አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////

ሚካኤልና ፀአዳ አንድ ሬስቷራንት ቁጭ ብለው ተፋጠዋል፡፡ከሁለቱም ፊት ለፊት ተከፍቶ የተቀመጠ ቢራ አለ..አንዳቸውም ግን አንስተው አልተጎነጩለትም፡፡

‹‹ለምን ጊዜችንን ትጨርሳለህ…የሆንከውን ካልነገርከኝ እንደማለቅህ ታውቃለህ››

‹‹ፀዲ..ለምን ችክ ትያለሽ..?ምንም አልሆንኩ የስራ ጉዳይ ነው አልኩሽ እኮ››

‹‹እኮ ግድግዳ በመዶሻ የሚያስነድል ምን አይነት የስራ ጉዳይ ነው?፡፡ሚኪ እኔ እኮ ለአመታት ነው የማውቀው..አንተን የስራ ጉዳይ በዚህ ልክ ሊያበሳጭህ…ኦረዲ አብደሀል እኮ››

‹‹ተይ ፀዲ አታጋኚ››

‹‹አጋነንኩ እንዴ…?የማትነግረኝ ከሆነ …››አለችና እጇን ወደ ሱሪ ኪሷ ሰዳ ስልኳን አወጣች፡፡
‹‹ምን ልታደርጊ ነው?››ግራ በመጋባት ጠየቃት፡

‹‹ብቻዬን አልቻልኩህም..ለአዲስ ደውልላትና ትምጣ..ከዛ ለሁለት እንሞክርሀለን››

‹‹በፈጠረሽ……የእሷን ጭቅጭቅና ለቅሶ የምሸከምበት ትእግስቱ የለኝም››

‹‹እና ንገረኛ››

‹‹እሺ ነግርሻለው››
ስልኩን ጠረጴዛ ላይ ከቢራ ጠርሙሱ ጎን አስቀመጠችና ሙሉ ትኩረቷን ወደእሱ አደረገች፡፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቁዘማ በኋላ እንደምንም አፉን ከፈተ‹‹የአባቴ ጉዳይ ነው››

‹‹እሱንማ አውቄለው…ከዛ ውጭ አንተን በዚህ ልክ ሊረብሽ የሚችል ሌላ ጉዳይ የለም…በዝርዝር ንገረኝ፡፡

‹‹አባቴ እናቴንም ሆነ እህቴን እንዳልገደላቸው ነገረኝ…እኔም አምኜዋለው››

ፀአዳ ክፉኛ ደነገጠች‹‹እና ማን ነው የገደላቸው..?ማለቴ እንዴት ሞቱ?››ተንተባተበች፡፡

‹‹እሱን አላውቅም…አባቴ ግን ከመሞቴ በፊት እናትህንና እህትህን እኔ እንዳልገደልኳቸው በትክክለኛ ማስረጃ አረጋግጥልኝ፡፡ከመሞቴ በፊት ልጆቼ እኔ ንፅህ ሰው መሆኔን ማወቃቸውን ማረጋገጥ እፈልጋለው››አለኝ በማለት ሙሉውን ታሪክ በዝርዝር ነገራት፡፡

‹‹እና አሁን ምን ልታደርግ ነው…?እንዴት አድርህ ማረጋገጥ ትችላለህ?››

‹‹ግድግዳውን የናድኩት ለዛ ነበር..አባቴ እዛ ግድግዳ ውስጥ የደበቃቸው የተወሰኑ ማስረጃዎች ነበሩ..አለና ስልኩን ከፍቶ  በሚሞሪ ያሰቀመጣቸውን ቪዲዬዎች አስደመጣት፡፡ሽምቅቅ አለች፡፡

‹‹በጣም ያሳፍራል አይደል?››አላት፡፡

‹‹በእውነት ምን እንደምልህ አላውቅም››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹አየሽ ክህደት ምን እንደሆነ ምን አይነት ህመም እንደሚያስከትል ከእኔ በተሻለ አንቺ ታውቂያሽ..አባቴ እነዚህን ሁሉ መረጃዎች ካወቀ በኋላ ሚስቱ እሱን ሳይሆን ሌላ ሰው እንደምታፈቅር ከተረዳ በኋላ…በጣም የሚወዳት ቀምጥል ልጁ የእሱ ሳትሆን የሌላ ሰው ልጅ እንደሆነች ካወቀ በኃላ  ….የሁለት መንታ ወንድ ልጆቹ እናት እሱን ጥላ ወደልጅነት ፍቅረኛዋ ልትሄድ ዝግጅት ላይ እንዳለች በግልፅ ካወቀ በኋላ  ምንድነው ማድረግ ያለበት?ይሄንን ሁሉ በደል እንዴት መቋቋም ይችላል…?እና  እሱ ቢቀውስና የእብድ ስራ ቢሰራ ይፈረድበታል?››

‹‹በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው…ግን እኮ አላደረኩትም ብለውሀል….›››

‹‹እሱማ  አዎ እወነቱን እንደሆነ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ….ግን እንዳውቀው ካስቀመጠልኝ መረጃ አንድም እሱ እንዳለደረገው የሚገልጽ ፍንጭ ማግኘት አልቻልኩም..እና መተንፈስ እስኪያቅተኝ ድረስ በጣም ግራ ተጋብቻለው፡፡

‹‹ምን እንደገረመኝ ታውቃለህ?››አለች፡፡

ትኩረቱን በሙሉ ወደእሷ ሰበሰበና‹‹ምን? ››ሲል ጠየቃት፡፡
አባትህ በግድያው ተጠርጥረው ፍርድ ቤት በሚመላሰሱበት ጊዜ ይሄንን አሁን ለአንተ የሰጡህን መረጃዎች ለምን ለፍርድ ቤቱ አላቀረቧቸውም….ቢያንስ እኮ የተፈረደባቸው የሞት ቅጣት ወደእድሜ ልክ ይቀየርላቸው ነበር፡፡››

‹‹አዎ..ትክክል ነሽ…መረጃዎቹን እንዳገኘው እኔም ወደ አእምሮዬ የመጣው የመጀመሪያ ጥያቄ እሱ ነበር..እና ትናንትና ወደወህኒ ቤት ሄጄ አግኝቼው ነበር….ለምን ለፍርድ ቤት እንደመረጃ አድርገህ አላቀረብከውም ስለው…ለእናንተ ስል?››ሲል መለሰልኝ፡፡

‹‹አልገባኝም… እንዴት ለእኛ ስትል ?››ብየየ መልሼ ጠየቅኩት፡፡
‹‹እንዳልከው ይሄንን ለፍርድ ቤት እንደወንጀል ማቅለያ አድርጌ ባቀርብ ኖሮ ይሄኔ እናትም አባትም ነበር የምታጡት፡፡በወቅቱ የእኛ ቤተሰብ ጉዳይ በየጋዜጣውና መፅኄቱ እንዴት እንደሚፃፍ ታውቃለህ..ይሄ ነገር ወጥቶ ቢሆን ኖሮ ስለእናትህ ምን እንደሚፃፍ አስበው…የተፃፈ ነገር ደግሞ ታሪክ ሆኖ ይቀመጣል…የልጅ ልጇቼ ጭምር ስለወንድ እና ሴት አያታቸው ታሪክ ሲያነብ ምን አይነት የልብ መሰበር ያጋጥማቸዋል…የእኛን ማህበረሰብ ለነገሮች ያለውን ብያኔ የምታውቀው ነው..በእኔ ጉዳይ ምን ያህል ፈተና እና መገለል እንደሚገጥማችሁ አውቃለው…ይሄ የእሷ ታሪክ ቢጨመርበት ኖሮ መግቢያ መውጫ ነው የሚያሳጦችሁ››በማለት መለሰልኝ፡፡

‹‹አይገርምም !!ወላጅ መሆን እኮ እዳ ነው..አንዳንዴ የነፍስ ክፍያ ለመክፈል እንኳን የማታመነታበት ምስጢራዊ ፀጋ ነው፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ››

‹‹አሁን አንድ ምርጫ ብቻ ነው ያለን››

በንቃት‹‹ምን ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ሰውዬውን ፈልገን ማነጋገር››

‹‹የትኛውን ሰውዬ?››

ፈራ ተባ እያለች ‹‹የእናትህን ጓደኛ…..››ስትል መለሰችት፡፡

የሚካኤል ደም ስር በንዴት ውጥርጥር አለ‹‹እሱ እኮ ጠላታችን ነው..እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ የከተተን እሱ ነው…ፊት ለፊት አግኝቼ እንድገድለው ነው የምትፈልጊው፡፡››

‹‹የሆነ ፍንጭ ለማግኘት የግድ እሱን ማግኘት አለብን…የግድ አንተ ልታናግረው አይገባም…ቆይ እስኪ››  አለችና ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጠችውን ስልክ አንስታ ከፈተች ..ምን ልታደርግ ነው ብሎ ሲጠብቅ‹‹ስሙ ማን ነበር››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹የማ?››

‹‹የሰውዬው ነዋ››

‹‹ለሚ በቀለ ››

ስሙን ሰርች ላይ ከታ መፈለግ ጀመረች፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ዳይሬክተር ዳይሬክቶሪት ደ/ር ለሚ  በቀለ የሚል ዜና አየች፡፡

‹‹እንዴ ሰውዬው ባለስልጣን ነው እንዴ?››

ምንም አልመለሰላትም..ዜናውን ከፍታ ለማንበብ ሞከራች…ከአምስት አመት በፊት የተፃፈ ዜና ነው፡እሱን ተወችና ….ሌላ ፈለገች ..ሶስት አራቱን ከከፈተች በኃላ በአራተኛው ትኩረት ሚስብ ዜና አገኘች‹‹የግብርና ሚንስቴሬ ዳይሬክተር ዳይሬክቶሬት የሆኑት ዶ/ር ለሚ  በቀለ በጤና እክል ምክንያት መልቀቂያ በማስገባት ስልጣናቸውን ለቀዋል ››ይላል፡፡ከአራት አመት በፊት የተለቀቀ ዜና ነው፡፡

ወደፌስብክ ገባችና በስሙ ፈለገች.. ዲአክቲቬት ከሆነ አመታት አልፈዋል፡፡

‹‹ሰውዬው ጥሩ ሁኔታ ላይ አይመስለኝም….ቆይ ለእኔ ተውልኝ››

‹‹ምን ልታደርጊ አሰብሽ….?››

‹‹ያለን ምርጫ አንድ ብቻ ነው፣ቢያንስ አሁን አንድ ነገር አውቀናል..ከአራት አመት በፊት ግብርና ሚኒስቴር ይሰራ ነበር…ስለዚህ አዛ ሄድና አሁን ሚገኝበትን አድራሻ ጠይቃቸዋለው…ቢያንስ ስልኩን ይሰጡኛል፡፡››

‹‹እስቲ እናያለን››ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡

‹‹አይዞህ ምንም አትጨነቅ..ይሄንን ነገር እንፈታዋለን….የፈለገ መስዋእትነት ያስከፍል የአባትህን ምኞት እናሳካለን….ይሄ ጉዳይ ዘሚካኤልንም ወደቤተሰቦቹ እንዲመለስ ለማድረግ ያግዘን ይሆናል፡፡››

‹‹እኔ እንጇ..ዘሚካኤል እናቱን እንደፈጣሪው ነው የሚወዳት..ለእሱ እሷ እንከን አልባ መልአክ የሆነች ሴት ነች…ይሄንን ሲሰማ ዳግመኛ ይበልጥ  እንዳይሰበር ነው የምፈራው፡፡

‹‹አይዞህ ….ከመሰበር በኃላ ያለ መጠገን ነው እኛን ሞርዶ ሙሉ ሰው የሚያደርገን፡፡ደግሞ እናትህ ጥፋት ያጠፋችው  በሚስትነቷ ነው እንጂ በእናትነቷ  እስከወዲያኛው ምሉ እንደሆነች ነው፡፡››
👍6610🥰1
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

አዲስ አለም በራሷ መኪና ግን ሹፌር እየነዳላት  ከአዳማ ወደአዲስ አበባ እየተጓዘች ነው፡፡

የተቀመጠችው ከኋላ ወንበር ላይ ሲሆን ከግራዋ የራሷ ልጅ ቅዱስ ሲኖር ከግራዋ ደግሞ የፀአዳ ልጅ ምሰር ትገኛለች፡፡

አዲስአለም ወደአዲስ አበባ የምትሄደው እናቷን ለመጠየቅ ነው፡፡ይሄ ቤተሰቦቾ አዳማ ለቀው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ  በወር ወይም በሁለት ወር አንዴ የምታርገው ነገር ስለሆነ ማንም ለምን እንዴት ብሎ የሚጠይቃት የለም፡፡ምስርን በምን ሰበብ አስፈቅዳ ከእሷ ጋር ይዛት እንደምትመጣ ግን ግራ ገብቷት ነበር፡፡ማታ ነበር ፀአዳ ጋር የደወለች፡፡

‹‹እሺ ጓደኛዬ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ ምነው ቀን ተገናኝተን ነበር እኮ..በዚህ መሀከል ምን ትሆናለች ብለሽ አሰብሽ?››.

‹‹አንቺ ደግሞ ከአፍሽ ቀና ነገር ቢወጣ ምን አለበት?››

‹‹በይ አሁን ምን ፈልገሽ ነው ወደገደለው ግቢ….››

‹‹በእናትሽ ነገ እነማዬ ጋር አብረን እንሂድ››

‹‹ነገ ››

‹‹አዎ ነገ››

‹‹ያምሻል እንዴ…?ስንት ስራ እንዳለብኝ  ስነግርሽ ውዬ እንዴት የማልችለውን ነገር ትጠይቂኛለሽ?››

‹‹ውይ ለካ ስራ አለብሽ..ብቻዬን መሄድ እኮ ደብሮኝ ነው››

ብቻሽን መሄድ ከደበረሽ  ታዛዥ እና ጣፋጭ የሆነ ምርጥ ባል አለሽ እሱን አስከትለሽ ሂጂ››

‹‹አንቺ እየሰማሽ እኮ ነው››

‹‹ላውድ ላይ አድርሽ ነው እንዴት የምታወሪኝ… አንቺ እኮ ቅሌታም ነሽ….ለነገሩ ሚኪን በተመለከተ መጥፎ ነገር እንደማልናገር እርግጠኛ ስለሆንኩ እንደፈልገሽ››

‹‹መጥፎ ነገር እንደማትናገሪ እኔም ምስክር ነኝ … ውሸት ግን ትናገሪያለሽ..ምን አልባት እንዳልሺው ጣፋጭ ሊሆን ይችላል ታዛዣ ግን አይደለም..ልክ እንደአንቺው ስራ አለኝ አልችልም የሚል መልስ ነው የሰጠኝ››

‹‹በቃ ከልጅሽ ጋር ሒጂ››

‹‹ወይ እንደውም ተውት ከልጆቼ ጋ ሄዳለው…ምስርን ቆንጆ አድርገሽ አሳምሪያትና ወደስራ ስትሄጂ ይዘሻት ውጭ.. በዛው መጥቼ ወስዳታለው››

‹‹ምን እያልሽ ነው?››ፀአዳ እንደመበሳጨት አለች፡፡

‹‹የራስሽው ምክር እኮ ነው፡፡ልጆቹን ይዤ ሄድና ዘና እንላለን…እናንተም ካለልጆቻችሁ ይድላችሁ…እሁድ ማታ ተመልሰን እንመጣለን፡፡››

‹‹አንቺ እኮ የሆነ መዠገር ነገር ነሽ…እኔ ለራሴ ስንት ስራ አለብኝ..?ገና አሁን እሷን ሰውነቷን ሳጥብ..ፀጉሯን ሰሰራ….››

አላስጨረሰቻትም፡፡‹‹በቃ…ጥዋት ሁለት ተኩል አካባቢ ስራ ቦታሽ እመጣና ወስዳታለው..ደህና እደሪ..እወድሻለው፡፡››ብላት ስልኳን ዘጋችው፡፡እንዳለችውም ጥዋት ስትሄድ ፀአዳ ከነንጭንጯ ልጇን ምስርን አስባና አሳምራ ነበር የጠበቀቻት፡፡

‹‹ውይ ጎደኛዬ ንዴት እንደሸወድኩሽ ስታውቂ እንዴት ትናደጂ ይሆን?›› ብላ አሰበችና ብቻዋን ፈገግ አለች፡፡

ሹፌሩ ጎሮ አካባቢ የሚገኘው የቤተሰቦቾ ቤት ካደረሳት በኃላ  ሚካኤል እንዲገዛለት ያዘዘው ዕቃዎች ስለሉ ወደመርካቶ ለመሄድ ተዘጋጀ….

‹‹በቃ ነገ አስር ሰዓት አካባቢ እዚህ ድረስ ››አለችው አዲስ፡፡

‹‹እዚህ የምትንቀሳቀሺበት አይቸግርሽም?››

‹‹ችግር የለውም..የትም የመውጣት እቅድ የለኝም…ምን አልባት የምወጣም ከሆነ ራይድ እጠቀማለው››አለችና ሸኘችው፡፡

ከዛ ልጆቹን ወደቤት አስገብታ እናቷን በቅጡ እንኳን ሰላም ሳትል ነው ወደጓሮ ሄዳ ስልክ የደወለችው፡፡ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ‹‹እንዴት ነህ ዘሚካኤል?››

‹‹ሰላም ነኝ..ግን አልተሳካልኝም ብለሽ እንዳታበሳጪኝ››

‹‹አረ ተሳክቶልኛል…መጥተናል እማዬ ቤት ነው ያለነው፡፡››

‹‹በጣም ጎበዝ…..በቃ ጎሮ አካባቢ ነው ያልሺኝ፡፡››

‹‹አዎ… ትክክለኛ አድራሻውን በሚሴጅ ልክልሀለው››

‹‹በቃ..በአንድ ሰዓት ውስጥ እመጣለው››

‹‹ጥሩ ነው..እኛም ገና አሁን መድረሳችን ስለሆነ እስከዛ ከእማዬ ጋ እንጫወታለን…በል ቻው››

‹‹አዲስ በጣም አመሰግናለው…ቻው››

ስልኩ ተዘጋ ፣፣እሷ ግን ፈዛ ቀረች…ከዘሚካኤል ጋር በዚህ መጠን መቀራረብ መቻሏ የተአምር ያህል ነው….ለዘመናት ስታልመውና ስትመኘው የነበረ ነገር ነው፡፡ግን በዚህ መንገድ ይሆናል ብላ ፈፅሞ ሀሳብ አልነበራትም..እሱ የእሷን የልብ ጓደኛ አፍቅሮ እሷ ደግሞ እሱን ከሚያፈቅራት ልጅ ጋር ለማቀራረብ ስትጥር….በራሷ ድርጊት ፈገግ አለች፡፡

‹‹ምን አለበት…. ለሚያፈቅሩት ሰው የሚያፈቅረውን ነገር እዲያገኝ መርዳት ትንሽ ህመም ቢኖረውም ግን ደግሞ ደስ የሚል ስሜት አለው፡፡››አለችና ለስሜቷ ድጋፍ ለመስጠት ሞከረች…የባሏ ሚካኤል ምስል በድንገት መጥቶ አየሩን ሞላው‹‹ፍቅሬ ምን እያሰብሽ ነው…?የገዛ ወንድሜን!!!››ብሎ በሀዘን በተሰበረ ስሜት ሲወቅሳት አየች፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ይሄ እኮ ያለፈ ታሪክ ነው….ታውቃለህ እሱን ለማግኘት ስትጥር ነበር ከአንተ ጋር የተቀራረብኩት…ከዛ እሱም ሀገር ጥሎ ጠፋ አንተም ለእኔ ምርጥና ተወዳጅ ሆንክልኝ..እናም  በሙሉ ልቤም ወድጄ አገባሁህ››

‹‹ግን ስታገቢኝ…ወደሽ ነው..ወይስ አፍቅረሺኝ?››

‹‹አይ አንተ ደግሞ ምን ቃላት ትመነዝራለህ….ለማንኛውም..የእሱ ያለፈ የአፍላ የወጣትነት ስሜት ነው..አሁን እየቀረብኩትና እየረዳሁት ያለሁት ያንተ ወንድም ስለሆነ ብቻ ነው››

‹‹እንዴ…!!ምንድነው  ጓሮ ተደብቀሽ ብቻሽን ምታወሪው?››የእናትዬው የመገረም ንግግር ነበር ከገባችበት ቅዠት መሰል ሀሳብ አባኖ ያወጣት፡፡

‹‹አይ እማዬ ..ምንም አይደል ..የሆነ ነገር እያሰብኩ ነበር››

‹‹የሆነ ነገር..ምነው ከሚካኤል ጋር ተጣላችሁ እንዴ?››

‹‹ወይ እማዬ ምንድነው የምታወሪው..?ከሚካኤል ጋር ለምንድነው የምጣለው?››

‹‹ባልና ሚስት ለምንድነው የሚጣሉት?››

‹‹እኔ እንጃ..እኔና ሚኪ ስንጣለ አይተሸን ታውቂያለሽ?››

‹‹እሱ መልካምና ታጋሽ ባል ስለሆነ ነዋ…እንጂማ እንደአንቺ መመነጫጨቅ ቢሆን… ››እናትዬው ነግግሯን ሳታገባድድ አንጠልጥላ ተወችው፡፡

‹‹እማዬ ደግሞ… የእኔ እናት ነሽ  የእሱ?››

‹‹የሁለታችሁም…ባሌ ነው ብለሽ አምጥተሸ ካስተዋወቅሺኝ ቀን ጀምሮ እኮ ልክ እንደአንቺ እሱም ልጄ ሆኗል…በዛ ላይ አሁን ወርቅ የሆነ የልጅ ልጅ ሰጥቶኛል…በይ አሁን ነይ ግቢ ቁርስ ቀርቧል…››አሏትና ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ፡፡ 

ዘሚካኤል እንዳለውም ከአንድ ሰዓት በኃላ በራፍ ላይ ደርሶ ደወለላቸው፡፡ተዘጋጅታ ስትጠብቀው ስለነበረ ወዲያውኑ ነው ልጆቹን ይዛ የወጣችው፡፡ከግዙፉ ሀመር መኪናው ወርዶ በራፍን ከፍቶ ቆሞ እየጠበቃቸው ነበር…የስድስት አመቷ ምስር እንዳየችው ደነገጠች…..መጀመሪያ የት እንደምታውቀው ነበር ግራ የገባት..ከዛ የምትወደው ዘፋኝና ተዋናይ መሆኑን ስታውቅ ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት እየተንደረደረች ወደ እሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ከቆመበት እጆቹን ዘርግቶ ወደእሷ ተንቀሳቀሰ…እቅፉ ውስጥ ወደቀች.. ጭምቅ አድርጎ አቀፋትና በአየር ላይ አንጠለጠላት..የምስርን ድርጊት ያየው ቅዱስ እጆቹን ከእናቱ እጅ አስለቅቆ ኩስ ኩስ እያለ ምስር እንዳደረገችው ወደዘሚካኤል ሮጠ….አዲስአለም በልጆቹ ያልተጠበቀ ድርጊት  በድንጋጤ አፏን ከፈተች ….ሚካኤል ቅዱስ ስሩ ሲደርስ ምስርን ወደአንዱ እጁ አዘዋወራትና ጎንበስ ብሎ ቅዱስን አቅፎ ወደላይ አነሳውና ጉንጮቹን እያገላበጠ ሳመው…..በዚህ ጊዜ አዲስ አለም ከመደነቅ ሳትወጣ ስራቸው ደርሳ ነበር፡፡

‹‹ቆይ ከእነዚህ ልጆች ጋር ከዚህ በፊት ትተዋወቁ ነበር እንዴ?››

ጉንጮቾን እያገላበጠ ሰማት..ትንፋሹ ልክ ሰው ፊት ላይ እደሚበትን አደንዛዥ ዕፅ ኃይል አለው…
👍6612
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ነው፤ የሆነ የሚንጠጣረር ነገር እያደነቆረው ነው፡፡በመከራ ነው ከእንቅልፉ የነቃው…የበራፉ መጥሪያ ድምፅ መሆኑ አወቀ..ስልኩን ከኮመዲኖ ላይ አነሳና ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ይላል፡፡ያልተለመደ ነገር ነው፡፡በዚህ ሰዓት ማን ነው በራፍን መጥሪያ የሚያንጣርረው?፡፡የፅዳት ሰራተኛዋ እንደማትሆን እርግጠኛ ነው፡፡እሷ አንደኛ በዚህ ሰዓት አትመጣም…ብትመጣም የራሷ የሆነ ቁልፍ ስላላት እሱን የምትቀሰቅስበት ምንም  አይነት ምክንያት የላትም….መኝታውን ለቆ ተነሳና ጋዎኑን ደርቦ መኝታ ቤቱን ለቆ ወጣ፡፡፡ሳሎን ደርሶ በራፉን ሲከፍት..እየተመለከተ ያለው  ፈፅሞ በአእምሮው ያልጠበቀውን ነው፡፡ፊቱን በጥፊ ደረቱን በጡጫ እየቀጠቀጠች ገፍትራ ወደውስጥ አስገብታ ትቦጫጭረው ጀመር….‹‹ምን አድርጌሀለው..?እንዴት በልጄ ስሜት እንደዛ ትጫወታለህ..?ምን አይነት አረመኔ ሰው ብትሆን ነው?፡፡››
እንደዚህ አውሬ የሆነች ሴት በእድሜ ዘመኑ አጋጥሞት  አያውቅም፡፡ፊቱን ከብጭሪያ ለመከላከል ሁለቱን  እጆቹን በፊቱ ዙሪያ አድርጎ ለመከላከል ሞከረ፡፡
‹‹አረ ፀዲ ተረጋጊ….››
‹‹አልረጋጋም..እንዲህ አሳብደሀኝ እንዴት ነው የምረጋጋው…..?ልጄን እንዴት እንዳሳደኩዋት ታውቃለህ…?››መደባደቧን እና ጮኸቷን አላቆረጠችም….እንባዋ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ እየረገፈ ነው፡፡ትናንት የሆነውን ከሰማችበት ደቂቃ ጀመሮ ማልቀሷን አላቆረጠችም… ለሊቱን እንቅልፍ ባይኗ ሳይዞር ስትቃጠልና ስትነፈርቅ ስላደረች የእናቱን ሞት አዲስ እንደተረዳ ሀዘንተኛ አይኖቾ ከማበጣቸውም በላይ ክፍኛ ደፍርሰዋል፡፡
ዘሚካኤል መከላከሉ ብቻ እንደማያዋጣ ገባው፡፡እንደምንም አለና ሁለት እጆቾን ያዘና ስቦ ከሰውነቱ ጋር አጣበቃት፡፡
‹‹ልቀቀኝ..ከዚህ ቀፋፊ ሰውነትህ ጋር መነካካት …..››አላስጨረሳትም የተከፈተ አፏን በአፉ ከደነው….በተቻላት መጠን ተወራጨች…ከእሱ ፈርጣማና የዳበረ ጡንቻ ማምለጥ አልቻችም…ከንፈሩን ነከሰችው….ለቀቃትና..ተስፈንጥራ ወደኃላ ልታመልጥ ስትል መልሶ በመያዝ ሙሉ በሙሉ ከስር ገብቷ ተሸከማት……እንደእፃን ልጅ በእግሯም በእጇም ተወራጨች… ወደሶፋው ይዟት ሄደ…ሶፋው ላይ ሊወረውረኝ ነው ብላ ስትጠብቅ እሷን አጥብቆ እንደያዘ እግሩን ዘረጋና ከሳፋው ላይ አንዱን ትራስ ወደወለሉ አወረደ….በፍጥነት ገለበጣትና እንደህፃን አቅፎ ወደታች በጉልበቱ ተንበረከከ እና ወለሉ ላይ አስተኛት…ሾልካ ከስሩ ለማምለጥ ታገለች… በጥንካሬ ጨምቆ ከወለሉ ላይ አጣበቃትና ጭንቅላቱን ቀና አድርጎ ትራሱ ላይ አስደገፋት …እንዳይጨፈልቃት በመጠንቀቅ እላዩዋ ላይ  ተቀመጠ…የለበሰውን ጋወን አውልቆ ወረወረው….
‹‹ምን ልታደርግ ነው?››አይኗቾ በድንጋጤ ፈጠጡ፡፡
ወደታች ጎንበስ አለና የለበሰችውን ቲሸርት ከግራና ከቀኝ ይዞ ወደታች ተረተረው….የመጨረሻውን ንዴት በመናደዷ ምክንያት ደምስሯ ተግተረተረ‹‹ምን እያደረክ ነው? ልትደፍረኝ ነው እንዴ..?እከስሀለው…ስምህን ነው ያማጠፋው….››የቀራት ብቸኛ መከላከያ ምላሷ ብቻ ነበር….ልታስፈራራው ሞከረች ፡፡ተንጠራራና ሌላ ትራስ አምጥቶ ከጎኗ በማድረግ ከላዬ ላይ ወርዶ ከጓና ተኝቶ ወደራሱ ገለበጣትና አቀፋት፡፡
ከታች እሱ በቁምጣ ሲሆን እሷ ደግሞ ልክ እንደወትሮዋ ጅንስ ሱሪ እንደለበሰች ነው፡፡
‹‹በፈጠሪ ስትበሳጪ እንዴት ነው የምታምሪው?፡፡››
‹‹እያሾፍክብኝ ነው?››
‹‹በፍፅም ..አይገባሽም እንዴ ..?ካንቺ ፍቅር ይዞኛል…ላገባሽ እፈልጋለው››
ምትሰማውን ቃል ማመን አቃታት‹‹ይሄ ደግሞ ሌላ ቀልድ መሆኑ ነው?ሕይወት እንደምትተውነው ተውኔት መሰለህ?››
‹‹እሱ እንዳያያዝሽ ነው …እኔ ግን የተናገርኩት ከልቤ ነው…ከፈለግሽ ዛሬውኑ ሄደን መጋባት እንችላለን…እንደማገባሽ እግጠኛ ስለሆንኩ ነው ምስርን ልጄ ነች ያልኩት፡፡››
‹‹እንዴት እሺ ትለኛልች ብለህ አሳብክ?››
‹‹እንደምትወጂኝ አይኖችሽ ውስጥ ስላነበብኩ››
የተፋቀረ ሁሉ ይጋባል ያለህ ማን ነው….ደግሞ እወቅ እኔ ፍቅር አልፈልግም…አሁን ልቀቀኝ ..ከአንተ እስከወዲያኛው መሸሽና መራቅ ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹አይ ከአኔ ሸሽተሸ ማምለጥ  አትችይም፡፡››
‹‹ልቀቀኝ አልኩ..›› ለመመናጨቅ ሞከረች አጥብቆ ያዛትና ከንፈሯ ላይ በድጋሚ ተጣበቀ… ሳላሳ ሰከንድ ያህል ብቻ ነው መታገል የቻለችው..ከዛ ቀስ በቀስ እየለዘበች…  የእጆቾ ጡንቻዎች እየለሰለሱ ..ከንፈሯቾ ለከንፈሮቹ መልስ እየሰጡ መጡ…እሱን ሲቧጭሩ እና ሲደበድብት የነበሩት ጣቶቹ ጀርባውናና መላ ሰውነቱን ማሻሸት ጀመሩ…ከዛ እሱ ቁምጣውን ሲያወልቅ እሷም በገዛ እጇቾ ጅንስ ሱሪዋን እያወለቀች ነበር….እዛ ግዙፍ የሳሎን ወለል ላይ 30 ለሚሆኑ ደቂቃዎች በፍቅር እየተንከባለሉ እና ከኮርነር  ኮርነር እየተሸከረከሩ በጣር የታጅበው ወሲብ ሲሰሩ በራፉ ክፍት መሆኑን እንኳን አላስተዋሉም ነበር፡፡
ከወሲብ በኃላ አርቃኗን ሆና ‹‹አንተ ምን አይነት አዚም ነው ያለህ ግን?››ስትል ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው የፍቅር አዚም ነዋ››
‹‹አይ አይመስለኝም…..የሆነ  የሚያደነዝዝ አይነት መስተፋቅርማ አለህ…አሁን ሻወር ቤቱን አሳየኝ..››አለችው፡፡
ከተዘረረበት ወለል እየተነሳ ወደእሷ ሄዶ ከስር ተሸክሞ ወደምኝታ ክፍሉ ተሸክሟት ገባ….‹‹ያው ግቢና ታጠቢ››
‹‹እሺ…ቲሸርቴን ቀዳደሀዋል….አሁን ምን ልለብስ ነው?››እያለች ገባች፡፡
‹‹አታስቢ አዘጋጅልሻለው….ግን አብሬሽ ሻወር መውሰድ እፈልጋለው፡፡››
‹‹ስርአት ይዘህ የምትታጠብ ከሆነ ትችላለህ›› አለችው፡፡በደስታ እርቃኑን ገባና ተቀላቀላት…መታጠብ ጀመሩ፡፡ ቃል እንደገባው ግን ስርዓት ይዞ አልታጠበም..እሷም በቃላት አውጥታ አትናገር እንጂ ስርዓት የለሽ መሆኑን ፈልጋው ነበር..ከዛ ሻወር ቤት ለመውጣት አንድ ሰዓት በላይ ነበር የወሰደባቸው፡፡ ከዛ ተያይዘው ሲወጡ ሁለቱም ሰውነታቸውን ማዘዝ እስኪያቅታቸው ዝለው ነበር.. ርቃናቸውን ተያይዘው አልጋ ውስጥ ነው የገቡት…ሁለት ሰው መሆናቸውን መለየት እስኪከብድ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተቃቅፈው ለሞት የተቃረበ እንቅልፍ ውስጥ ገቡ፡፡
///
ተመሳሳይ የበራፍ ተደጋግሞ መንጫረር ነበር ከእንቅልፉ ያባነነው..‹‹ዛሬ ደግሞ ምን ጉድ ነው ?››በማለት እየተነጫነጨ…እንደምንም ነቅቶ ስልኩን ሲመለከት..ከ30 በላይ ሚስኮል ነበረው…ሰዓቱን ሲመለከት 7ሰዓት ተኩል ሆኗል…ማመን አልቻለም፡፡ይሄ ሁሉ ሚስኮል ከማን ነው ብሎ ሲያየው አብዛኛው ከአዲስአለም ነው…ስለፀደይ ተጨንቃ እንደሆነ ገመተ ..አልጋውን ለቆ ሲወርድ ፀደይ እራሷን አታውቅም፡፡
ጋወኑን ቅድም ሳሎን ወለል ላይ ትቶት ስለነበረ….ቁምጣ እና ቲሸርት ለበሰና በድኑን እየጎተተ ወደ ሳሎን ሄዶ በራፉን ሲከፍት ክፍኛ የደነገጠችውና አይኗ  የፈጠጠው አዲስአለም በራፉ ላይ ተገትራለች
‹‹እዚህ አልመጣችም…?ወይኔ ጓደኛዬ….›
‹‹አረ ተረጋጊ..ግቢ ››
ወደውስጥ አስገባትና በራፉን መልሶ ዘግቶ ተመለሰ‹‹እሺ የት ሄደች ይባላል ?አንተ ደግሞ ለምንድነው ስልክህን የማታነሳው?››
‹‹አሁን ተረጋጊና ከተቻለሽ ቆንጆ ምሳ ስሪልን››
‹‹ምን እያወራህ ነው?ፀደይ ጠፍታለች እኮ ነው የምልህ››
👍6014
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///

ዘሚካኤል እንግዳው ላይ አፍጥጦ

‹‹አይ ምንም እየገባኝ አይደለም….?››አለ

ሰውዬውም ዘሚካኤል‹‹ቁጭ በል አስረዳሀለው..››አለና ወደውስጥ ገብቶ ቀድሞ ተቀመጠ…

ፀደይ  ዘሚካኤልን እየጎተተች ይዛው መጣችና አስቀመጠችው…እሷም ተቀመጠችን ስልኳን አውጥታ ሪከርድ ላይ አደረገችና ሰውዬው የሚናገረውን ለመስማት ዝግጁ ሆነች፡፡

‹‹ምን ድረስ ታውቃላችሁ?››

‹‹እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም››ዘሚካኤል በትግስተ የለሽነት መለሰ፡፡

ፀደይ ዝም አለች‹‹ጥሩ ከመጀመሪያው ብጀምርላችሁ ችግር የለውም..እኔ እና እናትህ የልጅነት ጓደኛሞች ማለት ፍቅረኛሞች ነበርን…በጣም ነበር የምንዋደደው…..ምንጊዜም ስለመጋባትና ዕድሜ ዘመናችንን ሙሉ አብሮ ስለመኖር ነበር የምናስበው…ከዛ ድንገት አባቴ ወደአሜሪካ መሄድ አለብህ አለኝ…ብዙ ወንድሞቹ እዛ ስላሉ ሀሳቡን ላስቀይረው አልቻልኩም….አባቴን በጣም ነበር የምፈራው..ከዛ ጥያቄውን ተቀብዬ ወደአሜሪካ ሄድኩ…ለካ እሷ በወቅቱ እህትህን ፀንሳ ነበር..፡፡››

‹‹ፀንሳ ማለት …ከማን?››

‹‹ከማን ይሆናል ከእኔ ነዋ››

‹‹እና እህቴ የአንተ ልጅ ነች…?.ምንድነው የምትቀባጥረው?››

‹‹አልቀባጠርኩም..ከፈለክ አባትህን ጠይቀው …ያውቃል…እናትህ እኔ ጥያት ስለሄድኩ በጣም ተበሳጭታብኝ ስለነበር እና በዛ ላይ አርግዛ ስለነበር…ወዲያው አባትህን አገባችው…ስታገባው..ለልጇ አባት ለማግኘት አንጂ አፍቅራው አልነበረም…እሱም ይወዳት ስለነበረ ተንከባከባት….እህትህም በሰባት ወር እንደተወለደች ነበር ያሰበው…የገዛ ልጁ ነበር የምትመስለው….ስለዚህ ትርሲትን  እንደልጁ አሳደጋት..ከዛ አንተ እና ወንድምህ ተወለዳችሁ፡፡እኔም ከሀያ አመት ቆይታ በኃላ ከአሜሪካ ተመለስኩ፡፡ለእሷ የነበረኝ ፍቅር ከውስጤ ስላልበረደ ፈልጌ አገኘኋት…በጣም ተበሳጭታብኝ የነበረ ቢሆንም ታፈቅረኝ ስለነበረ በሂደት ይቅር አለቺኝ…አባትህን  ፈታ እኔን እንድተገባኝ እጨቀጭቃት ጀመር…እሷም ምንም እንኳን ከእኔ ጋር ለመጋባት በጣም ፍላጎት ቢኖራትም እናንተን መበተን ስላልፈለገች በሀሳቤ ልትስማማ አልቻለችም፡፡

እኔም እሷን ትቼ ሌላ ሴት ማግባት ብሞክርም አልቻልኩም..አቃተኝ…ከዛ በቃ አንቺ እሺ ብለሽ ባልሽን ፈተሸ ማታገቢኝ ከሆነ ቢያንስ ልጄን የማግኘት መብት አለኝ..ለልጄ አባቷ እኔ እንደሆንኩ ንገሪያት እያልኩ በዚህ መጨቃጨቅ ጀመርን፡፡እሷም ያንን ማድረግ አልችልም እያለች መከላከል ጀመረች፡፡በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን በድብቅ እየተገናኘን ፍቅራችንን እንወጣ ነበር…

‹‹ለምን ያህል ጊዜ ከአባቴ እየተደበቃችሁ ..እንደዛ አደረጋችሁ?››ግሽግሽ ባለና ጥላቻ በተጫነው ስሜት ጠየቀው፡፡

‹‹አራት ወይም አምስት አመት››መለሰለት

‹‹እና አባቴ ይሄን ሁሉ ታሪክ ሲያውቅ ነዋ ..ቀልቡን ነስቶት ያንን  ወንጀል የፈፀመው?››

‹‹አይ አይደለም…ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ እስከዛሬ ድረስ ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ  አዝናለው..እመነኝ በጉዳዩ በጣም መፀፀት ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገሬን አጥቼበታለው….፡፡ ስራዬን፤ ጤናዬን …ብዙ ብዙ ነገር…ብዙ ጊዜም ራሴን አጥፍቼ ከልጄ ትርሲት እና ከእናትህ ጎን ለመተኛት ሞክሬ ነበር..ግን በሆነ መንገድ እተርፋለው…መጨረሻ ይሄው እንደምታየኝ የአያቴ መንደር መጥቼ በዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ጀመርኩ..ትንሽም ወደእዚህ ከመጣሁ ነው ጤነኛ የሆንኩት››

‹‹ሰውዬ እኔ ያንተን ፀፀት ለመስማተ  ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም..ስለዋናው ጉዳይ ንገረኝ››

‹‹ትዝ ይለኛል ቀኑ እሁድ ነበር….በእለቱ አባትህ ሞጆ የጓደኛው ለቅሶ ስለነበረ መሄዱን እናትህ ስትነግረኝ..መኪናዬን ከአዲስአበባ አስነስቼ አዳማ ሄድኩ ፡፡እናትህን ተቀጣጥረን ስለነበር ቡቲክ አገኘኋት …እሁድ በዛ ላይ ጥዋት  ስለሆነ የገበያ ግር ግር አልነበረም.. ከዛ የተወሰነ ከቆየን በኃላ የተለመደ ጭቅጭቃችንን ጀመርን‹‹ …ለልጄ አባቷ መሆኔን ወይ ቀድመሽ ንገሪያት ወይ እነግራታለው››አልኳት፡፡

‹‹እሷ ቅጣውን በልዩ ሁኔታ ነው የምትወደው …አባትሽ ቅጣው አይደለም ብላት ልጄ በጣም ነው ምትጎዳው››አለቺኝ፡፡

‹‹ብትጎዳም ለጊዜው ነው…ከውሸት ጋር ለዘላለም ከምትኖር እውነቱን አውቃ ለትንሽ ጊዜ ብትጎዳ ይሻልል››አልኳት
በዚህ ጉዳይ ላይ ለ30 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በከረረ ሁኔታ ስንከራከር ቆየን….ከዛ የስልክ ንግግር ድምፅ ነው  ሁለታችንንም ያነቃን….

እህትህ ትርሲት ከባንኮኒው ማዶ … ፊቷ በእንባ ታጥቦ…አይኖቾ ፈጠውና  አውሬ መስላ ቆማለች..ሱቁ ውስጥ ገብታ እዛ የቆመችበት ቦታ መች እንደቆመች አናውቅም..ምን ያህሉን እንደሳማችንም አናውቅም….ከሁኔታዋ እንደሚታው ግን የሚበቃትን ያህል እንደሰማችን ያስታውቃል…ሁለታችንም በርግገን ጎን ለጎን ተጣብቀን ከተቀመጥንበት ተነሳን….

‹‹ለማን እየደወለች ነው?››ሁለታችንም ግራ ተጋባን፡፡ወዲያው ስልኩ ተነሳላትና ማውራት ጀመረች፡፡

‹‹አባዬ  ….ያንተ ልጅ አይደለሁም እንዴ…?እማዬና ውሽማዋ ሲያወሩ ሰማው…አባዬ እኔ ያንተ ልጅ ካልሆንኩ መኖር አልፈልግም…የሌላ ሰው ልጅ መሆን በጣም ነው የሚቀፈኝ…አይ አልጠብቅህም ..በጣም ነው የምወድህ….››አለችና ስልኩን ግድግዳው ላይ ወርውራ ከሱቁ ወጥታ ተፈተለከች፡፡ልንደረስባት ሞከርን ግን ወዲያው ተሰወረችብን፡፡

‹‹ወይኔ ልጄ….ወይኔ ልጄ…››እናትዬው ተርበተበተች....እኔም የምይዝው የምጨብጠው ግራ ገባኝ….ሱቁን ዘጋንና….

‹‹ወደየት ነው የሄደችው?››ስል እናትህን ጠየቅኳት፡፡‹‹እኔ ምናውቃለው..ወደቤት ከሄደች…ሄጄ ልያት››አለችኝ

‹‹በቃ ነይ መኪና ውስጥ ግቢ››ስላት

‹‹እንዴ ..አንድ ላይ ስንሄድ..?››

‹‹አሁን እኮ ነገሮች ተደበላልቀዋል…ምንፈራው ሳይሆን የምንጋፈጠው ነው››አልኳትና እየጎተትኩ መኪናዬ ውስጥ ይዣት ገባው፡፡በየመንገዱ እየፈለግናት…ልትሄድ ትችልበታለች ብላ እናቷ የጠረጠረችበት  አንድ ሁለት ቦታ አቁመን አይተን መጨረሻ ወደቤት ሄድን…መኪናውን ራቅ አድርጌ እንዳቆም አደረገችኝና…‹‹እኔ ገብቼ ልያትና ካለች እነግርሀለው..ከሌለችም ሌላ ቦታ ሄደን እንፈልጋታለን›› ብላኝ ገባች፡፡እኔም በጭንቀት እየተንቆራጠጥኩ መጠበቅ ጀመርኩ…5 ደቂቃ ..10 ደቂቃ አለፈ..ስልኬን አውጥቼ ስደውል እናትህ ሞባይል አይነሳም…ራሴን መቆጣጠር አቃተኝና የሆነው ይሁን ብዬ ወደግቢው ገባው፡፡ሳሎኑ በራፍ እንደተከፈተ ነበር…ስገባ  ልጄ ኮርኒሱ ላይ ተንጠልጥላለች..እናትህ ደግሞ የገዛ ሆዷን ላይ ቢላዋ ሽጣ ተዘርራለች፡፡ይመስለኛል እናትህ ወደቤት ስትገባ እህትህ ተሰቅላ እራሷ አጥፍታ ስታያት ወዲያው አካባቢው ላይ ያገኘችውን ቢላዋ ሆዷ ውሰጥ የሻጠችው ይመስለኛል፡፡

ከዛ ደንዝዤ የምሆነው ጠፋኝ…ምን ላድርግ ..?ልጄን ከተሰቀለችበት ለማውረድ ገመድ መቁረጫ ለመፈለግ ወደውስጥ ገብቼ መቁረጫ ይዤ ስመለስ አባትህ ከውጭ ከሳሎኑ ሲገባ አየሁት፡፡በደመነፍስ ወደ ጎሮ በራፍ ሄድኩ…ዞሬ ከግቢው ወጣሁና መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ደም እንባ እያለቀስኩ ሁኔታዎችን መከታተል ጀምርኩ፡፡ ከዛ አንተና ወንድምህ አንድ አይነት ሰማያዊ የስፖርት ልብስ ለብሳችሁ ወደቤት ስትገቡ ተመለከትኩ፡፡ ከደቂቃዎች በኃላ ፖሊሶች ሰፈሩን ወረሩት…እናንተንም አባታችሁንም ፖሊሶች ይዘዋችሁ ሲሄድ የእናትህንና የእህትህን አስከሬን በአንብላንስ ሲወሰድ ከመንገድ ማዶ መኪናዬ ውስጥ ተቀምጬ እየተመለከትኩ ነበር፡፡ ሁለቱም እራሷቸውን  እንዳጠፉ እርግጠኛ ነኝ፡፡
👍6415
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡

የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አዲስ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ አንተስ?››

‹‹እኔ በጣም ደህና ነኝ…ሚካኤል ይደውልልኛል ብዬ እየጠበቅኩ ነበር፡፡››

‹‹ይደውልልሀል..አሁን ኩማንደሩ ቀጥሮት ሊያገኘው ሄዶል …ከእሱ እንደጨረሰ እርግጠኛ ነኝ ይደውልልሀል፡፡…አታስብ ኩማንደሩ ደግሞ ያንተ አድናቂ ስለሆነ ከአባታችሁ እንድትገናኙ ሁኔታውን ያመቻቻል….በዛ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው

‹‹ጥሩ ታዲያ አንቺ ሰላም ነሽ?››

‹‹በጣም ሰላም ነኝ…ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ  ነበር››

‹‹ምን?››

‹‹ከፀዲ ጋር እንዴት ናችሁ?››

ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኋላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡

ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››

‹‹ግልፅ ሆነህ ንገረኝ…ስለእሷ ምን ታስባለህ..ማለቴ አሁንም በፊት እንደነገርከኝ ታፈቅራታለህ?››

‹‹እንዴ!እንዴት በአንድ ወር ፍቅሩ ይተናል ብለሽ አሰብሽ? እንደውም ጥሩ ነገር አነሳሽልኝ…የሆነ ቀን አመቻችቼ ካንቺ ጋር መነጋገር እፈልግ ነበር..እኔ ላገባት እፍልጋለው..በቅርብ ቀን..እና እንዴት ጠይቄ ላሳምናት የሚለውን ከእኔ ይልቅ አንቺ ስለምታውቂ እንድታማክሪኝ እፈልጋለው፡፡››

‹‹እንግዲያው እንደዛ ከሆነ ሳይረፍድብህ ፍጠን››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ያንተን ልጅ አርግዛለች..››

የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…

‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››

‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡

በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል  ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ  ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል  ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኋላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››

‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በበቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡

የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ  መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡

ፀአዳ ቤት ሲደርስ በራፏ ዝግ ነበር..ሊደውልላት አልፈለገም ፡፡ሻንጣውን አወረደና በራፏ በረንዳ ላይ አድርጎ እሱ መኪናው ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ጀመረ…ከምሽቱ አንድ ሰአት ስትመጣ እሱ መኪና ውስጥ ሻንጣው በረንዳ ላይ ሆኖ ስታየው ፍፁም ነው ግራ የተጋባችው…ምስር  እሱ መሆኑን ስታውቅ ከእናቷ ተነጥላ ወደእሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ፈጥኖ ከመኪናው ወረደና እጇቹን እንደክንፍ ዘርግቶ ጠበቃት…ተጠምጥማበት በደስታ ጉንጩን ትስመው ጀመር…
ወደቤት እንደገቡ ፀደይ‹‹ምንድነው ጉዱ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምንም ..ለጥቂት ሳምንታት እረፍት ስለሆንኩ እዚህ ከእናንተ ጋር ለመቆየት ወስኜ ነው፡፡››

‹‹እዚህ ከእኛ ጋር?››

‹‹አዎ ከእናንተ ጋር››
ህፃኖ ምስር ‹‹ታድለን…ታድለን›› እያለች መጨፈር ጀመረች፡፡

ፀአዳ ልጇ ምስር ፊት ምንም ማለት አልቻለችም.‹‹እንግዲያው እደቤትህ ዘና በል…እኔ ልብስ ልቀይር ››አለችና መኝታ ቤት ገባች፡፡ከዛ እራት ሰርታ በሉና ከሶስት ሰዓት በኃላ ምስርን አስተኝተው ነበር እንደአዲስ ጭቅጭቁን የጀመሩት፡፡

‹‹ምን እየሰራህ ነው?››

‹‹እንደምታገቢኝ ቃል ገብተሸ ቀለበት እስክታስሪልኝ ድረስ ከዚህ ቤት ወጥቼ ወደቤቴ አልመለስም››ሲል ቁርጡን ፍርጥም ብሎ ነገራት፡

‹‹ጭራሽ ማግባት? እየቀለድክ ነው፡፡››

‹‹በፍፅም …ብቀልድ ነው እንደዚህ አይነት እርምጃ የወሰድኩት፡፡››

‹‹ስማ..እኔ ካንተ ጋብቻ ፍቅር ምናምን አልፈልግም››

‹‹ታዲያ ምንድንው ምትፈልጊው?››

ትኩር ብላ አየችው….
‹‹ንገሪኝ ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው….. ?››

‹‹ካንተ ወሲብ ብቻ ይበቃኛል….ማለቴ እስከአሁን የደረግነውን ለማለት ነው …ደግሞ  አሁንም እናድረግ እያልኩህ አይደለም፡፡››

በንግግሯ ሆድን እስኪያመው ሳቀ…በመሀል ስልክ ተደወለለት ..ከወንድሙ ነበር…በጉጉት አነሳው‹‹እሺ ሚካኤል ደህና አመሸህ?››

‹‹ሰላም ነኝ…ነገ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ አዳማ መገኘት ትችላለህ?››

‹‹ምነው ?አባዬን እንድናገኝ ፈቀዱልን እንዴ?››

‹‹አዎ በጣም ደስ የሚለው ደግሞ አንድ ላይ እንድናገኘው ነው ያመቻቹልን ቅር ካላለህ አዲስንና ቅዱስንም ይዘናቸው እንሄዳለን››

‹‹አረ ቅር አይለኝም ጥሩ ሀሳብ …ግን አባዬ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ የሚሆን ይመስልሀል?››ሰሞኑን ሲብሰለሰልበት የነበረውን ስጋቱን አንስቶ ጠየቀው፡፡

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከመሞቱ በፊት ማግኘት የሚፈልገው ብቸኛ ነገር እኮ አንተን ማናገር ነው…በደስታ  ነው የሚያነባው….እንኳን በአካል አግኝተሀው አባዬ ብለህ ስጠራው ሰምቶ ይቅርና ባለፈው ፎቶህን ሳሳየው እንዴት እያገላበጠ ሲስምና ሲያለቅስ እንደነበረ እኔ ነኝ የማውቀው…በል በዛ እርግጠኛ ሁን..ምንም አትጨናነቅ፡፡››

‹‹ምን ያስፈልገዋል…?ማለት ምን ይዤለት ልሂድ?››

‹‹የሚያስፈልገወን ነገር ሁሉ አዘጋጅተናል…አንተ ደግሞ ሚፈልገውን ነገር እንጠይቀውና በሚቀጥለው ዙር ትወስድለታለህ…ደግሞ ደስ የሚለው ከቦንጋ ያመጣችሁትን ከዶ/ሩ ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ለኩማንደሩ አሰምቼው በጣም ነው ያዘነው..እናም አባዬን ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር ወስነዋል…››

‹‹በጣም የሚያስደስት ነገር ነው እየነገርከኝ ያለሀው..ወንድሜ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንክ ታውቃለህ አይደል… በጣም ነው የምኮራብህ፡፡››

ሚካኤልም እንባ እየተናነቀው‹‹እኔም በጣም ነው የምኮራብህ››አለው

‹‹በቃ እሺ …...ሶስት ሰዓት ነው ያልከኝ አይደል?፡፡››

‹‹አዎ…መድረስ ትችላለህ አይደል…?››

‹‹በደንብ እንጂ ሁለት ተኩል ደርሼ ደውልልሀለው››

‹‹ጥሩ በቃ ደህና እደር››ስልኩን ዘጋ፡፡

ንግግራቸውን ሁሉ በገረሜታ ስትሰማ የነበረችው ፀደይ‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ሁለት ተኩል ትደርሳለህ?››ስትል በፈገግታ አሾፈችበት፡፡

‹‹ትቆጪኛለሽ ብዬ ነው እንጂ እዚህ ነኝ ልለው ነበረ››

‹‹ልፋ ቢልህ ነው ….ግን ለእናንተ ደስ ብሎኛል››

‹‹ማለት?››

‹‹አንተና ወንድምህ እንዲህ እየተደዋወላችሁ በሰላም ማውራት መቻላችሁ ትልቅ ነገር ነው…አረ እንደውም ከመነጋጋርም አልፋችሁ መሞጋገስ ጀምራችኃል››

‹‹እድሜ ለአንቺ ….ባንቺ ቀናነትና ጥረት ነው ለዚህ የበቃነው….››

‹‹እኔን ማሞገሱን እንኳን ለሌላ ጊዜ አቆየው..በነገራችን ላይ የአባትህ ጉዳይ ላይ  ይግባኝ ለመጠየቅ ሚቻል ከአሆነ አንድ ጎበዝ ጠበቃ አግኝኝቼ ሁኔታውን አስረድቼው ነበር….››

‹‹በእውነት ..ታዲያ ምን አለሽ?››
👍6721👎1👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
 
ፀጋ አባቷ  እቅፍ ላይ እንዳለች   ፈገግ በማለት የራሄልን ትኩረት ለመያዝ ሞከረች፣ በዚህ ጊዜ እናቷ ጣልቃ ገብታ መናገር ጀመሩ ፡፡

‹‹ራሄል፣ ከዶክተር ኤሊያስን  ጋር እንድትተዋወቂ  እፈልጋለሁ። እሱ የፀጋ  ሐኪም ነው…ዔሊ ይህች ልጃችን ራሄል ናት።››

ዶ/ሩ በስሱ ፈገግ በማለት ‹‹ሰለአንቺ ብዙ ሰምቼያለው ..አንድ ቀን እንደምንገናኝ አምን ነበር›› በማለት እጁን ወደ እሷ ዘረጋ

ጨዋነት ያልጎደለው ፈገግታ ፈገግ አለችለት እና የዘረጋውን እጅን ጨበጠች፡፡ወላጆቿ ከእሱ ጋር አማች ለመሆን እያሴሩ እና እሱንም እያደፋፈሩት እንደሆነ ታውቃለች…ቢሆንም  የሱ ጥፋት አልነበረም።

‹‹የሞተር ሳይክሉ  ሰው ነህ አይደል?››

‹‹አዎ… ነኝ›› አላት፡፡

እጁ ሞቃታማ፣ ጣቶቹ ረዣዥም ነበሩ፣ እና ሲነካት ለረጅም ጊዜ በእንቅልፍ የመወሰድ አይነት የግንዛቤ ብልጭታ በአእምሯዋ ተንፀባረቆ ነበር….ስሜቱን አልወደደችውም። ‹‹በዛ ፍጥነት   ስታበር  ገርሞኝ ነበር››አለችው፣ትንፋሽ ወሰደችና  ‹‹ደግሞ ዶክተር መሆን እና …..››

‹‹እና  ምን?›› ከአንደበቷ ቀልቦ ጠየቃት።

‹‹ከተሸከምከው ሃላፊነት  አንፃር  ሞተር ማሽከርከር….አንድ ነገር ቢደርስብህስ?››

‹‹ለጊዜው አቅሜ የሚፈቅደው ርካሹ እና ፈጣኑ  መጓጓዣ ሞተር ነው. እና  ደግሞ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አደርጋለሁ.››ሲል መለሰላት፡፡

ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ‹‹ሁሉም የሚያቀነቅናቸው ታዋቂ የመጨረሻ ቃላቶች ናቸው…ጥንቃቄ አደርጋለው..››አለች በንዴት፡፡

በመጠኑ ደፍረስ ባሉት አይኖቹ በትኩረት ተመለከታት…ከመተዋወቃቸው እየሰጠችው ያለው ጠንከር ያለ አስተያየት ግራ አጋብቷታል…

እናትዬው  ፀጋን  ከአቶ ቸርነት  እቅፍ  ወሰድና፡፡‹‹በሉ ወደምግብ ጠረጴዛው እንሄድ….ምሳ ዝግጁ ነው››ሲሉ አወጁ፡፡

ሁሉም ወደምግብ ጠረጴዛው ተከታትለው ሄዱ፡፡ራሄል፣ የተለመደውን ቦታዋ ላይ ተቀምጣለች፣ ዔሊያስ ከእሷ ፊት ለፊት ተቀምጠ።››
አቶ ቸርነት በቀኝ  እጇቸው  የሴት  ልጇቸውን እጅ ግራ እጇቸው ደግሞ  በዔሊያስ ትከሻ  ላይ ዘረጉና። ‹‹ብዙውን ጊዜ ከምግብ በፊት እንፀልያለን››ሲሉ ለዔሊያስ ገለጹለት።

‹‹እኔ ደስተኛ ነኝ. በቤተሰቦቼ ቤትም ስርዓቱ እንዲሁ  ነው.››ሲል መለሰ፡፡አባቷ እጇን ጨምቀው ነበር፣መጸለይ ሲጀምሩ አንገቷን ዝቅ አደረገች።አባቷ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገሩ ማዳመጥ ብትጀምርም  ከጸሎቱ ጋር በልቧ መቀላቀል አልቻለችም። እሷ በሀይማኖት ስርዓት ውስጥ ተወልዳ ያደገች ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ከመስመር ወጥታለች። አምላክ  በህይወቷ ጣልቃ እንዲገባ አትፈልግም ወይም  ደግሞም እሱ ራሱም ለእሷ ደንታ እንደሌለው ታምናለች።ስለዚህ ለምን ትጨቀጭቀዋለች፡፡ ወላጆቿ በዚህ መሳኔዋ  ደስተኛ እንዳልሆኑ በደንብ ታውቃለች ቢሆንም ግን ርቀታቸውን በመጠበቃቸው ታመሰግናቸዋለች። እና ምናልባት ወደቀልቧ እንድትመለስ ዘወትር ለእሷ በድብቅ ይፀልዩላት ይሆናል፡፡

ፀሎቱ ተገባዶ በ‹‹አሜን›› እንደተዘጋ እናትዬው ‹‹በሉ እራሳችሁን አስተናግዱ ››አለቻቸው፡፡ሁሉም ፊት ለፊቱ ባለው ሳህን ላይ ፊለፊታቸው ከተደረደሩት በርካታ የምግብ  ዓይነቶች የሚፈልጉትን  መጠን መውሰድ ጀመሩ፡፡ተ

‹‹ከቻልክ ክትፎውን  አቀብለኝ››ስትል ራሄል ወደኤልያስ እያየች አጉተመተመች፣
እናትዬው የራሄልን አስተያየት ውድቅ በማድረግ እጆቿን እያወዛወዘ ‹‹እስኪ እንደአንበሳ ስጋ ማሳደድሽን አቁሚ።››በማለት ገሰፃት፡፡  ቀጠል አደረጉና ‹‹ለሚያገባሽ ሰው አዝንለታለው።››ሲሉ  አከሉበት፡፡

‹‹ደህና፣ ደስ ሚለው ነገር ፍቅረኛ  የለኝም ››አለች ራሄል፡፡
‹‹እነዚህማ የተለመዱ ቃላቷችሽ ናቸው››

እናቷ በራሄል ንግግር ተከፍተው ‹‹አንድ ቀን ያንን በብቸኝነት  የቀዘቀዘ አፓርታማሽን እርግፍ አድርገሽ ጥለሽ  እንደ ዶ/ር ኤሊያስ ቤት አይነት  ግቢ  ወዳለው ቤት ትቀይሪ ይሆናል።››ሲሉ  ምኞታቸውን ተናገሩ፡፡

እናትዬው  ወደ ዶ/ሩ  ዘወር አሉን‹‹ቤትህን በማስተካከል ላይ እንዳለህ ሰምቼያለው?››

‹‹በእውነቱ ወንድሜ ቢንያም ነው እየተከታተለው ያለው። እሱ አናጺ  ነው። ስለ ኩሽና አሰራር አንዳንድ ውሳኔዎችን እንድወስን እየጨቀጨቀኝ  ነበር, ነገር ግን ዘመናዊ ይሁን ወይም ባህላዊ ጭብጥ ይኑረው  የሚለውን ለመወሰን  እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም››

አቶ ቸርነት‹‹ራሄልን  ይዘሀት ብትሄድ ልትረዳህ ትችል ይሆናል››የሚል ሀሳብ አቀረቡለት። ዔሊያስ የራሔልን መኮሳተር ችላ በማለት እንደ ተወደደ ልጅ ፊቱ እያበራ ነው።
አንቷም ‹‹አዎ የእኔ ልጅ …በኢንቴርዬር ዲዛይን  ላይ በጣም ጎበዝ ነች።››ሲሉ  የአባትዬውን ሀሳብ ደገፉ፡፡

ራሄል ስለእሷ የተሰጠ ያለው  አስተያየት ከየት እንደመጣ አታውቅም። ወላጆቿ አፓርታማዋን  በሚጎበኙበት ጊዜ  በዕቃዎቾ፤በምንጣፎች እና በመኝታ ቤቷ ቀለም ..ብዙ ብዙ ኔጌቲቨ  የሆነ አስተያየት ሲሰጧት እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ እንደውም እናቷ ‹ጥቂት እንኳን ለስሜቷ ሳይጨነቁ ቤቷን መኖሪያ ቤት ሳይሆን ሙዚየም እንዳስመሰለችው ነግረዋት  ነበር፡፡

‹‹የምፈልገውን በትክክል  አውቃለሁ። ትልቁ ችግሬ ግን ውሳኔዎችን ለመወሰን  ጊዜ ማግኘት አለመቻሌ ነው ›› ሲል ኤሊያስ መለሰ።

ራሄል የሆነውን ነገር የተረዳች መስላ‹‹እንድትጨርሰው  የምትገፋፋህ  ሴት የለችም?››ስትል ጠየቀችው፡፡
አባቷ  ራሄልን በግንባራቸው ገፆት ፡፡
ዶ/ሩ ‹‹ለጊዜው አቋሜ ልክ እንደአንቺው ነው….ለሴት ዝግጁ አይደለሁም››ሲል መለሰ።
ራሄል ውይይቱ ወደ መሃል ከተማ የትራፊክ ፍሰት፣ የኑሮው ውድነትና   ፣ እና የፖለቲካ ውዥንብር.እና የሰላም እጦት  የመሳሰሉት ጉዳዬች ላይ ሲያተኩር እፎይ አለች፡፡
በመሀል ወደ ዶ/ሩ አትኩራ እየተመለከተች ‹‹በቅርቡ የኖብል ፋውንዴሽን አመታዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት  አለ።በዝግጅቱ ላይ መገኘትህን ማረጋገጥ አለብህ››አለችው፡፡

‹አረ ችግር የለውም..አታስቢ እገኛለው››ሲል ቃል ገባላት፡፡
እናትዬው‹‹ቀኑ ደረሰ እንዴ..?እንግዲህ በስራ ጫና ድራሽሽ ሊጠፋ ነው››ሲሉ ስጋታቸውን ገለፁላት፡፡

ራሄል  ‹‹እማዬ ደግሞ ….እኔ ብቻዬን የማደርገውን አስመሰልሺው ። አብዛኛውን ስራ የሚሰሩልኝ  ትላልቅ ሰራተኞች አሉኝ እኮ››

‹‹ነገር ግን ለሰራተኞችሽ  በቂ ውክልና አትሰጪም።ቅድስትን ለመተካት እነዚያን ሁለቱን ረዳቶች መቅጠርሽን ስሰማ  ብዙ  የስራ ጫናሽን ያቃልሉልሻል ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን አሁን እንደማየው ከሆነ የበለጠ ስራ ነው ያበዛብሽ፡፡››

‹‹ሰራተኞቹ  በጣም አዲስ ናቸው ። ፋይሎቹን ብቻ ሰጥቻቸው ሁሉንም ነገር በራሳቸው እንዲቋቋሙት  መጠበቅ አልችልም።››

‹‹ዬኒቨርሲቲ ዲግሪ ያላቸውና …በደንብ የሰለጠኑ ናቸው እኮ።››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ..ግን የፋውንዴሽኑን ስራ በተመለከተ ትንሽ ተጨማሪ ልምድ ያስፈልጋቸዋል፣ሁሉም ሰው ወደሆነ አዲስ ስራ ሲሄድ ለተወሰነ ጊዜ ከአሰራሩ ጋር እስኪለማመድ አዲስ ሆኖ መገኘት አይቀርም››ለእናቷ ሌላ የማስጠንቀቂያ እይታ ሰጠቻት። ይህን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በማያውቁት ሰው ፊት መወያየታቸውን አልወደደችውም ።
‹‹ውዴ እወድሻለሁ፣ ግን ደግሞ አውቅሻለሁ።››ሲሉ  እናትዬው በአቋማቸው መፅናታቸውን አረጋገጡላት፡፡

የራሄልን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት ‹‹እና ሁሉንም ነገር መቆጣጠር እንደምትችይ  ማሰብ ማቆም አለብሽ። አንዳንድ ነገሮችን ለእግዚአብሔርን መልቀቅ አለብሽ።››ሲሉ ንግግራቸውን ደመደሙ፡፡
50👍5
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

ከወ.ሮ ላምሮት ጋር የተደረገው ስብሰባ በጣም ረጅም ጊዜ ወስዶ ነበር እና  ውጤቱ በጣም ጥቂት የሚባል ነበር፡፡

ራሄል  በጣም የደክማት ቢሆንም  ቢሮዋ ገብታም ስራዋን ቀጥላለች፡፡

‹‹ጥሩ ነው…በብሮሹሮች ላይ ስህተቶችን አግኝቻለሁ.››

ሎዛ  ወረቀቶቹን በመካከላቸው ባለው የእንጨት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠች። ራሄል በተቀመጠችበት የቆዳ  ሶፋ ላይ ወደ ኋላ ተደግፋ ከፊቷ ያለውን  ብሮሹር  ቃኘች። ‹‹ይህ ሰማያዊ ቀለም በጣም ደማቅ ነው….እና ይህ ቢጫው ደግሞ እንዲጠናከር እፈልጋለሁ። የቀረውን ደግሞ ደውዬ አሳውቃቸዋለሁ››

‹‹ለምን ያን እኔ ራሴ  እንድከታተል አትፈቅጂልኝም?›› አለች ሎዛ

‹‹አመሰግናለሁ ሎዛ.. ግን ማየት የምፈልገውን በትክክል አውቃለሁ።››

ሎዛ  ራሷን በይሁንታ ነቀነቀች፣  ራሄል ግን  በእሷ ውሳኔ ደስተኛ እንዳልነበረች አይታለች።

‹‹ለአሁን እንዳደርግ የምትፈልጊው ሌላ ነገር አለ?››ሎዛ ጠየቀች።

‹‹ አይ ምንም የለም… በቃ እጅሽ ላይ ያሉ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጊ።››የሚል ትእዛዝ ሰጠቻት፡፡

ራሄል ወረቀቶቹን በጠረጴዛዋ ላይ አስቀመጠች እና ሎዛ ቢሮዋን ስትለቅ ወደ ሮቤል ዞረች።

‹‹ሮቤል አንተ የሆነ ነገር አንድታደርግልኝ እፈልጋለው››አለችው፡፡

ሮቤል ጎንበስ ብሎ ከቆዳው ቦርሳ ውስጥ አንድ ወረቀት አወጣና‹‹ጥቂት ስልክ ደዋውዬ ከምንጩ  ያገኘሁት  መረጃ ነው።›› በማለት ተጨማሪ ወረቀቶችን አቀበላት።

‹‹ከስብሰባው ጥቂት ቀደም ብሎ ከድርጅቱ ኃላፊ ጋር በግል ተወያይቼ ነበር።››

‹‹ጉልበቱን ከየት አመጣው?››ስትል አሞገሰችው፡፡ ራሄል ከወ.ሮ ላምሮት  ጋር ከተገናኘ በኋላ ስላከናወናቸው ውይይቶችና ስለተለዋወጦቸው ቃላቶች በማሰብ ደክሞት  ነበር።‹‹ይህ በጣም ጥሩ ነው፣ቀጣዩ እርምጃችን የበጎ አድራጎት ልገሳ ሁኔታቸውን ማረጋገጥ እና ከቻልን በእነሱ ላይ አንዳንድ ጥልቅ የጀርባ ስራዎችን መስራት ነው።››

‹‹እንደተፈጸመ ቁጠሪው.››ሲል ሮቤል ፈገግ አለ። በዚህ ጊዜ ስልኳ ጠራ…እናቷ መስመር ላይ ነበረች።‹‹እንደገና አመሰግናለሁ ሮቤል።በቅርብ ጊዜ ፋውንዴሽኑን እንደተቀላቀለ ሰው ምርጥ ስራ ሰርተሃል.›› ብላ ስልኩን አነሳች፡፡

ራሱን ነቀነቀና ዞር ብሎ ከቢሮ ወጣ።ራሄል ከኋላው ባለው ትልቅ የቆዳ ወንበር ላይ ለመቀመጥ በጠረጴዟ ዙሪያ  ዞራ ሄደች።

‹‹ጤና ይስጥልኝ እናቴ››

‹‹ደህና ነኝ የእኔ ልጅ››

‹‹ እየሮጥኩ ያለሁት ባንቺ  ጉዳይ እንደሆነ ከግምት ውስጥ በማስገባት ልትደሰቺ ይገባሻል።››ስትል ራሄል ወንበሯ ላይ በመቀመጥ ተሸከረከረች፡፡

‹‹ውዴ፣ ሁሌም በአንቺ ደስተኛ ነኝ ፡ ታውቃያለሽ?››

‹‹እማዬ አውቃለው…የቸኮሌት ኬኩ በጣም ጥሩ ነበር. ሮቤል እና ሎዛ  አመስግኚልኝ ብለዋል.››

‹‹እንደተካፈላችሁት  በማወቄ ደስተኛ ነኝ። ግን አንቺን አንድ ውለታ ልጠይቅሽ ነው። አያቶችሽ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ አድዋ ሄደን እንደንጠይቃቸው ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን  ፀጋን ይዘን ለመሄድ መድፈር አልቻልንም ።እስክንመለሰ እሷን  ለመጠበቅ ፈቃደኛ ነሸ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡ራሄል  በድንጋጤ ስልኩ ሊያመልጣት ነበር..በመከራ ነው አጥብቃ የያዘችው።

‹‹ፈቃደኛ? ምናልባት…ቆይ እስኪ ፕሮግራሜን ልመልከት››አለችና የቀጠሮ ደብተሯን ለማየት ማስታወሻ ደብተሯን ከፈተች።  በዛን ወቅት የማይሰረዝ ፕሮግራም ኖሯት ያንን እንደምክንያት ማቅረብ እንድትችል በውስጧ ፀለየች፡፡

የወሩ የመጨረሻ ቅዳሜና እሁድ…..ቢንጎ …የበጎ አድራጎት ፈንድ የመሰብሰብ ፕሮግራም አለባት። ‹‹ይቅርታ እማዬ ባልሻቸው ቀናት መሰረዝ የማልችላቸው ፕሮግራሞች አሉብኝ…በነዛ ቀናት  አመታዊ የፋውንዴሽኑ ፈንድ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አለብኝ ።››

‹‹ኦህ ውዴ፣ አያትሽ ቤት የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ብቻ ነው።›› በለሆሳስ ተነፈሰች። እና ፀጋን  ከማንም ጋር ልተዋት እችላለው? ….እንደምታውቂው እስካሁን በጣም ደካማ ነች።››

‹‹ለምን ስለችግርሽ ከዶክተር ዔሊያስ  ጋር አታወሪበትም››ስትል ሀሳብ አቀረበች።

‹‹በእርግጥ ትክክል ብለሻል .. እሱ የግል ነርሲንግ ኤጀንሲን ወይም ተመሳሳይ ነገርን ሊመክረኝ ይችላል?››

ራሄል አሰበች፤ የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማት አይገባም። ወላጆቿ ይችን ልጅ ለማሳደግ መወሰናቸው  የሷ ሀሳብ አልነበረም። እና ፀጋ ብቃት እንደሌላት እና አቅመ ቢስነት እንዲሰማት ያደረጋት የሷ ስህተት አልነበረም።

‹‹እሷን መንከባከብ ካልቻልሽ ችግር የለውም…›› እናቷ ቀጠለች‹‹እርግጠኛ ነኝ ዔሊ ፀጋን የት ልንወስደት እንደምንችል ያውቃል።››

‹‹እንደሚያውቅ  እርግጠኛ ነኝ››ስትል ራሄል ተስማማች፣ እፎይታም ተሰማት።

‹እና ስለ ዶክተር ዔሊያስ ምን አሰብሽ? ››እናትዬው እንደቀልድ ሌላ ርዕስ ከፈተች፡፡

‹‹እሱ በጣም ደስ የሚል ሰው ነው…. ከፀጋ ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት አለው ››

ከእሷ ጋር ሊጣመር የሚችልበት ምንም እድል እንደማይኖር  ለእናቷ ግልፅ ለማድረግ ጊዜው አሁን እንደሆነ ተሰማት ‹‹ግን እሱ የእኔ ምርጫ አይደለም ።››ስትል መለሰችላት፡፡

‹‹ምን አልሽ?››

‹‹እማዬ… እባክሽ አሁን ለማንም  ቢሆን ጊዜ የለኝም… ታውቂያለሽ››

‹‹ባለፉት ስምንት አመታት ውስጥ ለማንም ጊዜ አልነበራሽም። ብዙ ማህበራዊ ህይወት የለሽም። የምታደርጊው አንድ ነገር ቢኖር ስራ መስራት ብቻ ነው።››

ራሄል ወንበሯን ትንሽ እያወዛወዘች ፊቷን ከሰከሰች። ‹‹ይህን ስራ እፈልገዋለሁ እናቴ…ለህይወቴ ትርጉም የሰጠኝ ስራዬ ነው››

‹‹ከጌታ ጋር ያለሽ ግንኙነትስ? ያ እንዴት አድርጎ ነው  ስራሽን  የሚጋፋው?››ወደ ማትፈልገው ሌላ  ርዕስ ከተተቻት፡፡

‹‹‹እናቴ ሆይ፣ የእኔ ስራ የተቸገሩ ህፃናትንና  አቅመ ደካሞችን መርዳት ነው። ኢየሱስ በዚህ ምድር እንድናደርግ የሚፈልገውን ተግባር ነው እያደረኩ ያለሁት።››ራሄል እናቷን የሚያስደስት ትክክለኛ ቃላቶችን ታውቃለች እና ያለ እፍረት ተጠቀመችባቸው፡፡

‹‹ያለ እምነት ሥራ የሞተ ነው ውዴ።›› እናቷ ወደ እምነቷ ሲመጣ…ጥልቅ የማሰብ ችሎታ ስላላት  ሁሉንም የልጇን የማጭበርበሪያ ስልቶች ታውቃለች።

ራሄል በመጨረሻ ‹‹እኔ ማድረግ የምችለው  ይህን ብቻ   ነው እናቴ››አለች. ቀጠለችናም ‹‹ለወንድ ጓደኛ ጊዜ የለኝም እና ለአንድም ሰው ፍላጎት የለኝም። ስለዚህ እባካችሁ ከአሁን በኋላ የማልፈልገውን አይነት አስጨናቂ እራት ለማዘጋጀት አትሞክሩ።››ስትል ንግግሯን በመኮሳተር ደመደመች፡፡

የእናቷ ዝምታ እጅ የመስጠት ምልክት እንደሆነ ተስፋ አድርጋ ነበር።‹‹ደስተኛ ነኝ እማማ›› እናቷ ብርሃኑን እንድታይ ለማድረግ ቆርጣ ገፋችበት። ‹‹ዓላማ እና ትርጉም ያለው  ንቁ ህይወት ነው እየኖርኩ ያለሁት ። ጓደኞች አሉኝ እናም በማህበረሰብ ውስጥ  አስፈላጊ የሚባል  ስራ አለኝ። እና አንቺ እና አባዬ እና ፀጋም  አለችሁልኝ። ተጨማሪ አያስፈልገኝም።››

‹‹እሺ፣ ይቅርታ፣ አንቺና ዔሊ ትመጣጠናላችሁ ብዬ ስላሰብኩ ነው። እሱ ጥሩ እና ደግ ሰው ነው..ለዛ ነው ከእሱ መዛመድ የፈለኩት ።››

ራሄል ፊቱ ላይ ስለተመለከተችው ፈገግታ አሰበች‹ደህና፣ ለአንድ ሌላ ሴት ግሩም ባል እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ግን ያቺ ሴት እኔ አይደለሁም፣ እማማ።››

ወ.ሮ ትርሀስ ቃተቱ። ‹‹ካስከፋሁሽ ይቅርታ።››

‹‹አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጠርሺብኝ እንጂ አላስከፋሺኝም።››
58👍6
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


እሁድ የእረፍት ቀን ስለሆነ ኤልያስ ከወንድሙና ከጓደኛው ጋር ካፌ ቁጭ ብለው ቁምነገሩንም ቀልዱንም ሲጫወቱ አረፈድና ሌላ የሚሄዱበት ቦታ ስለነበር ተያይዘው ወጡ፡፡ሶስቱም የቢኒያም መኪና ወዳቆመችበት ቦታ እየተለፉ እየሄዱ ሳለ ድንገት ኤልያስ ከወንድሙ ከቢኒያም ጉሽሚያ ለማምለጥ ወደኃላው ሲሸሽ ከአንድ ውብ ሴት ጋር ተላተመ ፡፡ሴትዬዋ በእጇ የያዘችው ወረቀቶቿ ከእጆቿ ተንሸራተው ወደቁ  እና ቦርሳዋ ከተከሻዋ  ተንሸራቶ ሊወድቅባት ነበር…እሷም ተነገዳግዳ ሚዛኗን ለመሳት ስትጥር  ኤልያስ በፍጥነት ተስፈነጠረና ክንዷን ያዛት  ። ተረጋግቶ ሲያያት አይኖቹን ማመን ነው ያቃተው ።፡ራሄል ነች፡፡ ሞባይል ስልኳ አንድ ጆሮዋ ላይ ተጣብቆል…ስልክ እያወራች እንደነበር ተገነዘበ፡፡

አቀርቅራ የተበተኑ ወረቀቷቾን እያየች‹‹ምንድነው…አይንህ አያይም እንዴ? አብደሃል?››ስትል ጮኸችበት ።ከዚያም ቀና ብሎ አያት።ሀዘን  ያረበባቸው አይኖቿ እሱን ሲያዩት ፣ ንዴቷ በጥልቀት ወደ ውስጡ ዘልቆ ሲገባ ተሰማው። በልቡ ክልል ውስጥ የሆነ ቦታ ላይ የብርሃን ብልጭታ ፈነጠቀ።ድንገት ወደጎን ዞር ብላ እሱ መሆኑን ስታውቅ በንግግሯ አፈረች፡፡‹‹እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ››ብላ አጉተመተመች፣ክንዷን ወደኋላ ጎተተች። አሁንም እንደያዛት ረስቶት ነበር። ፈጠን ብሎ  ለቀቃት። ርቀቱን ጠብቆ  በጉጉት እያዩ ወደነበሩት ወንድሙ እና ጓደኛው  እየተመለከተ። ‹‹ይቅርታ አላየሁሽም….ከወንድሜ ቢኒ ጡጫ እራሴን ለማራቅ   እየሞከርኩ ነበር.››አላት፡፡

‹‹ምንም አይደለም፣ እኔም ቀልቤ  የማወራው ስልክ ላይ ስለነበር መጠንቀቅ አልቻልኩም ።›› በማለት ወረቀቶቿን ለማንሳት ጎንበስ አለች።

‹‹ቆይ እኔ ላንሳልሽ›› ብሎ እሱም ጎንበስ አለ… ሁለቱም በአንድነት እጇቸውን ወደወረቀቱ ሲሰዱ እርስ በርስ ተነካኩ ፡፡በመሀከላቸው የኤሌክትሪክ ንዝረት አይነት ቅፅበታዊ ብልጭታ ተፈጠረ፡፡

‹‹እባክህ አትጨነቅ››  የውስጥ ስሜቱን  የሚቆሰቁስ  አይነት እንደገና የሚያነቃቃ ፈጣን ፈገግታ ሰጠችው።

ወረቀቶቹን ሰብስበው ከተነሱ በኋላ‹‹ለመሆኑ እዚህ ሰፈር ምን እግር ጣለሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ለስራ ጉዳይ››ስትል አፏ ላይ የመጣላትን ምክንያት ሰጠችው፡፡

‹‹ በእረፍት ቀን ትሰሪያለሽ እንዴ?››

ራሄል ፊቷን አኮሳትራ‹‹ስራ እስካለኝ ድረስ ቀን ሳልመርጥ ነው የምሰራው..ታውቃለህ  …ሥራዬ በጣም አስፈላጊ ነው።››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹ደህና፣ በቃ እንገናኛለን።››

‹‹ተስፋ አደርጋለው።›› አለችና መንገዷን ቀጠለች ፡፡

‹‹አሁንም አለሽ ራሄል?›› ከያዘችው የሞባይል ስልክ የአንድ ወንድ ድምፅ ተሰማ። እናም ራሄል እስከአሁን ስልኳ እንዳልተቆረጠ ስትረዳ  ‹‹ ሮቤል በቃ ቆይቼ ደውልሀለው … መንገድ ላይ ያልሆነ ነገር አጋጥሞኝ ነው›› ብላ ስልኩን ዘጋችው፡፡

ከዛም እርምጃዋን ሳታቋርጥ  ወደ ዔሊያስ ዞር ብላ ተመለከተች …በተገተረበት ቆሞ እያያት ነበር ..የሆነ ውርር የሚያደርግ ስሜት ተሰማት ፡፡መንገዱን አቋርጣ ወደካፌው ታጠፈችና ከእይታው ተሰወረች፡፡

ሁኔታውን በትኩረት ሲከታተሉ የቆዩት  ቢንያም እና ጓደኛው ወደ እሱ  ሮጠው ከጎኑ ቆመ

‹‹በቀጣዬቹ አመታት ውስጥ ያለህ የሕይወት እቅድ ውስጥ  ሴት እንደሌለችበት ደጋግመህ ነግረኸኝ ነበር? ››አለው ቢኒያም፡፡

‹‹እና ታዲያ?››

‹‹እናማ ይህቺ ሴት ማን ነች?።››

ዔሊያስ  ለወንድሙ  ‹‹የህይወት እቅዴ ላይ ምንም ማስተካከያ አልተደረገበትም..ያንን ካወቅክ ይበቃል።››ብሎት ወደመኪናው ጉዞውን ቀጠለ፡፡

ወንድሙም ከኋላው ተከትሎት‹‹እቅድህን ማስተካከል ትችላለህ …በቅድሚያ ግን ብድርህን ክፈል፣ ሞተርህን ሽጥና ትክክለኛ መኪና ግዛ፣ ከዛ  ኑሮህን የምትጋራ ሴት መፈለግ ትችላለህ››አለው

ዔሊያስ ሕይወት ሁል ጊዜ እንደማይተነበይ ከግል ተሞክሮ ያውቃል ።  ዔሊ በስድስት ዓመቱ ወደ ማደጎ ቤት ለመግባት ተገዶ ነበር፡፡   በወቅቱ ጮርቃ  ልጅ ነበር  እና ስለ ተፈጥሮ ወላጆቹ የሚያውቀው ብቸኛው ነገር አባቱ ሉቃስ እናቱ ደግሞ ትእግስት እንደምትባል ብቻ ነው፡፡ስለ እነሱ ያለው የመጨረሻ ትዝታ ቤተሰቡ በአንድ ላይ ሆነው እየተጓዙ እያለ አባቱ መኪናውን መቆጣጠር ተስኖት ሲጯጯሁ  ነበር፡፡አንድ አመት ሙሉ በህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ተጣለ፡፡በዛን ተመሳሳይ ወቅት ቢኒያምም የአንድ አመት ህፃን ሆኖ በወላጇቹ ተጥሎ እዛ ማደጎ ቤት ከእሱ ጋር ነበር፣ እንደእድል ሆኖ አሳዳጊዎቻቸው ለሁለቱም ልባቸው ራራና አንድ ላይ ወደቤታቸው ወስደው እንደገዛ ልጇቻቸው ተንከባክበው አሳደጓቸው..እነሱም እርስ በርስ የሚዋደዱና የሚደጋገፉ ወንድማማቾች ሆነው አደጉ፡፡ አሳዳጊ ወላጆቻቸው ሁለቱንም በፍፁም ፍቅር እና  …በስርዓት አስተምረው ለዚህ ደረጃ አበቁዋቸው፡፡

ቀጥታ ጓደኖቾ ይጠብቋት ወደነበረው ካፌ ገባች፡፡በጠረጴዛ ዙሪያ እየተጨዋወቱ እና እየሳቁ  ካሉት ከጓደኞቿ ጋር ተቀላቀለች፡፡

‹‹ደህና ናችሁ ፣ ውድ ጓደኞቼ››

እንዴት ነሽ ንግስቲቷ›› ሜሮን ነች ቀድማ ለሰላምታዋ መልስ  የሰጠቻት፡፡ከዛ ያሬድና ሌንሳ ተከተሉ፡፡እነዚህ ሶስቱ የልጅነት የትምህርት ቤት  ጓደኞቾ ናቸው፡፡ራሄል ልጅ ሆና  ፈጣን እና ጎበዝ ተማሪ ነበረች እና በዚህ ምክንያት ሁለት ክፍል በመዝለሏ ትምህርት ቤት ከገባችባቸው ልጆች ትንሿ ነበረች።   አንድ ቀን በክፍሏ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ልጃገረዶች በመጫወቻ ስፍራው ላይ ወደ  ጥግ ወስደው  ይሳለቁባት ጀመር። እንደአጋጣሚ ሶስቱ ጓደኛሞች በአካባቢው ሲያልፉ ሁኔታውን ተመለከቱ ..ዝም ብለው ሊያልፉ አልፈለጉም…ጣልቃ ገብተው  ራሄልን በክንፋቸው ስር ከልለው ታደጓት። ከዛን በኃላ ቋሚ ጓደኞቾ ሆኑ..ይሄው እስከዛሬ በህይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ፣ የእርሷ ምስጢረኞች አማካሪዎች እና ውድ ጓደኞቿ ሆነዋል።እና  ከአራት አመት በፊት ሌንሳና ያሬድ የጓደኝነት ግንኙነታቸውን ወደፍቅር ቀይረው በመጋባት  መንታ ልጆችን ለመውለድ ችለዋል፡፡

ያሬድ  የራሄልን የተዘበራረቀ ሸሚዞን እና የተበታተነ ወረቀቷን ተመለከተና ‹‹ደህና ነሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹አዎ..ደህና ነኝ››

‹‹ቆይ ምን ሆንሽ?››ሜሮን ተቀበለችው፡፡

‹‹ከመኪናዬ ወርጄ ወደእዚህ ስመጣ ..፣ከአንድ ጓረምሳ ዶ/ር ጋር ተጋጨው ››

‹‹ምን…!ከጎረምሳ…?ወይስ ከዶክተር?››ሌንሳ ጠየቀቻት፡፡

‹‹ጓረምሳ የሆነ ዶ/ር ..ምነው ግልፅ አይለም እንዴ?››

‹‹እኔ ያልገባኝ..ጎረምሳ መሆኑን በእይታ አወቅሽ እንበል..ዶክተር መሆኑንስ?››ሜሮን ጠየቀች፡፡

‹‹ባክሽ የማውቀው ሰው ነው …የእህቴ የፀጋ  ዶክተር ነው፡፡››ሸሚዙ እንደተከፈተ፣ እና ፀጉሩ በግንባሩ ላይ ተደፍቶ  እንደነበረ  ላለማሰብ ታገለች።

ሁሉም በአንድ ላይ አስካኩባት፡፡

‹‹ስሙ ማን ነበር?››ሌንሳ በማሾፍ ጠየቀች፡፡

ራሄል ግን ጥያቄዋን በቁም ነገር ወስዳ‹‹ዓሊ››ስትል መለሰች፡፡

‹‹ኤሊ ማለት?››ያሬድ በገረሜታ ጠየቀ፡፡

‹‹ማለቴ ኤልያስ….ዶ/ር ኤልያስ››
ሌላ የህብረት ሳቅ ተከተለ፡፡

‹‹ተመልከቷት ነገሩ ስር የሰደደ ይመስላል ። የዔሊን ስም ሲነሳ  መልኳ በደቂቃ ተለወጠ›› ሜሮን  ጮኸች።

‹‹እንዴት ነው ግን…?››ለሊሴ ጠየቀቻት፡፡

‹‹ እሱ ቆንጆ ነው ማለት ይቻላል...›› ቡድኑን ዞር ብላ ተመለከተች እና በራሷ ሳቀች።‹‹እንደ ያሬድ ወንዳ ወንድ ነው›› ስትል አከለችበት፡፡
ሁሉም ሳቃቸውን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡
52👍3
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ



ራሄልም እህቷን ይዛ እቤት እንደገባች ጓደኛዋ  ሜሮን ቤት እየጠበቀቻት ነው፡፡መጀመሪያ ቀጠሮውን ለመሰረዝ ፈልጋ ነበር…በኋላ ስታስበው ግን ሴትዬዋ ለስብሰባው ትኩረት እንዳልሰጠች አድርጋ ልትረዳት እንደምትችል ስላሰበች ለመሄድ ወሰነች፡፡ ከሆስፒታል እንደተነሳች ነበር ደውላ ቤት እንድትጠብቃት የጠየቀቻት፡፡፡‹‹ቀጠሮው በጣም ወሳኝ ስለሆነ  ነው ያስቸገርኩሽ፡፡››

‹‹አረ ችግር የለውም..ያንቺ እህት ማለት እኮ የእኔ እህት ነች››አለች ሜሮን፡፡

‹‹እሱስ እውነት ነው››

‹‹አዎ ደግሞም አሪፍ የምስራች አለኝ…››

‹‹እባክሽ ንገሪኝ ቀኑን ሙሉ ስጨናነቅ ነው የዋልኩት…ፈገግ ማለት አምሮኛል››

‹‹አንድ እምቅ ችሎታ ያላት እና በነርሲንግ የሰለጠነች ሞግዚት አግኝቼልሻለው›› አለቻት….ከሁለት ቀን በፊት ለሁሉም ጓደኞቾ  ስለፀጋ ነግራቸው የሰለጠነች ሞግዚት እንዲፈልጉላት አደራ ብላቸው  ነበር፡፡

‹‹አንቺ እኮ ሕይወት አድን ነሽ›› አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ጉንጯን ሳመቻት፡፡

ወደቀጠሮ ቦታ ይዛ የምትሄደቸውን ወረቀቶች ወደ ቦርሳዋ አስገባች።

‹‹ሞግዚት ማግኘት ከቻልኩ የፀጋ ዶ/ር የሰጠውን መመሪያ በሙሉ በጥንቃቄ እንዲተገበር ማድረግ እችላለው። ውዴ  ለአሁን ፀጋን ልትጠብቂልኝ ስለወሰንሽ  ደስተኛ ነኝ። ነገሮች ሁሉ ሰላም  እንደሚሆኑ አምናለው?››

‹‹ሄይ. ታውቂያለሽ እኔ  በጣም ጥሩ ጓደኛሽ  ነኝ.››

‹‹ብቃት ያለው ሞግዚት አግኝተሸልኝማ ያንን መካድ አልችልም…  በጣም ጥሩ ጓደኛ መሆን ብቻ ሳይሆን ህይወት አድንም ነሽ።››

‹‹ጥሩ እንደዛ ከሆነ እስኪ በመጠኑ ዘና ለማለት ሞክሪ….››

ራሄል  ከወ.ሮ ላምሮት ጋር ላላት ቀጠሮ የምትጠቀምባቸውን መረጀጃዎች የያዙ ወረቀቶች እየለየች ‹‹ዘና ማለት እንኳን የምችል አይመስለኝም…ደክሞኛል… በአእምሮዬ ውስጥ ብዙ ነገሮች አሉ,››ስትል መለሰችላት፡፡ቀጥላም‹‹‹‹በፋውንዴሽን ውስጥ ነገሮች በጥሩ መንገድ እየሄዱ አይደለም ፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ለጋሾችን አጥቻለሁ አሁን የምሄድባትን ሴትዬ ከዋና ለጋሾቻችን የመጀመሪያዋ ነች….እሷን የግድ ማሳመን አለብኝ ››

‹‹ለምን ሎዛ እንድትሰራው  አታደርጊም?››

ራሄል ነገሩን በማሰብ ትንሽ ቆም ብላ ራሷን በአሉታ ነቀነቀች።‹‹ይህን ከባድ ኃላፊነት በእሷ ትከሻ ላይ መጣል አልችልም››

‹‹ስለዚህ በራስሽ ላይ ትጥያለሽ ..እሱ ችግር የለውም ማለት ነው?››

‹‹ትከሻዬ ከሷ የበለጠ ልምድ ያለው ነው›› አለች ፡፡

‹‹ጓደኛዬ ጥቂት ስራዎችን ለሌላ ሰው  ብታስተላልፊ አለም አትገለባበጥም።እና ደግሞ የህይወት ሸክማችንን የሚያቀልልን ክርስቶስ ነው….በእሱ መታመን ችግራቸንን ያቀልልናል፡፡››

‹‹እና ለምን ያቺን አሁን በስቃይ የምታለቅሰውን  ትንሽ ልጅ  እንዲህ አጎጉል አደረጋት? በኢየሱስ አላምንም ብላ ይሆን ?››በራሄል ንግግር ሜሮን  በጣም ደነገጠች፣

‹‹ራሄል .. አንቺ እኮ ከዚህ የበለጠ አስተዋይ ነሽ ››ራሄል እጇን ወደ ላይ ዘረጋች።

‹‹አዝናለሁ ስለ ኃጢአት እና ክፋት ሁሉን ነገር አውቃለሁ እናም እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በቁጥጥሩ ስር እንደሆነም አምናለው, ስለዚህ ስብከት አንዳትጀምሪኝ››

ሜሮን  የጓደኛዋን ትከሻው በፍቅር እየዳበሰች‹‹ታውቂያለሽ አይደል …?ማመን ስለማትፈልጊ ብቻ ነው. እንዲህ የምትይው…ግን እወቂ አሁንም በኢየሱስ ጥበቃ ውስጥ ነሽ …አዎ፣ በግንኙነቶች ውስጥ ህመም አለ…በሆነ ግንኙነት ተሰብረን ሊሆን ይችላል፣ ቢሆንም  ልባችንን ሁሌ ለፍቅር ክፍት መሆን አለበት ››

‹‹ደህና፣ አሁን ለልብ ጉዳዬች ጊዜ የለኝም።ደግሞ እስከአሁን ለእኔ የሚሆን ሰው አላጋጠመኝም።›› መስታወት አወጣች እና ሜካፕ እና ፀጉሯን በፍጥነት አስተካከለች።

ሜሮን ‹‹ዶ/ሩ በጣም የሚስብ ይመስለኛል››ስትል አዲስ ድንገተኛ ርዕስ ከፈተች፡፡

ራሄል የጓደኛዋን ሹፈት ችላ በማለት ቦርሳዋን አነሳችና ትከሻዋ ላይ አንጠለጠለች ፡፡

‹‹እሱ ማራኪ ነው…እንዳልኩሽ  ግን ለጊዜው ለማንም ጊዜ የለኝም ።››በማለት መለሰችላት፡፡

ራሄል ወደ በሩ ስትሄድ ሜሮን ‹‹መልካም ጊዜ ይሁንልሽ›› ብላ ጮኸች።

////
ራሄል ከሴትዬዋ ጋር እያካሄደች ያለውን ስብሰባ አንድ ሰዓት በላይ ብታሳልፍም..እስከአሁን ሙሉ በሙሉ ልታሳምናት አልቻለችም፡፡

‹‹ባለቤቴ በዚህ ገንዘብ በጣም ነው የሚያምነኝ… እናም ይህን  በትክክለኛው መንገድ ማድረግ  ነው የምፈልገው፡፡››

‹‹ይገባኛል››አለች ራሄል። ነገር ግን የባለቤቷትን  እምነትን ለመጠበቅ ምርጡ መንገድ ገንዘቡን ለትክክለኛው ዓላማ ብቻ ለሚጠቀም በጎ አድራጎት መስጠት ነው።››
ወ.ሮ ላምሮት ፈገግ አለችላት፡፡

ወ.ሮ ላምሮት ራሄልን በትኩረት አየቻትና ‹‹አባትሽን ትመስያለሽ›› አለቻት። ‹‹እሱ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የሚሰራ የእግዚአብሔር ፍቅር ሁልጊዜ ምሳሌ ነው.››ስትል አከለችበት፡፡

ራሄል መራራ ህመም ተሰማት። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከአምላክ ጋር ብዙ ጊዜ አላጠፋችም። የወ.ሮዋ  ቃላት አብዝታ ወደ ጸለየችበት፣ መጽሐፍ ቅዱሷን በሰፊው ታንብበት  ወደ ነበረችበት ጊዜ አመጣት። ቤተክርስቲያን እና እምነት የመተንፈስ ያህል የእርሷ አካል ነበር። እምነቷን መልሶ ለማግኘት እና በአምላክ ላይ መታመን ለምን እንደሚያስፈልጓት አሰበች። ››

በወ.ሮ ላምሮት ፈገግ ብላ ሰዓቷን በጥበብ ተመለከተች። ለመውጣት ጊዜው ነበር፡፡

‹‹እኔ እንዳልኩት፣ እባኮት ይህን በትክክለኛው መንገድ  ለማድረግ ትንሽ ጊዜ ስጡኝ..ያንን ብቻ ነው የምጠይቀው››አለች ራሄል፣

ወ.ሮ ላምሮት ከግዙፉ መኖሪያ ቤቷ ስትሸኛት ራሄል የመጨረሻ የማሳመኛ ንግግሯን ተናገረች‹‹እርግጠኛ ነኝ .. ባለቤቷት በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲቸኩሉ አይፈልግም ››

ነገር ግን ከወ.ሮዋ ፊት ምንም ነገር ማንበብ አልቻለችም  ፡፡ሴትዬዋን ለማሳመን የተቻላትን ሁሉ አድርጋለች..ግን ይሳካላት አይሳካላት መገመት ስላልቻለች በጣም ተበሳጨች ፣ መኪናውን አስነሳችና ወደቤቷ ነዳችው…መኪናዋን አቁማ ወደአፓርታማዋ ተጠጋች… የአሳንሰሩን ቁልፍ ተጫነች እና ገባች፤ውስጥ ያልጠበቀችውን ሰው አገኘች፡፡የቆዳ ጃኬት ለብሶ ነበር። የሞተር ሳይክል ሄልሜት በእጁ ይዟል።

‹‹ሰላም. እዚህ ምን እየሰራህ ነው?››ብላ ጠየቀችው፣ እስትንፋሶ ተቆራረጠባት፡፡

‹‹በቃ ጎራ  ብዬ ከፀጋ ጋር እንዴት እየተለማመድሽ እንዳለሽ ለማየት አስቤ ነበር።››

‹‹ጥሩ አደረክ››አለችው

‹‹ወደ ውጭ ወጥተሽ ነበር?››

‹‹አዎ ጠቃሚ ስብሰባ ነበረኝ›

‹‹እንደ ሁሉም ስብሰባዎችሽ››አለ

‹‹አይዞህ አታስብ ጓደኛዬ በጣም ብቃት ያለት ሞግዚት ነች።እርግጠኛ ነኝ እሷ ከእኔ በተሻለ  ከፀጋ ጋር ትግባባለች።››ሊፍት ሲቆም ወደ ኋላ ዞር አለላት።ራሄል ቀድማ ወጣች..ተከተላት፡፡ ኮሪደሩን እንደረገጡ  የሚያለቅስ የህፃን ድምፅ በሁለቱም ጆሮ ገባ። የመጣው ከራሷ ቤት  ነው።ሁለቱም ርምጃቸውን አፈጠኑና ተከታትለው ወደቤት ገቡ ፡፡ሜሮን የምትጮኸውን ፀጋን  ተሸክማ እቤት ውስጥ ከወዲህ ወዲያ ትሽከረከራለች፣ የልጁቷ ክንዶች በሜሮን  ጀርባ ላይ ተዝለፍልፋው ይታያሉ፡፡

ራሄል ቦርሳዋን ጥላ ወደ ጓደኛዋ ሮጣ ሄደች። ጸጋ ራሄልን እንዳየች ከሜሮን እቅፍ ውስጥ ተስፈንጥራ  እጇን ዘረጋች። እንባዋ በጉንጮቾ እየተንከባለሉ በመርገፍ ላይ ናቸው፡፡
46👍3🥰1😢1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ



ደ ሆስፒታሉ በሚወስደው መንገድ ላይ ሞተሩን እያስጎራ በመብረር ላይ ነው፡፡ ሀሳቡ ግን አሁንም ወደኋላ እየጎተተው ነው፡፡ በዚህ የሰንበት ማለዳ ወደእነራሄል ወላጆች ቤት የሄድኩት ራሄል ፀጋን እንዴት እያስተዳደረች እንደሆነ ለማየት ብቻ ነበር። ጉብኝቱ  የህፃኗ ሐኪም በመሆኔ ያደረግኩት ነው።››ሲል ለራሱ ነገረው፡

አሁን፣ ፀጉሯን  በትና  እና የደበዘዘ ቲሸርት የለበሰች እንዲት ቆንጆ ሴት በአእምሮው ሰሌዳ ላይ ብልጭ ድርግም እያለች እየረበሸችው ነው፡፡ በባዶ እግሯ እና በሰማያዊ ጂንስዋ ምን ያህል ውብ እንደሆነች  እያሰበ ነበር፣እሷ የምትኖርበትን   ቤት እንዴት ግዙፍ እንደሆነ እና ወላጆቿ ምን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው እያሰበ ነበር። እና የተከበረ የመኳንንት ዝርያ አለን ብለው የሚያስቡ ወላጇች እንዳሏት እያሰበ ነበር… እና ደግሞ እሱ ሰለወላጇቹ ምን ይሁኑ ምን የሚያውቀው ነገር እንደሌለም እያሰበ ነበር፡፡በዚህም ሆነ በዚያ ሀሳቡ በራሄል ዙሪያ ከመሽከርከር ሊያቅበው አልተቻለውም፡፡

ኤልያስ አሳዳጊ ወላጆቹ ስለስጋ ወላጇቹ ብዙ ጊዜ  አይናገሩም ወይም የበለጠ እንዲያውቅ አያበረታቱትም። ወደፊት ፀጋም ልክ እንደእሱ  ስለ  እናቷ እና አባቷ ማወቅ እንደምትፈልግ ገመተ።ስለ ፀጋ ማሰቡ በትክክል ወደ ራሄል መለሰው።ሸሩባ የተሰራው ጥቁር ፀጉሯ  ፊቷን እንዴት እንደአሳመረው እና ሀዘን ያጠላባቸው ጎላ ጎላ ያሉ አይኖቿ ከብለል ሲሉ እንዴት ልብን እንደሚያርዱ አሰበ። ሆስፒታል ደርሶ ሞተሩን ሲያቆም እንኳ ሀሳብን መግታት አልቻለም ነበር፡፡
///
ራሄል ትሁት ቁርስ ስትበላ ፊቷ ላይ የተዝረከረከውን በደረቅ ጨርቅ በጥንቃቄ ጠራረገችላት። እቃዎችን እያጣጠበች ሳለ ፀጋ ወደ በረንዳ በሮች ስትሄድ አየች። ሰራተኛዋ አለም ሁል ጊዜ መስኮቶቹን በሚያብረቀርቅ ንፅህና ነው የምትይዛቸው ፣ ዛሬ ግን እሷና ፀጋ ብቻቸውን ናቸው..ሰራተኛዋ የረፍት ቀኗ ስለሆነ ዘመድ ጥየቃ ሄዳለች።እቃ ማጠቧን እንዳጠናቀቀች..ትንሿን እህቷን ለማየት ወደበረንዳ ስትወጣ  የጸጋ ትንሽዬ  የእጅ ህትመቶች መስታወቱን ጠቅላላ አዳርሰውት ሌላ ቅርፅ ሰጥተውት አገኘች፡፡ መጀመሪያ   መልሳ ለማፅዳት ስትሞከር ፀጋ ከኋላዋ እየተከተለች መልሳ ስታቆሽሽባት…በመናደድ ፋንታ ከት ብላ ሳቀችና ማፅዳቱን እርግፍ አድርጋ ተወችው፡፡

‹‹ከአንድ በላይ ልጅ ያላቸው ሰዎች እንዴት በህይወት መቆየት ቻሉ?››ስትል ገረሜታዋን ገለፀች ፡፡ከፀጋ ጋር በቀጣይ ምን ማድረግ እንደምትችል አሰበች.. ።ሰዓቱን ተመለከተች, ከዚያም ወደ እሷ ተመለሰች. ወላጆቿ ዘወትር እሁድ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሄዱ ታውቃለች። ወጣት ሳለች ሁልጊዜ አብራቸው  ትሄድ ነበር፣  ነገር ግን እጮኛዋ ኪሩቤል ከሞተ በኋላ ወደቤተክርስቲያን መሄዱን እርግፍ አድርጋ ተወችው፡፡ ይህ ድርጊቷ ወላጆቿን በጣም እንደሚያበሳጫቸው ታውቃለች፣ እነሱ ስለሚፈልጉ ብቻ ነገሮችን ማድረግ እንዳለባት አታምንም። እሷ የራሷን ሕይወት እየመራች ነበር፣ እና እግዚአብሔር የህይወቷ አካል አይደለም።
ፀጋን ስትመለከት ግን በድንገት ተጨማሪ ሀላፊነት  እንዳለባት ተሰማት። በእርግጥ የሁለት ዓመት ልጅ ነበረች፣ … ስለግል  እምነቷ ለራሷ ውሳኔ ማድረግ እንደምትችል ብታምንም ለዚህች ልጅም ተመሳሳይ ነገር ማድረጉ ትክክል ሆኖ አልተሰማትም።ወላጇቾ ቢኖሩ ይዘዋት እንደሚሄዱ እርግጠኛ ነች፡፡

‹ስለዚህ ወደ ፀጋ ጎንበስ አለችና‹‹የእኔ ቆንጅዬ እህት .. ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ትፈልጊያለሽ?›› ብላ ጠየቀቻት ፡፡

ህፃኗ በደስታ እየዘለለች‹‹ቤተክርስትያን እንሂድ፣ ቤተክርስትያን እንሂድ››አለች ፡፡ ራሄልም ልብሷን ቀያይራ  ካለባበሰቻት በኋላ ወደቤተክርስቲያን ይዛት ሄደች፡፡

ራሄል የኮሌጅ ትምህርቷን እስካጠናቀቀች ድረስ ንቁ ተሳታፊ ነበረች።ሁሉ ነገር የተቀየረው እጮኛዋ ከሞት በኋላ ነው።እና አሁን የመቅደሱ ዙሪያ ስትመለከት፣ የልጅነትና የጉልምስና ትውስታዎች  ሁሉ ተግተልትለው  በአእምሯ ውስጥ ብልጭ ድርግም አሉባት። የዚህ ቤተክርስቲያን መዘምራን አባል ሆና ለረጅም አመት አገልግላለች ፤እዚህ መድረክ ላይ ወጥታ ስለጌታ የአዳኝነት ስራ ስትዘምር ትዝ ይላታል፡፡ ድምፆ ተስረቅራቂ የሚባል አይነት ስለነበር ብዙውን ጊዜ ድምጽ ማጉያውን ይዛ መዝምራኖችን የምትመራው እሷ ነበረች፡፡እጮኛዋ ኪሩቤልንም እዚሁ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው የተዋወቀችው፡፡እሱም ልክ እንደ እሷ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነበር….  ከዚያ ከመቀራረብና አብሮ ከመዋል ብዛት የፍቅር ስሜት በመሀከላቸው ተፈጠረ፡፡በቤተክርስቲያኒቷ ፊት ቃልኪዳን ተግባቡ …ሀይስኩል ጨረሱ  ..ኮሌጅ ገቡ….እስከዛን ድረስ ሁለቱም በእምነታቸው የፀኑ ወጣቶች ነበሩ…ሁሉን ነገር ሀይማኖቱ በሚያዘው እና ቤተሰቦቻቸው በሚደሰቱበት አግባብ ለማድረግ ነበር እቅዳቸው…ሰርጋቸውን ባደጉበትና ባገለገሉበት ቤተክርስቲያን አደባባይ ላይ ለማድረግ ነበር ውጥናቸውና ጉጉታቸውም…ግን ምን ሆነ ህልማቸውን ሊኖሩ ወራት ሲቀራቸው..፣ኪሩቤል ድንገት ከእሷ ጋር ወደተቀጣጠረበት ቦታ ሞተር ሳይክሉን እያበረረ ሲመጣ እየተክለፈለፍ በፍጥነት ከሚያበር መኪና ጋር ተላትሞ በከፍተኛ ጉዳት ሆስፒታል ገባ…ይድንልኛል..መልሶ በእግሮቹ ቆሞ እንጋባላን ብላ ሆስፒታል ደረቅ ወንበር ላይ እየተኛች አንድ ወር ከግማሽ አካባቢ አስታመመችው…ግን አልተሳካም….የኪሩቤል ነፍስ ወደፈጣሪዋ ተጠርታ ሄደች..ከዛ ወዲህ ራሄል ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ሆነች…ሆስፒታል አስጠላት…የመድሀኒት ሽታ ቀፈፋት…ቤተክርስቲያንና እምነት አንገሸገሻት..የታመመ ሰው ማየት አቃታት…ይሄው አሁን ለታናሽ እህቷ  ስትል እዚህ ያደገችበት ቤተክርስቲያን ስትመጣ ቁስሏ ሁሉ ክፉኛ ተቀሰቀሰ፡፡  እና የሚቀስፍ አይነት  ህመም ተሰማት፣ ከዚሁ ሁሉ በጣም የሚገርመው ግን ለአፍታ ያህል ኪሩቤል ምን እንደሚመስል እንኳ ማስታወስ አለመቻሏ ነው ። ከሞቱ በኋላ አብዛኛዎቹን የኪሩቤልን ምስሎች በወላጆቿ ቤት  አስቀምጧቸው  ነበር እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አልተመለከቷቸውም። በጣም ተጎድታ ነበር። አሁን ምን እንደሚሰማት ግራ ተገባች።በመጨረሻም ጓዳኛዋ ሌንሳ ከወላጆቿ እና ከሁለት መንታ ልጇቾ ጋር ተቀምጣ አየች። ራሄል ከጎኗ ሾልካ ገባች።

‹‹ቤተክርስትያን መሄድ እርግፍ አድርገሽ የተውሽ መስሎኝ ነበር›› ስትል ወደጀ ጆሮዋ ቀርባ አንሾካሾከችላት፡፡
ሌንሳ   ወደኋላ ዞረችና እያወራቻት ያለችው ራሄል መሆኗን ስታውቅ በመገረም ‹‹ራሄል እዚህ ምን እየሰራሽ ነው?›› ስትል ወደኋላ ተስባ አቀፈቻት፡፡

‹‹ፀጋን  ማምጣት እንዳለብኝ ተሰማኝ››ስትል የመጣችበትን ምክንያት ነገረቻት፡፡

‹‹እሺ በምንም ምክንያት ይሁን በምንም  እዚህ በመገኘትሽ  ደስ ብሎኛል.››
የሌንሳ ወላጆችም በደስታ ሰላም አሏት፡፡

ዝግጅቱ እናዳለቀ ፀጋን እንዳቀፈች እነ ለሌንሳን ተከትላ ወደአውደ ምህረቱ ሄደች…ከረጅም ጊዜ በፊት የምታውቃቸውን በጣም ብዙ የድሮ ጎደኞቾንና ወዳጆቾን አገኘች፡፡ ብዙ ሰው ለምን እንደጠፋች እየጠየቃት በመምጣቷ እንደተደሰቱ ይነግሯት ነበር፡፡
36👍4😁1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///

ከሰዓት በኋላ ራሄል የፀጋን ጋሪ መኪናው ውስጥ አስገባች  ። የዳይፐር ቦርሳውን ያዘች፣ሁሉንም ነገር እንዳላት ለማረጋገጥ ቦርሳውን ሁለቴ ፈትሸች፣ከዛ መኪናዋን ከወላጆቾ ጊቢ  አንቀሳቀሰችና ነዳችው፡፡
ወደእንጦጦ ፓርኩ ነው የነዳችው፡፡ይህ ሀሳብ ድንገት ነው የመጣባት፡፡ እንደደረሰች  መኪናዋን ፓርክ አደረገችና ..የጸጋን  ጋሪ አወረደች…እሷን አነሳችና ጋሪው ላይ አስቀመጠቻት….አነስተኛ ሻንጣ  አነሳችና በጀርባዋ አዘለች፡፡ከዛ ጋሪውን እየነዳች ወደፊት ቀጠለች… ስትራመድ የፓርኩ ፀጥታ፣የፀሀይ የሳሳ ሙቀት እና እርጥበት አዘል ንፋስ እና የዛፉ ቅጠሎች ሹክሹክታ በፅሞና እያዳመጠች ነው ።በርቀት ልጆችን ሲስቁ እና ሲሯሯጡ ይታያል። በቡድን የሚዝናኑ ሰዎች….ሳይክል የሚያበሩ ወጣቶች..ብዙ ብዙ ነገር  እያየች ፀጋን ወደ ዳገቱ እየገፋች ወደፊ ቀጠለች ፡፡

‹‹ሄሎ፣ ሄሎ›› ፀጋን  አላፊ አግዳሚው ሰላምታ እየሰጦት ያልፉ ጀመር...ራሄል መንገዱን በመከተል  ደስተኛ ሆና በአእምሮዋ ብዙ ነገር እያሰላሰለች ቀጥላለች..  ዛሬ ጠዋት ከኬሩቤል ሞት በፊትም በውስጦ የነበሩትን አስደሳች  የበረከት ስሜቶችን ቀስቅሶባታል ።
የሚገርመው፣  ቤተክርስቲያን ሆና የእግዚአብሔር ቃል ሲነገር መስማት፣ መዝሙር ሲዘመር አብራ መዘመር መቼም አደርገዋለው ብላ የምታስበው ጉዳይ አልነበረም ፡፡ ምናልባት ለእግዚአብሔር ሁለተኛ እድል ልትሰጥ ትፈልግ ይሆናል።

ራሄል ዳገቱን ጨርሳ ቁልቁለት እየወረደች ሳለ ድንገት ሳታስበው የፀጋ ጋሪ ከእጇ አሟልጮ አመለጣት …ጋሪው እህቷን ይዞ በራሱ ወደታች ተንደረደረ….ራሄል በድንጋጤ በድን ሆና ጮኸች…  ጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ባለው ሳሩ ውስጥ ምንም ጉዳት ሳይደርስባት ወደቀች ..ወደእሷ ስትንደረደር  ቀድሟት አንድ ሰው ፀጋ ጋር ደርሶ ጋሪውና አቃንቶ አነሳና እሷን ከጋሪው አንስቶ አቀፋት…..‹‹ወይኔ በጌታ!!!›› አለች ራሄል…..ያስገረማት ፀጋ ሳትጎዳ መትረፏ ብቻ ሳይሆን ከሷ ቀድሞ የደረሰላት ደ/ር  ኤልያስ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡‹‹ይሄ ሰውዬ ይከታተለኛል ማለት ነው…?እንደዛ ካልሆነማ እንደጠባቂ መልአክ  በየሄድኩበት ሁሉ በድንገት አላገኘውም ነበር››ስትል አሰበች
በፈገግታ እንደተዋጠ‹‹አይዞሽ ..ምንም አልሆነችም››ሲል ሊያበረታታት ሞከረ፡፡

‹‹ቆይ እዚህ እንገናኝ ብዬ መልእክት ልኬልህ ነበር እንዴ ?።››ስትል ጠየቀችው
‹‹አዎ እንደዛ መሰለኝ..ምነው ስላገኘሺኝ ደበረሽ እንዴ?››

‹‹ለምን ይደብረኛል….ገርሞኝ እንጂ››

‹‹ላስገርምሽ ስለቻልኩ ደስ ብሎኛል››

ፀጋ እጆቿን እያጨበጨበች።‹‹ቤተክርስቲያን ሂድን››አለችው ፡፡

‹‹ቤተክርስቲያን?››ምን ለማለት እንደፈለገች አልገባውም፡፡

‹‹ወላጆቼ ሁል ጊዜ እሁድ እሁድ ቤተክርስቲያን  ይዘዋት ይሄዱ ስለነበር  ቅር እንዳይላት ብዬ ጥዋት ይዣት ሄድኩ…እሱን ልትነግርህ ፈልጋ ነው››ሥትል አብራራችለት ፡፡

‹‹እና እንዴት ነበር?››
‹‹በእውነቱ  በጣም ጥሩ ነው.››
‹‹እሺ ..ወደሆነ ካፌ ሄደን አረፍ እንበል?የሆነ ነገር ልጋብዛችሁ?››አላት፡፡

‹‹አይ…. ለእኔ እና ለፀጋ መክሰስ አዘጋጅቼ ነበር… ቡና, ወተት እና ኩኪስ አለን.. ካፌ ከተማም ሰልችቶናል…የሆነ ለመብላት ጥሩና ጸጥ ያለ ምቹ ቦታ   ፈልጌ ነበር.››

‹‹ከዚህ የአስር ደቂቃ የእግር መንገድ በአንዳንድ በዛፎች የተከበበ  ወንበርና  ጠረጴዛ ያለበት ቦታ አለ። ለፀጋም  ቅርብ የሆነ የመጫወቻ ሜዳ አለ። ከፈለግሽ ላሳይሽ እችላለሁ።››
ራሄል የጠቀሰውን ቦታ ማግኘት ያን ያህል ከባድ እንደማይሆንባት ታውቃለች።አረ እንደውም የሚለው ቦታ በትክክል ትዝ ብሏታል፡፡ግን አብሯቸው እንዲሆን ፍላጎቷ ነው፡፡

‹‹ካላስቸገርንህ ደስ ይለኛል››አለችው፡፡

ችግር የለውም..ጥቂት ደቂቃ ስጡኝ ጓደኞቼን ተሰናብቼ ልምጣ አለና ወደኋላ ሄዶ አብረውት ከነበሩት ሶስት ጓደኞቹ ጋር በመሳሳቅ ጥቂት ቃላትን ከተለዋወጠ በኃላ ተመልሶ መጣና የፀጋን ጋሪ እየገፋ ወደተባለው ቦታ እየመራ ይወስዳቸው ጀመር፡፡

በአሁኑ ጊዜ ስለ ምንም ጥልቅ ነገር ማሰብ አልቻለም,ከእርሷ ጋር አብሮ ሄደ,  ከዚህች ሴት አጠገብ ሲሆን ለራሱ ሐቀኛ እንዳይሆን ታደርገዋለች፡፡ብዙውን ጊዜ ከሴቶች ጋር መነጋገር ይከብደዋል ፣ ከፊቱ ላሉት የተወሰኑ አመታት ከሴት ራሱን ለማራቅ በተለይ ቆሚ የሆነ ግንኙነት ላለመመስረት ቁርጥ ያለ ውሰኔ ወስኖ ነበር።ለምን አሁን ራሄልን እንደሚያሳድዳት እርግጠኛ አይደለም። እሷ በተለምዶ የሚማረክባት አይነት ሴት አልነበረችም። ከመጀመርያው አንስቶ ለእሷ አሉታዊ አመለካከት ቢኖርም ፣ እሷ የሚያስደንቅ ጥንካሬ ባለቤት ሆና  በሀሳቡ ውስጥ ተሰንቅራ መቆየት ችላለች ።

‹‹ስራ እንዴትነው..ማለቴ ፋውንዴሽኑ?››ሲል ጠየቃት

‹‹ጥሩ ነው…ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥሬ ገንዘብ ፍሰት ላይ ችግር አጋጥሞናል.››

‹‹ ፋውንዴሽኑ ጥሩ ለጋሾች እንዳለው ከወላጆችሽ ተረድቼ ነበር እኮ።››

‹‹በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች አዎ ትክክል ነው፣ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ አዳዲስ በጎ አድራጎት ድርጅቶችን  ገንዘብ እየጠየቁን ነው። እነዚህ ሁሉ መመርመር አለባቸው፣ ይህም ደግሞ ገንዘባቸውን ምን ላይ እንደዋለ ለማረጋገጥ ለሚፈልጉ ደንበኞችም የምናደርገው ነው። አጋጣሚ ሆኖ ደግሞ በሆነ እንግዳ ምክንያት ላለፉት ጥቂት ወራት የተወሰኑ ለጋሾችን አጥተናል።››ንግግሯን   አቁማ የይቅርታ ፈገግታ ፈገግ አለችለት ።

‹‹ይቅርታ ስለ ፋውንዴሽኑ ሳወራ መጮህ እጀምራለሁ:››

‹‹አረ ችግር የለውም..አልጮኸሽም..ደግሞ ማወቅ ያለብሽ አንቺን ማዳመጥ ሁልጊዜ አስደሳች ነው።አንድ ሰው ስለ ሚወደው ነገር   ሲናገር ሁል ጊዜ በጣም ስሜታዊ መሆኑ የሚጠበቅ ነው።››ሲላት ሳቀች።

‹‹ጓደኞቼ ከስራዬ ጋር እንደተጋባው አድርገው ያወራሉ። ፋውንዴሽኑ ለእኔ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አይረዱም። እዚያ መስራቴ ለእኔ ረድቶኛል ከጥልቅ ሀዘኔም እንዳገግም ያገዘኝ ስራዬ ነው ።››ቀና ብላ ተመለከተችው፣ ዓይኖቿ በብርታት እያበሩ ለሥራው ያላትን ቁርጠኝነት አጥርቶ ያሳይ ነበር።

የተባለበት ቦታ ደርሰው ቆሙ፡፡

‹‹በቂ  ቡና እና ተጨማሪ ስኒ አለኝ። ከእኛ ጋር ትቆያለህ አይደል?›› ስትል ጠየቀችው…  ።ለአፍታ እርግጠኛ ያልሆነች የትምህርት ቤት ልጅ ትመስላለች። ይህም ለዔሊ ግብዣዋን እንዲቀበል በቂ ማበረታቻ ሰጥቶታል።ራሄል ፌርሙሱን እና ኩባያዎቹን ስታወጣ  ትሁት ከእሱ አፈንግጣ ወደ መጫወቻ ሜዳ ሄደች።

ተመቻችተው ተቀመጡና ጫወታ ጀመሩ

‹‹ ለምን ሆስፒታሎችን ትጠያለሽ?››ሲል ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡

ራሄል ራሷን ነቀነቀች፣ ለአፍታ ያህል መልስ እንደማትሰጠው አሰበ። በኋላ ግን ጉልበቷን ወደ አገጯ ሳብ አድርጋ እጆቿን አነባብራ ማውራት ጀመረች።‹‹ከስምንት አመት በፊት በሆስፒታል ውስጥ ለአንድ ወር  ከግማሽ አሳልፌያለሁ….ኪሩቤልን እግዚአብሔር እንዳገባው  የፈቀደልኝ  የልቤ ሰው መስሎኝ ነበር…አደጋው በደረሰበት ጊዜ እንደሚድን በማመን አልጋ አጠገብ ተቀምጬ ነበር። ለስድስት ሳምንታት ያህል  እግዚያብሄር እንዲያድልንኝ ያለማቆረጥ ጸለይኩ። የሆስፒታል የመተንፈሻ መሳሪያ ድምፅ እንዴት እንደሆነ ጠንቅቄ ያወቅኩት በዛን ጊዜ ነው፣ የልብ መቆጣጠሪያውንም እንደዛው። ጸሎቴ ግን ለውጥ አላመጣም…››ድምጿ በመጨረሻው ቃል ላይ ደምቆ ተሰማ፣ እና ዔሊ ታሪኩ ወዴት እንደሚሄድ ተረዳ። በእሷ ላይ ያለውን
58👍4👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
_
__
///
‹‹ነይ የኔ ማር፣ ዝም በይ፣ ላደርቅልሽ እፈልጋለሁ።››ራሄል ትሁትን ከመታጠቢያ ገንዳው ውስጥ አውጥታ በፎጣው  ጠቀለለቻት።

ወደ ምትሄድበት የስብሰባ ቦታ ፀጋን መውሰድ እንዳለባት ወስናለች፡፡  ህጻኗን ዛሬ ከሰአት በኋላ  ለረጅም ሰዓት እንቅልፍ እንድትተኛ አድርጋ ስለነበር  ማታ ከሶስት ሰዓት በፊት   እንደማትተኛ ታውቃለች። ልብስ ልታለብሳት እየተዘጋጀች ሳለ ሕፃኗ ከንፈሯ ላይ በጥፊ  መታቻት። ትልቅ ሰው በጥፊ ያጠናገራት ነው የመሰላት‹‹አንቺ ትንሽ ድርዬ›› ብላ አጉተመተመች፡፡ ‹‹ምን ፈልገሽ ነው የምትደባደቢው?›› ጠየቀቻት፡፡

  በዛው ቅፅበት  የበሩ ደወል ጮኸ። ለመክፈት ፊቷን ስታዞር የራሄል እግር ይዛ  ታገለቻት ሳትወድ በግዷ ጎንበስ ብላ አቀፈቻት፡፡ አሁንም በፎጣው ተጠቅልላለች። ራሄል በረዥሙ ኮሪዶር ላይ ወርዳ የራሷን ክፍል አልፋ ወደ መግቢያ በር ቀረበች። መጥሪያው ከእንደገና ጮኸ…

‹‹መጣሁ፣ መጣሁ››ስትል ራሄል አጉተመተመች፣ አሁንም በደረጃው ላይ ነች።ከታች ስትደርስ የእብነበረድ ወለሉ ቅዝቃዜ በባዶ እግሯ ዘልቆ ተሰማት ፡፡በሩን በዝግታ ከፈተችው።ዶ/ር  ኤልያስ ነበረ፡፡

ወደ ውስጥ ስትጋብዘው ተንደርድራ ጉንጩ ላይ ተጣብቃ ልትስመው ፈልጋ ነበር…እንደምንም እራሷን ተቆጣጠረች፡፡
እሱ የፀጋ ሐኪም ብቻ ነው። እሱ የእህቷን ደህንነትን ሊቆጣጠር እናሊከታተል ብቻ ነው ወደቤታቸው የሚመላለሰው ። በማለት እራሷን ለማረጋጋት ጣረች፡፡ የዔሊ ሞቃታማ ሰማያዊ አይኖች ቀና ብላ ስትመለከት፣ውስጧ ተናወጠባት፡፡
‹‹ኤሊ ውሰደኝ…››ትሁት ጮኸች፣
ራሄል እህቷን ችላ ብላ ከኤልያስ ጋር ማውራቷን ቀጠለች፡፡‹‹አንዲት ብዙ ገንዘብ ለፋውንዴሽናችን የምትለግስ ሴት ማግኘት አለብኝ እና ምርጫ ስለሌለኝ ፀጋን ይዣት ልሄድ ነበር ያሰብኩት…ምን ትላለህ?››

‹‹ማታስቸግርሽ ከሆነ ምንም ችግር የለውም….››አላት

‹‹ እሱ የእኔም ስጋት ነው….ድፍረት ካልሆነብኝ ልትረዳኝ ትችላለህ?››

‹‹ለምን አይሆንም?እዚህ ሆኜ እንድጠብቅልሽ ነው የምትፈልጊው?››

‹‹ኮስተር አለችበት‹‹እሱም ይቻላል..ግን አብረኸን ብትሄድና እዛ ሴትዬዋ ጋር በምነጋርበት ሰዓት አንተ ፀጋን ታጫውትልኛለህ ብዬነበር ያሰብኩት…እኔም እንዲህ ሆና ይሆን ከሚል ስጋት ተገላግዬ በተረጋጋ መንፈስ ከሴትዬዋ ጋራ አወራለው››አለችው፡፡

ሳቀባት…….
በሳቁ ግራ ተጋባች‹‹ምነው ያልሆነ ነገር ተናገርኩ እንዴ?››

‹‹አይ…አሁን ኦርጂናል እናት እየሆንሽ እንደሆነ ስለታዘብኩ ነው…እዚህ ለእኔ እንኳን ቢሆን አምነሽ ጥለሻት ልትሄጂ አልፈቀድሽም…በእውነት ደስ ብሎኛል…አብሬችሁ እሄዳለው››

‹‹እሺ ይህችን ልጅ  ላልብሳት እና እኔም ለብሼ መጣን ….አስር ደቂቃ ታገሰን››

‹‹ችግር የለም..ሂዱ›› ፈቀደላቸው…ሄለን ፀጋን እንዳቀፈች ወደመኝታ ቤት አመራች፡፡ፀጋን ካለበሰች በኃላ የራሷን ልብስ ቀየረችና መስታወት ፊት ስትቆም ቅድም ፀጋ የመታቻት ከንፈሯ ቀልቶ እና አብጦ ተመለከተች….፡፡
ወደፀጋ ዞራ ልንቦጯን ዘርግታ እያሳየቻት ‹‹ውይ አንቺ ልጅ ….እይው እስኪ ያደረግሺኝን››
ፀጋ እየተመለከተቻት ሳቀችባት፡፡ራሄል ከፍሬጅ ውስጥ በረዶ አወጣችና ያዘችበት፡፡ከዛ ቀይ ሊፒስቲክ አወጣችና በስሱ በመቀባት የቀላውን ከንፈሯን ከሌላው ክፍል ጋር አመሳሰለችው፡፡
ከዛ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ከተረዳች በኃላ ቦርሳዋን ይዛ በአንድ እጆ  የፀጋን እጅ ጨብጣ ወደሳሎን ሄደች፡፡ተያይዘው ከቤት ወጡ፡፡

ራሄል ከንፈሯን አስጨነቀች፣ ጸጋና መሀከላቸው አድርገው ወደ  ራሄል መኪና ሲያቀኑ ልክ በቅርብ የተጋቡ ባልና ሚስቶች ይመስሉ ነበር፡፡ፀጋን ከኋላ በስርዓቱ ቀበቶዋን አሰሩላትና እነሱ ገቢና ጎን ለጎን ተቀመጡ..መኪናውን የምታሽከረክረው ራሄል ነበረች፡፡
ለተወሰነ ደቂቃ በዝምታ ነበር የተጓዙት ያሉት፡፡በፋውንዴሽኑ ውስጥ ስላሏት ችግሮች ለአንድ ሰው መንገር ፈልጋ ነበር። የሮቤል ሚስጥራዊነት አሳስቧታል።ትናንት ማታ  አነጋግራዋለች። ለምን ጥሪዋን እንዳልመለሰላት ስትጠይቀው ሞባይሉን ቤቱ ረስቶ እንደነበር  ነው የነገራት።በበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ያገኘኛቸውን መረጃዋች በማጠናከር ላይ ተጠምዷ ስለነበር ጊዜ አልነበረውም .. እሱ የሚፈልገው አንድ ነገር እንዳለ በግልፅ ነግሯታል….እሷም ልታምነው ፈለገች ነገር ግን አልቻለችም እና ዛሬ ከሰአት በኋላ በፋውንዴሽን ከኮምፒውተሯ ጋር ስትገናኝ፣ ሌላ ሰው የቢሮውን ኮምፒውተር ላይ እንደገባ አስተዋለች። መረጃዋን የሚበረብር ማን እንደሆነ ግራ ተጋብታለች፡፡

የአእምሮዋን ፍጭት ያነበበ ይመስል‹‹የምታናግሪው ሰው አለ?›› ስል ጠየቃት። ራሄል ወደ
‹‹ስለዚህ ነገር በተለምዶ ከአባቴ ጋር ነበር የምንነጋገረው፣ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ እንደምታውቀው በእናቴ ጉዳይ በጣም የተጠመደ ነው እና እሱን ማስቸገር አልፈልግም።››

‹‹የፋውንዴሽኑ ቦርድ እንዴት ነው? አይረዳዱሽም እንዴ?››

ራሄል አንገቷን በአሉታ ነቀነቀች። ‹‹አይ አሁን ያጋጠመን … ውስጣዊ ችግር ነው እነሱን ወደዚህ ጎትቼ ማስገባት አልፈልግም….እኔ በራሴ በምችለውን መንገድ መፍትሄ መፈለግ አለብኝ››

‹‹ሁሉንም ነገር በራስሽ ብቻ ማድረግ የለብሽም››ኤሊ ተቃወማት ።በዚህ ጊዜ የሚሄዱበት ቦታ ደርሰው መኪናዋን እያቆመች ነበር፡፡
ትንሽ ሳቅ ብላ‹‹በቅርብ ጊዜ ሁሉንም ነገር በራሴ የማደርገው ይመስላል››ስትል ቦርሳዋን አንጠልጥላ ከመኪናዋ ወረደች፡፡ራሄል ከመኪናው ጎን በመጣችበት ጊዜ ኤሊያስ ፀጋን ከታሰረችበት ቀበቶ እየፈታት ነበር። የዳይፐር ቦርሳውን ለራሔል ሰጣት እና በሩን ዘጋው።  ራሄል ወደ ወ.ሮ ላምሮት መግቢያ ደረጃ ሲወጡ‹‹ልክ  እንደ ትንሽ ቤተሰብ እንመስላለን››ስትል አሰበች።

መግቢያ በራፉ ላይ ደረሱና ደወሉን ተጫኑት፡፡ ‹‹ማግባት ምን አይነት ጣዕም ሊኖረው  ይችላል?››እራሷን ጠየቀች፡፡ ጋብቻ ከኪሩቤል  በኃላ ያልተጠቀመችበት ቃል ነበር።የስሙ ትዝታ የደስታ ስሜት እንዲሰማት አደረጋት፣ ከዚያም የታማኝነት መጉደል ውስጧን ሲያንቀጠቅጣት ተሰማት። እንዲህ ያሉ የቀን ህልሞችን እንድታልም ስውር ኃይል የነበረው ኪሩቤል ብቻ ነበረች። ከዚህ በፊት ወይም በኋላ ማንም ሌላ ሰው ያንን  ስሜት ሊቀሰቅስባት አልቻለም ።
ራሄል ድጋሚ ደወሉን ልትደውል ስትል በሩ በራሱ ተከፈተ። ራሄል ወደ አንድ ትልቅ አዳራሽ መሳይ ሳሎን ውስጥ ገባች ወዲያው ጥርት ያለ ሰማያዊ ቀሚስ የለበሰች ሴት ተቀበለቻት።

‹‹ወ/ሮ ላምሮት ከኋላ ባለው አትክልት ስፍራ እየጠበቀችሽ ነው።››በማለት ዘወር ብላ ወደ ሌላ በር መራቻቸው፡፡ ወደ ዔሊ ተጠግታ በሹክሹክታ  ‹‹ፀጋ ከስርህ እንድትርቅ አትፍቀድላት። ››ስትል ተናገረች፡፡ፈገግ አለላት….በፊት ፀጋን በተመለከተ እንዲህ አድርጊላት… ይሄንን ተጠንቀቂላት… እያለ የሚያጨናንቃት እሱ ነበር..አሁን ግን ይሄው በተቃራኒው ለእሱ መመሪያ እየሰጠችው ነው፡፡እያሳየች ባለችው ለውጥ በውስጡ እርካታ ተሰማው፡፡
ወ.ሮዋ ከተቀመጠችበት መድረክ መሳይ ውብ ቦታ ባሻገር በሁለት በኩል በጡብ ግድግዳ የተከበበ አበባ ሞልቶ ነበር። ወ.ሮ ላምሮት በትልቅ ዣንጥላ በተከለለ የመስታወት ጠረጴዛ ጎን ከተቀመጠችበት ልዩ ወንበር ተነስታ ‹‹ ጤና ይስጥልኝ ራሄል …በድጋሚ እንኳን ደህና መጣሽ ›› አለቻት ፡፡
53👍2👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ



ከወ.ሮ ላምሮት ቤት እንደተመለሱ ቀጥታ ወደራሄል  ወላጇቾ ቤት ነው የሄዱት፡፡ኤልያስ ቤት ድረስ አብሯቸው የመጣው በሁለት ምክንያት ነው…አንድም ሊሸኛቸው ሲሆን ሌላው ግን ጥዋት ከቤት ወጥቶ አብሯቸው ሲሄድ  ሞተር ሳይክሉን እዛው ጥሎ ስለነበረው የሄደው እሱን ለመውሰድ ነው…"ካለበለዚይ ጥዋት ወደስራ ለመግባት ታኪሲ ፍለጋ መጋፋት ሊጠበቅበት ነው…ያ ደግሞ በጣም የሚጠላው ነገር ነው፡፡

ደርሰው  ራሄል መኪናውን ፓርክ አድርጋ እንዳቆመች እሱ ፈጠን ብሎ ወረደና ፀጋን አንስቶ አቀፋት..ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷት ስለነበረ ሲያቅፍት  ልጥፍ አለችበት፡፡ራሄል ቦርሳውን አንስታ አንጠለጠለችና ተከተለቻቸው እና ወደ ግዙፍ ቤት ተከታለው ሲገቡ ጥዋት ተሰምቷት የነበረ ስሜት ተመልሷ ተሰማት…ባሏ… ተወዳጅ ልጇን አቅፎ ወደቤት ሲገቡ….ሀሳቡ የደስታ  ውስጧ በደስታ ስሜት እንዲጥለቀለቅ ስላደረጋት ‹‹እንዴት ደስ ይላል››ስትል በለሆሳሳ አንሾካሾከች፡፡ከፊት ቀደመችና ሳሎኑን ሰንጥቃ እየመራች ወደፀጋ ክፍል ይዛው ሄደች… ቶሎ ብላ ብርድ ልብሱን ገለጠችለት…ቀስ ብሎ አስተኛትና ተጋግዘው አለባበሳትና ቆመ…ተከትላው ቆመች…በመሀከላቸው ያለው ርቀት ከአንድሜትር አይበልጥም…አንደኛው ሌለኛው ላይ አፍጥጧል….በሚገርም ሁኔታ የትንፋሽ ማጠር አጋጠማት. …ቀስ እያለ ተጠጋትና እጇቹን በወገቧ ላይ አሳረፈ፡፡
ውርር የሚያደርግ ጥሩ ስሜት ተሰማት…ከዛ በምን ፍጥነት እንደሆነ ሳታውቅ ከንፈሮቹ በእሷ ከንፈር ላይ አረፉ …የራሄል አይኖች ተዘጉ፤ እና ለአፍታ ድንጋጤ ተሰማት ፣  እጆቹ በወገቧ ዙሪያ  ተጠመጠሙባት እና ወደራሱ ጎትቶ አስጠጋት። ራሄል ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ  ሙሉ በሙሉ በቀጣይ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር የማወቅ ጉጉት ተሰማት። የበለጠ ልትለጠፍበትና ልትደገፍበት ፈቀደች፡፡ ‹‹ይህ ጥሩ ሥነ ምግባር አይደለም?››በውስጧ ነበር ያሰበችው… በድንገት የከበደውን ከባቢ አየር ማቅለል ፈለገች። ለብዙ ዓመታት ሳትወድቅ ከቆየችበት ቦታ ለመመለስ ተፍጨረጨረች።

‹‹የእህቴን  ሐኪም መሳም ?››ከእቅፉ ሳትወጣ  የሹክሹክታ ድምፅ አሰማች።ወደፊቷ የተደፋውን  ፀጉሯን ወደኃላ በመመለስ አስተካከለላት፡፡ከዚያም ,  ቀስ ብሎ ከከንፈሯም ከአካሏ ተላቀቀ እና እራቅ አለ።

‹‹ ፀጋ ቅሬታ እንደማታቀርብ አምናለው››አለችና  ዓይኗን በእፍረት ደፍች፡፡  ለእሱ ያላትን መስህብ በውስጧ መቅበር እስከቻለች  ድረስ፣ እራሷን ከእሱ ለይታ ማቆየት እስከቻለች ድረስ፣ እነዚህን አዳዲስ እና አደገኛ  ስሜቶች መቋቋም እንደምትችል ታስብ ነበር።አሁን ግን?በጣም ለረጅም ጊዜ የናፈቀችውን ነገር ቀምሳለች። ከንፈሯ ላይ መች ተጠግቶ እንደተጣበቀባት  እንኳን አላወቀችውም። ፍቃዷን እና ሙሉ  ስሜቷን ለዚህ ሰው እስክትሰጥ ቅፅበት ድረስ  ልቧን በኪሩቤል የመቃብር ቦታ ለዘመናት ቀብራው ነበር፡፡ በደረሰባት ኪሳራ ተበሳጭታ ስለነበረ  ራሷን ዳግመኛ እንደዚህ ላለ ሁኔታ ለማጋለጠ ፈፅሞ እንደማትፈቅድ ቃል ገብታ ነበር። አንድን ሰው በጥልቀት ለመንከባከብ መፍቀድ ራስን ነገ በድንገት ለሚመጣ ህመም ማመቻቸት እንደሆነ ህይወት አስተምራታለች።ከዛ ስቃይ ለማገገም እና እንደገና ወደህይወት  ለመመለስ ዓመታት ፈጅቶባታል።

‹‹ይሄ ጉዳይ  በጣም ያስፈራኛል።››አለችው፡፡
አገጯን በአውራ ጣት ዳባበሳት እና ‹‹ምንም አይደለም እኔም  እፈራለሁ:: ግን  ፍርሀታችንን ለማለስለስ ብዙ ጊዜ አለን››አለና ሊያበረታታት ሞከረ፡፡
በረጅሙ ተነፈሰች፣ ከዚያም ፈገግ አለች።

ጭንቅላቷ ላይ ሳማትና ከዚያም በሹክሹክታ ‹‹ባዬ ራሄል››በማለት ክፍሉንም  ቤቱንም ለቆ ወጣ ።ራሄል እስከሳሎን ተከተለችውና  ከኋላው በሩን ዘጋች፡፡ የሞተር ሳይክሉን ድምፅ በመኪና መንገዱ ላይ ሲንደቀደቅ ሰማች። ጭንቅላቷን ቀዝቃዛው  መስታወት ላይ አስደገፈች፡፡ …በድንገት መጸለይ እንዳለባት ተሰማት።‹‹ጌታ ሆይ እሱን ጠብቀው›› አለች ‹‹ራሷን ለሌላ ሰው በዚህ መንገድ እከፍታለው ብላ ፈፅሞ አስባ አታውቅም ነበር? የፀጋ የታፈነ ጩኸት  ተሰማት…ራሷን ከተደገፈችበት  መስታወት  ቀና አደረገች እና ተንቀሳቀሰች…ከዛ ወደ ፀጋ ሄደች። እህቷን ለመከታተል ወደ ደረጃው እየሮጠች ስትሄድ፣ ቀድሞ የነበረባትን ስሜት እየሰመጠ እንደሆነ ተረዳች።
///
ዔሊያስ የቤቱን ዙሪያ ገባ ተመለከተ። ምንም ያማረ ነገር የለም። በራሱ ቤት ውስጥ በራሱ ሶፋ ላይ ተቀምጦ የነበረ ቢሆንም፣ አእምሮው ከአንድ በሰአት በፊትና በተለያት ሴት ላይ ተጣብቆ ነበር።ከአንድ ሰአት በፊት የሳማት ሴት አሁንም ልቡ ውስጥ እየተገላበጠች ነው።እንደዛ ያለ ድንገተኛ እርምጃ እንዲወስድ ያነሳሳው ምንድን ነበር?ቢያስብ ቢያስብ ሊገለፅለት አልቻለም፡፡
እረፍት አጥቶ ከሶፋው በመነሳት ቢንያም ወደተኛበት ክፍል ተራመደ… ሀሳቡ  ዋና መኝታ ቤቱ በጥቂት ቀናት ውስጥ ማለቅ እንዳለበት ሊነግረው ነበር ። ነገሮች እንዳሰበው ሚሄዱ ከሆነ እና የገንዘብ እጥረት ካላጋጠመው ቤቱ በስድስት ወር ውስጥ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋል። በእቅዱ መሰረት ቤቱን ካጠናቀቀ በኃላ ቀጣዩ እቅዱ አዲስ መኪና መግዛት ነው።  እና ከዚያ ምናልባት ይህንን ንፁህ እና በስርዓት የተቀነበበ  ህይወቱን የምትካፍለው ሴት መፈለግ ይኖርበት ይሆናል። ከአመታ በፊት  እቅዱን  በዚህ መንገድ በቅደም ተከተል ሲያስቀምጥ ሁሉም ነገር እንከን የለሽ እንደሆነ እርግጠኛ ነበር፡፡  ነገር ግን ያ ራሔል ከፊቱ ከመጋረጧ በፊት ነበር ።

የወንዱሙን ክፍል ለመክፈት እጄታውን ከያዘ በኃላ ሀሰቡን ቀየረ…ራሴ ተረብሼ ለምን እሱን እረብሸዋለው..በማለት ወደኃላ ተመለሰና ወደራሱ መኝታክፍል ገባ፡፡የልብሱን መሳቢያ ከፍቶ ከአሳዳጊ ወላጆቹ ቤት ያመጣውን የስጋ ወላጇቹን የፎቶ ሳጥን አወጣ ፡፡ራሄል ያቀረበችለትን ሀሳብ በድጋሚ አሰበበት።  ምናልባት አሳዳጊዎቹ ይሄንን የወላጆቹን ፎቶ ከእሱ ለማራቅ ጥሩ ምክንያቶች ነበሯቸው።በወላጆቹ ፊት ላይ የራሱን አሻራ ለማግኘት እየሞከረ ፎቶውን አገላብጧ ተመለከተ። አገጩን በእናቱ፣ ዓይኖቹ በአባቱ መልክ ላይ በጨረፍታ የተመለከተ መስሎት ነበር። ወይም ምናልባት ምኞት እንደዛ ስለሆነ ይሆናል፡፡ ፡፡እሱ እንደ አብዛኛው የማደጎ ልጆች ፣ስለ ወላጆቹ  ይበልጥ ለመማር  እና ለማወቅ ፍላጎት ነበረው ።እሱን በተመለከተ  በህፃናት ማሳደጊያ ተቋሙ ውስጥ ያለው ፋይል ውድ የሆኑ ጥቂት መረጃዎችን የያዘ ሲሆን አንዳንድ ነገሮችን እንዲያውቅ አድርገውታል፡፡ታዲያ ለምን መርካት አልቻለም?

ራሄል የማንቂያ ሰዓቱን ላይ ባለማመን አፈጠጠች።እንቅልፍ አልወስዳት ብሎ  ከግራ ወደቀኝ እየተገላበጠች ለአንድ ሰአት ተሰቃየች… የሰዓቱ መንቀርፈፍ የዘለአለም መሰላት። ደጋግማ  ከኤሊ ጋር ስታጫውተው የነበረውን ትዕይንት አዲስ እንደወጣ ተወዳጅ ፊልም ደጋግማ በምልሰት በማሰብ  አጣጣመችው፣ የከንፈሮቹን ንክኪ እንደገና ተሰማት።መላልሳ ባሰበችው ቁጥር በእያንዳንዱ ትውስታ  አዲስ ስሜት ይሰማት ነበር። በቀጣይ ምንድነው የሚሆነው….?እራሷን ትጠይቃለች….አእምሯዋ ለጥያቄዋ መልስ ከመስጠት ይልቅ ግራ መጋባት ውስጥ  አሽቀንጥሮ ይጥላታል፡፡
ያለፈውን የልቧን ጭለማ ጓዝ  እንዴት መልቀቅ እንዳለባት እስከአሁን አላወቀችም፣ አልደፈረችም።
46👍9👏2