#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል
....ከቤተሰቦቼ ጋር የነበረኝ ግንኙነት እምብዛም ሳያፈነግጥና ሳይቀርብ፣
ሳይጥምና ሳይሆመጥጥ ቀጠለ የወዲያነሽ አንድ ዓመት ከመንፈቋ እንደ አንድ የደስታ ቀን ፈጥኖ ዐለፈ፡፡ አንድ ቀን እሑድ ከሰዓት በኋላ ከአንድ ጓደኛዬ
የተዋስኩትን መቅረፀ ትርዒት (ካሜራ ወይም ፎቶ ማንሻ ይዤ ወደ ዕጓላ
ማውታ ሄድኩ
ከዚያ ቀደም ሲል ከወሰድኩለት ልብሶች መካከል ጥሩዋን ልብስ አልብሽ አነሣሁትና እንዴት እንደሚደርሳት ቀደም ብዪ ጨርሼ ስለነበር በሳምንቱ እሑድ
የልጇን ፎቶ ይዤ በጉልላት መኪና ወህኒ ቤት ሄድኩ። እንደ ተለመደው !
፣አስጠራኋት፡፡ የአጥሩን አግዳሚ ዕንጨት ተደግፋ ጥቂት አወራራን ድንገት !ሳታስበው ፎቶግራፉን ከኪሴ መዥረጥ አደረግሁና «በይ እስኪ በቃሽ እዪና ጥገቢው፡ ነጋ ጠባ፣ ልጄ! ልጄ ስትይ!...» ብዬ በወታደሪቱ ኣስተላላፊነት
አቀበልኳት፡፡ የወረቀቱን ግራ ቀኝ ጠርዝ በሁለት እጆቿ ይዛ ትኩር ብላ
ተመለከተችው:: ፊቷ ላይ ስታሸበሽብ የቆየችው ኮስማና ፈገግታ ደብዛዋ ጠፋ።
ወዲያው ብርሃኗ በጥቅጥቅ ጭጋግ እንደ ፈዘዘ ጨረቃ ፈዘዘች። እንባዋ
በዐይኖቿ ዙሪያ ግጥም አለ፡፡ አቀረቀረች። በሰንበሌጥ ላይ እየተንኳላላች እንደምትወርድ ጠፈጠፍ እንባዋ ጉንጯን ሳይነካ ከትንሿ ወረቀት ላይ ተንጠባጠበ።
ከሩኅሩኅ የእናትነቷ ባሕሪ የመነጨ የፍቅር ኩልልታ ስለነበር ለመጪው
ጊዜ የሚቀመጥ የትዝታ ጥሪት አስቀመጥኩ፡፡ ደግማ ደጋግማ ሥዕሉን ሳመች።እምብዛም ነገሬ ሳትለኝና እህ! ብላ ሳታዳምጠኝ ተሰናብቻት ተመለስኩ።
ከሌላ ስድስት ወር በኋላ የወዲ ያነሽ ሁለት ዓመት ሞላት።
እሑድ ከሰዓት በኋላ ነበር፡፡ የዕለቱን ጋዜጣ እያነበብኩ እንግዳ መቀበያ
ክፍል ውስጥ ተቀምጬ ሳለሁ የውብነሽ አጠገቤ ተቀመጠች። የያዘችውን
የአማርኛ ሰዋሰው መጽሐፍ እንደተገለጠ አጭሯ ክብ ጠረጴዛ ላይ ዘረጋችው።
ዐይኔ ተወርውራ የጊዜ ተውሳከ ግሥ የሚለውን ርዕስ አየች። ለነገርና
ለወሬ ማነሣሻ ይሆነኝ ዘንድ «ይልቅስ የአኳኋንና የሁኔታን ተውሳከ ግሥ
አታጠኚም» ብዬ መጽሐፉ ውስጥ የማነበው ያለኝ ይመስል አገላብጬ
አስቀመጥኩት። «እኔ የጊዜ ተውሳከ ግሥ አልዘለቅ ብሎኛል። አንተ ደግሞ
ሌላውን ትለኛልሀ» አለችና እጄ ላይ የነበረውን ጋዜጣ ወስዳ የመጀመሪያን ገጽ አርእስቶች በለሆሳስ አነበበች፡፡
«ሥራ አለብሽ እንዴ የውቢ? ከሌለብሽ አንድ ቦታ ደረስ ብለን እንምጣ» ብዬ ጸጉሬን አሻሸሁት፡፡ ጋዜጣውን አጣጥፋ አስቀመጠችው:: «እሺ እንሂድ፡፡ ይህን ማታም ቢሆን ልፈጽመው እችላለሁ» ብላ ከንፈሯን በምላሷ እያራሰች።
«ምንም እንኳ ለጊዜው አሳዛኝ መስሎ እንደሚታይሽ ባውቅም የኋላ ኋላ
ግን ያስደስትሽ ይሆናል» ብዩ ኩራትን ለመግለጽ በሚያስችል ወፍራም ደርባባ
ድምፅ ተናገርኩ። ካንተ ጋር ከሆንኩ ምን ያሳዝነኛል? በመጨረሻ የሚያስደስተኝ
ነገር ሁሉ ደስ ይለኛል፡፡ እንሂድ ካልክ ልብሴን ልቀያይርና እንሂድ» ብላ ተነሣች፡፡ እንዲሁ ገባ እንዳለች ዘርፈጥ ብላ የተቀመጠችበት ቀሚሷ ከበስተኋላዋ
ልሙጥነቱ ጠፍቶ ወደ ልዩ ልዩ አቅጣጫ የተሰበጣጠረ ጭምድ መስመሮች
ሠርቷል። ልብሷን ለመቀያየር ወደ መኝታ ቤት ስትገባ እኔም ጸጉሬን ለማበጠር
ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡
የልብሴን መስተካከል በመስተዋት ከተመለከትኩ በኋላ ጸጉሬን በደረቁ
እበጥሬው ወጣሁ፡፡ ደረጃውን ወርጀ እንደ ጨረስኩ ደረሰችብኝ።
ምንም እንኳ ወዴት እንደምንሄድ ባታውቅም «የምንሔድበት ቦታ ብዙ
ሰዎች አለበት እንዴ?» ብላ ጠየቀችኝ፡፡ «ማንም የለም። የምንሄደው አንድ እሳዛኝ
ሰው ለማየት ነው» ብዬ አለባበስና አረማመዷን እያየሁ መንገድ ገባን፡፡ ደማም ወጣትነቷና እንስታዊ ውብ ቅርጺ ማራኪነት ሰጥቷታል፡፡ ፈገግ ስትል ፍልቅቅ የሚሉት ነጫጭ ውብ ጥርሶቿ ከደም ግባቷ ጋር የአተር አበባ አስመስለዋታል፡፡
እግረ መንገዳችንን ልዩ ልዩ የሚባሉ ነገሮች ገዛሁላት። ዐሥር ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በታክሲ ዕጓለ ማውታ ደረስን፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት
አስከትዩ በመሄዴ ያ ዘወትር ብቻዬን ስመላለስ የሚያየኝ ዘበኛ የውብነሽን
በማየቱ የመገረም ፈገግታ ታየበት።
አብዛኛውን ጊዜ ከቤቱ ታዛ አካባቢ ከብዙ ከልጆች ጋር ተቀምጦ ሲጫወት ከሩቁ የማውቀው በልብሱ ስለነበር ሜዳው መኻል ቆም እያልኩ የቢቶቹን የፊት ዙሪያ ተመለከትኩ፡፡ ብዙ ልጆች ጨዋታቸውንና ልፊያቸውን እየተዉ አዩን፡፡ ወደ መኝታ ክፍሉ ይዣት ገባሁ። እሱኑ ከሚያካክሉ ሁለት ልጆች ጋር ወለሉ ላይ ተቀምጦ እየተኮላተፈ ይጫወታል። ሁለቱ ልጆች መለስ ብለው ካዩን በኋላ ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡ የእኔ ልጅ ዐይኖች ግን እኔ ላይ
ተተከሉ፡፡ ጎንበስ ብዪ አነሣሁት፡፡
አባባና እማማ የሚባሉ ቃላት የማያውቀው፣ የወላጅ ፍቅር ያልቀመሰው
ልጄ እንደ ወፍ ዘራሽ የመስክ አበባ ያምራል። ለምን ወደ ዕጓለ ማውታ እንደ
መጣች ግራ የገባት የውብነሽ በመጠኑ ደንገጥ አለች፡፡ ወደ እርስዋ ዞሬ ትከሻዋን
ቸብ ካደረግሁዋት በኋላ እስኪ ይህን ልጅ ተመልከችው የውብነሽ ቆንጆ ልጅ
አይደለም እንዴ? ብዬ ጠየቅኋት። እ..ብላ ዝም አለች።
ሰውነቷ በጥርጣሬና በሐሳብ የተጠመደ መሰለ፡ ድንገት ከእንቅልፏ ነቅታ ባጋጣሚ ያየችው ይመስል ሁለት እጆቿን ዘርግታ «እውይ እማምዬ ማማሩ! ደስ ማለቱ?» ብላ ከእጁ ላይ ወስዳ ታቀፈችው፡፡
በፊቱ ላይ አንዳችም ሌላ ለውጥ ሳይታይና ፈገግታው ሳይቀንስ ዝርግፍ
ብሉ ወደ እርሷ በመሄዱ በጣም ደስ አለኝ፡፡ እንዲያውም እዚያች ጠባብ ደረቷ
ላይ ልጥቅ አለ፡፡ ነገር ግን ልጄን ለመጀመሪያ ጊዜ ያቺ የማፈቅራትና
የምንሰፈሰፍላት የወዲያዬ ሳትሆን እኅቴ አቅፋው በማየቴ በፋይዳ የለሽ ጥላቻ
ተናደድኩ፡፡ ጉንጮቹን ሳም ሳም ካደረገች በኋላ ፊቷን ወደ እኔ መለስ አድርጋ
<<የማን ልጅ ነው ?» ብላ በጓጓ ስሜት ጠየቀችኝ። የምናገረው እውነተኛና ርግጠኛ እንዲመስል ለመመለስ የማሰላሰያ ጊዜ አልወሰድኩም፡፡ «አንቺ የማታውቂው አንድ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ የዚህ ልጅ አባት ማለቴ ነው። ትዝ እይልሽም ይሆናል እንጂ እኛም ቤት አንድ ሁለት ቀን ያህል መጥቶ ነበር» ካልኩ በኋላ የነገሩን
ድምጥማጥ ይበልጥ ለማጥፋት «ነገር ግን ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት
በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሞቷል፡፡ ልጁ ግን ለጊዜው አሳዳጊ ዘመድ በማጣቱ
ይኸው እዚህ በምታይው ሁኔታ በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ልጅ አባት በጣም
ግሩም ሰው ስለ ነበር እሱን በማሰብና ለልጁ በማዘን ብቻ አልፎ አልፎ ብቅ
እያልኩ እጠይቀዋለሁ፡፡ ጉልላትም አንዳንድ ቀን እየመጣ ያየዋል» ብዬ ዋሸኋት፡፡ግንባሩን ሁለት ጊዜ ያህል ስማ ውብ ዐይኖቹን ባንጸባራቂ ሸጋ ዐይኖቿ ትኩር ብላ ተመለከተቻቸው::
«ምነው አንተም እንዲህ የሚያምርና የሚያስጐመዥ ልጅ በነበረህ» ብላ
እንደ ወይን እሽት የሚያስጐመዡትን ጉንጮቹን ሳመቻቸው:: ንግግሯ ለጊዜው
ረግቶና በርዶ የቆየውን የሕሊናዬን ባሕር በብስጭት ማዕበል አረሰው፡፡
“ምናልባት ሚስት ባገባ ማስቴን በርግዝናዋ ወራት ከቤት አታባርሯት
እንደሆነ ነዋ እንዲህ ያለ ልጅ ማግኘት የሚቻለው» ብዩ በሽሙጥ መለስኩላት።
ድንገተኛው የንግግሬ ይዘት ፊቷን አስቀጨመው:: ልጁን ከሰጠችኝ በኋላ
አንገቷን ስብራ አቀረቀረች። ከጥቂት ዝምታ በኋላ ከወለሉ ላይ ቃላት
እየለቃቀመች ትናገር ይመስል ወለሉን እያየች «ያ ያለፈው ሁሉ ሌላ ጉዳይ
ነው፡፡ የማይገናኙ ነገሮች አታገናኝ እኔን ምን አድርጊ ትለኛለህ? አንተ ከእኔ
የበለጠ ብልህ መሆንህን ዐውቃለሁ አባታችን ቢሰማ ኖሮ በአንተና በእርሱ
መካከል ትልቅ ጠብና ማለቂያ የሌለው

👍4
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ስድስት ወራት አለፉ። ጌትነት የስድስት ወር ደሞዙን በላ፡፡ በዚች አጭር ጊዜ ውስጥ ራሱን በብዙ ነገር ቀየረ። አዲስ ልብስም ገዛ፣ ዩኒቨርሲቲ በሶሻል ሳይንስ "አካውንቲንግ ዲፓርትመንት" ትምህርቱን
ጀመረ። በወር ከሚያገኘው ሁለት መቶ ብር ደመወዝ ላይ ለእናቱ ተቆራጭ አድርጎላት ለአባቱ የገባውን የአደራ ቃል ለማክበርና ትምህርቱን በሚገባ በመከታተል በመጀመሪያው ሰሚስተር ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ቻለ። በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ስም ዝርዝር በሚለጠፍበት ሠሌዳ ላይ የጌትነትን ማንነት ለማያውቁት ሁሉ አስተዋወቀ። "እንኳ” ደስ አላችሁ!!" በሚለው ማስታወቂያ ስር ስማቸው ከተዘረዘረው ጥቂት ተማሪዎች መካከል ጌትነት መኩሪያ ግንባር ቀደሙ
ሆነ፡፡ በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች "ኤ" በማገኘቱ ስሙ በግሬት ዲስቲንክሽን ሊስት ውስጥ ተካተተ፡፡ የክፍሉ ተማሪዎች “እሱ ማን ነው?" ብለው ውስጥ ለውስጥ ሲነጋገሩበት ከረሙ:: በኋላም እሱ አንገቱን የደፋው፣ እሱ ትህትና ያልጎደለው፣ እሱ ብቻውን ገብቶ ብቻውን የሚወጣው በመጨረሻ ወንበር ላይ የሚቀመጠው ያልጠበቁት ሰው ሆኖ
አገኙት፡፡ በአብዛኛዎቹ ዘንድ በአድናቆት መታየት ጀመረ። ከሁሉ የበለጠ ስለሱ ማንነት ለማወቅ የተጨነቀችው ግን አማረች ነበረች፡፡ አማረች በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ በሂሳብ ሠራተኛነት ተቀጥራ የምትሰራ በትምህርቱ ጎበዝ የሆነ ስው የምትወድ ቆንጆ ልጅ ናት። ያንን ከፍተኛ ፉክክር ያለበትን የዩኒቨርሲቲ ህይወት ለመምራት ተማሪ እርስ በርሱ
ይፈላለጋል፡፡ በተለይ ጎበዝ ተማሪ አድኖ ለመያዝ ሩጫው ብዙ ነው። ለዚህ ነበር ያንን አመርቂ ውጤት አምጥቶ ለአካውንቲንግ የመጀመሪያ አመት የዲግሪ ተማሪዎች ቁንጮ የሆነውን “እንኳ” ደስ አለህ” የተባለውን የክፍሏን ተማሪ ማንነት ለማወቅ የተጣደፈችው። ብዙ ጊዜ አልወሰደባትም። አወቀችው፡፡አማረች የቀይ ዳማ ናት። ሰውነቷ ሞላ ቁመትዋ ዘለግ ያለ ፀጉርዋ እንደ ስንዴ ነዶ ጀርባዋ ላይ ዘፍ ያለ እንደ ስሟ
መልኳ የሚያምር፡፡ የመጀመሪያው ትምህርት ክፍለ ጊዜ ደርሷል። የዛ
ሬውን 'ሌክቸር የሚስጠው መምህር ዘግይቶ ነበር፡፡ አማረች ሆን ብላ ያንን ጎበዝ ተማሪ፣ ያንን ቁመቱ ዘንከት ያለ የሚስብ ልጅ ልትተዋወቀው ፈለገች፡፡ በቀጥታ ሄደችና ከአጠገቡ ባለው ባዶ ወንበር ላይ ዐይኖቿ” ተከለች።ሌሎቹ ተማሪዎች ደብተሮቻቸውን ገልጠው መምህራቸውን በመጠባበቅ ላይ ነበሩ፡፡
"ሰው አለው?" በጣቷ ባዶውን ቦታ እየጠቆመች በፈገግታ ተጥለቅልቃ
ጠየቀችው፡፡ ቀና ብሎ አያት። ደነገጠ፡፡
"የለው...እ? አለው!" ከሩቁ የሚጠላት ልጅ. በአብዛኛው መልኳ ሸዋዬን
የምትመስለው ልጅ.. ቀድሞውኑ ሲያያት ያልወደዳት ልጅ የምትቀመጥበትን የፊት ወንበር ትታ እሱ አጠገብ ከኋላ ለመቀመጥ መፈለጓ ድንገተኛ ሆኖበት መልሱን ለመስጠት ተደነጋገረው፡፡ የልጁ ሁኔታ አማረችን ገረማት። ሰው የሌለበትን ወንበር አለበት በማለት አሳፈራት። ማንም
እንደዚህ አሳፍሯት አያውቅም፡፡ እየሳቀችና እየተገላመጠች ወደ ቀድሞ
ቦታዋ ሹክክ ብላ ተመለሰች። "እሽ" ብላ አፍራ ምልስ ስትል አሳዘነችውና ተፀፅቶ ራሱን ወቀሰ፡፡ ለምን ያንን ቦታ እንደፈለገችው ገርሞት በዐይኖቹ ተከተላት።
የትምህርቱ ክፍለ ጊዜ አብቅቶ መውጣት ሲጀምሩ አማረች ቀስ ብላ ጭለማውን ተገን አድርጋ የጌትነትን እንቅስቃሴ ትከታተል ነበር። የዩኒቨርሲቲውን ምድረ ግቢ እንደለቀቀ ግራ ቀኝ ሳይል ታክሲውን ይዞ በረረ፡፡ በሚቀጥለውም በወዲያኛው ቀንም ተከታተለችው። ብቻውን እየወጣ ታክሲውን ተሳፍሮ ይከንፋል። ባደረገችው ተደጋጋሚ ጥናት የሴትም ሆነ የወንድ ጓደኛ እንደሌለው አረጋገጠች። አማረች በምቾት ያደገች የሚያምር ተክለ ቁመና ያላት የጠበቃው የአቶ በልሁ ወዳጄነህ
የመጀመሪያ ልጅ ናት። ከሁሉ የበለጠ የሚስበው ውብ ተክለ ቁመናዋ ነው። አነስ አነስ ያሉት ሳቂታ ዐይኖቿ ጉርድ ያለው አፍንጫዋ ከትንሿ ክብ ፊቷ ጋር በህብረት ሲታዩ በትልቅ ሰውነት ላይ የተቀመጠ የህፃን ልጅ ፊት ያስመስላታል፡፡ አማረች ከቁንጅናዋ ይልቅ የደስ ደሷ ከሩቁ ይጣራል። ጉንጮቿ እንጆሪ ይመስላሉ፡፡ ጌትነት እንደዚያ ይጥላት እንጂ ብዙዎቹ ወንዶች ሲያይዋት ጉሮሯቸው እስከሚጮህ ድረስ ምራቃቸውን ይውጣሉ፡፡ አቤት በተለይ ሱሪ ለብሳ የመጣች ዕለት! በዐይኖቻቸው
ሱሪዋን አውልቀው ያንን የሚገላበጥ ዳሌዋን በምናብ እየቃኙ በስሜት
ከወንድነታቸው ጋር ሲታገሉ ይውላሉ። ያያት ወንድ ሁሉ ቢመኛትም አማረች ግን ቁጥብ ነበረች፡፡ በቀላሉ የምትገኝ
አወጣ የተባለ ወንድ ሎተሪ እንደወጣለት ተደርጎ የሚጋነንበት ሁኔታ ነበር፡፡ ሲበዛ ፈታኝ ሰው ነች። ይሄ ሁሉነትዋ ግን በጌትነት ዘንድ ዋጋ አጥቷል። ሰው መስላ አልታየችውም። በሸዋዬነት ውስጥ የበቀለች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ሲል ደምድሟል።ይቺ በመማሯ ሽዋዬ ደግሞ በማይምነቷ መካከል ያለ ልዩነት እንጂ በሴትነት ባህሪያቸው አንድ ናቸው ብሎ የራሱን ድምዳሜ ሰጥቷል። በመልክ በጣም ይቀራረባሉ። በሌላ ፀባያቸውም ያው ናቸው የሚል እምነት ነው ያደረበት፡፡ አማረች አብዛኛው የሀሳብ ክፍሏን ለጌትነት አሳልፋ ሰጠች። ወደ ክፍል ሲገባና ከክፍል ሲወጣ ደጋግማ በስውር ተከታተለችው። ብቸኛ መሆኑን ካረጋገጠች በኋላ "ምን ችግር ቢኖርበት ይሆን?" ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ቀርባ ልታነጋግረውና ስለማንነቱ በሰፊው ለማወቅ ተንስፈሰፈች። ናቅ ስላደረጋት ነው መስል ምን ሲደረግ? የሚል እልህ ተናነቃት። ሌሎች ለሷ ያላቸውን ግምት በሚገባ ታውቃለች። ታዲያ ጌትነት
የምን ትዕቢት ነው? በትምህርቱ ጎበዝ ስለሆነ? መልከ መልካም ስለሆነ?
እኛ ስላለችው? ወይስ ሰው መስዬ ስላልታየሁት? ራሷን በብዙ ጥያቄዎች ዙሪያ በጭንቀት እንድታሽከረክር አደረጋት። ልቧ ዋተተ። እሱ እሷን በሚሸሽበት፣ በሚጠላበት ልክ እሷ ደግሞ እሱን ለመተዋወቅ ልቧ
ሽፈተ።
✨ይቀጥላል✨

👍1
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....በማግስቱ ጠዋት ዘመድ ወዳጁን ሞት የነጠቀው፣ የቆሰለበትና ገና የሆነውን ነገር በውል ያላወቀ የዲላ ነዋሪ ሁሉ ማልዶ ተነሳ፡፡ ማልዶ ወደ
መናኸሪያ ተመመ። ማልዶ ጉዞ ጀመረ፡፡ የተሽከርካሪ ችግር አልገጠመውም። በዲላ ዙሪያ ባሉ መዳረሻዎች ይሰሩ የነበሩ በርካታ ተሸከርካሪዎች ሁሉ ለዕለቱ አስቸኳይ ጉዞ ተመድበዋል። መሄድ የፈለገ ሁሉ ተሳፍሯል፡፡ ሽኝቱ በለቅሶ የተደበላለቀ ነበር፡፡
በልሁም አንዱ ተጓዥ ነበርና በታፈሡ በሔዋንና በርዕድ እየየ እና ጩኸት ተሽኘ፡፡
ገዞው ከወትሮው ፍፁም የተለየ ነበር። ሁሉም ሀዘንተኛ በመሆኑ የተኳረፈ ይመስላል ፀጥ ረጭ ባለ ሁኔታ ይጓዛል፡፡ አብዛኛው ሰው ጋቢና ነጠላ እንዲሁም
ጥቋቁር ልብስ ለብሷል፡፡ የፍተሻ ኬላዎችም ረግበዋል። በየመኪናው ውስጥ ገባ
ብለው ወጣ ከማለት ውጪ ተጓዡን ከመኪና ላይ አስወርደው ሁሉን ነገር በመበርበር ያጠፉት ጊዜ አልነበረም፡፡ ሾፌሮችም የጫኑትን ሕዝብ የውስጥ ስሜት
ያውቁ ነበርና ለከሰል ግዢ የትም ቦታ አልቆመም፡፡ እየተከታተሉ እንዳንዴም እየተሽቀዳደሙ በመብረር እረፋዱ አራት ሠዓት ተኩል ላይ ከዚያ አደጋ የደረሰበት
ቦታ ደረሱ፤ ከዝዋይ ከተማ በስተደቡብ በአሥራ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፡፡
ያ ቦታ ለአየው ሁሉ ይሰቀጥጣል። ወጭ ወራጅ ሁሉ ከሚጓዝበት መኪና ላይ እየ'ወረደ ያለቅስበታል። የተጋጩት መኪኖች ራሳቸው እንደ ሰው ያሳዝናሉ፡፡
ከሞጆ ወደ ሻሸመኔ ስትበር የነበረችው ሊዮንቺን ለዓመታት ስትረገጥ የኖረች ጣሳ መስላ ተጨራምታለኝ፡፡ ሁሉም ወንበሮቿ ሜዳ ላይ እንደ ቆሉ ተበትነዋል። ከዲላ ወደ አዲስ አበባ ይሄድ የነበረው አውቶብስ ደግሞ ፊት ለፊቱ ተቦድሶ ከግራ በኩል ያለው ጎኑ እስከ ኋላ ድረስ ከውጭ ወደ ውስጥ ተጠርምሷል
ከሎንቺኗ በአጠቃላይ፣ እንዲሁም በአውቶቡሰ ግራ በአል ከተቀመጠ ተሳፋሪ መሀል ሰው
ይተርፋል ብሎ ለመገመት እጅግ ያስቸግራል።
መኪኖቹን ተወት አድርጎ የተጋጩበትን አካባቢ መሬት ሲያዩት ደግሞ የባሰ አንጀት ያላውሳል። የአደጋ ሰለባዎች ደም ቦይ ሰርቶ ተንኳሉበታል። ከፈረሱ
ጭንቅላቶች የተበተነ አንጎልን በያለበት ተረጭቶ ዝንቦች ሰፍረውበታል፡፡ የተለያየ
ቅርጽ' ቀለምና መጠን ያላቸው የወንዶችም የሴቶችም ጫማዎች ሚዳው ላይ ተበታትነዋል፡፡ ደም
የተጠረገባቸው ጨርቆችና ስስ ወረቀቶች በየቦታው ተበታትነዋል፡፡
በዚያ ላይ ያ የዲላ ተሳፋሪ ሁሉ ከቦታው ደርሶ ከየመኪናው
እየወረደ፤ እንባ ሲራጭበት ያ ቦታ የባሰውነ መዓት ወረደበት።
በልሁ ትናንት ጠዋት አስቻለውን ሲሸኝ የተቀመጠበትን ቦታ አይቷልና ከመኪና እንደ ወረደ በቀጥታ በፊት በር በኩል ወደ አውቶቡሱ ሮጠ፡፡ በዚያ ቦታ
ላይ ያየው ሁኔታ መሬት ላይ ካለው የባሰ ነው፤ ደም ተጋግርበታል። የሞተሩ ክዳን
ወደ ኋላ ተጨራምቶ ወደ ወንበሩ መደገፊያ በመጠጋቱ ከዚያ ውስጥ ሰው ከነነፍሱ ሊወጣ ይችላል ብሎ መገመት ያስቸግራል። በልሁ በሁለት እጆቹ ራሱን ይዞ በለቅሶ
ሲንሰቀሰቅ ከቆየ በኋላ ድንገት የአስቻለውን የአካል ቁራጭ የሚያገኝ መስሎት ጎንበስ ብሎ በተጨራመተው የሞተር ክዳን ሥር ሲመለከት የአስቻለውን የቀኝ
እግር ቢጫ ጫማ አያት።
ድምጹን ከፍ እድርጎ «ወየው ወየው ወየው ወየው..» ካለ በኋላ
በመኪናው በር በኩል አንገቱን መጣ አድርጎ ጎበዝ ጎበዝ ጎበዝ ድረሱልኝ ጎበዝ ድረሱልኝ!» ሲል ዕርዳታ ጩኸት አሰማ፡፡ በአካባባው የነበሩ ሰዎች ሰምተውት ኖሮ ጠጋ ጠጋ ብለው ምነው? ምነው?» ሲሉት በልሁ እያለቀሰ «የወንድሜ እግር
እዚህ ቀርቷል! ኑ አውጡልኝ! ቶሎ በሉልኝ!» አላቸው።
ሰዎቹ ወደመኪናው ውስጥ ገብተው በልሁ ወደ ጠቆማቸው ቦታ ጎንበስ እያሉ ሲያዩ፡ እውነትም ቢጫ ነገር ታያቸው። ያን የሞተር ክዳን እንደ ምንም ተረዳድተው ወደ ፊት ከመለሱ በኋላ ከመኪና ስፖንዳ ጋር ተጣብቃ የነበረችውን
ጫማ ፈልቀቁኝው በማውጣት ለበልሁ ሰጡት::
በልሁ ያቺን ቢጫ ጫማ ይዞ ከመኪናው ላይ ወረደና ጫማዋን ወደ ላይ ከፍ፡ አድርጎ ለሕዝብ እያሳየ «እዩት ወገኖቼ! እዩዋት የወንድሜን ጫማ! የሆነውን
ነገር በዚህ ገምቱ! ወንድሜ ሞቷል! ወንድሜ ሞቷል! ...» እያለ ይጮህ ጀመር።
አስቸለህኑን የማያውቅ ሁሉ የሆነውን ነገር እየገመተ እንባውን አፈሰስ፡፡
ወዲያው ደግሞ ጥቂት ሰዎች በስቲሽን ዋገን ቶዮታ መኪና አስከሬን ጭነው ከቦታው ደረሱ፤ የጠይሟ ልጃገረድ አስከሬን ኗሯል፡፡ ህዝቡ ሁሉ ግርር
ብሎ፤ ኸደ መኪናዋ ሲሮጥ
በልሁም አብሮ ተጠጋ። ሌላው ሰው ከኋላ ከተሳፈሩት ሰዎች ጋር ሲነጋገር በልሁ ግን የልጅቷን አባት ጋቢና ውስጥ ሆኖ ሲያለቅስ
አየውና ጠጋ ብሎ፡
“አቶ ዘመድኩን!» ሲል ጠራው እንባውን በጉንጩ ላይ እያፈሰስ፡፡
“እንዲህ ሆንኩልህ በልሁ! የድሃ ልጄን ጉድ ተሰራሁ! ስንት ሆኔ ያሳደኳትን የበኩር ልጁን ወይኔ ወይኔ በማለት እያለቀሰ ሀዘኑን ለበልሁ ገለፀ።
«አስክሪን የት አገኘህ?» ሲል ጠየቀው በልሁ አሁንም እያለቀሰ፡፡
ከናዝሪት ውስቢታል ነው የሰጡኝ በልሁ::
«ምናልባት የልጅህን አስከሬን ስታወጣ ልብ ያልከው ነገር ይኖር ይሆን?» ሲል በልሁ ጠየቀው። ዘመድኩን የበልሁ ፍላጎት ገብቶታል።
«ምኑ ይለያል ብለሀ በልሁ? የሬሳ መዓት ተከምሯል፡፡ በያ ላይ እንዳንዱ ምነም ምነም አያስታውቅ፣ ስውነቱ ሁሉ ፈራርሷል። ብታይ እኮ ጉድ ነው
የሚታየው::» አለው ፊቱን በመሀረብ ሞዥቅ አድርጎ እየጠረንገ።
በልሁ አንጀቱ ብጥስ ያለ መስለው፡፡ መቆም አቃተውና ከመኪናዋ ራቅ ብሎ ሜዳው ላይ ቁጭ አለ፡፡ ያቺን የእስቻለውን ጫማ ከፊቱ አስቀምጦ በእግሮች
መሀል እጎንብሶ እያየ ያለቅስ ጀመር፡፡
የጠይሟን ልጃገረድ እስከሬን የጫነችው መኪና ወደ ዲላ ጉዞ ስትጀምር ወደ ናዝሬት የሚሄዱ አዘንተኞችን የጫኑ መኪኖች ሾፌሮችም ወደየመኪናው እንዲገባና ጉዞው እንዲቀጥል ይለምኑ ጀመር። በዚያ ሰዓት ስለ
አደጋው ያጠኑ የነበሩ የትራፊክ ፖሊሶችም መንገድ በማስለቀቅ ሰበብ ሕዝቡ እንዲሳፈር ወደ መኪናው መግፋት ጀመሩ። በልሁንም ደጋግፈው በማንሳት ወደ መቀመጫው ወስደው አስቀመጡት፡፡
ጉዞው ተጀመረ። ማታ እራት በወጉ፣ ጠዋትም ቁርስ ያልበላ ሀዘንተኛ ሁሉ ዝዋይ ሲደርስ እህል ልቅመስ አላለም፡፡ ሾፌሮቹ እንኳ አልከጀሉም፡፡ ዝም ብለው አለፉ፡፡ መቂና አለም ጤና እንዲሁም ቆቃ ከተሞች ታለፉ፡፡ ህዝቡ ደግሞ
አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ አልቅሶ አልቅሶ ደክሞት ስለነበር ጉዞውም ፀጥ ረጭ ያለ ሆነ፡፡ በአብዛኛው የተሳፋሪ እምነት የናዝሬት ሃይለ ማርያም ማሞ ሆስፒታል የአስክሬን መልቀምያ ወይም የቁስለኛ መገኛ ነውና ሁኔታዎች መቀየር የጀመሩት
ሞጆ ከተማ ታልፋ ወደ ናዝሬት ማቆልቆል ሲጀምር ነው፡፡ በተለይ ከናዝሬት መዳረሻ የመጨረሻዋ ዳገት ላይ ሲደርስ ለጥ ባለ ሜዳ ላይ የተቆረቆረችውን የናዝሬት ከተማ ሲያይ ሁሉም ተሳፋሪ ያለቅስ ጀመር፡፡ ከተማ ውስጥ ሲገባ ደግሞ ጫጫታና ኡአታ። ሆስፒታሉ በር ላይ ሲደርስ ደግሞ አገር ቀለጠ፡፡
ሕዝቡ ከየመኪኖቹ ላይ እየተሽቀዳደመ በመውረድ እያለቀሰና እየጮኸ ከሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲገባ ወዴት አቅጣጫ መሄድ እንደነበረበት

👍5
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
“ሺሕ ዓመት ንገሥ።"
ምንትዋብ፣ አፄ በካፋ ወደ መሠሪ እንድትመጣ ሲልኩባት፣ ሕይወቷ
ዳግም ተለወጠ። ለጥቂት ቀናት መሠሪ ሱባዔ ገብተው ስለነበር
ጨርሰው ነው ብላ አስባለች። ከእናቷና ከአያቷ ጋር መሠሪ ስትደርስ፣የበካፋ ታማኝ እልፍኝ አስከልካዮች ቴዎድሮስ፣ ገላስዮስና ድንጉዜ ዐይኖቻቸው ደም መስለዋል። እጅ ነስተዋት ስትገባ መሠሪ ከብዶታል፤
ጨላልሟል። ከወትሮው ጠባብ ሆኖባታል።
አፄ በካፋ ከተኙበት ኣልጋ ራስጌ የነፍስ አባታቸው አባ ዐደራ
መስቀላቸውን ይዘው ቆመዋል። ኒቆላዎስ ከንጉሠ ነገሥቱ ግርጌ
አቀርቅሮ ቆሟል። ምንትዋብ ርምጃዋን ገታ አድርጋ ክፍሉንም
ሰዎቹንም ቃኘች።
ነገሩ አላምር አላት። መንፈሷ ተረበሸ። ሱባዔ ላይ የነበሩት ባሏ ምን እንደደረሰባቸው መገመት አቃታት። ወደ አልጋቸው መራመድ ፈልጋ እግሮቿ አልታዘዝ አሏት፤ ትንፋሽ አጠራት። ልቧ ደረቷን ሲደልቅ እንደ ማጥወልወል አላት። ሐውልት ይመስል ደርቃ ቀረች። ዐይኗ ኒቆላዎስን ኣልፎ ንጉሠ ነገሥቱ ላይ ሲያርፍ፣ ፊታቸው ተሸፍኗል።
ዕለቱ ማክሰኞ፣ ቀኑ መስከረም አስራ ስድስት ዓመተ ምህረቱ 1723 ነው። እኒያ ቅኔ የሚቀኙት፣ መንፈሳዊ መጻሕፍትን የሚፈትሹት፣ አደን የሚወዱት፣ ለሃገራቸው ፊደላት ጥብቅና ቆመው፣ “ፊደል አሳስቶ የጻፈ
እጁ ይቆረጣል” ብለው አዋጅ የጣሉት፣ ሥነ-ጥበብ እንዲዳብር፣ ቃላት እንዲበለፅጉ የጣሩት፣ በወባ ንዳድ ርደው እንደተራ ሰው ባላባት ቤት መደብ ላይ የተኙት፣ ላይ ታች እያሉ ያመጸውን ያስገበሩት፣ ያጠፋውን አይቀጡ ቅጣት የቀጡት፣ እንደ ቀደምት ነገሥታት የሃይማኖት ክርክር
ያከራከሩትና አሻራቸውን ለመተው የራሳቸውን ግንብ የገነቡት አፄ
በካፋ በነገሠ በዘጠኝ ዓመት ከዐራት ወራቸው፣ ምንትዋብን ባገቡ በሰባት ዓመታቸውና በተወለዱ በሰላሳ ሰባት ዓመታቸው ሕይወታቸው
አልፏል።
“ምንድርነው? ጃንሆይ ምን ሁነዋል?” አለች፣ ምንትዋብ፣ ድምጾ ይርበተበታል ።
ተጠጋቻቸውና ቡሉኮውን ከፊታቸው ላይ ገለጥ አደረገችው።አፍንጫቸው ጫፍ ላይ ደም አየች፤ መላ ሰውነቷ ራደ። ኒቆላዎስ ላይ አፈጠጠች።
“ድንገት ነው የሆነው። ባፍ ባፍንጫቸው ደም ፈሰሰ... ምንም ያህል አልቆዩ ዐረፉ” አላት።
ራሷን በሁለት እጆቿ ይዛ “ኡኡኡኡ...” አለች። እናቷና አያቷ
ፈጠን ብለው ግራና ቀኝ ደገፏት።
“ምነው ሳትነግሩኝ? ስለምንስ ከፋችሁብኝ?” እያለች ጮኸች።
መሬት ላይ ተንከባለለች።
ያን ጊዜ እናቷና አያቷ አብረዋት ጮሁ። እንደ እሷ መሬት
ላይ ተንከባለሉ። መሠሪ ጩኸት በጩኸት ሆነ። ዋይታ በረከተ።
ምንትዋብ ለያዥ አስቸገረች። እነግራዝማች ኒቆላዎስ ተጨነቁ፡
ለቅሶው እንዳይሰማ። የቤተመንግሥት ባለሟሎች እንኳን እንዲሰሙ አልተፈለገም።
ምንትዋብ የምትሆነው ጠፋት። ከቶውንም የደረሰውን ማመን
አቃታት። አጎንብሳ፣ “ወዮ እኔ! ይብላኝ ለኔ” እያለች እንባዋን አዘራች።ኒቆላዎስና አባ ዐደራ ግራና ቀኝ እጆቿን ይዘው እንድትቀመጥ ግድግዳ ተጠግቶ ወደ ተቀመጠ ወንበር ሊወስዷት ሞከሩ።
“ተዉኝ... ተዉኝ! ለባሌ ላልቅስ።
ተዉኝ!” እያለች እሪ አለች።
“እቴጌ ባክዎ ለቅሶዎ እንዳይሰማ” አሏት፣ አባ ዐደራ።
“ይሰማ ይሰማ! አገር ይስማ! እኔ አለባል ልዤ አላባት መቅረታችንን...አገር ይስማ... ወዮ እኔ...ወዮ ልዢ ።”
እነኒቆላዎስ እንደ ምንም አባብለው አስቀመጧት። አንዴ ንጉሠ ነገሥቱ የተኙበትን አልጋ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጣራውን ደግሞም ወለሉን እያየች እንባዋ ረገፈ። ሐዘኗ መሪር ሆነ። የደረሰባትን ድንገተኛ ሐዘን
ጫንቃዋ መቋቋም የሚችል አልመስል አላት። ዓለም አስፈሪ ቦታ ሆነችባት። ሕይወቷ ላይ የሐዘን ጥላ አጠላችበት። የመኖር ተስፋዋን ሸረሽረችው። ትናንት ማሾ እያበራች ፈለጓን የተከተለችው መሬትም
ድንገት ጨለመችባት።
አልጋ ባልጋ የመጣው የሕይወቷ መንገድ ፍጻሜው የተቃረበ
መሰላት።
እንደገና ጩኸት ጀመረች። እነኒቆላዎስ ተደናገጡ። የእሷም
ሆነ የእናቷና የአያቷ ጩኸት እንዳይሰማ ፈሩ፤ ለማባበል ሞከሩ፤ አልሆነላቸውም። ምንትዋብን ብዙ ኃላፊነት እንደሚጠብቃት ኒቆላዎስ
ለማስረዳት ቢሞክር አልሰማ አለችው።
“ባሌ ኸሞቱ ገዳም ገብቸ መመንኮስ አለብኝ” አለችው።
እንባዋ ደረቷ ላይ ይወርዳል። ያቺ ፀዳል የመሰለች ሴት ፊቷ ድንገት
ጨለማ ለብሷል። ከመቅጽበት ዕድሜዋ ላይ ዓመታት የተጨመሩ
መስለዋል። ከዐይኗም ከአፍንጫዋም የሚወርደው ፈሳሽ አልቃሻ ሕፃን ልጅ አስመስሏታል።
ኒቆላዎስና አባ ዐደራ ተረበሹ። እናቷና አያቷ ለቅሷቸውን አቋርጠው በድንጋጤ ተመለከቷት።
“አዎ... ኸዝኸ በኋላ ምን ዓለም አለኝ? እኔም እንደ ባለቤቴ መሬት
እስትገባ ዓለሜ ምናኔ ነው። እሳቸው ሙተው እኔ እንዴት ባለም
ኖራለሁ? ልዤን ይዤ ኸዳለሁ” እያለች ጮኸች።
ኒቆላዎስ፣ “የለም የለም፤ እኼማ አይሆንም” አላት፣ ተጠግቷት።
“ደሞስ ምናኔ ማን ያደርስሻል? የጃንሆይ ጠላቶች ወይም ወህኒ
አምባ ያሉ ደጋፊዎች ምንገድ ላይ ጠብቀው አንቺንም ልዥሽንም
ይገድሏችኋል። ባይገድሏችሁ ስንኳ መውጫና መውረጃ የሌለው ወህኒ አምባ ወስደው ያስሯችኋል። ገዳም ብትገቢም ጃንሆይ ቅባት ሃይማኖት
ተከታይ ነበሩ ተብለው ስለሚጠረጠሩ እዚያ ብዙ የተዋሕዶ መነኩሴ ጠላቶች አሏቸው፤ ይጣሉሻል” አላት።
እሷ ግን፣ “በቁስቋሟ ተዉኝ! ተዉኝ” እያለች እጆቿን እያርገበገበች ተማጸነቻቸው።
ያን ጊዜ አባ ዐደራ፣ “እቴጌ መቸም መቀበል እንጂ ምን ማረግ ይቻላል? ኸሞት ሚቀር የለ። አሁን እርስዎ እንደዝኸ ሲሆኑ ሳንዘጋጅ የጃንሆይ መሞት የተሰማ እንደሁ ሁከት ይነሳል። ወህኒ ያሉትም እግረ ሙቃቸውን ፈተው ይመጣሉ። ንጉሥ ሞተ ሲባል ሚሆነውን እናውቃለን። ባክዎ ይጠንክሩልን” እያሉ ተለማመኗት።
ዮልያናም፣ “የኔ ልዥ! ባክሽ ጠንክሪ። እንደዝህ መሆን ደግ ማዶል” እያሉ እንባዋን በነጠላቸው ጠራረጉላት፣ የራሳቸውን ለመግታት
እየታገሉ።
“ልጄ በጡቴ ይዤሻለሁ! በኢያሱ ይዠሻለሁ! በምትወጃት በቁስቋም ማርያም ይዠሻለሁ! በምትወጃቸው ባባትሽ አጥንት ይሻለሁ በርቺልኝ” እያሉ እንኰዬም ሙሾ እንደሚያወርዱ ሁሉ እጃቸውን ወደ ኋላ አድርገው እንባቸውን እያዘሩ ለመኗት።
እሷ ግን እንባዋን መግታት አቃታት፤ አልጽናና አለች።
ኒቆላዎስ አንዴ እንድታዳምጠው ለምኗት የንጉሠ ነገሥቱን ኑዛዜ
ቃል በቃል ነገራት።
“ምን እንደተሰማቸው አላወቅሁም ብቻ እኔን አስጠሩኝ። ኒቆላዎስ...
ዐደራ ምልህ ልዤን... አሉኝ፣ ድምጣቸው እየተቆራረጠ። ልዤን
ኢያሱን እንድታነግሥልኝ። ለነገሥታት ሚደረገውን ሥርዐት ሁሉ... ቅባዓ ንጉሡንም ዘውዱንም... አርገህ እንዲነግሥልኝ። እናቱ ምንትዋብ
ብልህ ናት ትርዳው፤ ኸጎኑ ትሁን። እሷ አገር መምራትና... ማስተዳደር
ትችላለች። አርቆ አስተዋይና እዝጊሃር የባረካት ሰው ናት። አገሬን... አገሬን ኸልዣችን ጋር ሁና፣ ተባህር እስተ ባህር ታስተዳድር። አገሬ.. ምንም ዓይነት በደል እንዳይፈጠምባት። እኔ የዠመርሁትን ሁሉ. አጠናክረሽ ቀጥይ፤ በዐጸደ ነፍስ ኹኜም አልለይሽም በልልኝ። ሁላችሁም ቃሌን ንገሩልኝ…. ዐደራ” ብለው አንቺን እንድንጠራላቸው
ሲጠይቁ፤ ደም ባፍ ባፍንጫቸው ያለማቋረጥ ወረደ። ግዝየም አላገኙ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች።”
ምንትዋብ፣ ተናግሮ ሲጨርስ ሳግ እየተናነቃት ጣሪያውን፣
ግድግዳውን፣ ወለሉን፣ ሁሉንም በየተራ ተመለከተች። እነሱ ምን
እያሰበች እንደሆነ መገመት አቃታቸው። አንዴ እርስ በእርስ እየተያዩ ሌላ ጊዜ እሷን እያዩ ከአፉ የሚወጣውን ለመስማት ተጠባበቁ።

👍11❤1
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
ጥሪ
የሳጥናኤል ኮከብ
የሴሰኝነት ጥሪ
ሲልቪ
እኔና ሲልቪ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ፓሪስ ተጓዝን። በሷ መሪነት
ከፓሪስ ጋር ይበልጥ ተዋወቅኩ። በሲልቪ አስተማሪነት ከቅናት ጋር
ይበልጥ ተዋወቅኩ፡፡ ራሴንም ይበልጥ አወቅኩ ፓሪስ በገባን በሁለት ቀናችን፣ እንደ ልማዷ አንድ ደስ የሚላት ጎረምሳ አየችና አጣድፋ ወደ ሆቴላችን ወሰደችኝ፡፡ መብራቱን አጠፋች፡፡ እንደ “ልማዷ በኔ ገላ ጎረምሳውን ተደሰተችበት፣
አቃሰተች፣ ነገሩ ሊያልቅ ሲል ጮኸች። ተኛን፡፡ ያን ጊዜ እኔም
እሷም አላወቅነውም እንጂ፣ ከኔ ጋር እንዲህ ስትሆንና ስታደርግ
የመጨረሻ ጊዜዋ ነበር ነቃሁ። ጭለማ ውስጥ ነኝ። ምን እንደቀሰቀሰኝ እንጃ:: ከጎኔ
ተንቀሳቀሰች፡፡ በእንቅልፍ ልቧ «“Non! Non! Non!" እያለች
እየተጨነቀች ተፈራገጠች። በጣም የሚያስፈራ ህልም መሆን
አለበት። እየቀሰቀስኳት
«አይዞሽ አይዞሽ፣ ከኔ ጋር ነሽ» አልኳት ራሷን እየደባበስኩ።
በሀይል እየተነፈሰች ተጠጋችኝና
«አንድ ነገር አስደነገጠኝ፡፡ መብራቱን አብራልኝ አለችኝ
አበራሁት። አይኔ ብርሀኑን ከለመደው በኋላ ታየችኝ፡፡ ጥቁር
ረዣዥም ፀጉሯ ጉንጭና አንገቷ ላይ ተጠምጥሟል፣ተለጣጥፏል። ግምባሯ ላይ ላቡ ያብለጨልጫል፡ ጠረግኩላት፣
ፀጉሯን ወደ ኋላዋ ሰበሰብኩሳት
ውሀ» አለችኝ፡፡ ራስጌ ካለው ጠርሙስ አጠጣሁዋት
«ደህና ነሽ?» ስላት፣ ሳቅ ብላ
«አጥፋው» አለችኝ። አጠፋሁት፣ አቀፍኳት
«ቅዠት ነበር፡፡ ኮሙኒስቶች የኢራንን ሻህ መንገድ ላይ
አግኝተውት በጩቤ ሲገድሉት አየሁ፡፡ በኋላ ግን ባህራም ሆነ።
«አይዞሽ ነቅተሻል፡ አይዞሽ» እያልኩ እጄን ጀርባዋ ላይ
ሳንሸራትት ትንሽ ከቆየሁ በኋላ
Tu es plutôt une mére Française qu' un sauvage Africain"
አለችኝ («ፈረንሳዊት እናት ነህ እንጂ አፍሪካዊ አረመኔ
አይደለህም ኮ») ሁለታችንም በሳቅ መንፈርፈር ጀመርን። ታድያ'ኮ ያን ያህል የሚያስቅ አልነበረም፤ ያን ጊዜ መሳቅ ስላስፈለገን ነው
እንጂ፡፡ እየተጠመጠመችብኝ፣ ደስታ ባፈነው ድምፅ
«መኖር እንዴት ጥሩ ነው!» አለችኝ
ካንቺ ጋር ሲሆኑማ!»
የኔ ካስትሮ፣ ይልቅ ካንተ ጋር ሲሆኑ ነው እንጂ፡፡»
እቅፍ አድርጌ ጉንጯን ሳምኳት። በጭለማው ላዬ ላይ ወጣች፡
እንደምትወደው ጀርባዋንና አንገቷን እያሻሸሁ
«ምን ይሰማሻል?» አልኳት
እንደምትወደኝ ይሰማኛል»
«አውቀሻል»
«የተለየ ስጦታህ ምን እንደሆነ ልንገርህ?»
«ምንድነው?»
«የሰላም
ተሰጥዎ ነው ያለህ፡፡ ካንተ ጋር ስሆን ሰላም ይሰማኛል። ካንተ ጋር ስሆን ፀፀትና ንስሀ አያስፈልገኝም፡፡»
«ፀፀትና ንስሀ?»
በተለወጠ ድምፅ
«ቅድም ስለበደልኩህ ገላህን ለጋራ ጥቅማችን ሳይሆን ለግል
ደስታዬ ስላዋልኩት»
ፀፀት ሊጀምራት እንደሆነ ገባኝ፡ አሳዘነችኝ
«የኔ ቆንጆ፡ ቂል አትሁኚ። አንቺ ገላሽን እንድደሰትበት
ትሰጪኝ የለ?» አልኳት
«አዎን»
«ታድያ እኔ ገላዬን እንድትደሰቺበት ብሰጥሽ ምናለበት?»
«ከዚያ ይለያላ»
«አስር ጊዜ ልዩ ይሁን። በናንተ አገር ፍቅር ማለት ምንድነው?
መስጠትና መቀበል አይደለም?»
«ነው»
«ታድያ ገላዬን ብሰጥሽና ተቀብለሽ ብትደሰቺበት ምን ፀፀት
ያስፈልገዋል? እኛ አገር መስጠት ማለት መስጠት ነው። ገላዬን
ከሰጠሁሽ የራስሽ ሆነ ማለት ነው፡፡ የራስሽ ከሆነ ደሞ የፈለግሽውን ልታረጊበት ትችያለሽ ማለት ነው።
«እንደሱ ሆኖ ነው እሚታይህ?»
«ነው እንጂ»
«እንዴት ጥሩ ነህ! እኔ ግን እንዴት መጥፎ ነኝ!»
እንዴት?
«ውሸታም ነኛ!»
«ውሸታም?»
«አዎን፡፡ ለምሳሌ፣ ያን ጊዜ ስትጠይቀኝ የሌላ ሰው ገላ
እያቀፍሽ በሰውየው ገላ ከኔ ጋር ተኝተሽ ታውቂያለሽ ወይ?”
አላልከኝም? እኔ ምን አልኩህ? »
«በጭራሽ አድርጌው አላውቅም አልሽኝ»
«አዎን። ግን ውሽቴን ነበር። ላንተ
መዋሸቴ በጣም ይቆጨኛል፡፡ ስለዚህ አሁን አንድ ውል እንግባ። አንተ ላለፈው ውሸቴ ይቅርታ አድርግልኝ። እኔ ደሞ ለወደፊቱ ሁልጊዜ እውነቱን እነግርሀለሁ፡፡»
«ስሚኝ የኔ ቆንጆ:: ለኔ ምንም ነገር መንገር የለብሽም፡፡»
“አውቃለሁ። ለዚህ ነው ልነግርህ የምፈልገው:: ከዚያም በላይ፣
አንተ ልትረዳኝ ትችል ይሆናል፡፡ እውነቱን ልንገርህ?»
«እሺ»
«አትጠላኝም?»
«በጭራሽ አልጠላሽም»
እሺ፡፡ ያኔ ታስታውሳለህ?»
የኔ ሻህራዝድ የኔ ቆንጆ፣ እንዴት ልረሳው እችላለሁ?»
“ተመስገንን ፍለጋ የምመጣ ይመስልህ ነበር፡፡ እኔ ግን አንተን
ለማግኘት ነበር የምመጣው፡፡ ሳይህ በጣም ደስ ትለኝ ነበር።
ካስትሮን ትመስለኝ ነበር። ስንቀልድ ስንስቅ ጥርስህን አፍህን ሳየው
አንቀህ እንድትስመኝ እመኝ ነበር፡፡ ታድያ አንተ እምቢ አልክ።
ስለዚህ ካንተ ስለይ፡ ተመስገን ጋ እሄድና አይኔን ጨፍኜ አንተን
እያሰብኩ አቅፈው ነበር፡፡»
«ያውቅ ነበር?»
«ምስኪን ተመስገን! እንዴት አርጎ ይወቅ?»
እንጃ፣ ነግረሽው ሊያውቅ ይችላል ምናልባት?»
«እንዲህ አይነት ነገር እንዴት ሊገባው ይችላል?»
»እሺ ቀጥዪ»
«ትጠላኛለህ»
«እንግዲህ ቂል አትሁኚ፡፡ በኔ የመጣ ስለምንም አለመግባባት
አትስጊ። ንገሪኝ፡፡»
«እንዴት አርጌ ልንገርህ?»
«እንደመጣልሽ»
ከነገርኩህ በኋላ ምን እንደሚመስልህ ትነግረኝ እንደሆን»
“Parole d'honneur?'' (የከበሬታ ቃልህን ሰጥተሃል?»)
“Parole d'honneur” («የከበሬታ ቃሌን ሰጥቻለሁ»)
«እሺ። እንዲህ ነው:: አየህ፣ ካንተ ጋር ግብረ ስጋ በጣም
ደስ ይለኛል። ደጋግሜ ነግሬሀለሁ፡፡ ያንተን ግማሽ እንኳ ያህል እኔን ማስደሰት የቻለበት የለም፡፡ ብቻ ምን ልበልህ፣ ታጠግበኛለህ፡፡ ግን
በሽታዬ ይመጣል። ሲመጣ ደሞ መከላከያ የለኝም። ገባህ?»
«ገና አልገባኝም
«እንዳልኩህ፤ ታጠግበኛለህ፡፡ ግን በሽታዬ ይመጣል፡፡ በጣም
ታምረኛለህ፣ በሀይል እመኝሀለሁ
«ታድያ አለሁልሽ አይደለም?»
“እንደሱ አይደለማ የምታምረኝ»
ልቤ መምታት እየጀመረ
“ታድያ እንዴት ነው?» አልኳት፣ ጐሮሮዬም መድረቅ ጀምሯል
በሀይል ታምረኛለህ፣ ምኞቱ ያንገበግበኛል። ግን ስትተኛኝ
በገዛ ገላህ እንዳይሆን ያስፈልጋል። የሌላ ወንድ ገላ ተውሰህ፣ በሱ ገላ አንተ እንድትተኛኝ ፈልጋለሁ። እንደዚህ ያማርከኝ ጊዜ፣ ካንተ
ተለይቼ መሄድ ይኖርብኛል።»
«ወዴት?» ጉሮሮዬ ጨርሶ ደርቋል
“አንተን ፍለጋ፣ ሌላ ወንድ ፍለጋ»
«ታገኚዋለሽ?»
«ምን ይመስልሀል?» ጉሮሮዋ ውስጥ ወፍራም ተንኮለኛ ሳቅ
ተሰማኝ ቅናት ማለት ይሄ ይሆን እንዴ? ታድያ ንዴቱና ብስጭቱ
የታለ? እኔን የሚሰማኝ ጥልቅ የሆነ እሳት የሆነ የሚያቃጥል
ቅንዝር! እንደ ዛሬም አንገብግቦኝ አያውቅ! ተለይታኝ ስትሄድ፣
ወፍራም ዳሌዋን እያወዛወዘች፣ ውብ ኣይኖቿን ክፍት ክድን
እያረገች፣ በፍትወተ ስጋ እስኪፈነዱ ብልታቸውን በሚያሳብጠው ፈገግታዋ የመረጠችውን እድለኛ ወንድ ስትጣራ ታየችኝ። ስጋዬ
አላስታግስ አላስችል አለኝ፣ እላዬ ላይ እንደተጋደመች በጥድፊያ
ገለበጥኳትና ጭኖቿን ፈልቅቄ ስገባ፣ በሙዚቃዊ ፈረንሳይኛዋ፣
በቅንዝር ድምፅዋ
“Ah. cheri, comme tu es sauvage! C'est delicieux"

👍20
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
ኮዜት
ኦርዮን የተባለ መርከብ
ከአሁን በኋላ በጣም ዝርዝር ውስጥ ባንገባ ይሻላል፡፡ ግን በሚቀጥለው ቀን ጋዜጣ ላይ የወጣውን ባጭሩ መጥቀስ ደህና ሳይሆን አይቀርም፡፡
«ዣን ቫልዣ የተባለ ወንጀለኛ ካመለጠበት ተይዞ ለፍርድ ቀርቦአል፡፡ይህ ወንጀለኛ ከእስር ቤት ካመለጠ በኋላ ስሙን በመቀየሩ በቀላሉ በፖሊሶች
ሳይያዝ ቆይቶ ነበር፡፡ እንዲያውም ከነአካቴው ከጮሌነቱ ብዛት ከሀገራችን በስተሰሜን ለምትገኝ አነስተኛ ከተማ ከንቲባ እስከ መሆን ደረሰ፡፡ በዚህች ከተማ ውስጥ ብዙ ጥቅም የሚያስገኝለት ሥራም ሠርቷል፡፡ በመጨረሻ ግን በባለሥልጣኖች ታላቅ ጥረትና ድካም ማንነቱ ታውቆ ለመያዝ በቅቷል፡፡
በተያዘበት ወቅት በእቁባትነት ያስቀመጣት ሴት አዳሪ በድንጋጤ ሞታለች፡፡
ይህ እንደ ጎልያድ በጣም ጉልበተኛ የሆነ ሌባና ቀማኛ በድንገት ቢያመልጥም
በፖሊሶች ጥረት ከሦስት ቀን በኋላ ከፓሪስ ወደ ነበረበት ከተማ በሚጓዝ መኪና ውስጥ ሊገባ ሲል ተይዟል፡፡ ከተያዘ በኋላም ለሦስት ቀን የተሰወረው ከባንክ የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ለማውጣት እንደሆነ ተደርሶበታል::
የነበረውም ገንዘብ ከስድስት እስከ ሰባት መቶ ሺህ ፍራንክ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከባንክ ያወጣውን ገንዘብ ግን የት እንዳስቀመጠው ከራሱ በቀር ማንም ስላላወቀ ገንዘቡን ለመውረስ አልተቻለም:: ይህ ዣን ቫልዣ የተባለ ቀማኛ የአንድ ሕፃን ልጅ ገንዘብ በመዝረፉ ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት ቀርቦአል፡፡ይህ ሽፍታ የተከሰሰበትን ጉዳይ ለመካድ አልፈለገም፡፡ ገንዘቡን የዘረፈው
ዣን ቫልዣ ብቻውን ሳይሆን የዘራፊዎችን ቡድን በመምራት እንደሆነ በሥራቸው የተመሰገነና አንደበተ-ርቱዕ የሆኑ የመንግሥት ባለሥልጣኖች አረጋግጠዋል:: ይህም በመሆነ የዣን ቫልዣ ወንጀለኛነት ስለተረጋገጠ
በሞት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል፡፡ ወንጀለኛው ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወይም ወደ ንጉሡ ይግባኝ ብሎ ወደ እድሜ ልክ እስራት እንዲለወጥለት ቢጥርም አልሆነለትም:: ዣን ቫልዣ ቱሉን ወደሚገኘው ወህኒ ቤት
ወዲያውኑ ተወስዶአል፡፡ ዣን ቫልዣ ቀደም ሲል የተሰጠው የእስር ቤት ቁጥር ተለውጦ አዲስ ቁጥር ተሰጥቶታል፡፡ አዲሰ ቁጥር 9430 ነው::
ወንጀለኛው ዣን ቫልዣ ለጥቂት ቀናት በተሰወረበት ሰሞን
ባለሥልጣኖች ሞንትፌርሜ ካተባለ መንደር ሲንሸራሽር መታየቱን ተናግረዋል:: ሞንትፐርሜ ከተባለ መንደር ውስጥ አንድ ወደ ዱር አዘውትሮ
መሄድ የሚወድ ሽማግሌ ነበር:: ሽማግሌ በአንድ ወቅት እስር ቤት
እንደነበር ሕዝቡ ይናገራል:: ፖሊሶችም በዓይነ ቁራኛ ይጠብቁታል:: ይህም ሽማግሌ ሥራ በማጣቱ በጣም ዝቅተኛ በሆነ ክፍያ የአውራ ጉዳና ጠጋኝ
ሆኖ እንዲሠራ መንግሥት ይቀጥረዋል፡፡
አንድ ቀን የተበላሽ መንገድ ለመጠገን በጠዋት ወደ ሥራው ቦታ ሲሄድ ከጫካ ውስጥ ከአንድ ዛፍ አጠገብ አካፋና ዶማ ተቀምጦ ያያል:: ከዚያም በመቆፈሪያውና በአካፋው አንድ ጊዜ እቃ እንደጠፋበት ሰው
አካባቢውን ያስሳል፤ ቆይቶ ደግሞ ትንንሽ ጉድባዎችን በጥድፊያ ይቆፍራል::
ይህን ተግባር ሲፈጽም የአንድ ትምህርት ቤት ዳይሬክተርና የአንድ ሆቴል ቤት ባለቤት የሆነው ሚስተር ቴናድዬ የተባለው የኮዜት አሳዳሪ በማየታቸው በጣም ይገረማሉ፡፡ «ታስሮ እኮ ነበር» ይላል ሚስተር ቴናድዬ ፤ «ጫካ ውስጥ እኮ ምን እንዳለ አይታወቅም፧ ምን ይሠራ ይሆን!»
ሁለቱ ሰዎች ጓደኛሞች ሲሆኑ ሽማግሌው ጋርም ቅርበት ነበራቸው:: በሌላ ቀን ሚስተር ቴናድዬ ተንኮል አስቦ ሰውዩው በመጠጥ ኃይል ወገቡ እስኪጐብጥ ድረስ በማጠጣት ያሰክሩታል፡፡ ይህ ቡላትሩስ የተባለው ግለሰብ በጣም ብዙ ስለጠጣ ብዙ ይለፈልፋል፡: በስካር መንፈስ የተናገረውን
በማቀናጀት የትምህርት ቤት ዳይሬክተሩና ሚስተር ቴናድዬ ከሚቀጥለው መደምደሚያ ላይ ይደርሳሉ::
«አንድ ቀን ጠዋት ሊነጋጋ ሲል ቡላትሩስ ወደ ሥራው ቦታ
ሲሄድ አካፋና ዶማ ከቁጥቋጦ ስር ተወሽቀው በማየቱ በጣም ይገረማል፡፡ ሆኖም መሣሪያዎቹ ምናልባት ከሠፈርተኞች መሃል አንዱ ረስቷቸው የሄደ ይሆናሉ ብሎ ከመገመቱ በስተቀር ምንም ነገር ሳያደርግ ያልፋቸዋል፡፡ ነገር
ግን በዚያው ቀን ወደማታ ለዓይን ያዝ ሲያደርግ ቡላትሩስ የሚያውቀው ሰው በትልቅ ዛፍ ተከልሎ ይመለከታል፡፡ ቡላትሩስን ግን አላየውም፡፡ ሰውዬው ለአገሩ ባዳ ለሰው እንግዳ ሲሆን በእነቴናድዬ አተረጓጉም ቡላትሩስ
ግለሰቡን የሚያውቀው እስር ቤት ነው:: ይህ ሰው ከዛፉ ከለላ ወጥቶ ጥቅጥቅ ወዳለው ጫካ አመራ፡፡ ሽማግሌው ምንም እንኳን ቢሰክርም
የሰውዬውን ስም ለመናገር አልፈቀደም:: ግለስቡ አንድ በጋ የተጠቀለለ አነስተኛ ሻንጣ መሳይ ነገር ይዟል፡፡ ከሁለትና ከሦስት ሰዓት በኋላ ሰውዬው
ጥቅጥቅ ካለው ጫካ ተመልሶ ወደ ውጭ ሊወጣ ቡላትሩስ አይቶታል፡፡
ሲመለስ ግን የያዘው ሻንጣ ሳይሆን ዶማና አካፋ ብቻ ነበር፡፡ በሚቀጥለው ቀን በጠዋት ሰውዬው በሄደበት አቅጣጫ ቡላትሩስ ይሄዳል፡፡ ግን ያ
ግለሰብ ከዚያ ሥፍራ አልነበረም:: በላትሩስ ምን ብሎ ያስባል? «ማታ ሰውዬው ይዞት በነበረው ዶማ ጉድጓድ ቆፍሮ ያንን ሻንጣ መሳይ ነገር ከቀበረ በኋላ በያዘው አካፋ አፈሩን በመመለስ ደፍኖታል:: መቼስ የቀበረው
ነገር ሰው አይሆንም፣ ምክንያቱም ሳጥንዋ ትንሽ ናት:: ስለዚህ የቀበረው ገንዘብ ነዋ» በማለት ደመደመ::
ስለዚህ ገንዘቡን ለማግኘት ቡላትሩስ ፍለጋውን ቀጠለ፡፡ ወጣ፣ ወረደ ፣ አዲስ የተነካካ አፈር ባገኘ ቁጥር ቆፈረ፤ መሬቱን ጠራረገ፣ የወደቀ ቅጠል
አገላበጠ፡፡ ግን ልፋቱ ሁሉ ከንቱ፡ ሆኖ ምንም ነገር አላገኘም::
ቡላትሩስ በሰከረ ቁጥር ይህን ታሪክ በመዘላበድና በመቀባጠር
ያወራል፡፡ ሆኖም ማንም ሰው ምንም ነገር ስላላገኘ ወሬው ከጊዜ በኋላ እየተረሳ ሄደ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በ1923 ዓ.ም. ወደ ጥቅምት ወር መገባደጃ ላይ የቱሉን ከተማ
ነዋሪዎች ኦርዮን የተባለ የጦር መርከብ ሲመጣ በሩቁ ያያሉ፡፡ ሰው ተሰባስቦ መርከቡን ይጠብቃል፡፡ መርከቡ ጉዳት ደርሶበት ለጥገና ነበር
የመጣው:: አንድ ቀን ጠዋት የመርከቡ ሠራተኞች የጥገና ሥራ ሲሰሩ ያልታሰበ አደጋ ይደርሳል፡፡
የመርከቡ ሠራተኛ ከመርከቡ ጫፍ ላይ ቆሞ ገመድ እየጠቀለለ ሳለ መቆሚያውን ስቶ ሊወድቅ ይንገዳገዳል፡፡ ቀጥ ብሎ ለመቆም ጥቂት ከታገላ
በኋላ ለመመለስ ስላልቻለ ጥልቀት ካለው ባህር ውስጥ ሊወድቅ ሲል ባንድ እጁ ገመድ ይዞ ይንጠላጠላል፡፡ ከዚያም በሁለት እጁ ገመዱን ጥፍር
አድርጎ ላለመውደቅ ትግሉን ይቀጥላል:: ገመዱን ከለቀቀ በርቀት ተወርውሮ ጥልቀት ካለው ባህር ውስጥ ሊወድቅ ሆነ፡፡ ከዚያ ርቀት ከወደቀ እንደሚሞት
ያውቃል፡፡ ሰውዬውን ለመርዳት መሞከር ማለት ደግሞ ከትልቅ አደጋ ውስጥ መውደቅ ማለት ነበር፡፡ ግለሰቡን ለማዳን የሚሞክር ሰው ከባህሩ
ውስጥ መውደቅ ማለት ነበር፡፡ ግለሰቡን ለማዳን የሚሞክር ሰው ከባህሩ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ከዚያ የነበረ ሁሉ የሚያውቀው ነበር። ስለዚህ ግለሰቡን ለመርዳት ማንም አልደፈረም:: ሰውዬው ግን እየደከመ ሄደ::

👍17❤1🥰1
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...."“እስኪ…” አለች ዶክተር ከብዙ ዝምታ በኋላ፣ ወደ በሩ እያመለከተቻቸዉ። “እስኪ አድ አፍታ ላስቸግራችሁ፣ ዉጪ ጠብቁ ያለ ምንም ጥያቄ ሁሉም ምሰስ እያሉ ሲወጡ፣ በክፍሉ እኔና እሷ ብቻ ቀረንበት.
“ልጄን…” ስል ተቀበልኋት፣ ባልቻን የሸኙ ዓይኖቿ ወደኔ ሲመለሱልኝ፡
“ልጄ አታሳዪኝም?”
“ናፈቀችሽ አይደል?”
“ኧረ አልቻልሁም ሽዊት”
“ይገባኛል። አዉቃለሁ”
“ታዲያ አምጭልኛ”
“እያወቅሽዉ? እንደሱማ አይሆንም”
“እንዴት ናት ግን? እንደ ፈራነዉ ሆነ ወይስ እግዜር ተአምሩን አሳየሽ?” አልኋት፣ ፈራ ተባ እያልሁ።
“ኹለቱም”
የምትለዉን እንድትል ጠበቅኋት፡
“እንደ ፈራሁትም ነዉ፤ እግዚአብሔርም ተአምሩን አሳይቶኛል። ኹለቱንም”
አሁንም ጭጭ ብዬ አዳመጥኋት፡ ጠበቅኋት እያየኋት የግንባሯ ሰማይ ዳመነ፡ የዳመኑ ዓይኖቿም እንባ አዘሉ፡ ምንም ሳይቆይ ያዘለዘለ እንባዋ ቡልቅ እያለ ሲወርድ እኔም አልቻልሁም: የኔም ጉንጮች ቀዝቃዛ እንባ አለፈባቸዉ: ከመሬት ተነስቶ ብርድ አንሰፈሰፈኝ
“ቁርጤን ልስማዉ?” አልኋት፣ መጥፎ ነገር ብትነግረኝ ፍጥርቅ ብዬ ለመሞት እየተሰናዳሁ: ከመሞት በቀር ምን ምርጫ አለኝ? ምንም:: እሞታለሁ
“ግልጹል ንገርሽ: ወደ ኦፕራሲዮን ክፍሉ ስገባ፣ አንቺን ለማትረፍ
እንጂ ልጅሽ በሕይወት ትመጣለች ብዬ አልጠበቅሁም ነበር። በሆድ
ሳለች የልብ ምቷ ስናዳምጠዉ በጣም አስፈሪ ነበር። አንቺም ትናትና እንዳልሽኝ በሆድሽ ዉስጥ እየተንቀሳቀሰች አልነበረም: በዚያ ላይ ከመደበኛዉ የመወለጃ ጊዜ እጅግ ቀድማ ስለመጣች፣ ላንቺ ፈርቼልሽ ነበር: በግልጽ ልንግርሽ አይደል ዉብዬ? የልጅሽ በሕይወት መትረፍ፣ ያንቺም በጤና መገላገል የእግዚአብሔርን ሥራ በዓይኔ በብረቱ ያየሁበት
ተአምር ነዉ”
“እንግዲያዉ ምድነዉ የሚያስለቀሰሽ?”
ለመናገር ዳዳችና ተወችዉ፡፡
በጥያቄ የተጥለቀለቀ ፊቴን ስታይ ቆይታ፣ የነርሶቹን መጥሪያ ደወል ተጫነችዉ፡ ደወሉን ሳትለቀዉ ገና፣ ከቅድም ጀምራ በተለየ ሁኔታ ጠብ እርግፍ ስትልልኝ የነበረችዋ ነርስ ያለንበትን ክፍል ከፈት አድርጋ ገባች
“አቤት ዶክተር''
“እስኪ ባክሽ አንድ ነገር ላስቸግርሽ”
“ምን ልታዘዝ ዶክተር?''
“እስኪ ባክሽ ዉብርስት ወደ lCሀ ክፍል እንዉሰድና አንዳፍታ ልጇን
በዓይኗ እናሳያት”
“ኧረ?” አለች፣ ድንግጥ እያለች:
“አይዞሽ፤ አብሬሽ አለሁ: ኃላፊነቱን ራሴ እወስዳለሁ” ስትል
አደፋፈረቻት፣ ነፍሴን የያዘልኝ ግሉኮስ የተንጠለጠለበትን ዘንግ ራሷ ከፍ አድርጋ እያነሳችና መንገድ እየጀመረች:
ነርሷም ትንሽ እንደ ማቅማማት ስትል ከቆየች በኋላ መታዘዟን
አስበልጣ የተንጋለልኩበትን አልጋ
ማሽከርከር ጀመረች መኪና ማቆም ከሚያያስችለዉ የሕንጻዉ ሰፊ አሳንሰር ከነአልጋዬ ከጫኑኝ በኋላ ኹለት ፎቆች ወደ ላይ ወሰዱኝ፡ ከአሳንሠሩ ወርደን ትንሽ እንደ ሄድን፣ ጥልቀት ያለው እንክብካቤ ወደሚደረግበት (ICU) ክፍል ደረስን፡ እጅግ ሰፋ
ወዳለዉ አዳራሽ ከመግባቴ፣ የተለያየ ስምና መጠን ያላቸዉ ማሽኖች ተደርድረዉ አየሁ፡ በአብዛኛዎቹ ማሽኖች፣ በተለይም ያለ ዕድሜያቸው የተወለዱ ሕጻናት ተኝተዉባቸዋል፡ ያዉም በሆድ፣ አፍና አፍንጫቸ
ላይ በልዩ ልዩ ማስተላለፊያዎች ተተብትበዉ፡ በነዚህ ትብታቦች
አማካኝነት በዋናነት ምግብ እና አየር የሚያገኙ ሲሆን፣ ማሽኖች
የየራሳቸዉ ማሞቂያም ሆነ ማቀዝቀዣ የተሟላላቸዉ መሆናቸዉን በስማቸዉ አዉቃቸዋለሁ መሀል ለመሀል እየወሰዱኝ ሳለ፣ በግራም
በቀኝም በኩል ዓይኔ ዉስጥ የገቡትን ሕጻናት ሥራዬ ብዬ ተመለከትሁ ሁሉም እንደየአቅማቸዉ እግርና እጃቸዉን ያወራጫሉ።
ቱናትን ላያት ነዉ፡
ብዙ የተገመተላትን፣ የልጄን ዓይን በዓይኔ ላየዉ ነዉ፡፡ ልጄ ቱናት
ያለችበት ክፍል ዉስጥ መሆኔን ሳዉቅ፣ ይኼ ነዉ ብዬ መግለጽ
የማልችለዉ ሽብር ወረረኝ፡፡ ፍርሃቴም ናፍቆቴም ተደራርበዉ ልቤን ጫፍ ላይ አደረሱብኝ፡፡ ልትወጣ ምንም አልቀራትም፡፡
ፍርሃቴ ጫፉ ላይ ደርሷል፡
“ይቅርታ” አለች ዶክተር፣ ወደ ነርሷ ዘወር ብላ፡ ሲመስለኝ ቱናት
ያለችበት አጠገብ ደርሰናል በዓይኔ ባጣብራት ግን ላገኛት አልቻልሁም ጭንቅላቷ ከፍ ያለ ልጅ ፍለጋ ዓይኔን ባንከራትትም አላገኘኋትም፡ የዶክተሯ ጥቅሻ ገብቷት ነርሷ የያዘችዉን የአልጋዬን ብረት ለቀቀችና
ተመልሳ ወጣች:: ኹለት የክፍሉ ባለሙያዎች በክፍሉ ያሉ ቢሆንም፣በማሽኖች አጠገብ ግን አይደለም የቆሙት ዝም ብለዉ ብቻ እንደ ንቁ ወታደር፣ ወዲያ ወዲህ ይንጎራደዳሉ።
እኔም እሷም ወደ'ዚህ ክፍል ለመግባት፣ ቢያንስ የእነሱ ፈቃድ
እንደሚያስፈልግ እኔም ገምቻለሁ
በመሆኑም በየስማቸዉ ጠርታ ሰላም እያለቻቸዉ ወደ እነሱ ቀረበች: ምን እንደ ተባባሉ ባይሰማኝም፣ ብቻ የሆነ ነገር ብላ አሳምናቸዉ መጣች: በአንድ እጇ ግሉኮስ የተንጠለጠበትን የብረት ዘንግ፣ በሌላ እጇ ደግሞ አልጋዬን በትራስጌ በኩል እየገፋች ዉስጥ ለዉስጥ ተሂዶ ወደሚገኝ ሌላ ክፍል አደረሰችኝ፡: ጠጋ ብላ
ካነጋገረቻቸዉ ባለሙያዎች አንደኛዉ ቀደም ብሎ በመዳፉ አሻራ በሩን ከፈተልንና ገባን፡፡ እሱን በደረቅ ፈገግታም ጭምር እጅ ነስታ ከሸኘችዉ በኋላ፣ እስከ አሁን በጭራሽ አይቼባት የማላውቀዉን ፊቷን አሳየችኝ፡፡
ከተለዩትም የተለየ እክብካቤ ስለሚያስፈልጋት፣ ልጅሽ ያለችዉ
በዚህኛዉ ለይቶ ማቆያ ክፍል ነዉ: ልጅሽን የማየት መብት ቢኖርሽም፣ መንገዱ ግን አሁን የመጣንበት አይደለም: እንግዲህ ያለ ግርግር መምጣት የፈለግሁበት ምክንያት አንቺም የምታጭዉ አይመስለኝም”
ለጥያቄ አፌን እያሞጠሞጥሁ ሳለ፣ ቀልጠፍ ብላ ከአጠገባችን ያለዉን ማሽን ቁልፎች መነካካት ጀመረች ማሽኑ እጅግ ግዙፍ ሲሆን፣ ከላይ የተገለበጠ ሙኸዶ የሚመስል ክዳን አለዉ፡ ልክ መነካካት ስትጀምር፣
ቀድሞ ወደ ላይ ተስቦ የተከረፈደዉ ይኼዉ ክዳን ነዉ፡ በእርግጥ ክዳኑ ብርሃን አስተላላፊ ስለሆነ፣ ለቆመ ሰዉ እንደ ተከደነም ቢሆን ወደ ዉስጥ
ከማየት አይከለክልም፡ እኔ ግን እንደ ተንጋለልሁ ስለሆነ ተከፍቶልኝ እንኳን ልጄን ማየት አልቻልሁም እስከመጨረሻዉ ድረስ አልጋዬን ከወገብ በላይ አቃንታልኝ፣ ራሷ የመሸከም ያህል ደግፋ ቀና አደረገችኝ
እና ወደ ዉስጥ እንድመለከት አመቻቸልኝ፡
በሙሉ ዓይን ባይሆንም፣ አንገቴን ቀና አድርጋ አሳየችኝ አየኋት
ቱናትን አገኘኋት።እንደ ተፈራዉ ናት።
“ስንት ኪሎ ሆነች?” አልኋት፣ የጭንቅላቷን ግዝፈት እያስተዋልሁ፡አትሆንም እንጂ ኹለት ኪሎ እንኳን ብትሞላ ከግማሽ በላዩን የሚመዝነዉ ጭንቅላቷ እንደሚሆን ያስታዉቃል፡ ዓይኖቿ ወደ ዉስጥ
መቀበራቸዉ ሳያንስ ከተመለከቱም የሚመለከቱት ቁልቁል ብቻ ነዉ፡ እንቅስቃሴ የሚባል የላትም፡ የተኛ ሰዉ እንኳን ሲተነፍስ ሆዱ ላይ ብቅ ጥልቅ ይታይበታል፡ ልጄ ግን ጸጥ ብላለች፡ እኔን ልጄ!
“መቼስ እግዚአብሔር ምን ይሉታል?” አልሁ፣ ተአምሩን ለእኔም ያልገለጠልኝን አምላክ በመቀየም እና በማመስገን መካከል ሆኜ:
“ኧረ እንጃ። ከፊት ለፊትሽ ግን እንዲህ ነዉ የማይሉት ፈተና እንዳለ ልዋሽሽ አልፈልግም: ትእዛዝ ተቀባይ ነርቮች ብዙዎቹ በትክክል አይሠሩም: ስፓይናቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ ከጠበቅናቸዉም በላይ ሆነዉ

👍30
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ሚስተር ካርይል ከካስል ማርሊንግ ወደ ዌስትሊን እንደ ተመለስ ጥፋቱ እንዳይሰማበት ለመደበቅ የተገደደ ተማሪ ይመስል ተጨነቀ ምንም እንኳን ሰውየው ነገሩ ሁል ጊዜ ግልጽ ቢሆንም • በአሁኑ ጊዜ የተፈጸውን ነገር ከመግለጽ መቆጠቡ የተሻለ መስሎ ታየው ምክንያቱም እኅቱ የሱን ጋብቻ እንድትሰማ የማትፈልግ ከመሆኗም በላይ ለመልከ ቀና ሴቶች ደግሞ አዘኔታም ፍቅርም ስላልነበራትና ወይዘሮ ሳቤላንም እንደማትወዳት ያውቅ ስለነበር ነው ስለዚህ ነገሩ
ከሚስ ካርላይል ጆሮ የደረሰ እንደሆነ የምትቃወመውና ምናልባትም ጋብቻቸውን ለማፍረ
መሞከሯ እንደማይቀር አሰበና ተነጋግሮ መምጣቱን ደበቃት እንዲያውም ኢስትሊን ለመከራየት መጥተው የነበሩትን ሰዎች ከልክሎ እንደ መለሳቸው እንኳን አልነገራትም "
ሚስተር ካርላይል ከካሰል ማርሊንግ ከተመለሰ ከሶስት ሳምንት በኋላ ባርባራ ሔር አንድ ቀን ማታ ሚስ ካርላይልን ለማየት መጥታ ከተለመደው ሰዓት ቀደም
ብለው ሻይ ሊጠጡ ሲሉ አገኘቻቸው "
ቀደም ብለን ራት በላንና አርኪባልድ ሻይ ሳይጠጣ እንዳይቀር ብዬ ገበታ ሲነሳ ወድያው ቶሎ ሻይ እንዲቀርብ አዘዝኩ ” አለቻት ሚስ ካርላይል ።
ባልጠጣም ምንም አይለኝ” አለ ሚስተር ካርይል ገና የማከናውነው ብዙ ሥራ አለብኝ።
“ ለምን ተብሎ? እኔም ካልጠጣህ ደስ አይለኝም " ቆብሽን አውልቂው ባርባራ ሥራው ሁሉ ከሰው የተለየ ነው ይውልሽ ነገ ወደ ካስል ማርሊንግ ልሔድ ነው ይላል እስከ ዛሬ ዝም ብሎ ገና አሁን ነው የነገረኝ ”
ታመመ የተባለው ሰውዬ እስከ ዛሬ እዚያ ነው እንዴ ያለው ?
“ እስከ ዛሬ እዚያ ነው " አለ ሚስተር ካርላይል "
ባርባራ ስለምትቸኩል አይሆንም ብትልም በግድ ሻይ ለመጠጣት እንድትቀመጥ ሆነ » ሚስ ካርላይል ደግሞ ባርባራ ንግግሯን ሳትጨርስ አቋረጠቻትና
ወንድሟን ዞር ብላ ዕቃውን ልታዘጋጅለት እንደምሔድ ነገረችው "
“ አይ የለም ” አላት ፈጠን ብሎ " ዕቃውን እኔ ራሴ አሰናዳዋለሁ ፒተር ሻንጣውን ወደ ክፍሌ አስገባልኝ » ትልቁን ነው ... ገባህ ? ”
“ ትልቁን ” ብላ ጮኸች ያለ እሷ ጣልቃ ገብነት ምንም ነገር የማያልፈው ኮርነሊያ“ ደሞ ቤት የሚያህል ሻንጣ እየጎተትክ የምትሔደው ለምንህ ነው?
“ከልብሴ ሌላ ጨምሬ የምይዛቸው ሰነዶችና ሌሎችም ነገሮች አሎኝ "
“ እኔ እንተ የምትላቸውን ነገሮች ሁሉ በትንሹ ሻንጣ ማስገባት እችላለሁ ብላ ድርቅ አለች ኮርነሊያ « “ እሞክረዋለሁ አንተ ብቻ የምትፈልገውን ዕቃ ንገረኝ ፒተር ... ትንሹን ሻንጣ ከጌታህ ክፍል አስገባ " አለችው "
ሚስተር ካርሳይል ፒተርን ሲያየው መልሶ አየውና ራሱን በእሽታ ነቀነቀ“ ዕቃዩን ራሴ ሳሰናዳው ነው ደስ የሚለኝ ኮርነሊያ እጅሽን ደግሞ ምን አደረግሽው? ” አላት "
“ዕብደት አታውቅም አለችው ሚስ ኮርነሊያ አለልቧ ከቢላዋ ጋር ስትጫወት ጣቷን ቆረጠችና ' ' ልጥፍ የሚል ፕላስተር አለህ ? " አለችው "
“ የኪስ ማስታወሻ ደብተሩን ከጠረጴዛው ላይ አድርጎ ገለጠውና ከውስጡ አንድ ጥቁር ፕላስተር ሲያወጣ የማያርፉት የኮርነሊያ ዐይኖች አንድ ደብዳቤ ከደብተሩ ውስጥ አዩ " ምንም ሳትጠይቅ እጅዋን ሰዳ ብድግ አድርጋ ገለጠችው።
“ ከማን የመጣ ነው የሴት ጽሕፈት ነው "
ለማንበብ ከመሞከሯ በፊት ሚስተር ካርላይል እጁን ዘርግቶ ሸፈነባትና ፡ “ይቅርታ ኮርነሊያ. . . . የግል ደብዳቤ ነው " አላት "
“ ኧረ ወዲያ ምስጢር ብሎ ነገር ' ከኔ የሚደበቁ የምስጢር ደብዳቤዎች እንደ ማይዶርሱ እርግጠኛ ነኝ የፖስታ ቤቱ ማኅተም የትናንት ነው ።
“ ይሀን ደብዳቤ ልቀቂልኝ” አላት ሚስ ካርላይል በዚያ ረጋ ያለ ሥልጣን አዘል ድምፁ ሲነግራት ከበዳትና ለቀቀችለት "
"ምን ነካህ... አርኪባልድ?”
ምንም ” አላት ፕላስተሩን ከአወጣላት በኋላ ደብዳቤውን ወደ ኪስ ደብተሩ እየመለሰ “ የወንድ ልጅ ደብዳቤዎችን ማየት ደግ አይደለም " ነው እንዴ ! ባርባራ ? '' አለና ወደሷ እየተመለከተ ሣቀ " በዚህ ጊዜ ፊቱ ሲለዋመጥ አየችው "
በቀላሉ የማትለቀው ኮርነሊያ ደግሞ ፡ “ ደብዳቤው የቬን ቤተሰብ ዐርማ ታትሞበታል ” አለችው "
“ የቬን ዐርማ ከደብዳቤው ላይ ኖረውም አልኖረውም ጽሑፉ ለኔ ዐይኖች ብቻ የተላከ ነው ” ሲል ቁርጥ ያለው አነጋገሩን ሰምታ ዝም አለች
ሁሉም ዝም ሲባባሉ ጊዜ 'ባርባራ ዝምታውን ጥሳ ንግግር ጀመረች "
“ ባሁኑ ጊዜ ማውንት እስቨርኖችን ትጠይቃቸዋለህ እንዴ ? ”
“ አዎን ”
“ስለ ወይዘሮ ሳቤላ ጋብቻ ምን ይወራል... ልጄ የሰማኸዉ ነገር አለን ? ”
“እኔ የሰማሁትንና ያልሰማሁትን ማስታወስ ይቸግረኛል ባርባራ ሻይሽ ሱካር ሳያንሰው አልቀረም " አይደለም እንዴ ! ”
“ አዎን ጥቂት ” ስትለው ' የሱኳሩን ማቅሬቢያ ጠጋ አደረገና ተው ከመባሉ በፊት አምስት አንኳር አንሥቶ ጨመረበት።
“ለምንድነው ይህን ያህል?” ስትለው ከት ብሎ ሣቀና የምሠራውንም ረሳሁ "
ባርባራ ይቅርታ አድርጊልኝ ኮርኒሊያ ሌላ ስኒ ትሰጥሻለች ” አላት "
“ ባንድ ስኒ ሻይ የባከነው ይኸ ሁሉ ሱኳርስ ቀላል ነገር መሆኑ ነው ? ” አለችው ኮርኒሊያ ቆጣ ብላ "
ሻይ ተጠጥቶ እንደ አበቃ ባርባራ ለመሔድ ተነሣች “ አቤት ጨለመብኝ በዚህ ጨለማ ብቻዬን በመውጣቴ እማማ ትቆጣኛለች ” አለች "
“እርኪባልድ ያደርስሻል " አለቻት ኮርኒሊያ "
ባርባራ ሚስ ኮርነሊያን ተሰናብታ ከሚስተር ካርላይል ጋር ወጣች ጃንጥላዋን ተቀበላትና በእርሻዎቹ መካከል አቋርጠው እየተጫወቱ ሔዱ።
ባርባራ ሳቤላ ቬንን ልትረሳት አልቻለችም ሚስተር ካርይል ወደ ኢስትሊን ሲመላለስ በነበረበት ጊዜ ከልቧ አድሮባት የነበረው ቅናት አልጠፋም " አሁንም
በጫወታቸው ወደዚሁ ርዕስ ተመለሰችበት "
ወይዘሮ ሳቤላ ቬን ስለ ማግባቷ ጉዳይ የሰማኸው እንዳለ ጠይቄህ እኮ መልስ አልሰጠኸኝም .. አርኪባልድ ” አላችው "
አኔ የምሰማውን ሁሉ ማስታወሱ አልችልም ብዬ አልነገርኩሽም? ”
“ብልኸኝ ነበር ? ”
“አስጨንቀሽ ያዝሺኝ አይደለም እንዴ ! " ብሎ ሣቅ አለና አዎን ነምቴገባ ይመስለኛል ” አላት "
" ማንን ? ” አለችው ያስጨነቃት ሐሳብ እንደ መልቀቅ እያደረጋት "
አሁንም ፈገግታው ከከንፈሩ ሳይለቅ “ ሁሉን ነገር ባንድ ጊዜ ማወቅ እችል ይመስልሻል ?
ምናልባት ከካስል ማርሊንግ ስመለስ ልነግርሽ እችል ይሆናል "
“ በል አረጋግጠህ እንድትመጣ ምናልባት ሎርድ ቬንን ይሆን የምታገባው !ማን እንደሆነ እንጃ እንጂ ብዙ ጋብቻዎች የሚጠነሰሱት ብዙ ጊዜ ከመቀራሪብ ነው ብሏል ” ስትለው ትክ ብሎ አያትና ሣቀባት "
“እንዴት ያለሽ ግምት ዐዋቂ ነሽ ? ሎርድ ሔል እኮ ያምስት ወይም የስድስት ዓመት ልጅ ነው " ይልቁንስ ካነሣሺው እንዴት ያለ ጥሩ ልጅ መሰለሽ " እኔ ልጆች
ቢኖሩኝ እንደሱ ቢሆኑልኝ ነው የምመኘው "
ድፍን ዌስት ሊንን ሳታገባ መቅረትህን ካሳመንከው በኋላ እንዲህ መናገርህም
ትልቅ የምሥራች ነው "
“ እኔ ከዌስትሊን ሰው አላገባም ብዬ ቃል መግባቴን አላስታውስም
ባርባራ ሣቀች” “ ዌስትሊን በመልክ ግምት ይሔዳል መሰለኝ አንድ ሰው ሠላሳ ዓመት ከሞላው ...ኀ
“ እና ታዲያ ሠላሳ አልሞላኝ ደግሞ ሠላላ ሳይሞላኝ አባ ወራ እሆናለሁ” አላት ሚስተር ካርላይል ከመንገዱ ዳር የነበረውን የድንበር ቅጠል በያዘው ጃንጥላ ያለ ልቡ እየጨፈጨፈ ሲጓዝ "
ሚስትህን መርጠህ አኑረሃል ማለት ነው ? ”

👍13
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...የምስጋና ቀንና ገና እንደቀረበ ሊያስታውሰን ህያው የቀን መቁጠሪያችን የሆነው የረጅሙ አትክልት አገዳ ትንሽ እምቡጥ ያዘ፡ ያልደረቀው ብቸኛ አትክልታችን እሱ ብቻ ስለነበር በጣም የምንወደው ንብረታችን ነበር᎓ ጣሪያው ስር ካለው ክፍል አንስተን አንድ ሞቃት ምሽት ከእኛ ጋር እንዲያሳልፍ ወደ መኝታ ክፍላችን ወሰድነው: በየማለዳው ገና ሲነጋ ኮሪ ያቺ እምቡጥ ምሽቱን በደህና ማሳለፏን ለማረጋገጥ ሮጦ ሄዶ ይመለከታታል ኬሪም ተከትላው ሄዳ አጠገቡ ትቆምና ሌሎች ሲደርቁ ብቻዋን በመቆየቷ ያቺን ድል አድራጊ ጠንካራ ተክል ታደንቃለች አፈሩ ውሀ የሚፈልግ መሆኑ መንትዮቹ ቢሰማቸውም፣
ግድግዳው ላይ የተሰቀለውን ቀን መቁጠሪያ እየተመለከቱ ቀኑ አረንጓዴ ተሰምሮበት፣ አትክልቱ ውሀ የሚፈልግበትን ቀን እንዲያመለክት ይጠብቃሉ።
ያ ስለማይሆንና በራሳቸው ለማድረግም እርግጠኛ ስለማይሆኑ ወደ እኔ ይመጡና “አትክልቱን ውሀ እናጠጣው? ውሀ የጠማው፦ ይመስልሻል?” ሲሉ ይጠይቁኛል።
ስም የምንሰጠውና የኛ የምንለው ግዑዝም ሆነ ህያው ነገር የለንም
አትክልታችን ብቻ ከኛ ጋር ለመኖር ቆርጧል ኬሪም ሆነች ኮሪ ከባዱን ማሰሮ ይዘው በቅርብ የፀሀይ ብርሃን ወደሚኖርበት ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ለመውሰድ ጥንካሬ አልነበራቸውም፡ ስለዚህ እኔ አትክልቱን እንድይዘው ተፈቀደልኝ ሲመሽ ደግሞ ክሪስ ወደታች ይመልሰዋል በእያንዳንዱ ምሽት ተራ በተራ ቀኖቹን በቀይ ቀለም ምልክት እናደርጋለን፡ እስካሁን መቶ ቀኖች
ላይ ምልክት አድርገናል።
ክረምቱ በመግባቱ ዝናብ መጣ፡፡ ሀይለኛ ንፋስ እየነፈሰ ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ከባድ ጭጋግ የጠዋቷን የፀሀይ ብርሀን ይከልላታል ምሽት ላይ ደግሞ
ነፋሱ የደረቁትን የዛፍ ቅርንጫፎችን ከቤቱ ጋር ሲያስታክካቸው ከእንቅልፌ
ያባንነኝና የሆነ አስፈሪ ነገር መጥቶ የሚበላኝ እየመሰለኝ ትንፋሽ ያጥረኛል በኋላ ላይ ወደ በረዶ ሊለወጥ የሚችል ዝናብ እየወረደ ባለበት ቀን እናታችን
ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ የምስጋና ቀን በዓል እንዲመስልልን ጠረጴዛችንን
የምናስጌጥባቸው የሚያማምሩ የግብዣ ጌጣጌጦች ይዛ ወደ መኝታ ክፍላችን ገባች በተጨማሪም ብሩህ ቢጫ ቀለም ያለው የጠረጴዛ ልብስና ጥልፍ
ያለበት ብርቱካናማ የአፍ መጥረጊያ መሀረቦች ይዛ ነበር።
የያዘችውን ዕቃ በሩ አጠገብ ያለው አልጋ ላይ እያስቀመጠችና ለመውጣት ፊቷን እያዞረች: “ነገ እራት ላይ እንግዶች አሉብን” ስትል አብራራች: “እና አንደኛው ለእኛ ሌላኛው ደግሞ ለሰራተኞቹ የሚሆን ሁለት ዶሮዎች
ይጠበሳሉ፡ ነገር ግን አያታችሁ የሽርሽር ቅርጫት ይዛ በምትመጣበት ወቅት አይደለም ግን አትጨነቁ፣ ልጆቼ በምስጋና ቀን ለቀኑ የሚመጥን ምግብ
ሳይኖራቸው በዓልን አያሳልፉም እንደምንም ብዬ እኛ ከምንበላው ምግብዐለእናንተ የማመጣበትን መንገድ እፈልጋለሁ ለአባቴ ራሴ እንዳቀርብለት እፈልጋለሁ ብዬ ብዙ አዘጋጅና ለእሱ የማቀርበውን ሳሰናዳ በሌላ ትሪ ደግሞ
ለእናንተ ላስቀምጥላችሁ እችላለሁ ነገ ሰባት ሰዓት አካባቢ ጠብቁኝ” አለች።
በትልቅ ሳህን የሚቀርብ ትኩስ የምስጋና ቀን ምግብ ለመብላት በመጠበቅ ደስታ ውስጥ ጥላን ልክ በበሩ በኩል እንደሚገባው ነፋስ ገብታ ወጣች።
“የምስጋና ቀን ምንድነው? አለች ኬሪ።
“ከምግብ በፊት ከማመስገን ጋር አንድ ነው” ሲል ኮሪ መለሰላት በአንድ በኩል ልክ ነው ብዬ አስባለሁ።
ሰባት ሰዓት መጣ፣ ሄደ። ኬሪ ጮክ ብላ አጉረመረመች “አሁን ምሳችንን እንብላ፣ ካቲ!”
“ታገሺ እናታችን ልዩ ትኩስ ምግብ፣ ዶሮና ማባያዎቹ ሁሉ ያሉበት ትሪ ይዛ ትመጣለች ይኼኛው ለእራታችን ነው ምሳ አይደለም” አልኳት: የእኔ የቤት እመቤትነት ስራ ለጊዜው አለቀና በደስታ አልጋው ላይ ጥቅልል ብዬ
ማንበብ ጀመርኩ።
ካቲ ሆዴ ትዕግስት የለውም” አለ ኮሪ፤ ክሪስ በሸርሎክ ሆልምስ ታሪክ ተመስጧል፡ መንትዮቹ ሆዳቸውን ፀጥ እንዲል አድርገው እንደ እኔና እንደ ክሪስ ቢያነቡ ጥሩ አልነበር?
“የተወሰኑ ዘቢቦች ብላ ኮሪ”
“ምንም የተረፈ የለም”
“ለውዝ ብላ”
“ለውዙም ሁሉም አልቋል”
“እሺ ብስኩት ብላ”
“የመጨረሻውን ብስኩት ኬሪ በልታዋለች”
“ኬሪ ብስኩቶቹን ለምን ለወንድምሽ አላካፈልሽውም?”
“የዚያን ጊዜ አልፈልግም ብሎኝ ነው”
ስምንት ሰዓት ሆነ አሁን ሁላችንም እርቦናል። ሁልጊዜም ልክ ስድስት
ሰዓት ላይ ነው የምንበላው፡ እናታችንን ምን አዘገያት? በመጀመሪያ ራሷ ልትበላና ከዚያ ልታመጣልን ነው? ግን'ኮ እንደዚያ አላለችንም ነበር።
ዘጠኝ ሰዓት አለፍ እንዳለ እናታችን በችኮላ ገባች ከላይ በሳህኖች የተሸፈነ ትልቅ ብራማ ቀለም ያለው ትሪ ይዛለች። ሰማያዊ የሱፍ ቀሚስ ለብሳለች። ፀጉሯ ደግሞ ከፊቷ ላይ ተሰብስቦ ኮሌታዋ አካባቢ ዝቅ ብሎ በፀጉር መያዣ
ተይዟል፡ እንዴት ታምራለች! “እንደራባችሁ አውቄያለሁ።" ወዲያውኑ ይቅርታ መጠየቅ ጀመረች: “በመጨረሻዋ ደቂቃ ላይ አባቴ ሀሳቡን ቀይሮ
ተሽከርካሪ ወንበሩን በመጠቀም ከእኛ ጋር ለመብላት ወሰነ።” በመጠኑ ፈገግ አለችልን። “ካቲ ጠረጴዛውን ቆንጆ አድርገሽ አዘጋጅተሽዋል። ሁሉንም ነገር
በትክክል ነው ያደረግሽው: እኔ ግን አበቦቹን ስለረሳሁ ይቅርታ: መርሳት አልነበረብኝም: ዘጠኝ እንግዶች ነበሩብኝ ሁሉም እያዋሩኝና ለብዙ ጊዜ የት
እንደነበርኩ ሺ ጥያቄዎችን እየጠየቁኝ ነበር እና ጆኒ ሳያየኝ የአስተናጋጆቹ ጓዳ ውስጥ መግባት እንዴት ችግር እንደሆነ አታውቁም ያ ሰው ከኋላው
ሳይቀር አይን ያለው ነው የሚመስለው ማንም ሰው እንደኔ ከምግብ ላይ አስር ጊዜ ቁጭ ብድግ ሲል አይታችሁ አታውቁም
“እንግዶቹ ጨዋ እንዳልሆንኩ፣ ወይም ሞኝ እንደሆንኩ ሳያስቡ አይቀርም ግን ያም ሆኖ ሳህኖቻችሁን መሙላትና መደበቅ ችዬ ነበር ከዚያ ወደ መመገቢያው ጠረጴዛ መመለስ፣ ፈገግ ማለትና ሌላ ክፍል ገብቼ አፍንጫዬን
ከማፅዳቴ በፊት ደግሞ አንዴ መጉረስ ነበረብኝ፡፡ መኝታ ክፍሌ ውስጥ ባለው የግል መስመር የተደወሉልኝን ስልኮች መመለስና ማንም እንዳይገምት ድምፄን
መቀነስ ሁሉ ነበረብኝ የዱባ ኬክ ላመጣላችሁ ፈልጌ፣ ጆን ቆራርጦ ሳህኖች ላይ አድርጓቸው ነበር። ምን ማድረግ እችላለሁ? አራት ኬኮች ቢጠፉበት ማወቁ አይቀርም:"በአየር ላይ ሳመችን ደስ የሚል ግን የችኮላ ፈገግታ ሰጠችንና ከበሩ ወጥታ ተሰወረች: አምላኬ ሆይ! እውነትም ህይወቷን አወሳስበንባታል! ለመብላት ወደ ጠረጴዛው ተጣደፍን፡ ክሪስ አንገቱን ዝቅ አድርጎ ጆሮዎች ልብ የሚነካ ምስጋና በሚሰሙበት በዚህ ቀን እግዚአብሔርን ብዙም የማያስደስት የችኮላ ምስጋና አቀረበ፡ “ጌታ ሆይ፣ ስለዚህ ስለዘገየ የምስጋና ቀን ምግብ
እናመሰግንሀለን፡፡ አሜን!”
በክሪስ ቀጥታ ወደ ጉዳዩ የመግባት ባህርይ እየሳቅኩ፣ አስተናጋጃችን እርሱ በመሆኑ ሳህን አቀበልኩትና አንድ በአንድ ምግባችንን ሳህኖቻችን ላይ አደረገልን ምግቦቹ እየቀዘቀዙ ነበር: “ቀዝቃዛ ምግብ አንወድም!” አለች ኬሪ ሳህኗ ላይ የተደረጉላትን ምግብ እየተመለከተች።
የእውነቴን ለእናቴ አዘንኩላት ለእኛ ትኩስ ምግብ ለማምጣት ስትሞክር የራሷን ምግብ በስርዓት ሳትበላ በእንግዶቹ ፊት እንደሞኝ ተቆጥራ፣ አሁን ደግሞ እነዚህ ሁለቱ ሶስት ሰዓት ሙሉ ራበን እያሉ ሲነጫነጩ እንዳልቆዩ
ስለቀዘቀዘ አንበላም ይላሉ… አይ ልጆች!
ክሪስ በየጠዋቱ በሽርሽር ቅርጫት መጥቶ ከሚወረወርልን የችኮላ ምግብ በተለየ በሚጥም ሁኔታ የተሰራውን ምግብ በመብላት በደስታ አይኖቹን ጨፈነ። እውነት ለመናገር አያታችን አንድም ቀን ረስታን አታውቅም።

👍31❤6🥰1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
.... ሄሪ ዙሪያ ገባውን ተመለከተና ‹‹እዚህ ክፍል ውስጥ አራቱ ወንበሮች
ክፍት ናቸው፣ ሌሎቹ ክፍሎች ውስጥም እንዲሁ ነው፡፡››
‹‹አልተሳሳትክም፧ ይህ ክፍል ቀን ቀን አስር ሰው፣ በመኝታ ጊዜ ግን ስድስት ሰው ብቻ ነው የሚይዘው፡፡ ከራት በኋላ መኝታ ስናመቻች ታያለህ፡ እስከዚያው ዘና ብለህ ቁጭ በል›› አለው።
ሄሪ ዊስኪውን እየተጎነጨ ነው፡፡ አስተናጋጁ ታዛዥና ፈጣን ቢሆንም ለንደን ሆቴሎች ውስጥ እንደሚሰሩት አስተናጋጆች ግን ጠብ እርግፍ
አይልም፡፡ አሜሪካውያን አስተናጋጆች የተለየ የደምበኛ አቀባበል ስርዓት
ሳይኖራቸው አይቀርም ሲል ገመተ፡ በለንደን ሆቴሎች አስተናጋጆች በአክብሮት አንገታቸውን እያጎነበሱ ‹‹ጌታዬ ምን ልታዘዝ›› የሚሉትም አቀባበል የበዛ ትህትና ሆኖ ነው ያገኘው፡፡
ሻምፓኟን እየተጎነጨች መጽሔቷን የምታገላብጠውን ማርጋሬት ኦክሰን ፎርድን መወዳጃው ሰዓት ሳይደርስ አይቀርም ሲል አሰበ ሄሪ፡፡ ከእሷ ዓይነት ኮረዶች ጋር ብዙ ጊዜ የማገጠ ስለሆነ ሴቶችን የመቅረብ ችግር የለበትም፡
‹‹ለንደን ነው የምትኖሩት?›› ሲል ጨዋታ ጀመረ፡
‹‹ለንደን ውስጥ ቤት አለን ነገር ግን ብዙ ጊዜያችንን የምናጠፋው ገጠር
ነው:፡ አባታችን በርክሻየን የሚባል አገር ርስት፣ ስኮትላንድ ውስጥ ደግሞ
የጠመንጃ ተኩስ መለማመጃ ቦታ አለው›› ስትል በተሰላቸ ሁኔታ መልስ
ሰጠችው ርዕሱ እንዲነሳ እንዳልፈለገች ሁሉ፡
‹‹አውሬ ታድናላችሁ?›› ሲል ጠየቃት፤ሃብታሞች በሙሉ አደን ስለሚወዱና ስለእሱም ማውራት ደስ እንደሚላቸው ስለሚያውቅ፡፡
‹‹ብዙም አናድንም›› አለች ‹‹ከዚያ ይልቅ ተኩስ እናዘወትራለን››
‹‹ተኩስ ታዘወትሪያለሽ?›› ሲል ጠየቃት ተገርሞ ተኩስ የወይዛዝርት
ተግባር እንዳልሆነ ስለሚያውቅ፡፡
‹‹እንደዚህ አይነት የማይረቡ ጥያቄዎችን ለምን ትጠይቀኛለህ?››
አለችው ፊቷን ወደእሱ አዙራ፡
ሄሪ ያልጠበቀው ምላሽ በመሆኑ ደንገጥ አለ፡፡ ቀጥሎ ምን ሊላት
እንደሚችል አላወቀም፡ የዚህ አይነት ጥያቄዎች በርካታ ኮረዶችን ጠይቋል፧
ሁሉም ግን እንደዚህ አይነት ምላሽ አልሰጡትም፡፡ ‹‹እነሱ የማይረቡ ሆነው
ነው?›› ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹እኔ የት እንደምኖር ወይ አደን ላድን አላድን አንተን ምን ያገባሃል?››
‹‹ታዲያ እኮ ባለጸጎች ይህን ነው ሲያወሩ የሚውሉት››
‹‹አንተ ታዲያ ባለጸጋ አይደለህ›› አለችው፡፡
ወደ እንግሊዛዊ የአነጋገር ዘይቤ ተመለሰ፡፡
ማርጋሬት ሳቀችና ‹‹ይሻላል›› አለችው፡፡
‹የአነጋገር ዘይቤዬን ቶሎ ቶሎ መቀየር አልችልም እደነጋገራለሁ››
‹‹እንግዲያው የጅል ጥያቄ የማትጠይቀኝ ከሆነ የአሜሪካውያንን
የአነጋገር ዘይቤህን እታገስልሃለሁ››
‹‹አመሰግናለሁ ማርዬ›› አላት ሄሪ ቫንዴርፖስት ነኝ ብሎ ራሱን አሳምኖ፡፡ ብዙም አስቸጋሪ እንዳልሆነች ገምቷል፡፡ ይህንንም ሁኔታዋን ወዶላታል
‹‹ሽወዳውን ተክነኸዋል›› አለችው፡፡
የውይይታቸውን ርዕስ መለወጥ ፈለገ፡፡ ልቧን እንዴት ማሸነፍ እንደሚችል አልከሰትልህ አለው። ከሌሎች ጋር እንደማገጠው ከእሷ ጋር ለመማገጥ ቀላል እንዳልሆነ አውቋል፡፡
‹‹እኔ ብዙም ትምህርት የለኝም›› አላት፡፡ ብዙዎቹ ባለጸጎች ስለተማሩት
ትምህርት ሲያወሩ ውለው ሲያወሩ ቢያድሩ አይሰለቻቸውም፡፡ ማርጋሬት
እንደ እሷ ካሉ ሴቶች ጋር ስትነጻጸር ጨዋ መሆኗ አስደስቶታል፡፡
‹‹ስለ ትምህርት ሲነሳ ምን እንደሚሰማኝ እኔ ነኝ የማውቀው ምክንያቱም እኔም ብሆን በስርዓቱ አልተማርኩም›› አለች፡፡
‹‹ይሄ ሁሉ ገንዘብ እያላችሁ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች ‹‹ይኸውልህ ትምህርት አልተማርንም››
ሄሪ ጆሮውን ማመን አቃተው፡ ለሰራተኛው መደብ የለንደን ነዋሪ
ልጅን ትምህርት ቤት አለማስገባት እንደ ውርደት ነው የሚቆጠረው፡
ተማሪዎች ጫማዎቻቸውን ለጫማ ሰፊ ሲሰጡ ከትምህርት ቤት አስፈቅደው ይቀራሉ ተለዋጭ ጫማ ስለሌላቸው፡፡ ‹‹ነገር ግን ልጅን ትምህርት ቤት
አለማስገባት ማለት የሚታሰብ አይደለም›› አለ ሄሪ፡፡ ‹‹የማይታመን ነው፡
ሃብታሞች ሁሉን ማድረግ የሚችሉ ነበር የሚመስለኝ፡፡››
‹‹አባታችን ግን ለየት ያለ ሰው ነው››
‹‹ወንድምሽ?›› ሲል ጠየቃት ባገጩ ወደ እሱ እያመለከተ።
‹‹ኦ እሱ ኢንተን ነው የሚማረው›› አለች በምሬት በለንደን ውስጥ አሉ
ከሚባሉት ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱን እየጠቀሰች ‹‹ለወንዶች ሲሆን
ጉዳዩ የተለየ ነው››
ሄሪ ‹‹ይህ ማለት ከአባትሽ ጋር ለምሳሌ እንደ ፖለቲካ በመሰለ ጉዳይ ልዩነት አለሽ ማለት ነው?››
‹‹አዎ ልዩነት አለን፡፡ እኔ የሶሻሊዝም ደጋፊ ነኝ፡፡››
‹‹እኔ የኮሚኒስት ፓርቲ አባል ነበርኩ›› አለ፡፡ እውነቱን ነው፡፡ አስራ
ስድስት ዓመት ሲሞላው አባል ሆነና ከሶስት ሳምንት በኋላ ወጣ፡፡
ይህን ስትሰማ ለወሬ አቆበቆበች ‹‹ለምን ወጣህ?››
እውነታው የፖለቲካ ስብሰባዎች ስልችት ስለሚሉት ነው፡፡ ‹‹በቃላት
መግለጽ ይከብደኛል›› አላት፡፡
እሷ ግን በቀላሉ አለቀቀችውም ‹‹ለምን እንደተውከው ማወቅ
እፈልጋለሁ››
“ለኔ እነዚያ ስብሰባዎች የሰንበት ትምህርት ቤትን ያስታውሱኛል›› አላት።
ይህን ስትሰማ በሳቅ ተንከተከተች፡፡
‹‹ለማንኛውም የወዛደሩ መደብ በላቡ ሰርቶ የሚያገኘውንና በበዝባዦች
የተነጠቀውን ሀብት ለአምራቹ ለራሱ በመመለስ በኩል ከኮሚኒስቶች በተሻለ
ሁኔታ ሳልሰራ አልቀረሁም››
‹‹እንዴት ማለት? ሀብታሞችን ብቻ ነው የምትመነትፈው ማለት ነው?
‹‹ደሀው የሚዘረፍበት ምንም ምክንያት የለም ምንም ስለሌለው፡››
እንደገና ሳቀችና ‹‹መቼም በስርቆት ያገኘኸውን ሀብት እንደ ሮቢን ሁድ አታከፋፍልም?››
‹‹እኔ የእርዳታ ድርጅት አይደለሁም›› አለ ትከሻውን እየሰበቀ ‹‹ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ደሃ የምረዳበት ጊዜ አለ››
‹‹የሚገርም ነው›› አለች ‹‹እንዳንተ ያሉ ሰዎች መኖራቸውን አውቃለሁ፡ ነገር ግን ከእንደዚህ ያለ ሰው ጋር በአካል መገናኘት ሌላ ነገር ነው:.
‹ብዙም አታካብጂው ነፍሷ አለ በሆዱ፡፡ ስለ እሱ ማወቅ የሚፈልጉ ሴቶች ሰላም ይነሱታል፡፡ ‹‹እኔ ከሌላው ምንም የምለይበት ነገር የለም የመጣሁት አንቺ ከምታውቂው የህብረተሰብ ክፍል ነው፡››
በዚህ ርዕስ ላይ ብዙ ተነጋገርን፤ አሁን ሌላ ርዕስ መቀየር ይኖርብናል› ሲል አሰበና ‹‹ድህነቴን እንዳስታውስ አድርገሽ እፍረት ውስጥ ከተሺኛል›› አለ ፊቱ በሃፍረት ቀልቶ፡፡
‹‹ኦ ይቅርታ›› አለች ተሰምቷት፡፡ ትንሽ አሰብ አደረገችና ‹‹አሜሪካ
ለምን ትሄዳለህ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ከሬቤካ ሞግሃም ፍሊንት ለማምለጥ››
ሳቀችና ‹‹አይ የምሬን ነው የምልህ››
ይቺ ሴት አንዴ ከያዘች የምትለቅ አይደለችም አለ በሆዱ ‹‹እስር ቤት
እንዳልገባ ነው አገር ለቅቄ የምሄደው››
‹‹እዚያ ስትደርስስ ምን ልትሰራ ነው ያሰብከው?››
ካናዳ አየር ኃይል ለመግባት ሃሳብ አለኝ፡፡ አይሮፕላን ማብረር መማር እፈልጋለሁ››
‹‹እንዴት ደስ ይላል!››
‹‹እናንተስ ለምንድነው አሜሪካ የምትሄዱት?››
‹‹አገር ጥለን እየጠፋን ነው›› አለች እያንገሸገሻት፡፡
‹‹ምን ማለትሽ ነው?››
‹‹አባታችን የፋሺስት አስተሳሰብ አራማጅ እንደሆነ መቸም ሳታውቅ
አትቀርም››
ሄሪ ራሱን በአዎንታ ነቀነቀ ‹‹ጋዜጣ ላይ አንብቤያለሁ››
‹‹በእሱ አስተሳሰብ ናዚዎች ግሩም ሰዎች ስለሆኑ ከእነሱ ጋር ውጊያ መግጠም ተገቢ አይደለም ብሎ ያምናል፡ አገር ውስጥ ከቆየም ወህኒ መውረዱ አይቀሬ ነው፡››
‹‹ስለዚህ አሜሪካ ልትኖሩ ነዋ››

👍14👏1
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታረ
“ሶራ ልታስብበት ይገባል" አለችው በጥሞና እያየችው፡
"ወደ ኢትዮጵያ አብሬሽ ልሂድና የአያትሽን የትውልድ ቦታ ላፈላልግሽ እፈልጋለሁ፡፡ ያሳየሽኝ መቀመጫ ታችኛው የኦሞ ወንዝ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ማህበረሰቦች በሙሉ ይጠቀሙበታል። ኤርቦሬ
ሐመር በና ካሮ መቀመጫው በእርግጥም የኦሞ ህዝቦች ብቻ
እንደሆነ አምናላሁ" አላት።
ጥሩ! እኔ የተዘጋጀሁት ለአንድ ሰው በሚበቃ ባጀት ነው" በግልፅ ችግሯን ገለፀችለት፡
“እኔ ደግሞ የራሴን እችላለሁ በዚያ በኩል አታስቢ"
አመሠግናለሁ ሶራ በእውነት አንተን ማግኘቴ ያላሰብሁት
እድል ነው" ብላ ፈገግ አለችለት::
ሶራና ኮንችት በዚህ መልክ ለአፍሪካ ጉዞዋቸው
መሰናዶአቸውን አብረው ቀጠሉ፡፡
ከሁዌልቫ ሊዝበን በመርከብ የሚፈጀወ ጊዜ ግማሽ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከጅበላርታር ለንደን በሚወስደው የጉዞ መስመር መርከቡ
አቅጣጫውን ካስተካከለ በኋላ ተጓዡ እንደየግል ፍላጎቱ ተሰማራ፡፡
ኮንችትና ሶራ በመርhቡ ግራ ጎን ባለው ማማ ላይ ወጥተው በርቀት የተዘረጋውን የአትላንቲክ ውቅያኖስ እያዩ ተቀምጠዋል፡፡
ኮንችትና ሶራ የለበሱት ነጭ ቲሸርት ነው፡፡ በሁለቱ መካከል የአለባበስ ልዩነቱ ኮንችት ነጭ አጭር ቀሚስ በሰፊ ቀበቶ ሶራ
ደግሞ ቡላ ሲልክ ሱሪ መልበሳቸው ነው፡፡ ሁለቱም ጥቁር የፀሐይ መነፅር አድርገዋል። ቀኑ ሞቃታማና ፀሐያማ ነው፡፡
ወደ ሊዝበን የመሄዱን ሐሳብ ያመጣችው ኮንችት ናት ሶራን የተለያዩ ቦታዎችን ሙዚዬሞችን ታሪካዊ ቦታዎችን መዝናኛዎችን… እንዲያይ ብዙ ጊዜ እየጋበዘች ወስዳዋለች፡፡
ስለ ፖርቹጋሎች ምን ታውቃለህ?" አለችው አንድ ቀን በማድሪድ ከተማ መናፈሻ ውስጥ እንደተቀመጡ፡፡
“ባህረተኞችና ቅኝ ገዥዎች እንደነበሩ"
“አዎ! ፖርቹጋሎች ማንም እሚያውቃቸው በባህር ላይ
ህይወታቸውና ለቅኝ ገዥነት በብዙው የዓለም ክፍል በተለይም በአፍሪካና በላቲን አሜሪካ ያደርጉት የነበረውን ቅኝት ነው፡ ይህ ጥንት ሌላው ስለእነሱ ያውቅ የነበረው እውቀት ነው በአሁን ሰዓት ግን ፖርቹጋል ብዙ ቱሪስት የሚስተናገድባት አገር ናት።
“ሙዚየሞቻቸው የዓለምን ቅርስ የያዙ ናቸው ይባላል።
ስለ ዓለም ይበልጥ ማወቅ የማፈልገው ይህ ትውልድ ደግሞ ቅርሶች አሉ የተባለበት መጉረፉ የተለመደ ነው፡፡
“አፍሪካ የራሷ ካሏት ቅርሶች ይልቅ በአውሮፓ ያሏት ቅርሶች ይበልጣሉ፡ የሚያሳዝነው ግን አፍሪካ ለቅርሷ የባለቤትነት
መብት የላትም፡፡ በኮለኒያሊስቶች የተዘረፈችው ቅርስ አሁንም የእነሱ ኪስ ማድለቢያ ነው፡፡
“ከኢትዮጵያ የመጡ
ቅርሶች ከዚህ በፊት ፈረንሳይ እንግሊዝ ጣሊያን… ሄጄ አይቻለሁ፡፡ ፖርቹጋልም እንደዚሁ ብዙ
የሃይማኖት መጽሐፍትና የታሪክ ቅርሶች አሉ: አንዳንዴ ሳስበው እንዲያውም ኢትዮጵያውያን
የታሪክ የባህል ተመራማሪዎች ወደ ፊት በአገራቸው ታሪክና ባህል ላይ ምርምር ማድረግ ቢፈልጉ ዋቢ ቅርሶችን ለማየት ወደ አውሮፓ ብቅ ማለታቸው የግድ
ይመስለኛል
“አውሮፖና በሌላው የሰለጠነው ዓለም አንድ ወቅት የቅርስ ዝርፊያ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በስምምነት አንዱ ዘንድ ያለው ወደ ሌላው እየተመለሰ ነው። ባይመለስ እንኳን የዛ ቅርስ ባለቤት
የሚሆነው በመጀመሪያ ባለቤት የነበረው አገር ነው፡፡ ለዚህ ውጤት
ግን ብዙዎች ልሳናቸው እስኪዘጋ እየጮሁ ታግለዋል፡፡ ግዞት ስደት
እስራትም ደርሶባቸዋል: አሁን ግን ቀስ በቀስ ህልማቸው እውን
እየሆነ ነው:
ሶራ አንተም ፖርቹጋል ያሉትን ሙዚየሞች ስታይ
እርግጠኛ ነኝ ብዙ የአገርህን ቅርሶች ታያለህ የኢትዮጵያ ቅርሶች
የሚል ጽሁፍ ግን አይታይባቸውም፡፡ አንድ እውነት ግን በህሊናህ
ይመጣል! ቅርስ ለአንድ ሀገር ህዝብ ማንነት ምን ያህል አስፈላጊ
መሆኑን ትገነዘባለህ፡፡
የአውሮፓውያን ስልጣኔ ባሰባሰቡት ቅርስ ላይ የተመስረተ ነው ለቅርሶች ልዩ ከበሬታ መስጠትም የአንድ ሃገር ስልጣኔያዊ
ብስለት መለኪያ ነው፡
“ሶራ ስለ! ሌላውን ለማወቅ ከሌላው ለመማር ራስሀን
ለማነፃዐር ያጣኸውን ለመፈለግ… ጉብኝት አስፈላጊ ነው" አለችው፡፡
ልክ ነሽ ኮንችት ለምን ለጊዜው ፖርቹጋልን አብረን
አናይም?” አላት፡
“በደስታ! ሶራ" ብላ ሳቋን ለቀቀችው: ኪሊሊ... የሚለውን ሳቋን ሰማው: ናፍቆት ነበር ሣቋ::
“ሳቅሽ ደስ ይለኛል አላት ፈገግ ብሎ፡፡
“አመለግናለሁ” አለችው። ኪሊሊ ብላ እየሳቀች:: እያያት አሰበ: ሌላውን ማወቅ ነው….. የተናገረችውን አስታወሰ፡
አውሮፓውያን ስልጣኔ ባሰባሰቡት ቅርስ ላይ የተመሰተ ነው ገረመው: በልተህ በልተህ ወደ አገርህ አንጋጥ ተሪቱማ እሱም
አገር አለ፡፡ ተግባሩ ግን ጠፋ፡፡ ሌላው እስኪጀምረው መጠበቅ አንዱ የአፍሪካውያን ችግር ነው። እና የሚጠቅመውን ሁሉ ለአገሩ ጆሮ
ለማድረስ ለአገሩ ሕዝብ ለማሳየት የተማረውን ዜጋ ህሊና ለማንኳኪያ ከእንቅልፍ ለመቀስቀሻ ሊጠቀምበት እንደሚገባ ቃል ገባ: እራሱን ግን ተጠራጠረው “ፍርፋሬ ያዘናጋኝ ይሆን?” አለ።
ኮንችት ያለውን አልሰማችም፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሁለቱ መንገደኞች መርከቡ ጉዞ ከጀመረ በኋላ
ጨዋታቸውን ጀመሩ፡፡
“…ለወላጆቼ የመጀመሪያ ነኝ፡ ከኔ በታች ሁለት ታናናሽ
ወንድሞች አሉኝ፡ በተለይ ከኔ ተከታይ ጋር በሰፊ አልጋ አብረን ነበር የምንተኛው።
አባቴ ፍራንሲስኮ ፔሶ ቤኒ ለወደፊቱ መፃኢ እድላችን
ስለሚያስብ ገንዘብ ለማስቀመጥ ቢጥርም ግማሽ ኢትዮጵያዊቷ እናቱ
ካሪና ግን ለግል ውበቷ ብቻ የምትጪነቅ አባካኝ በመሆኗ አባቴ
እንዳሰበው ገንዘብ የማስቀመጥ ህልሙ አልሳካ ሲለው በእናቴና
በአባቴ መካከል አለመጣጣሙ እየበዛ በመምጣቱ ተለያዩ በዚህ
ሳቢያ አባቴ ወደ ቤታችን የሚመጣው በጣም እየቆዬ ሆነ፡ እኔ ደግሞ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኔ መጠን የአባቴን ፍቅር በምሻበት
ወቅት ላገኘው ባለመቻሌ ከልቤ ጠላሁት ስለዚህ ከአባቴ ይልቅ ለኢትዮያዊው አያቴ ለሎካዬ ሆነ ፍቅሬ” ብላ ክሊሊ… ብላ ሳቀች
እሱም ፈገግ አለ ጉሮሮዋን ለማራስ የቆርቆሮ ቢራዋን ለመክፈት ዘወር ስትል የቢራው ቆርቆሮ ወደቀባት ለማንሳት ጎንበስ ስትል
አየው ጥቁር ፓንቷን
አፈር አለና ፊቱን ወደ አትላንቲክ ውቂያኖስ አዙሮ
ሲመለከት hርቀት የሆነ ብረት አዬ
ኮንችት ተመልከች ያ ምንድው?” አላት።
መርከብ ነው የመሬት ክብነትን ስትማር ስለዚህ
አልተማርህም..."
አዎ አሁን ትዝ አለኝ: ሳታይ የተማርሽው ቶሎ
ይዘነጋል እሽ ጨዋታሽን ቀጥይ? አላት አንጋጣ አንዴ ጉንጯን ሞልታ ተጎነጨችና
"ኧህ ብላ ጨዋታዋን ያቆመችበትን አሰብ በማድረግ
ቸበርቻቻ ወዳጅዋን እናቴን ግን እወዳት ነበር በፊት
እንነገርሁህ በቁመናዬ ሳቢያ በትርፍ ጊዜዬ የግል ገቢ ማግኘት የጀመርሁት ገና በህፃንነቴ ቢሆንም እናቴ እናደ ሌሉች ልጆች
አስባ ልብስ ስለማትገልኝና ከሷ የምጠብቀውን አንድም ቀን "ቆንጆ ብላኝ ስለማታውቅ ለእሷ የነበረኝ ፍቅር እየሟሽሽ የጥላቻ
ስሜት ህሊናዬን ይተናነቀው ጀመር አንድ ቀን እንዲያውም አባቴ ጠፍቶ ከርሞ በመጣበት አጋጣሚ
እናቴና አባቴ አንድ ላይ በሚገኙበት ወቅት ጠባቂ በነበረኝ ገንዘብ ላይ ስጦታ ገዝቼ አልጋቸው ላይ አስቀመጥኩላቸ
ንግግሯን ሳትጨርስ ሶራ
አቋረጣትና
ይቅታ ስላቋረጥኩሽ የዚያን ጊዜ የስንት ዓመት ልጅ ነበረሽ።
ምናልባት የአስራ አራት ዓመት ከዚያ አይበልጠኝም
አለችው።
እሽ ቀጥይ አላት ሶራ

👍21
#እህቴ_በባትሆኚ_አገባ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ስንት ጊዜ በፍቅር ፍላፃ ይወጋል..?ማወራው በወንድና ሴት መካከል ስላለ ፆታዊ ፍቅር ነው።አንዳንድ ፍቅር አንዴ ብቻ ነው..ሌላው ጊዜያዊ ስሜት ነው ይላል። ብዙሀኑም ያንን ተቀብሎ ያስተጋባል።መሬት ላይ ያለው እውነታስ ምንድነው የሚያሳየው?መልሱ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ እናገኘዎለን ... የእውነት ፍቅር አንዴ ነው ብለን የምናምን ከሆነ ወይ የህይወት ጅማሮ ላይ የምንገኝ ቲኔጀሮች ነን...ወይ ደግሞ ባጋጣሚ በልጅነታችን ከአንድ ሰው ጋር የመሰረትነው ፍቅር እስከእርጅናችን ዘልቆልን ማጣጣም የቻልን እድለኞች እንሆናለን ።
እንጂማ በእውነታው ፍቅር ደጋግሞ ሊጎበኘን ይችላል.. ለአመታት አብሮን ሊዘልቅ አልያም ለአንድ ቀን ብቻ ብልጭ ብሎ ድርግም ሊል ይችላል። አንዳንድ ፍቅር በቃላት ልውውጥ እና በአይን መሠራረቅ ላያልፍ ይችላል።ሌላው እስከስሜት መጋራትና በወሲብ እስከመደራት ድረስ ከዘለቀ በኃላ ሊቆረጥ ይችላል ወይም እስከጋብቻ ዘልቆ ልጅ ከተወለደ በኃላም ሊሰናከል ይችላል።ታዲያ ይሄኛው ፍቅር ነበረ ይሄኛው ደግሞ ዝምብሎ ግንኙነት ነው ብለን ፍርድ "የምንሰጥበት ምን አይነት ተቀባይነት ያለው የህግ አንቀፅ የለንም?።ደግሞ ተፍቅሮ የተጣመረ ሁሉ ሲለያይ የግድ ፍቅሩ አልቆ ብቻ አይደለም...አንዳንዴ በተጣማሪዎች መካከል ፍቅሩ ሞልቶ ተርፎ ግን በሌሎች አብሮ ለመኖር ምቾት በሚነሱ ምክንያቶች የተነሳም ሳይወድ በግዳቸው ፍቅራቸውን በልባቸው ቀብረው ጉዞቸውን በተለያየ ጎዳና ይቀጥላሉ።ምክንያቱም ለሁለት ጥንዶች አብሮ ለመኖር ፍቅር የአንበሳውን ድርሻ ይያዝ እንጂ ግን ደግሞ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም።
እንዲህ ስለፍቅር የምፈላሰፈው ከጄኔራሏ ጋር ወደ ቤቷ እየሄድኩ ባለሁበት ጊዜ ነው፡፡በራሷ መኪና ሰፈር ድረስ መጥታ ነው የወሰደችኝ፡፡ …ከ20 ደቂቃ በኃላ ፍፀም ያልጠበቅኩት ሰፈር ይዛኝ ገባች…፡፡አደነጋገጤን አትጠይቁኝ፡፡ይሄነው ቤቴ ብላ የመኪናውን አፍንጫ ወደአንድ ቢላ ቤት በራፍ አዙራ በማስጠጋት የመኪናዋን ጡሩንባ አስጮኸች፡፡
እኔ በራፉ ከመከፈቱ በፊት የመኪናውን በራፍ ከፍቼ ወረድኩና ፊቴና ወደማዶ አዙሬ ፈዝዤ ቆምኩ፡፡.ይሄ እንዴት አጋጣሚ ሊሆን ይችላል..?ከጄኔራሏ ቤት ፊት ለፊት የሚታየው የድሮ ስሪት ቢላ ቤት እትብቴ የተቀበረበት ቤት ነው.. የወላጆቼ ላብ ጉልበት የፈሰበት ጥሪት ሀብታቸው ነው፡፡እዚህ ቤት ውስጥ ነው ደግሰው የተጋቡት፤እዚህ ቤት ውስጥ ነው ተፋቅረው ኖረው ልጅ የወለዱት፤ ከእዚህ ግቢ ውስጥ ነው እሬሳቸው ወጥቶ የተቀበረው….፡፡የዚህ ቤት ወራሽ አሁን እኔ ነኝ፡፡ግን በሞግዚትነት ስታስተዳድረው የነበረችው እቴቴ ማለት አክስቴ ስለነበረች አሁንም በእሷ እጅ እንዳለ ነው፡፡የእሷን አይን ለማየት ድፍረት በማጣቴ ምክንያት ይሄንን ንብረቴን መረከብ አልቻልኩም፡፡በአሁኑ የአዲስአባ ገበያ ባዶ መሬቱ ብቻ ቢያንስ 10 ሚሊዬን ብር ያወጣል.፤አቤቱ ሲጨመርበት ገምቱት..አዎ አሁን እኔ ባልጠቀምበትም ወደፊት ለልጄ ይሆናል ስል ተፅናናሁ፡፡
‹ኸረ ግባ በራፉ ተከፍቷል…ምንድነው እንዲህ ያፈዘዘህ..?››
‹‹እ እሺ ›ብዬ ከደነዘዝኩበት እንደመባነን አልኩና ወደውስጥ ገባሁ፡፡
እሷም መኪናዋን ወደግቢው ውስጥ አስገብታ አቆመችና ወረደች፡፡ለዘበኛው ሰላምታ ሰጠችውና ወደ ውስጥ ገባን ፡፡ግቢው ማህል ላይ እድሜ ጠገብ ትልቅ ቢላ ቤት ያለ ሲሆን ወደ አንድ ጥግ ደግሞ በግምት ሶስት ወይም አራት ክፍል ያለው አዲስ ህንፃ ይታያል…ወደ አዲሱ ህንፃ በረንዳ ላይ ሁለት ህፃናት ይጫወታሉ…
.‹‹ያንን አከራይቼው ነው››፡፡ብላ ወደ አሮጌው ቤት ይዛኝ ገባች፡፡
የድሮ መኳንንት መኖሪያ የመሰለ ባለብዙ ክፍል ቤት ነው፡፡ሙሉ ቤቱ የባለሞያ ጥበብ ያረፈበት ባለግርማ ሞገስ ሲሆን በጥንታዊና ዘመናዊ እቃዎች ስብጥር ተሞልቷል፡፡ለምሳሌ ከወደቀኝ ኮርነር አካባቢ ዘመናዊ የሆነ ባለነጭ ልባስ ሶፋ ሲታይ፤ ከእሱ ፊት ለፊት ፍፅም ባህላዊና ከጠፍርና ከእንጨት የተሰራ ልዩ መቀመጫዎች ይታያሉ፡፡ብቻ ቤቱ መኖሪያ ቤት ሳይሆን ሙዚዬም ነው የሚመስለው፡፡
‹‹ደህና አደራችሁ?››ብዬ ገባሁ
‹‹ቁልፍ ከፍቼ እየገባሁ እያየህ ደህና አደራችሁ ትላለህ እንዴ?፡፡››
‹‹ምን ላድርግ ይሄንን የሚያህል ግዙፍ ቤት ሰው አልባ አይሆንም ብዬ ነዋ››
‹‹በጊዜውማ ልጇች ትላለህ የልጅ ልጆች ሲተረማመሱበት ነበር.. ቁጭ በል
ቁጭ አልኩ‹አሁንስ?››
‹አሁን ግማሹ የራሱን ቤት እየመሰረተ ወጣ…ሌላው አውሮፓ..የተቀረው አሜሪካ ገብቷል…እኔና ቤቴ ግን ይሄው አለን››
‹‹ወላጆችሽስ?.››
‹›አባቴ ሞቷል ፤ እናቴ ትንሽ የጤና እክል ስላለባት አሜሪካ እህቶቼ ጋር ነው የምትኖረው….መጣሁ ዘና በል…››ብላኝ ወደኪችን መሰለኝ ገባች፡፡
‹‹ለዚህ ቤት አዲስነት አልተሰማኝም..ምንድነው ፊልም ተሰርቶበት እዛ ላይ አይቼው ይሆን እንዴ…?.››ሪሞት አነሳሁና ፊት ለፊት ያለውን ቴሊቭዝን ከፈትኩ..ጄኔራሏ ከነማዕረጎ የተነሳችው ፎቶ በትልቁ ፊተ ለፊት ግድግዳ ላይ ገጭ ብሏል፡፡ በሙሉ አይን ማየት ፈራሁና አንገቴን አቀረቀርኩ…፡፡የሙሉ ቤተሰቡ ፎቶ እዚህና እዛ በተናጠልና በጋራ የተነሱት ቤቱን ሞልቶታል፡፡ሲታዩ የደላቸው ቤተሰብ መሆናቸው ያስታውቃል፡፡ድንገት የተቀመጥኩበት ጠረጴዛ ስር የፎቶ አልበም አየሁ፡፡ መቼስ አልበም ፊት ለፊት እንግዳ ሲመጣ የሚቀመጥበት ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጠው…የመጣው ሁሉ እንዲያየው ነው ብዬ አወጣሁና ማየት ጀመርኩ…፡፡አብዛኛውን ስለማላውቃቸው ብዙም ስሜት አይሰጠኝም፡፡ ቤዛወርቅ ያለችበትን የህፃንነቷን ቲኔጀር ሆና የተነሳችው ….የሚገርመው ከልጅነቷም ስፖርተኛና ተቦቃሽ ነገር ነች..እንዴ ምንድነው..?ይሄ ፎቶ እዚህ ምን ይሰራል…..?ፎቶውን እንደያዝኩ ከመቀመጫዬ ተነሳውና ወደኪችን ተንደረደርኩ፡፡
‹‹…ቤዝ.ቤ..ዝ….››እያለከለኩ ቅድም ስትገባ ወደያኋት ክፍል ገባሁ
‹‹ምነው ምን ተፈጠረ ..?ቢላዋ በእጇ እንደያዘች ጥሪዬን ሰምታ ስትወጣ በራፍ ላይ ተገጣጠምን …..አልበሙን ወደ እሷ ዘርግቼ‹‹ይህቺ ማነች…?ይህቺኛዋስ?›
‹‹ጤና ትባላለች…በሚያሳዝን ሁኔታ አሁን በህይወት የለችም…..?ምነው ከሰው ጋር ተመሳሰለችብህ እንዴ?››
‹ጤናዬ ማለት? ጤናዬ አስረስ…የበሪሶ አያና ሚስት፡፡››
‹‹አዎ ጋሼ በሪሶ..የት ነው የምታውቃቸው….?››በገረሜታ ጠየቀችኝ፡፡
ፊቴን አዞርኩና ወደሳሎን ተመለስኩ…ሶፋው ላይ ዝርፍጥ አልኩና ጭንቅላቴን ያዝኩ፡፡
ቤዛ ሁሉ ነገር ግራ ገባትና ከኃላዬ ተከትላኝ መጣች ‹‹ቆይ ቆይ እነሱ እኮ ከሞቱ ቢያንስ 20 አመታት አልፏቸዋል….ቅድም ስንመጣ ከመኪና ወርደህ እቤታቸው ላይ ስታፈጥ ነገሩ ምድነው ብዬ ግራ ተጋበቼ ነበር››
‹‹ለመሆኑ አንቺ ታስታውሺያቸዋለሽ…?››
‹‹አዎ ሲሞቱ የደረስኩ ወጣትና 12ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ ሁሉን ነገር ነበር የማስታውሰው…ቤተሰብ ነበርን…አንድ ልጅ ነበራቸው..የሚያምር ወንድ ልጅ… ክርስትና ያነሳው አባቴ ነበር.አበልጆች ነበርን..?አይ እዬብ ይሄኔ አድጎ ትልቅ ሰው ሆኗል….ስሙ እዬብ ነበር…፡፡››
‹አዎ ስሜ እዬብ ነው፡፡››
‹‹ምን ?አንተ…!!!እኔ አላምንም..፡፡እዬቤ ነህ…፡፡ቆይ ቆይ…. ››አልበሙን ነጠቀችና ገለጥ ገለጥ አድርጋ እኔ ያለሁበትን ፎቶዎች አወጠች…፡፡ እሷ አቅፋኝ የተነሳሁት..አባቷ ታቅፈውኝ የተነሳሁት..አራት የሚሆኑ ፎቶዎችን አሳየችኝ….ከዛ በኃላ ቁርሱም ተረሳ.፡፡
✨ይቀጥላል ✨

👍70😱9❤7😁5
#ባል_አስይዞ_ቁማር
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
በማግስቱ ከስራ መመለሻ ሰዓቱን ጠብቃ ደወለችለት .ተገናኙ መክሰስ ጋበዘችው.ከዛ ቡዙ ብዙ ነገር አወሩና በድንገት በየራሳቸው ሀሳብ ውስጥ በመግባት በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ..ልዩ እንዲህ እርቃና ጠልቃ የምታስበው ፊት ለፊቷ ሰለተቀመጠው ሰው መሆኑ ደግሞ አስገራሚ ነው‹‹ዛሬም ያለሁት እዛው የተገናኘንበት ቦታ ላይ ነኝ። አንዳንድ አጋጣሚዎች በቅፅበት ቢገባደድም በአዕምሮችን ውስጥ ግን መሽከርከራቸውንና መንቀሳቀሳቸውን ይቀጥላሉ...አዎ ዛሬም እነዛ የተረገሙ ጣቶቼን ኪስህ ውስጥ ከትቼ ሞባይልህን እየመዘዝኩ ነው...አሁን በዚህች ሰአት"ተዋት ልጅቷን ገደላችኋት እያልክ እየጮህክ ነው...አዎ የተረገሙ እጆቼን በቅድስ እጇችህ አጥብቀህ ይዘህ ከረጋሚዎችህና ከደብዳቢዎችህ መካከል ጎትተህ እያወጣኸኝ ነው... ፡፡
እንዴት ከዚህ ቦታ ተንቀሳቅሼ ወደፊት መጓዝ እንደምችል አላውቅም...በምን አይነት ተአምር እየሠማዎቸው ያለሁትን ልስልስ ድምፅህን ወደ አእምሮዬ ውስጠኛ ማከማቻ ገፍቼ ጨምሬ ፊት ፊቱን ባዶና ንፁህ እንደማደርገው አምላክ ነው የሚያውቀው...ምን አልባት ከተጣበቅኩበት ቅፁበት መላቀቅ አልችል ይሆናል።አዎ ይሄም ሌላው ተጨማሪው በሽታ ሆኖ ተጣብቶኝ ሊሆን ይችላል...እንግዲህ መድሀኒት የማይቀበለው ሰውነት እንዴት አድርጎ በምንስ ተአምር ይፈወስ ይሆን? የምረግጠው ቦታ ሁሉ እየከዳኝ ነው...ደረቅ መሬት መስሎኝ በሙሉ ክብደቴ ስጫነው ያዳልጠኝና ሰማይ ደርሼ መሬት እፈርጣለሁ።መሬት ሳርፍ የእጆቼን ቆዳ ጠጠርና አሸዋው ገሽልጦ ያቆሳስላቸዋል።ወገቤ ለሁለት ይከፈላል።ቢሆንም በወደቅኩበት እየተንከባለልኩ ማላዘን አይሆንልኝም። እንደምንም እራሴን አበርትቼ እነሳለሁ ።የጀርባዬ ህመም ጥዝጣዜው እስኪያቅለሸልሸኝ ድረስ ቢያመኝም ከአቋቋሜ ሽብርክ አልልም ..ፊቴንም አልቋጥርም.... ወደፊትም ከመራመድ አልሰንፍም። የራሴን ህመም ለራሴው በሚስጥር ይዘዋለሁ።እኔ እንዲህ ነኝ።››
ከረጅም ዝምታና ማሰላሰል በኃላ እሱ ቀድሞ ዝምታውን ሰበረና መናገር ጀመረ
‹‹እስኪ ይጠቅምሽ ከሆነ አንድ ታሪክ ልንገርሽ››አላትና እሷን ከሀሳብ ባህር ውስጥ መዞ አወጣት፡፡
እሷም በፍጥነት ከገባችበት መደበት በመውጣት እራሷን አንቅታ‹‹በናትህ ንገረኝ››ስትል ልክ እድሜዋን እንደጨረሰች ወሬ አሳዳጅ አሮጊት የሚነግራትን ለመስማት ተስገበገበች…ስለሆነ ነገር እንዲነግራት ፈልጋ አይደለም..በቃ ስለምንም ይሁን ስለምንም ዘለግ ያለ ወሬ እንዲያወራትና ምስጥ ብላ ከአንደበቱ የሚወጡትን ቃላቶች ለማድመጥ አይኖቹን ሲያንከባልላቸውና ፊቱ ቆጠረ ፈታ ሲያደርግ ለማየት ነው፡፡
ሊነግራት የፈለገውን ታሪክ መተረክ ጀመረ
‹‹አንድ ወቅት ነው ሀዋሳ ነበርኩ፡፡እና በእለቱ ጭፍግግ ብሎኛል... እራሴን ዘና ለማድረግ ወደባህር ዳርቻ ሄድኩ...ጠፍጣፋ እና ምቹ ድንጋይ ላይ ተቀምጬ የሀይቁን ዳር አርቄ በማየት እየተደመምኩ ሳለ አንድ ያጎበደድና ዕድሜ የተጫናቸው አዛውንት ከዘራቸውን እያንቋቁ መጥተው በግማሽ ሜትር ርቀው ከጎኔ ተቀመጡና "ልጄ ምነዋ ተክዘሀልሳ?"ሲሉ ጠየቁኝ…እኔም ቀና በማለት በትኩረት ካየኋቸው በኃላ ለጥያቄያቸው መልስ በመመለስ ፋንታ ሌላ ጥያቄ ጠየቅኳቸው?
‹‹እኔ በ35 ዓመቴ መኖር እንዲህ የከበደኝ እርሷ ይሄን ሁሉ ጊዜ እንዴት ቻሉት?"
"በእኔ የደረሰ አይድረስብህ?"አሉኝ፡፡
"እንዴት አባቴ"
"አንድ ህይወት መኖር ፋፅሞ ሊከብድህ አይገባም.....ተወልደህ ፤አድገህ፤ ተምረህ፤ ስራ ይዘህ፤አግብተህ ወልደህ ፤የልጅ ልጅ ስትል የተሰጠህ ህይወት እልቅ ትልና ሾልከህ እንደመጣህ ሾልከህ በመሄድ ትገላገላለህ፡፡"
"እና እርሶ በእኔ የደረሰ አይድረስብህ ያሉኝ ለምንድነው? አልገባኝም እርሷም እኮ በአንድ ህይወት እንደተንገሸገሹ ያስታወቅቦታል።››
‹‹ልጄ የእኔ ነገርስ ግራ ነው።››
‹‹እስኪ ልስማዋ።››
‹‹ድሮ ነው በጣም ድሮ…ጌታ ሆይ አንድ ነገር እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ "ስል ለአመታት ፀለይኩ።..እግዚያብሄርም ...የፀሎትህ ድምፅ በጆሮዬ አንቃጭሏል:: አሁን አንድ ነገር ያልከኸውን ጠይቀኝ...ወዲያው ሰጥሀለሁ..አንድ ማስጠንቀቂያ ግን አለኝ.."አለኝ አለ
።"አምላኬ ምንድነው?"ስል በከባድ ትህትና ጠየቅኩት።
"የጠየከኝን አንዴ ከሰጠውህ በኃላ መልሰህ ውሰደልኝ ብትል የሚሆን ጉዳይ አይደለም፤ስለዚህ የምትጠይቀውን ደግመህ አስብበት።" ብሎ አስጠነቀቀኝ፡፡
"ግድየለም ለአመታት ያሰብኩበት ጉዳይ ነውና ምንም የሚያፀፅት ነገር አይኖርም"አልኩት
"እንግዲያው ጠይቅ"ሲል ፈቀደልኝ።
"አንድ ነፍስ ብቻ አይበቃኝም...ስድስት ነፍስ አድርግልኝ...ይሄ ነው ልመናዬ ።"አልኩት
"ጥያቄህ ቀላል ነው… .ግን ስድስት ይበቃሀል?"አለኝ።
"ካላስቸገርኩህማ ዘጠኝ ብታደርግልኝ ምስጋናዬ የዘላለም ነው።"አልኩት"
ያው እንግዲያው ከዚህች ደቂቃ በኃላ ባለዘጠኝ ነፍስ ነህ"አለኝና ተሠወረ...የሆነ ኃይል በሰውነቴ ሞገድን ሲረጭና ሲያንዘረዝረኝ ተሰማኝ። ወዲያው ነበር የፀፀተኝ"እንዲህ ቀላል ከሆነ ምነው አስራስምንት ነፍስ ጠይቄው በሆነ"የሚል የስስት መንፈስ እንደቅንቅን መላ ሰውነቴን በላኝ።
" ውለው ሲያድርስ ?እንዳልተፀፀቱ ተስፋ አደርጋለሁ"አልኳቸው
"ፀፀት ብቻ አይገልፀውም።"
‹‹አልገባኝም… ዘጠኝ ነፍስ ማለት እኮ ዘጠኝ ተከታታይነት ያለው የተለያየ ህይወት የመኖር እድል ማለት ነው።››
"አዎ ትክክል ነህ...ዘጠኝ የመሞት እድልም አብሮት እንዳለ አትዘንጋ...በራስህ እየው በአንድ ህይወት ውስጥ ያለው ስቃይ፤ ህመም ፤ስጋትና መረበሽ፤ተስፋ መቁረጥና ቁዘማ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እየው...እና ይሄንን በተለያየ ዘመን ውስጥ ዘጠኜ ለዛውም ያለማቋረጥ ስትደጋግመው ምን ያህል እንደሚከብድ?
"እና ዘጠኝ ነፍስ ነበረኝ እያሉ ነው?››ስል ጠየቅኳቸው፡፡
አይ አሁን እንኳን የቀረኝ ሶስት ነፍስ ነው...ስድስቱን ኖሬ አልፌዋለሁ፤የስድስት ህይወት ደስታ ተደስቼ የስድስት ህይወት መከራ አሳልፌያለሁ፤መኖር ብቻ ሳይሆን ስድስቴ ሞቼያለሁ ማለት ነው..እና አሁን ምንም ነገር ትርጉም አልባ ሆኖብኛል፤መጠጣት መዳራት፤ቤት መስራት ፤ሀብታም መሆን፤ዝነኛ መሆን..ሁሉንም በየተራ አይቻቸዋለው..አሁን አየር ስተነፍስ እንኳን ከመሰላቸቴ የተነሳ እየደከመኝ ነው፡፡ "አሉኝ
‹‹እና እውነታቸውን ዘጠኝ ነፍስ ኖሮቸው ስድስቱን የኖሩ ይመስልሀል? አምነሀቸዋል…?››ስትል በነገራት ግራ አጋቢ ታሪክ ገራ ተጋብታ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ማመን አለማመኑ አይደለም ዋናው ጉዳይ… ሰውዬው በታሪኩ ውስጥ ሊያስተላልፉልኝ የፈለጉትን ነገር ነው ላካፍልሽ የፈለኩት››አላት
‹‹ማለት?››
‹‹ማለትማ..ህይወት ልሙጥ ሆና አትከሰትም፤ደስታውም ሀዘኑም የእኛው ነው፤በሽታውም ጤንነቱም እንደዛው……መኖር እንደተሰጠንም ሁሉ ሞትም ስጦታችን ነው፡፡እና ህይወትን ሙሉ ፓኬጆን ነው መቀበል ያለብን፡የዛን ጊዜ በህይወት የሚለገሰን ደስታው ፈንጠዝያ፤በኑሮ የሚያጋጥመንም መከራ ደግሞ ችግርና ስቃይ ብቻ አይደለም ፤ይልቅስ በንቃት ተቀብለን የሁለቱንም ባላንስ በመጠበቅ ከተጠቀምንባቸው ባላሰብነው መንገድ ስብዕናችንን ይሞርድልናል፤ የአእምሮችን የተለያዩ የማሰላሰያና የሀሳብ ማብላያ ሞተሮችን በተገቢው መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ልክ እንደዘይት ሆኖ ያለሰልሱልናል።››
‹‹እና ምን እያልከኝ ነው?››

👍121❤8🥰4🤔3👏2🔥1😁1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
..ሁለቱም የሚያጠግባቸውን እህልም በልተው ካጠናቃቁ በኃላ እሷ የተረፋትን ከድና ለነገዋ ስታስቀምጥ አሱ ደግሞ በመንቁሩ ነከሰና አሽቀንጥሮ ወደጫካው ወረወረው…በአካባቢው የነበሩ ሌሎች አውሬዎች ሲሻሙበት ተመለከተች፡፡
‹‹እንግዲህ እንደዛ አትየኝ እኔ ብወረውርላቸውም ጩኮ የሚበላ አውሬ የለም››
‹‹እውነቴን ነው ደግሞ ቢኖርስ እናቴ ወዟን ጠብ ያደረገችበትን ጣፋጭ ምግብ ለሌላ በሊታ የምሰጥ ይመስልሀል…?አሁን በል እዚህ ዛፍ ላይ ልውጣ ወይስ አንተ ታወጠኛለህ፡፡?››
ከተቀመጠበት አለት ድንጋይ ተነሳና በአየር ላይ ሆኖ ክንፉን በማርገፍገፍ የሻንጣዋን ማንጠልጠያ በመንቁሩ ይዞ በአየር ላይ ተንሳፈፈና ወደላይ ወደዛፉ ጫፍ በመሄድ ተደላድሎ ተቀመጠ፡፡
ሳትወድ በግዷ አሳቃት‹በቃ እንዲህ ተንኮለኛ ሆነህ ቀረህ…ይብላኝ ላንተ እኔስ ይህቺን መውጣት አያቅተኝም›› አለችውና አገልግሉን በአንገቷ አጥልቃ የጫማዋን የተፈታ ማሰሪያ በማጠባበቅ እንደለመደችው እየቧጠጠች ዛፍን መውጣት ጀመረች.. እሱ ያለበት ለመድረስ 5 ደቂቃ ፈጀባት..፡፡
‹‹ይሄው በጣም ደክሞኛል ደስ አለህ?›አለችውና ከጎኑ ተመቻችታ ተቀመጠች፡፡ ካለበት ተነስቶ ተፋዋ ላይ ዘፍ ብሎ ተደላድሎ ተቀመጠ፡፡ ሻንጣውን ተንጠራርታ ወደራሷ ሳበችና ውስጡ ያለውን አልጋ ልብስ አውጥታ እራሷንም እሱንም አለበሰችና ጋደም አለች፡፡
ለሊት 11 ሰዓት ነው ከእንቅልፍ የነቃችው፡፡.ያው ንስሯ እሷ በምትነቃበት በማንኛዋም ሰዓት እሱም ይነቃል..እና ጊዜ ሳያባክኑ ነበር ጉዞ የጀመሩት… 5 ሰአት ሲሆን የአፍሪካ ጣሪያ ላይ ተፈናጣ በሁለት እግሮቾ መቆም ቻለች፡፡ኪሊማጀሮን ለመጎብኘት ያደረገችው አስደማሚ ጉዞ በውስጧ ኩራት ፈጠረባት፡ አካባቢውን ስትቃኘው እጅግ ግራ ሚያጋባና አስደማሚ ነው፡፡
፡፡ኪሊማንጀሮ ተራራ በአመት ከግማሽ ሚሊዬን በላይ ቱሪስቶች የሚጎበኙት ተአምራዊ ቦታ ነው።በአለም ላይ ተጠቃሽ ከሆኑት 5 ተራሮች መካከል አንዱ ሲሆን ለተራራ መውጣት እስፓርት ከሁሉም የተሻለ ተመራጩና ምቹ ነው።
በግራ በኩል ለብቻው እንደግድግዳ የተዛረጋ ውበቱ ልብን የሚያርድ ግግር በረዶ ይታያል። ከፊት ለፊቷ እንድ አነስተኛ የእግር ኳስ ሜዳ በሚመስል ስፍራ አመድና አፈር የሞላበት እንቅስቃሴው የተገታ እሳተጎመራ ይታያል፡፡፡ ይሄንን አይነት መልካ ምድርን ስትመለከት ሀገሯ ምድር ላይ የሚገኘውን ኤርታሌ ዘወትር የሚንቀለቀል እና ሲፍለቀለቅ የሚውል ከዚህኛው በጣም በተለየ ሚደንቅና ውበት ብቻ ሳይሆን አስፈሪነት የተጎናፀፈ ልዩ ነው. አሁን ከፊቷ ያለው በዛ ልክ ባይሆንም ግን የራሱ የሆነ ውበት አለው፡፡ ወደሌላ አለም መሽሎኪያ ሚስጥራዊ በር ነው የሚመስለው ..
ወደፊቷ የተወሰነ ተራመደችና ቁልቁል ጭው ወደለው የተራራው መነሻ መስረት ለማየት ሞከረች ፤ ከእይታዋ አቅም በላይ ሆነባት፡፡ ከእሷ 5 ሜትር ያህል ራቅ ብሎ የሾለ ድንጋይ ላይ ጉብ ብሎ የተቀመጠውን ንስሯን ተመለከተች ።
‹‹እባክህ እርዳኝ›› ስትል ጠየቀችው ።ፍቃደኛ ሆኖ አዕምሮውን ከፈተላት… የንስሯ እይታ ያው እንደሚታወቀው 5 ኪ.ሜትርም የራቀ ስለሆነ ሰፊ ስፍራን ያካለለ እይታ አገኘች ..ድንገት የሰው ድምፅ ሰማች..ትኩረቷን ሰበሰበችና ለማዳመጥ ሞከረች … እንደውም ባህላዊ የጋራ ዘፈን ነው እየስማች ያለችው… በርከት ያሉ ስዎች በህብረት የሚዘምሩት ዝማሬ ድምፅ
… ወደእሷ እየቀረበ እንደሆነ አውቃለች ..እንደውም ሰው አየች …ከሆነ ሽለቆ ከመሰለ ከለላ ውስጥ ቀስ በቀስ በየተራ እየወጡ በቀጭኑ ጠመዝማዛ መንገድ እሷ ወዳለችበት እየመጡ እንደሆነ ገባት ለመቀመጫ የሚሆን ጠፍጣፋ ድንጋይ ፈለገችና ተቀምጣ ትጠብቃቸው ጀመር ፡፡በአስር ደቂቃ ውስጥ ስሯ ደረሱ.. ስምንት የሚሆኑ የጓዝ ሻንጣና ሌሎች እቃዎችን የተሽከሙ የሀገሬው ስዎችና 5 የሚሆኑ ፈረንጆች ናቸው። የሀገሬው ስዎች ወገብ የሚያጎብጥ ሽክም የተሽከሙ ቢሆንም አሁንም ተጨማሪ መንገድ የመጓዝ አቅሙ እንዳላቸው በሁኔታቸው መገንዘብ ይቻላል።ፈረንጆቹ ግን ያንጠለጠሏቸው እቃዎች አነስተኛና ቀላሎች አንዳንዶችም ባዶቸውን ቢሆንም ስሯ ሲደርሱ ትንፍሽ እጥሯቸውና ድካም አዝሎቸው በየቦታው ተዘረሩ...የሀገሬውን ስዎች ጨምሮ ፈረንጆቹም በዛ የኪሊማንጀሮ ከፍታ ላይ አንድ ሴት ከአንድ ንስር አጠገብ ያለፍርሀት እና ድካም ቁጭ ብላ ሲያዮት መገረም ውስጥ ገብ….አብዛኞቹ በአካባቢው ሌላ ሰው ካለ በማለት ለማየት ዙሪያ ገባውን ቢያማትሩም ምንም የስው ዘር ማየት አልቻሉም፡፡ ከፈረንጆቹ መካከል አንድ በግምት 35..40 የሚሆነው መልከ-መልካምና ፈርጣማ ሰው ትንፋሽ ለመሰብሰብ እየጣረ … ከተዘረረበት እንደምንም ተነስቶ ወደእሷ ቀረበና… የአሜሪካ አክስንት በተጫነው እንግሊዘኛ ‹‹አንድሪው እባላለሁ"አላት፡፡
"ኬድሮም እባላለሁ..."በአጭሩ መለሰችለት...ሲጠጋት የሆነ ነገር እየተሰማት ነው ፡፡ልትገልፀው የማትችል ከዚህ ቀደም ተሳምቷት የማያውቅ አይነት ስሜት …ምክንያቱንም ማወቅ አልቻለችም፡፡
"ጓደኞችሽ...የት ሄድ?"
"ያው ጓደኛዬ"መለሰችለት ...እራቅ ብሎ ወደሚታየው ንስሯ በእጇም በአይኗም እየጠቆመችው
"ሌሎች ከእሱ ጋር የመጡ መንገደኞች ፈንጠር ፈንጠር ብለው እረፍት ለመውስድ ከተቀምጡበት ሳይንቀሳቀሱ በከፊል እየተከታተሏቸው ነው፡፡
..በምንም አይነት ሁኔታ ብቻዋን ሆና እዚህ ቦታ ድረስ ይሄን ሁሉ እጅግ ፈታኝና ተአምረኛ የሆነ ተራራ መውጣት እንደማትችል እርግጠኛ ሆኖ"እየቀለድሽ ነው አይደል?"አላት
‹‹በፍፅም እውነቴን ነው"አለችው ፍርጥም ብላ፡፡
‹‹መች ነው እዚህ የደረሺው?"
"ከ20 ደቂቃ በፊት"
እንደ አዲስ ከስር እስከላይ አያት ... እይታው ውስጧን እረበሻት
"ምነው ችግር አለው? "አለችው።
"በዚህ ቅፅበት ከድካምሽ እንዴት አገገምሽ...?እኛ ወንዶቹ እንዴት እንደተዝለፈለፍን አታይም።"
"እሱ ሚስጥር ነው"
በዚህ ቅፅበት መንገድ መሪና ጓዝ ተሸካሚ የሆኑት የሀገሬው ስዎች ጉዞቸውን መቀጠል እንደለባቸው አሳስበው ያሳረፍትን ጓዝ እርስ በርስ አንድ አንድን እያሽከመ ከጨረሱ በኃላ ሽቅብ ወደ መጨረሻው መዳረሻ ጉዞ ጀመሩ …ፈረንጆቹም እነሱን ለመከተል እራሳቸውን አበርታተው ከወዳደቁበት በመነሳት መራመድ ጀመሩ፡፡አንድሪውም ከኬድሮም መነጠል የፋለገ አይመስልም"ታዲያ አሁን ጓደኛ እንሁንና አብረን እንሂዳ"የሚል ግብዣ አቀረበላት…
አልተግደረደረችም...‹‹ ደስ ይለኛል›› ብላ በቅልጥፍና ከተቀመጠችበት ተነሳችና አገልግሉን ከመሬት በማንሳት በትከሻዋ በማንጠልጠል ለመራመድ ፊቷን ስታዞር እሱ ሻንጣዋን ሊይዝላት ከመሬት ለማንሳት ጎንበስ ሲል...‹‹ተወዉ ይቀመጥ››አለችው፡፡
‹‹ለምን ?ያንቺ አይደለም?››
ወደ ንስሩ በማመልከት"የእኔ ብቻ አይደለም የእኔ እና የእሱ ነው፡፡ ስለዚህ እሱ ይዞ ይመጣል።"አለችው፡፡
ፍጥጥ ብሎ አያት...በቋንቋም ያልተግባቡ መሰለው፡፡እጁን ያዘችና የነገረችውን አምኖ እንዲከተላት ጎተተችው፡፡ ወደኃላው በመገላመጥ አንዴ ሻንጣውን አንዴ ከተቀመጠበት ንቅንቅ ያላለውን ንስሯን እየተመለከተ ተከተላት….ጎን ለጎን ሆነው እየተደጋገፉ ጉዞቸውን ቀጠሉ፡የኪሊማንጀሮ የመጨረሻው ጫፍ እንደደረሱ ቀድመዋቸው የደረሱ ከሶስት በላይ የሆኑ ቡድኖች ድንኳናቸውን ተክለው አገኞቸው ፡እሷም ያለችበት ቡድን የተሻለ ክፍተት ያለበት ቦታ ፈለጉና ሸክማቸውን አራግፈው አረፍ አረፍ አሉ፡፡አብረዋቸው

👍100❤5😁1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ዕለተ ቅዳሜ 9፡45 ቢሾፍቱ ድሪምላንድ ሆቴል ሁለተኛ ዕድሉን ለመሞከር ከትንግርት ጋር ጎን ለጎን ተቀምጠዋል፡፡ ዛሬ እንደ ትላንቱ ጉጉት ሳይሆን ፍራቻም ጭምር ስሜቱን ቀፍድዶ ይዞታል፡፡
‹‹ዛሬ የማገኛት ይመስልሻል?›› ትንግርትን ነበር የጭንቀት ጥያቄ የጠየቃት፡፡
‹‹በምን አውቃለሁ ብለህ ነው?››
‹‹እንዴት ምን አውቃለሁ? አማካሪዬ እንድትሆኚ ነው እኮ ይዤሽ የመጣሁት፡፡››
‹‹ትልቁ ስህተትህ እሱ ነው፡፡››
<እንዴት?>>
‹‹እንዴት ልታምነኝ ቻልክ ?>>
‹‹እንዴት አላምንሽም ጓደኛዬ አይደለሽ ...?
‹‹ ምክር ብለግስህ እንኳን ጠቃሚ ምክር ይሆናል ብለህ እንዴት ታስባለህ? እርግጥ ጓደኛህ ነኝ፤በተጨማሪም ፍቅረኛህ፤ይቅርታ ማለቴ የድሮ የወሲብ ደንበኛህ፡፡ ስለዚህ የሆነ የሚሠማኝ ነገር ያለ አይመስልህም?ቅናት
በአግራሞት ‹‹እውነትሽን ነው?››ጠየቃት፡፡
<<አዎ::>>
‹‹እኔ ግን ፍፁም እንደዚህ ይሠማሻል ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡ቅናት የሚባለውን ቃል እራሱ የምታውቂው አይመስለኝም፡፡ እርግጥ ጥሩ የወሲብ ጥምረት እንደነበረን አልክድም ቢሆንም እኔ እንደማፈቅርሽ እንጂ አንቺ ታፈቅሪኛለሽ ብዬ በፍፁም አስቤ አላውቅም ፤ግንኙነታችን ከፍቅረኝነት ይልቅ የጓደኝነት ቃናው እንደሚያይል ነው የምረዳው፡፡››
‹‹እንደዚህ የተሠማህ እያስከፈልኩህ ስለምወጣልህ ይሆን?››
‹‹የክፍያው ጉዳይማ ድራማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ አድርገሽዋል፡፡››
‹‹እንግዲያው ስለሴቶች ገና ብዙ ያልገቡህ ነገሮች አሉ ማለት ነው፡፡ለማንኛውም ይሄ ያከተመለት ጉዳይ ነው ፤ እርሳውና ወደ ስራህ ተመለስ ሠዓቱ ደርሶልሀል፡፡››
የእጁን ሠዓት ተመለከተ፤ እውነትም 11፡05 ሆኗል፤ ዙሪያውን ቃኘ፡፡ ሴት የሚባል አስተናጋጅ የለም፡፡አንድ ሦስት የሚሆኑ ወንዶች ፈንጠርጠር ብለው ይታያሉ፡፡ ዓይኑን ዙሪያውን በተራራዎች ተከቦ ክብ ቅርፅ ኖሮት ገደል ውስጥ የሚገኘውን አስፈሪና አስደማሚ እይታ ያለውን የቢሾፍቱ ሀይቅ ላይ ተክሎ ከትንግርት ጋር ስለተለዋወጡት ቃለ ምልልስ ያሠላስል ጀመር፡፡ ትንግርት ማለት ለእሱ ሊያጣት የማይፈልግት በጣም የቅርብ ሠው ነች፡፡ ሁሉ ነገሯ ይመቸዋል፡፡ በአሁኑ ማንነቷ ውስጥ ሲገመግማት ብቻ ሳይሆን በሽርሙጥና ስራዋ ላይ እያለችም ስለእሷ ለራሱም የሚገርመው አይነት ስሜት ነው የሚሠማው፡፡ ባለፈው አመት አንድ ወርክሾፕ ላይ ለመሳተፍ ጀርመን ለሦስት ወር ሄዶ ነበር፡፡ በወቅቱ ጓደኞቹ... ስራው... ቤቱ ወይንም አገሩ አልነበረም በአይኑ ላይ የሚበሩት ትንግርት እንጂ ...ሀሳቡን ሳይቋጭ ትንግርት ከኋለው ጎንተል አድርጋ አቋረጠችው፤ እንደመባነን ብሎ ‹‹እ .. እ ... ምነው?››
‹‹እይ ከጀርባህ፡፡››
ዛሬም መፅሀፉን ይዛለች፡፡አለባበሷን ግን ከትላንቱ ተቀይሮል፡፡ በቀሚስ ፋንታ ከሠውነቷ ተጣብቆ ቅርፅን አጉልቶ የሚያሳይ ወደ ቡኒ የሚያደላ የጨርቅ ሱሪ ለብሳለች፡፡ ከላይ የለበሠችው እጅጌ ሙሉ ሠማያዊ ቲሸርት ሲሆን ፀጉሯን ትከሻዋ ላይ ለቃዋለች፡፡ ያ ጠይም ፊቷ ከትላንትናው ይበልጥ ወዝቷል፡፡ ግን ዛሬም መፅሀፍ ላይ እንዳቀረቀረች ነው፡፡ ውስጡን ብርድ ብርድ አለው፡፡ ደስታ ይሁን ፍራቻ መለየት አልቻለም፡፡
‹‹ምን ትላለህ?››
‹‹ምን እላለሁ እሷ ትሆን እንዴ?››
‹‹ያንተን አላውቅም እኔ ግን ሳትሆን አትቀርም እላለሁ፡፡››
‹‹ምን አልባት አጋጣሚ ቢሆን ዛሬም እዚህ የተገኘችው፡፡››ጥርጣሬውን ገለፀላት፡፡
‹‹እንዲህ አይነት አጋጣሚ እንዴት ይኖራል? ሳትቀጣጠር በተከታታይ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የተለያየ ቦታ መገናኘት ይቻላል?››
‹‹በደንብ ይቻላል፡፡›› አለ በአግራሞት አይኑን በቀኝ በኩል ካለ መቀመጫ ላይ ተክሎ፡፡
‹‹አልገባኝም›› ትንግርት ነች፡፡
‹‹በደንብ እንዲገባሽ ወደ ጀርባሽ ዙሪ››
ቀስ ብላ ዞረች
አገጯን በአግራሞት ደግፋ‹‹አጃኢቭ ነው›› አለች፡፡
‹‹ምን እየተካሄደ ነው?›› መልሳ ጠየቀችው፡፡
ከትላንትናዎቹ ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለተኛዋን ነበር የተመለከቱት፡፡ ዕድሜ ጠና ያለችውን፡፡ አለባበሷም ሆነ ጠቅላላ ሁኔታዋ ልክ እንደትላንቱ ነው፡፡ ዛሬም አይኖቿን እሱ ላይ ከመትከል አልቦዘነችም፡፡
<<የሆነ ነገር የገባኝ መሠለኝ፡፡››
<<ምን?>>
‹‹ይህቺ እርጉም የዋዛ አይደለችም፡፡ ከሲ.አ.ይ.ኤ ተባራ የመጣች ሳትሆን አትቀርም፡፡እንዲያደናግሩኝ አራትና አምስት ሴት አሠማርታብኛለች፡፡ ከትላንትናዎቹ መካከል የቀሩት አሁን ይመጣሉ፡፡›› ተናግሮ ሳይጨርስ ትናንት ሲጋራ እያጨሠች ስትነፈርቅ የነበረችው ከሲታ ወጣት በተንቀዠቀዠ አረማመድ አልፋቸው ፊት ለፊታቸው ካለ ወንበር ጀርባዋን ሠጥታቸው ፊቷን ወደ ሀይቁ አዙራ ተቀመጠች፡፡አስተናጋጅ ቀረባት፡፡ ጭማቂ አዘዘችው፡፡
ትንግርት ከት ብላ ሳቀች፡፡ ‹‹ኪኪ . ኪ . ኪ››
‹‹ምን ያስቅሻል?››
‹‹እንዴት ምን ያስቅሻል? ከማሳቅም በላይ ነው እንጂ፡፡ ቀድማ ብትነግረን እኮ የፊልም ዳይሬክተርና ካሜራማን አዘጋጅተን እያንዳንዷን ድርጊት እናስቀርፀው ነበር፡፡ህዝብ በወረፋ ለማየት የሚራኮትበት ልብ አንጠልጣይ ድንቅ ፊልም እንደሚወጣው አይታይህም፡፡ ጉድ ሠራችን፡፡ የቢዝነስ ሠው አይደለችም ማለት ነው፡፡ ግን አያት ያሳደጋት ልጅ ሳትሆን አትቀርም፡፡
‹‹አልገባኝም››
‹‹አየህ አያቶች ሲያሳድጉ እንቆቅልሽና ተረት እየጋቱ ነው፡፡ ይህቺም ያንተዋ ሴት እንዲህ ሰራዋ ሁሉ እንቆቅልሽ የሆነው በዛ የተነሳ ይሆናል ብዬ ነዋ፡፡››
‹‹የእኔን ችግር ለመፍታት የሚበጅ መፍትሄ ባይኖረውም፤ጥሩ ግምት ነው፡፡›› አለ ተስፋው በሰለለ ድምፅ ፡፡
ሠዓቱ 11፡ዐዐ ሞልቷዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ተስተናጋጆች ወጣቶች ናቸው፡፡ በመጠኑ ጠና ያሉም ይገኙበታል፡፡ የእሱ ትኩረት ግን ትናንት ያያቸው ሦስት ሴቶች ላይ ብቻ ነው፡፡
‹‹እንግዲህ ከሦስቱ አንዷ ነች ማለት ነው›› ሁሴን ነው፡፡
‹‹ከአራቱ በል እንጂ››
‹‹አራተኛዋ ደግሞ የቷ ነች?›› በብስጭት ጠየቃት፡፡
‹‹እንደውም አምስት ናቸው፡፡››
‹‹አሹፊብኝ ...አንቺ ምን አለብሽ?››
‹‹ምን አሾፍብሀለሁ ... ያቺን ከፈረንጆቹ ቀጥሎ የተቀመጠችውን ልጅ አየኋት?››
ወደ ጠቆመችው አቅጣጫ ፊቱን ላከ፡፡ ፊታቸው የተሸበሸቡ ሁለት ያረጁ ሴት ፈረንጆች ተመለከተ፡፡ በዚህ ዕድሜያቸው ሠው አገር ምን እንደሚያንከራትታቸው አሠብ አደረገና ተወው፡፡ ከነሱ ቀጥሎ አንድ ወጣት ሴት አለች፡፡ ከፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ ፋንታ ከነጠርሙሱ ቁጭ ብሏል፡፡ አሁን በአትኩሮት ሲቃኛት አበሻ መሆኗን ለየ፡፡ ወደ ነጭነት ያደላ ቅላት አላት፡፡ ድቅልም መሠለችው፡፡ ታምራለች ፀጉሯ በአገራችን ያልተለመደ አይነት ነው፡፡ ቡኒ ቀለም አለው፡፡ ያብረቀርቃል፡፡
‹‹እንዴት እሷ ትሆናለች ብለሽ ገመትሽ?››
‹‹እሷም ትናንት እዛ ስለነበረች ነዋ፡፡››
‹‹በፍፁም አልነበረችም›› የድምፁ መጠን ለእሷ ሳይሆን ለተስተናጋጆች ሁሉ እንዲሠማ ያሠበ ይመስላል፡፡
ትንግርት ግራና ቀኟን እያየች፡፡‹‹ቀስ ብለህ አውራ፡፡›› አለችው፡፡
‹‹ይሄውልህ ትያት አትያት አላውቅም እንጂ ይህቺ ልጅ ትናንትና እዛ ነበረች፡፡ ሌላው ቢቀር ያንን ፀጉሯን እንዴት እረሳዋለሁ?››
‹‹የት ጋር ነበር የተቀመጠችው››
‹‹ዋናው ቡና ቤት በረንዳ ላይ››
‹‹ለዛ ነዋ ያላየኋት፡፡ ለምን ታዲያ አላሳየሽኝም?››
‹‹በወቅቱ ትያት አትያት እርግጠኛ አልነበርኩም፤ ደግሞም ምርጫዎችህ በዝተው እንድትደናገር አልፈለኩም ነበር፡፡››
‹‹እሺ አምስተኛዋስ የትኛዋ ነች››

👍84❤11👏1