ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
📌
"ሁለቱ ማንነቶች"
ልዩ ክፍል
🐐 "ፍየል ወዲ ቅዝምዝም ወድያ!"↔️
"ሁለቱ ማንነቶች!" በሚል ርዕስ ተከታታይ #፬ ክፍሎችን ማድረሴ ይታወሳል። ይኽውም በእስልምና ውስጥ ካሉ ኃጥያቶች ሁሉ የከፋው ማሻረክ ወይም #ማጋራት እንደሆነ እየነገሩን በዛው በእስልምና መዛግብት አላህን ብቻ ሳይሆን ሙሐመድንም ማምለክ እንደሚገባን፤ ተጋሪ አድርጎ ማቅረቡን ነበር ያተትኩት። ይህንንም ለሙሐመድ👳‍♂ መገዛት፣ ሙሐመድን መታዘዝ፣ ሙሐመድን መከተልንና ሙሐመድን መውደድን አንስተን እንደ ማስረጃ ዱያለሁ። ይህችም #ልዩ ክፍል ቃል በገባሁት መሰረት በበለጠ ዳሰሳ🔦🔍 ከመመለሴ በፊት ለማስታወሻም ለማርከሻም😉 ትሆን ዘንድ እንካችሁ ያልኳት ቅንጭብ ናት።📝
"በእውነት ሙሐመድን👳‍♂ መገዛት፣መታዘዝ ፣ መከተልና መውደድ ለሌላውም መልእክተኛ የሚደረግ አይደለም ወይ?"🤔 ባለፈውም እንደከተብኩት "ምኑን ከምኑ አገናኘኽው?" ካላችሁኝ የዘረዘርኳቸው🗞 መሰረታዊ ልዩነቶችን መለስ ብሎ መቃኘት ሙግቱም ያልገባው😴 ደጋግሞ በሰከነ🧐 አእምሮ ማየት መልካም ነው። አልያ "አይ መታዘዝ፣ መገዛት ወዘተ ለሌሎቹም የምንሰጠው ነውና ምን አዲስ ነገር አለ?"🤷‍♂ ብሎ መመለስ ሙግቱ እዚ መልሱ እዚያ፤ ፍየል ወዲ ቅዝምዝም ወድያ ማለት ነው። ይሁንና በመዛግብቱ መሐመድን መታዘዝ፣ መገዛት፣ መከተልም ሆነ መውደድ ከሌላው የሚለይበትን ነጥብ በነጥብ በድጋሚ እነሆ፦
👉 ስለ መታዘዝና ለሙሐመድ ፍርድ ስለ መገዛት ስናወራ ከሌላው እኮ እንደሚለይ 📚ኢቡኑ ካቲር በምዕራፍ 4፡65 ላይ የሰጠውን ማብራራያና የጥቅሱን "መገለጥ" ስናይ አንድም ሙሐመድን #በፍፁምመታዘዝ መታዘዝን አማኝ ለመባል የሚጠይቅ ሁለትም አንድምታው የመሐመድን ፍርድ ያልተስማማውን ሰው በቅፅበት ጭንቅላቱን ያስቀላን አንድምታ እያነበብን እንዴት ነው ከሌላው ጋር አንድ ነው እምንለው ጃል?🤔 አላህስ ይህን አስከትሎ ካልታዘዝክ ዋ! ያለው ለማነው? የቱስ መልዕክተኛ ነው እንዲህ ባለ መገዛት ተገዙት የተባለው ጭንቅላትስ #የተቀላለት?