ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#እዛ_ማዶ ጭስ ይጨሳል አጋፋሪ ይደግሳል
____________________________________
ማለት እስራኤል ከግብጽ ባርነት በወጡ ጊዜ በጭስ የተመሰለ ጉምና ደመና እየመራቸው ቅዱስ ሚካኤል መና እያወረደላቸው ስለወጡ ጭስ የተባለው የደመናው ምሳሌ ፤ አጋፋሪ የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
#ያችን_ድግስ ውጬ ውጬ በድንክ አልጋ ተገልብጬ
____________________________________
ማለት በድግስ የተመሰለውን መና እስራኤል 40 ዘመን በአጋፋሪ በተመሰለው በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት እየተመገቡ በድንክ አልጋ የተመሰለችውን ኢየሩሳሌምን መውረሳቸውን የሚያመለክት ነው፡፡ “ያቺ ድንክ አልጋ ሆ አመለኛ ሆ ያለ አንድ ሰው ሆ አታስተኛ” ሆ” መባሉ እስራኤል ከግብጽ ሲወጡ 600,000 ሆነው ሲሆን ነገር ግን ሁሉም በምድረ በዳ አልቀው ኢየሩሳሌምን የወረሳት አንድ ኢያሱና አንድ ካሌብነው ለማለት ነው፡፡ #መልካም በዓል
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን።

"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ!"

"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!"
ቅዳሴ ማርያም

ዛሬ ....
#ለክርስቶስ ጸሀይ ምስራቅ ድንግል #ማርያም የተወለደችበት ቀን ነው ።
(አንቲ ምስራቁ ለክርቶስ እንዲል ቅዱስ ህርያቆስ)

#ለክርስቶስ ዝናብ ደመና ድንግል #ማርያም የተዘረጋችበት ነው ።
(አንቲ በአማን ደመና እንተ አስተርያ ለነ ማየ ዝናም እንዲል ቅዱስ ያሬድ በዝማሬው)

#ለክርስቶስ መብል ፍሬ ድንግል #ማርያም የተተከለችበት ነው ።
(እስመ ወለድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን እንዲል ቅዳሴ ማርያም )

#መልካም_በዓል
#የልደትሽ_ቀን_ልደታችን_ነው
#ስለ_ሀገር_መጸለይን_አታስታጉሉ


©️ ከመምህር ዲ/ን እስጢፋኖስ ደሳለኝ
በዚህ ዕለት ሐምሌ 7 ቀን #ቅድስት_ሥላሴ በአብርሃም ቤት የገቡበት እና ሣራ ይስሐቅን እንደምትወልድ የተናገረበት ዕለት ነው፡፡

ዳግመኛም በዚህ ዕለት ልደቱ እና ዕረፍቱ በአንድ ቀን የገጠመለት የእመቤታችን ወዳጅ ፣ ኢትዮጲያዊው ቄርሎስ የተባለ የሃይማኖት ጠበቃ ፣ ቅዱስ እና ሊቅ #አባ_ጊዮርግስ_ዘጋስጫ ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው።

#ቅድስት_ሥላሴ

አባታችን አብርሃም ከተመሳቀለ ጐዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ መንገደኞችን ዅሉ በእንግድነት እየተቀበለ ሲያስተናግድ ይኖር ነበር፡፡ ጥንተ ጠላታችን ሰይጣን ለተንኮል አያርፍምና ይህንን መልካም ግብሩን ለማሰናክል አሰበ፡፡ አስቦም አልቀረ፤ የተጐዳ ሰው መስሎ ከጐዳና ቆሞ አብርሃም እንግዳ መቀበል እንደ ተወ፤ እርሱ ሊበላ ሊጠጣ ከቤቱ ቢሔድ ራሱን ፈንክቶ፣ ደሙን አፍሶ፣ አጥንቱን ከስክሶ፣ ልብሱን ገፎ እንደ መለሰው ወደ አብርሃም ቤት ለሚሔዱ ሰዎች ይናገር ጀመር፡፡ በዚህ የተነሣም እንግዳ ወደ አብርሃም ቤት አልመጣ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ አብርሃምም ማዕደ እግዚአብሔርን ያለ ምስክር (ያለ እንግዳ) አልመገብም ብሎ ሦስት ቀን ሳይመገብ ጾሙን አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን ይህን ደግነቱን እግዚአብሔር ተመልክቶ በሦስት ሰዎች አምሳል አንድም በሥላሴው (በሦስትነቱ) ከአብርሃም ቤት ገብቷል (ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ፣ 4 ፥32 )፡፡

በኦሪት ዘፍጥረት 18 ፥ 1 -19 ተጽፎ እንደምናገኘው በቀትር ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በሦስት ሰዎች አምሳል በመምሬ አድባር ዛፍ ተገልጦለታል፡፡ አብርሃምም ሦስት ሰዎች ቆመው ባየ ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ወደ እነርሱ ሮጠ፡፡ ወደ ምድርም ሰገደና ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ኾነ ባርያህን አትለፈኝ?›› ብሎ ተማጸነ፡፡ በመቀጠል አብርሃም ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፡፡ ቍራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፤ ልባችሁንም ደግፉ፡፡ ከዚያም በኋላ ትሔዳላችሁ፡፡ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና›› ሲላቸው እነርሱም ‹‹እንዳልህ አድርግ›› ብለውታል፡፡

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ጠርቶ ‹‹ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?›› አለው፡፡ አብርሃምም ከድንኳኑ ውስጥ እንዳለች ነገረው፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች›› ብሎ ለአብርሃም አበሠረው፡፡ ሣራ ይህንን ቃል በሰማች ጊዜ ባለቤቷም አርጅቶ፤ እርሷም የሴቶች ግዳጅ ትቷት ነበርና ‹‹‹ሲያረጁ አምባር ይዋጁ› እንዲሉ ‹‹እስከ ዛሬ ድረስ ቆንጆ ነኝን? ጌታዬ አብርሃምስ ገና ጐረምሳ ነውን?›› ብላ በማሰቧና መውለዷን በመጠራጠሯ ሳቀች፡፡ እግዚአብሔርም ምሥጢሩን በአጽንዖት ለማስረዳትና አስረግጦ ለመንገር አብርሃምን ‹‹ሣራ ለምን ትስቃለች? በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?›› አለው፡፡ ሣራም ስለፈራች ‹‹አልሳቅሁም›› አለች፡፡ እግዚአብሔርም መሳቋን እንዳወቀባት ከነገራት በኋላ በድጋሜ በዓመቱ ወደ አብርሃም ቤት እንደሚመጣና ሣራ ወንድ ልጅ (ይስሐቅን) እንደምትወልድ አብሥሯቸዋል፡፡

የቅድስት ሥላሴ ረድኤታቸው አይየን!
የቅዱስ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አማላጅነቱ አትለየን ። ሀገራችንን ቅድስት ኢትዮጺያን ሊለያይ የሚሽቀዳደመውን ዲያብሎስን በመስቀሉ ይምታልን።

©️ ዮቶር ደሳለኝ
#መልካም_በዓል
#ጸልዩ_በእንተ_ቤተክርስቲያን_ቅድስት@zdk24_5_21_official