያ ከ መሊክ ያስተላለፈው ሓዲዝ እሱም ከ ዘይድ ኢብን አስላም ከ ኢብን ያሳር ከ አብዱላህ አስ-ሱናቢሂ፣ ነብዩ ሙሓመድ እንዲህ ብሏል ፦ "ፀሓይ ስትወጣ የ ሰይጣን ቀንድ አብሯት ይወጣል፣ ፀሀይም ትንሽ ከፍ ስትል ቀንዱ ይለያታል። ከዛ ፀሃይዋ ልክ ሜሪዲያን ( ምኻከል ላይ)  ስትደርስ ቀንዱ መልሶ ይገናኛታል፤ ከዛም ትንሽ ዝቅ ስትል ቀንዱ ይለያታል። እሁንም መጥለቂያዋ ሰዓት አከባቢ መልሶ ቀንዱ ይገናኛታል።" ስለዚ የ አላህ መልዕክተኛ በነኚ ሰዓታት ማንም እንዳይፀልይ ከልክሏል።

زَيْدِ بْنِ أَسْلَمَ، عَنْ عَطَاءِ بْنِ يَسَارٍ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ الصُّنَابِحِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِنَّ الشَّمْسَ تَطْلُعُ وَمَعَهَا قَرْنُ الشَّيْطَانِ فَإِذَا ارْتَفَعَتْ فَارَقَهَا ثُمَّ إِذَا اسْتَوَتْ قَارَنَهَا فَإِذَا زَالَتْ فَارَقَهَا فَإِذَا دَنَتْ لِلْغُرُوبِ قَارَنَهَا فَإِذَا غَرَبَتْ فَارَقَهَا ‏"‏ ‏.‏ وَنَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنِ الصَّلاَةِ فِي تِلْكَ السَّاعَاتِ ‏.‏

ነጥቦቻችን

1. ለ አመታት "እስልምናና ሳይንስ እጅና ጒንት ናቸው" ስትሉን የከረማቹ እስኪ ይህንን ሓዲዝ ለ NASA ሳይንቲስቶች አሳዩአቸውና መልሳቸውን እንስማ!!

2. ክፍል 1 ና 2 ላይ ሰይጣን ሰዎች አከባቢ የሚኖረው እንደ ኩበት ያሉትን ቆሻሻዎችን ለመብላት እንደሆነ ሓዲዞቹ ነግረውናል። አሁን ደግሞ ሰይጣን ወደ ፀሃይ የወጣው ለምን ይሁን???  "ሊበላት ነው" እንዳትሉ ስጋቴ ነው

3. ፀሃይ በ አንድ ቦታ ስትወጣ ሌላ የ ምድር ክፍል ላይ ደግሞ መሃል ላይ፣ ሌላው ላይ ደግሞ እየጠለቀች እንደሆነ ግልፅ ነው። ምክኒያቱም ምድር ክብ የሆነች እና ፀሃይ ላይ ስለምትዞር።  ስለዚህ ጥያቄያችን " በየትኛው የ ምድር አካል ላይ ነው የሰይጣን ቀንድ ፀሃይን የሚያጅበው?? ምክኒያቱም በ አንድ ጊዜ ላይ የ ሰይጣን ቀንድ ሁለቱንም ስራ መስራት አይችልም (መውጣትና መግባት) ። ለ ምሳሌ ኢትዮጺያ ላይ ስትጠልቅ ሌላ ሓገር ደግሞ ትወጣለች።ይሄ ነገር ነብዪ ሙሓመድ " መሬት ክብ ሳትሆን እንደወረቀት የተዘረጋች (flat as a paper)   እንደሆነች አሰበው መናገራቸውን አያሳይምን??

4. በነኚ ሰዓታት ማንም እንዳይፀልይ የከለከሉትስ ለምን ይሆን?? ሰይጣንን ፈርተው ይሁን???

ጥበብ ይህ ነው ከተባለ ጠቢብ መሆን ቢቀርብንስ??
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
🤥እብለት አያልቄው ትንግርተኛው ሙሀመድ ግዑዛን ነገሮች ልክ እንደ ሰብአውያን አፍ አውጥተው የሚናገሩና የሰብአውያንን ተግባራት እንደሚተገብሩ ለተላላ ተከታዮቹ እንዲህም አስተምሯል፡፡

የቂያማ ቀን ከመድረሱ በፊት ሙስሊሞች ከአይሁዶች ጋር ጦርነት በሚገጥሙበት ወቅት አይሁዶች ከድንጋይ ጀርባ ይደበቃሉ፡፡ ያኔ ሙስሊም የሆነ ድንጋይ አፉን አውጥቶ 🙃የአላህ ባሪያ ሆይ አንድ አይሁዳዊ ከጀርባየ ተደብቋል ናና ግደለው በማለት ያጋልጠዋል፡፡ ዝም ካለ ግን አይሁዳዊ ነው ማለት ነው በማለት መሀመድ ተናግሯል፡፡ (ቡኻሪ ቅጽ 4 ጥራዝ 52 #176)፡፡
የድንጋዩ መናገር ሲገርመኝ ጭራሽ ብሔርም አለው፡፡🙉😱

🙊በሙሳ ዘመን እስራኤላውያን ገላቸውን የሚታጠቡት እርስበርሳቸው እየተያዩ ነበር፡፡ ነገር ግን ሙሳ የሚታጠበው ለብቻው ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ እስራኤላውያን ሙሳ የቆዳ በሽታ ቢኖርበት ነው ለብቻው የሚታጠበው እያሉ ያሙት ነበር፡፡ስለሆነም አንድ ቀን ሙሳ ገላውን ሊታጠብ ልብሱን ድንጋይ ላይ ሲያስቀምጥ ያ ልብስ ያስቀመጠበት ድንጋይ የሙሳን ልብስ ይዞ መሮጥ🧐 ጀመረ፡፡ ሙሳም😤 ድንጋይ ሆይ እባክህ ልብሴን መልስልኝ በማለት ከኋላ ይከተል ጀመር፡፡ እስራኤልዊያንም የሙሳን ገላ አይተው ምንም አይነት የቆዳ ችግር እንደሌለበት አስተዋሉ፡፡ ድንጋዩም የሙሳን ልብስ ይዞ ቆመ፡፡ ሙሳም ልብሱን ከለበሰ በኋላ ድንጋዩን በደምብ አድርጎ ደበደበው 🤪 ከድብደባውም የተነሳ ድንጋዩ ላይ 6 እና 7 ሰንበሮች ይታዩ ነበር🤭፡፡ በማለት ሙሄ ድርሳነ ባልቴቱን አስተምሮ አልፏል፡፡(ቡኻሪ ቅጽ 1 #813-814)
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
💥 እስልምና ቀልድ ነው💥

⚡️በ ገነት ሴቶች ይሸጣሉ⚡️

ሙስናድ አቢ ሁሬይራ ሙስናድ አህመድ ኢብን ሐምባሊ ቁጥር 10511

“የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- ‘በገነት የሰው ዝቅተኛው ስልጣን ሰባት ደረጃ አለው፤ ስድስተኘ ደረጃ ላይ ያለውና ከእርሱ ከፍ ብሎ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ያለ ሰው 300 አገልጋዮች አሉት፤ በየቀኑ 300 የወርቅ ትሪ ምግብ ይቀርብለታል፡፡ በያንዳንዱ ትሪ ላይ ያለ ምግብ ዐይነት አንዱ ከሌላው ይለያል፤ ምግቡም ጥፍጥና ከጅምሩ እስከ መጨረሻ አንድ ነው፡፡ እንዲህም ይላል፡- "ጌታየ ሆይ! ለገነት ሰዎች እንድመግብና
የሚጠጡት እንድሰጣቸው ስልጣን ብትሰጠኝ ከእኔ ምግብ ቅንጣት ያህል
አይቀንስም፤" ደግሞም በምድር ከነበሩት ሚስቶቹ የተለዩ 72 ልጃገረድ ሚስቶች
ይኖሩታል፤ የእያንዳንዷ ድንግል
የመቀመጫ ስፋት የምድር አንድ ማይል (1.6 ኪ.ሜ) 🤡🤡 ያህል ነው'፡፡”

ኢማም ጋዛሊም ኢህያ በተሰኘው መጽሐፋቸው እንዲህ አስፍረዋል፡-

አንድ ሰው ነቢዩን እንዲህ ሲል ጠየቀ፡-

"የአላህ ነቢይ ሆይ የገነት ነዋሪዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት ይፈጽማሉን? ከእነርሱ መካከል የሆነ እያንዳንዱ ሰው ከእናንተ የሰባት ሰዎችን ያህል የወሲብ ጥንካሬ ይሰጠዋል፡፡ ነቢዩም እንዲህ አሉ፡- የገነት ነዋሪዎች 500 የገነት ሴቶች፣ 4000 ያላገቡ ሴቶችና 8000 አግብተው የፈቱ ሴቶች ይኖሩታል፡፡…ጨምረውም እንዲህ አሉ፡- በገነት ገበያ ይኖራል፤ በዛ ምንም አይሸጥበትም አይገዛበትም፤ ነገር ግን ወንዶችና ሴቶች ይኖሩበታል፡፡ ማንኛውም ወንድ ከሴቶቹ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለማድረግ ከፈለገ በፍጥነት ያደርጋል፡፡
የገነት ሴቶቹም በመለኮታዊ ንጽህናና ምስጋና እንዲህ እያሉ ይዘፍናሉ፡- "እኛ የገነት ሴቶች እጅግ ቆንጆዎች እና ለመቶ ባሎች ሚስቶች ነን።🙈🙈
.....ከ ሳሂህ ኢመን ፅሁፍ!!

ውድ አንባቢዎች፣ብዙ ጥያቄ ማንሳት ይቻላል ግን አንድ ብቻ እንጠይቅ፦

ሴቶችስ??ቀኑን ሙሉ ከ ገበያ ወንዶችን ገዝታቹ ግብረ-ስጋ ግንኙነት ስትፈፅሙ ትውላላቹ ብትባሉ ደስተኛ የምትሆኑ ይመስላቹሃል???

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
የሙሀመድ የንፅህና አስተምህሮ ፦

ከዚህ በታች ያሰፈርኳቸውን የሙሀመድ እጅግ ተአማኒ የሱና ትረካዎች በተለይም ውሀንና ንፅህናን አስመልክቶ እንደ አንድ የአንደኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ ተማሪ ሆናችሁ እንድታነቧቸው እጠይቃለው፡፡

አቡሰይድ አል ኩድሪ እንደተረከው፦ ሰዎች የአላህን መልክተኛ (ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ሲሉ ጠየቁ፥ ቡዳሃ ከተባለው ሴቶች የወር አበባ ጨርቃቸውን አጥበው ከሚደፉበት፣ የሞቱ እንስሳት እንደውሻ ያሉ ከሚጣሉበት እና የሚሸት ነገር ሁሉ ከሚወረወርበት የጉድጓድ ውሃ ቀድተን ኡዱ ማድረግ እንችላለን? እሳቸውም ሲመልሱ፥ ውሃ ንጹህ ነው በምንም ነገር አይቆሽሽም አሉ። (ሱናን አቡ ዳውድ መጸሃፍ 1 ቁጥር 66) እንዲሁም ይኸው ተመሳሳይ ሀዲስ በሱናን አቡዳውድ መፅሃፍ 1 ቁጥር 67 ይገኛል፡፡

አስ ሳይብ ቢን ያዚድ እንደተረከው፦ አክስቴ ወደ ነብዩ ወሰደችኝ እና፥ “ኦ የአላህ መልክተኛ! የእህቴ ልጅ እግሩ ላይ በሽታ ይዞታል።” እጃቸውንም በጭንቅላቴ ላይ አደረጉና ወደ አላህ ከጸለዩልኝ በኋላ፥ ኡዱ የፈጸሙበትን ውሃ እንድጠጣው አደረጉኝ,,, ።” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቮሉይም 1 መጽሃፍ 4 ቁጥር 189) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቮሉይም 4 መጽሃፍ 56 ቁጥር 741፣ ሳሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 3 ቁጥር 5792 ይመልከቱ)

አቡ ቡርዳ እንደተረከው፦ አቡ ሙሳ አለ፥ ,,, ነብዩ በውሃ መቅጃ ውሃ እንዲመጣላቸው አዘው እጃቸውንና ፊታቸውን ታጥበውበት አፋቸውንም ተጉመጥምጠው ውሃውን በውስጡ ከተፉበት በኋላ፥ “ከዚህ ጠጡና ግማሹን ፊታችሁንና ደረታችሁን አብሱበት ,,, ።” ከውሃው ጠጥተን እንደተባልነውም አደረግን። እሙሰላማም ከመጋረጃው በስተጀርባ፥ “የተወሰነ ለእናታችሁ አስቀሩላት።” ለእናታቸውም ትንሽ አስተረፉላት። (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቮሉይም 5 መጽሃፍ 59 ቁጥር 617) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቮሉይም 1 መጽሃፍ 4 ቁጥር 187 ይመልከቱ)

አል ሚስዋር ቢን ማክራማ እና ማርዋን እንደተረኩት፦ ,,, በአላ፥ የአላህ መልክተኛ ምራቃቸውን ሲተፉ በተከታዮቻቸው እጅ ላይ ይወድቅና ፊታቸውንና ሰውነታቸውን ያሻሹበታል፤ ሲያዙዋቸውም ተጣድፈው ነው የሚፈጽሙት፤ ኡዱ ያደረጉበትንም ውሃ ለመጠቀም ይጋፉ ነበር።,,, (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቮሉይም 3 መጽሃፍ 50 ቁጥር 891) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቮሉይም 1 መጽሃፍ 4 ቁጥር 188 ይመልከቱ)

ኢብን አባስ እንደተረከው፦ ነብዩ አሉ፥ “በምትበሉ ጊዜ እጃችሁን ልሳችሁ ሳትጨርሱ ወይም ሌሎች የእናንተን ሳይልሱ እንዳትጠርጉት።” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቮሉይም 7 መጽሃፍ 65 ቁጥር 366)

አብደላህ ኢብን አባስ እንደተረከው፦ ነብዩ (ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) አንድዋ ሚስታቸው ገላዋን በታጠበችበት ውሃ ኡዱ ማድረግ ፈለጉ። እስዋም የሽንት መሽኒያዬ ቆሻሻ አለበት ብትላቸውም፥ ነብዩ ውሃ በምንም አይነት ነገር አይቆሽሽም አሉ። (ሱናን አቡ ዳውድ መጸሃፍ 1 ቁጥር 68)

መቼም ስለ ንፅህና በተለይም ስለውሀ ንፅህና ለመወቅና ለሌሎች ለማስረዳት ሊቀጠበብት መሆን አይጠይቅም፡፡ ነፍስ ያወቁ ህፃናት እንኳን እንዲህ ያለውን መጃጃል የሚቀበሉት አይመስለኝም፡፡ ሞቶ የጠነባ እንስሳ እንዲሁም ሌሎች ውራጅ ቆሻሾች ያሉበትን ውሀ ቀርቶ ስንት የማጣራት ሂደት ያለፈውን መደበኛው የቧንቧ ውሀ ለመጠጣት ምን ያህሎቻችን እንደሚቀፈን የታወቀ ሆኖ እያለ፡፡ የነብያት ሁሉ አውራው ሙሄ ተጉሞጥሙጦ የተፋበትን ውሀ ለተከታዮቹ ካማጠጣት ጀምሮ ውሀ በማንኛውም ነገርና ሁኔታ ሊበከል እንደማይችል ለተላላ ተከታዮቹ አስተምሮ አልፏል ድንቁርና ይሏል ይሄ ነው፡፡ የሙስሊም ምሁራኑ ከሙሀመድና ከእስልምና ቀደም የነበረውን ጊዜ የጀሀሊያ ወይም የድንቁርና የኋላ ቀርነት እንዲሁም የጨለማ ወቅት እንደነበር ሲያትቱ ይስተዋላል፡፡ ነገር ግን ስልጡኑን የአረቢያ ምድር ቁልቁል ወደ ድንቁርና አዘቅት የዘፈቀው ሙሀመድና እስልምና ለመሆኑ እንዲህ ያለው ከሳይንስ የሚጫለም የተጃጃለ ትምህርት አንዱ ማስረጃ ነው፡፡
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
🌙እራሱን መግዛት ተስኖት የ አላህን ሕግ የጣሰው ነብይ🌙

ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ እንደተመለከትነው፣ አላህ ቁርአኑን  የሚያወረደው የሙሓመድን ፍላጎት ለማሟላትና  ጥማቶቹን ለማርከት ይመስል ሁልጊዜ ሙሓመድ ስህተት ሲሰራ ምንም ያህል ነገሩ ሓጢአት ቢሆንም አላህ ሙሓመድን ትክክል ለማድረግ ቀድሞ ቁርአን ውስጥ የወረዱትን ሕጎች ሽሮ ሙሓመድ ትክክል እንደሆነ የሚናገር ጥቅስ ያወርድለታል። ለምሳሌ ሙሓመድ የ ጉድፈቻ ልጁ የ ዘይድን ሚስት ዘይነብን፣ ዘይድ በሌለበት ወደ ቤቷ ሒዶ እራቆቷን ካየ በኊላ ስለ እሷ ማሰብ ማቆም ሲሳነው 😍ዘይድን ከ ሚስቱ እንዲፋታና ሙሓመድም የተፈታችውን ሚስት እንዲያገባ ሱራ 33:37 አወረደለት። 🤔🤔(የ አል-ጠበሪ ታሪክ ቅጽ 8 ገጽ 3,4)

በተመሳሳይ ሁኔታ ሙሓመድ ቁርአን ውስጥ የወረዱ ሕጎች እሱን የማይመለከት ይመስል ሕጎችን ይጥስ እንደነበርና የአላህንም ሕጎች የማያከብር የግብዝነት ባህሪ ያለው ሰው መሆኑን የሚያሳይ አንድ ርዕስ ይዤ እቀርባለው።

ቁርዓን በ ሱረቱል በቀራ ቁጥር 222 ላይ ወንዶች የወር አበባ ላይ ያለችን ሴት እንዳይቀርቡ ይናገራል። ወደነሱ መቅረብም ሓጢአት እንደሆነ ግልፅ ያደርጋል፦

"ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡ እርሱ አስጠያፊ ነው፡፡ ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ ራቋቸው፡፡ ንጹሕ እስከሚኾኑም ድረስ አትቅረቡዋቸው፡፡ ንጹሕ በኾኑም ጊዜ አላህ ካዘዛችሁ ስፍራ ተገናኙዋቸው፡፡ አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡ ቁርዓን 2:223

ሓዲዞቹ ውስጥ ገብተን ስናጠና ግን ሙሓመድ ይህንን ሕግ ጥሶ እናገኘዋለን። መጣስ ብቻ ሳይሆን ሙሓመድ ከ አይሻ ጋር በ ወር አበባዋ ጊዜ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳደረገ በ ማስረጃ እናያለን።

 ሳሂህ አል ቡኻሪ መጽሓፍ 6:ቁጥር 298

አይሻ እንዲህ ብላ ዘግባለች። እኔና ነብዪ (ሙሓመድ) ከ አንድ ገንዳ ገላችንን እንታጠብ ነበር። በ ወር አበባዬም ጊዜ ከ ወገብ በታች "ኢዛር" አስለብሰውኝ(ነብዩ)  ይደባብሱኝ ነበር (fondle me= ወሲብ ቀስቃሽ በሆነ መንገድ የሚል ትርጉም ይሰጠናል)

ከላይ ያነበብነው ሓዲዝ የ ዶ/ር ሙሕሲን ኻሀን ትርጉም ሲሆን  "ደባበሰ" ተብሎ የተተረጎመው የ አረብኛ ቃል  " فَيُبَاشِرُنِي" "ፋዩባሺሩኒ" የሚል ሲሆን "ባሸራ " ከሚል ቃል የ መጣ ነው። َ ትርጉሙ ግብረ ስጋ ግንኙነት ለመሆኑ ማስረጃዎቻችን እነሆ፤

1.ከ መዝገበ ቃላት (ዲክሺነሪ ) ይመልከቱ፦
بَاشَر

      የሚለውን ቃል "ግብረ ስጋ ግንኙነት"ብሎ ተርጉመውልናል። ፎቶ አንስቼ ከታች እለጥፍላቹዋለው።

2. ሌሎች የ ቁረዓን ጥቅሶች بَاشَر  የሚለውን ቃል "ግብረ ስጋ ግንኙነት" ብለው ተርጉመውታል።

ሱራ 2:187 -" It has been made permissible for you the night preceding fasting to go to your wives [for sexual relations]..... So now, have relations with them( فَٱلْـَٰٔنَ بَٰشِرُوهُنَّ) 
...በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ እነርሱ ለናንተ ልብሶች ናቸው፤ እናንተም ለነርሱ ልብሶች ናችሁ፡፡ አላህ እናንተ ነፍሶቻችሁን የምትበድሉ መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ በእናንተም ላይ ተመለሰላችሁ***፡፡ ከእናንተም ይቅርታ አደረገ፡፡ አሁን ተገናኙዋቸው፡፡
ስለዚህ فَٱلْـَٰٔنَ بَٰشِرُوهُنَّ "ፈልዓና ባሺሩ ሁና" የሚለው ተመሳሳይ (the same)  ቃል ለ ግብረስጋ ግንኙነት መጠቀሙ ግልጽ ነው።

ስለዚህ ሙሓመድ ከ አይሻ ጋር በ ወር አበባዋ ጊዜ ግብረ ስጋ ግንኙነት አድርጒል።

ሙሓመድ ይደባብሳት ነበር እንጂ ግንኙነት አልፈፀመም ቢባል እንኲን ብዙ ጥያቄዎችን ያስነሳል።

1. አላህ በቁረዓን ውስጥ በ ወር አበባ ጊዜያቸው ራቁአቸው ብሏል። አሁን ሙሓመድ አይሻን በ ወር አበባዋ ጊዜ በ ወሲብ ቀስቃሽ ንኪኪ ምን ይሁን ብሎ ነው የሚደባብሳት?? ለ ጥቂት ቀን መታገስ አቅቶት እንደሆነ ልትነግሩን ንውን?? የ አላህን ትዕዛዝ መጣስስ አይደለምን??

2. ታላቁ የ ዘመናችን የ እስልምና ምሁር "scholar" " ዩሱፍ አልቀረዳዊ" በ መፅሓፋቸው "THE LAWFUL AND THE PROHIBITED IN ISLAM" ውስጥ ሲፅፉ እንዲህ ብሏል ".. In Islamic principle If something is prohibited, anything which leads to it is likewise prohibited" "በ እስልምና ውስጥ አንድ የተከለከለ ነገር ቢኖር ወደዛ ነገር የሚወስዱ ልምምዶችም የተከለከሉ ናቸው"

ስለዚህ 'ሙሓመድ ግንኙነት ሳይፈፅም ደባበሳት' ቢባል እንኲን ከ ላይ ካነበብነው የምንረዳው ሙሓመድ ወሲብ ቀስቃሽ ልምምዶችን በ ወር አበባ ጊዜ ይፈፅም ስለነበረ አሁንም ሙሓመድ ሕጉን ጥሶ እናገኘዋለን!!

አንዳንድ ሙስሊሞች ሙሓመድን ከዚህ ጉድ ለማዳን " ሙሓመድ ግንኙነት ፈጽሞ ቢሆን ኢዛር ባላለበሳት ነበር" ይላሉ።

ወገኔ obviously በ ወር አበባ ጊዜ የሚፈፀም ግንኙነት ንፁህ አከባቢ እንደማይፈጥር ግልፅ ነው። ኢዛር መልበስ ደግሞ ትንሽም ቢሆን ከዚህ ይከላከላል፣ ቦታውንም ፅዱ ለማድረግ ይጠቅማል እንጂ ከ ግንኙነት አይከለክልም!!!

ለዚህ ነገር መፍትሄ ፍለጋ እንቅልፍ ለምታጡ ሙስሊሞች አንድ መፍቴሄ ልስጣቹ፦
  "እስልምናን በ ጊዜ ለቀህ ውጣ"

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
🤔እውነት እየሱስ የተላከው ለእስራኤል ሕዝብ ብቻ ነውን??🤔

እስልምና እና ሙሓመዳውያን የ ጀርባ አጥንት የሌለው ሙግት ይዞ መቅረብ የጀመሩት አብዛኞቻችን እንደምናስበው ከ "ዘመነ አህመድ ዲዳት" ወዲህ ሳይሆን ልክ ሙሓመድ "ጅብሪልን አየሁ" ብሎ ማንነቱ እንኲን የማይታወቅና  የሞት ያህል እስኪሰማው ድረስ ሙሓመድን ከ ድንጋይ ጋር ጨፍልቆ በመያዝ  ያሰቃየውን ፍጡር  ማየት ከጀመረ ወዲህ እንደሆነ የ እስልምና መጽሓፎች ሕያው ምስክር ናቸው። ሙግቶቹን በየጊዜው አንድ በ አንድ እያየን የምንሔድ ሲሆን ዛሬ የ ሙሓመድ ፍሬዎች ከሚያነሱያቸው ነጥቦች አንዱን እናያለን።

እንግዲህ ሙሓመዳውያን እየሱስ የ አለም ሁሉ አዳኝ ሳይሆን ለ እስራኤል ብቻ የተላከ ነብይ ለመሆኑ ቀጥሎ ያለውን ጥቅስ ይጠቀማሉ።

" እርሱም መልሶ። ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 15:24)

መልሶቻችን፦

የ እስራኤል ህዝብ በ እግዚያብሔር ዘንድ የተመረጠ ህዝብ መሆኑን መፅሓፍ ቅዱስ ቢቻ ሳይሆን ቁርዓንም ይመሰክራል።ለምሳሌ፣

ሱራቱል በቅራ 2:47
"የእስራኤል ልጆች ሆይ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬንና እኔም በዓለማት ላይ ያበለጥኳችሁ (አባቶቻችሁን በጊዜያቸው ከነበሩት ዓለማት ያበለጥኩዋቸው) መኾኔን አስታውሱ፡፡'

"O Children of Israel, remember My favor that I have bestowed upon you and that I preferred you over the worlds."
 
 የ እየሱስን ተልዕኮ ለ ሁለት ከፍለን እናያለን።
1. የማዳን ስራው በ መስቀል ላይ ሳይፈፀም
2. የ ማዳን ስራው በ መስቀል ላይ ከተፈፀመ በኊላ

1. የ ማዳን ስራው ከመሰራቱ በፊት እየሱስ እስራኤላውያን የተመረጡ የ ኪዳን ልጆች ስለሆኑ እንደ ልዩ መብት "previlage"   አስቀድሞ ከ ማንም በፊት እነሱን ማስተማር  እቅዱ ነው።

ማስረጃ፦
" እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም። በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ።"
ለእናንተ #አስቀድሞ #እግዚአብሔር #ብላቴናውን #አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።
(የሐዋርያት ሥራ 3:25-26)

ስለዚህ ምድር ላይ በሚመላለስበት ጊዜ ክርስቶስ የሚያስተምረው ይሄ የተመረጠ ህዝብን ነው ማለት ነው።  ሌሎችን ቢያስተምርም የ እስራኤልን አምላክ ከ ጥንት ጅምሮ ስለማያውቁና ስለማይረዱት ለ ተልዕኮው( አምነው ተረድተውም አለምን ሁሉ የማዳረስ) ውጤታማነት አይረዳውም። ስለዚህ መጀመሪያ አስቀድሞ ሕዝቡን ማስተማር በ መቀጠል ደግሞ በነሱ በኩል አለምን ማድረስ እቅዱ ሆኖ እናገኘዋለን።

ዋናው ጥያቄ፤ የ እየሱስ የ ማዳን ስራ ለ እስራኤል ብቻ ነውን??? የ ሚል ሲሆን፣ መልሱ #አይደልም ነው። እየሱስ አንድም ቦታ
 " በኔ የሚገኘው ድነት ለ ኢስራኤል ብቻ ነው" አላለም።

ይልቁንስ በ ክርስቶስ የሚገኘው ድነት ለ አለም ሁሉ መሆኑን የምንረዳው የተልዕኮው ሁለተኛ ክፍል ላይ  ፦
1: እየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምራቸው ከነገራቸው ጥቅሶች
2.እየሱስ ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት ወደ አለም ሁሉ መላክ ሲጀምር መሆኑን መፅሓፍ ቅዱስ ግልጽ ነው።

1. " በእርሱ የሚያምን #ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ #ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:16)

2." እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥"በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት #ከኢየሩሳሌም ጀምሮ #በአሕዛብ #ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።"
(የሉቃስ ወንጌል 24:46-47)

3." ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም #እስከ #ምድር #ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።"
(የሐዋርያት ሥራ 1:8)
4." ኢየሱስም። ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤"" ሕያው የሆነም #የሚያምንብኝም #ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።"" እርስዋም። አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ #ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 11:25-27)

5. " ሰዎች #ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:3-4)

6." ራሱንም #ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:6)

ቁርዓንስ ምን ይላል???

ሱረቱል መሪየም 19:21
አላት (ነገሩ) እንደዚህሽ ነው ፤ ጌታሽ ፦ እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፤ ለሰዎችም ታምር፣ ከኛም ችሮታ(ምህረት=mercy) ልናደርገው (ይህንን ሠራን) የተፈረደም ነገር ነዉ አለ፤ (ነፋባትም)።

He said, "Thus [it will be]; your Lord says, 'It is easy for Me, and We will make him a sign to the people and a mercy from Us. And it is a matter [already] decreed.' "

ልብ በሉ ቁርዓን እራሱ እየሱስን "ለ ሰዎች ምህረት ልናደርገው" ይላል እንጂ "ለ ኢስራኤል" አይልም!!!!

ስለዚህ ሙስሊሞች "እየሱስ ለናንተም ሞቷል" ሞትንም አሸንፎ ተነስቷል። ሙሓመድ ግን ለራሱም መዳኑን እርግጠኛ አልነበረም( Sahih al-Bukhari, Volume 5, Book 58, Number 266,  ቁርአን 46:8,9) ። ስለዚህ ከዘላለም ጥፋት 'ይዳን አይዳን' የማይታወቅ
ነብይ ከመከተል "የሞትና የ ሲኦል መክፈቸ በ እጄ ነው" ያለውን ክርስቶስን ተከተሉ ጥሪያችን ነው!!
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
እስልምና የ ሰላም እምነት ነውን

በአሰቀቂ ሁኔታ በሙሓመድ የተገደለችው እናት

"አስማ ቢንት ማርዋን"  ትባላለች። ሙሓመድ ወደ መዲና ከመጣ በኊላ የሱን ነብይነት ካልተቀበሉት ሰዎች ውስጥ አንዷ ናት።

ሙሓመድ ወደ የትሪብ ሲመጣ ብዙ ተከታዮችን እያፈራ፣ በ ሃይልም እየበረታ ነበር። ሆኖም ተቃዋሚዎቹም ነበሩ።  ከነሱ ውስጥ አስማ አንድ ነበረች። ተቃውሞዋ ግን የጉልበት ወይም አመጽ የማስነሳት ሳይሆን ነብዩ ሙሓመድን ለምን እንዳልተቀበለችና ሌሎችም ለምን መቀበል እንደሌለባቸው "ግጥም" መፀፉዋ ነው።

የደረሰባትን ግድያ የምፅፍላቹ ከ ሁለት ቀደምት ከሚባሉ መፅሓፍት ነው።
1. ሲረት ረሱል አላህ በ ኢብን ኢቫቅ ገፅ 675 እና 676
2. ኪታብ አል-ታባቃት አል ከቢር በ ኢብን ሳድ ቅጽ 2 ገጽ 30-31

አስማ ቢንት ማርዋን የፃፈችው ግጥም እነሆ

መሊክንና ናቢትን ንቄያቸዋለው
አውስንና ካዝረጅንም እንደዛው
የናንተ ያልሆነ እንግዳ ሰው ተቀበላቹ
ከ ሙራድም ከማዝሒጅም ያለሆነ ሰው
የራሳቹ መሪ ሲሞት እንዴት እሱን አመናቹ
ለ አጃና ለ ወጥ ጥማት እንዳለው ሰው
አረ ጎበዝ ሰው የለም ክፍት ሁኔታዎችን ተጠቅሞ ይህን ተስፋቸውን የሚያቊርጥ ሰው???

ሙሓመድ ይህንን ሲሰማ እንዲህ አለ
 " አስማ ቢንት ማርዋን የሚጨርስልኝ መነው??"
-ኡመይር ቢን አዲይ አል ኻታሚ  የሚባል ከነብዩ ጋር የነበረ ሰውም ተነስቶ ሔደለት። (ኢብን ኢሻቅ)

ወደ እሷ ቤትም ሲደርስ በልጆቿ ተከባ ነበረች። አንደኛ ልጇን ደግሞ ጡት እያጠባች እያለች ልጁን ከጡቷ አላቅቆ ልቧን በ ሰይፍ በጀርባዋ እስኪወጣ ድረስ ወግቶ ገደላት። (አል ተበቃት አል ከቢር)

ተመልሶም ለ ነብዩ ሲነግረው ነብዩም እንዲህ ብሎ መለሱለት
" አላህን እና መልዕክተኛውን ረድተሃል"
"You have Helped Allah and his messenger"

ወገኖቼ፣ ይህቺ ሴት ሙሓመድን በ ቃል ደረጃ ስለተቃወመች ብቻ ሙሓመድ በ አሰቃቂ ሁኔታ ማስገደሉ ዛሬ ISIS (ኢስላሚክ ስቴት) በ ሶሪያ፣ በ ረቃ ወዘተ ውስጥ ከሚሰራቸው ስራ በምን ይለያል???

ነጥቦቻችን

1.ሙሓመድ እራሱ  በ "ሳሂህ ሙስሊም" መፅሓፍ-31 ቁጥር-6159 ላይ የ እስልምና ምርጥ ትውልድና ሁሉም ሊከተላቸው የሚገባ ትውልድ፦እራሱ የሙሓመድ ትውልድና ከሱ ቀጥሎ የሚመጡ እስከ ሶስተኛ ትውልድ ያሉ እንደሆነ ተናግሯል። ስለዚህ ዛሬ ላይ ሙስሊሞች የሙሓመድ ስም ሲነቀፍ ሙሓመድንና ሰሃባዎቻቸውን( ተከታይዎቻቸውን) ተከትለው ልክ ከላይ እንዳየነው ታሪክ መግደል አይጠበቅባቸውምን?? በሓዲዙ መሰረትስ ISIS ትክክለኛ የሙሓመድ ተከተዮች አይደሉምን??

2. ሙሓመድ "አላህን ረድተሃል" ሲል ምን ማለቱ ነው??? አንድ ምንም የሌላት ብቻ ልጇን የምታሳድግ እናት ሙሓመድ ላይ ጥቂት ቃላትን ስለተናገረች አላህ እጅጉን ፈርቷትና እራሱ እሷን መበቀል ስላልቻለ የሚያግዘውን ሰው ፍለጋ ተነሳ" ልትሉን ነውን?,

እስልምና ሙሓመድና አላህን ያልተቀበለ ሰው ፍርዱ ግድያ እንደሆነ ቀጥሎ በምናነበው ሓዲዝ አሳይቼያቹ የ ISIS እስልምና ከመሬት ተነስቶ የሚፈፀም እንዳልሆነ ግልፅ በማድረግ እቊጫለሁ።

ሳሂህ ሙስሊም፦ሓዲዝ ቁጥር 30
በ አቡ ሁሬይራ ስልጣን የተዘገበው ሓዲዝ እንዲህ ይላል፤ የ አላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብሏል፦ ሰዎች ሁሉ "ላ ኢላሃ ኢለላህ" ብሎ እስኪመሰክሩ ድረስ እንድዋጋቸው(fight them) ታዝዤያለው።.."

It is reported on the authority of Abu Huraira that the Messenger of Allah said: I have been commanded to fight against people so long as they do not declare that there is no god but Allah, and he who professed it was guaranteed the protection of his property and life on my behalf except for the right affairs rest with Allah.

ታላቁ የእስልምና ሙፈሲር  " ኢብን ከሲር"  ሱራ 9:30 ላይ በሰጡት ተፍሲር እንዲህ ብሏል፦
Fighting the Jews and Christians is legislated because they are idolaters and disbelievers. Allah the Exalted encourages the believers to fight the polytheists, disbelieving Jews and Christians, who uttered this terrible statement and utter lies against Allah, the Exalted. As for the Jews, they claimed that Uzayr was the son of God, Allah is free of what they attribute to Him. As for the misguidance of Christians over Isa, it is obvious

ትርጉሙ፦
ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን መዋጋት ተገቢ(ሕጋዊ) ነው፣ ምክኒያቱም ጣኦት አምላኪዎች ስለሆኑ። ምዕመናን( ሙስሊሞች)  እነኚህን ጣኦት አምላኪዎች፣ ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን እንዲዋጉ አላህ ያበረታታቸወል። ምክኒያቱም እነሱ በ አንደበታቸው አፀያፊ ነገርን ተናግሯል። አይሁዶቹ "ኢዝራ" የ አላህ ልጅ ነው አሉ። አላህ ግን ከዚህ የፀዳ ነው። ክርስቲያኖቹ ደግሞ እየሱስን እንደዚያው ብሎ እንደተሳሳቱ ግልፅ ነው!!

ይሄ ነው እንግዲህ የ ሰላም እምነት!!!
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
👆
ሰሂህ አል ቡሃሪ፤ (ቅጽ 4 መጽሃፍ ቁጥር 56 ሀዲስ ቁጥር 784)
==========================
ጃቢር ቢን አብደላህ ዘግቦታል፤

ከቀናትም በአንዱ አርብ እለት መልዕክተኛው የቴምር ዛፍ ስር ቆመው ነበር። ከአንሳር ወገን የሆነ(ች) ሴት ወይም ወንድ " ኦ የአላህ መልእክተኛ እዚህ የቆምክበት ቦታ መድረክ እንስራልህ ሲል(ትል) ጠየቀው(ችው)። መልእክተኛውም እንደፍላጎታችሁ ይሁን አሉ። እነሱም መድረኩን ሰሩለት የአርብ የጸሎት ስነስርአት ለመምራትና ለማስተማር መድረኩም ላይ ወጡ። ማስተማር ሲጀምሩ መድረኩ አጠገብ ያለችው የቴምር ዛፍ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች😭

መልእክተኛውም ከመድረኩ ወርደው የምታለቅሰውን ዛፍ አቅፈው አባበሏት ዛፏም ከመንሰቅሰቅ ቀስ በቀስ በሂደት ልክ ህጻን ልጅ ማልቀሱን ሊያቆም ሲል እንደሚያሰማው አይነት የለሆሳስ ድምጽ 😢በማሰማት ለቅሶውን አቆመች።

መልእክተኛውም አሉ "የቴምር ዛፏ ያለቀሰችው ከዚህ በፊት ትሰማው የነበረውን የሃይማኖት ትምህርት ከጊዜ በኃላ በድጋሚ ስለሰማችው ናፍቆቱ ነው ያስለቀሳት አሏቸው።😂

No comment!!!!
😁1
  📌ሙስሊሞች ያላወቁት ጉድ📌

የዘመናችን ቁርዓን ከማን የተዘገበ ነው??

አብዛኞቻችን እንደምናውቀው ዛሬ ሙስሊሞች የሚያነቡት ቁርኣን ኻሊፋ ኡስማን ያዘገጃው ብለው የሚያስቡትን "version"  ነው። ኻሊፋ ኡስማን ቀድመው የነበሩት "ቁርአኖች" ሰፊ ልዩነት ስለተገኘባቸው ቁርኣኑ በ ቁረይሽ አነባበብ ዘዴ ብቻ እንዲፃፍ በማድረግ ሌሎች የቀሩትን ሁሉ አቃጥሏል።
-Sahih al-Bukhari: vol. 6, bk. 61, no. 510
-Sunan al-Tirmithi: 3104

ኻሊፋ ኡስማን ባሳተመው ቁርኣን ግን ለ ነብዩ ሙሓመድ ቅርብ የሚባሉ የቁረኣን አዋቂዎች ሁሉም አልተስማሙም። ለምሳሌ " አብዱላህ ኢብኑ መስዑድ" እና "ኡበይ ቢን ከዓብ"
 
ለምሳሌ ያህል ኢብኑ መስዑድን እንመልከት

አብዱላህ እብኑ መስዑድ ማነው?
----------------------------------------
ነብዩ ሙሓመድ በ ሕይወት እያሉ፣በ ቁረአን እውቀታቸው ላቅ ያለ ደረጃ አሏቸው ከሚባሉ ደቀ መዛሙርት አንዱ አብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ነው። ነብዩም በገዛ አንደበታቸው "ቁርኣንን ከሱ ተማሩ" ብሏል።

ሳሂህ አልቡካሪ ቅጽ 6 መጽሓፍ 61 ቁጥር 521

ማስሪቅ ዘግቦታል፦
አብዱላህ ቢን ኣዕመረ፣አብዱላ ኢብን መስዑድን ጠቅሶ እንዲህ ብሏል፤ " እሱን ሰው (ኢብን መስዑድን) ለዘላለም ልወደው ይገባኛል። ምክኒያቱም ነብዩ ሙሓመድ (ﷺ) እንዲህ ብለው ሰምቻለው፦ "ቁርዓን ከአራት ሰዎች ተማሩ፤ #አብዱላህ ኢብኑ መስዑድ፣ሳሊም፣ሙዓዝ እና ኡበይ ቢን ካዓብ"
... "‏ خُذُوا الْقُرْآنَ مِنْ أَرْبَعَةٍ مِنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ وَسَالِمٍ وَمُعَاذٍ وَأُبَىِّ بْنِ كَعْبٍ ‏"‌‏.‏

ኢብኑ መስዑድ መካ ውስጥ ከ ሙሓመድ ቀጥሎ ቁርዓንን ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ የቀራ ሰው ነው። ( ኢብን ኢሻቅ፣ ሲረት ረሱል አላህ ገጽ 141)

በሌላ ሓዲዝ ላይ ደግሞ አብዱላህ ኢብኑ መስዑድ በራሱ አንደበት እያንዳንዷን የቁርዓንን ጥቅስ (አያ) በጥንቃቄ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ዬት ቦታ ላይ እንደወረደችም ሳይቀር እንደሚያውቅ እንዲያውም ከሱ በላይ እውቀት ያለው ሰው እንዳላጋጠመው ተናግሯል።
ማስረጃ፦ ሳሂህ አልቡካሪ ቅጽ 6 መጽሓፍ 61 ቁጥር 524
Narrated' Abdullah ibn Mas'ud:
By Allah other than Whom none has the right to be worshipped! There is no Sura revealed in Allah's Book but I know at what place it was revealed; and there is no Verse revealed in Allah's Book but I know about whom it was revealed. And if I know that there is somebody who knows Allah's Book better than I, and he is at a place that camels can reach, I would go to him.

ነጥቦቻችን

1. ኻሊፋ ኡስማን የቁረዓን ቅጂዎቹን ሲያቃጥል፣አዲሱን ቁረዓን አስተካክሎ እንዲፅፍ የታዘዘው ሰው"ዘይድ ቢን ሳቢት" ይባላል። 
በቁረአኑ ስብስብም ሆነ ፅሑፍ ውስጥ ሙሓመድ የመሰከረላቸው 'አብዱላህ ኢብኑ መስዑድም' ሆን 'ኡበይ ቢን ከዓብ' አልተካተቱም። (Al Bukhari 6,61,526)

 ይልቁንስ አብዱላህ ኢብኑ መስዑድ እንደተናገረው ዘይድ ቢን ሳቢት በኡስማን ትዕዛዝ ያዘጋጀው ቁርኣን ሕዝቡን የሚያስት ትክክልኛ ያልሆነ መፅሓፍ እንደሆነ ነው።

ማስረጃ፦ ኢብን ሳድ ኪታብ አል ተበቃት አል ከቢር ቅጽ 2 ገጽ 444
ኢብን መሱድ እንዲህ ብሏል፤
ሙስሊሙ ሕዝብ በ ቁርአኑ ንባብ በርግጥ ተታሏል። እኔ የማነበው ልክ ነብዩ ይቀሩት እንደነበረ አድርጌ ነው። ነብዩንም ከዘይድ ቢን ሳቢት አብልጬ እወዳለው። ከሱ በቀር ሌላ አምላክ በሌለው አምላክ እምላለው፤ ገና ዘይድ ቢን ሳቢት ሕፃን ሆኖ ከልጆች ጋር ጫወታ ሳይጨርስ ከ 70 በላይ የሚሆኑ ሱራዎችን ከነብዩ አፍ ተምሬያለው"

በተጨማሪም፣ ኢብኑ መስዑድ ኡስማን ያዘጋጀው ቁርኣን ትክክል አለመሆኑን ሲገልጽ ይህንን ተናግሯል
"ሙስሊም ሆይ ቁርዕኑን ኮፒ ከማድረግ ተቆጠቡ፤በ አንድ ሰውም እጅ ላይ( ዘይድ) እምነታቹን አትጣሉ።በ አላህ፣ እሱ ገና ሙስሊም ሳይሆንና በ አባቱ እቅፍ እያለ እኔ ሙስሊም ነበርኩ።..የኢራቅ ሕዝብ ሆይ ቁርኣኖቻችሁን ደብቁ፣ ያላችሁን ቁርኣን ሁሉ ደብቁ።"
-ተፍሲር አል ቁርጡቢ ቅጽ 1 ገፅ 53
-ሳሂህ ሙስሊም መፅሓፍ 31:6022

ስለዚህ፣ ከ እብኑ መስዑድ የምንረዳው የዘመናችን ቁረዓን ለሙሓመድ ከወረደው ቁርዓን የተለየ ነው ማለት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ አንድ አስደንጋጭ ነገር ሳናጠና አናልፍም።

ቁርአን፣ልክ እንደ ሓዲዝ ታማኝ ተብለው ከሚታመኑ የ ዘጋቢዎች ሰንሰለት "ኢስናድ" (chain of narration) የተዘገበ መሆን አለበት። ( Yasir Qadhi: An Introduction to Science of the Qur'an page 187)

ዛሬ ላይ ወደ 27 የሚሆኑ የቁርአን አይነት "version" አሉ። ከነኚህ ውስጥ 95%ፐርሰንቱ ሙስሊም "ሓፍስ" የተሰኘውን ቁረዓን ነው የሚያነበው። "ሓፍስ" የተባለበትም ምክኒያት የቁርዓኑ "ኢስናድ" የተዘገበው ከ "ሓፍስ" ስለሆነ ነው። ይህንን ከ ሓፍስ ቁረዓን መጀመሪያ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻለል።

ማስረጃ ለምትፈልጉ ሙስሊሞች 'ኢስናዱ' እነሆ፦
رواية حفص بن سليمن بن المغيرة الاسدي الكوف لقراة عاصم بن ابي النجود الكوفي التابعي حن ابي عبدالرحمن عبااله ابن حبيب السلم عن عٽمان بن عفان, وعلي بن اب طالب, وزيد بن ٽابت, وابي ابن كعب عن النبي

ጥያቄያችን ይህ የ ሙስሊሞች እምነት የተጣለበት "ሓፍስ" የሚባለው ሰው ታማኝ ነውን???  አብረን እንመልከት

ሙስናድ ኢማም አህመድ እብን ሓንባል ቅጽ 1 ሓዲዝ ቁጥር 1267( 1268)
  " መልዕክተኛውን (ሙሓመድ) እንዲህ አሉ፦ ቁርአንን በልቡ የሚያነብና የሚማር ሰው 10 ለሚሆኑ የቤተሰብ አባሎቹ ከ ጋህነም እንዲወጡ ምልጃ የማድረግ መብት ይሰጠዋል"

እዚው ሓዲዝ ላይ የሓዲዙ ፀሓፊ እንዲህ ብሏል
"1. ይህ ሓዲዝ "ዳኢፍ" ነው ወይም "ደካማ" ነው። ምክኒያቱም በ ዘጋቢዎች ሰንስለት ውስጥ #ሓፍስ ስላለ ነው።"
 2. "ሓፍስ በ ሓዲዝ ውስጥ የተጣጣለ ወይ ደካማ ዘጋቢ ነው "وحو متروك الحديٽ" ዋሁወ መትሩኩ አል ሓዲዝ"
(He is rejected in Hadeeth)
3.ቀጥሎም እንዲህ ይላል " ትላልቅ የ እስልምና ምሁራን እነ ኢማም አል-ቡኻሪ፣አል ሓፊዝ እንድህ ብሏል " #ሓፍስ #ተቀባይነት #የለውም"

4. ቀጥሎ እንዲህ ይላል "ሓፍስ መፅሓፍትን ከ ሰው ወስዶ በዛው ሰርቆ ይጠፋል"

5. ቀጥሎ እንዲህ ይላል "و كان كذاب" "ወካነ ከዛባን"
#ውሸታም ነበረ  ( He was a liar!!")

ድምዳሜ

ሙስሊሞች ዛሬ ላይ የሚያነቡት ቁርኣን በ ባሕሪይው #ውሸታም #ሌባ #የማይታመን ሰው የዘገበውን ቁርዓን እንደሆነ ሙግታችንን በ ግልፅ አቅርበናል።

ሙሓመዳውያን ነብዩ ሙሓመድ እራሳቸው የመሰከሩለት የ አብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ቁረዓንን ጥለው ውሸታሙን "ሓፍስ" የተቀበሉበት ምክኒያት ምን ይሆን??? ታድያስ ቁርኣኑ ይታመናል ስንል ትንሽ እንኲን አይከብድም???
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
ሰዎች ሙሓመድን 'እማግጥ' 'womanizer' ይሉት ነበር

ነብዩ ሙሓመድ ማንም ሴት መጥታ "አግባኝ" ብትላቸው "እሽ" ከማለት ወደ ኋላ እንደማይሉ ማስረጃዎች አሉን። በሚገርም ሁኔታ ሰዎች ሴት ልጆቻቸውን እንኳን ለሙሓመድ እጅ መስጠት አይፈልጉም ነበር። በእርግጥ ሰዎቹን እረዳቸዋለው፤ምክኒያቱም ነብዩ በ ጋብቻ ታሪክ ውስጥ ተፈፅሞ የማያውቁ ነገሮችን ሲሰሩ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ በ አንድ ሌሊት እየዞሩ ከ 9ኙም ሚስቶቻቸው ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት እየፈፀሙ የሚያድሩ ሰው ነበሩ። ይሄ ነገር ደግሞ ለዬትኛዋም ሴት ጥሩ ስሜት አይሰጣትም።
 ሓዲዙ እነሆ፦
Narrated Anas: The Prophet (ﷺ)used to visit (have sexual intercourse with)all his wives in one night and he had nine wives.”
"ነብዩ (ﷺ)በ አንድ ለሊት እየዞሩ ከ ሁሉም ሚስቶቻቸው ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት ይፈፅሙ ነበር። በዚያም ጊዜ ዘጠኝ ሚስቶች ነበሯቸው።"
Bukhari Book 62 Hadith 6

ይሄም አንሶ ነብዪ አንድ ቀን በሚስታቸው በ "ሓፍሳ" አልጋ ላይ ከገረዳቸው "ማሪያ" ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት እየፈፀሙ ሓፍሳ ያዘቻቸው። ከዛ ለሓፍሳ ሁለተኛ በዚህ ድርጊታቸው እንደማይመለሱበት ቃል ከገቡ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ጉደኛው አላህ ቀጥሎ ያለውን ቁርዓን አያ (ጥቅስ) አወረደላቸው።

ቁርዓን 66:1
"አንተ ነቢዩ ሆይ አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትሆን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ፤ አላህ እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው።" 😉
 ስለዚህ አላህ ከ ማርያ ጋር እንዲቀጥሉ ፈቀደላቸው ማለት ነው።

ማስረጃዎቻችን፦
1.ተፍሲር አል ጃለሌይን በ ሱራ 66:1 ላይ
2. ሱናን አን ነሳዒ 3411

እኔም ብሆን ልጅ ቢኖረኝና እንዲህ አይነት ሰው እሷን ለማግባት ቢጠይቀኝ በፍፁም አልስማማም። ለዚህም ነው በዚያን ጊዜ የነበሩ ሰዎች ሙሓመድን "አማግጥ" "womanizer" ብለው ለመጥራት የደፈሩት። ለዚህ ደግሞ ማስረጃዬን በ መቀጠል አቀርባለው።

የ አል ጠበሪ ታሪክ ቅጽ 9: ገጽ 139

'ለይላ" የምትባል አንዲት ሴት ነብዩ ጀርባቸውን ለፀሓይ ሰጥቶ በተቀመጡበት ከኋላ ወጥተ ትክሻቸውን ነካ ነካ አረገቻቸው። እሳቸውም "ማን ነው?" ብሎ ጠየቁ። እሷም መልሳ "የ አንድ 'ንፋስ ጋር ተፎካካሪ' ልጅ ነኝ፤ ለይላ ቢንት አል-ኻቲም እባላለው። ለ እርሶ እራሴን ለመስጠት (በ ጋብቻ) መጥቻለው፤ ስለዚህ አግባኝ።" አለቻቸው። ነብዩም መልሶ "እሽ፣ እቀበላለው" አሉ።እሷም ተመልሳ ለ ወገኖቿ ነብዩ እንዳገቧት ነገረቻቸው። ሰዎችም እንዲህ አሏት " ምን ሆነሻል?? አንቺ የተከበረሽ ልጅ ነሽ። ነብዩ ግን #እማግጥ "Womenizer" ። ስለዚህ ሒጂና ሓሳብሽን እንደቀየርሽ ንገሪው።" እሷም ሒዳ ጋብቻው እንዲቀር ጠየቀቻቸው። እሳቸውም ተስማሙበት። "ይላል
"...it is reported that Layla bt. al-Khatim b. 'Adl b. 'Amr b. Sawad b. Zafar b. al-Harith b. al-Khazraj approached the Prophet while his back was to the sun, and clapped him on his shoulder . He asked who it was, and she replied, "I am the daughter of one who competes with the wind. I am Layla bt. al-Khatim. I have come to offer myself [in marriage] to you, so marry me." He replied, "I accept." She went back to her people and said that the Messenger of God had married her. They said, "What a bad thing you have done! You are a self-respecting woman, but the Prophet is a womanizer. Seek an annulment from him." She went back to the Prophet and asked him to revoke the marriage and he complied with her request.

ሙስሊሞች ኮስተር ብላቹ ይህ ሰው ነብይ ነው ተቀበሉት ስትሉን ትንሽ እንኳን ሊከብዳቹ ይገባል።
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
ነብዩ ሙሓመድን ሶስት አመት ዘግይቶ የገደለው መርዝ "ከነ ስሙ" ላሳውቃቹ!!!

Solving Mystery: ሙሓመድ ከ ሶስት አመት በኋላ ስለሞተ የገደለው መርዙ አይደለም ለምትሉ ሙስሊሞች👇👇

በ መጀመሪያ ደረጃ ነብዪ ሙሓመድ ተመርዞ ቢሞቱ የ አምላክ ነብይ ላለመሆናቸው ማስረጃ ነውን??

መልስ ከመስጠቴ በፊት ቀጥሎ ያለውን ሓዲዝ ላስነብባቹ።

ሳሂህ ሙስሊም መፅሓፍ 26 ሓዲዝ ቁጥር 5430

"አናስ ዘግቦታል፦ አንዲት አይሁድ ሴት ወደ አላህ መልዕክተኛ(ﷺ) የተመረዘ ስጋ ይዛ መጣች። የ መርዙም ስሜት ሲሰማቸው አስጠሯት እና ጠየቋት። እሷም እንዲህ ብላ መለሰች፤ "እርሶን ለመግደል ፈልጌ ነው"።ነብዩም እንዲህ አሉ፤ "#አላህ #ይህንን #እንድታደርጊ #ስልጣን #አይሰጥሽም።…"

ልብ በሉ፣ አላህ ለ አይሁዳዊቷ ልጅ ነብዩን እንድትገድል ስልጠን እንደማይሰጣት የተናገሩት ነብዩ እራሳቸው ናቸው። ስለዚህ ለ ቅድሙ ጥያቄያችን መልስ የሚሆነው፦ነብዩ በ ገዛ አንደበታቸው "ከዚህ መርዝ አልሞትም" ብለው ስለተናገሩ፣ ከመርዙ ከሞቱ የአምላክ ነብይ የመሆናቸው ነገር ጥያቄ ውስጥ ይገባል ማለት ነው።

የሚቀጥለው ጥያቄ፣ ነብዩ ከ አይሁዳዊቷ ልጅ እጅ በቡሉት መርዝ ነው የሞቱት?? ሲሆን መልሱ "#አዎ" ይሆናል።

ማስረጃዎቻችን፦

1. ነብዩ እራሳቸው በሞቱበት እለት ለስቃያቸውና ለ ሞታቸው ምክኒያት የሆነው በ ኸይባር ከዚህች አይሁዳዊት ልጅ እጅ የበሉት መርዝ እንደሆነ መናገራቸው።

ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅጽ 5፣ መፅሓፍ 59፣ ሓዲዝ 713
Narrated 'Aisha: The Prophet in his ailment in which he died, used to say, "O 'Aisha! I still feel the pain caused by the food i ate at Khaibar,and at this time, I feel as if my Aorta is being cut off FROM THAT POISON"
አይሻ ዘግባለች፦ ነብዩ ታመው በሞቱበት እለት እንዲህ እያሉ ይናገሩ ነበር፤ "ኦ አይሻ! እስከዛሬ ቀን ድረስ በ ኽይበር ከበላሁት ምግብ የሚሰማኝ የሕመም ስሜት አለኝ፤ ከበላሁትም መርዝ አሁን ትልቁ የልብ የደም ቱቦዬ (AORTA) እየተቆረጠ እንዳለ አይነት ስሜት ይሰማኛል..." አሉ።

2. ነብዩ የሞቱት ከተመረዙ ከ 3 አመት በኊላ ነው። ታድያስ 3 አመት ቆይቶ የሚገድል መርዝ አለ???
መልሱ በሚገርም ሁኔታ #አዎ ነው። ተከታተሉኝ!!!

ኦርጋኖፎስፌት (Organophosphates) ይባላሉ። ምንነታቸውንና የሚያመጡትን ውጤት (effect) ከነብዩ አሟሟት ሁኔታ ጋራ እያነፃፀርኩ አቀርብላቹሃለው።

ኦርጋኖፎስፌቶች ምንድናቸው??ስራቸውስ እንዴት ነው??
----------------------------------------------------------

ኦርጋኖፎስፌቶች ከ ካርቦንና ከ ፎስፈረስ የተሰሩ ኬሚካሎች ሲሆኑ "acetylcholinestrase" (አሴታይልኮሊን ኢስትሬስ) የተባሉ ኤንዛይሞችን በመጣበቅ ስራቸውን በትክክል እንዳይሰሩ ያደርጋል። እነኚህ ኤንዛይሞች በተፈጥሮያቸው፣ ሌላ"አሴታይልኮሊን" (acetylcholine) የሚባል በነርቮች መካከልና በነርቭ እና በ ጡንጫዎች ሴል መኻከል   (synapse, and neuro-muscular junction) የሚገኙትን መቆጣጠር ሲሆን በ ኦርጋኖፎስፌቶች ሲጠቁ ግን ይሄንን መስራት ያቅታቸወል። በ ሰውነት ላይ የሚያመጡትም ችግሮች በ ጊዜ አንፃር ለሶስት ይከፈላሉ።

1. Acute Toxicity( በ ቅጽበት( ጊዜ ሳይፈጅ)የሚያደርሱት ችግር)
 አንድ ሰው ተለቅ ያለ የ ኦርጋኖፎስፌት ዶዝ ቢወስድ የሚከተሉ ምልክቶችን ያሳያል።
ሀ. ሙስካሪንክ ምልክቶች፦ ማንባት፣ሽንት አለመቆጣጠር፣ማስታወክ፣ትንፋሽ ማጠር..ወዘተ

ለ. ኒኮቲንክ ምልክቶች፦የ ጡንቻዎች መዳከም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ እራስን መሳት
ልብ በል፤አንድ ሰው ከ ሁለቱ ምልክቶች አንዱን ብቻ ማሳየት ይችላል

አሁን፣ ነብዩ ሙሓመድ ሲመረዙ ከሳቸው ጋራ የተመረዘ ሰው ነበር። ሰውዬውም ይህንን የ ኒኮቲንክ ምልክቶችን አሳይቶ ሞቷል።

ኢብን ሳዓድ ገጽ 252-253፦ ነብዩ ከተመረዘው ስጋ ትንሽ (piece) ወሰዱ።  "ቢሽር ኢብኑ አል ባራ" የሚባልም የ ነብዩ ተከታይ ይሄን አይቶ ምግቡን ምብላቱን ቀጠለ። ነብዩ ቁራሿን ሲበሉ እሱ መብላቱን ቀጠለበት። #ሌሎችም በሉ።ከዛ ነብዩ እንዲህ ብለው ጮሁ፤ "እጃቹን ሰብስቡ፤ይህ የበጉ ታፋ እንደተመረዘ ነግሮኛልና።" ቢሽርም እንዲህ አለ፤ "እርሶን ባከበረው በ አላህ ስም እምላለው፣ ምግቡ እንደተመረዘ ልክ የራሴን ስውስድ ነው ያወቅኩት፤ነገር ግን ይ እርሶን(ነብዩ) ማዕድ አላበላሽም ብዬ መብላቴን ቀጠልኩ።...ቢሽርም ከቦታው #መነሳት #አልቻለም ቀለሙም መቀየር ጀመረ"

i. ቢሽር መነሳት ለምን አልቻለም?? የ ጡንቻው መድከም( ኒኮትኒክ ኢፌክት)
ii.ለምንስ ቀለሙ ተቀየረ? ትንፋሽ እጥረት( respiratory failure) ፣ ልብ በሉ አንድ ሰው ወደ ሠውነት ክፍሉ በቂ ኦክሲጂን ካልሔደ "cyanosis" "የ ሰውነት ወደ ሰማያዊ መቀየር ባህሪ ያሳያል።  ኒኮትኒክ ምልክት።
iii. ነብዩስ ለምን እንደ ብሽር ቶሎ አልሞቱም፦ ምክኒያቱም ቢሽር የወሰደው ዶዝ ከ ነብዩ በላይ ነው። ልብ በሉ ነብዩ የወሰዱት አንድ ቁራጭ ብቻ ነው። በተጨማሪም ሌሎችም ሰዎች ከነሱ ጋር የበሉ ነበሩ። ግን "እነሱም ሞቱ" የሚል የለም። ስለዚህ የነብዩ መኖር ተኣምር አይደለም።

2. intermediate effect

ቀጥለህ አንብብ...
3. ከ ሳምንታት እስከ አመታት በኋላ የሚመጡ ችግሮች። Long term Effect
የረጅም ጊዜ ውጤቶቹ ብዙ ቢሆኑም አሁን የምናየው አንዱን ብቻ ነው።
በ ኦርጋኖፎስፌት የሆነ ጊዜ ላይ  ተመርዞው ግን በ ሕይዎት የቆዩ ሰዎች ከ #ሶስት እስከ #አምስት አመት ጊዜ በሚሆኑ ጊዜ ውስጥ "ኮሮነሪ አርቴሪያል ዲዚዝ"(Coronary artery disease) ማለትም "የ ልብ ደም ስሮች በሽታ"  በ ተሰኙ በሽታዎች የመያዝ እደሉ እጅጉን ከፍ ያለ እንደሆነ የማያከራክር የ ጥናት ውጤት ነው። ይሄም "Long term effect of organophosphate poisoning" ይባላል።

ማስረጃ፦ Dong-Zong Hung, Hao-Jan Yang,  and Sally C. W. Tai; The long term effect of organophosphate poisoning as a risk factor of CVD;(ሙሉ ሶይቴሽን ግርጌ ይመልከቱ

ከነኚህ በሽታዎች ዋናው " ማዮካርዲያል ኢንፍራክሽን" (mayocardial infraction) ይባላል። ምልክቶቹም ቀጥሎ ያሉት ይሆናል።
1.በ ልባችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ሕመም። ሕመምተኞቹ ሲገልፁት ልክ በ ቢላ ልቡ ላይ እንደተወጋ ሰው ወይም ልቡ ተጨምድዶ እንደተያዘ ሰው ይሰማቸዋል
2. አንዳንዴ ሕመሙ ወደ ትክሻ ወደ እጅም ይሔዳል..ወዘተ

ነብዩ ሙሓመድ ይህንን የሚመስል ምልክት አሳይቷልን?? ቅድም ካነበብነው ሓዲዝ እንዲህ ብሏል፦
"..ኦ አይሻ! እስከዛሬ ቀን ድረስ በ ኽይበር ከበላሁት ምግብ የሚሰማኝ የሕመም ስሜት አለኝ፤ ከበላሁትም መርዝ አሁን ትልቁ #የልብ #የደም #ቱቦዬ (AORTA) #እየተቆረጠ እንዳለ አይነት ስሜት ይሰማኛል!!"

ልብ በሉ፣ ነብዩ ልባቸው ላይ የተሰማቸውን ሕመም ልክ ከተመረዘ ከ አመታት በኋላ በ ኮሮነሪ አርቴሪያል ድዚዝ እንደተጠቃ ሰው አገላለፅ ገልጿል።

መደምደሚያ

1. የ ቢሽር አሟሟት የ ኦርጋኖፎስፌት የ ቅጽበት ምልክቶችን ይገልፃል
2. የ ነብዩ አሟሟት የ ኦርጋኖፎስፌት የረጅም ጊዜ ውጤት ምልክቶችን ይገልፃል
3. ስለዚህ ነብዩ (most likely) ከ ኦርጋኖፎስፌት ሞቷል

ስለዚህ "እንዴት ሰው ተመርዞ ከዛው መርዝ ከ 3 አመታት በኋላ ሊሞት ይችላል??" ለምትሉ ሙስሊም ምስኪኖች በቂ መልስ ነው። አከተመ!!!

ዋቢ መጻሕፍት፤

1.Stapczynski, J. S., & Tintinalli, J. E. (2016). Tintinalli's emergency medicine: A comprehensive study guide (8th ed.). New York, N.Y.: McGraw-Hill Education LLC. PP 1318-1326

2. UpToDate 21.2

3. Hung D-Z, Yang H-J, Li Y-F, Lin C-L, Chang S-Y, Sung F-C, et al. (2015) The Long-Term Effects of Organophosphates Poisoning as a Risk Factor of CVDs: A Nationwide Population-Based Cohort Study. PLoS ONE 10(9): e0137632. doi:10.1371/journal. pone.0137632

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
👉አድርጎ የሚያሳየኝ ሙስሊም ካለ👈

ስለ መርዝ
ሙስሊሞች ልክ ሰይጣን እየሱስን ከ ከፍታ ቦታ ላይ እራሱን  እንዲወረውር በ ፈተና መልክ ጥያቄ እንዳቀረበለት እኛ ክርስቲያኖችን ቀጥለን በምናነበው የ መፅሓፍ ቅዱስ ክፍል ጥያቄ ያቀርቡልናል።

" የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።"
(የማርቆስ ወንጌል 16:18)

ጥያቄውም፣ "እውነት ይሄ የ አምላክ ቃል ከሆነ መርዝ ላምጣልህና እንደማይገድልህ ታሳየኛለህ። ይሄ ቃል ነብያችን ያስተማሩት ትምህርት ቢሆን እኔ ያለ ምንም ጥርጥር መርዙን ጭልጥ አድርጌ እጠጣለሁ!! አንተ ብቻ ከ ቁርዓን ወይም ከ ሳሂህ ሓዲዝ አምጣልኝ" የሚል ነው።

ለዚህ ጥያቄ መልስ የምሰጠው ቀጥዬ በምለጥፋቸው ፅሁፎች ሲሆን አሁን ግን፦ * ይሄ ቃል ነብያችን ያስተማሩት ትምህርት ቢሆን እኔ ያለ ምንም ጥርጥር መርዙን ጭልጥ አድርጌ እጠጣለሁ!! አንተ ብቻ ከ ቁርዓን ወይም ከ ሳሂህ ሓዲዝ አምጣልኝ*   ለሚሉ ሙስሊሞች፣ "Challenge accepted" እያልኩ፤ ይሄው አመጣሁላቹ እላለው።

ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅጽ 7 መፅሓፍ 65 ሓዲዝ 356

ሳዓድ ዘግቦታል፦
የ አላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፤ "ጠዋት ጠዋት 7  "የ ቴምር ፍሬ" የሚበላ ማንኛውም ሰው ፍሬውን በበላበት ቀን ላይ ምንም አይነት *መርዝ* "سم" ወይም  አሥማት ሊጎዳው አይችልም!!"
"...he will not be affected by poison or magic"

እኔ ፍቃደኛ ለሆነ ሙስሊም ቴምር አዘጋጅለታለሁ። ከዛ ምሳ ሰዓት ላይ መርዝ እሰጠዋለው። እስኪ እውነት እንደሚፎክሩት መርዙን እጠጣለው የሚል ካለ በውስጥ መስመር ያግኘኝ።😂
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
📌አምላክ እንዴት አምላክ ይኖረዋል?📌

ሙሓመዳውያን ስለ እየሱስ አምላክነት ሲጠይቁን ውሃ ከማይቋጥሩ ሙግታቸው መካከል አንዱ "እየሱስ እራሱ እግዚያብሔር አብን አምላኬ ብሏል፤ታድያ እናንተ እየሱስን አምላክ የምትሉት ከዬት አምጥታችሁት ነው?? አምላክስ አምላክ ሊኖረው ይችላልን??" የሚል ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ እኛ እግዚያብሔር አብ የ እየሱስ አምላክ ("የሰውነት ማንነቱ") መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን።  እየሱስም ወደ ምድር ሲመጣ በ አምላክነት ማንነቱ የ ሰውነት ማንነተ ስለተዋሃደ  ጠቅልለን "የ እየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ" እንላለን።

ሙግት አንድ

እየሱስ መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚያብሔር አብን "አምላኬ" ብሎ ጠርቶታል (ማቴዎስ 27:46)፤ ጳውሎስም "የእየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ" ብሏል።
" በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:3)። እየሱስ ካረገ በኋላም "አምላኬ" ብሏል። (ራእይ 3:2)


ታድያ እየሱስ አማላክ ከሆነ እንዴት አምላክ ይኖረዋል??

" እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ  "יְהוָ֔ה" እግዚአብሔር "אֱלֹהֵ֖י" ነኝ"(ትንቢተ ኤርምያስ 32:27)
"27 Behold, I [am] the LORD ""  , the God of all flesh: is there any thing too hard for me?"
(Jeremiah 32:27)

በዚህ በክፍል ላይ እግዚአብሔር ያህዌ #የስጋ #ለባሽ ሁሉ አምላክ እንደሆነ ግልፅ ነው። እየሱስ ደግሞ ወደ ምድር ሲመጣ ስጋን ለብሷል። ልበ በል "ማንነቱን (essence) ቀየረ" ሳይሆን፤ ሌላ ማንነትን (ሰውነትን) ጨመረ ማለት ነው። ስለዚህ እየሱስ ሁለት ማንነት በ አንድ አካል (one person) ሆኖ ተገልጧል ማለት ነው። ስለዚህ እየሱስን በ አረፍተ ነገር ውስጥ ስናመለክት ሁለቱ ማንነቶች የተለያዩ ቢሆኑም ለይተን አንጠራም ማለት ነው። ስለዚህ እየሱስ የሰውነት ማንነት(human nature) ስላለው፣ በ ኤርሚያስ 32:27 መሰረት፣ ስጋ ያልለበሰውን እግዚያብሔር አብን "አምላኬ" ብሎ መጥራት ነበረበት። ስለዚህ እየሱስ እግዚያብሔር አብን አምላኬ ስላለ እየሱስ አምላክ አይደለም ማለት አይደለም። ምክኒያቱም በአምላክነት ማነቱ ለዘለአለም ከ አብ ገር " አንድ ማንነት (one being)" ኖሮት ይኖር ስለነበረ። 

" #አሁንም፥ አባት ሆይ፥ #ዓለም #ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ #በነበረኝ #ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።"(የዮሐንስ ወንጌል 17:5)፤  

(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
1፤ በመጀመሪያው ቃል ነበረ( En arche(ልብ በል "ኤጌኔቶ" አይልም) en o logos)፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

2፤ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።

(የዚህን ክፍል ጥልቅ ማብራሪያ በ ግሪክ ሰዋስውና ፊሎሶፊ በቅርብ ቀን እናያለን።)

ስለዚህ እየሱስ እግዚያብሔር አብን "አምላኬ" ብሎ እንዲጠራው ያደረገው የሰውነት ባህሪይ ነው እንጂ ፍጡር ስለሆነ #አይደለም

ሙግት ሁለት፦ ካረገ በኋላስ??

እየሱስ ካረገ በኋላም በሁለቱ ማንነቶቹ ይኖራል። ሲጀመር የትንሳኤ ሃሳብ እራሱ የስጋ ማንነትን "pre suppose"  ያደረገ ነው።(ሉቃስ 24:39)
ለዚያም ነው ጳውሎስ ሲናገር "አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤"(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:5) ብሎ የሰውነት ማንነቱን ብቻ የ ገለፀው። የ እየሱስ ክርስቶስ መካከለኛነት በ ስጋዊ ባህሪው (በመሞት) የተፈፀመ ስለሆን "ሰው የሆነው" ብሎም ተናግሯል። ልብ በሉ "ሰው ብቻ" አላለም። ከሁለቱ ማንነቱ አንዱን በ አውዱ (መካከለኛ መሆን) መርጦ ተናግሯል። ጳውሎስም በ ኤፌሶን 1፡3 "የ እየሱስ አባትና አምላክ" ያለው አሁንም እየሱስ በ ሁለት ማንነቱ ስላለ ነው።

ሙግት ሶስት፦ አንተ ብቻ እውነተኛ አምላክ

" እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።"(የዮሐንስ ወንጌል 17:3)
"3 And this is life eternal, that they might know thee the only true God, and Jesus Christ, whom thou hast sent."(John 17:3)

እግዚያብሔር አብ ብቻ እውነተኛ አምላክ ከተባለ እየሱስ እንዴት እምላክ ይሆናል??

መልሱ " ስላሴ ውስጥ ነው። ሎጂኩን ላሳያቹ

1. ስላሴ ብቻ እውነተኛ አምላክ ነው
2 ስላሴ በ አንድ አምለክ ማንነት ( in only one being=God) ሶስት አካል (person) ለዘለአለም በአምላክነት ባህሪያቸው እኩልና አንድ የሆኑ አብ፣ወልድና መንፈስ ቅዱስ አሉ። ስለዚህ እያንዳንዱ የስላሴ አካል በ ነጠላም ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው

መደምደሚያ። አብ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው፤ ወልድ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው። ልብ በል፤ "እውነተኘ አምላክ" አንድ "essence" ነው፤ "አካል" (person) አይደለም። ሶስቱ ደግሞ "አካል ናቸው"።

ስለዚህ በ ስላሴ አውድ "አብ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው" ማለት ወልድ #አይደለም ማለት አይደለም።

ይቀጥላል...
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
1👍1
Forwarded from ለምን አልሰለምኩም? (Naol Jigy)
 በ አላህ ስሞች ዙሪያ "ሙግት"

የ እስልምና መፅሓፍቶች፣ አላህ 99 ስሞች እንዳለው ይነግሩናል።

Bukhari Vol. 3, Book 50, Hadith 894
Narrated Abu Huraira:

Allah's Messenger (ﷺ) said, "Allah has ninety-nine names, i.e. one-hundred minus one, and whoever knows them will go to Paradise."
አቡ ሁረይራ የዘገበው ሓዲዝ ነው፦ የ አላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፣ " አላህ 99 *ስሞች* አሉት ፤ መቶ ሲቀነስ አንድ። ሁሉንም የሚያውቅ ሰው ወደ ገነት ይግባል።

በ Sahih Muslim – Book 35 Hadith 6476 ላይ፤ ከላይ ባነበብነው ሓዲዝ ላይ ጨምሮ እንዲህ ይላል። " አላህ የሚታወቀው በ ጎዶሎ ቁጥር (odd number) ስለሆነ (አንድ ስለሆነ) ጎዶሎ ቁጥርን ይወዳል።"

ጥያቄያችን፦
 1.በ 99ኙ የ አላህ ስሞች ውስጥ "አላህ" የሚልው አልተካተተም። ስለዚህ " አላህ" ከተጨመረበት 99 ሳይሆን 100 ይሆናል። ስለዚህ ከላይ "አላህ 99 ስም አለው" " አላህ የሚወደው ጐዶሉ ቁጥርን ነው" የሚሉ ሓዲዞች ውድቅ ሆኑ ማለት ነው።

2. አይ! "አላህ" የሚለውን አይጨምርም ካላቹ ፣ታዲያ "አላህ"  የሚለው 'ስም' ካልሆነ ምንድን ነው??

3.  አይደለም! 99ኙ ስሞች ለ ፍጡርም ያገለግላሉ፤ ስለዚህ መግለጫ ብቻ ናቸው ('አላህ' ከሚለው ስም ይለያሉ)ካላቹ ደግሞ፣ በ ምሳሌ ብንወስድ ከ 99ኙ ስሞች አንዱ  الْخَالِقُ "አል ኻሊቅ" "ፈጣሪ"  የሚል እንውሰድ። ስለዚህ ፍጡር ሆኖ ፈጣሪ አለ ልትሉን ነው??

4.አይ! ለ ፍጡር አንጠቀማቸውም፣ ካላቹ፤፦ እየሱስ ከ 99ኙ የ አላህ ስሞች በ ብዙ እራሱን ጠርቷል። ስለዚህ እየሱስ ፍጡር ነው ብላቹ የምትሟገቱት ሙግት ውድቅ ይሆናል ማለት ነው። ለምሳሌ፤ ከ 99ኙ የ አላህ ስሞች፦
A. "አል አዋሉ" እና "አል አኺሩ" "የ መጀመሪያ፣ የ መጨረሻ" الأوَّلُ እና الآخِرُ "the beginning and the end" አሉ። ቁርአንም እንዲህ ይላል * ሱራ 57:3

እርሱ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ፣ ግልፅም ስውርም ነው፤ እርሱም ነገርን ሁሉ ዐዋቂ ነው።
He is #the #First and #the #Last, the Ascendant and the Intimate, and He is, of all things, Knowing.

እየሱስም እንዲህ ብሏል

(የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 1)
----------
17፤ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ። አትፍራ፤ #ፊተኛውና #መጨረሻው #ሕያውም እኔ ነኝ፥

18፤ #ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።

B. An-noor النُّورُ The light ሌላ የ አላህ ስም ነው
 
እየሱስም በ ዮሓኒስ 14:6 " ..እኔ ብርሃን ነኝ" " The light"። ልብ በሉ "Al-' ወይም " The" የሚለው definite article ለ አላህም ለ እየሱስም ተጠቅሟል። ይሄ ደግሞ ዝም ብሎ ለተራ ሰው የምንጠቀምው ሳይሆን "ልዩ" መሆናቸውን የሚገልፅ ነው።

C. الباعث አል-ባእዝ "ትንሳኤ" "The resurrection" ወይም "The Resurrector" ወይም  "አዲስ ሕይወት ሰጪ"
እየሱስም በዚህ ስም ተጠርቷል፦

" ኢየሱስም። #ትንሣኤና #ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤"
(የዮሐንስ ወንጌል 11:25)

" ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን #አስነሣዋለሁ።"...The Resurrector!!
(የዮሐንስ ወንጌል 6:54)

ስለዚህ "የ አላህ ስሞች ለ ፍጡር አንጠቀምም" በሚለው ሙግት ከሄድን እየሱስ በ አላህ ስም ስለተጠራ #እየሱስ ፍጡር ሳይሆን #ፈጣሪ ነው ማለት ነው።


 "እየሱስ ዬት ጋር ነው 'እኔ አምላክ ነኝ' ያለው??" ለምትሉ ሙስሊሞች መልሱ ከላይ እንዳነበባችሁት ነው እንላለን!!
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
1
ግራንቪል ሻርፕ በ ቲቶ 2:13

የ ሙሓመዳውያን ኡሥታዞች ከ ስላሴ ትምህርት ተቃዋሚያን ፅሁፍ በሚቃርሙት የተሳሳተ መረጃና እጅጉን አሳፋሪ በሆነ አለመረዳትና አለማወቅ የክርስቶስን አምላክነት ለመቃወም በ ፅሁፎቻቸው እራሳችውን ማዋረድና ማውረድ ከጀመሩ ሰንብቷል። ከነኚህ ትችህቶች ውስጥ ዛሬ የምናየው ቲቶ 2:13 ላይ የተነሱትን ይሆናል።

" ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም #የታላቁን #የአምላካችንንና #የመድኃኒታችንን #የኢየሱስ #ክርስቶስን ክብር #መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤"
(ወደ ቲቶ 2:12-13)
προσδεχόμενοι τὴν μακαρίαν ἐλπίδα καὶ ἐπιφάνειαν τῆς δόξης τοῦ μεγάλου #θεοῦ καὶ #σωτῆρος ἡμῶν #Χριστοῦ #Ἰησοῦ,

while we wait for the blessed hope—the appearing of the glory of our great #God and #Savior, #Jesus Christ ( tou megaluo #Theou kai #Soteros hemon Christou 'Iesou)

ከላይ እንዳነበባችሁት ክፍሉ እየሱስን # θεοῦ God ወይም #እግዚያብሔር ብሎ እየጠራ እንደሆነ ግልፅ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ከንቱ ተቺዎች "θεοῦ" የሚለው ለ እየሱስ ሳይሆን #ለአብ ነው ብሎ ሙግት አቅርቧል። ሙግቱም አንድ የ ግሪክ ቋንቋ ምሁር (Scholar)፣ ስሙም "ግራንቪል ሻርፕ" የተባለ ሰው ባስቀመጠው የ ሰዋሰው ሕግ ላይ የተመሰረተ ነው። ይሁን እንጂ ይህንን ሙግት ያቀረበው 'ተቺ'፥ ሕጉንና ቲቶ 2:13'ን  አንድ ላይ ቢያጠና ኖሮ፣ ክፍሉ እንዲያውም የ ክርስቶስን አምላክነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ስለሚረዳ አፉን ይዞ ቁጭ ይል ነበር። የሚገርመው ግራምቪል እራሱ ሕጉን ተጠቅሞ ቲቶ 2:13 እየሱስ አምላክ መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ፅፏል።

1ኛው የ ግራንቪል ሕግ ምን ይላል??

“When the copulative kai connects two nouns of the same case, [viz. nouns (either substantive or adjective, or participles) of personal description, respecting office, dignity, affinity, or connexion, and attributes, properties, or qualities, good or ill], if the article ho, or any of its cases, precedes the first of the said nouns or participles, and is not repeated before the second noun or participle, the latter always relates to the same person that is expressed or described by the first noun or participle”

καὶ(kai, 'እና') የተሰኘች መስተፃምር ሁለት ተመሳሳይ ሙያ ያላቸውን ስሞች ለማያያዝ ስትገባና ከመጀመሪያው ስም በፊት ho ወይም τοῦ ("The") የሚለው definite article ከገባ  ግን ሁለተኛው ስም(noun) በፊት ሳይገባ ከቀረ እነኚህ ሁለቱ ስሞች የሚናገሩት(የሚገልፁት) ስለ አንድ ሰው ነው።
(Remarks on the Uses of the Definitive Article, 3)
(ይህንን ካላሟላ ግን ሁለት የተለያዩ አካላትን ለመግለፅ ነው የሚለው ሙግት ከዚህ የመጣ ነው፤ሁል ግዜ ትክክል ባይሆንም)

ይሁን እንጂ ይሄ ሕግ ከላይ የተገለፀውን የ አርፍተ ነገር አወቃቀር ለሚያሟሉ  ሁሉ ይሰራል ማለት #አይደለም። ሕጉ የሚሰራው ቀጥለን ይምንዘረዝራቸውን ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟሉ #ብቻ ነው።

1. ስሞቹ ሕልውና ላላቸው (ለሰው, ለ አምላክ) ብቸ የተጠቀሙ መሆን አለባቸው (they must refer to a person;not a thing)

2. የተፀውኦ ስም (Proper name) መሆን #የለባቸውም

3. ተመሳሳይ ሙያ መሆን አለባቸው (The same case)

4. ነጠላ መሆን አለባቸው (singular in number)

ዋቢ መፅሓፍት

ሀ. A Reexamination of the Granville Sharp rule by Daniel B.Wallace, Ph.D. Associate professor of New Testament Studies;

ለ. Wallace, Greek Grammar, 280-290

ሐ. Robertson, Grammar, 785-90

ስለዚህ በዚህ ሕግ መሰረት ቲቶ 2:13 "እየሱስ አምላክ ነው" ይላል?? መልሱን የምንሰጠው ክፍሉ የ ግራንቪልን ሕግ ሙሉ ለሙሉ ማሟላቱን ነጥብ በ ነጥብ እያየን ይሆናል።

1. 'tou' 'The' የሚለውን definite article የተጠቀመው በ መጀመሪየ ስም ላይ ብቻ ነውን?
መልስ- #አዎ
#tou megaluo #Theou kai #Soteros hemon Christou 'Iesou (ቲቶ 2:13)
θεοῦ(Theou, አምላክ, God) የሚለው የመጀመሪያ ስም ሲሆን σωτῆρος(Soteros, አዳኝ ወይም መድሃኒት, saviour) ሁለተኛ ስም ነው። tou' የሚለው የገባው በ θεοῦ ፊትለፊት ብቻ ነው።

2. ስሞቹ የተጠቀሙት(Theou እና Soteros) "ህልውና ላለው( personal) ነውን??
መልስ፦አዎ። ምክንኒያቱም ሁለቱም እየሱስን ለመግለፅ ነው የገቡት።
"..የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን #የኢየሱስ #ክርስቶስን.."

3. θεοῦ እና σωτῆρος ሁለቱም የተፀውኦ ስም (Proper name) #አይደሉም። ስለዚህ አሁንም ክፍሉ 2ኛውን  ቅድመ ሁኔታ ያሟላል ማለት ነው።

4. θεοῦ እና σωτῆρος ተመሳሳይ ሙያ ናቸውንህ??

θεοῦ=Noun #Genetive masculine singular
σωτῆρος=Noun #Genetive masculine Singular
ስለዚህ መልሱ "አዎ! ሁለቱም ተመሳሳይ ሙያ ናቸው።"

5. θεοῦ እና σωτῆρος ሁለቱም #ነጠላ (singular) ናቸው። ስለዚህ የመጨረሻውንም ቅድመ ሁኔታ ያሟላል።

ስለዚህ፤ ቲቶ 2:13 ሁሉንም የ ግራንቪል የ ሰዋሰው ሕግ ያሟላል። ማለትም θεοῦ እና σωτῆρος ( God and saviour, አምላካችንና መድሓኒታችን) ብሎ የተቀመጠው ሁለቱም #እየሱስን ለመግለፅ ነው ማለት ነው። ስለዚህ እየሱስ 'አምላክ" እና "መድሃኒት" ነው ማለት ነው።

ሙስሊሙ 'ተቺ"ይህንን ክፍል ለማክሸፍ የተጠቀማቸው ጥቅሶች ሁለት ናቸው።

1. ማቴ 21:12 ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ *የሚሸጡትን* እና *የሚገዙትን* ሁሉ አወጣ። "እነኚህ ሁለቱ ስሞች የተለያዩ ሰዎችን ይገልፃሉ" ብሎ ፅፏል።

ይሄ ክፍል በ አረፍተ ነገር አወቃቀሩ ቲቶ 2:13ን ቢመስልም (τοὺς πωλοῦντας καὶ ἀγοράζοντας*Those selling and buying) ግን ቅድመሁኔታዎችን ስለማያሟላ ውድቅ ነው። ምክኒያቱም "የሚሸጡትን* እና *የሚገዙትን" የሚሉ ሁለቱም ቃላት #ነጠላ አይደሉም።የ ግራምቪልን ሕግ አያሟሉም። ስለዚህ ክፍሉን እንደማስረጃ ማቅረብ በራሱ አሳፋሪ ነው።

2. ኤፌሶን 2:20 *በሐዋርያት* እና *በነቢያት* መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥

አሁንም በዚህ ክፍል "በሐዋርያት* እና *በነቢያት"  የተባሉት ሁለቱም ብዛትን የሚያሳዩ እንጂ ነጠላ አይደሉም። ስለዚህ አሁንም ማስረጃው የ ግራንቪልን ሕግ ስለማያሟላ  ውድቅ ይሆናል
@Jesuscrucified
ግራንቪል ሻርፕ፦የዮሓኒስ ወንጌል 20:28

ሙሓመዳውያን መፅሓፍ ቅዱስ ውስጥ ተፅፎ የክርስቶስን አምላክነት በ ግልፅ የሚያሳዩ ጥቅሶችን ከራሳቸው ሳይሆን ከ ስላሴ ተቃዋሚያን፣ ግን ክርስቲያን ነን ባዮች በሚሰበስቡት የወረደና በ ብዙ ምሁራን የፈረሰ ሙግት ይዞ እንደ አዲስ መቅረባቸውን ቀጥሏል። ዮሓኒስ 20:28 ከ ጥቅሶቹ መካከል አንዱ ነው።


(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 20)
----------
27፤ ከዚያም በኋላ ቶማስን። ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።

28፤ ቶማስም። #ጌታዬ #አምላኬም ብሎ መለሰለት።

29፤ ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።

ἀπεκρίθη Θωμᾶς καὶ εἶπεν #αὐτῷ#κύριός μου καὶ ὁ #θεός μου.( ho Kyrios mou kai ho Theos mou)

"28 And Thomas answered and said unto #him, The #Lord of me and The #God of me."
(John 20:28)

ከላይ ያነበብነውን ፅሁፍ በ አጭሩ ስንገልፅ
1. ቶማስ እየሱስን ጌታዬ እና #አምላኬ(θεός) ብሎ ጠራው
2. እየሱስም ቶማስ ለሱ የሰጠውን ስም (ጌታና #አምላክ) ተቀበለ፦ (…ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው)

3. ስለዚህ እየሱስ #አምላክ ነው ማለት ነው።

ይሁን እንጂ ሙሓመዳውያን ይህንን ክፍል ለማፍረስ አሁንም ልክ ቲቶ 2:13 ላይ እንዳነሱት ግራንቪል ሻርፕ ባስቀመጠው ሕግ ይሟገታሉ።  የሚያሳዝነው ግን የ ግራንቪል ሻርፕ ሕጎችን እንኳን ማወቅ ይቅርና ክፍሉን ራሱ እንደላጠኑ ያሳውቅባቸዋል።

የ ሻርፕ ስድስተኛው ሕግ

የ ግሪክ ቋንቋ ስኮላር ግራንቪል ሻርፕ እራሱ በ 1798 "The"( ὁ) የተሰኘች definite article አጠቃቀም ዙሪያ ላይ ባሳተመው መፅሓፍ ውስጥ ስድስተኛው ሕግ ላይ ቀጥሎ ያለውን ሕግ ፅፏል።

"ሁለት ተመሳሳይ ሙያ (same case) ያላቸው ስሞች
 καὶ (እና) በሚለው መስተፃምር ተያይዞ ግን በ ሁለቱም ስሞች ፊትለፊት 'ὁ' 'The' ከገባ፣ ሁለቱ ስሞች ሁለት የተለያዩ አካላትን ይገልፃሉ።... ነገር ግን ሕጉን የሚገድቡ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ።

1. የ አረፍተ ነገሩ አውድ
2. ከ አረፍተ ነገሩ ፊትለፊት ሁለቱም ስሞች ለ አንድ አካል መሆኑን የሚያሳይ ገላጭ ካለ (e.g. pronoun) ሁለቱም ስሞች ለ አንድ አካል( person) መሆኑን ያሳያል።

ምሳሌ፦  ራእይ 1:8

" ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ። አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።"
"Ἐγώ εἰμι #τὸ Ἄλφα καὶ #τὸ Ὦ,.."
I am #The Alpha and #The Omega

በዚህ ምሳሌ ላይ 'አልፋ' ፊትለፊት እንዲውም ደግሞ 'ኦሜጋ' ፊትለፊት "THE" የሚለው አርቲክል ገብቷል። ነገር ግን ሁለቱም "እየሱስን" ለመግለፅ እንጂ 'አልፋ' እየሱስን ገልፆ 'ኦሜጋ' ደግሞ አብን ለመግለፅ አልገባም። ምክኒያቱም፦
1. Ἐγώ (እኔ፣ I) የሚለው personal/possessive pronoun Nominative ሲሆን ሁለቱ ስሞች (አልፋና ኦሜጋ) አንድን አካል (እየሱስን) እንደሚገልፁ ያሳያል።
2. አውዱም (context) እየሱስ እረሱን፣ማንነቱን ለመግለፅ የተጠቀመበት እንደሆነ ግልፅ ነው።

በተመሳሳይ ሙግት የዮሓኒስ ወንጌል 20:28ን እንመልከት

#αὐτῷ#κύριός μου καὶ ὁ #θεός μου

"28 And Thomas answered and said unto #him, The #Lord of me and The #God of me."

በዚህ ክፍል በ ሁለቱም ስሞች ፊትለፊት  (κύριός(ጌታ) እና (θεός) ) ' Ὁ' "The" ገብታለች። ስለዚህ እውነት ሙስሊሞቹ እንደሚሉት "ጌታ" የሚለው ለ እየሱስ ሲሆን " አምላክ" የሚለው ደግሞ ለ አብ ነውን??

በ እርግጥ ይህንን ሙግት የሚያቀርበው ከንቱ ተቺ፣ወይ የ ሕጉን ቅድመ ሆኔታዎች ባለየ አልፎታል ወይም ሕጉን አላጠናም።

መልሱ 'በ ፍፁም አይደለም' ነው። ግራምቪል እራሱ በ መፅሓፉ ገጽ 14-16 ላይ የዮሓኒስ 20:28ን ሰዋ ሰው ሲያብራራ ሁለቱም ስሞች((κύριός(ጌታ) እና (θεός) ) ለ አንድ person እሱም #ለእየሱስ እንደሆነ ማስረጃ አቅርቧል።

1. αὐτῷ( said unto #him; 'አለው') የሚለው personal/possessive pronoun dative ሲሆን፣ ሁለቱም ስሞች (ጌታ እና አምላክ)የሚገልፁት አንድን person እሱም #እየሱስን እንደሆነ ያሳያል። ልብ በል " dative case(ሙያ)" መሆኑ አረፍተ ነገሩ ላይ ችግር አያመጣም።ምክኒያቱም ሕጉ ተመሳሳይ ሙያ እንዲሆኑ የጠየቀው ለ ስሞቹ( nouns) እንጂ ለ pronoun አይደለም።

2. የ ክፍሉ አውድ የሚነግረን ቶማስ ለ እየሱስ ለራሱ ይህንን ንግግር እያደረሰ ስለሆነ ሁለቱም ስሞች እየሱስን የሚገልፁ ናቸው።

ልብ በሉ፤ ይህ ደካማ ተቺ፣ ሙግቱን ያቀረበው ግራንቪል ሻርፕን ምንጭ (reference) አድርጎ ነው። ግን ሒደን ግራንቪል እራሱ በዚህ ክፍል ላይ (ዮሓኒስ 20:28) የሰጠውን ማብራሪያ ስናነብ " ክፍሉ እየሱስን" "አምላክ" እንደሚል ተብራርቶ እናገኛለን።  ለዛም ነው ይህንን ኡስታዝ ነኝ ባይ "ከንቱ" ያልነው።

ግራንቪል በራሱ እጅ የፃፈውን ከታች በፎቶ አያይዝላቹሓለው። አንብቡት!!

እየሱስ ለዘላለም ጌታ ነው!!

" እንግዲህ። በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:24)

Reference

Remarks on The Uses of the Definitive Article  in the Greek text of Of the New Testament, Granville Sharp; page 14-16
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified