አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የመልስ_ጉዞ_ወደ_መነሻ
:
#ክፍል_ስድስት
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
..… እንደነርኮችሁ የመራመዴ ጉዳይ ተአምራዊ በሆነ መንገድ እልባት ካገኘ ቡኃላ እናቴ ለአንደበቴ መከፈት መጓጓት ጀመረች፡፡ያው እናት አይደለች ፡፡በተለይ ስድስት አመት ከሞላኝ ቡኃላ እኩዬቼ ሁሉ ወደትምህርት ቤት ሲጓዙ እኔ አንደበቴ መላቀቅ ባለመቻሉ ምክንያት እቤት በመቅረቴ ውስጧ ተጎዳና እንደአዲስ እኔን ለማዳን የምታደርገውን እንቅስቃሴ ጀመረች ፡፡በዚህ እንቅስቃሴዎ ወቅት ስታልፍም ሆነ ስታገድም የሚያገኞት ሰዎች ሁሉ የሆነ ነገር ሳይሏት ዝም ብለው አያልፎትም፡፡
መቼስ ሀበሻ ባህል ውስጥ አንዱ አስቸጋሪው ነገር የሆነ ሰው ችግር ላይ በወደቀ ቁጥር ምክር ሰጪ ሰው መብዛቱ የታወቀ ነው፡፡ለምን ጠበል አትወስጂውም……?አዋቂ ቤት ይሻልሻል……?እዚህ ከተማ ላይ አዲስ ሀኪም መጥቷል አሉ….…? ውጌሻ ጋር አይሻልሽም….የማይባል ነገር የለም፡፡ታዲያ ይሄ ችግር ውስጥ ላለችና ግራ ለገባት እናቴ በወቅቱ ምን ያህል ግራ አጋቢና አስጨናቂ እንደሚሆንባት መገመት አይከብድም፡፡
እናቴ አንደወትሮዋ እኔን ለማዳን ስትንከራተት ውላ ስትመለስ አባቷ ይናገራታል፡፡
-ልጄ በቃ ለአምላክ ተይው…እሱ እንዳደረገ ያድርገው
-እንዴት እንዳደረገ ያድርገው ስትል…?...ትጠይቃለች
-በቃ አንዳንዴ ከአምላክ ጋር እልክ መጋባት አያስፈልግም…አሱን አድናለው ብለሽ ከእዚህ እዛ ስትካለቢ አንቺም ከሰውነት ጓዳና ወጣሽ…እራስሺን እስኪ እይ… የአርባ አመት አሮጊት መስለሻል እኮ…ገና በሀያ ሶስት አመትሽ ፊትሽን ማድያት እየበላው ነው፡፡በዚህ ከቀጠልሽ የከፋ በሽታ ላይ መውደቅሽ አይቀርም፡፡
-እና ምን አድርጊ ነው የምትለኝ፡፡…?
በቃ እሱን አድናለው ብለሽ ከወዲህ ወዲያ መንከራተቱን አቁሚ.. እግዜያብሄር እግሩን ተርትሮልሻል …በቃ በዛ ተመስገን ብለሽ ሌላውን ተይው…ይሄው ለዓመታት ተንከረተሽ፡፡ ..ህክምናውንም ጠበሉንም ሞክረሻል፡፡ይሄ ነው ችግሩ ብሎ ሊነግርሽ የቻለ የህክምና ጠቢብ የለም፡፡ይሄ ማለት ደግሞ የልጅሽ ችግር ሚስጥር በአምላክ እጅ ብቻ እንደሆነ ነው የሚገባኝ፡፡ በእሱ እጅ ከሆነ ደግሞ ታአምሩን የሚያደርግበት የራሱ ቀንና ጊዜ አለው፡፡እሱን በትዕግስት መጠበቅ ነው፡፡ስለሆነም መንከራተቱን አቁሚ፡፡እዚሁ እንከባከበዋለን፡፡ምንም ነገር እንዳይጎልበት ማድረግ እንችላለን፡፡የሚጠብቁት ተጨማሪ ሰራተኞችም ልንቀጥርለት እንችላለን፡፡አንቺ ግን ከዚህ በላይ እራስሽን አትጣይ፡፡ ……
-አባዬ እናቱ እኮ ነኝ፡፡እንዴት ይሄ የእግዜር ስራና ፍቃድ ነው ብዬ እጆቼን አጣጥፌ ተስፋ ቆርጬ ልቀመጥ እችላለው…?፡፡አንተ እኔ እንደዛ ብሆንብህ የሆነችውን ትሁን ብለህ ተስፋ ቆርጠህብኝ ትተወኝ ነበር…?፡፡…….የትዝብት ጥያቄ ጠየቀቺው፡፡
-አይ…ስለልጅ ልጄ እኮ ነው እያወራን ያለነው… ለአንቺ ብቻ ሳይሆን ለእኔም ልጄ ነው፡፡ጨካኘ ሆኜ አይደለም፡፡ግን እሱን ለማደን በሚል ያልተረጋገጠ ተስፋ አንቺን እንዳላጣ ስለፈራው ነው፡፡ሰለጨነቀኝ ነው፡፡
-በቃ አባዬ በቃ …. መቼም በልጄ ተስፋ አልቆርጥም፡፡መቼም እግዜር እንዳደረገ ያድርገው ብዬ ልቤን አረጋግቼ እድሜ ልኩን ከሰው ተገልሎ በተዘጋ ቤት ውስጥ እንዲኖር በመፍረድ እኔ ለመሽቀርቀርና እራሴን ለማሽሞንሞን አልሞክርም…..መቼም፡፡……ብላ ከአባቷ በንዴት እና በለቅሶ ተለይታ እኔን ወደመኝታ ቤት ይዛ ገብታ ግንባሬ ላይ ተደፍታ በእንባ እየታጠበች ከፈጣሪዋ ጋር ለሳዕታት በምሬት ካወራች..(እናንተ ከፀለየች )ብላችሁ ማንበብ ትችላላችሁ አቅፋኝ ትተኛለች፡፡
ማለዳ ሊነጋጋ ሲል ጥርት ያለ ህልም ታያለች፡፡ተመሳሳይ አይነት ህልም እኔም አይቻለው፡፡ልዩነቱ እሷ ያየችውን ህልም ለአባቷ መናገር ስትችል..እኔ ደግሞ ምናገርበት አንደበት ስላልነበረኝ ለእሷ እንኳን መናገር አልቻኩም፡፡
-ህልሙ እንዲህ ነው
ጠይም የተለጠለጠ ኑግ የሚመስል የሰውነት ቀለም ያላቸወ ፊታቸው በአደገ እና በተንዠረገገ ነጭ ፀጉር የተሸፈነ ሽማግሌ መኝታ ክፍላችን ሰተት ብለው ይገባሉ፡፡እናቴ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣ እኔን ጉልበቷ ላይ ታቅፋ በተመስጦ ላይ ሳለች ሰውዬው ወደእኛ ቀርበው ወለሉ ላይ በርከክ ይሉና ጭንቅላቴን እየዳበሱ
‹‹ ..ልጅሽ ታላቅ ሰው ይሆናል፡፡አንድ ቀን ዓለም ስለእሱ በመደመም ያወራል፡፡ምድራዊውን አለም ከመንፈሳዊው አለም ጋር ድልድይ ሆኖ ያስተሳስራል…ስለዚህ አንቺ መጨነቅሽን አቁሚ .. እሱ በፈለገ ቀን እራሱን ማዳን ይችላል፡፡ ከራሱም ተርፎ ሌላውን ያድናል፡፡ግን ሲፈልግ…ቀኑ ሲደርስ ብቻ ነው እንደዛ የሚያደርገው፡፡
-አባት ስለእኔ ልጅ ነው የሚያወሩት..?በጥርጣሬ እና ያሉትን ባለማመን ትጠይቃለች፡፡
-አዎ ልጄ ..እኔ የአማላክ መልዕክተኛ ነኝ፡፡ አምላክ እንደገለፀልኝ ከሆነ የልጅሽ እውቀት ጥልቅና ከዛኛው አለም ይዞት የመጣው ነው፡፡
-ከዛኛው አለም ሲሉ…?፡፡
ዳግመኛ ስለመወለድ የምታውቂው ነገር አለ ልጄ.?.
-እኔ እንጃ ብቻ ከዚህ በፊት የሰማው መሰለኝ፡፡አዎ ክርስቲያን አይደለው..ሰው ከውሀና ከመንፈስ ዳግመኘ ካልተወለደ በስተቀር ወደመንግስቱ መግባት እንደማይችል አምላክ ተናግሯል፡፡
-ትክክል እኔ ግን እያልኩ ያለውት ልጅሽች ወደ እዚህች ምድር ሲመጣ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ከሁለት ሺ አመታት በፊት ነፍሱ እዚህች ምድር ላይ ነበረች…የበለፀገ ህይወት እና በእውቀት የተሞላ ስብዕና ነበረው..እና ያንን እውቀት ነፍሱ ይዛው የመጣች ይመስለኛል፡፡
-እና እኔ ምን ላድርግ …?
-ምንም ፤እራሱ ፈልጎ የሆነ ነገር ማድረግ እስኪችል ድረስ አትጫኚው..አንቺም አትባክኚ፡፡ ብቻ በእሱ ላይ ሁሌም እምነት ይኑርሽ..ወስጡ የተቀበረውን እውነትና እውቀት ብቻ እንዲገለፅለት ሁሌ ከጎኑ ሁኚ…ከጎኑ መሆንሽ ብቻ ለእሱ በቂው ነው..ሌላውን በጊዜው እራሱ ያደርገዋል፡፡
-ሽበታሙ መልዕክት አድራሽ ሽማግሊ ከክፍላችን ሳይወጣ ነበር የሰራተኛችን የመኝታ ቤታችንን በራፍ መቆርቆር ሁለታችንንም ከእንቅልፋችን የቀሰቀሰን
-እናቴ ህልሙን ልትረሳ ሰውዬውንም ልትዘነጋ አልቻለችም፡፡ሰራ አልቻለችም..ሰውዬውን ልትዘናጋ.
ዘወትር እንደምታደርገው ማታ አካባቢ ቤተክርስቲያን ሄድን፡፡የተለመደውን የማታ ትምህርት ተከታትላ..ያው እንደወትሮዋ ከአምላኮ ጋር አንሾካሽካ ፤ስትጨርስ ስለህልሞም እያሰበች የመልስ ጉዞ ለማድረግ የቤተክርሲቲያን አጥር ግቢ ወጥተን ብዙም ሳንርቅ እኛ ሁለታችንም በህልማችን ያየናቸው ሽማጊሌ በትክክል እሳቸው ድንገት ከፊታችን ተደንቅረው መንገዳችንን ገቱት.እኔ ብዙም ባይደንቀኝም እናቴ ግን በድንዛዜ ሀውልት መስላ ነበር ባለችበት የቆመችው
-ሰውዬው ለእናቴ ድንጋጤ ብዙም ትኩረት ሳይሰጡ ጎንበስ ብለው እጃቸውን ጭንቅላቴ ላይ አሳርፈው በመዳበስ እይታቸውን ወደእናቴ አድርገው ‹‹ጌታ ችግርሽን ይፍታልሽ…እግዜያብሄር ለቅሶሽን ሰምቶል ››በማለት የብስራት ቃላቸውን አሰሟት
-ተአምር ነው፡፡እርሷ መላአክ ኖት…?
-አይ አይደለውም ሰው ነኝ፡፡ተራ ሰው ለሶስት ቀን በተከታታይ በህልሜ ሳያችሁ ነበር፡፡ህልሜን አምኜ እዚህ ስመጣ ደግሞ በአካል አገኘዋችሁ፡፡››
-እኔም አይቼዎታለው››
-በይ እንግዲህ የምኞትሽ ይሙላልሽ ?
-በህልሞት ምንም እንዲነግሩኝ አልተነገሮትም.››
-አይ ሁሉንም ለእሷ ነግሬያታለው..አንተ ብቻ አግኛትና ልጇን ደባብስላት ነው የተባልኩት፡፡……..ብለው አልፈውን መንገዳቸውን ሲቀጥሉ…እናቴ ከድንዛዜዋ ባና -እሺ እግዜር ይከተሎት..አለቻቸው
-አንቺንም ልጄ....ከእነልጅሽ እግዜያብሄር ይጠብቅሽ ፡፡ብለው ከእይታችን ተሰወሩብን
ከዛ ቡኃላ እናቴ ፍፁም ተረጋጋች
👍4
በእኔ ላይ ያላትም እምነትና ተስፋ እንደአዲስ ደርጅቶ አበበ፡፡በዛም መሰረት እንደማንኛውም ልጅ በ7 ዓመቴ አንደኛ ክፍል አስገባቺኝ ፡፡

💫ይቀጥላል💫

አረ Like እየቆጠባቹ ነው 👍👍 Like እያደረጋቹ እንጂ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#የመልስ_ጉዞ_ወደ_መነሻ
:
#ክፍል_ሰባት
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
ትምህርት ቤት ገባው፡፡መናገር ባልችልም የምማረው ከተናጋሪዎች ጋር ነበር፡፡አርግጥ ተማሪዎቹም ሆነ አስተማሪዎቹ ብዙም አይጥሙኝም፡፡ትምህርቱም እንደዛው ፡፡ግን ተማርልኝ ያለቺኝ እናቴ ስለሆነችና እሷ ያለቺኝን ነገር ሁሉ ተመቸኝም አልተመቸኝም …አስደሰተኝም ፤አስከፋኝም ማድረግ ስላለብኝ ነው ያደረኩት፡፡
አንደኛ ክፍል አንደኛ ሴሚስተር በከፍሉ ካሉት 56 ተማሪዎች 55ተኛ ደረጃ ወጣው ፡፡የበለጥኩት አንድ ልጅ በመጨረሻዎቹ የፈተና ቀኖች ትምህርት ቤት ተገኝቶ ዋናውን ፈተና መውሰድ ስላልቻለ እና ካርዱ ላይ የተቀመጠለት ውጤት ቴስት ላይ ያገኛቸው ውጤቶች ብቻ ነበሩ፡፡
እኔ ባመጣውት ውጤት ማንም አልተደነቀም ምክንያቱም ማሰብ እንደምችል እራሱ የሚያምን ሰው ጥቂት ነው፡፡ማሰብ ማይችል ሰው እንዴት መማር ይችላል ብለው ይገምታሉ…?፡፡ ካርዴን ይዤ መጥቼ ለእናቴ ስሰጣት እቤቱ ሙሉ ወዳጅ ዘመድ በተሰበሰበበት ነበር፡፡ልክ ድንበር ሊወር የመጣን የጠላት ወታደር ፊት ለፊት በጀግንነት ተፋልሞ በማሸነፍ የድል ብስራት ለወገኖቹ እንደሚያስር ወታደር ደረቴን በኩራት ገልብጬ…
-አይ ዝም ብለሽ እኮ ነው የምትለፊው…..እቤት ከነበሩት መካከል አንዱ ዘመድ የተናገረው ነበር..
-እንዴት ዝም ብዬ…?
-ትምህርት እኮ ለእሱ ይከብደዋል፡፡እንዲሁ ከልጆች ተቀላቅሎ ይዋል ብለሽ እንደሆነ ይገባናል፡፡ግን ማሰብ ያለብሽ ወደሁለተኛ ክፍል ለመዘዋወር ስንት አመት ይፈጅበታል የሚለውን ነው……?ሶስት……?አራት….…?
.
-ለእኔ ስሜት ሳይጨነቁ እንደአፌ አእምሮዬም ዝግና ዱልዱም መሆኑን እርግጠኛ ሆነው እናቴን የሚያሳቅቁበት መርዝ ንግግር ሰነዘሩ..
እናቴ ከተቀመጥኩበት ወደራሷ ስባኝ ጭኖቾ ላይ በማጋደም ጭንቅላቴን እየዳበሰች…
-ልጄ በአመቱ መጨረሻ ወደ ሁለተኛ ክፍል በበቂ ውጤት አልፎ ካልገባ እኔ ላይ ሳቁብኝ፡፡…አለቻቸው እሷም ልክ እንደእኔው ጀግና ልጅ እንዳለት እርግጠኛ በመሆን ደረቷን ነፍታ..
-አረ ተይ የማይሆነውን ….ብለው ወዲያውኑ ሳቃቸውን የለቀቁት በርከት ይሉ ነበር….እኔ ግን የእናቴ ንግግር ትንሿን አዕምሮዬን ሰንጥቆ ነበር የገባው፡፡‹በዓመቱ መጨረሻ ልጄ ወደ ሁለተኛ ክፍል ካላለፈ ሳቁብኝ›…ፃድቋ እናቴ ላይማ ማንም አይስቅባትም…..ወሰንኩ፡፡
-ማታ ብቻችንን ሆነን ደረቷ ላይ ተኝቼ ማስበው ወደ ሁለተኛ ክፍል ስለማለፍ ነበር፡፡
-ምን ማድረግ አለብኝ…?፡፡በአንደኛ ሲሚስተር እንዴት እንደተማርኩና …?እንዴት እንደተፈተንኩ…? አሰብኩ.. አስተማሪዎች ሲያስተምሩ አንድም ቀን አዳምጬያቸው አላውቅም…አንዳንድ ቀን በመስኮት አሻግሬ ሜዳ የሚጫወቱትን ልጆች ወይም ዛፍ ላይ አርፋ የምትዘምረዋ ወፍ ወይም በሰማይ ላይ የሚጓዘውን ደመና ስመለከት ነው ክፍለ ጊዜው የሚያልቀው፡፡አንዳንዴ ደግሞ ወረቀት ቀድና በምራቄ አለስልሼ ጆሮዬ ውስጥ ጠቀጥቃለው..
---አንድ ቀን ይሄንን ሳደርግ እጅ ከፍንጅ የያዘኝ አንድ መምህር..አንደበትህን እንደዘጋው ጆሮህንም እንዲደፍንልህ ትፈልጋለህ…ሲል ጠየቀኝ በመገረምና በንዴት አፍጥጦብኝ
ግንባሬን በመወዝወዝ‹‹አዎ…›› የሚል ምልክት አሳየውት
አማተበና‹‹አንተንስ ትልቁ አጋንንት ነው የተጠጋህ ››ብሎኝ ወደማስተማሩ ተመለሰ…..ከዛን ቀን ቡኃላ ጭራሽ የዛ ክፍል ተማሪ እንዳልሆንኩ በመቁጠር ረሳኝ … እኔም ተመቸኝ..፡፡
ስለዚህ አሁን በዓመቱ መጨረሻ እኚ ወሬኞች እናቴ ላይ እንዳይስቁባት..አስተማሪዎች የሚሉትን ትንሽ ትንሽም ቢሆን ማዳመጥ መጀመር አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡
የትምህርት ዘመኑ ተጠናቆ ..ሰኔ ሰላሳ መጥቶ የወላጆች በዓል ላይ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ….ልዩ ተሸላሚ ሆኜ መድረክ ላይ ተጠራው.. ሰው ሁሉ የፀባይ ሽልማት መስሎት ነበር..ያው ድዳ በመሆኔ ተናግሬ መበጥበጥ ስለማልችል በተጨማሪም በፀባዬ ጠማማነትም የተነሳ ከልጆች ጋርም እንደማልገጥም ብዙዎች ስለሚያውቁ የፀባይ ሽልማትማ ይገባዋል… ብለው ነበር ያሰቡት፡፡
-የትምህርት ቤቱ ዳሪክተር ግን እኔን ስራቸው አቁመው ጭንቅላቴን ልክ እንደ አባት እየዳበሱ በአስገምጋሚ ሻካራ ድምፃቸው የትምህርት ቤቱን ግቢ ለሞሉት ተማሪዎቻቸውና ወላጆቻቸው መናገር ጀመሩ…
***
በ25 ዓመት የማስተማር ልምዴ እንዲህ አይነት ተአምር ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ማመን አቅቶን ውጤቶቹን ሁሉ ደግመን ፈትሸን ነበር የሚገርመው ምንም እንከን አልተገኘባቸውም ፡፡በአንደኛ ሴሚስተር ከክፍሉ የመጨረሻውን ደረጃ ነበር የያዘው…
ኹ ..ሁሁሁ ብሎ ታደሚው ሁሉ አውካካ..
በዚህኛው ሴሚስተር ደግሞ አንደኛ ….ከሰባት ትምህርት ስድስቱን መቶ.... አንዱን ዘጠና ስምንት ነው ያመጣው፡፡አማካኝ ደረጃው 23ተኛ ደረጃ ፡፡እንዲህ አይነት ለውጥ በማምጣቱ ትምህርት ቤታችን እንዶኮራበት ወላጆቹም ልትኮሩበት ይገባችሆል..በቀጣይ በዚሁ እንዲቀጥልም አስፋላጊውን ድጋፍ አድርጉለት ..በማለት ከአቅሜ በላይ የሚከብድ መዝገበ ቃላት በሽልማት መልክ አሸከሙኝ››
መድረኩን ለቅቄ እየወረድኩ እናቴን አየዋት… ከአምስት ወራት በፊት ሳቁብኝ ብላቸው ወደነበሩ ወዳጆቾ ዞራ ቅዱስ የእርካታ ሳቅ እየሳቀችባቸው ነበር….እኔም በፈገግታ አገዝኳት።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍7
<<ነ>>

ሀገርን የሚያክል ህላዊ እያለነ፤
በዘርና ብሄር በጎጥ በሀይማኖት፤
ተሸነጋገልነ፤
ተፈነጋገልነ፤
የኔ የሱ የሷ የኛ ኬኛ እያልነ፤
ይሄው ይሄኛውን ሳብነ፤
ያኛውን ገፋነ፤
አለቅጥ ዘቀጥነ፤
አለቅጥ ጠበብነ፤
ምነ ! ምነ! ምነ !
እንዲህ የወረድነ፤
እንዲህ የጠበብነ፤
ቀን በየሄድንበት፤
ሌት በተኛንበት በየትም አቅጣጫ፤
እንደያለንበት፤
አለቅጥ ጠበነ፤
አለቅጥ አንሰነ፤
እንጨነቅበት እንሰራው ጠፋነ፤
እንሆነው አጣነ፤
በዚ ሆነ በዛ ራስ ወዳድ ሆነ፤
ራስ አበዛነ ባገኘነው ሁሉ አንድነት ትተነ፤
ስንወጣ ስንገባ ጎጥ እየነዛነ፤
ዘር እየመዘዝነ፤ህዝብ አሰቃየነ
ሀገር አሸበርነ፤
ምነ! ምነ! ምነ!
እንደዚ ታወርነ፤ለማጥላት አንዱነ
ጉድጓድ እየማስነ፤
አንዶንዱን ለመነጥነፍ ነፍጥ እየተኮስነ፤
ታሪክ በርዘን፤
የማያግባባነ ታሪክ እየፃፍነ፤
የሚለያየነ፤ስልት እየደፈነ፤
እጅጉን አነሰነ፤ነጥብን አከልነ፤
ከልፍነት ወጣነ፤
ምነ !ምነ ምነ !
እንደዚ የጠበብነ፤እንደዚ ያነስነ፤
ሌላው ስለአንድነት፤አለም ስለህብረት፤
እየተጨነቀ የኛ ግን አንድነት እያደር ሟሸሸ
እያደር አለቀ ምነ ! ምነ ! ምነው ! አረ ምነ!
እንዲህ የጠብነ ይሻልን ትተነ፤
አንዷዱን መክሰሻ ቅጥያ፤
እንደጆሮ ሰርክ እየለጠፍነ፤
ዱላ ለመማዘዝ ጥይት ለመታኮስ፤
ጥላቻ ሌት ተቀነን እያሰራጨነ፤
ፍቅር እየገፋነ፤ ቂም እየገዛነ፤
መተሳሰብ ይሉት ባፍጢሙ ደፍተነ፤
ትብብር ሲያሻነ፤ንጥጥል መርጠነ፤
መደማመጥና በሀሳብ መላቅን
ሺ ክንድ እርቀነ፤
በነጋ በጠባ አጀንዳ ፈጠርነ
ቂምን አባዛነ፤ ተንኮልን ነደፍነ፤
የተረሳን ቁስል ብሶት ቀሰቀስነ፤
ምነ ! ምነ ! ምነ !
እንደዚ ጠበብነ፤
ምነ ! ምነ ! ምነ !
ፍቅር እንደሰማይ እንዲህ የራቀነ
ምነ ! ምነ ! ምነ !
እንደዚህ ያነስነ፤
ካገራችን ይልቅ የጎሳችን ጉዳይ ሰርክ አስጨነቀነ፤
ባለመደማመጥ ሽኩቻ ታመስነ፤
ተንኮል በመጎንገን በሴራ ታመምነ፤
ጠበብነ፤
ጠበብነ፥
ይሄው ከልክ አልፎ፤
በየኛና ኬኛ ህዝብ አወዛገብነ
እናት አስጨነቅነ፤ አገር አሸበርነ፤
ምነ! ምነ!ምነ! ምነው !አረ ምነ!
ማን ረገመነ ?
የሀሳብ ቋንጃችን ተበተበ በነ፤
መላወሻችንን ማን አሰረብነ፤
ትላንትን ዘክሮ፤ ዛሬን ተተርሶ፤
ነገንም አስታውሶ፤
ከታሪክ ፈልፍሎ መፍትሄ የሚያመጣ
አንድ ሰው ያጣነ፤
እውነት ግን እናተ ማን እረገመነ ?
ምነ! አረ ምነ!
ያገር ውላችንን ማን ቋጠረብነ ?
እንዲህ በአጭር ጊዜ፤
ተስፋችን በጠዋት ጉም ሸፈነበነ፤
አምና ይሄን ግዜ ከመቶ ሚሊዮን
አንድ ሰዉ ስጠነ ብለን ተጨንቀነ፤
ከዚህ የጭንቅ ውሀ የሚያሻግረነ፤
ከፍቅር ደሴት ዘንድ አቅፎ የሚያደርሰነ፤
የኛ ዘመን ሙሴ አገኘን ብለነ፤
በየአደባባዩ እንዳልተሰለፍነ፤
አኛ እንሙት ብለነ፤
ቦንብን ያህል ነገር ካየር ላይ ቀልበነ፤
እንዲያ እንዳልቆሰልነ፤
ወይም እንዳልሞትነ፤
እናዳልተሰዋነ፤ አመት ሳይሞላነ፤
ከዚያኔው ሰቀቀን የባሰ፤
የሚመስል የጨነቀ ነገር ምነ ገጠመነ፤
ጎራ ለይተነ አንደኛው ካንደኛው፤
እየተቧደነ አንገት ለመቀንጠስ ምነ ተፋለግነ፤
ወደ ነበርንበት ወደዛ ክፉ ቀን መመለስን ሻትነ፤
ምነ ! ምነ ! ምነ !
ፍትህን ብለነ ለውጥ ይምጣ ብለነ፤
በጎንደር በአንቦ በአገር ዙርያ ገባ፤
ደሙ ደማችን ነው እዳልተባባልነ፤
በጋራ ሁነነ እየተባበርነ፤
እየተሳሰብነ የጨለማውን ቀን እናዳልቸሻገርነ፤
ባይዞህ አይዞህ እታ ክፉውን፤
አቀበት እንዲያ እንዳልወጣነ፤
የለውጥ አየር ሲነፍስ ምኑ ዞረብነ፤
ምን ሰይጣን ገባነ፤
ባቢሎን ሆነን የኛ ኬኛ የሚል ቋንቋ አደባለቅነ፤
አረ እንደማመጥ አረ እንነጋገር፤
ምነ ! ምነ ! ምነ ! ምነው? አረ ምነ !
የትላት ጥንቡሳስ ምነ ቢበቃነ፤
ለትላንት አዙሪት ባትመልሱነ፤
ምነ ! ምነ ! ምነ !
አረ በፊደሏ አረ በ ነ ! በ ነ !
ጠዋት ማታ ስጋት እንደጨው ሟሟነ፤
መሞት መፈናቀል ሆነ እጣችነ፤
ምነ ! ምነ ! ምነ !
ባታስጨንቁነ፤ አንድ አመት ሳይሞላ
እንዳምና ካቻምናው አታሸብሩነ፤
አረ በፊደሏ አረ በ ነ! በ ነ!
በብሄር መናቆር ስለሰለቸነ፤
ስላሳቀቀነ አታለያዩነ፤
አታነጣጥሉነ፤ አታበላልጡነ፤
ይልቅ በኩልነት ወደ ፊት ምሩነ፤
ያንድ ኢትዮጵያ ልጆች እኛ ሁላችንም፤
ከዘራችን በፊት፤
ሰው ነነ ! ሰው ነነ !!

💚 💛 ❤️
#የመልስ_ጉዞ_ወደመነሻ
:
#ክፍል_ስምንት
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...ከዛ ቡኃላ የትምህርት ቤቱ አስደናቂ ኮከብ ተማሪ ሆኜ ቀጠልኩ ፡፡እስከሶስተኛ ክፍል እስካጠናቅቅ ድረስ አንደበቴ እንደተዘጋ ነበር፡፡አስር አመት ከሆነኝ ቡኃላ አንድ ለሊት እኔና እናቴ የሰላም እንቅልፍ ተኝተን እያለ…ባልተለመደ ሰዓትና ሁኔታ የቤታችን መንጓጓት ሁለታችንንም እኩል ከእንቅልፍችን ቀሰቀሰን…. ሁለታችንም እኩል ዙሪያችንን ስንቃይ እቤቱ በድቅድቅ ጨለማ እንደተዋጠ ስለነበር ምንም ሊታየን አልቻለም … መብራቱን ለማብራት እኔም እናቴም እልደፈርንም….. …እናቴ ከክንዷ ላይ እኔን በማውረድ ከእቅፎ አውጥታኝ በዝግታ በመነስታ እና ቁጭ በማለት ምን እንደተፈጠረ ለማረጋጋጥ ጆሮዋን አቀናች..እኔም እሷን ተከትዬ ለመነሳት ስሞክር በእጇ ደፍቃ ባለውበት አስቀረቺኝና ወደጆሮዬ ተጠግታ በሹክሹክታ‹‹..አርፈህ ትንፋሽህን ውጠህ ተኛ..››በማለት አስጠነቀቀቺኝ …
ወዲያው የመኝታ ቤቱ በራፍ ሲበረገድና ባትሪ ግንባራችን ላይ ሲበራ እናቴ ‹ዋይ› የሚል ድምጽ አሰምታ ‹ልጄን ›በማለት እኔ ላይ ድፍት አለች
…ሁሉም ቅፅበታዊ ነበር…ውር ውር የሚል የባትሪ ብርሀን ግድግዳው ላይ ወዲህ ወዲያ ሲራወጥ እና የእግር ኮቴ ሲዘዋወር ይሰማኛል…
‹‹በል ፈትሽ ..ኮመዲኖውን ክፈት››ድምጽ ተሰማ
‹‹እንቀሳቀሳለው ብለሽ አንቺን ሳይሆን ልጅሽን ነው ፀጥ የምናደርግልሽ..››ሌላው እናቴን አስፈራራ…..
እናቴ የራሷን ትንፋሽ ወደውስጧ ማፈኗ ሳያንሳት እኔንም እላዬ ላይ እንደተደፋች በእጆቾም አንደበቴን ከደነችው፡፡
‹‹-አዎ ሁሉንም በሻንጣ ክተት..አዎ ወርቅም አገኘህ…ጥሩ ልብሶቹንም እንዳትተው››ይላል
ሶስት መሆናቸው በድምጻቸው ልዩነት ገምቼያለው፡፡ያው መዘረፋችን ቢያሳዝነኝም ዋናው እናቴን አለመጉዳታቸው ነው ብዬ በመጽናናት ስራቸውን እስኪጨርሱ እናቴ እንዳፈነቺኝ ታፍኚ በተኛውበት ተረጋግቼ የሚያደርጉትን ማየት ባልችልም የሚናገሩትን በትዕግስት እየሰማው ሳለ
በቃ እንሂድ ››በማለት አንዱ የመጡበትን ማጠናቀቃቸውን አበሰረን….››እፎይ ምንልበት ጊዜ ደረሰ.. ስል ተደሰትኩ
‹‹በል እናትዬውን እሰራት..አፎንም አሽገው››የሚል ደባሪ ድምጽ ወደጆሮዬ ገባ
‹‹ለምን አስፈለገ.…?.››ሌላው ጠየቀ
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ ..ከዚህ ሳንወጣ ጩኸቷን ብትለቀውስ…?›› ስጋቱን ተናገረ
‹‹እናንተ ብቻ የያዛችሁትን ይዛችሁ በሰላም ውጡልኝ …በልጄ ምላለው ምንም አልጮህም››እናቴ ተማፀነቻቸው
አንደኛው‹‹ዝም በይ..›› ብሏት በምኑ እንደሆነ አላውቅም ከላይ ወገቧን ሲነርታት የህመሙ ስሜት ከስር ያለውትን እኔን ሳይቀር ተሰማኝ …
‹‹ና በል አንሳትና ከእዚህ የአልጋ እግር ጋር ጠፍንገህ እሰራት …ልጇንም እንደዛው….››ሲለውና ሌላው ትዕዛዙን ለማክበር እናቴን መንጭቆ ከላዬ ላይ ሲያነሳት ..የሆነ የማላውቀው ኃይል በሰውነቴ ሲሰራጭ ታወቀኝ
…እናቴ ‹‹ልጄን … ልጄን እንዳትነኩብኝ ››..እያለች ስትወራጭ…የድምፆ ቅጭልጭልታ ጆሮዬን እየነዘረ ወደጭንቅላቴ ሲሰርግ እና የሆነ የማላቀውቀው መንፈስ ሲቆጣጠረኝ አንድ ሆነ…..
ወደእኔ ከመምጣታቸው በፊት ተሸከራከርኩና በተቃራኒው በኩል ከአልጋው ተንከባልዬ ወረድኩ …… አዛዥ ቢጤው‹‹ልጁን ያዘው.. ልጁን ያዘው›› ሲል ይሰማኛል፡፡ አልጋውን ዞሮ ወደእኔ ከመምጣቱ በፊት ለእኔም ግልፅ ባልሆነልኝ የደመነፈስ ውሳኔ እና የእኔ ባልሆነ ፍጥነት የቁም ሳጥኑን መሳቢያ ስቤ ሽጉጥ አወጣውና ወዲያው መብራቱን በማብራት በኮማዲኖ በራፍ መላ አካሌን በመከለል ጭንቅላቴን ብቻ በከፊል ብቅ አድርጌ ሁኔታውን ቃኘው ….፡፡አዎ እንደገመትኩት ሶስት ናቸው፡፡ሁሉም ፊታቸው ላይ ጭንብል አጥልቀዋል፡፡ግን የጠበቅኮቸውን ያህል አስፈሪና ወጠምሻ አይነት አይደሉም…አንዱ የብረት ዱላ ሁለቱ ጩቤ ይዘዋል፡፡አንዱ በራፉ ጋ ቆሞ በቀኝ እጁ የያዘውን ባትሪ እኔ ወዳለውበት ቀስሯል፡፡ማብራቱን ካበራው ቡኃላ እንኳን አላጠፋውም..ሌላ እናቴን እያሰራት ነው..ሶስተኛው ሊይዘኝ ወደእኔ እየተንደረደርረ ነበር ..ሊያንቀኝ ሁለት ሜትር ያህል ብቻ ነበር የሚቀረው፡፡ከተሸሸኩበት ሳልወጣ ልክ ፊልም ላይ ደጋግሜ እንደማየው የያዝኩትን ሽጉጥ ቃቃ አድርጌ በማቀባበል እጄን ወደፊት በግንባሩ አቅጣጫ ቀስሬ ‹‹ ግንባርህን እንዳልፈረክሰው ባለህበት ቁም…››
ስለው ሳያቅማማ ደንዝዞ ትዛዜን አከበረ…እሱ ብቻ ሳይሆን ሶስቱም ያልጠበቁት ስላጋጠማቸው በሉበት ሲርበተበቱ በሰከንድ ሽርፍራፊ ቃኘው …ብዙም ልምድ የሌላቸው የመንደር ሌቦች መሆናቸውን ወዲያው ተረዳው፡፡
አናቴን እያሰራት ወደነበረው ሽጉጡን አዙሬ …‹‹እናቴን ልቀቃት…››ጮህኩበት …
ማሰሩን አቁሞ ቁጢጥ ካለበት በመነሳት ቀጥ ብሎ ቆመ…
ትዕዛዜን ቀጠልኩ ‹‹…አሁን አንድ ሰው ከመግደሌ በፊት እቃውን አስቀምጣችህ እቤቱን ለቃችሁ ውጡ ››
ተያዩና በምልክት በመነጋገር ወደኃላ መሳብ ጀመሩ…በራፍን ካለፉ ቡኃላ በሩጫ አስነኩት…
ከእውነተኛ ሽጉጥ ጋር በእጅ ካልያዙት በስተቀር ምንም ልዩነቱ የማይታወቀውን ልጅ ሆኜ የተገዛልኝን መጫወቻ ሽጉጥ መሬት ጥዬ ወደእናቴ ተንደረደርኩና አፎ ውስጥ የጠቀጠቀውን ጨርቅ ቀድሜ አውጥቼ በመጣል…. እጆቾን ልፈታ ስጣጣር እሷ እልልታዋን እስነካችው…
-እንዴ ምን እየሆነች ነው…?፡፡ግራ ገባኝ፡፡ ሰው እቤቱ ሌባ ሲገባበት ኡኡ ነው ማለት ያለበት ወይስ እልልል….…?
ወይ ድንጋጤ
- …እማ አይዞሽ ተራጋጊ …በማለት እጆን ፈትቼ ስጨርስ ተጠምጥማብኝ እያገላበጠች ትስመኝ ጀመረች
‹‹አደረከው..ልጄ አደረከው….አንድ ቀን እንዲህ እንደሚሆን አምን ነበር…እግዚያብሄር ሁሌም ካንተ ጋ ነው…አዎ አንተ ልዩ ነህ፡፡››
‹‹እማ ..አዎ ደርሼልሻለው … ከአሁን ወዲህ አይኔ እያየ ማንም ሊያጠቃሽና ሊያመናጭቅሽ አይችልም.. ማንም እንደዛ እንዲያደርግ አልፈቅድለትም…››ፎከርኩ
‹‹ እሱ አይደለም ልጄ …እሱ አይደለም..መናገር ቻልክ..ተናገርክ..እያወ
ራሀኝ ነው››ስትለኝ ድንግርግሬ ወጣ….እንዴ እያወራው ነው እንዴ ….…?.ከመገረሜ ሳልወጣ የእናቴን እልልታ የሰሙ የቤታችን ተከራዬች አያቴም ጭምር ከሚጣፍጥ የለሊት እንቅልፋቸው ተነስተው በመምጣት ወደቤታችን ሲንጋጉ ሰማን….

💫ይቀጥላል💫

የኛ ክፍያችን የናንተ ደስታ ነው ስሜታችሁን Like 👍👍 በማድረግ ግለፁልን

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍4
#ሰፊ_ሀገር_ጠባብ_ዜጋ

ሀገሬ ሰፊ ናት ከአድማስ አድማስ የራቀች
ሀገሬ እሩቅ ናት ከሰማየ ሰማይ የመጠቀች
ሰማይ ናት ሀገሬ የከዋክብት አድባር
ሰማይ ናት ሀገሬ የመላእክት ሀገር
#ሌላም
ሀገሬ ሳሌም ናት የአዳም መሰረቱ
የተፈጠረባት መገኛ የጥንቱ
የሰው ዘር ያለባት ደግሞ እንስሳ አውሬ
ጥርት ኩልል ያለች መሬት ናት ሀገሬ
የሚመግብባት አብርሃም ታላቁ
ፀሐይ ያቆመባት ኢያሱ ምጡቁ
ባህርን ያቆመባት ነቢያችን ሙሴ
ሁሌ ' ሚሰማባት የሰማይ ቅዳሴ
ጻድቃን በስራቸው የሚጠለሉባት
ኀጥአን በስራቸው የሚሰወሩባት
የንጹሀን ሀገር ሀገሬ ኤደን ናት
#ግን
ጠባብ ሰው ገጠማት ሰፊ ሁና ሳለ
ያላየውን ሁሉ የኔ ነው እያለ
ለምለም ሳር እያለ ደረቅ በል እንስሳ
ስጋ ሞልቶ ተርፎ እጸ በል አንበሳ
ውሃ ጠጪ ድመት ወተት ሞልቶ ተርፎ
ቅጠል ለበስ ትውልድ ጥጡ ተረፍርፎ
ሁሉም በዝተው በዝተው ግብራቸው ተሽጦ
ሀገር ጠባብ ሆነች ስሟ ተለውጦ
#ግሩም ነው
ስንት ኪሎ ሜትር የማይመጥናትን
ስንት ስንት ማይል የማይገድባትን
ጠባብ ሰው ለክቷት ስሟም ተቀየረ ቁጥሩ እየባከነ
የአገሬ ስፋቷ ሴንቲ ሜትር ሆነ!!!!
ጠቢብ እስኪፈጠር አስኪታወቅ ልኳ
ለጊዜው ጠባብ ነው የሀገሬ መልኳ

🔘ሞገስ ሁንያለው🔘
👍1
#የመልስ_ጉዞ_ወደ_መነሻ
:
#ክፍል_ዘጠኝ
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...ከአስር አመት ቡኃላ ማለቴ አንደበቴ ከተፈታ ቡኃላ ያለኝ ህይወት ከዛ በፊት ከነበረው ፍጽም በተቃራኒ መንገድ የተጓዘ ነበር፡፡
በተለይ አንደበቴ እንዲፈታና እንድናገር ምክንያት የሆነው የቤታችን የመዘረፍ ሙከራ እና እኔ እራሴንም ሆነ እናቴን ከጥቃት የታደኩበት ሁኔታ ቅጽበታዊ የአንድ ቀን ክስተት ብቻ ሆኖ አላለፈም ፡፡የህይወቴን አቅጣጫና መላ አመለካከቴንም ሙሉ በሙሉ ነው የቀየረው፡፡
ሌቦቹ ልምድ ያላቸው ደፋርና ጨካኝ ቢሆኑ ኖሮ የዛን ለሊት እኔና እናቴ አልቆልን ነበር ማለት ነው፡፡ወይ ሞተን ወይ ደግሞ አካላ ጎዶሎ ሆነን ነበር፡፡ከዛ ታሪክ የተማርኩት በዚህ አለም ላይ አሸናፊ ሆኖ ለመኖር ብልህነት ብቻ ሳይሆን የአካል ጥንካሬም ወሰኝ እንደሆነ ነው፡፡
ብዙውን ጊዜ ምሉዕ እና ስኬታማ የሆኑ ሰዎች የአዕምሮአዊና እና የአካላዊ ጥንካሬያቸው ምርጥ በሚባል የብቃት ደረጃ የሚገኝ መሆኑን ታሪክ ይመሰክራል ፡፡ያ መሆኑ ሰዎቹ በሚጓዙበት በህይወት መስመር ላይ የፊት መሪ ሆነው ለመመረጣቸው ባይመረጡም እንኳን እራሳቸውን በራሳቸው መሪ አድርጎ ለመሾም እና ለዛም የሚደግፎቸው በርካታ ሰዎች በዙሪያቸው ማሰለፍ የመቻላቸው ሚስጥር የነፍስ ልህቀት ቅኝታቸው እና የአካል ጥንካሬ ብርታታቸው እኩል ዳብሮ መገኘቱ …በማድረግ ብቃታቸው ላይ ሆነ ሌላው ማህበረሰብ ላይ ተፅዕኖ የማሳደር ሚስጥራዊ ሀይል እንደሚያጎናጽፋቸው ገና በጥዋቱ በአስር አመቴ ተገለፀልኝ፡፡እና ሰፈራችን የሚገኝ ቴኮንደ ማሰልጠኛ ቤት መማር እንደምፈልግ ለእናቴ የነገርኮት ወዲያውኑ ነበር፡፡ለምን ፈለከው . ..?ምን ያደርግልሀል..? ምናምን ብላ ሳትጨቀጭቀኝ..ወዲያው የሚከፈለውን ከፍላ ወስዳ እስመዘገበቺኝ፡፡እናቴ የእኔ ጀግና ፡፡
ታዲያ የዛ ውጤት 15 ዓመት ሲሞላኝ ደረቴ ወደፊት የተገለበጠ…ሆዴ እንደብረት ጠጥሮ ወደ ውስጥ የተጠቀለለ…የእጆቼ ጡንቻዎች ፈርጣማ ..ተፈጥሮ ከለገሰኝ ዘለግ ያለ ቁመት ጋር የሀያ አመት ጓረምሳ አስመስለኝ፡፡በአካልም ሆነ በአዕምሮ ከእኩዬቼ አንፃር በጣም በሚባል ደረጃ ቀድሜ አደኩ፡፡ በዚህ ምክንያት ይሁን በተፈጥሮ ባለኝ መስህብ በእንስቶች የፍቅር እይታ ውስጥ በቀላሉ እገባለው፡፡ይቀርቡኛል …ሊፈትኑኝ፡፡ሸሻቸዋለው… እንዳይጥሉኝ ፡፡
ሌላው ትምህርቴን በተመለከተ በቀላል ልፋት አስደማሚ ውጤት ማምጣት ለእኔ የሚወዱትን አስደሳች የካርታ ጫወታ የመጫወትን ያህል ቀላል ሲሆን ለሌላው ተመልካች በተለይ በቀን ስንት ሰዓት እንደማጠና ..?ምን ስሰራ እንደምውል..? ለሚያውቁ ሰዎች እና ጓደኞቼ አስደማሚ እና ግራ አጋቢ ነበር፡፡
‹በልጅነቱ እናቱ አብሾ አግታው ነው ጎበዝ የሆነው ›ብለው ሚያሙኝ እኩዬቼም ሆኑ የሰፈር አዛውንቶች እንዳሉም አውቃለው፡፡
***
ሌላው ባህሪዬ ከትምህርት ጉብዝናዬ ጋር የማይሄድ የማፊያነት ባህሪ ይታይብኝ የጀመረው ገና በጥዋቱ ነበር፡፡መጀመሪያ በእኔ መሪነት የሚንቀሳቀሱ ሶስትና አራት ልጆችን በማስተባበር ጥቃት የሚደርስባቸውን የሰፈር እና ሌሎች የማቀቸውን ሰዎች ከጥቃት በመከላከል ነበር የጀመርኩት፡፡እያደር ግን በትምህርት ቤቱ ስውር መንግስት ሆንኩ፡፡እኔ ያወጣውትን ህግ እንኳን ተማሪዎች አስተማሪዎች ወደውም ሆነ ፈርተው ይተገብሩታል፡፡
ግን ጉልበት አለኝ ብዬ በመታበይ ከመሬት ተነስቼ ሰውን አልጋጭም፡፡በማንም ላይ ከአስፈላጊው በላይ ጉልበትም ሆነ ጫና አልፈፅምም ፡፡ግን ተገቢውን እርምጃ በተገቢው ጊዜና መጠን ለመውሰድ ሰውዬው ማንም ይሁን ማንም አልፈረምም …ላቅማማምም፡፡
ኃይልን በተመለከተ አንድ ምክር ልስጣችሁ ፡፡የሆነ ስልጣን አለኝ ወይም አስተማማኝ ጉልብት አለኝ ብላችሁ ማንኛውንም የመጨረሻ ደካማ ነው የምትሉትን ሰውም ላይ ቢሆን የመጨረሻ ውን ተስፋ እስኪቆርጥ ድረስ አትቅጡትም … አትግፉትም ፡፡..ያንን ካደረጋቹ የራሳችሁን ጉድጓድ እየቆፈራችሁ መሆኑን እወቁት ፡፡ተስፋ የቆረጠ ድመት የነብር አንገት መቀንጠስ ቢያቅተው እንኳን የነብርን አይን ለማጥፋ አይሰንፍም፡፡
እና ምን ጊዜም ይሄ የሀይል አጠቃቀም ለእኔ መመሪያዬ ነው፡፡ያሸነፍኩትን በምን ያህል መጠን መቅጣትና መቼ ይቅር ማለት እንዳብኝ በጥንቃቄ አስብበታለው፡፡
ያው የትምህርት ቤቱ ስውር መንግስት ነኝ ብያችሁ የለ፡፡መጀመሪያ በዘፈቀደ ነበር ነገሮችን የምከውን የነበረው፡፡ዋናው ትኩረቴ የሆነ ታዛዥ ጦር ከኃላዬ ማሰለፌ እና በሚያውቁኝም (እጄን በቀመሱትም) ወይም በዝና ብቻ በሰሙትም ዘንድ መፈራቴ እና መከበሬ ነበር፡፡
በነገራችን ላይ በሄድኩበት ሁሉ የመከበርና እና የመደመጥ ሱስ አለብኝ፡፡ማንም ቢሆን በእድሜ እኩያዬ ይሁን ወይም ታላቄ ትኩረት እንዲነፍገኝ ወይም ዝቅ አድርጎ እንዲያኝ ፈጽሞ አልፈቅድም፡፡ሲያከብሩኝ ደስ ይለኛል፡፡አዎ ማንኛውም ሰው ከቻለ እየወደደ ቢያከብረኝ ደስ ይለኛል ካልሆነ ግን እየጠላኝም ቢሆን እንዲፈራኝና እንዲያከብረኝ ፈልጋለው፡፡በሚወዱኝም ሆነ በሚጠሉኝ ሰዎች እኩል መፈራትና መከበር ፍላጎቴ ነው፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#የቦርሳሽ_ላይ_ስእል
:
ካነገትሽው ቦርሳ ፥ ከጀርባሽ ላይ ካለው
የዚያ ዘፋኝ ምስል ፥ ደምቆ የታተመው
ልብ ብዬ ሳየው ፥ ሁሌም ይገርመኛል
እንደ ኪነት ተውኔት ፥ ማርኮ ያስቀረኛል
:
#ያንን_የጨርቅ_ቦርሳ
በደብተር በመፅሃፍ ፥ የወጠርሽው ለታ
በድምፃዊው ፊት ላይ ፥ ይታያል ፈገግታ!
ባዶ ሲሆን ደ'ሞ ፥ ወይ አንድ-ሁለት ደብተር፤
#ጨርቁ_ተጨማዶ
አያለሁ ስእሉን ፥ ደርሶ ሲኮሳተር !
:
ይህ አይደለም ወይ? የእኛስ ህይወት ዳራ
ሁለት አይነት ምስል ፥ በአንድ የስእል ሸራ!
ትንግርቱ ገፃችን፤
በቀን አስር ጊዜ ፥ ተቋጠሮ 'ሚፈታ
ሲጎድል ትካዜ ፥ ሲሞላ ፈገግታ!!
#የመልስ_ጉዞ_ወደ_መነሻ
:
#ክፍል_አስር
:
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...አደኩ፡፡ጎረመስኩ፡፡ጉንጬ ላይ ብጉር አገጬ ላይ ፀጉር አበቀልኩ፡፡ያንንም ተከትሎ
➶➶➶
ፍቅሬ አስትንፋስህ ህይወቴ ነው፡፡ያንተ መኖር ደግሞ ለእኔ ብቸኛ የመኖር ዓላማዬ፡፡አንተ ፀሀዬ ነህ፡፡ እንጦጦ ተራራ ላይ በበቀለ አረንጎዴ ሳር ላይ በጀርባ ተንጋለው ከጥዋት ሦስት ሰዓት አካባቢ የሚሞቋት ሰውነትን የምታፍታታ፤አዕምሮን የምታነቃቃ፤የቆዳን ቀለም የምታፈካ ምጥን የእግዜር ፀሀይ፡፡ አዎ አንተ እንደዛ ነህ፡፡ሙሉ ፀሀይ ከእነግለቷ፤ ሙሉ ፀሀይ ከነኩነቷ ፡፡ከአንተ ሙቀት ተሸርፎ አኔ ጋር የሚደርሰው ሙቀት ፍፅም ያኖረኛል…ፍፅም ያፈካኛል፡፡
እንደእኔው ፈገግታህን ለማድነቅና ከዛም አለፍ ሲል በሙቀትህ ለመቅለጥ በመፈለግ በየእለቱ በዙሪያህ ሲያንዣብቡ የሚውሉ የትምህርት ቤታችን ቆነጃጅቶች እንዳሉ አውቃለው፡፡ግን ደግሞ አንዳቸውም በእኔ መጠን ውብ እንዳልሆኑ በእኔ መጠንም አንተን አንደማያፈቅሩ በእርግጠኝነት አውቃለው፡፡ባውቅም ዳሩ ተረጋግቼ መቀመጥ አልቻልኩም ፡፡..ልቤ በቅናት ያራል….ውስጤ እርብሽብሽ ይላል፡፡አንዳንዴ የሆነ ሽጉጥ ፈልጌ በእየእለቱ አንትን በሙሉ አይኗ ለማየት የምትደፍርን ማንኛዋንም ልጅ-አገረድ ግንባሯን ብቀነድባት ደስታዬ ነው፡፡ግን ያንንነ ለማድረግ ችሎታውም ሆነ ድፍረቱ ለጊዜው የለኝም፡፡በቅርብ ግን አምላክ ኃይሉን እንደሚያጎናፅፈኝ አምናለው..እናም የዛን ጊዜ አደርገዋለው፡፡ለአንተ ስል ከተማ አቃጥላለው፤ ለአንተ ስል ሺ ሰው ገድላለው…ለአንተ ስል እራሴን ከ20 ኛው ፎቅ ላይ ልወረውርም ችላለው…ለአንተ ስል የማላደርገወ ነገረ የለም…አስፈላጊ ከሆነ ለአንተ ስል አንተ ራስህንም መግደል ችላለው፡፡
ጊዜው ደርሷ ሁሉን ማድረግ እስክችል ግን አንተን የመጠበቅ አደራውን ለአንተው ለራስህ ሰጥቼያለው፡፡ የእኔ ጀግና ሴቶችን በተመለከተህ ባለህ አቋም ታኮራኛለህ እናም በዚሁ ቀጥል፡፡ ለአንዳቸውም ፊት አትስጣቸው፤ለአንዷም የልብህን ወርቃማ በር አትክፈትላት…የትኛዋም ብትሆን በብሩህ አይኖችህ አይታ ውስጥ አትግባ…ክንዶችህ የማንኛዋንም ወገብ ለማቀፍ አይሞክሩ …ወለላ ማር የሚንጠባጠብባቸው ሚመስሉ ከንፈሮችህ የማንኛዋም ቆርፋዳ ከንፈር ላይ አይረፍ …ቅዱስ ትንፋሽህን የትኛዋም ሄዋን ከእራሷ ሙትና ደካማ ትንፋሽ ጋር ቀይጣ ወደውስጦ ለመሳብ እድል አታግኝ ፡፡…በማንም ሴት ቀልድ ጥርሶችህ ተፈልቅቀው ፈገግታህ እንዳይረጭ…፡፡ለአንተ የምገባህ እኔ ነኝ..ከጎንህ አጥንት ተፈልቅቄ የተፈጠርኩ ሄዋንህ…ብትረግጠኝ ማይቆረቁረኝ፤ ብትገለኝ ቂም ማሊዝብ፡፡ብታቅፈኝ ማልጎረብጥህ ብትሰመኝ የማስደስትህ፡፡እኔ ለአንተ ጌጥህ እኔ ለአንተ ክብርህ ነኝ …፡፡በፈለከው ደቂቃ ጥራኝ በርሬ ወዲያው መጣለው፡፡ያሰኘህ ቦታ ቅጠረኝ ሲኦልም ቢሆን እገኛለው፡፡ ………..
***
ይሄ አስራ አምስት አመትና የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እያለው ከክፍሌ ልጅ የተፃፈልኝ የመጀመሪያው የፍቅር ደብዳቤዬ ነው፡፡ከዛ ቡኃላ ያለውን የአፍላነት የፍቅር መሳሳቡንና የስሜት መላተሙን አትጠይቁኝ ፡፡ ይሄንን ለእናንተ እንደምሳሌ መናገር የፈለኩት እያደኩ ስመጣ ምን ያህል ማራኪ ወንዳ ወንድ እና ተፈቃሪ ወጣት መሆኔን እንድትገዘቡልኝ ስለፈለኩ ነው።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍4
#በኔ_ቤት
:
በኔ ቤት……
ፍየል ቅጠል አይታ፤ሳትበላ ታድራለች
ዶሮ ጥሬ ረግጣ፤ልፆም ነው ትላለች
ውሻ ስጋ እያየ፤በረሀብ ይሞታል
ሰው እህል ቀርቦለት፤ባዶ ድስት ይከፍታል


#በኔ_ቤት

አንበሣ ሚዳቋን፤አቅፎ ይስማታል
ጅብ ስጋ ላይበላ፤ምሎ ይገዘታል
ዕባብ ሰውን አይቶ፤አይተናኮልም
ነብር ጎሽ አይጥልም


#በኔ_ቤት

አንድ ብር ላይ ያለው
ትንሹ እረኛ መሳቁን ያቆማል
የሰፌዱም ስፌት፤ሳንቲም ላይ ይሆናል
ወተት የጠጣ ህፃን፤ሰክሮ ተንገዳግዶ
የአስር ዓመት ልጅ፥አስር ልጆች ወልዶ
የሰፈር አዛውንት፥ሰፈር ይቦርቃል
ሩቅ ያለው ቀርቦ፥ቅርብ ያለው ይርቃል


አሁንም…
ከጣልሺኝ ቦታ ላይ፤ብቻዬን ቁጭ ብዬ
ታምራዊ ስዕል፤በአይምሮዬ ስዬ
ሀሳቤን ጥጃለሁ፥ማይበስል ማይመስል
ዳግም በህይወቴ፥አገኝሽ ይመስል

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
👍3
#የመልስ_ጉዞ_ወደመነሻ_ጉዞ
:
#ክፍል_አስራ_አንድ
:
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...18 ዓመት ወጣትና የ12 ክፍል ተማሪ ሆኜ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችለኝን ማትሪክ ፈተና ዝግጅት ላይ እያለው አስቀያሚ ነገር ተከሰተ፡፡አስቀያሚ ስላችሁ የመጨረሻ አስቀያሚ ማለቴ ነው፡፡ትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ በማማር ላይ ሳለው በስልኬ መልዕክት መጣ ፡፡ሳየው ከአያቴ ነው፡፡ያልተለመደ ነገር ነው፡፡የሚያስተምረውን አስተማሪ ትኩረት እንዳልስብ እየተጠነቀኩ ከፈትኩና አነብኩት….ደብተሬን እንኳን አልሰበሰብኩም፡፡ ተስፈንጥሬ ከመቀመጫዬ ተነሳው ፡፡ የክፍሉ ተማሪ አይን ከአስተማሪው ተነቅሎ ወደእኔ አነጣጠረ..አስተማሪው ማስተማሩን አቋርጦ ምን እንደሆንኩ መጠቅ ጀመረ …እየተንደረደርኩ ክፍሉን ለቅቄ ወጣው፡፡ሳይክል ሚጠቀሙ ተማሪዎች ሳይክላቸውን ወደሚያቆሙበት ስፋራ ነው የሮጥኩት፡፡ከመካከሉ ቁልፉ ያልተቆለፈውን አዋጣውና እየጋለብኩ ግቢወን ለቅቄ ወጣው፡፡ ሳይክሉ የማን እንደሆነ አላውቅም ግድም አልነበረኝም..
ሆስፒታል እንደደረስኩ ሳይኩል ወረድኩና ከመንገድ ዳር አጋድሜ ወደውስጥ ሮጥኩ… ኮሪደር ለኮሪደር እየተሸከረከርኩ አያቴን ወይንም ሌላ የማውቀው ሰው መፈለግ ጀመርኩ...አዎ አያቴን አገኘውት
-እናቴ የታለች …?እናቴ ምን ሆነች…??እማ!!
ተረጋጋ…ምን እንደሆነች አናውቅም…ድንገት ነው እራሷን የሳተችው ፡፡እያከሟት ነው፡፡ይውጡና ሚሉትን እንሰማለን፡፡››አለኝ አያቴ በሚርበተበት ድምፅ..
‹‹እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡‹‹ቆይ አያቴ እንደዚህ አይነት ነገር እንዴት ይፈጠራል …?እናቴ ፍጽም ጤነኛ ነበረች፡፡እንኳን እራስ መሳት ይቅርና እራሷንም ሲያማት አይቼ አላውቅም ፡፡››
‹‹ለእኔም አንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ ልጄ››አየቴ መለሰልኝ
ንግግሬን ሳልጨርስ እናቴ ስትታከምበት ከነበረው ክፍል አንድ ዶክተር ወጣ… ተንደርድረን ከበብነው፡፡ዶክተሩ እኔንና አያቴን ወደቢሮ ይዞን ሄደ፡፡ ካዘነው በላይ የሚያሳዝን …ከደነገጥነው በላይ የሚያስደነግጥ መርዶ ነገረን፡፡
‹‹የሚቀጥሉትን ሶስት ቀን እዚህ ትቆይና …ከዛ ትወስዶታላችሁ››
‹‹ተመስገን›› አለ አያቴ …ረጅም ግን ደግሞ ደካማ ትንፋሽ ተንፍሶ፡፡
‹‹ዶ/ር በሶስት ቀን ይሻላታል ማለት ነው…?››ጠየቅኩት በመፍለቅለቅ ….ለማረጋገጥ፡፡
ዶክተሩ አንገቱን እንደመድፋት አለና የተወሰነ አየር ወደውስጡ ስቦ ጭንቀት በሚለቅ ድምጽ ‹‹አዝናለው ..ይሻላታል ብዬ ተስፋ ልሰጣችሁ ብችል ደስ ይለኝ ነበር…ግን እሷን የማዳኑ ጉዳይ ረፍዶብናል››
‹‹ማለት …?››
እቤት ወስዳችሁ ያላትን ቀሪ አንድ ወርም ሆነ ሁለት ወር በደስታ አሳልፋ …በሰላም እንድታርፍ ከማድረግ ውጭ ሌላ ምርጫ የላችሁም፡፡››አለ የመለማመጥ ቃና ባለው ድምፀት፡፡
ከመቀመጫዬ ተንሳፍፌ ተነሳውና የሸሚዝኑን የጋወኑን ኮሌታ አንድ ላይ ጨምድጄ ከተቀመጠበት አንጠልጥዬ አስነሳውትና በአየር ላይ አንሳፍኩት…ሰውዬው አይኑ ተጉረጠረጠ..እጆቹን እንድለቀው ማወራጨቱን ቀጠለ
አያቴም ከድንዛዜው እንደምንም ባኖ ይለምነኝ ጀመር
‹‹ልጄ ምን እየሰራህ ነው..…?ሰውዬውን ልቀቀው..…?ልጄ የሰው ሰው እንዳትገል፡፡››
‹‹እናቴን ታድናታለህ አታድናትም.…?››አርገፍግፌ መሬት አድርሼ ለቀቅኩት
ዶክተሩ ጉሮሮውን በእጆቹ እየዳበሰ ደጋግሞ ካሳለ ቡኃላ‹‹.አዝናለው አልችልም…ማንም ሊያድናት አይችልም….››ብሎ ስለበሽታዋ አይነትና ከባድነት የደረሰበትን ደረጃ በተቆራረጠ ቃላት ይዘረዝርልን ቀጠለ.
በእናቴ ስም እምላለው…ከሞተች አገድልሀለው..አንተን ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ እዚህ ግቢ ውስጥ ያላችሁትን ሀኪሞች ጨርሳችሆለው …ሆስፒታሉንም አቃጥለዋለው፡፡አረ ከተማወናም ነው የማቃጥለው…››በማለት ቢሮውን ጥዬ ወጣውና እናቴ ወደተኛችበት ክፍል ተንደረደርኩ ፡፡በራፍ ላይ የቆመችውን ነርስ ገፍቼ ፍቃዷንም ሳልጠይቅ ወደውስጥ ገባው፡፡እማዬ ዝርር ብላ ተሰትራ የሆስፒታሉ አልጋ ላይ ተኝታለች፡፡አይኖቾ ተከድነዋል፡፡ትንፋሿም አይሰማም ፡፡በሁለቱ አፍንጫጮ ቀዳዳ ቱቦ በክንዶቾ የግሉኮስ ላስቲክ ተሰክቶል፡፡
በራስጌዋ ሄድኩና ወለሉ ላይ ዝርፍጥ ብዬ ግንባሬን አልጋዋ ላይ ደፍቼ ወደ ፊቷ ተጠግቼ አስደገፍኩና በሹክሹክታ አወራት ጀመር….
ማሂ ምን እየሰራሽ ነው…?፡፡ምንድነው ዶክቱሩ የሚቀባጥረው…?፡፡ጥላህ ልትሄድ ነው እያለኝ ነው፡፡ስለማያውቅሽ ነው የሚቀባጥረው ፡፡አንቺ መቼም መቼም እኔን ጥለሽ መሄድ እንደማትችይ ስለማያውቅ ነው፡፡ገነትም ቢሆን እኔ ከሌለው መኖር እንደማትችይ ስለማውቅ ነው፡፡ማሂ ከተወለድኩበት ቀን አንስቶ ስትበይ እንብላ ብለሺኝ ስትተኚ እንተኛ ብለሺኝ ፤ስትተነፍሺ እንኳን የእኔንም መተንፈስ አረጋግጠሸ ነበር…ታዲያ ዶክተሮቹ እንደሚሊት አሁን ልትሞቺ ከሆነ እንዴት ልንሞት ነወ ተዘጋጅ ሳትይኝ .. …?ነገሩ ተይው እውነት ዶክተሩ አንዳለው ሸውደሺን ለመሞት የተዘጋጀሽ ከሆነም ግድ የለም እኔ ዝግጅት አያስፈልገኝም፡፡
ንግግሬን ከጀርባዬ ሆኖ ሲያዳምጥ የቆየው አያቴ በሽማግሌ አንጀቱ እየተንሰቀሰቀ በማልቀስ ዝቅ ብሎ አስነሳኝና
‹‹ተው ልጄ ተረጋጋ…አይዞህ እግዜር አለ ያድንልናል፡፡››
እንግዲህ እግዚያብሄር አለ የምትል ከሆነ በምትግባቡበት ቋንቋ ንገረው…ተው የሰው እናት አትንጠቅ በለው…እሷን አጥቶ መኖር አይችልም በለው…ከሰማህ ጥሩ ነው ፡፡ ካልሰማህ ደግሞ እኔንም ተሰናበተኝ ፡፡ እናም ከእናቴ ጋር በአንድ ጉድጓድ መቀበር ነው የምፈልገው..እንዳትረሳ በአንድ ጉድጓድ ፡፡ይህ ኑዛዜዬ ነው፡፡››ብዬው ጥዬው ወጣው ፡፡ወደየት እንደምሄድ ባላውቅም የሆስፒታሉን ቅጥር ጊቢ ለቅቄ ወጣው….

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍42
#ስንቴ_ገረዝኩት✂️
:
#ክፍል_አንድ
:
:
ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
“አንቺማ አትገርዢኝም። በስመአብ! ” አለ እያማተበ ለመቀመጥም ለመነሳትም በቀረበ አኳኋን አየሩ ላይ ተንጠልጥሎ።
“አየር ላይ ነህ፣ አረፍ ትል?” አልኩት አኳኋኑ ሳቄን እያመጣው
“የታለ ዶክተሩ ከምር? ” አለኝ ወንበሩ ላይ ተስተካክሎ እየተቀመጠ
“እኔ ነኝ!!” አልኩት ምን እንደሚያስብ ለመገመት እየሞከርኩ
ካርዱ ላይ የተፃፈው እድሜ 33 ይላል። ወጣት ነው፣ ማንም ሴት አይታው የምትደነግጥለት ዓይነት ቁመናና መልክ፤ በራሱ የሚተማመን የሚመስል ገፅታ ፤
“አንቺማ አትገርዢኝም። ይዤው አረጃታለሁ እንጂ………” አለኝ ለኔ ሳይሆን ለራሱ የሚያወራ በሚመስል ድምፅ
“ለምን? ሴት ስለሆንኩ?”
“አወና ፣ ሴት ብቻ አይደለሽም። ህልም የመሰልሽ ቆንጆ ሴት ነሽ። ሆ!!”
“እሱ ከስራዬ ጋር ምን አገናኘው?”
“ላንቺ ነዋ ስራ…………” ቀጥሎ ያልሰማሁትን ነገር አጉተመተመ
“ይቅርታ አቶ ሲሳይ ብዙ አገልግሎት ፈላጊዎች ውጪ ተሰልፈዋል። ስራችንን እንቀጥል?”
“እህ ስለተቆጣሽ ይሰማሽ መሰለሽ እንዴ?” አለ ወደሱሪው ዚፕ አይኑን እየላከ። መሳቅ አምሮኛል ግን መሳቅ የለብኝም።
“እንዴት ሳትገረዝ ……….?” ጥያቄዬን የምጨርስበት ቃል ስፈልግ
“አረጀህ? አይባልም ግን እሺ! ……….. ባክሽ አንጀት ነው ታሪኩ። ………… ተረት ነገር ነው የሚመስለው።”
“እየሰራሁ ታወራኛለሃ!!”
ብድግ ብሎ ገላውን አራቆተው።
“እንዴ እዚህ አይደለም የምሰራው።።።” አልኩት
“ቆይ ግን ትልቅ ወንድ ገርዘሽ ታውቂያለሽ?” አለኝ ምንም የተጋለጠ ሳይመስለው ተረጋግቶ ልብሱን ወደሰውነቱ እየመለሰ።
” አዎ። አውቃለሁ። ”
“እኔን የሚያህል?”
” ካንተም የሚበልጡ”
“ይሄን ነገር መቼም እንዲህ እንደቆመ አትገዘግዢውም አይደል?” እፍረት አይታይበትም። ስለቆመው አክሱም እንጂ ስለቆመው ንብረቱ ያወራ አይመስልም። በድጋሚ መሳቅ አምሮኛል። ፊቴን አዙሬ ፈገግታዬን ደበቅኩበት። ጭንቅላቴ ውስጥ ብቅ ያለው ሀሳብ ግን ቆሞ ነበር እንዴ? የሚለው ነበር። በየሱስ ስም!
“ማደንዘዣ እሰጥሃለሁ።”
“እህ! አይደለም ማደንዘዣ ፀሀይ የመሰልሽ ሴት ነክተሽው ሞቼ እንኳን ቢሆን አይቆምም?”
አሁን አለመሳቅ አልችልም ነበር። መጥሪያዬን ተጭኜ እጄን ከማንሳቴ ሲስተር ገባች።
“ኸረ ፍጥነት? በሩ ላይ ነበረች እንዴ? ” በማያገባው የሚገባ ሰው በቸልታ ማለፍ አልችልም እኮ ግን እንዳልሰማ ወደ ሲስተር ዞርኩ
”OR 2 ይዘጋጅልኝ። ማረፊያውን ታሳይሃለች እዛ ቆየኝ።” ካርዱን ለሲስተር አቀበልኳት። እሷ ያልኳትን ሰምታ ወጥታለች። እሱ እንደተቀመጠ በትዝብት ያየኛል።
“ምንድነው?”
“ይሄን ፊትሽን ግን ስሞትልሽ ፀብ ሲኖረኝ ሲኖረኝ እዋስሻለሁ። እንቢ እንዳትዪኝ! ኸረ በኪዳነምህረት!! “
“አቶ ሲሳይ የሚመለከተን ነገር ላይ ትኩረት እናድርግ?“
“you see እያናደድኩሽ እንኳን ፈገግ ብለሽ ነው የምትቆጪኝ። ምክንያቱም ደሞዝሽን የምከፍልሽ እኔ ነኛ! ባትመቺኝ ሌላ አማራጭ እንደምጠቀም ታውቂያለሽ። ስለዚህ ምን ያህል ስድ የሆነ costumer እንኳን ቢገጥምሽ በትህትና ታስተናግጃለሽ። ረዳቶችሽ ወደውሽ እንጂ ደመወዝ ስለምትከፍያቸው ፈርተውሽ እንዲታዘዙሽ አታድርጊ! እንደዛ ሲሆን አብረውሽ ያሉት ምርጫ እስካጡ ድረስ ብቻ ነው ማለት ነው።”
ልለው ያሰብኩት ብዙ ነበረ። ዋጋ ያለው ስላልመሰለኝ ተውኩትና እንዲወጣልኝ ብቻ በሩን አሳየሁት። ተነስቶ እየወጣ በሩን ተደግፎ ቆም አለና
«ያንቺን ስራ ደመወዝ ከፍለሽ እንደምታሰሪያቸው ሳይሆን እነርሱም የስራው አካል እንደሆኑ እንዲሰማቸው አድርጊ ያኔ ላንቺ ወይ ለደሞዝ ብለው ሳይሆን የራሳቸው ስራ መሆኑን ስለሚያስቡ ማንም ስራው እንዲበላሽበት አይፈልግም።»
«አቶ ሲሳይ ስድስት አመት ይሄን ሆስፒታል ቀጥ አድርጌ አስተዳርያለሁ። ሰራተኞቼን እንዴት መያዝ እንዳለብኝ አንተ አትነግረኝም!!» እንዴት ያለው ነው? እያናደደኝኮ ነው። ፈገግ ብሎ ከወጣ በኋላ መለስ ብሎ
«አይባልም ግን እሺ! ቤት ውስጥ የተቀጠረ ሰው እንኳን አሁን ቀርቷል ሰራተኛ አይባልም። ሆስተስ፣ አቀናባሪ ምናምን ነው የሚባለው። በሙያቸው የሚረዱሽን ሰዎች ሰራተኞቼ? ኸረ አይባልም!» ብሎኝ በሩን ዘጋው!! ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ ምን አይነቱን ነው ዛሬ ደግሞ የጣለብኝ?
★ ★ ★
በሶስት ቀናት ውስጥ የተኛሁባቸው ሰዓታት 7 መሙላታቸውን እንጃ። እቤቴ ሄጄ አላውቅም። ተረኛ ታካሚ እስኪገባ ስጠብቅ እያወራ ወደ ውስጥ ዘለቀ።
“ስንቴ ነው የምትገርዢኝ?”
“ማለት?”
“ቁስሉ ተቦትርፎልሻል። ጨርሺኝ ብዬ ነው አንቺውጋ የመጣሁት።”
“አልገባኝም። እስኪ እዛጋ ሁንልኝ። ምን ሆኖ ነው?” አልኩት
“እኔ አንቺን ማሰብ ማቆም አቃተኝ። እሱም አለመቆም አቃተው። ተነፋፋሁ ሲል ቁስሉ ጣጣጣ…………” የሚያሾፍ ይመስላል። ቁስሉ ግን እንዳለው ቆስሎ ነበር።
“ስነስርዓት ባለው መንገድ እንደአዋቂዎች እናውራ?” አልኩት።ማንም ደንበኛ በዚህ መጠን ነፃነት እንዳወራኝ አላስታውስም።
“እኔ የምለው ማሂ?” አለ ኮስተር እንዳለ
” ዶክተር ማህደር” መለስኩለት
“ኡፍ! ከክብርና ከፍቅር የቱ ይበልጥ ይመስልሻል?”
“ሁለቱም ዋጋ ያላቸው የማይነፃፀሩ ነገሮች ናቸው።”
” ዶክተር ብልሽ ያከበርኩሽ ሊመስል ይችላል። ማሂ ስልሽ ግን ውዴታዬን እየነገርኩሽ ነው። ከክብር ሁሌም ፍቅር ይበልጣል። በክብር ውስጥ ፍቅር ላይኖር ይችላል። በፍቅር ውስጥ ግን ሁሌም ክብር አለ” የሆነ ነገሬን ያወቀ ስለመሰለኝ ተናደድኩ። ለተናገረው ትኩረት የሰጠሁ ባለመምሰል
“ጨርሻለሁ። ተጨማሪ አንድ መድሀኒት አዝልሃለሁ። በትክክል መድሀኒቱን ከወሰድክ በድጋሚ እዚህ መመላለስ አያስፈልግህም።” አልኩት
” OK አልጋ ልትሰጪኝ ማለት ነው? እሱ ጥሩ ሀሳብ ነው። ”
“አቶ ሲሳይ ለጨዋታ ጊዜ የለኝም።”
” ሊኖርሽ ግን ይገባል ማሂ!። ” መልስ ሳይጠብቅ የፃፍኩለትን ወረቀት ተቀብሎኝ ወጣ።

⚫️ይቀጥላል⚫️

ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ Like 👍 እያደረጋቹህ ምርጦቼ😘

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍91
#ስንቴ_ገረዝኩት ✂️
:
#ክፍል_ሁለት
:
:
ደረሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
....“ዶክተር? ያው ሰውዬ ነው የላከልሽ………” ሲስተር ቀለም በፈገግታ በደመቀ ፊት ጠረጴዛዬ ላይ በፎይል የተጠቀለለውን ምሳ አስቀምጣው ወደ በሩ ተመለሰች
“ሲስተር ከዛሬ በኋላ የሚያመጣውን ምሳ እንዳትቀበሉት።” አልኳት
ለሁለተኛ ጊዜ ታክሞ ከሄደ ጀምሮ ሶስት ቀኑ ነው። የምሳ ሰዓት እየጠበቀ ምሳ ይልካል። ጠዋት ፅዳቶቹ አፅድተው ሲጨርሱ አበባ ይልካል።
“አበባውንም ነው ዶክተር?”
“አዎን። ምንም ነገር!!”
“እሺ!!” ብላኝ ወጣች
ሲስተር ለምንድነው የምትሽቆጠቆጥልኝ? ስለምታከብረኝ? ደሞዝዋን ስለምከፍላት? አለቃዋ ስለሆንኩ? እንጂ አትወደኝም…………… ትጠላኝም ይሆናል። ይሄ የተረገመ ሰው ምን እንዳስብ እያደረገኝ ነው?
★ ★ ★
ሆዴ ምግብ አስፈልጎታል። ሆስፒታሉ አቅራቢያ ያለ ሬስቶራንት እራቴን ለመብላት አዝዤ ተቀምጫለሁ። ከየት መጣ ሳልል ከፊቴ ያለውን ወንበር ስቦ ተቀመጠ።
“ማሂ……ዬ……… ?” አለ በተሟዘዘ አጠራር
“አንተ ሰው ለምን አትተወኝም?”
“አቶ ሲሳይ ታፈሰ። ማዕረግ ያለኝ ሰው ነኝ እሺ።”
“Whatever አቶ ሲሳይ ምን እያሰብክ እንደሆነ አልገባኝም። እኔና አንተ ግን ምንም መሆን የምንችል ሰዎች አይደለንም።”
“ምክንያት? በእድሜ ስለምትበልጪኝ?”
“አቤት? ”
“በ18 ዓመትሽ ዩንቨርስቲ ብትገቢ፣ 7 ዓመት ዶክተር ለመባል ብትማሪ……”
“ዶክተር ለመሆን ” አቋረጥኩት
“ስፔሻሊስት ለመባል የሆነ ዓመት… …… ይሄን ሆስፒታል ከከፈትሽ 6 ዓመት… …… በስሱ 37 የግልሽ ነው። ”
እንዲያውቅብኝ ባልፈልግም ተናድጃለሁ። ለምን ተናደድኩ? ትክክለኛ እድሜዬን ስለነገረኝ። እና ምን አናደደኝ? ምክንያት እንኳን የለኝም።
“ቁስልህ ዳነልህ?” ወሬውን መቀየር ነው ፍላጎቴ
“እየደረቀ ነው። ላሳይሽ?” ከመቀመጫው ብድግ አለ
“ኸረ አንተ ሰው?” ለመቀመጥም ለመነሳትም በቀረበ አኳኋን አየሩ ላይ ተንሳፈፍኩ
“አየር ላይ ነሽ! አረፍ ትዪ……” ብሎኝ ተመልሶ ተቀመጠ
ያዘዝኩት ምግብ መጣ። ተነስቶ እጁን ታጥቦ እስኪመጣ ጠብቂኝ ባይለኝም ጠበቅኩት። የጠቀለለውን ሊያጎርሰኝ ዘረጋ
“ጉርሻ አልወድም።” አልኩት
“እንዴ? በሞቴ? በፍቅራችን?” ሆነ ብሎ ሬስቶራንት ውስጥ ያለው ሰው እንዲሰማ ጮክ ብሎ ነው የሚናገረው። ሰዎች እየዞሩ ያዩናል። ግማሾቹም ፈገግ እንደማለት ይላሉ። ጎረስኩለት።
“ማሂዬ ለክብርሽ ይሄን ያህል አትጨነቂ። ……” አለ የተናገረው ተራ ነገር እንደሆነ ሁሉ ለሌላ ጉርሻ እየተሰናዳ። ተበሳጭቻለሁ። ይበልጥ ያበሳጨኝ ደግሞ ያለው እውነት መሆኑ ነው።
“ክብር አንጃ ግራንጃህን ተወኝ። ባለትዳር ነኝ ለባለቤቴ …………”
ሳቁ አቋረጠኝ። አስቂኝ ተረት እንደነገሩት ህፃን ተንፈቀፈቀ::
“ምን ያስቅሃል?”
“ባለቤትሽ ነዋ ያሳቀኝ ሃሃሃሃ ”
“ምን ለማለት ፈልገህ ነው?”
” እንዳንቺ አይነት ሴቶች ወይ አላገቡም፣ ወይ አግብተው ፈተዋል፣ ወይ ከባላቸው ጋር ሰላም አይደሉም።”
“እኔ ምን ዓይነት ሴት ነኝ?”
“ካልኳቸው ምድብ ውስጥ ከሌለሽ ልቀጣ? እ?” መልሴን ጠበቀ
መልስ አልነበረኝም። ተነስቼ ጥዬው መሄድ ነበር ፍላጎቴ እግሮቼን ማዘዝ አቃተኝ። ሽንፈቴን መቀበልም መሰለኝ። ልከራከረውም አቅሙ አልነበረኝም።
“እኔ ምን አይነት ሴት ነኝ? ” ድምፄ የቅድሙ ጥንካሬ የለው
“እውቀትና ደረጃዋን ድክመትና ሽንፈቷን ለመሸፈን የምትጠቀም ዓይነት ሴት”
ከዚህ በላይ መስማት የሚያሳምመኝ መሰለኝ። ተነስቼ ስወጣ ድምፁ ተከትሎኛል።
“አየሽ አንቺ ይህቺ ነሽ። ትፈረጥጫለሽ።”
እኔ ምን አይነት ሴት ነኝ? የትኛውን ሽንፈቴን ነው በደረጃዬ የሸፈንኩት?
★ ★ ★
ወትሮም ለእንቅልፍ እምብዛም የሆነው ዓይኔ ጭራሽ አልከደን አለ። እቤቴን ጠላሁት። ልብሴን ለመቀየር ካልሆነ በቀር አዳሬም ሆስፒታል ከሆነ ሰነባበትኩ። ምግቤንም የምመገበው እዛው እያስመጣሁ ሆነ። ከዛ ቀን በኋላ ሲሳይን አላገኘሁትም። ከዛ ቀን በኋላ ግን ስላወራናቸው ነገሮች አለማሰብ አቃተኝ። ሁኔታዬን ይብስ ያባባሰው ደግሞ ከቀናት በፊት የገጠመኝ ነገር ነው። ዶክተር ሰይፈ!!! በግምት የ12 አመት ልጅ የምትሆን ህፃን በዊልቸር እየገፋ ሲያልፍ ነበር ያየሁት። ደሜ ሰውነቴ ውስጥ ሲቀዘቅዝ ታውቆኝ ነበር።
«ሲስተር? ዶክተር ሰይፈ ልጅ አለው እንዴ? » ቢሮ እንደገባሁ ጠየቅኳት። ጥያቄዬ ይሁን ሰይፈ የትኛው መሆኑ ግራ ያጋባት አልገባኝም። « ዶክተር ሰይፈ የህፃናት……………»
«እኮ ገብቶኛል። መጠየቅሽ ገርሞኝ ነው። አዎን ሁለት ሴት ልጆች አሉት። አንዷ ልጁ የመኪና አደጋ ደርሶባት she is totally paralyzed እሱ ነው የሚንከባከባት። አይኗም የማየት አቅሙ እየተዳከመ ነው።» አነጋገሯ ውስጥ ያለው ድምፀት ያሳምማል። አንቺ ምን ግድ አለሽ አይነት ነው።
« ሚስቱስ?»
«ህምምም……. ሚስቱ እኮ ሞታለች ዶክተር!»
« ለምን አልነገራችሁኝም? እንዴት አንድ ሰው አይነግረኝም?» ፀፀቴን ማራገፊያ አጥቼ እንጂ እሷ ላይ የምጮህበት ምክንያትም መብትም የለኝም።
« ምን ብለን? ዶክተር አንቺ ልብ ስለማትዪ እንጂ እኮ ለህክምና እዚህ ትመላለሳለች።» ብላኝ በመገረም እያየችኝ ወጣች።
ኡፍፍፍፍፍፍፍ በየሱስ ስም ምንድነው የሰራሁት? ዶክተር ሰይፈ በሙያው ማንም እንከን የማያወጣለት ጎበዝ ነው። በተደጋጋሚ እያረፈደ እና እየቀረ ስላስቸገረ ቦርዱን ሰብስቤ ከስራው እንዲባረር ያደረግኩት ቀን ያሳየኝን ፊት ትርጉም የምረዳው አሁን ነው። ምክንያቱን እንኳን ሊነግረኝ የደከመው ነበር የሚመስለው። እሺ ብቻ ነበር ያለኝ። ከቦርድ አባላቱ አንዱ ምክንያቱን እንድሰማው ጠይቆኝ ነበር። «ተውት ምክንያቴን ለእናንተ እያስረዳሁ ህመሜን አላበዛም። ለእስከዛሬው ቆይታችን አመሰግናለሁ!» ያለው በሰአቱ ምን ያለ መስሎኝ ነው ከምንም ያልቆጠርኩት? እንዴት ግን አንዳቸው እንኳን ልጁን እያስታመመ ነው አይሉኝም? ይሄን ያህል ድንጋይ ልብ ያለኝ ነው የምመስላቸው? ይጠሉኛል ማለት ነው አይደል?
ማሰብ ይደክማል እንዴ? ማሰብ ደከመኝ:: ስልኬ መልዕክት መቀበሉን ነገረኝ። ከፈትኩት። የማላውቀው ቁጥር ነው።
“ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ አይነኬ የህይወት ክፍል አለው። ያን ሽሽት የሆነ ነገር ውስጥ ይደበቃል። ሌት ተቀን ህሙማንን ማገልገልሽ ለብዙዎች ታታሪነትሽን ይነግራቸዋል። ስራሽ መደበቂያሽ መሆኑን ግን አሳምረሽ ታውቂዋለሽ።”
ከሱ ውጪ ማንም አይሆንም። ቁጥሩን ደወልኩበት። ይሄ ደግሞ ሊያሳብደኝ ነው እንዴ ሀሳቡ?
“ምንድነው ከኔ የምትፈልገው? ምንድነው ግን ችግርህ?”
“ደህና እግዜአብሄር ይመስገን!! ምሳ እንኳን አይመቸኝም። እራት ቢሆንልኝ እመርጣለሁ።” አለኝ ዘና ብሎ።
ምን ልለው ነበር የደወልኩት? ቁጣዬን ምላሴ ላይ ምን ያልከሰክሰዋል?
“እራት ልጋብዝሽ?” አለኝ ዝምታዬን ተከትሎ። ምን እንደምመልስለት ግራ ገባኝ።
“ማሂ ፕሊስ?……… እኔ ደስ ብቻ ነው የሚለኝ። ዶክተር ማህደር እራት ተጋበዘችልኝ ብዬ ቀላል ሴት የሆንሽ አይመስለኝም።” የማስበውን እኔ ከስቤ ሳልጨርሰው ከሱ አፍ እሰማዋለሁ።
“የባለፈው ሬስቶራንት 12 ሰዓት ላይ ላግኝሽ! ውብ ቀን ዋዩ!!” ብሎኝ እንቢም እሺም ሳልለው ስልኩን ዘጋው።

⚫️ይቀጥላል⚫️

ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ Like👍👍 እያደረጋችሁ የኔ ምርጦች😘


ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍122
#የመልስ_ጉዞ_ወደመነሻ_
:
#ክፍል_አስራ_ሁለት
:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...ሶስተኛ ቀን ነው፡፡እንደነጋ እናቴን ይዤ ከሆስፒታል ወደቤት እሄዳለው፡፡ከዛ አስክትሞትበት ቀን ድረስ አብሬያት ስሮ ተኛለው፡፡ስትነቃ ነቃለው ስትተኛ አብሬት ተኛለው፡፡ምንያህል እንድምወዳት ያለማቆረጥ በየቀኑ ነግራታለው፡፡የሚያስደስቷትን ዘፈኖች ዘፍንላታለው፡፡የሚያዝናናትን ታሪክ አወራታለው፡፡የሚትወዳቸውን ምግቦች ሁሉ በገዛ እጆቼ እያበሰልኩ እመግባታለው፡፡ከዛ የመጨረሻው ቀን ደርሶ ስትሞት ደቂቃዎችን ሳላባክን እከተላታለው፡፡እራሴን ለማጥፋት የሚያስፈልገኝ መሳረያ …. እንዴት እንደምሞት እቅድ አውጥጬ ዝግጅቴን ሁሉ ጨርሼያለው፡፡በዚህ ለሊት ሆስፒታል የበሽተኛ አልጋ ላይ ዝርግትግት ብላ ከተኛችወ እናቴ ጎን ካላ ሌላ አልጋ ላይ ተቀምጬ ነው እቅዴን እየከለስኩ ያለውት፡፡ሳላገባድድ የክፍሉ በረፍ በዝግታ ተከፈተ፡፡
በዚህ ሰዓት ነጭ ጋወን የለበሰ ባለሞያ እናቴ ወዳለችበት ክፍል ምምጣት የተለመደ ነገር ነው፡፡አዲስ የሆነው የመጣችው ልጅ ነች ፡፡በጥቁር እና በቅላት መካከል ያለ የሰውነት ከለር ፤የተመዘዘ የሰውነት ቁመት ያላት ቀጭን የምትባል ሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለች ፡፡በዚህ ለሊት ይሄ ሁሉ ፈግታ ገረመቺኝ፡፡ባለፉት ቀናት ልምዴ ሁሉም ዶክተሮች ሆኑ ነርሶች ለሊት ሲመጡ ከቀን ሁኔታቸው ባለይ ኮስተር ብለው ነው የማያቸው..ምን አልባ እንቅልፍ እየፈተናቸው ስለሚሆን ነው የሚል የራሴን ግምት ወስጄያለው..ምንም ቢሆን ሰው አይደሉ…?
ይህቺ ግን …ደግሞ ካለዛሬ ኮ አይቼያት አላውቅም፡፡
<<ተኝታለች…?››
<<አዎ ›
<<ወንድሞ ነህ…?››
ወንድሞም፤ጓደኛዋም፤ልጆም ነኝ››
‹‹ገባኝ …ግን እኩያዋ ነህ …ተናሽና ታላቅ እህትና ወንድም ነው የምትመስሉት፡፡በዚህ እድሜዋ አንተን ማድረሶ ሚገርም ነው፡፡››አለቺኝ በፈግታዋ እንደተሞላች በእጆ የያዘችውን እናቴን የህክምና የክትትል ሪከርድ እየተመለከተች
‹‹ልጆ መሆኔን አመንሽ ማለት ነው.…?አልኳት ..እንዴት እርግጠኛ ልትሆን እንደቻለች ግር ብሎኝ
‹‹አዎ ..አንዳንድ ነገሮችን ትንሽ ትኩረት ካደረግኩ ሳይነገረኝም ማወቅ እችላለው፡፡››
‹‹እሺ አንቼ በራፍን ከፍተሸ ከመምጣትሽ በፊት ምን እያሰብኩ ነበር››ዝም ብዬ ለቀልድ ያህል ነበር የጠየቅኳት…?
በእጆ የያዘችውን ወረቀት እናቴ የተኛችበት አልጋ ጠርዝ ላይ አስቀመጠችና በዝግታ እርምጃ ወደእኔ ተጠጋች .፡፡እንደመደንገጥ አልኩ‹‹እጅህን ስጠኝ ››አለቺኝ…ያለጥያቄ ቀኝ እጄን ዘረጋውላት፡፡ በሁለት እጆቾ መካከል አስገብታ ጨበጠችውና በመንፈስ ተሞልቶ እንደሚፀልይ ፓስተር አይኖቾን ጨፈነችና ለተወሰኑ ሰከንዶች ከቆየች ቡኃላ የመወርወር ያህል እጄን ለቃ ወደኃላ አፈገፈገችና ያስቀመጠችውን ወረቀት አንስታ ያዘች
‹‹ምነው ከበደሽ…?››
‹‹እናትህም ባንተ ቦታ ብትሆን እንደዛው ነበር የምታደርገው›› አለቺኝ
‹‹አልገባኝም››
‹‹የታመምከው እና ትሞታለህ የተባልከው አንተ ብትሆን እናትህም እንደአንተው እራሷን ለማጥፋት ዝግጅት ታደርግ ነበር..››
ከተቀመጥኩበት በድንጋጤ ተነሳውና ቆምኩ..መልሼ ቁጭ አልኩ
‹‹እንደዛ እያሰብኩ እንደሆነ እንዴት አወቅሽ…?››
‹‹እርሳው …አለቺኝና የእናቴን ሙቀት መለካት ጀመረች
‹‹አይ አረሳውም…ስለእናቴ የተጠቀሰው በሽታ የእውነት እንዳሉት በአጭር ቀናት ….››ዓ/ነገሩን ልጨርሰው አልቻልኩም፡፡
በብጫቂ ወረቀት ላይ ‹‹አዎ…እናትህ 25 ቀን ብቻ ነው ያላት፡፡››ብላ ፅፋ አቀበለቺኝ
እንደእኔ ሁሉ እሷም በአንደበቶ መናገር ከብዶት ይሁን ወይም እናቴ በእንቅልፍ ልቧም ቢሆን ልትሰማ ትችል ይሆናል ብላ በማሰብ አልገባኝም
ወረቀቱን ከነብኩ ቡኃለ ጠቅልዬ አፌ ውስጥ ከትኩት እና አኝኬ ዋጥኩት…ከዛ ፀጥ አልኩ…ምንም ልላት አልቻልኩም ፡፡የምታደርገውን አድርጋ በል አይዞህ በርታ ብላኝ እንደአመጣጦ ወጥታ ሄደች፡፡
መብሰልሰሌ በእጥፍ ጨመረ ..ይህቺ ዶክተር ማን ነች……?የእውነት ነች ወይስ ከመንፈስ ጋ እያወራው ነበርኩ…?››፡ከተቀመጥኩበት ተነሳውና ክፍሉን ለቅቄ ወጣው፡፡
ተረኛዋን ዶክተር ማናገር እንደምፈልግ ስናገር ቢሮዋ እንዳለች ጠቆሙኝ፡፡ሄድኩና በስሱ አንኳኳው፡፡
‹‹ግባ›› የሚል ድምፅ ከውስጥ ስሰማ …ከፈትኩና ገባው፡፡ አቀርቅራ መፅሀፍ እያነበበች ነበር፡፡አዎ የእውነት ነች ማለት ነው…? ፡፡እየቃዠው አይደለም፡፡
‹‹ቁጭ በል ››
ቁጭ አልኩ
‹‹ሳይሽ ዛሬ የመጀመሪያ ቀኔ ነው፡፡››
‹‹አዲስ ነኝ ፡፡ዛሬ ነው ስራ የጀመርኩት፡፡ይህቺ ለሊት የመጀመሪያ ቀኔ ነች፡፡››ብላ አስገረመቺኝ
‹‹ታዲያ እንዴት በመጀመሪያ ቀን ስራሽ እናቴን 28 ቀን እንደቀራት መናገር ቻልሽ…?››
አንደኛ የህክምና ውጤቱ ሪከርድ ተደርጓል፡፡እዚህ ፊት ለፊቴ ያለው ኮምፒተር ውስጥም አለ፡፡ወደእናንተ ከመምጣቴ በፊት አንብቤዋለው፡፡
‹‹28 ቀን ይቀራታል ይላል…?››ፍርጥም ብዬ ጠየቅኩ፡፡
‹‹አይ ቀኑንማ አይናገርም፡፡እሱ የእኔ ትንበያ ነው፡፡በነገራችን ላይ አንድ ውለታ ልውልልህ እያሰብኩ ነው፡፡››
‹‹ምን አይነት ውለታ…እናቴን የምትድነበት ሆስፒታል ወይም ሀገር ልትጠቁሚኝ ነው…?››
‹‹ፍጽም…እናትህን የሚያድናት ዘመናዊ ህክምና የትም ብትሄድ አታገኝም››
‹‹ታዲያ ሌላ ውለታ ምን ያደርግልኛል…?፡፡አልኮት ለምቦጬን ጥዬ
‹‹አንድ ማውቀው የባህል ህክምና አለ ፡፡ፈጽሞ አያድናትም ግን ቢያንስ ዕድሜዋን በሶስት አመት ያራዝመዋል፡፡››
ከተቀመጥኩበት በድንጋጤ ተነሳው.. ተንደርድሬ እግሯ ላይ ተደፋው…‹‹በፈጠረሽ ..በምታምኚው ይዤሻለው እባክሽ እናቴን አትሪፊልኝ››
‹‹ላተርፋት አልችልም…ሶስት አመት ብቻ›
‹‹ይሁን …ሶስት አመት .››
‹‹ሶስት አመት እኮ ብዙ አይደለም…ሳታስበው ነው የሚደርሰው››
ግድ የለሽም ..አንቺ ብቻ እሱን አድርጊልኝ… እስከዛ የሚሆነውን ማን ያውቃል…?፡፡››
‹‹እሺ ሂድ ከግማሽ ሰዓት ቡኃላ እመጣለው፡፡››
‹‹እመጣለው ስትይ..››
‹‹መድሀኒቱን ይዤ እመጣለው››
አላመንኳትም ፡፡እንዴ ባለፉት ሶስት ቀናቶች እንቅልፍ ባለመተኛቴ አዕምሮዬን እየሳትኩ ይሆን እንዴ …?ይሄ ነገር የእስካሁኑ ሁሉ ህልም እንዳይሆን..…?፡፡ጎንበስ አልኩና የእጄን መዳፍ ጠረጵዛዋ ላይ ዘረግቼ እጆ ላይ ያለውን እስኪሪብቶ ተቀበልኩና በኃይል ወጋውት .የእስኪሪብቶው ጫፍ የተወሰነ ጥልቀት ወደ መዳፌ ውስጥ ሲገባ እግሬ ድረስ ነዘረኝ..
‹‹በህልም ውስጥ አይደለውም ማለት ነው›…?አልኩ
‹‹ይሄ ያደረከው እኮ ማረጋገጫ አይሆንም ፡፡ምክንያቱም በህልምህም ቢሆን ይሄንን የማረጋገጫ ሙከራ ልትሞክር ትችላለህ ፡፡››ብላኝ ከስጋቴ እንዳልወጣ አደረገቺኝ…ለማንኛውም እንዳለቺኝ ቢሮዋን ለቅቄ ወደእናቴ ተመለስኩና በናፍቆትና በጭንቀት እጠብቃት ጀመር።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍11
#ስንቴ_ገረዝኩት ✂️
:
#ክፍል_ሶስት
:
:
ደረሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
....እግሬና ሀሳቤ ሳይስማሙ እግሬ ቀድሞ ሬስቶራንቱ ውስጥ ተገኘ። ሲሳይ ቀድሞኝ ተገኝቷል። ልጨብጠው የዘረጋሁትን እጄን ሳብ አድርጎ አቀፈኝ። የምቀመጥበትን ወንበር ሳበልኝ። እራትና ወይን አዘዝን። ከእርሱ ጋር መጨቃጨቁ ትርፉ የሌላ ሰው ትኩረት ከመሳብ ያለፈ ስለማይሆን ዝም ብዬ የሚያደርገውን ከማየት ውጪ ተቃውሞም መስማማትም አልተነፈስኩም። አፉ ከማውራት እጁ ከማጉረስ ሳይቦዝን ነበር እራት ተመግበን የጨረስነው።
“እኔ ከዚህ በላይ አልጠጣም። ስራ መመለስ አለብኝ።” ያልኩትን የሰማ አይመስልም። ቀዳልኝ። በአትኩሮት ሲመለከተኝ ከቆየ በኋላ
“ሴክስ ካደረግሽ ስንት ጊዜሽ ነው? ወራት? አመታት?” አለ ቀለል አድርጎ
“አንተ? ያምሃል እንዴ? ” አልኩት ደንግጬ ይሁን አፍሬ ሳይገባኝ
“ምነው? አንቺ? ጭራሽ… ……ዜሮ ዞሮ ነሽ እንዴ?” በማብሸቅ ለዛ ነው ያወራው ። ደሞ አብሽቆኛልም።
“አንተ እኔን ለማንጓጠጥ የሚያስችለህ ቦታ ላይ እንዳለህ ነው የሚሰማህ?” ሳልጨርስ መንፈቅፈቁን ያዘው
” ማሂ ከእኔ ጋር ስታወሪ ጨዋ ቃል አትፈልጊ…… ሃሃሃሃ ‘ትናንት እጄ ላይ ሸለፈትህን ተገርዘህ፣ ልጅህን በማስገረዣ እድሜህ አንዠርግገኸው…ምናምን ……‘ በይው ”
“እንደሱ ለማለት እንኳን አልነበረም።” መለስኩለት
“በጨዋኛ ስለብድ ምን ታውቅና? እንደማለት አይደል?”
“በየሱስ ስም!» ከመደንገጤ የተነሳ ወንበሬ ላይ ዘልያለሁ። እሱ ምንም እንዳላለ ሁሉ በሁኔታዬ ይንፈቀፈቃል።
“ያልተገረዘ ሴክስ አያደርግም ያለሽ ማነው?” አባባሉ ቀዝቃዛ ስሜት ስለነበረው ስሜቱን የጎዳሁት ስለመሰለኝ ወንዶች ስለማይገረዙባቸው ሀገራት፣ ገጥመውኝ ስለሚያውቁ አጋጣሚዎች ነገርኩት።
“ኮንዶም የለ፣ ምን የለ… … ጫፉን ሸብ አድርጎ መሰማራት ነው። ተፈጥሯዊ ኮንዶም በይው ሃሃሃ” ብልግና ያወራ፣ በራሱ ያላገጠ አይመስልም። ደንግጬ ፈጥጬ አየዋለሁ።
“ኸረ ስቀልድሽ ነው አንቺ!!” አለ መሳቁን ሳያቆም።
በህይወቱ ውስጥ የሚያስከፋው፣ የሚያፍርበት፣ ሊያወራው የማይፈልገው ነገሩ ምን ይሆን? ብዬ አሰብኩ። ሲያወራ ፍፁም ጨዋ፣ ደግሞ ፍፁም ባለጌ፣ ደግሞ ፍፁም አዋቂ፣ ደግሞ ፍፁም ህፃን………ሁሉንም ይሆናል። ሲሳይን ማወቅ ከበደኝ። ያልተገረዘው ቤተሰባቸው ወንድ ልጅ እየሞተ ሲያስቸግራቸው የሄዱበት ጠንቋይ እንዳይገረዝ ስለነገራቸው መሆኑን እንደለመደው በራሱና በቤተሰቡ እየቀለደ ነገረኝ።
“እያደግኩ ከመጣሁ በኋላ መገረዙ አሳፈረኝ እና አረጀሁ።”
“በፍፁም አፍረህበት የምታውቅ ግን አትመስልም ነበር።”
“አንቺጋ ስመጣማ ከማፈር አልፎ አስጠልቶኝ ነበር።”
ሲያወራ በራስ መተማመኑ ለሰከንድ አይለየውም። ደጋግሞ ከሚያወራቸው ነገሮች በወላጆቹና በ6 እህቶቹ የተለየ ፍቅር ተሰጥቶት እንደኖረ ገባኝ። ከብዙ ሰው ጋር መግባባቱ፣ ብዙ ጓደኞች ማፍራቱ ምናልባትም ከተማረው የሳይኮሎጂ ትምህርቱጋ ግንኙነት ይኖረው ይሆናል ስል አሰብኩ።
“ጓደኞች የሉሽም? የሆነ አብረሻቸው አንዳንዴ ዘና የምትዪበት ምናምን?”
“የሉኝም!!”
“እሺ ሲደብርሽ፣ ሲከፋሽ፣ ደስ ሲልሽ ወይ የተለየ ነገር ሲገጥምሽ ለማን ታወሪያለሽ?” አለኝ አይኖቹ የሚያነቡኝ ስለሚመስሉኝ እሸሻቸዋለሁ
“ለራሴ አወራዋለሁ።” አልኩት አይኑን ሳይሰብር አየኝ። “አንተስ?” አልኩት
“ያ ስሜት በተሰማኝ ሰዓት አጠገቤ ላገኘሁት ሰው። ለምሳሌ በኋላ ሸኝቼሽ ስመለስ ለሆስፒታላችሁ ዘበኛ ደስ እንዳለኝ ልነግረው እችላለሁ።” ቀለል አድርጎ ነው የሚያወራው
“እየቀለድክ ነው?”
“የምሬን ነው። ምነው?”
“የምልህ ከእኩዮችህ፣ ቢያንስ ከቤተሰብህ……… ባንተ ደረጃ ካሉ ሰዎች ጋር……… ” አላስጨረሰኝም።
“ደረጃ ምንድነው? ደረጃ መዳቢውስ ማነው? እኔን ከኒኛ ዘበኛ ወይ ከዚህ አስተናጋጅ በላይ ወይ በታች ደረጃ የሰጠን ማን ነው? የኔ መማር እና ቢሮ መቀመጥ? የሳቸው የእኔን እድል አለማግኘትና ዘበኛ መሆን? ንገሪኝ እስኪ እሳቸው የሚያውቁትን ወይ የሚችሉትን ደረጃ ብለን ባወጣንላቸው ዘበኝነት እንዴት እንመዝነዋለን?” አይቼበት የማላውቅበትን የለበጣ ፈገግታ ፈገግ ብሎ ቀጠለ
“አፈር ምን ደረጃ አለው? ነፍስስ ብትሆን ያው ነፍስ አይደለች? በምትሰራው ስራ ካልዳኘናት በቀር? የሰው ደረጃው ‘ሰውነቱ‘ ነው።” አለኝ። ዝም አልኩት። ምንስ ልለው እችል ነበር?
“ቤተሰቦችሽ? የት ናቸው?” አለኝ ወዲያው ከዛኛው ስሜት ወጥቶ
“ቤተሰቦቼ………?…… ”
“ምነው? ሞተዋል? ተጣልታችኋል? ወይስ…… እንደ እህል ዘርተውሽ ነው የበቀቀልሽው?…” ተናድጄ አቋረጥኩት ቁስሌን እያወራ እንደሆነ አልገባውም።
“ምንም ስነስርዓት አታውቅም። ባለጌ ነህ እሺ!!” አልኩት
“እሺ!” አለኝ ቁጣዬን ከምንም ሳይቆጥረው እጄን እየዳበሰ።
“እሺ ግን ንገሪኝ። ማወቅ እፈልጋለሁ።
ምኑን ልንገረው? አባቴ ከእህቱ ልጅ እንደወለደኝ እና ወንድ አያቴ እንዳሳደጉኝ? አድጌ ራሴን እስከማውቅ አባትና እናቴን እንደማላውቅ? ቤተሰቡ ውስጥ እንደ አንዳች መዓት ሲፀየፉኝ እንደኖርኩ? አያቴ ሲሞት ያየሁትን አስቀያሚ የህይወት ገፅታ? የቱን ልንገረው? ለማንም ለማውራት የሚቀል አልነበረም። እንባዬ መጣ። እያየኝ ማልቀስ አልፈለግኩም። ፈርጣጭ ይበለኝ። ተነስቼ መውጣት እንደጀመርኩ እንባዬን ማስቆም አቃተኝ።
ሬስቶራንቱን መግቢያ እንዳለፍኩ እሮጦ ደረሰብኝ። አቀፈኝ። እንደህፃን ደረቱ ላይ አጥብቆ አቀፈኝ። አለቀስኩ። አላባበለኝም። ፀጉሬን እየደባበሰና እየሳመ ለቅሶዬን እስክተው ጠበቀኝ። ያስለቀሰኝ ምን እንደነበረም አልጠየቀኝም። እንደተለመደው እያሳቀኝ የሆስፒታሉ መግቢያ ድረስ ሸኘኝ። ሲሰናበተኝ መልሶ አቀፈኝ። እቅፉ ውስጥ ብዙ መኖር ፈለግኩ። ከሆነ ነገር የሸሸገኝ መሰለኝ። ሰላም ያለበት ዓይነት። እሱም የገባው ይመስል አቅፎኝ ለደቂቃዎች ቆየ። ግንባሬን ሳመኝ።
“ዶክተር ሰላም አይደለሽም እንዴ?” ሲስተር ቀለም መግባቷንም አላስተዋልኩም።
“ሰላም ነው ሲስተር”
“ዶክተር ታዴ እየፈለገሽ ነው ኢመርጀንሲ ነው። ስልሽ እኮ አልሰማሽኝም።” እያወራችኝ የሻከረ መዳፏን ታፍተለትላለች።
እስከዛሬ እጇን አይቼው አላውቅም። ከድምፅዋ በቀር ምኗንም አስተውዬ አላውቅም። ለምንድ ነበር አውርቻት የማላውቀው? ለምንድነው ግንባሬን እንደቋጠርኩ ገብቼ የምወጣው? እንዲያከብሩኝ? ሲሳይ እንዳለኝ በራሴ ስለማልተማመን? ወይስ ደረጃዬን ስጠብቅ?
“ሲስተር ቤተሰብ አለሽ እንዴ?” አልኳት ለመሄድ እየተሰናዳሁ
“አዎን ባለትዳር ነኝ። አንድ ልጅም አለኝ። ምነው? ምን አጠፋሁ?”
ጉልበቴ ከዳኝ። ዞሬ አየኋት። በደቂቃ ብዙ ነገር አሰብኩ። ትፈራኛለች ምክኒያቱም ስራዋን ማጣት አትፈልግም። ከስራ ውጪ ስለምንም ነገር አውርቻት አላውቅም።ደሜ ቀዘቀዘ። እንዴት አይነት ጭራቅ አድርገው ነው የሚያስቡኝ?
“እንዲሁ ማወቅ ፈልጌ ነው።ለምን ትፈሪኛለሽ? አንቺ በጣም ታታሪ ሰራተኛ ነሽ እኮ!!” ትከሻዋን ዳበስ አድርጌ ወጣሁ።
★ ★ ★
ፈገግ እያልኩ መሆኔ ለራሴ ይታወቀኛል። ታካሚዎቼን እየፈገግኩ እንደማዋራቸው ገብቶኛል እያፏጨሁም መሰለኝ።ሰሞኑን በተደጋጋሚ ከሲሳይ ጋር እራቴን መብላቴን ተከትሎ እንደዚያ እየሆንኩ ነው ዶክተር ሰይፈን ይቅርታ መጠየቄ የሆነ ጭነት ከላዬ ላይ እንደማራገፍ ነበር ወደ ስራ እንዲመለስ የሚያስፈልገውን ሁሉ እንደማደርግ ስነግረው ግን
«ይቅርብኝ» ካለው ቃል በላይ ከቃሉ ጋር ከንፈሩን ነክሶ የፈገገው ፈገግታ ራሴን ደጋግሜ እንድረግም አድርጎኛል
ሲስተር ቀለም በተረኛ ታካሚ ፈንታ ገባች
“ዶክተር ሰው ይፈልግሻል?”
“ሲሳይ ነው? ትንሽ ታገሰኝ በይውና ተረኛ ታካሚ
👍6😁1
አስገቢልኝ።” “ዶክተር ……… ባለቤትሽ ነው።”

⚫️ይቀጥላል⚫️

ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ Like👍👍 እያደረጋችሁ የኔ ምርጦች😘


ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#ፍቅር_ማለት_ውዴ

የህልሙ ዘራችን የዕውን ፍሬ አፍርቶ
ቆንጅየ ልጅ ወልደን እሱም፤
ፍቅር ሊማር አንደበት አውጥቶ ፤
ፍቅር ማለት..እማ? ብሎ ቢጠይቅሽ ፤
ይህንን ንገሪው ሳትፈሪ ሳይጨንቅሽ ፤

#ፍቅር_ማለት_ልጄ

የተራ ሆሄያት ባዶ ጥርቃሚ ፤
የሶስት ፊደል ጥምረት
የቀል ልቅምቃሚ ፤የደቂቃ ስሜት
ወይ ጊዜያዊ ጥቅም አይደለም ምስጢሩ፤
#መስጠት
#መስጠት
#መሰጠት .....በቃ ሁሌም #መስጠት
እናም ልጄ ይህ ነው የፍቅር ቀመሩ ፤
ብለሽ ንገሪልኝ እንዲገባው አርገሽ ፤
ፍቅርን ሠጥቶ፤ምላሽ እንዳይጠብቅ
በደንብ አስጠንቅቀሽ ፤
.......ደግሞም እንዲህ በይው.........

#ፍቅር_ማለት_ልጄ

በአንዲት ውብ ማሳ ውስጥ..
ከአረም ከቁጥቋጦ ፈፅሞ በራቀች ፤
ከአንድ ገበሬ እጅ..
በፅናት ተዘርታ በዕምነት የበቀለች ፤
........... .............ፍቅር ቡቃያ ነች ፤
የአለምን ሃይሎች አጣምሮ ያደላት ፤
የተንኮል ገሞራ .....
የሃሜት አውሎ ንፋስ ገፍትሮ ማይጥላት ፤
ገንዘብ ጎርፍ ሆኖ.....
ስሯን ቢያጥለቀልቅ ፈፅሞ ማይነቅላት ፤
#ፍቅር ቡቃያ ናት..........."
......ብለሽ ንገሪልኝ....
ግን ይህን ሁሉ ቃል ከአንደበትሽ ሰምቶ ፤
....ፍቅር ማለት እማ ????
ብሎ ከጠየቀሽ ሳይረዳው ቀርቶ ፤
....ይህንን ንገሪው
"ገበሬው አምላክ ነው ማሳዋ ልባችን ፤
ዘሩ የፍቅር ቃል ቡቃያው ልጃችን ፤
እንዲያውም እንዲያውም....
ከተራ ቃላት ጋር ምን አፈታተነን ፤
ፍቅር ማለት ውዴ!!!!
በቃ እኔና አንች ነን 💝
#የመልስ_ጉዞ_ወደመነሻ
:
#ክፍል_አስራ_ሶስት
:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...ዶክተሯ ቃሏን ጠብቃ ከሀያ ደቂቃ ቡሃላ በአነስታኛ ብልቃጥ ሀመራዊ አይነት ዝልግልግ ፈሳሽ ይዛ በምጣት ያለምንም ንግግር መድሀኒቱን ከብልቃጥ ውስጥ በስሪንጅ በምጠጥ ከእናቴ ደምስር ጋር ከቴያያዘው የጉልኮስ የፕላስቲክ ከረጢት ውስጥ ጨመረችውና …እንዳአመጣጦ ምንም ሳትናገር ወጥታ ሄደች፡፡
እኔም ደንዝዤ ስለነበረ የምታርገውን በፅሞና ከመታዘብ በዘለለ አንደበቴን አላቅቄ ቃላት ማውጣት አልቻልኩም..ምን እየተፈጠረ ነው..?እውነት እንዳለችው ይህ መድሀኒት እናቴን ይፈውሳት ይሆን…..?ነው ወይስ እያሾፈችብኝ ይሆን…..?እንደዛማ ከሆነ በህይወቷ ወስናለች ማለት ነው፡፡እዛው የቢሮዋ ወንበር ላይ እንደተቀመጠች በእነዚህ መዳፎቼ አንገቷን ፈጥርቄ ፀጥ ነው የማደርጋት ፡፡….በውስጤ ዛትኩ
በተጋደምኩበት ይሄንን እና የመሳሰሉትን ግትልትል ሀሳቦች እያሰብኩ ሳይታወቀኝ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ ብሎ ነበር ለካ ፡፡አይፈረድብኝም የሶስት ሙሉ ቀን እንቅልፍ ነው ያለብኝ፡፡
‹‹…ፀጋ …የእኔ ልጅ››የሚለው ከገነት ከመላዕክት አንደበት የሚፈስ የሚመስል ጡዑም ዜማ ያለው የእናቴ የጥሪ ድምጽ ነበር ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ… ደንግጬ ከተጋደምኩበት የሆስፒታል አልጋ በርግጌ በመውረድ ወለሉ ላይ እናቴ ፊት ለፊት ተገተርኩ
‹‹..አረ ተረጋጋ የእኔ ጌታ..››ጥርት ያለ ንፅህ የእናቴ ድምፅ..
ማመን አልቻልኩም፡፡በስነስርአት ትራስ እንኳን መንተራስ ሳያስፈልጋ ቁጭ ብላለች፡፡ምንም በበሽታ የመድከም ምልክት በፊቷ አይታይም፡፡
‹‹እማ ደህና ነሽ…..?ተሸለሽ…..?አሁን ምን ይሰማሻል..?››በጥያቄ አጣደፍኳት
‹‹ይሄው እንደምታየው በጣም ደህና እና ፍፅም ጤነኛ ሆኜ ነው የተነሳሁት፡፡ይገርምሀል ለሊ,ት ተኝቼ ጠይም መላዕክ መጥታ ከጭንቅላቴ አንስታ መላ አካላቴን ስትዳብሰኝ ነበር…እግዜያብሄር ያአንተ ፀሎት ሰምቶ ምሮኛል መሰለኝ፡፡››አለቺኝ በተፍለቀለቀ የደስታ ድምፀት
ተንጠራራውና አቀፍኳት ፡፡ግንባሯን …ጉንጮን …አፍንጫዋን እያፈራረቅኩ ሳምኳት ‹‹…አዎ እማ ድነሻል…እግዜያብሄር ይመስገን ተሳክቶልናል…ልጅቷ እንዳለችው ማድረግ ችላለች…ምትገርም ሴት ነች፡››
‹‹ስለማን ነው የምታወራው..?›› አለችኝ መቀባዠሬ ስላልገባት
‹‹አይ በህልሜ አየዋት ስላልሽው መላዕክ ነው ማወራው….ስላዳነችሽ መላአክ››አልኩና ርዕሱን አስቀየርኳት
‹‹አዎ እግዜር ነው የላከልኝ..ሄድ አሁን ሀኪም ጥራልኝ››
‹‹ምነው .. ..?የሚያምሽ ቦታ አለ እንዴ..?›› በድንጋጤ ጠየቅኳት
‹‹አረ በፍጽም… ይሄን ግሉኮስ ከላዬ እንዲነቅሉልኝ ነው…ሽንት ቤት መሄድ ፈልጋለው ›› ስትለኝ..ሮጬ ወጣውና በ10 ደቂቃ ውስጥ ተረኛውን ዶክተር አስከትዬ መጣው፡፡ይሄ ዶክተር እናቴ ሆስፒታል ከገባች ቀን ጀምሮ በዋናነት ስለጤናዋ ይከታተላት የነበረው ስለነበር እንዳያት ደነገጠ..በጣምም ግራ ተጋባ..ከግምቱ ውጭ የሆነ ሁኔታ ላይ ሆና ነው ያገኛት .
‹‹ማህሌት ምን ይሰማሻል. .?››
‹‹ፍጽም ጤነኝነት››
በጣም ጥሩ ..አሁን ወደቤት ከመሄድሽ በፊት ሙሉ ምርመራ ማድረግ አለብን ..››አለና ጉሉኮሱን ከእጇ ላይ በማለያየት ወጥቶ ሄደ …እኔም እሱ ለምርመራ ሚገለገልባቸውን መሳሪያዎች ይዞ እስኪመጣ ድረስ ስልኬን አወጣውና ለአያቴ ደወልኩለት…
‹‹ሄሎ አባ የት ነህ.?››
‹‹የት እሆናለው ልጄ… ቤተክርስቲያን ነኝ…ምነው ልጄ ባሰባት እንዴ .?›› ስብርብር ባለ ተስፋ የቆረጠ ደካማ ድምፅ ጠየቀኝ
‹‹አረ አባ ፍፅም ደህና ነች…ፀሎትህን ከጨረስክ ቀጥታ ወደሀስፒታል ና ››
‹‹አሟታል ማለት ነው ..መች አጣውት …እግዜያብሄር ዘንድሮ ሊያዋርደኝ ነው››አምላኩ ፊት መቆሙን እንኳን ዘንግቶ ተነጫነጨ
‹‹እወነቴን ነው አባ …ቆይ እንደውም…›› ብዬ ስልኩን ከጆሮዬ ላይ አነሳውና ለእናቴ አቀበልኳት ..የጠራ እና የነቃ ድምፆን በስልክ ከሰማ ቡሃላ በደስታ ሰክሮ እልልታውን ሲያቀልጠው በስልኩ ውስጥ ተሰማኝ…በዚህ እድሜው ልጁ ስትሞት አይቶ ባለመሳቀቁ ውስጤን ሀሴት ተሰማው …ቢያንስ ለጊዜው ይደሰት ..
እስከአራት ሰዓት መደረግ ያለበት ምርመራ ሁሉ ተደርጎላት ተጠናቀቀ..ውጤቱም ዶክተሮቹን በጣም ያስደመመ እና የበፊቱን የምርመራ ውጤት እንዲጠራጠሩ ያደረገ ነበር…እኔም ስለሆነው ነገር በውስጤ አፍኜ አብሬያቸው ከማደነቅ ውጭ ምንም ነገር ትንፍሽ ማለት አልቻልኩም…አልፈለኩምም፡፡
አዲሱ የህክምና ውጤት እንደሚያሳየው የእናቴ በሽታ ሙሉ በሙሉ የጠፋ ባይንም ደረጃው ግን 50 ፐርሰንት ወደኃላ የተመልሰል ነበር…ይህ ማለት ደግሞ ዋናው ሀኪምም እንዳረጋገጠልኝ በቅርብ ጊዜ ትሞታለች የሚለው ስጋት በአስተመማኝ ሁኔታ እንደተወገደ ነው፡፡
እንዴት እንደሆነ ባይገባኝም በእናቴ ላይ ተአምር ተፈፅሟል …ሙሴ የእስራኤልን ባህር በበትሩ ከፍሎ ወገኖቹን ያሻገራቸውን አይነተ ተአምር….አስራሁለት አመት ደም ሲፈሳት የነበረች ሴት የክርስቶስን የልብስ ጫፍ በእምነት ዳብሳ ከህመሞ ፈውስ ያገኘችበትን አይነት ተአምር ፡፡እርግጥ ታአምሩ ጅምር ነው…ምን አልባት በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ሙሉ በሙሉ ልትፈወስና እኛንም ይበልጥ ልታስደምመን ትችል ይሆናል፡፡
በሰተመጨረሻ ለመሄድ ዝግጅታችንን እንዳጠናቀቅን ወደዋናው ዶክተር ቀረብኩና ‹‹አመሰግናለው ዶክተር..ሁላችሁንም እግዜር ይስጥልኝ አልኩ››
‹‹ኦኬ ..ያ ማለት ለህይወታችን መስጋት አይጠበቅብንም ማለት ነው..?››
‹‹ማለት . ..?አልገባኘም ..?››
‹‹እንደምትገለን በርግጠኘነት ዝተህብን ነበር…አሁን እናትህ በከፊልም ቢሆን በመዳኗ ለጊዜው የተረፍን ይመስለኛል››አለኝ ፈገግ እያለ
አንገቴን አቀረቀርኩ‹‹በጣም አዝናለው…እናቴ ለእኔ መላ ነገሬ ስለነበረች አብዝቼው ነበር…ያን ያህል ስለታገሳችሁኝ ውለታችሁን መቼም አረሳውም..››
‹‹አረ ስቀልድህ ነው..እኔም ሆንኩ ባለደረቦቼ በወቅቱ የነበርክበትን ሁኔታ በደንብ ስለተረዳን ምንም አይነት ቅሬታ እልተሰማንም …ነገሩን ያነሳውልህ እንዲሁ ልቀልድ ብዬ ነው ›አለኝ
እናቴን በጓደኛቼ በዘመድና በጎረቤት ሰዎች አሳጅቤ እባቴ ስንደርስ አምስት ሰዓት ሆኖ ነበር… እናቴን ወደጆሮዋ ተጠግቼ የምሄድበት ቦታ እንዳለና ልቆይ እንደምችል ነግሬት ከአጀብ ውስጥ ወጥቼ ወደሆስፒታል ተመለስኩ …ከተቻለ ዶክተሯን ለማግኘት ፤ ከለበላዛ እንዴት እዳማገኛትና ከዛም አልፎ ስለማንነቷ መረጃዎችን ከገኘው ለማጣራት…
ምክንያቱም ስለእሷ በአዕምሮዬ ውስጥ የሚጉላሉ ጥያቄዎች ከቁጥጥር ውጭ እያደረጉኝ እና መንፈሴን ክፉኛ እየረበሹት ነው.
1/ይቺ ዶክተር ማነች....?የትኛው ከተማ ወይም የትኛው ገጠር ተወልዳ የትኛው ዩኒቨርሲቲ ገብታ ተምራ እዴት እዚህ ተማድባ መጣች..?
2/እንዲህ አይነት ከሳይንስ አቅም በላይ የሆነ ህምምን ለመፈወስ የሚያስችል የባህል ህክምና ጥበብን በዚህ ዕድሜዋ እንዴት ልትካንበት ቻለች;..?››
3/በምን አይነት ተአምራዊ አጋጣሚ ሄስፒታሉ ለመስራት በተመደበች በመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያዋ ታካሚዋ እናቴ ልትሆን ቻለች..?
2/ከእኔ እፈልገዋለው ያለችው በውለታዋ ምላሽ እንድከፍል የሚጠበቅብኝ ምንድነው....?ብር እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ ፡፡አንገቷ ላይ ያጠለቀችው እባብ የመሰለ ጥምዝ ወርቅ እና ጆሮዋ ላይ ያንጠለጠለችው የከበረ ጌጥ የኑሮ ደረጃዋን ያሳብቅባታል፡፡የባህል መድሀኒት በሆስፒታል ቅጥር ግቢ በድብቅ እየቸረቸረች ገንዘብ የምትሰበስብ አይነት ሰው አይደለችም..አዎ በዛ እርግጠኛ ነኝ ፡፡ግን ምንም እንዳደርግላት ብትጠይቀኝ ግድ የለኝም…እራስህን አጥፋልኝ ብትለኝም አደርገዋለው…
👍5
ለእናቴ አንድ ተጨማሪ ቀን ለማግኘት የእኔን አንድ ሙሉ አመት ሰዋለው …
ቢሆነው እነዚህ እና ሌሎች ጥያቄዎቼን በቅደም ተከተል መልስ ሊያገኙ የሚችሉት በከፊል የሚያውቋት ሰዎች ሳገኝና ሳናግር ሙሉ በሙሉ ደግሞ በቀጥታ ከአሷ ተገናኝቼ ሳወራት ነው፡፡
እንዴት ግን ትናንትናውኑ ስልኳን ሳልጠይቅና ሳልቀበላት… .? ዳሩ በዛ ውድቅት ለሊት በሚሆኑት አስደማሚ ክስቶች ሁሉ እንደዛ ደንዝዤ ስልክ መቀበል እንዳለበኝ ብዘነጋ ብዙም የሚገርም አይደለም፡፡
.ሆስፒታል ስድስት ሰዓት ከመሆኑ በፊት ብደርስም ስለ አዲሷ ዶክተር እንደተመደበች ከማወቅ በዘለለ አብዛኞቹ ምን እንደምትመስል እኳን እስካአሁን በአካል አላዮትም …አስተዳደር ክፍል ገባውና ስልኳን እንዲሰጡኝ በግግምና ጠየቅኳቸው፡፡የግለሰብ የግል ስልክ ካለፍቃዱ ለማንም መስጠት እንደማይችሉ ነገሩኝ፡በስተመጨረሻ በመከራ ለምኜ በቢሮ ስልክ ደውለው ቀጥታ እንዲያገኛኙኝ አሳመንኮቸው… ደወሉላት፡፡
‹‹ሄሎ ዶክተር››
‹‹ሄሎ ጤና ይስጥልኝ…ማን ልበል፡፡››ጥርት ያለ ግን ደግሞ ያዛዥነት ተፅዕኖ ያለው ከባድ የሴት ድምፅ ከዛኛው ጫፍ ተሰማ…
‹‹አታውቂኝም ማለቴ….››ቃላትን በቀላሉ ሰካክቼ ከአንደበቴ በማውጣት ሀሰቤን መግለፅ አቃተኝ
‹‹ማለትህ የማታው ልጅ ነኝ…እናቴን አክመሽ ስላዳንሺልኝ ላመሰግንሽ ነው..፡፡ልትለኝ አይደል .?››
ለማለት ፈልጌ ማለት ያቃተኝን ቀጥታ ከአንደበቷ ስሰማ ቃላቶቼ ሁሉ አንደበቴ ውስጥ እየሞሙ ሲበተኑ ታወቀኝ
‹‹አዎ..ት..ክ..ክ.ል››
‹‹ተቀብያለው…››
‹‹እና ላገኝሽና በአካል ላመሰግንሽ ፈልጋለው፡፡››
‹‹ልታገኘኝ ባትፈልግም የግድ አገኘሀለው ….የማይሻር ውል አለን አይደል .?፡፡››
‹‹አዎ አረሳውትም››
‹‹ጎበዝ ልጅ …መርሳትም የለብህም …ለማንኛውም ስልክ ቁጥሬን ያዝ 09 13 303030 ነው…ደውልልኝ፡፡››
‹‹እሺ አመሰግናለው…እደውልልሻለው››ቅልስልስ ባለ ድምፅ
‹‹ቸው››ስልኩ ተጠረቀመ
እኔም የስልኩን እጃታ ቦታው መልሼ የተባበሩኝን ሰዎች በደመነፍሰ አመስግኜ እግሬን እየጎትትኩ የቢሮውንም የሆስፒታሉንም ቅጥር ግቢ ለቅቄ ወጣው፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍31
#ስንቴ_ገረዝኩት ✂️
:
#ክፍል_አራት (የመጨረሻ ክፍል)
:
:
ደረሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
....“ባለቤትሽ? ኢሳያስ?…………”
“ቢሮዬ ድረስ እየመጣህ ለምን ትረብሸኛለህ ኢሳ?”
“ናፈቅሽኝ!! ከዚህ በላይ ሳላይሽ መቆየት አልችልም።”
ከዩንቨርስቲ ጀምሮ የማውቀው ሰው ነው ኢሳያስ ። ለ6 ዓመት አብሮኝ የቆየ የትዳር አጋሬም ነው። አብረን በኖርንባቸው ጊዜያት መጀመሪያዎቹ አመታት በፍቅር ያጌጡ ነበሩ። እየሰነባበተ ግን ሳንጨቃጨቅ ያለፉ ቀናት ውስን ሆኑ። የሁለት ዓመት ልጃችን በሞት ስትለየን ሰላማችን ይብስ ደፈረሰ። ልጃችን የሞተችው በምግብ መመረዝ ነው። ታማ ስትሰቃይ ሁለታችንም ልንደርስላት አልቻልንም ነበር። ሰራተኛዋ ስትደውልልኝ ስራ ላይ ነበርኩ። ስልኬን እየሰማሁት ቆይቼ ለመደወል አስቤ ተውኩት። ግን ቆይቼም አልደወልኩም። ሌላ ስራ ያዝኩ። እናም ልጄን ሳልደርስላት ሞተች። እሱም በተመሳሳይ ምክንያት ስልክ ሳይመልስ ቀረ። ቆይቼ ስደርስ ዘግይቼ ነበር። ለዚህ በደሌ አንድ ሚሊየን ጊዜ ራሴን ብቀጣውም በቂ አይሆንም። ከኢሳያስ ጋር መወቃቀሱ አቁሳይ ስለነበር በሆነው ባልሆነው ሰበብ እየፈለጉ መነታረክ ሆነ ምሽታችን። ቤቱን ለቆ ከወጣ ሶስት ወር አለፈው።
“ቁጭ ብለን እንድናወራ እፈልጋለሁ።” አለኝ አይን አይኔን በልመና እያየ።
ምንድነው ልለው የነበረው? ‘ውጣልኝ‘ ነበር ሌላ ጊዜ ቢሆን የምለው። አሁን የምትሸሸዋን ሴት አይደለሁም። ምንም ቢሆን የምትጋፈጠዋን ማህደር እየተለማመድኳት ነው።
“እደውልልሃለሁ።” ያልኩትን ያመነኝ አይመስልም። ተገርሞ እያየኝ ተሰናብቶኝ ወጣ። የገባኝ አንድ ነገር ሲሳይ በብዙ ፍጥነት ማንነቴን እያሾረው መሆኑ ነው።
ወደ ቤቴ ገብቼ ሲሳይ ያለኝን አደረግኩ።
«በህይወትሽ የምትሸሺው ነገር ምንድነው? መስታወት ፊት ቁሚና ለራስሽ ንገሪው። እመኚው!! መቀየር የማትችዪውን ነገር መቀበል ነው የሚፈውሰው።» ነበር ያለኝ
የልጄን ፎቶዎች ከደበቅኩበት አወጣኋቸው። በመጀመሪያው ቀን ቀላል አይሆንም ነበር ያለኝ። ቀላል አልነበረም። ሁሉንም ፎቶዎች በፊት የተሰቀሉበት መለስኳቸው። መሸሽም መደበቅም መድሃኒት አይሆንም። ስሸሽ የተጠራቀመው እንባዬ ገደቡን ጥሶ አይኔን አደፈራረሰው። ስልኬ መጥራቱን እንኳን የሰማሁት ብዙ ከጠራ በኋላ ነበር።
«ምን ሆነሻል? አልቅሰሽ አይደለምኣ?» ሲሳይ ነው።
«ነው! አልቅሼ ነው።» እያልኩት ጭራሽ መንፈቅፈቅ ጀመርኩ።
«እህህህ ምን ተፈጠረ ቆይ?» እቤቴ ደጅ ድረስ አድርሶኝ ነበር የተመለሰው። መልስ መመለስ እስኪያቅተኝ ሲቃዬ አነቀኝ።
« በቃ በቃ እሺ መጣሁ። ስልኩን አትዝጊው እያወራሁሽ እደርስልሻለሁ። እኔ አጠገብሽ ሆኜ እንደፈለግሽ እንድታለቅሺ ፈቅድልሻለሁ። እስከዛ ግን ስወድሽ አታልቅሺ?» ብሎኝ ሊያስቀኝ እየሞከረ ከቤቱ ሲወጣ፤ «ብርድ እንዳይመታህ በደንብ ልበስ» ስለው «አትስጊ ካልሲ አጥልቄለታለሁ» ሲለኝ
ታክሲ ሲያናግር
«የኔ እመቤት ደሞ ስስ ፒጃማ ፍለጋ ቁምሳጥኑን ዘረጋግፊው አሉሽ!» ሲለኝ ሲከፍል
«ስንቴ መስታወት አየሽ?» ሲለኝ
ሲደርስ እውነትም ማልቀሴን ትቼ ልቤ ተሰቅሎ እየጠበቅኩት ነበር። በሩን ከፍቼ ተጠመጠምኩበት። ሙሽራውን በሰርጓ እለት ወደ መኝታ ቤታቸው እንደሚያስገባ ሙሽራ አቅፎኝ ወደሳሎኑ ገባ! ማልቀሴን እረሳሁት። ሳሎኑ ውስጥ የተሰቀለውን የእኔንና የኢሳያስን የሰርግ ፎቶ አይቶታል። ግን አልጠየቀኝም። ሌላ ነገር እያወራ ሲያስቀኝ ቆየ።
«ሲስ?»
«ወዬ እመቤቴ?»
«ስለእኔ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ።»
«ምኑን ትነግሪኝ? በፎቶ አሳየሽኝኮ አስጎበኘሽኝ።» አለ ወደፎቶው እየጠቆመኝ።
«እየቀለድኩ አይደለም ሲስ! ከምሬ ነው።»
« እሺ እመቤቴ ንገሪኝ! ይኸው! Am all yours!»
ስለኢሳያስ እና ስለልጄ ነገርኩት ብቻዬን ስለፈልፍ ሲያባብለኝ እና ሲደባብሰኝ ብቻ ቆየ። ብዙ ደቂቃ እቅፉ ውስጥ ካቆየኝ በኋላ
« ባንቺ ደረጃ ካሉ ሴቶች ይልቅ አንዲት ምንም የማታውቅ የቤት እመቤት የሰመረ ትዳር ለምን የሚኖራት ይመስልሻል?» አለኝ
« ጭራሽ እንደዛ ስለመሆኑም እንጃልህ! ምን ለማለት ፈልገህ ነው?»
«ይሄ ሀቅ ነው ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በጋራ ስምምነት ባስቀመጥነው ደረጃ ብዙዎቹ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሴቶች በትዳራቸው ስኬታማ አይደሉም።»
«ምናልባት ከትዳራቸው ሌላ ትኩረታቸውን የሚሻ ሌላ ስራ ስላላቸው?»
«እኔ አይመስለኝም። እነዛ በትዳር ውስጥ ለፍቅር ወይ ለልጃቸው አልያም በሌላ ምክንያት ዝቅ ማለትን ያውቁበታል። እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? ክርስቶስ ለባል የሰጠው ትእዛዛ ሚስትህን ክርስቶስ ቤተክርስትያንን በወደደበት ፍቅር ውደድ የሚል ነው። ያ ማለት ነፍሱን እስከመስጠት። ለሚስት ያላት ግን ሚስት ለባሏ ትገዛ ነው። የቱ የሚከብድ ይመስልሻል?» ሳልመልስለት ራሱ ቀጠለ።
«ባትወጂም መገዛት ትችያለሽ። ወደሽ አለመገዛት ግን በፍፁም አትችዪም።» ዝም ነበር መልሴ። ከአንዱ ስሜት ወደሌላው መሻገር ምንም አይከብደውም። መከፋቴን አስረስቶኝ አመሸን።
«ያው እንደምታውቂው ድንግል ነኝ። በዛ ላይ ቁስሉ ራሱ ሰበብ አይፈልግም።» ብሎኝ እኩለ ለሊት አልፎ ወደ ቤቱ ሄደ።
★ ★ ★
በሚቀጥለው ቀን በስራ የደከመ ሰውነቴን እየጎተትኩ መኪናዬጋ ደረስኩ። መሽቷል። እቤቴ ገብቼ ማረፍ ነው ያማረኝ። ስልኬ ጠራ። ሲሳይ ነው።
“እራት በላሽ?”
“አልበላሁም። ግን ደክሞኛል በጣም።”
“እማ ቆንጆ እራት ነው የሰራችው። እየጠበቀችሽ ነው።”
“ትቀልዳለህ እንዴ? ማን ነኝ ብዬ ነው እናትህ ቤት እራት ልበላ የምመጣው?”
“ማንም መሆን አይጠበቅብሽም። ሰው መሆን የእማን እራት ለመብላት በቂ ነው።”
★ ★ ★
አመመኝ። የቤተሰቡ ፍቅር አሳመመኝ።
“ደህና ነሽ ግን?”
“ምነው ደስ አላለሽም?”
“ምነው ልጄ ከፋሽሳ?”
ይሉኛል እየተቀባበሉ ። አመመኝ። የሚታገለኝን እንባ እየዋጥኩ የደመቀ እራት በላሁ። የቤተሰብ ፍቅር ህመሜ፣ ንጭንጬ ፣ ሽንፈቴ፣ ድክመቴ……… መሆኑ አልገባቸውም። ይሄን ፍቅር በዘመኔ አይቼው አንጊንቼው እንደማላውቅ አያውቁም። የሲሳይ እናት ፊቴን እያገላበጡ፣ ፀጉሬን እየዳበሱ የሆንኩትን ሲጠይቁኝ እናት እንደማላውቅ አያውቁም። አባትየው እየደጋገሙ ‘ልጄ‘ ሲሉኝ። አይኑ ለማያይ ያአረጀ አያቴ እየተላላኩ እና ምርኩዝ ሆኜ እንዳደግኩ አልገባቸውም። እህቶቹ እግሬ ስር በርከክ እያሉ ‘ሲሳይ አስከፍቶሽ ነው? እሱ እኮ ክፍት አፍ ነው።” ሲሉኝ አያቴ ሞቶ የአክስቶቼ ልጆች እንደምናምንቴ እየቆጠሩኝ ተምሬ መጨረሴን አያውቁም። ብዙ አወሩኝ። እቤት ይዟት የመጣ ብቸኛ ሴት መሆኔን ነገሩኝ።
★ ★ ★
እንደምንም ያመቅኩትን እንባዬን መኪናዬ ውስጥ ሲሳይ እቅፍ ውስጥ ዘረገፍኩት። አላባበለኝም። እየደጋገመ እንባዬን እየጠረገ ፣ ፀጉሬን እያሻሸ ጠበቀኝ።
“አውሪኝ። የተሰማሽን ሁሉ አውሪኝ።” አለኝ። ሲቃዬ አላስወራ አለኝ።
ጣቶቹን ፀጉሬ ውስጥ ሰዶ ወደራሱ አስጠጋኝ። ይበልጥ ሲቀርበኝ ከመቃወም ይልቅ ልስመው ፈለግኩ። በሌላኛው እጁ እንባዬን ከጉንጬ ላይ ጠራረገው። ከንፈሩ ከንፈሬን የሚነካበት ሰዓት ረዘመብኝ። መጠበቅ አቃተኝ። ሳምኩት። ነፍስ በሚያሳርፍ መሳሙ ለደቂቃዎች ሳመኝ።
“ምንም ይሁን ንገሪኝ፣ አንድም ሳታስቀሪ የተሰማሽን ንገሪኝ፣ አንቺ ራስሽን ከምትረጂው በላይ እረዳሻለሁ። እንባሽ ከመጣ አልቅሺ ብቻ ልስማሽ!” አለኝ መረጋጋቴን ሲያይ
“አሁን እኮ መሽቷል። ሌላ ቀን ላውራህ?”
“ማደር ካለብኝ እየሰማሁሽ አድራለሁ።”
አውርቼ የማላውቃቸውን ብዙ ነገሮች ነገርኩት። ሳለቅስ አያባብለኝም። እጄን እየደባበሰ ይሰማኛል። ስለቤተሰቦቼ ሁሉንም ነገርኩት። አያቴ ሲሞት ከልጅነቴ ጀም
👍111