ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ግራንቪል ሻርፕ በ ቲቶ 2:13

የ ሙሓመዳውያን ኡሥታዞች ከ ስላሴ ትምህርት ተቃዋሚያን ፅሁፍ በሚቃርሙት የተሳሳተ መረጃና እጅጉን አሳፋሪ በሆነ አለመረዳትና አለማወቅ የክርስቶስን አምላክነት ለመቃወም በ ፅሁፎቻቸው እራሳችውን ማዋረድና ማውረድ ከጀመሩ ሰንብቷል። ከነኚህ ትችህቶች ውስጥ ዛሬ የምናየው ቲቶ 2:13 ላይ የተነሱትን ይሆናል።

" ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም #የታላቁን #የአምላካችንንና #የመድኃኒታችንን #የኢየሱስ #ክርስቶስን ክብር #መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤"
(ወደ ቲቶ 2:12-13)
προσδεχόμενοι τὴν μακαρίαν ἐλπίδα καὶ ἐπιφάνειαν τῆς δόξης τοῦ μεγάλου #θεοῦ καὶ #σωτῆρος ἡμῶν #Χριστοῦ #Ἰησοῦ,

while we wait for the blessed hope—the appearing of the glory of our great #God and #Savior, #Jesus Christ ( tou megaluo #Theou kai #Soteros hemon Christou 'Iesou)

ከላይ እንዳነበባችሁት ክፍሉ እየሱስን # θεοῦ God ወይም #እግዚያብሔር ብሎ እየጠራ እንደሆነ ግልፅ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ከንቱ ተቺዎች "θεοῦ" የሚለው ለ እየሱስ ሳይሆን #ለአብ ነው ብሎ ሙግት አቅርቧል። ሙግቱም አንድ የ ግሪክ ቋንቋ ምሁር (Scholar)፣ ስሙም "ግራንቪል ሻርፕ" የተባለ ሰው ባስቀመጠው የ ሰዋሰው ሕግ ላይ የተመሰረተ ነው። ይሁን እንጂ ይህንን ሙግት ያቀረበው 'ተቺ'፥ ሕጉንና ቲቶ 2:13'ን  አንድ ላይ ቢያጠና ኖሮ፣ ክፍሉ እንዲያውም የ ክርስቶስን አምላክነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ስለሚረዳ አፉን ይዞ ቁጭ ይል ነበር። የሚገርመው ግራምቪል እራሱ ሕጉን ተጠቅሞ ቲቶ 2:13 እየሱስ አምላክ መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ፅፏል።

1ኛው የ ግራንቪል ሕግ ምን ይላል??

“When the copulative kai connects two nouns of the same case, [viz. nouns (either substantive or adjective, or participles) of personal description, respecting office, dignity, affinity, or connexion, and attributes, properties, or qualities, good or ill], if the article ho, or any of its cases, precedes the first of the said nouns or participles, and is not repeated before the second noun or participle, the latter always relates to the same person that is expressed or described by the first noun or participle”

καὶ(kai, 'እና') የተሰኘች መስተፃምር ሁለት ተመሳሳይ ሙያ ያላቸውን ስሞች ለማያያዝ ስትገባና ከመጀመሪያው ስም በፊት ho ወይም τοῦ ("The") የሚለው definite article ከገባ  ግን ሁለተኛው ስም(noun) በፊት ሳይገባ ከቀረ እነኚህ ሁለቱ ስሞች የሚናገሩት(የሚገልፁት) ስለ አንድ ሰው ነው።
(Remarks on the Uses of the Definitive Article, 3)
(ይህንን ካላሟላ ግን ሁለት የተለያዩ አካላትን ለመግለፅ ነው የሚለው ሙግት ከዚህ የመጣ ነው፤ሁል ግዜ ትክክል ባይሆንም)

ይሁን እንጂ ይሄ ሕግ ከላይ የተገለፀውን የ አርፍተ ነገር አወቃቀር ለሚያሟሉ  ሁሉ ይሰራል ማለት #አይደለም። ሕጉ የሚሰራው ቀጥለን ይምንዘረዝራቸውን ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟሉ #ብቻ ነው።

1. ስሞቹ ሕልውና ላላቸው (ለሰው, ለ አምላክ) ብቸ የተጠቀሙ መሆን አለባቸው (they must refer to a person;not a thing)

2. የተፀውኦ ስም (Proper name) መሆን #የለባቸውም

3. ተመሳሳይ ሙያ መሆን አለባቸው (The same case)

4. ነጠላ መሆን አለባቸው (singular in number)

ዋቢ መፅሓፍት

ሀ. A Reexamination of the Granville Sharp rule by Daniel B.Wallace, Ph.D. Associate professor of New Testament Studies;

ለ. Wallace, Greek Grammar, 280-290

ሐ. Robertson, Grammar, 785-90

ስለዚህ በዚህ ሕግ መሰረት ቲቶ 2:13 "እየሱስ አምላክ ነው" ይላል?? መልሱን የምንሰጠው ክፍሉ የ ግራንቪልን ሕግ ሙሉ ለሙሉ ማሟላቱን ነጥብ በ ነጥብ እያየን ይሆናል።

1. 'tou' 'The' የሚለውን definite article የተጠቀመው በ መጀመሪየ ስም ላይ ብቻ ነውን?
መልስ- #አዎ
#tou megaluo #Theou kai #Soteros hemon Christou 'Iesou (ቲቶ 2:13)
θεοῦ(Theou, አምላክ, God) የሚለው የመጀመሪያ ስም ሲሆን σωτῆρος(Soteros, አዳኝ ወይም መድሃኒት, saviour) ሁለተኛ ስም ነው። tou' የሚለው የገባው በ θεοῦ ፊትለፊት ብቻ ነው።

2. ስሞቹ የተጠቀሙት(Theou እና Soteros) "ህልውና ላለው( personal) ነውን??
መልስ፦አዎ። ምክንኒያቱም ሁለቱም እየሱስን ለመግለፅ ነው የገቡት።
"..የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን #የኢየሱስ #ክርስቶስን.."

3. θεοῦ እና σωτῆρος ሁለቱም የተፀውኦ ስም (Proper name) #አይደሉም። ስለዚህ አሁንም ክፍሉ 2ኛውን  ቅድመ ሁኔታ ያሟላል ማለት ነው።

4. θεοῦ እና σωτῆρος ተመሳሳይ ሙያ ናቸውንህ??

θεοῦ=Noun #Genetive masculine singular
σωτῆρος=Noun #Genetive masculine Singular
ስለዚህ መልሱ "አዎ! ሁለቱም ተመሳሳይ ሙያ ናቸው።"

5. θεοῦ እና σωτῆρος ሁለቱም #ነጠላ (singular) ናቸው። ስለዚህ የመጨረሻውንም ቅድመ ሁኔታ ያሟላል።

ስለዚህ፤ ቲቶ 2:13 ሁሉንም የ ግራንቪል የ ሰዋሰው ሕግ ያሟላል። ማለትም θεοῦ እና σωτῆρος ( God and saviour, አምላካችንና መድሓኒታችን) ብሎ የተቀመጠው ሁለቱም #እየሱስን ለመግለፅ ነው ማለት ነው። ስለዚህ እየሱስ 'አምላክ" እና "መድሃኒት" ነው ማለት ነው።

ሙስሊሙ 'ተቺ"ይህንን ክፍል ለማክሸፍ የተጠቀማቸው ጥቅሶች ሁለት ናቸው።

1. ማቴ 21:12 ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ *የሚሸጡትን* እና *የሚገዙትን* ሁሉ አወጣ። "እነኚህ ሁለቱ ስሞች የተለያዩ ሰዎችን ይገልፃሉ" ብሎ ፅፏል።

ይሄ ክፍል በ አረፍተ ነገር አወቃቀሩ ቲቶ 2:13ን ቢመስልም (τοὺς πωλοῦντας καὶ ἀγοράζοντας*Those selling and buying) ግን ቅድመሁኔታዎችን ስለማያሟላ ውድቅ ነው። ምክኒያቱም "የሚሸጡትን* እና *የሚገዙትን" የሚሉ ሁለቱም ቃላት #ነጠላ አይደሉም።የ ግራምቪልን ሕግ አያሟሉም። ስለዚህ ክፍሉን እንደማስረጃ ማቅረብ በራሱ አሳፋሪ ነው።

2. ኤፌሶን 2:20 *በሐዋርያት* እና *በነቢያት* መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥

አሁንም በዚህ ክፍል "በሐዋርያት* እና *በነቢያት"  የተባሉት ሁለቱም ብዛትን የሚያሳዩ እንጂ ነጠላ አይደሉም። ስለዚህ አሁንም ማስረጃው የ ግራንቪልን ሕግ ስለማያሟላ  ውድቅ ይሆናል
@Jesuscrucified
ግራንቪል ሻርፕ፦የዮሓኒስ ወንጌል 20:28

ሙሓመዳውያን መፅሓፍ ቅዱስ ውስጥ ተፅፎ የክርስቶስን አምላክነት በ ግልፅ የሚያሳዩ ጥቅሶችን ከራሳቸው ሳይሆን ከ ስላሴ ተቃዋሚያን፣ ግን ክርስቲያን ነን ባዮች በሚሰበስቡት የወረደና በ ብዙ ምሁራን የፈረሰ ሙግት ይዞ እንደ አዲስ መቅረባቸውን ቀጥሏል። ዮሓኒስ 20:28 ከ ጥቅሶቹ መካከል አንዱ ነው።


(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 20)
----------
27፤ ከዚያም በኋላ ቶማስን። ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።

28፤ ቶማስም። #ጌታዬ #አምላኬም ብሎ መለሰለት።

29፤ ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።

ἀπεκρίθη Θωμᾶς καὶ εἶπεν #αὐτῷ#κύριός μου καὶ ὁ #θεός μου.( ho Kyrios mou kai ho Theos mou)

"28 And Thomas answered and said unto #him, The #Lord of me and The #God of me."
(John 20:28)

ከላይ ያነበብነውን ፅሁፍ በ አጭሩ ስንገልፅ
1. ቶማስ እየሱስን ጌታዬ እና #አምላኬ(θεός) ብሎ ጠራው
2. እየሱስም ቶማስ ለሱ የሰጠውን ስም (ጌታና #አምላክ) ተቀበለ፦ (…ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው)

3. ስለዚህ እየሱስ #አምላክ ነው ማለት ነው።

ይሁን እንጂ ሙሓመዳውያን ይህንን ክፍል ለማፍረስ አሁንም ልክ ቲቶ 2:13 ላይ እንዳነሱት ግራንቪል ሻርፕ ባስቀመጠው ሕግ ይሟገታሉ።  የሚያሳዝነው ግን የ ግራንቪል ሻርፕ ሕጎችን እንኳን ማወቅ ይቅርና ክፍሉን ራሱ እንደላጠኑ ያሳውቅባቸዋል።

የ ሻርፕ ስድስተኛው ሕግ

የ ግሪክ ቋንቋ ስኮላር ግራንቪል ሻርፕ እራሱ በ 1798 "The"( ὁ) የተሰኘች definite article አጠቃቀም ዙሪያ ላይ ባሳተመው መፅሓፍ ውስጥ ስድስተኛው ሕግ ላይ ቀጥሎ ያለውን ሕግ ፅፏል።

"ሁለት ተመሳሳይ ሙያ (same case) ያላቸው ስሞች
 καὶ (እና) በሚለው መስተፃምር ተያይዞ ግን በ ሁለቱም ስሞች ፊትለፊት 'ὁ' 'The' ከገባ፣ ሁለቱ ስሞች ሁለት የተለያዩ አካላትን ይገልፃሉ።... ነገር ግን ሕጉን የሚገድቡ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ።

1. የ አረፍተ ነገሩ አውድ
2. ከ አረፍተ ነገሩ ፊትለፊት ሁለቱም ስሞች ለ አንድ አካል መሆኑን የሚያሳይ ገላጭ ካለ (e.g. pronoun) ሁለቱም ስሞች ለ አንድ አካል( person) መሆኑን ያሳያል።

ምሳሌ፦  ራእይ 1:8

" ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ። አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።"
"Ἐγώ εἰμι #τὸ Ἄλφα καὶ #τὸ Ὦ,.."
I am #The Alpha and #The Omega

በዚህ ምሳሌ ላይ 'አልፋ' ፊትለፊት እንዲውም ደግሞ 'ኦሜጋ' ፊትለፊት "THE" የሚለው አርቲክል ገብቷል። ነገር ግን ሁለቱም "እየሱስን" ለመግለፅ እንጂ 'አልፋ' እየሱስን ገልፆ 'ኦሜጋ' ደግሞ አብን ለመግለፅ አልገባም። ምክኒያቱም፦
1. Ἐγώ (እኔ፣ I) የሚለው personal/possessive pronoun Nominative ሲሆን ሁለቱ ስሞች (አልፋና ኦሜጋ) አንድን አካል (እየሱስን) እንደሚገልፁ ያሳያል።
2. አውዱም (context) እየሱስ እረሱን፣ማንነቱን ለመግለፅ የተጠቀመበት እንደሆነ ግልፅ ነው።

በተመሳሳይ ሙግት የዮሓኒስ ወንጌል 20:28ን እንመልከት

#αὐτῷ#κύριός μου καὶ ὁ #θεός μου

"28 And Thomas answered and said unto #him, The #Lord of me and The #God of me."

በዚህ ክፍል በ ሁለቱም ስሞች ፊትለፊት  (κύριός(ጌታ) እና (θεός) ) ' Ὁ' "The" ገብታለች። ስለዚህ እውነት ሙስሊሞቹ እንደሚሉት "ጌታ" የሚለው ለ እየሱስ ሲሆን " አምላክ" የሚለው ደግሞ ለ አብ ነውን??

በ እርግጥ ይህንን ሙግት የሚያቀርበው ከንቱ ተቺ፣ወይ የ ሕጉን ቅድመ ሆኔታዎች ባለየ አልፎታል ወይም ሕጉን አላጠናም።

መልሱ 'በ ፍፁም አይደለም' ነው። ግራምቪል እራሱ በ መፅሓፉ ገጽ 14-16 ላይ የዮሓኒስ 20:28ን ሰዋ ሰው ሲያብራራ ሁለቱም ስሞች((κύριός(ጌታ) እና (θεός) ) ለ አንድ person እሱም #ለእየሱስ እንደሆነ ማስረጃ አቅርቧል።

1. αὐτῷ( said unto #him; 'አለው') የሚለው personal/possessive pronoun dative ሲሆን፣ ሁለቱም ስሞች (ጌታ እና አምላክ)የሚገልፁት አንድን person እሱም #እየሱስን እንደሆነ ያሳያል። ልብ በል " dative case(ሙያ)" መሆኑ አረፍተ ነገሩ ላይ ችግር አያመጣም።ምክኒያቱም ሕጉ ተመሳሳይ ሙያ እንዲሆኑ የጠየቀው ለ ስሞቹ( nouns) እንጂ ለ pronoun አይደለም።

2. የ ክፍሉ አውድ የሚነግረን ቶማስ ለ እየሱስ ለራሱ ይህንን ንግግር እያደረሰ ስለሆነ ሁለቱም ስሞች እየሱስን የሚገልፁ ናቸው።

ልብ በሉ፤ ይህ ደካማ ተቺ፣ ሙግቱን ያቀረበው ግራንቪል ሻርፕን ምንጭ (reference) አድርጎ ነው። ግን ሒደን ግራንቪል እራሱ በዚህ ክፍል ላይ (ዮሓኒስ 20:28) የሰጠውን ማብራሪያ ስናነብ " ክፍሉ እየሱስን" "አምላክ" እንደሚል ተብራርቶ እናገኛለን።  ለዛም ነው ይህንን ኡስታዝ ነኝ ባይ "ከንቱ" ያልነው።

ግራንቪል በራሱ እጅ የፃፈውን ከታች በፎቶ አያይዝላቹሓለው። አንብቡት!!

እየሱስ ለዘላለም ጌታ ነው!!

" እንግዲህ። በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:24)

Reference

Remarks on The Uses of the Definitive Article  in the Greek text of Of the New Testament, Granville Sharp; page 14-16
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
👉 ታዘዙኝ ተከተሉኝ ሲል ሙሐመድ ዝም ብሎ አይደለም ንፅፅርን አቅርቦ እንጂ! ይኽውም #ተራን መከተል መታዘዝን ሳይሆን #ክርስትያኖች #እየሱስን #ይከተሉትና #ይታዘዙት #በነበረበት #ልክ፣ ጠርዝና ሙላት ነው እኮ ነው የሚሉን ኢብኑ አባስ ለምዕራፍ 3፥31-32 በሰጡት ማብራርያ። መቼም ሙሐመድ ከኔ በፊት ነበሩ እንዳላቸው የእስልምና ነብያት ሳይሆን አምላክ አድርገው ክርስትያኖች እየሱስን እንደያዙት ያዙኝ ማለት ቀጥታ አምልኩኝ ካልሆነ ምንድነው?🤦‍♂
👉 ሙሐመድ እኮ ውደዱኝ፤ ለኔ ያላችሁ ፍቅር ለዘላለማችሁ ወሳኝ ነው ያለው አሁንም በ ሳሂህ አል ቡካሪ ቅፅ 1 መፅሀፍ 2 ሀዲዝ ቁጥር 15 እና 16፣ ሳሂህ ሙስሊም መፅሀፍ 001 ሀዲዝ ቁጥር 70 እና 71 #ከሰውዘር ሁሉ በላይ እንዳለ ለምን እንዘነጋለን ጎበዝ?
- በመጨረሻም "መታዘዝ ማለት ማምለክ አይደለም!" ለሚል #ልክነው፤ እኛስ መች አልን እንደዛ? ነገር ግን ከትልቅ ምስጋና ጋር በዚህ የሚስማማና "ይህን የሚል ሐሰተኛ ነው!" የሚል ሙስሊም ካለ ካለበት ግዜ አንስቶ ሙስሊም አደለሁም ስላለ እጃችንን ዘርግተን እንቀነለዋለን። እንዴት ካላችሁ እንዲህ፦
🖊 አንድን የሐይማኖት አባት የሚሉትን መስማትና መታዘዝ እርሳቸውን #ማምለክ አደለም።
🖊 አይ መታዘዝና ያሉትን ማድረግ ማምለክ ነው! ያለ የተፋለሰን ሐሳብ #ተናግሯል
🖊 የተፋለሰን ሐሳብ የተናገረ #ስህተተኛ ነው።
📌 ሲጠቀለል ሙሐመድ(ኢብኑ ካቲር ለምዕራፍ 9፡31 በዘገበው ላይ) "መታዘዝና ሊቃውንቶች ያሉትን ማድረግ ማምለክ ማለት ነው።" ካለ ከላይ ባለው ዝርዝር መሰረት የተፋለሰን ሐሳብ ተናግሯል። እናም #ሙሐመድ "#ስህተተኛና የተፋለሰን ነገር #ተናጋሪ ነው!" የሚለውን ስለሚያረጋግጥልን እናመሰግናለን።🤓
.................//................
" እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:32)
🙏አርነት በእውነት ይሆንላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው🙏🙏🙏