ምርኩዙ ሆኜ ስላደግኩ ያለውን ንብረት ሁሉ ተናዞልኝ ነበር የሞተው። በንብረቱ ሳቢያ ዘመዶቼ ሁሉ በፊት ይጠሉኝ ከነበረው በብዙ እጥፍ ጠሉኝ።
የደበቅኩት የለም ሁሉንም ነገርኩት። ያልሰማኝ የለም። ያለፍትን ውሳኔዎቼን በሙሉ ቆም ብዬ እንዳይ አደረገኝ። እቤቴ ስገባ እንደሌላው ቀን ኢሳያስ የሌለበት ወና ቤት አላስጠላኝም። አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ከራሴ ጋር አወራሁ።
“በራስሽ መተማመን ካለብሽ ራስሽን እወቂው። ጠንካራ ጎንሽን እና ድክመትሽን ለዪ፣ ድክመትሽን በጠንካራው ነገርሽ ለመሸፈን አትሞክሪ፣ ተጋፈጪው ማሻሻል ያለብሽን አሻሽዪ፣ ያለፈ ቁስልሽን ተቀበዪው እመኚው እንጂ አትሽሺው።” ያለኝን የሲሳይ ንግግር አሰብኩት። ደስ ብሎኝ ተኛሁ።
★ ★ ★
በጠዋት ወደስራ ስገባ ሲስተር ቀለምን ቀድማኝ አገኘኋት ። ጠርቻት ለልጆቿ የሆነ ነገር እንድታደርግ የተወሰነ ገንዘብ ሰጠኋት። እጄን እያገላበጠች ስትስም እንባዋ ነካኝ። አቀፍኳት። እስከዛሬ ልረዳት ባለመቻሌ ራሴን ረገምኩት። እቤቷ ሄጄ ልጆቿን ላይላት ለሳምንቱ መጨረሻ ቀጥርያት ስራ ጀመርን።
በህይወቴ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደስተኛ ነኝ። ግን ደግሞ መንታ መንገድ ላይም ነኝ። ሲሳይና ኢሳያስ!!
የብዙ ዓመት አለሁሽ ባዬ ግን በራሴ ትህምክትና ፍራቻ ያልተረዳሁት ኢሳያስ
ሳልነግረው የማስበው እና የሆንኩት የሚገባው ሲሳይ
መወሰን ነበረብኝ። ማናቸውንም መምረጥ ህመም አለው። ፈሪ ግን አይደለሁም። አልሸሽም።
★ ★ ★
ውሳኔዬን መጀመሪያ ለሲሳይ ማሳወቅ ፈለግኩና አገኘሁት። ነገርኩት።
“እርግጠኛ ነሽ?” አለኝ መጀመሪያ ግራ እየተጋባ
“አዎን። መቼም እንደዛሬ እርግጠኛ የሆንኩበት ውሳኔ የለም። ” መለስኩለት
“አሁን ነው የገረዝሽኝ። ያማል።” አለኝ ድምፁን ዝግ አድርጎ
“አዝናለሁ። አንተ በህይወቴ ፈጣሪ የላከልኝ መልዓክ ነህ። ባልጎዳህ በወደድኩ። ” አልመለሰልኝም። ግንባሬን ሳመኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፋው አየሁት። ሊሄድ መንገድ ከጀመረ በኋላ መለስ ብሎ እንዲህ አለኝ
“ኢሳያስን እድለኛ መሆኑን ንገሪው!!”
★ ★ ★አሁን ጨረስን።★ ★ ★
አስተያየትቶን በ @atronosebot አድርሱን
ድርሰቱስ ተመችቶአችኋል? አሳውቁን።

👍8
ተስፋዬን በሙሉ አንች ላይ ብጥልም
የወደፊት ህልሜን ባንች ብገነባም
ከፈጣሪ በታች አንችኑ ባመልክም
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
#ማነው_እንዲህ_ያለሽ?
"ህይወት ይቋረጣል ህላዌ አይቀጥልም"
ለአመታት ደክሜ
የፀነስኩት ፍቅር የቀመምኩት ቅማም
እንደ ባቢሎን ግንብ ባንድ ጊዜ ቢናድም
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ማነው እንዲህ ያለሽ?
"ህይወት ይቋረጣል ህላዌ አይቀጥልም"
ፀሃይ ብትገባ ሰማዩ ቢጨልም
ደስታ ከኔ ርቆ ሀዘን ቢከበኝም
ካንች ተነጥዬ ብቻዬን ብቀርም
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
የጨለመው ሌሊት
የወረሰኝ ፅልመት መገፈፉ አይቀርም
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
የዳመነው ሰማይ የወረደብኝ ዶፍ
የጣለው በረዶ ያጥለቀለቀኝ ጎርፍ
ይዘገያል እንጅ ማባራቱ አይቀርም
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
#እውነቱን_ልንገርሽ?
እናልሽ የኔ አለም
ሌላ ህላዌ አለ ህይወት አትቆምም።
የወደፊት ህልሜን ባንች ብገነባም
ከፈጣሪ በታች አንችኑ ባመልክም
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
#ማነው_እንዲህ_ያለሽ?
"ህይወት ይቋረጣል ህላዌ አይቀጥልም"
ለአመታት ደክሜ
የፀነስኩት ፍቅር የቀመምኩት ቅማም
እንደ ባቢሎን ግንብ ባንድ ጊዜ ቢናድም
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ማነው እንዲህ ያለሽ?
"ህይወት ይቋረጣል ህላዌ አይቀጥልም"
ፀሃይ ብትገባ ሰማዩ ቢጨልም
ደስታ ከኔ ርቆ ሀዘን ቢከበኝም
ካንች ተነጥዬ ብቻዬን ብቀርም
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
የጨለመው ሌሊት
የወረሰኝ ፅልመት መገፈፉ አይቀርም
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
የዳመነው ሰማይ የወረደብኝ ዶፍ
የጣለው በረዶ ያጥለቀለቀኝ ጎርፍ
ይዘገያል እንጅ ማባራቱ አይቀርም
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
#እውነቱን_ልንገርሽ?
እናልሽ የኔ አለም
ሌላ ህላዌ አለ ህይወት አትቆምም።
👍2
#ቂም_የሸፈነው_እውነት
:
#ክፍል_አንድ
:
✍ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
:
“መለያየት እፈልጋለሁ። ፍታኝ?” አልኩት በመኪናው መስኮት አሻግሬ ዓይኖቹን እየሸሸሁ።
“እሺ!!” ነበር መልሱ:: ቢያንስ ‘ለምን?’ ብሎ እንዴት አይጠይቀኝም?
“መች ነው እንዲሆን የምትፈልጊው? አሁን? ነገ? ከሳምንት በኋላ? መቼ?” ቀለል አድርጎ ቀጠለ። ቀጥዬ የምለው ጠፋኝ። ለራሴ ምክንያት መስጠት እፈልጋለሁ። ተናዶ እንዲናገረኝ እሱ ላይ እንከን ማግኘት አጥብቄ እፈልጋለሁ።’ፈታችው’ ከመባል ሌላ ቅጥያ ተጨምሮበት ‘ስላናደዳት ፈታችው’፣ ‘ስለመታት ፈታችው’……… ብቻ ምክንያቱ ከሱ ቢመጣ ደስ ይለኛል።
“ካለቀልን ዛሬም ብንፋታ ደስ ይለኛል።”
“ከዛሬ በኋላ ተፋተናል። የግድ በህግ መፋታት የለብንም። እኔን መፍታት አይደል የፈለግሽው? ስለወደድኩሽ እንጂ ማንም ስለፈረመ እና ምስክር ስለተጠራ አላገባሁሽም።” ብሎኝ ከመኪናው ወረደ እና የኔን በር ከፈተልኝ። ቤታችን ደጅ ደርሰን ነበር። ተናደድኩ።
“የንብረት ክፍፍሉ……..” አላስጨረሰኝም።
“የትኛውን ንብረት ነው የምትፈልጊው?” የአጥሩን በር ከፍቶ በእጁ እንድገባ አሳየኝ።
“ድርሻዬን::”
“ህምምምም…….. ቅር ካላለሽ ትንሿን መኪና ልውሰዳት ሌላውን ንብረት አልፈልገውም። ከዛሬ በኋላ ባልሽ አይደለሁም። ምንም ንብረትም የለኝም።” ብሎኝ ‘ትንሿ’ ያላት መኪናው ውስጥ ገብቶ ተመልሶ ሄደ።
ምን እንደምፈልግ ግራ ገባኝ። ካሳሁንን ሳላገባው በፊት ነበር የምፈታው ቀን የሚናፍቀኝ። ሳላገባው ፈትቼዋለሁ። እሱ ያገባኝ የመሰለው ቀን እኔ አግብቼም ፈትቼዋለሁ።ታዲያ ለምን አገባሁት? እሱን አላገባሁትም። ገንዘቡን እንጂ። ወንዶች ‘ሴት ልጅ ገንዘብ ያለው ወንድ ትወዳለች’ ሲሉ ሳቄ ያመልጠኛል። ወይ ሰውየው ማርኳታል ወይ ገንዘቡ ማርኳታል። ለአንዳቸው ቅድሚያ ትሰጣለች።ለገንዘቡ ብላ ከሆነ ገንዘቡን እንጂ እሱን አትወደውም። ገንዘቡ እስካለ ወይም የምትፈልገውን እስክታገኝ ድረስ አለች። እነሱ ግን ራሳቸውን ሳይሆን ገንዘባቸውን ያቀርቡላታል። ምክንያቱም የቁስን ያህል ራሳቸውን አያምኑትም። ስለዚህ ከቁሳቸው ይልቅ ራሳቸውን ተወዳጅ አድርገው ማቅረብ ሲሳናቸው ለገንዘቤ ብላ ነው የወደደችኝ ይላሉ እንጂ ገንዘቤን ነው የወደደችው አይሉም። ሰውየውን ከወደደችው ለገንዘቡ ብላ፣ ለቁመናው ብላ፣ ለወዙ ብላ…. የሚሉት ቀልድ አይጥመኝም። በቃ ሰውየውን ነው የወደደችው።
የዛን ቀን ምሽት አልመጣም። ጠበቅኩት። እውነቱን እንደሆነ ገባኝ። ካሳሁን ፈቶኛል። ሁለተኛው ቀን መሸ ።አልመጣም። አልደወለም። ሶስተኛ ቀን ሆነ……… አራተኛ ቀን መጣ… … አስር ቀን ሞላው። አልመጣምም። አልደወለምም። የገባኝ ግን ቢመጣ ደስ እንደሚለኝ ነው።እሱን መፍታት ያስደስተኛል ብዬ ያሰብኩትን ያህል አልነበረም የደስታዬ መጠን።
“አልወደውም። ከሀብቱ እንጂ ከእርሱ ጉዳይ የለኝም።” ለራሴ ብቻዬን አነበነብኩ። ስልኬን እልፍ ጊዜ ልደውልለት አነሳሁ። እልፍ ጊዜ ተውኩት። በአስራአንደኛው ቀን ስልኬ ጠራ። እሱ ነበረ። ለምን ደስ አለኝ? አብሬው መኖር የማልፈልገው ሰው ድምፁን መስማቴ እንዴት አስደሰተኝ?
“ደህና አደርሽ ሰብሊ? …… ላግኝሽ?”
“እሺ:: የት እንገናኝ?”
“ስራ ቦታ:: አራት ሰዓት ላይ መጥቼ ወስድሻለሁ።”
ስራ የመግባት ፍላጎት አልነበረኝም።ቁምሳጥኑን ከፍቼ ሊያቆነጀኝ ይችላል ብዬ ያሰብኩትን ሁሉ ልብስ ሞከርኩ። ላማልለው? ወይስ ከሱ በመለየቴ አለመከፋቴን ለማሳየት? ለራሴ የምሰጠው ምክንያት ባይኖረኝም በሱ ፊት ቆንጆ ሆኜ መታየት ፈለግኩኝ። አምስት ዓመት በትዳር አብሬው ስኖር ይሄ ግድ ሰጥቶኝ አያውቅም ነበር። በጥንቃቄ ስዋብ ብዙ ሰዓት ፈጅቼ ደረስኩ። ተጋብተን ብዙም ሳንቆይ ነበር ካሳሁን እቤት ከምትውዪ ብሎ ለንግድ ተስማሚ የሆነ ቦታ ላይ ትልቅ የሴቶች ፀጉር ቤት የከፈተልኝ ። በሩ ላይ ሲደርስ የት ይዞኝ ሊሄድ እንደሆነ እያሰብኩ ነበር። ብዙም ግድ ያልሰጠው ሰላምታ ሰጥቶኝ የመኪናውን በር ከፍቶ አስገባኝ። በሚከብድ ዝምታ መኪናውን መንዳት ጀመረ። ላገኘው እንዳልቸኮልኩ። ተጨነቅኩኝ።
“የት ነው የምንሄደው?” አፌ ይሄን ይበል እንጂ የትም ብንሄድ ግድ አልነበረኝም።
“የምንጨርሰው ጉዳይ አለን።”
ባንክ ቤት በር ጋ ስንደርስ በሁለታችን ስም የነበረውን የባንክ አካውንት ሊያዛውርልኝ መሆኑን ነገረኝ። በተዘባረቀ ስሜት ውስጥ ሆኜ የሚጠበቅብኝን ፈፀምኩ። እድሜውን ሙሉ የሰራው ገንዘብ መሆኑን እያወቅኩ ‘አንተስ?’ ብዬ እንኳን አልጠየቅኩትም። ነገር ዓለሙ ዞረብኝ። ምንም ሳንነጋገር ፀጉር ቤቱ በር ጋር ደርሰን።በር ሊከፍትልኝ ከመድረሱ ዘልዬ ከመኪናው ወረድኩ። በሌላ ትህትናው መቁሰል አልፈለኩም።
“የት ነው ያለኸው?” አልኩት
“ቤት እስካገኝ ሆቴል ነው ያረፍኩት::”
“ለጊዜው እኮ እቤት መሆን ትችላህ::”
“በሚቀጥለው ሳምንት በአንዱ ቀን የቤት ባለቤትነቱን ስም አዛውርልሻለሁ:: ሰሞኑን ስራ ስለሚበዛብኝ የምችል አይመስለኝም።” ብሎኝ መኪናው ውስጥ ገብቶ ሄደ። ራሴ የሚፈነዳ መሰለኝ።የማብድ የማብድ መስሎ ተሰማኝ። ወደቤቴ ሄድኩ።
የደስታዬ ጫፍ ይሆናል ብዬ የማስበው ቀን ሲመጣ እርካታን ሳይሆን ባዶነትን ተሸክሞ ነው የመጣው። የምፈልገው ሁሉ ኖረኝ።የማስበው ሁሉ ሰመረልኝ። ግን ትርጉም አልባ፣ ደስታ የለሽ ሙት ሆነብኝ።
**********
እንደማንም ያልነበረው ልጅነቴ፡-
ሰዎች ስለልጅነታቸው ሲያወሩ ‘እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ…..’ ሲሉ እገረማለሁ:: ‘ማንኛውም ኢትዮጵያዊ’ እኔን ያቀፈ ማዕቀፍ ይሆንን?
በቀን አንዴ ትርፍራፊ ለመቅመስ መስገብገብ፣ ጎዳና ላይ በገነባቻት የላስቲክ ቤት አጠገብ ተቀምጣ የምትለምን ወፈፍ የሚያደርጋት እናት፣መለመኛ የሆኑ መንታ ታናናሽ እህትና ወንድም፣ አስር ሳንቲም ለመመፅወት የሚመፃደቅ ሂያጅ፣ በባዶ እግርና በእኮዮች ምፀት ታጅቤ የምዳክርበት ትምህርት ቤት…….. ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ የተለየ ልጅነት ነው።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እናቱ ልመናን ተናዛለት አባት አልባ ህፃናት መንገድ ዳር አስታቅፋው አልሞተችም።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እናቱ የሚበር መኪና ውስጥ ገብታ ስትሞት የሚሰማውን ከእብደት ያልተለየ ስሜት አያውቀውም።
የኔ ልጅነት ‘እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ’ የሚባለው ማዕቀፍ ውስጥ የማይገባው ልጅነት የሚባለው ዘመኔ በአስር ዓመቴ አክትሞ የሁለት አመት ጨቅላ መንታ ታናናሾቼን እየለመንኩ ማሳደግ ግዴታዬ ስለነበር ነው። ዓለም ስትከረፋብኝ፣ በርሃብ ከሚጮሁ ታናናሾቼ ጋር ኡኡኡ ብዬ ሳለቅስ “እንደእናቷ ጠሸሸች” እተባልኩ አራት ዓመታትን ጎዳና መግፋቴ ነበር።
አንድ ምሽት ታናናሾቼን አስተኝቼ ነትቦ እርቃኔን ያጋለጠውን ልብሴን እየሳብኩ ከላስቲክ ጎጆአችን ፊት ለፊት ቆሚያለሁ። መኪና ሲጢጥ ብሎ ሲቆም ሰማሁ። የሰከረ ወንድ ድምፅ ተከትሎ ተሰማኝ።
“እሙዬ ነይ እስኪ……”
🌑ይቀጥላል➡️
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ የኔ ምርጦች
አመሰግናለው
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

👍4
#ጨረቃ_ና_ናፍቆት
#እቱ_የጥንቲቱ
የጥርስሽ ንጣቱ
የጉንጭሽ ቅላቱ
ውል ይለኛል ዛሬም የገላሽ ሙቀቱ
የእግሮችሽ ኮሽታ
የፍቅርሽ ሹክሹክታ
ያ የሣቅሽ ዜማ የበዛው ክትክታ
ይሠማኛል ዛሬም ናፍቆት ሲበረታ
#እቱ_የጥንቲቱ
አንቺም ትዝ ካለሽ ካለብሽ ናፍቆቱ
ይህ ነው መዳኒቱ
ባስለመድኩሽ ሰዓት ባለሽበት ቦታ
ቀና በይ ላንድ አፍታ
እኔም ባለሁበት ባስለመድሽኝ ሰዓት
ዓይኖቼን አቅንቼ
ጨረቃን አይቼ ልግባ ተፅናንቼ
አንቺም በዚያች አፍታ
ጨረቃዋን ፈክታ
ካየሻት ተጽናኚ
በይ ቃሌን እመኚ
ምንም ብንራራቅ ካንድ ሰማይ ሥር ነን
ነገ አብረን ለመኖር ታላቅ ተሥፋ አለን
🔘ሳምሶን መኮንን🔘
#እቱ_የጥንቲቱ
የጥርስሽ ንጣቱ
የጉንጭሽ ቅላቱ
ውል ይለኛል ዛሬም የገላሽ ሙቀቱ
የእግሮችሽ ኮሽታ
የፍቅርሽ ሹክሹክታ
ያ የሣቅሽ ዜማ የበዛው ክትክታ
ይሠማኛል ዛሬም ናፍቆት ሲበረታ
#እቱ_የጥንቲቱ
አንቺም ትዝ ካለሽ ካለብሽ ናፍቆቱ
ይህ ነው መዳኒቱ
ባስለመድኩሽ ሰዓት ባለሽበት ቦታ
ቀና በይ ላንድ አፍታ
እኔም ባለሁበት ባስለመድሽኝ ሰዓት
ዓይኖቼን አቅንቼ
ጨረቃን አይቼ ልግባ ተፅናንቼ
አንቺም በዚያች አፍታ
ጨረቃዋን ፈክታ
ካየሻት ተጽናኚ
በይ ቃሌን እመኚ
ምንም ብንራራቅ ካንድ ሰማይ ሥር ነን
ነገ አብረን ለመኖር ታላቅ ተሥፋ አለን
🔘ሳምሶን መኮንን🔘
#የመልስ_ጉዞ_ወደመነሻ_ጉዞ
:
#ክፍል_አስራ_አራት
:
✍ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
....ቀጥታ ወደቤቴ በመሄድ ፋንታ ብቻዬን ሆኜ በፀጥታ ወደምተክዝበት ቦታ ነበር የተጓዝኩት፡፡ወደቢሾፍቱ ሀይቅ ሄድኩና ቁጥቆጦ ጥቅጥቅ ካለበት ቦታ ሀይቁ ዳር ላይ ወደሚገኝ ገዘፍ ካለ የድንጋይ አለት ላይ ቁጭ ብዬ አይኖቼን አስፈሪው እና ዙሪያውን በተራራ በተከበበው ሀይቅ ላይ ተክዬ ማሰላሰል ጀመርኩ .፡፡ሙሉ አዕምሮዬን የሞላችው ዶክተሯ ነች…እኔ እንጃ አላውቅም በውስጤ ህይወቴ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀየር እና እስከአሁን ስሄድበት ከነበረበት መንገድ ፍፅም በተቃራኒና በማይገመት አይነት መስመር መጎዝ እንደምጀምር እየተሰማኝ ነው፡፡ከሀሳቤ ሳልፈልግ ያናጠበኝ ከቆጥኞቹ ስር የሚሰማዋ መንሾካሾክ ነው፡፡ሰው መጥቶ ፀጥታዬን ሊረብሸው ነው እንዴ ? ብዬ ትኩረቴን ከሀይቁ ወደቁጥቆጦው ስመልስ ያልጠበቅኩት ነገር አየው …..ግዙፍ ዥንጉርጉር ጥቁር እባብ ሽልልል እያለ ከቋጥኙ ውስጥ ቅጠሎችንና ቅርንጫፎቹን እየገላለጠ ወደ እኔ አቅጣጫ እየተሳባ እየመጣ ነው..
ወደእኔ በመገስገስ ላይ ያለውን እባብ ምላሱን በደም ስሬ ሰክቶ መርዙን ወደውስጤ ለመትፈት የቆመጠ በሚያስመስለበት ሁኔታ ጭንቅላቱን በአየር ላይ አንሳፎ አስፈሪውን ሹል ምላሱን ትሪዕታዊ በሆነ ሁኔታ ሲያወዛውዛቸው እያየው ነው፡፡ በድንጋጤም በመገረምም ከተቀመጥኩበት ቋጥኝ በቅልጥፍና ተነሳውና ዙሪያ ገባዬኝ ማቃኘት ጀመርኩ… ጭንቅላቱን ብዬ የምገላግልበት ደህና ዱላ ነገር ፍለጋ …ያን ያህል አስተማማኝ ባይሆንም አንድ ሁለት ክንድ የሚረዝም ደረቅ እንጨት አገኘውና አፈፍ አድርጌ አነሳውና አስተካክዬ ያዝኩትና ለፍልሚያ ተዘጋጀው…….፡፡
በእኔ እና በእባቡ መካከል ያለው ክፍተት ከሁለት ሜትር አይበልጥም…እኔም እንዴት አድርጌ ላጥቃው እያልኩ እስትራቴጂ ሳወጣ 3 የሚሆኑ ደቂቃዎች አለፉ …እባቡም ከእኔ ተመሳሳዩን እያሰበ ይመስለኛል፡፡ከዛ ቀድሞ ያጠቃል ብዬ በምጠብቅበት ጊዜ በሚገርም ፍጥነት ተወርውሮ ወደመጣት ዞረና ተስፈንጥሮ ቁጥቋጦው ውስጥ ተመልሶ ገባ ፡፡ድላዬን እንደቀሰርኩ ተከተልኩት…ሊያመልጠኝ አይገባም..ደረስኩና ቁጥቋጦውን በጥንቃቄ ስገላልጥ በዛኛው ወገን ያልጠበቅኩት ነገር አያው ..ድንጋጤዬ ጨመረ.. ፈጣን ውሳኔ ወሰንኩ ..ቁጥቆጦውን በግራ በኩል አልፌ ተጠምዘዝኩና ስሮ ደረስኩና ወገቧን በአንድ እጄ አቅፌ አንጠለጠልኩና ከቁጥቆጦ ውስጥ አርቄ በመውሰድ መልሼ አስቀመጥኳት..
-ምን እያደረክ ነው?በሳቅና በመኮሳተር መሀል ባለ ስሜት ጠየቀቺኝ፡፡
-አንቺው ንገሪኝ እንጄ .እዚህ ምን እያደረግሽ ነው... ? እንዴት መጣሽ ..?.ለምን መጣሽ..?
-አንተን ለማግኘት ነዋ የመጣውት
-እኔ እዚህ እንዳሆንኩ ማን ነገረሽ… ? ውይ ይቅርታ ለካ አንቺ ነሽ››
-አዎ እኔ ነኝ…ግን ምን አየሆንክ ነው ዱላው ለማን ነው ?
-ባክሽ አንድ እባብ ሊያጠቃኝ ነበር …ግን ሀሳቡን ቀይሮ ወደእዚህ ቋጥኝ ገባብኝ … አንቺንም ሊያጠቃሽ ይችል ነበር
-እኔን እንኳን አያጠቃኝም?
-ለምን ?
-ያየኸው እባብ እራሴው ነበርኩ….እራሴን በራሴ እንዴት ላጠቃ እችላለው?፡፡
-ቀልዴን እንኳን አይደለም…ጭንቅላቱን ማለት ነበረብኝ››
-ለምን.?
-እባብ ደግሞ ለምን ይባላል ? የሰው ልጅ እና እባብ ለዘመናት ያላቸውን ጠብ እያወቅሽ… ? ለማንኛውም ነይ ብዬ ቀድሞ ወደነበርኩበት ቆጥኝ ድንጋይ ይዤት ሄድኩና ቀድሜት ተቀመጥኩ ተከተለቺኝና ከገጎኔ ተቀመጠች፡፡
-እኔ ግን ስለሰው እና እባብ ግንኙነት ተቃራኒውን ነው የማውቀው …በማለት ወደ አቋረጠነው ውይይት መለሰችን
-እንዴት ማለት እስኪ አስረጂኝ አልኳት ? ይህቺ ተምረኛ ልጅ ሳለስበው ባገኘዋት ቅፅበት የመጀመሪያ ውይይታችን ስለእባብ የመሆኑ አጋጣሚ ገርሞኝ፡፡
-እሷ ኮስተር ብላ ማብራራት ጀመረች፡፡
‹‹የእባብና የሰው ልጅ እውቅናም ሆነ ልባዊ ወዳጅነት ጥንታዊና መሰረት ያለው ነው፡፡የሰው ልጅ አግዜያብሄር በመልኩና በሀምሳሉ ፈጠረው፡፡የዘን ጊዜ ከጦጣ ወይም ከዝንጀሮ ብዙም የማይሻል ነበር፡፡አንድ ነገር በቃ ልክ እንደ እኛ እና እንደ እግዜያብሄር ከፈጣራቸው ነገሮች መካከል መናገር የሚችል ቢሆንም ከእኛ እኩል ግን የማሰብ ጥበብ አልነበረውም፡፡እግዜያብሄር እንደዛ እንዲሆን አልፈቀደም ነበር፡፡በዚህ ጊዜ የእኔ አባት ቀዳሚው እባብ በውስጥ ሀዘኔታ ገባው፡፡››
-ቆይ ነገሮችን ግልጽ እያደረግሺልኝ ሂጂ..እያወራሽ ያለሽውን እያስተዋልሽ ነው…እባብ ነኝ እያልሺኝ ነው…የሰው ስጋ ለብሼ እንደሰው ማሰብና እንደሰው መሰራት የምችል ለየት ያልኩ ፍጡር ነኝ እያልሺኝ ነው ? ››
-ለየት ያልኩ ፍጡር መሆኔን ትጠራጠራለህ እንዴ?
-አረ በፍፅም …እባብ ነኝ ያልሺውን ነው ማመን ያልቻልኩት ?
-መብተህ ነው …በሂደት ታምናለህ …እስከዛው ዝም ብለህ ተረት እያወራውህ እንደሆነ አድርገህ ስማኝ ..
-እሺ ተስማምቼያለው..ቀጥይ
- እንዳልኩህ እኛ የእባብ ዝርያዎች ቀደምት ስንፈጠር እንደሰው ልጅ በእግዜያብሄር ሀምሳል ባንፈጠርም ቆሞ በእግር መሄድ፤መናገርና ፤ክፉውንና ደጉን፤ ሚጠቅምና ሚጎዳውን በጥበብ አንጥሮ እንደእግዚያሄር ከማሰብ ፀጋ ጋር ነበር የተፈጠርነው፡፡ይሁን እንጂ እግዚያብሄር በወቅቱ በዛ ነገር ደስተኛ አልነበረም፡፡
-ምን ማለትሽ ነው…? እግዚያብሄር አይደለም የፈጠራችሁ ?››
-አዎ እራሱ ነው ? ››
-ታዲያ እሱ አስቦና ፈቅዶ ከፈጠራችሁ ብኃላ እንዴት ደስተኛ ላይሆን ይችላል ? ፡፡
-በእኛ ብቻ እኮ አይደለም ቡኃላም እናንተን ከፈጠረ ቡኃላ ተፀፅቷል ፤ለዚህ ማስረጃ ደግሞ መፃፍ ቅዱሳችሁ‹‹እግዜያብሄር ሰውን በመፍጠሩ ተፀፀተ››ይላል፡፡
-ገባኝ ተዲያ እንዴት ሆናችሁ?....ጠየቅኳት በተረቷ ተመስጬ
-የእኛ ዝርያ ባለው ጥበብ ልክ እንደ እግዚያብሄር ክፉና ደጉን አንጥሮ ማሰብንና …ያሰበወንም ማድረግ በመቻሉ በወቅቱ በነበሩት ፍጥረታት ላይ ድንጋሬ ነበረ…
-ምን አይነት ድንጋሬ?
-አምላካችን የትኛው ነው.. የሚል?
-እና እግዚያብሄርነት… በጥበብና በፍጽሞና ማሰብን ብቻ ሳይሆን ዘላለማዊነትንና ሁለንተናዊአዋቂነትን መያዝ ይጠይቃል…
በዚህ መካከል የሰው ልጅ እግዜያብሄርን መስሎ ተፈጠረ…ከዛ አባቴም በእግዜያብሄር ላይ አቂሞ ነበርና ለዚህ የስው ልጅ ለሚባል አዲስ ፍጥረት እንዴት እግዜያብሄር እንደሚሆን ላስተምረው ብሎ በቀናነት ተነሳ…
-እርግጠኛ ነሽ በቀናነት ነው ?
-እግዚያብሄር ለመሆን የሚያስፈልጉ ሁሉን አዋቂነት እና ዘላለማዊነትን የሚያስገኙ በገነት አትብሉ ብሎ ያገዳቸውን እንዲበሉ በሴቷ በኩል ምክር ለገሳቸው፡፡…የመጀማሪያዋን በልተው ሁለተኛውን ከመድገማቸው በፊት ግን ሲርበተበቱ ደረሰባቸው …
-ምን ጠቀማቸው ታዲያ ከገነት እንዲባረረ ምክንያት ነው የሆናቸው ? ፡፡..የእኔ አስተያየት ነበር፡፡
-እሱ የራሳቸው መንከርፈፍ ነው..ደግሞ እንዳለው ነው… ክፉና ደጉን ያወቁት አባቴ ብሉ ያለችውን እጽ ከበሉ ቡኃላ ነው ሁለተኛውንም ዕፅ በልተው ቢሆን ኖሮ ልክ እንደ እሱ ይሆኑ ነበር…አባራሪና ተባራሪ አይኖርም ነበር
-ያልገባኝ ነገር ታዲያ አባትሽ ማለቴ አባቡ ከዚህ ምን ይጠቀማል..እንደውም ሁለተኛ እግዚያብሄር በላዩ ላይ ይነግስ ነበር…
-አይ የአባቴ እቅድማ ሶስት እግዚያሄር እንዲኖር ነበር…
-እንዴት ሆኖ ?
-ከሄዋን ጋር ሚስጥራዊ ውለታ ነበራው፡፡አባቴ የሚፈልጋትን ሁለተኛዋን ዕጽ ለእሷ እና ለአዳም ስትቆርጥ ለእሱም ለሚስቱና ለልጁ የሚበቃ እንድታመጣለት፡፡ከዛ በሶስት ግዛቶች የተከፋፈለ ሶስት እግዜያብሄር ይኖር ነበር፡፡እቅዱ እንደዛ ነበር፡፡ከዛ ሲርበተበቱ ተያዙ እራሳቸውም

👍4👎2❤1
ከገነት ተባረው እኛን እንድንባረር አደረጉን፡፡በተለይ እኛ በጣም ነው የተጎዳነው፡፡
-እስቲ ስለዕወቀት ፍሬዋ ንገሪኝ ?
-ስለእሷ ምን ልንገርህ?
-የዛን ጊዜ አንደበሉ በአዳምና ሄዋን ላይ ያስከተለው ለውጥ፡
-ፍሬዋ እንደምታስባት በአንዴ ሁሉን ነገር ግልጽ ምታደርግ አይደለችም….ቁልፍ በላት ፡፡የሆነ መግባት የምትፈልግበት ቤት ቁልፍ ስታገኝ ሰረገላ ውስጥ መክፈቻውን ትከተዋለህ ከዛ ታሽከረክረዋለህ…ትከፍተውና ወደ ውስጥ በመግባት የምትፍልገውን ነገር ለማግኘት መዞዞርና በየክፍሉ መቃኘት አለብህ፡፡
-ያቺ ዕፅ ማለት ቁልፍ ብቻ ነች፡፡ሰውን ማሰብ እንዲችል ወይም ክፉና ደጉን መለየት እንዲችል መጋረጃውን መክፈቻ..ለሌው ግን በአንዴ የሚሆን አይደለም፡፡ፍሬው ልክ እንደወይን በአመታተ ቆይታ ኃይል እየጨመረ እና ጣዕሙ እያማራ ሚሄድ ነው፡፡ከአባት ወደልጅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር ይበልጥ እየጠለቀ እና እያደገ የሚሄድ እውቀትና መገለፅ ከአባት ወደልጅ ፤ከዛም ወደልጅ ልጅ እየተሸጋገረ በሄደ ቁጥር እየዳበረ እና በዕወቀት እየበለፀገ የሚሄድ ነው፡፡
-ቆይ እሺ እሱን ለጊዜው ተይውና እናቴን ስላዳንሺልኝ እንዴት እንደማመሰግንሽ አላውቅም፡፡
-እንድታመሰግነኝ አይደለም ያደረኩልህ …በመልሱ እንድታገባኝ ስለምፈልግ ነው፡፡
-የእወነቴን ነው አትቀልጂ…በጣም ነው የማመሰግንሽ›
-እኔም የእወነቴን ነው…ካንተ ሁለት ነገር ነው የምፈልገው …አንድ እንድንጋባ እና አንድ ልጅ እንድንወልድ …ሁለተኛውን ደግሞ ሌላ ቀን ነገርሀለው…አለቺኝ ኮስተር ብላ
-እኔም ይህቺ ገራሚ ሴት እውነተዋን ይሆን እንዴ ? ስል ሌላ የሀሳብ መብሰልሰል ውስጥ ገባው።
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

#ሽ_ወይም_ሺ_ጨምሪበት
ታምሜ ከአልጋ ፥ ተሰፍቼ ስውል
መላ አካላቴ ፥ ቅንጥስ ስብር ሲል
ህመሜን ረስቼ ፥ ጤናሽ ያሳሰበኝ
በሽታ ሳይነካሽ ፥ ጤናሽ ያስጨነቀኝ
'ወድጄ' አይምሰልሽ ፥ እንዲያ ምንከራተት
ይልቁስ ከገባሽ ፥ 'ሽ' ጨምሪበት
ስላንቺ ማሰቤን ፥ ከልቤ አምርሬ
መወድዴን ስነግርሽ ፥ አንቺኑ ማፍቀሬ
ከቁብም ሳትቀጥሪው ፥ የያዘኝን ፍቅር
እንዳልሰማ ሆነሽ ፥ ስትይብኝ ዞር
እኔም ሳይሰለቸኝ ፥ ደግሜ ስነግርሽ
በመሰላቸት 'እ' ፥ ነበረ መልስሽ
ጭራሽ ሳልሰላች ፥ ከቶውን ሳልታክት
እኔ እልሻለሁ ፥ 'ሺ' ጨምሪበት
ማነው እሱ ካሉሽ፥ ካሻሽ ንገሪያቸው
ህመምሽ የሚያመው ፥ ጤናሽ ሚያሳስበው
መውደዱን ሲነግርሽ ፥ ግራ ቀኝ ያጋባሽ
ገገማ የሆነ ፥ ያሰለቸሽ ጭራሽ
ኧረ ማነው እሱ ፥ ብለው ከጠየቁሽ
'ሺበ' ሚለው ቃል ላይ ፥ ሺ ጨምሪበት
እናልሽ
ሕመሜን ዘንግቼ የቆየሁ ወድጄ-ሽ
መውደዴን ስነግርሽ እ-ሺ በይም ያልኩሽ
ሺበ-ሺ እባላለሁ እኔ፥ ምስኪኑ አፍቃሪሽ
ከአትሮኖስ ቻናል ተከታታይ የተላከ
👉 @cleopas4 አስተያየታችሁን አድርሱት
ታምሜ ከአልጋ ፥ ተሰፍቼ ስውል
መላ አካላቴ ፥ ቅንጥስ ስብር ሲል
ህመሜን ረስቼ ፥ ጤናሽ ያሳሰበኝ
በሽታ ሳይነካሽ ፥ ጤናሽ ያስጨነቀኝ
'ወድጄ' አይምሰልሽ ፥ እንዲያ ምንከራተት
ይልቁስ ከገባሽ ፥ 'ሽ' ጨምሪበት
ስላንቺ ማሰቤን ፥ ከልቤ አምርሬ
መወድዴን ስነግርሽ ፥ አንቺኑ ማፍቀሬ
ከቁብም ሳትቀጥሪው ፥ የያዘኝን ፍቅር
እንዳልሰማ ሆነሽ ፥ ስትይብኝ ዞር
እኔም ሳይሰለቸኝ ፥ ደግሜ ስነግርሽ
በመሰላቸት 'እ' ፥ ነበረ መልስሽ
ጭራሽ ሳልሰላች ፥ ከቶውን ሳልታክት
እኔ እልሻለሁ ፥ 'ሺ' ጨምሪበት
ማነው እሱ ካሉሽ፥ ካሻሽ ንገሪያቸው
ህመምሽ የሚያመው ፥ ጤናሽ ሚያሳስበው
መውደዱን ሲነግርሽ ፥ ግራ ቀኝ ያጋባሽ
ገገማ የሆነ ፥ ያሰለቸሽ ጭራሽ
ኧረ ማነው እሱ ፥ ብለው ከጠየቁሽ
'ሺበ' ሚለው ቃል ላይ ፥ ሺ ጨምሪበት
እናልሽ
ሕመሜን ዘንግቼ የቆየሁ ወድጄ-ሽ
መውደዴን ስነግርሽ እ-ሺ በይም ያልኩሽ
ሺበ-ሺ እባላለሁ እኔ፥ ምስኪኑ አፍቃሪሽ
ከአትሮኖስ ቻናል ተከታታይ የተላከ
👉 @cleopas4 አስተያየታችሁን አድርሱት
#ቂም_የሸፈነው_እውነት
:
#ክፍል_ሁለት (የመጨረሻ ክፍል)
፧
✍ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
......“ምን ፈለግክ?”
“አንቺን”
“ሸርሙጣ አይደለሁም።”
“ታዲያ እዚህ ምን ይገትርሻል?”
“ቤቴ ነዋ…..” ብዬ የላስቲክ ቤቴን በእጄ ጠቆምኩት።
“ስንት ዓመትሽ ነው?”
“አስራ አራት” ከመኪናው ወርዶ እየተንገዳገደ ተጠጋኝ።
“300 ብር እሰጥሻለሁ።”
“ሸርሙጣ አይደለሁም አልኩህ እኮ……”
“ሸርሙጣ ነሽ ማን አለሽ? ጎዳና እያደርሽ ምንም አልቀመስኩም ለማለት ነው?” እዚያ ጎዳና ላይ ስኖር ከዛ በላይ ፀያፍ ቃላቶች ሰምቼ አውቃለሁ። የዛን እለት ግን ሰውየው የተናገረው ንግግር ሰቀጠጠኝ። አጠገቤ ያገኘሁትን ድንጋይ አንስቼ ከፍ አደረግኩ
“በዚህ አናትህን ሳልከፍልህ ሂድ ከዚህ ጥፋ”
“ምንም የማታውቂ ከሆነ 1000 ብር እሰጥሻለሁ”
ደጋግሜ የብሩን መጠን ለራሴ አነበነብኩት። በህልሜ እንኳን አስቤው የማላውቅ ዓይነት ነበር። ምን ያህል ፍርሃት ቢያርደኝም ከብሩ መጠን ጋር ሲወዳደር ቀለለኝ። በዛው ቅፅበት ምን እንደማደርግ እቅድ አወጣሁ። ጭንቅላቴ እጄን አላዘዘውም። የመኪናውን በር ከፍቼ ገባሁ። ሲኦልን የዛን ምሽት አየኋት። በአለም ላይ ካሉ አስቀያሚ እና ጨካኝ ፍጥረታት መሃከል ዋነኞቹ ወንዶች መሆናቸውም የዛን እለት ገባኝ። ገና የ14 ዓመት ልጅ ነበርኩ፣ በችግር ሰውነቴ ደቆ የእድሜዬን ያህል ያላደግኩ፣ ምንም የማላውቅ………… ሰው እንዴት በህፃን ህመም ይደሰታል? እየተሰቃየሁ በፈሰሰኝ ደም እንዴት ድል እንዳደረገ ይፈነጫል? እሱ ወዙን ሲያዘንብ እኔ እንባዬ ሲዘንብ እንዴት ሰብዓዊነት አይሰማውም? እንዴት በ1000 ብሩ ስቃዬን ይገዛል? እንዴትስ ያ ደስተኛ ያደርገዋል? ይኼ ፍጡር ወንድ ነው።…… በስቃይና በተስፋ ተሰቅዤ ሊነጋ አካባቢ ወደ ላስቲክ ቤቴ ተመለስኩ። እነ አቢን ቀሰቀስኳቸው። …………… ርሃብ የለም። ልመናም የለም። ገበያ ይዣቸው ወጣሁ። ለብሰውት የማያውቁትን ልብስ ገዛሁላቸው። ካፌ ወስጄ ኬክ አበላኋቸው ጠግበን ዋልን።
በዚያው ሰሞን በተረፈኝ ገንዘብ መንገድ ላይ ሲቆሙ የማያቸው ሴቶች የሚለብሷቸውን የመሳሰሉ አልባሳት ገዛሁ። ያደርጉታል ብዬ ያሰብኩትን አደረግኩ።ይመስላሉ ብዬ ያሰብኩትን መሰልኩ። ዘወትር ማታ ሲዖል ደርሶ መልስ የኑሮዬ አንድ ክፍል ሆነ። ገንዘብ እየተቀበልኩ ስቃዬን መጨጥ (ለወንዶቹ እርካታቸውን) የየቀን ስራዬ ሆነ። አሁን ገንዘብ ማግኘት ቻልኩ። እንዳቅማችን ቤት ተከራየን እህትና ወንድሜ ትምህርት ቤት ገቡ።
ወንዶችን አልወድም ገንዘባቸውን እንጂ። ከወንድነታቸው የሚተርፈኝ ስቃይና ላባቸው ነው። ገንዘባቸው ግን የማልፈውን ሲኦል ያስረሳኛል። መንገድ መቆሙን ትቼ ትልልቅ ሆቴል ውስጥ መስራት ጀመርኩ። እንደዋዛ ትልቅ ሴት ሆንኩ። ሃያ አንድ ዓመት ሞላኝ በዚህ ወቅት ነው ካሳሁንን ያገኘሁት የሆቴሉ ደንበኛ ነው።
“ቆንጆ እኮ ነሽ እዚህ ቦታ መገኘት አልነበረብሽም::” አለኝ።
“አየህ ተፈጥሮ ቁንጅናን እንጂ የተደላደለ ህይወትን አብራ አልሰጠችኝም::” መለስኩለት።
“የዛሬ ገቢሽን ልስጥሽና እቤትሽ አርፈሽ ተኚ?”
“ይበዛብሃል::”
“እጥፍ ላድርግልሽ!!”
በራሱ መኪና እቤቴ አደረሰኝ።የጠየቅኩትን ገንዘብ ሳያቅማማ ሰጠኝ። በተደጋጋሚ እንዲህ አደረገ። ለዘመናት የሆቴሉ ደንበኛ ሲሆን ከሆቴሉ ሴቶች ጋር ስሙ ተነስቶ እንደማያውቅ ሰማሁ። ከአመታት በፊት ብቸኛ ወንድሙ ከእርሱ ጋር ተጣልቶ በባህር አቋርጦ ወደውጪ ሀገር ሊሄድ ሲሞክር የመሞቱን መርዶ ከሰማ ጀምሮ በየምሽቱ ይመጣል፣ እራቱን ይበላል፣ ይጠጣል፣ ለሴቶቹ ይጋብዛቸዋል፣… … ወደቤቱ ይሄዳል። ከቀናት በኋላ አብሬው እንዳድር በትህትና ጠየቀኝ። እቤቱ ነበር ይዞኝ የሄደው። ከሱ ጋር ካደርኩ በኋላ ወደ ሆቴል ተመልሼ መሄድ አላስፈለገኝም። በየእለቱ ማታ እቤቱ እጠብቀዋለሁ። ሲነጋ ወደቤቴ እመለሳለሁ።
እንዳገባው የጠየቀኝ ቀን እብደት የቀላቀለው ስሜት ነበር የተሰማኝ። ምክንያቱ ባል ማግኘቴ አይደለም። ባል ወንድ ነው ወንድ ደግሞ የገንዘብ ምንጭ ነው። ከዛ ያለፈ አይደለም ለኔ። ካሳሁን ብዙዎች የሚያውቁት ሀብታም ነጋዴ ነው። …… በቃ!! ብር አገኛለሁ። የትኛውም ወንድ እንደሸቀጥ የሚገዛት ሴት መሆኔ ይቀራል፣ እነ አቢዬ ያለስጋት ትምህርታቸውን ይማራሉ፣ በለውጥ ገላዬን እሰጠዋለሁ። ልቤ ያውቀዋል እንደምፈታው። ተጋባን። እህትና ወንድሜን ይዤ እኔ ገንዘብን እሱ ትዳሩን ስንጠብቅ ኖርን።
*
ሳምንታት አለፉ። ሲመቸው ለቤቱ ፕሮሰስ እንደሚመጣ ቢነግረኝም ካሳሁን አልመጣም ። አልደወለም። በቤቱ ምክንያት ቢመጣና ባየው ተመኘሁ።ቤቱ አስክሬን የወጣበት ቤት መስሎ ረጭ አለ።
የቤቱ ድምቀት፡- ትልቅነቱ፣ የቀለማቱ ስብጥር፣ በውስጡ ያጨቀው ውድ እቃ አልነበረም። ሞገሱን ተገፏል። ካሳሁን የለበትም።
የምግቡ ጣዕም የሰራተኛዋ ጥበብ አልነበረም። ከካሳሁን ጋር የምግብ ጠረጴዛው ላይ መታደሙ እንጂ።
የእንቅልፉ መጣፈጥ የአልጋው ምቾት አልነበረም በካሳሁን እቅፍ ውስጥ ማደሩ እንጂ።
ይሄ ሁሉ የገባኝ አምስት ዓመታት ዘግይቶ ሆነ። የህይወት ዘመን ልምዴንና እውቀቴን ያስከነዳው እውነት ካሳሁን ‘ሴት ልጅ ለገንዘብህ ስትል ትወድሃለች’ ብለው እንደሚያስቡ ወንዶች አልነበረም። ገንዘቡን እንደወደድኩት እንጂ ለእሱ ግድ እንደሌለኝ ያውቃል። ራሱን እንድወደው ነበር አምስት ዓመት ሙሉ ሲጥር የነበረው። የፈለግኩትን ሁሉ እንኳን አጊንቼ እሱ ከሌለበት ባዶ መሆኑን ነበር ያሳየኝ። እድሜውን ካፈራው ንብረት እንደበለጥኩበት አሳይቶኝ እድሜዬን ሙሉ የጓጓሁለት ሀብታምነት ከንቱ መሆኑን ነገረኝ። አብሬው ስኖር ያላየሁት እውነት ያ ነበር።
“ ማንም የኔን ያህል አውቆሽ አያውቅም።” ይለኝ ነበር ሁሌም ሳበሳጨው። አሁን ነው ምን ያህል እንደሚያውቀኝ የገባኝ። ባዶነቴ በፍቅር እንጂ በገንዘብ እንደማይሞላ ያውቅ ነበር። እሱ ብቻ ይሄን ያውቅ ነበር።
ስልኬን አንስቼ ደወልኩለት።
“ሰብሊ ይቅርታ ደንበኞች እያናገርኩ ነው። ቆይቼ እደውላለሁ።” ብሎኝ ስልኩን ዘጋው። ‘ቆይቼ’ ያለው ሰዓት ዘላለም መሰለኝ። ሲሊፐር እንዳጠለቅኩ ተነስቼ ከቤት ወጣሁ። እንዲህ ላብድ የሚመስለኝ ሰዓት እብደቴን የማስታግሰው እህትና ወንድሜ ጋር ስሆን ነበር። አሁን እነሱ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው። እንድረብሻቸው አልፈልገኩም። ደግሞም ካሳሁንን የአባታቸው ያህል ነው የሚወዱት። በቀስታ እየተራመድኩ ማሰብ ጀመርኩ። አሁን ያለኝን ሁሉ አጥቼ ካሳሁንን ብቻ ማግኘት ተመኘሁ። እግሬን ጭንቅላቴ አላዘዘውም። ወደካሳሁን ቢሮ ሮጥኩ። ርቀቱ፣ አለባበሴ፣ የፀጉሬ መንጨፍረር…….. ምኑም ግድ አልሰጠኝም። ትንፍሼ ቁርጥ ቁርጥ እያለ በሩን ከፍቼ ገባሁ። ሁኔታዬ ያስደነገጣት ፀሃፊው መውጣቱን ነገረችኝ። በደከመ ነፍሴ ወደቤቴ ማዝገም ጀመርኩ። የመጣሁት መንገድ ርቀቱ የታወቀኝ ስመለስ ነው። ብዙ መንገድ ሮጫለሁ። መንገዱ ዳር ድንጋይ ላይ ተቀመጥኩ። ለብዙ ቀናት የረባ ምግብ ያለመብላቴን፣ እረፍት ያለው እንቅልፍ ያለመተኛቴን አሁን ነው ያስታወስኩት። ላዳ ይዤ ወደቤቴ ሄድኩኝ። በሩ ላይ የካሳሁንን መኪና ቆሞ ሳየው ‘እሪሪሪሪረ……’ ማለት አማረኝ። በሩጋ ስደርስ እሱ እየወጣ ነበር። ከላይ እስከታች እያስተዋለኝ
“ስደውልልሽ አታነሺም?”
“ስልኬን ጥዬው ነው የወጣሁት። ቢሮህ እኮ ሄጄ…..”
“አሁን መጥታ ነበር ሲሉኝ ነው ወደቤት የመጣሁት። ሰላም አይደለሽም?” ይዞኝ የመጣው ታክሲ ጥሩንባውን አስጮኸው።
“አልከፈልሽውም እንዴ?” ብሎ እጁን ኪሱ ውስጥ እየከተተ ወደታክሲው አመራ። በዛው የማይመለስ መሰለኝ። ድጋሚ ለሳምንታት የማላየው መሰለኝ

👍4👏1
ምን እንዳደረግኩ የገባኝ ካደረግኩት በኋላ ነው። አፌን ጭንቅላቴ አላዘዘውም።
“እሪሪሪሪሪሪ…….” ብዬ አቀለጥኩት። በታክሲውና በኔ መሃከል ባለ እኩል እርቀት መሃል ደንግጦ ዞረ።
“ምን ሆንሽ?” አጠገቤ ዘሎ ደረሰ። ምን እንደምለው ግን ግራ ገባኝ። የእንባዬ ጠብታ መሬቱ ላይ ተከታተለ። ባለታክሲው በጩኸቴ ተደናግጦ መውረዱን ሳይ ደነገጥኩ።
“ምንም አልፈልግም። ሁሉም ይቅርብኝና አትሂድብኝ!!” እንባዬን እየታገልኩ ያወጣሁት ቃል ይሄ ነው።
“አልሄድኩም እኮ ታክሲውን ልሸኘው ነው::”
“አልፈልግም እኮ ነው የምልህ። ቤቱንም ብሩንም ምኑንም አልፈልግም። ሁሉንም አልፈልግም። አልፈልግም በቃ!!” በእንባዬ ታጅቤ አምባረቅኩኝ።
ያልኩት እንዳልገረመው ፤ እንዲህ እንደሚሆን እንደሚያውቅ ሁሉ ፈገግ እንደማለት ብሎ ወደታክሲው ሹፌር ፊቱን አዞረ። መሬት ላይ እየተንከባለልኩ መጮህ አማረኝ። ብሩን ሰጥቶት ሲመለስ በእንባ በተጋረደ ዓይኔ አየዋለሁ።
“ላቆሰልኩህ ቁስል በሌላ በፈለግከው ነገር ቅጣኝ እባክህ ትተኸኝ አት….” ያልኩትን የሰማ አይመስልም። አጠገቤ ከመድረሱ ከንፈሮቼን ጎረሳቸው።
አምስት ዓመት ሙሉ እንዲህ ነበር የሳመኝ?
▪️አለቀ▪️
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ የኔ ምርጦች
አመሰግናለው🙏
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot ጀባ በሉኝ

👍13
#አንድ_ነን
ጠረኔ ሲሸተኝ፤ጠረንህ መሰለኝ
ፊቴን ስዳብሰው፤ፊትህን መሰለኝ
አይኖቼን ሳሻቸው፤ አይኖችህ መሰሉኝ
የራሴው ጆሮዎች፤ የራስህ መስሉኝ
አንድ ነገር ግን፤የኔ የሆነው
ያንተ አልመስልሽ አለኝ
ከሁሉ ነገሬ፤እሱ ግን ቀረብኝ
ትለኝ እንዳልነበር
እኔ ማለት አንቺ፤አንቺ ማለት እኔ
ልዩነት የለንም፤ አንድ ነን ሄዋኔ
ትለኝ እንዳልነበር
ታዲያ ምን ለየው፥መልስልኝ ፍቅሬ
ብዬ ስጠይቅህ፤ገረመኝ ምላሽህ
ድስትና ግጣሙ
የተጋጠሙት፤ልዩ ቢሆኑ ነው
አንድ ላይ የሆኑት
እኔ ማለት አንቺ፤አንቺ ማለት እኔ
በእርግጥም ልክ ነው፤እውነት ነው ሄዋኔ
ፆታችን ቢለያይ፤ምንም አይግረምሽ
ሁልጊዜም አንድ ነው
ነገሬ ነገርሽ፤እንደዚያ ስኖን ነው
እንደ ድስቱ እና፤ ክዳኑን ምንሆነው
አቻም የምንሆነው
ጠረኔ ሲሸተኝ፤ጠረንህ መሰለኝ
ፊቴን ስዳብሰው፤ፊትህን መሰለኝ
አይኖቼን ሳሻቸው፤ አይኖችህ መሰሉኝ
የራሴው ጆሮዎች፤ የራስህ መስሉኝ
አንድ ነገር ግን፤የኔ የሆነው
ያንተ አልመስልሽ አለኝ
ከሁሉ ነገሬ፤እሱ ግን ቀረብኝ
ትለኝ እንዳልነበር
እኔ ማለት አንቺ፤አንቺ ማለት እኔ
ልዩነት የለንም፤ አንድ ነን ሄዋኔ
ትለኝ እንዳልነበር
ታዲያ ምን ለየው፥መልስልኝ ፍቅሬ
ብዬ ስጠይቅህ፤ገረመኝ ምላሽህ
ድስትና ግጣሙ
የተጋጠሙት፤ልዩ ቢሆኑ ነው
አንድ ላይ የሆኑት
እኔ ማለት አንቺ፤አንቺ ማለት እኔ
በእርግጥም ልክ ነው፤እውነት ነው ሄዋኔ
ፆታችን ቢለያይ፤ምንም አይግረምሽ
ሁልጊዜም አንድ ነው
ነገሬ ነገርሽ፤እንደዚያ ስኖን ነው
እንደ ድስቱ እና፤ ክዳኑን ምንሆነው
አቻም የምንሆነው
ልብሽ ከወደደኝ በዪኝ ወድካለሁ
ያው እድለኛ ነሽ መውደድ መታደል ነው።
::::::::
ካልወደድሺኝ ደሞ ውስጥሽ አያመንታ
ፍቅር በፍቅር እንጂ ሲሆን በይሉኝታ
ፍሬ መች ያፈራል የማታ የማታ።
::::::::
ግን እየወደድሺኝ አትበይ አልወድክም
ስሜትን በማፈን ጎጆ ፀንቶ አያውቅም።
::::::::
ሳትወጂኝም ደሞ አትበይ ወድካለሁ
ይህንም ታውቂያለሽ ...
ማስመሰል ካረጀ ጧሪ ዘመድ የለሁ።
:::::::::
እናም እኔ ዛሬ ላንቺው ሹክ የምልሽ
አልስማማ ብለው አፍሽና ልብሽ
ቡጢ ተጨባብጠው ከፀፀት ሳይጥሉሽ
ጎጆሽ እንዲቃና ፍቅር ተረብርቦ
ጥሪና አስማሚያቸው .....
ልብሽን ካራምባ አፍሽን ከቆቦ።
ያው እድለኛ ነሽ መውደድ መታደል ነው።
::::::::
ካልወደድሺኝ ደሞ ውስጥሽ አያመንታ
ፍቅር በፍቅር እንጂ ሲሆን በይሉኝታ
ፍሬ መች ያፈራል የማታ የማታ።
::::::::
ግን እየወደድሺኝ አትበይ አልወድክም
ስሜትን በማፈን ጎጆ ፀንቶ አያውቅም።
::::::::
ሳትወጂኝም ደሞ አትበይ ወድካለሁ
ይህንም ታውቂያለሽ ...
ማስመሰል ካረጀ ጧሪ ዘመድ የለሁ።
:::::::::
እናም እኔ ዛሬ ላንቺው ሹክ የምልሽ
አልስማማ ብለው አፍሽና ልብሽ
ቡጢ ተጨባብጠው ከፀፀት ሳይጥሉሽ
ጎጆሽ እንዲቃና ፍቅር ተረብርቦ
ጥሪና አስማሚያቸው .....
ልብሽን ካራምባ አፍሽን ከቆቦ።
❤2
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_አንድ
:
✍ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
“ተሳፋሪዎቻችን ይህ የበረራ ቁጥር 206 ነው… … ” ጭንቅላቷ እየሸወዳት እንደሆነ የማውቀው እንዲህ ማለት ስትጀምር ነው። በግልቡ እብደቷ እየጀመራት ነው ማለት ነው። እናቴ ናት!!
ይሄን ሀረግ ማለት ከጀመረች ትርጉሙ የዛሬ 20 ዓመት ወደ ኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆስተስ የነበረችበት ዘመን ላይ ናት… … ማርጀቷን አታውቅም፣ እኔንም አታውቀኝም ፣ ባሏ እሷን ትቶ ጓደኛዋን እንዳገባ አታውቅም ፣ ንብረቷን እንደተቀማች አታውቅም ፣ ጡቶቿ እንደተቆረጡ አታስታውስም ………… አንዳንዴ ራሷንም አታውቅም ~ ሰው ካላያት ራሷን ትጎዳለች። እብደቷ ሲነሳባት መከራዬ ናት። ምሬቴ ናት። ስቃዬ ናት። …… ጥለሻት ጥፊ ጥፊ ይለኛል። ጭንቅላቴን በቅውሰቷ ትዋጀዋለች። ብገላገላት የምታስመኘኝ መንቻካ አሮጊት ትሆናለች። መድሃኒቷን አትውጥልኝም፣ እንድነካት አትፈቅድልኝም ፣ አምናኝ እንቅልፏን አትተኛም…… ከየት የምታመጣው እንደሆነ የማይገባኝ ጉልበት አላት…… ታጠፋበታለች። እንደእኔ የምትጠላውና የምትፈራው አይኖራትም።
“የማላውቅሽ መስሎሽ? ቅናታም መርዘኛ! …… መድሃኒቱን በምግብ ለውሰሽ ልታበይኝ? አንድዬን ልትወስጂብኝ? እኔ አይናለም በህይወት ሳለሁ ቤቴ ሊፈርስ?” ትለኛለች ያገኘችውን እቃ እየወረወረችብኝ። አንድዬ የምትለው አባቴን ነው። የድሮ ባሏን።
“ማነሽ ደግሞ አንቺ? ወደ ቤቴ ውሰዱኝ… …… ኡኡኡኡኡ… … መድሃኒት ሊያበሉኝ ነው።……”
ዶክተሯ መጥቶ መርፌዋን እስኪወጋት በሷ እብደት እኔ አብዳለሁ። ስትረጋጋልኝ እብዷ እናቴን ከጠባቂ ጋር እቤት አስቀምጬ እወጣለሁ። …… ያበደች እናት እንደሌላት፣ አንዲት የኑሮ ሰበዝ እንዳልጎደለባት ፣ እንደደላት ሴት ሁኜ…… አዘውትሬ እንደምለብሰው ሙሉ ልብሴን አጊጬ ወደ ስራዬ እሄዳለሁ።
“ ኪዳነ ምህረት ምን በደልኩሽ? ምነው ጌታዬ ስቃዬን ቆለልክብኝ? ምናለ ብትገላግለኝ?” ስትል ደግሞ ትርጉሙ ወደ አሁን ተመልሳለች ማለት ነው። ያሳለፈችውን ስቃይ እያስታወሰች መታመም ጀምራለች ማለት ነው። እብደቷ ሲተዋት ታስለቅሰኛለች። ሆዴ ኩርምትምት ይልላታል። እንዳሰቃየችኝ ታውቀዋለች። ላበደችባቸው ቀናት እንግልቴ ስትከፍለኝ ጡት የለሽ ደረቷ ላይ ለጥፋኝ ታባብለኛለች። ምን መስማት እንደምትፈልግ አውቃለሁ።
“እማ በህይወት እስካለሽ አልተውሽም። ምንም ብታደርጊ እችልሻለሁ።” እላታለሁ። አትመልስልኝም። ብቻ ጨምቃ አቅፋኝ ትንሰቀሰቃለች። የአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታል መግባት ሞቷ ነው። ትለምነኛለች። ሁለቴ ገብታ ታውቃለች። ይብስባታል እንጂ አይሻላትም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰውነቷም እየደከመ ህመሟም እያዛላት ነው። ትናንትና የሚሚን የሰርግ መጥሪያ ወረቀት ካየች ጀምሮ የበረራ ቁጥሯን መቁጠር ጀምራለች።
ሚሚ አባቴ ከሌላ ሚስቱ የወለዳት እህቴ ናት። ሰርጉን እኔም እናቴም እንደማንሄድ ያውቃሉ። ለምን እንደማይተውን አላውቅም። ባገኙት ሰበብና አጋጣሚ እኔና እናቴ ሰላም እንዳይሰማን ይታትራሉ። እማዬን ለማረጋጋት እማይኮነውን ሁሉ እየሆንኩ እንፈራገጣለሁ። በሚሚ ሰርግ ጉዳይ ግን ከእማዬ ይልቅ እንዳላብድ መጠበቅ ያለብኝ እኔ ነበርኩ። ምክንያቱም ሚሚ የምታገባው የልጅነት ፍቅረኛዬን ነው። የሰርግ ወረቀቱን ለእኔ አምጥተው የሰጡበት ምክንያትም እንደእናቴ እንዳብድላቸው ነው። ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ……
እኔ በሙያዬ ጠበቃ ነኝ። ……… በአንድ ቅሌታም ከፍተኛ ባለስልጣን ኬዝ ሰበብ ስሜ በሀገሪቷ የናኘ ጠበቃ…… አስታወሳችሁትኣ? አያቱ ከሚያክሉ አሮጊቶች ጋር የሚወሰልተው ሰውዬ…… አዎን ለደፈራቸው የ70 ዓመት ምስኪን አሮጊት የቆምኩት እና ያስፈረድኩበት እኔ ነበርኩ። ያ መርገምት ካርቱሚስት በአንደኛው ሳምንታዊ ጋዜጣ ላይ ጥርስ የሌላት ድዳም እና ምላሷ ከፒያሳ እስከመገናኛ የሚደርስ አሮጊት አድርጎ የሳለኝ… … አዎን እኔ ነኝ። ……… አሁን ማን እንደሆንኩ አወቃችሁ?
“ቢሮሽ ሰው እየጠበቀሽ ነው።” አለችኝ ወይኗ ገና ከመግባቴ።
“ደህና አደርሽ ወይኗ።” ብዬ እየተጣደፍኩ ስገባ
“አባትሽ ነው። አባቷ ነኝ ነው ያለው። አባት እንዳለሽ አልጠረጠርኩም ነበር። ……” አለኝ ፍትህ።
“አባትሽ?” ተንደርድሬ ቢሮዬ ገባሁ። ደንግጦ ተነሳ። በዓይኔ ካየሁት እንኳን ሰባት ዓመት ሆኖኛል። ምናባቱ ሊሰራ ነው አሁን የሚፈልገኝ? ጭራሽ ቢሮዬ ድረስ?
🌑ይቀጥላል➡️
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ የኔ ምርጦች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ በ Like ጭንቅንቅ አድርጉኝ እስቲ 👍 😁
አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን

👍9
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_ሁለት
:
✍ደራሲ:- ሜሪ ፈለቀ
:
:
:
...“አቤት?” አልኩት ለሰላምታ የዘረጋውን እጁን ችላ ብዬ ወንበሬ ላይ እየተቀመጥኩ። ፀጉሩ አልፎ አልፎ ከመሸበቱ ውጪ ብዙም አልተለወጠም።
“ደህና ነሽ ሚሚሾ?”
“ምን ፈልገህ ነው የመጣኸው? ደህና መሆኔ አሳስቦህ አይሆንም መቼም!! የልጅህ ሰርግ ጥሪ ወረቀት እንደደረሰኝ ለማረጋገጥ ከሆነ ደርሶኛል። እማም ደርሷታል። ጨርቄን ጥዬ እንደሆን እንድታይ ሚስትህ ከሆነ የላከችህ። ሂድና ንገራት! ረስተናችኋል። እባካችሁ ከህይወታችን ውጡ። እና ከቢሮዬም ውጣ……” መናደድ አልፈልግም። ግን አስቤያቸው አለመናደድ ያቅተኛል። ሁሌም እንዲህ ናቸው። ስተዋቸው አይተውኝም። ዝቅጥ ብለው ያዘቅጡኛል። ስለእውነቱ የሁሉም ክፉ ነገር ሀሳብ ባለቤት ሚስቱ ናት። እሱ መልሱ ዝምታ ነው። ጋግርት። ግን ከእርሷ ቅጥ የለሽ ክፋት በላይ የሱ ዝምታ ይሰብረኝ ነበር።
“ለግሌ ጉዳይ ነው የመጣሁት።” አለኛ አፉን ሞልቶ።
“ሰውየው ከእኔ ጋር የሚያገናኝ የግል ጉዳይ የለህም። እባክህ መጥፎ ነገር አታናግረኝ። ውጣልኝ……”
“የውብዳርን ልፈታት ነው። በመሀከላችን ብዙ ጣጣዎች ስላሉ ጠበቃ ያስፈልገኛል። …” ወደ በሩ እየተራመደ “… ትረጂኛለሽ ብዬ ተስፋ ነበረኝ። ጭራሽ ልትሰሚኝ እንኳን ፈቃድሽ ካልሆነ ምን አደርጋለሁ? ባልደረቦችሽን ላማክራቸዋ?” በሩን ከፍቶት ወጣ። ምን? እኮ የቤተሰቤን ጉድ ባልደረቦቼ ሊሰሙ? በተለይ ደግሞ ፍትህ? ኡኡኡ ልል ትንሽ ነበር የቀረኝ። በሩጫ ተከተልኩት። አጠገቡ ስደርስ እልህም ንዴትም አነቀኝ። ጮኬ ማውራት ግን አልችልም። እኔን የሚያነድበት አንዲት የነገር ሽራፊ ለሚፈልገው ፍትህ ራሴን አላጋልጥም።
“ምንድነው ግን ከኔ የምትፈልገው? ምን አድርጌ ነው እየተከታተላችሁ ልታጠፋኝ የምትተጉት? በምትወዳት ልጅህ ይሁንብህ ተወኝ?” አልኩት ጥርሴን ነክሼ ከእንባዬ እየታገልኩ። ሁሌም እንደዚህ ነው። ቤተሰቤን አስመልክቶ መጨረሻዬ እንባ ነው። ተሸናፊ ነኝ። አሸናፊዎች ናቸው። በፈለጉበት ቀን መጥተው ከዓይኔ እንባዬን ለመቅዳት የመብታቸው ያህል ቀላል ነው። የፈለጉትን ይቀሙኛል። …… እኔ ይህቺ ነኝ! የአደባባይ አንበሳ! የቤቴ አይጥ ነኝ።
“አንድ ጊዜ ብቻ ቁጭ ብለሽ እንድትሰሚኝ እፈልጋለሁ። እውነቱን ላስረዳሽ እፈልጋለሁ። የምፈልገው እሱን ነው።”
“እባክህ ሂድልኝ። እባክህ ተወኝ። አንድ ያልነጠቃችሁኝ ነገር ስራዬ ነው። አንድ የእናንተ የክፋት እጅ ያልደረሰበት ቦታ የስራ ቦታዬ ነው። እባክህ ልለምንህ እሱን ተውልኝ።………” ከየት መጣ ሳልለው ፍትህ አጠገባችን ደርሶ
“እንዴ አባባ ሻይ ቡና ምን ይምጣሎት?…” እየለፈለፈ እያለ አየኝና ደነገጠ። “…… እንዴ ቦስ ችግር አለ እንዴ?ምነው የተፈጠረ ነገር አለ?” አብረን ስራ የጀመርን ሰሞን ሊያናድደኝ ሲፈልግ ‘ቦስ’ እያለ መጥራት ጀመረ። ዛሬም ድረስ እንደዛ ነው የሚጠራኝ። ዝም ካልኩት መጠየቁን እስከማታ አያቆምም።
“ፍትህ ዘወር በልልኝ!” ብዬ ጮህኩበት።
ለምኜም ተቆጥቼም አባቴን ሸኘሁት። ሌላ ቀን እንደሚመለስ ነግሮኝ ሲወጣ ያዘነልኝ ይመስል ነበር። የውላችሁ…… እዚህ ተረክ ውስጥ ማንም ጥሩ ማንም መጥፎ የለም። ሁሉም ጥሩ አይደሉም። ሁሉምም መጥፎ አይደሉም። እናቴን ጨምሮ!! ስለቤተሰቦቼ ሁሉንም ባላውቅም አንዳቸውም ንፁህ አይደሉም። የተዘራሩትን ነው የሚተጫጨዱት። ለነገሩስ የሰው መቶ ፐርሰንት ጥሩ ወይ መጥፎ የታለው? ጥሩ የምንለው ሰው ክፋቱን በጥሩነቱ የሸፈነ። ክፉ የምንለውስ ጥሩነቱን በክፋት የሸፈነ አይደለምን? እንጂማ ሁሉም የክፋትና የመልካምነት ስብጥር አይደል? ጎልቶ ባሳየው ይጠራበታል።
እኔስ? ባልበላሁት ጉሮሮዬን እየቧጠጠ ያስመልሰኛል። ያልዘራሁት እሾህና አሜኬላ እየበቀለ እድሜዬን ሙሉ ሲያንቀኝ አለ። ራሴ ከዘራሁት መልካም ዘር ቀድሞ እነሱ የዘሩት እንክርዳድ ደርሶ እበላዋለሁ። እንደአረቄ አዙሮ ይደፋኛል።
“ቦስ ቡና ላምጣልሽ?” ቢሮዬ መጥቶ ነው።
“እባክህ ፍትህ… … እየደጋገምክ የቢሮዬን በር መክፈት አቁም።”
“Am just worried… … የሆንሽውን እያየሁ ዝም ብዬ ልቀመጥ?”
“አዎን እንደሱ አድርግ። ዝም በለኝ።”
“እሺ እቤት ሄደሽ እረፊ። እዚ ሆነሽ ምንም ነገር በትክክል አትሰሪም።” አለኝ። እማ ትዝ አለችኝ። ኮቴን አንስቼ አልፌው ሄድኩ። እቤት ስደርስ የቀረበላት ምግብ ላይ ትተክዛለች። የማይሰማ ነገር ታጉተመትማለች። ሰራተኛዋ ቆማ እየጠበቀቻት ነበር።
“እማ እባክሽ ዛሬ አይሆንም። ዛሬ ደህና ሁኚልኝ። ዛሬ አልችልም። አልችልም!!”
ቀና ብላ አየችኝ። “አንቺ ደግሞ ማነሽ? የውብዳር ናት የላከችሽ? ” አምላኬ ሆይ አይሆንም! አይሆንም!!
“አይደለም እማ አንዱዓለም ነው የላከኝ።” ከቃላቶቹ ጋር እንባዬ ይወርዳል። እሷ የእሱ ስም ከተነሳ እያለቀስኩ ይሁን እየሳቅኩ ግድ የላትም። ሲጀምራት ሰሞን የእርሱ ስም ያረጋጋታል። እሱ ይሄን ማወቁን እንጃ! እብደቷም መድሃኒቷም እሱ ነው።
“እና ምን አለሽ?”
“የኔ ጨረቃ ናፈቅሽኝ እኮ! ባክሽ ይሄ ስራ ይቅርብሽና ሁሌ ማታ ማታ ልይሽ?………”ባሏ እሷ ስራ ስትሄድ የፃፈላት ደብዳቤዎች ናቸው። እሷም በቃሏ ሁሉንም ታውቃቸዋለች። እኔም እንደዛው። ለዓመታት በቃሌ አነብንቤላታለሁ። አብራኝ ቃሎቹን እያጣጣመች እንቅልፍ ይወስዳታል። ……… ዛሬም ለአንድ ሰዓት ያህል የባሏን መልእክት ነግሪያት እሷ ሶፋው ላይ ፈገግ እንዳለች እንቅልፍ ጣላት።
🌑ይቀጥላል➡️
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ የኔ ምርጦች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ በ Like 👍የሚለውን ይጫኑ

👍9❤1
#አሜን_በይ_ልርገምሽ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፀጉርሽን ይምለጠው ዳግም ላይበቅልልሽ
፡፡፡፡
ይቁሰል ይድማ ደግሞም የራስ ቅልሽ
፡፡፡፡
አይኖችሽ ይፍሰሱ ትል ይውጣ ከውስጡ
፡፡፡፡
ውበታቸው ይጥፋ ወዛቸውን ይጡ
፡፡፡፡
ይቆረጥ አፍንጫሽ ማሽተት እስኪያቅተው
፡፡፡፡
ማራኪ መአዛን ማሽተት እስኪያቅተው
፡፡፡፡
አሜን በይ ልርገምሽ
፡፡፡፡
ውበትሽን ያጥፍው ሰው አትምሰይ ፍቅሬ
፡፡፡፡
ገላሽ ተልቶ ደምቶ ሆኖ የደም ጎሬ
፡፡፡፡
ብዙ ቀንድ እንዳለው የሚዋጋ በሬ
፡፡፡፡
አስፈሪ እንስሳ ያስመስልሽ አውሬ
፡፡፡፡
አሁንም ልርገምሽ
፡፡፡፡
ጠረንሽን ያጥፋው ሰው ሰው አያሰኝሽ
፡፡፡፡
እንኳን የአዳም ዘር ጅብም አይመኝሽ
፡፡፡፡
ጥርሶችሽ እረግፈው በድድ ያስቀርሽ
፡፡፡፡
ሰው ፊት መሄድ መቆም መሣቅ ያስፈራሽ
፡፡፡፡
አይለይ ውበትሽ ከሰል ሁኚ ያጥቁርሽ
፡፡፡፡
ያኔ ያለ ግፍያ ብቻዬን ላፍቅርሽ።
❤️❤️❤️
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፀጉርሽን ይምለጠው ዳግም ላይበቅልልሽ
፡፡፡፡
ይቁሰል ይድማ ደግሞም የራስ ቅልሽ
፡፡፡፡
አይኖችሽ ይፍሰሱ ትል ይውጣ ከውስጡ
፡፡፡፡
ውበታቸው ይጥፋ ወዛቸውን ይጡ
፡፡፡፡
ይቆረጥ አፍንጫሽ ማሽተት እስኪያቅተው
፡፡፡፡
ማራኪ መአዛን ማሽተት እስኪያቅተው
፡፡፡፡
አሜን በይ ልርገምሽ
፡፡፡፡
ውበትሽን ያጥፍው ሰው አትምሰይ ፍቅሬ
፡፡፡፡
ገላሽ ተልቶ ደምቶ ሆኖ የደም ጎሬ
፡፡፡፡
ብዙ ቀንድ እንዳለው የሚዋጋ በሬ
፡፡፡፡
አስፈሪ እንስሳ ያስመስልሽ አውሬ
፡፡፡፡
አሁንም ልርገምሽ
፡፡፡፡
ጠረንሽን ያጥፋው ሰው ሰው አያሰኝሽ
፡፡፡፡
እንኳን የአዳም ዘር ጅብም አይመኝሽ
፡፡፡፡
ጥርሶችሽ እረግፈው በድድ ያስቀርሽ
፡፡፡፡
ሰው ፊት መሄድ መቆም መሣቅ ያስፈራሽ
፡፡፡፡
አይለይ ውበትሽ ከሰል ሁኚ ያጥቁርሽ
፡፡፡፡
ያኔ ያለ ግፍያ ብቻዬን ላፍቅርሽ።
❤️❤️❤️
👍2
👆👆 ለላይኛው ግጥም ከቻናሉ ተከታታይ የተላከ የመልስ ግጥም ከ #kaki
--------------------------------------------------------------
#አሜን_ብልህ_እማ...
ፀጉሬ ቢመለጥ ዳግም ባይበቅልልኝ
ቢቆስል ቢደማ ደሞም ባይድንልኝ
አይኖቼ ቢፈሱ ትልቢወጣ ከውስጡ
ውበታቸው ቢጠፋ ወዛቸውን ቢያጡ
ቢቆረጥ አፍንጫዬ ማሽተት እስኪየቅተው
ማራኪ መአዛ ማሽተት ቢያቅተው
ውበቴ ቢጠፍ ሰው ባልመስል ፍቅሬ
ገላዬ ደምቶ ተልቶ ቢሆን የደም ጎሬ
ብዙ ቀንድ እንዳለው የሚዋጋ በሬ
አስፈሪ እንስሳ ቢያስመስለኝ አውሬ
ጠረኔ ቢጠፍ ሰው ባያሰኘኝ
እንኩዋን የአዳም ዘር ጅብ ባይመኘኝ
ጥርሶቼ እረግፈው በድድ ቢያስቀኝ
አሜን ብልህ እማ
ትተኸኝ ትሄድና ብቻዬን ቀራለው
በረገምከኝ መርገምት ላይንክ እቀፍለው
አንተ የወደድከው ፀጉሬን እኮ ነው
አንተ ያማለሉህ እይኖቼኮ ናቸው
ጠረንህን ሚያሸተው አፍጫዬኮ ነው
ገላዬን እኮ ነው አንተ የምትነካው
ያንን የደምጎሬ እንደምን አሰብከው
እንደምን ተመኘህ አስፈሪ እንስሳ
ብዙ ቀንድ ያለው አስፈሪ አበሳ
ጠረኔ ቢጠፍ ምኔን ታሸታለህ
እንዴትስ ብለህ እኔን ትቀርባለህ
ጥርሶቼ ቢረግፍ በምን ትማረካለህ
የአዳም ዘር ቢርቀኝ በማን ትኮራለህ
አሜን ብልህ እማ
ፍቅሬ ሳታስበኝ
ዳግም ላትመኘኝ
ዞረ አንዴ ላታየኝ
አሜን ብልህ እማ
ምንም ሳታንገራግር አይንህን ጨፍነህ
እያንገፈገፈ ትተከኝ ትሄዳለህ።
አስተያየታችሁን ላኩልኝ 👉 @atronosebot

👍3
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_ሶስት
:
✍ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
:
...ከሀያ ዓመት በላይ የሆናቸው በወጣትነቷ ውዷ ከፃፈላት ደብዳቤዎች ዛሬም ድረስ አብረዋት ያሉ እያንዳንዱን በቃሏ የምታውቃቸው 23 የፍቅር ደብዳቤዎች አሏት። ሁሉንም ከነተፃፉበት ቀን ሳይቀር እኔም በቃሌ አውቃቸዋለሁ። እንደዚህ ከፍ ያለ ፍቅር መቋጫው እንዴት አስከፊ መለያየት እንደሆነ ሳስብ ይገርመኛል። እሷ ዛሬን ማሰብም መኖርም አትፈልግም። በትናንት ትዝታዋ ውስጥ ተወሽቃ ቀኖቿን መጨረስ ነው የምትፈልገው። እናቴ ያልገባት ነገር የሷን ትዝታ ስተዘትዝ የእኔም ቀኖች ከመድረሻቸው እየተቀነሱ እንደሆነ ነው።
“ቦስ ሰላም ነሽ?” ለሶስተኛ ጊዜ ስልክ ደውሎ ነው።
“ደህና ነኝ አልኩህ እኮ ፍትህ! ነገ እንገናኛለን። በቃ ደህና እደር!”
“እሺ ምግብ በልተሻል? አድራሻሽን ከነገርሽኝ ያለሽበት ላምጣልሽ?”
“ፍትህ ምግብ በልቻለሁ። ራሴን መንከባከብ አያቅተኝም። ባክህ እረፍ!”
ፍትህ ማለት በብዙ የሚያበሽቀኝ በበሽ የሚያበግነኝ ባህሪ ያለው ነው። ቢሯችንን የከፈትነው ከሁለት ምርጥ ጠበቆች ጋር በጋራ ነበር። አንደኛው ከወራት በፊት በግሉ ምክንያት ስራ ሲያቆም ፍትህን የቅርብ ጓደኛውና ጎበዝ ጠበቃ መሆኑን አሳምኖን ነው አብረን መስራት የጀመርነው።ፍትህ ቅንጡና ለብዙ ነገር ግድ የለሽ ነው። ለምን በየዕለቱ ቢሮ እንደሚገባም ሆነ ለምን ጠበቃ መሆን እንደፈለገ አይገባኝም። ምክንያቱም ለስራው ፍቅርም ትጋትም የለውም። ገንዘብ የሚያሳስበው ሰው እንዳልሆነ ለመገመት ደግሞ የሚጠቀማቸውን ቁሶችና አላስፈላጊ ወጪዎቹን ማየት በቂ ነው።
ከነገረስራው ሁላ ሴትን ልጅ ከአልጋ ወርዳ ማሰብ የሚከብደው ብሽቅ መሆኑ ያናድደኛል። ስማቸውን እንኳን በውል ከማያስታውሳቸው እልፍ ሴቶች ጋር ነው።
“ባል ሳታገቢ ነው የምታረጂው ታስታውቂያለሽ።” ይለኝ ነበር ስራ የጀመረ ሰሞን እራት ልጋብዝሽ ብሎኝ እንቢ ስላልኩት ሲያበሽቀኝ።
“አንቺ የሴት ልስላሴ የለሽም። ነገር ላይ እርርርር ትያለሽ። ጠብሰሽ ማወቅሽንም እንጃ።” ይለኛል በሌላ ቀን። ልስማው አልስማው ግድ የለውም ይለፈልፋል። ልቀየመው ልናደድበት ግድ የለውም አፉ እንዳመጣለት ነው የሚመርገው።
“አለቃ አለቃ መጫወት ትወጃለሽ። ሁሉም ቦታ ዋና አክተር መሆን አይደብርሽም?” ይለኛል በምንም ጉዳይ አስተያየት ልሰጠው ከሞከርኩ።
“በራስሽ ትመፃደቂያለሽ። ራስሽን ለዓለም ህዝብ እንደተላከ መሲህ ነው የምትቆጥሪው። ሁሌ ልክ እንደሆንሽ፣ ካንቺ በላይ አዋቂ እንደሌለ ነው የምታስቢው።……” ብሎኛል ጠጥቶ አድሮ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ያመለጠው ቀን ልክ እንዳላደረገ ስነግረው። ለምን እንደሆነ አይገባኝም ብቻ የምሰራው ሁሉ አይዋጥለትም። እንደማንኛዋም ሴት መሆኔን ሳይጠቁመኝ አያልፍም። እኔን የሚናገርበት ስህተት ያገኘብኝ ከመሰለው አለቀልኝ። በነገር ሲተረኩሰኝ ይሰነብታል።
አባቴ ቢሮ መጥቶ ዓይኖቼ በእንባ ተሞልተው ሳወራው ካየኝ ቀን ጀምሮ የማውቀው ፍትህ አልሆነም። ምናልባት ግትርና ደንዳና የምትመስለው ሴትዮ ተሸንፋና ተመሳቅላ ስላያት የቆለላት ሴት ተንዳበት ግራ ገብቶታል ወይም ደካማ ጎኔን አውቆ ሊሳለቅ እየተከታተለኝ ነው አልያም አሳዝኜዋለሁ። ሁሉም እንዲሆኑ የማልፈልጋቸው ናቸው።
“ቦስ ቅድም አባትሽ መጥተው ነበር።” አለኝ ከፊቴ ላይ ስሜቴን እየዘገነ
“እና?” አልኩት ምንም ያልተሰማው ለመምሰል ዘና እያልኩ።
“እኔን ፈልገው ነው የመጡት። አንቺ ፍርድ ቤት መሆንሽን አስቀድመው አረጋግጠው ነው የመጡት።” አነጋገሩ ‘ምን ማድረግ እችል ነበር?’ የሚል አንድምታ አለው። ፀጥ አልኩ። ለሰከንዶች ጭንቅላቴ ረጭ አለ። ማሰብ አቆምኩ።
“ከእናትሽ ጋር መፋታት እንደሚፈልጉ እና አንቺ እንቢ ስላልሻቸው ሊያማክሩኝ ነበር። ጠበቃቸው እንድሆን ይፈልጋሉ።” የውብዳርን እናትሽ ማለቱ ብዙ እንዳላወሩ ገባኝ። …… ጭንቅላቴ ወና ስለሆነ የምጠይቀውም የማወራውም አልነበረኝም።
“የእህትሽን የሰርግ ካርድ ሰጥተውኝ ነው የሄዱት። እንዳልቀርና ብዙ የሚያጫውቱኝ ነገር… …” ቀጠለ…… “የሆነ ነገር በይኛ ቦስ?” ምን ልበለው? አትሂድ? እንደውም አባቴን አታናግረው? ለአባቴ ጠበቃው ከሆንክ ስለእኔ ብዙ ታውቃለህና ይቅርብህ? እናስ? ደከማ ጎኔ እንዳይታወቅ? ፍትህ እንዳያሸንፈኝ? በስራዬ የሚያውቁኝ ሁሉ የሚያውቋትን ጠንካራ እና በራሷ የምትተማመን ሴት ዙፋን ለማስጠበቅ?
ስራዬንም ቢሮዬንም እወደዋለሁ። ምክንያቱ ደግሞ ከቢሮዬ ውጪ ያለውን ፣ ያለፈውንና የሚመጣውን የማላስበው እዚህ ነው። እዚህ ሌላ ሴት ነኝ። አንድ ደራሲ መፅሃፍ ሲፅፍ የሚቀርፃቸውን ገፀ ባህሪያት ኑሮ ሲያበጅ ራሱን በፈጠራቸው ገፀ– ባህርያትና ዓለም ውስጥ የሚደብቅ ይመስለኛል። ለኔ ስራዬ እንደዛ ነው። በማገለግላቸው ደንበኞቼ ውድቀትና መነሳት ውስጥ ራሴን ደብቃለሁ። አንዳንዱ በመጠጥ አንዳንዱ በሌላ ሱስ ያደለው ደግሞ በሚወደው ሰው እና በፍቅር ውስጥ ራሱን እንደሚደብቀው።
ፍትህ የአባቴ ጠበቃ ሆነ ማለት ስለቤተሰቦቼ እኔ የማላውቀውንም ጉዳይ ጭምር አወቀ ማለት ነው። ያ ማለት ደግሞ ቢሮዬ ውስጥ የነበረኝ በራስ መተማመን እና ነፃነት ጠፋ ማለት ነው። ከዛ ቢሮ መግባት እጠላለሁ። ያኔ ራሴን የምሸሽግበት ቦታ አይኖረኝም። አደባባይ ተሰጣሁ ማለት ነው። ያኔ ለመንኮታኮት ተምዘገዘግኩ ማለት ነው።
“እና ትሄዳለህ? ማለቴ ሰርጉን?” አልኩት በመጨረሻ። ሰርጉ የድሮ ፍቅረኛዬና የእህቴ እንዳልሆነ ሁሉ እንደማንኛውም ‘ሰርጉን’ ብዬ
“ለምን እቀራለሁ?”
“ጠበቃው ልትሆን ወስነሃል ማለት ነው?”
“እንዳልቀበል የሚያደርገኝ ምክንያት አለሽ?”
“አይ ምክንያት የለኝም። ግን ባትቀበለው ደስ ይለኛል።”
“እኮ ለምን?” ለምንም ነገር ግድ የሌለው ሰው ይሄ ኬዝ እንዲህ ሀሳቡን የሰረቀው ከእኔ ጋር ስለተያያዘ ብቻ ነው። ለ‘ለምኑ’ መልስ የለኝም።
🌑ይቀጥላል➡️
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ የኔ ምርጦች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ Like👍👍 ያድርጉ

👍8❤1
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_አራት
:
✍ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
:
....“ልትነግሪኝ የምትፈልጊው ነገር አለሽ?”
“ማለት? ስለምን?”
“እኔ እንጃ ቦስ አባትሽ እዚህ ቢሮ እግራቸው ከረገጠ ቀን ጀምሮ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ፍፁም ልክ አይደለሽም። ያዘንሽ ያዘንሽ ፣ የተከፋሽ ፣ የሆነ ነገር ያደከመሽ አይነት ነው የምትመስዪው።” ሲለኝ ለቅፅበት ያደከመኝን ሁሉ ልነግረው ዳድቶኝ ነበር።
ራሴን አውቄ ሀላፊነትን መሸከም ከቻልኩበት ጊዜ ጀምሮ ለሚያውቀኝ ሰው ወይም በምንም አጋጣሚ ቢሆን ድጋሚ ላገኘው ለምችለው ሰው ስለራሴ ተናግሬ አላውቅም። ነገር ውስጤ ተቆልሎ የሆነ ዓይነት እምቅ ሀይል ሆኖ እንደ ኒውክለር ሊፈነዳ የመሰለኝ ወቅት ላይ አንድ ሶስቴ ከዛን ቀን በኋላ ፊታቸውን አይቻቸው ለማላውቃቸው ሰዎች የተሰማኝን ዝርግፍግፍፍፍ አድርጌ ከመፈንዳት ተርፊያለሁ። አንዷ ‘ነገ አረብ ሀገር ልሄድ ነው።’ ያለችኝ ፀጉር ቤት ያገኘኋት ሴት ናት። ፀጉራችንን ተስርተን ስንወጣ ለማኪያቶ ካፌ ተቀምጠን ያወራኋት። ሁለተኛው ናዝሬት ለስራ ሄጄ ያረፍኩበት ሆቴል ብቻዬን ራት ስበላ አይቶኝ ‘እንብላ’ ባለኝ ሰበብ ያወቅኩት ጎልማሳ ነው። (ሊበላኝ(ሊያባላኝ) ባሰበ ምሽቱን የተበላው።) ሶስተኛው ከቂሊንጦ ስመለስ ሊፍት የሰጠኝ ሽማግሌ ነው። አንዳቸውንም ከዛ በፊትም ሆነ ከዛ በኋላ አይቻቸው አላውቅም። ስሜን አያውቁም ፣ ማን መሆኔን ፣ የት መሆኔን አያውቁም……… ሳወራላቸው ነገ ሲያዩኝ ምን ይሰማቸዋል? አልልም…… ሳለቅስ ወይ ስዝረከረክ ይዳኙኛል አያሰጋኝም…… በነሱ ፊት መሸነፌ ወይ ተስፋ መቁረጤ ድክመቴ አይሆንም። …… ለምንም ግድ የለኝም። ልግባቸው ላደናግራቸውም ጉዳዬ አይደለም። የተሰማኝን በሙሉ ዘርግፌ ተንፍሻለሁ።
ለሚያውቀኝ ሰው እንደዛ አላደርግም። ለሚያውቁኝ ሁሉ(ከቤተሰቦቼ ውጪ) ያቺ አልቅሳ የማታውቀው ፣ብርቱዋ ፣ ደካማ ጎኗን ማንም የማያውቅባት፣ መጠቃቷን ማንም የማያውቅላት… … የጉብዝና ምሳሌ የሆነችዋን ራሔል ነኝ።
“ፍትህ አንተ ደግሞ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ስራህን እርግፍ አድርገህ ትተህ እኔን ስራ አድርገኸኛል። am fine!! በቀን አስሬ ቢሮዬን የምትከፍተውን ነገር አቁም። please?” አልኩት። ብዙ ቀን ብዬዋለሁ ሰበብ እየፈለገ በጥያቄ ይወጥረኛል እንጂ።
“እሺ። ከፈለግሽኝ ግን አለሁ።” ብሎኝ ቆይቷል። ከቢሮዬ ግን አልወጣም። ከወንበሩም አልተንቀሳቀሰም። ሁሌም የማስበው የኖህ ታሪክ ትዝ አለኝ። ከውሃ ጥፋቱ በኋላ ኖህም ገበሬ ሆነ። ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ። …… በድንኳንም ውስጥ ራቁቱን ሆነ ታናሹ ልጁ ካምም የአባቱን እርቃን ባየ ጊዜ ተሳለቀ። በአባቱ ገመና ሙድ ያዘ። ሁለቱ ልጆቹ ያፌትና ሴም ግን እርቃኑን እንኳን እንዳያዩበት አክብረውት ፎጣ በትከሻቸው አድርገው የኋሊት እየተራመዱ የአባታቸውን እርቃን ሸፈኑ… …… ኖህም ካምን ረገመው… ………… ይመስለኛል። ሲመስለኝ ሲመስለኝ……… የካም ነገድ የአክሱምን ልጅ ወለደ…… የአክሱምም ልጅ ልጆች በወንድምና ወዳጃቸው ገመናና ድክመት ሲደነቋቆሉ… … ሲሸረዳደዱ…… አንዱ የአንዱን ድክመት ሲጋለቡ ኖረው ኖረው። የእንጀራ እናቴ አባት ላይ ደረሱ። እሳቸውም ቀንደኛ ሸርዳጅ የሆነች ትውልድ አፈሩ……… ምናምን ምናምን………
የኖርኩት ዘመን የተረዳሁት አብዛኛው ሰው ከትልቁ ስኬትህ ውስጥ እንኳን ምናምኒት የምታክል ውድቀትህን ወይ እንከንህን ይፈልጋል። ካገኘብህ አለቀልህ። ሰማይ ያከለ ስኬትህን የጎመንዘር በምታክል እንከንህ ያጣፋልሃል።
“ፍትህ?”
“አቤት ቦስ?”
“ነገ ሰርጉን ትሄዳለህ እንዴ?”
“አወና!! እንዴ ቆይ ቆይ…… ትሄዳለህ ነው ትመጣለህ? ያ ማለት የእህትሽ ሰርግ ላይ አንቺ አትኖሪም ማለት ነው? ኦ……ኬ …… I think ይሄ ኬዝ ካሰብኩት በላይ ሊመስጠኝ ነው። ምንድነው እሱ?”
“ምንም big deal አይደለም። መሄድ አለመሄድህን ለማወቅ ነው። አበቃ!! የሆነ ታላቅ ግኝት ያገኘህ አታስመስለው።”
“እሄዳለሁ።” ብሎኝ ዓይኖቹን ዓይኖቼ ውስጥ ዘፍዝፎ ስሜቴን ሊጨምቅ ይታገላል።
“መልካም።” አልኩት ድምፄ ከስሜቴ ጋር አብሮ ሲወርድ እየታወቀኝ።
“በቃ?” ብሎ አፈጠጠብኝ ከተቀመጠበት መንጭቆ እየተነሳ። “በቃ ሌላ የምትዪኝ ነገር የለም?”
“እንዴ? ምን እንድልህ ነው የምትፈልገው?”
“አላውቅም!! ብቻ ከቤተሰብሽ ጋር በተያያዘ አንድ እንዳላውቅ የፈለግሽው ነገር ያለ ይመስለኛል። አላውቅም!! ንገሪኝ ማወቅ ያለብኝ ነገር ካለ ከሌላ ሰው ከምሰማው በፊት ንገሪኝ!”
“Excuse me? ከሌላ ሰው ከመስማትህ በፊት?ራስህን ምን ቦታ ላይ ነው የሰቀልከው ባክህ?” ሆኖ እንደማያውቀው እየጯጯህን ነው።
“Sorry boss! ራስን መስቀል አይደለም። እንደጓደኛ……”
“እኔና አንተ ጓደኛሞች አይደለንም! ደግሞ ቦስ አትበለኝ። አለቃህ አይደለሁም። ስም አለኝ። እኔና አንተ የስራ ባልደረቦች ብቻ ነን። የሚያገናኘንም ስራ ብቻ ነው።” ንግግራችን የማያስፈልገውን ያህል ቁጣ እየተቆጣሁ እንዳለሁ ራሴን ስሰማው አውቃለሁ። ግን ቁጣዬ ምክንያቱ ፍትህ ብቻ አልነበረምና መመጠን አልችልም።
“እሺ ጓደኛሽ አድርጊኝ? I mean not just for sayin… … real ጓደኛሽ ልሁን?።” አለኝ ሹክሹክታ በመሰለ ድምፅ እና ከኔ በተቃረነ እርጋታ። ሁኔታዬ ራሴኑ አሳፈረኝ። እሱ ላይ የምጮህበት ምንም ምክንያት የለኝም። ፀጥ አልኩ። ጠረጴዛዬ ላይ በአንድ መቀመጨው እየተቀመጠ
” I know አንቺ በጣም ጠንካራ ሴት ነሽ። ያ ማለት ግን ሰው አያስፈልግሽም ማለት አይደለም። ያንቺን ጭንቀት ማወቄ ላንቺ ያለኝን ቦታ አይቀንሰውም። በምታልፊበት ነገር ሁሉ ውስጥ አልፈሽ እዚህ መገኘትሽ ምን ያህል ጠንካራ ሴት መሆንሽን ያገዝፍብኛል እንጂ።” አለኝ የፍትህ በማይመስል እርጋታና ብስለት።
“ለምን ብለህ ምክንያቱን አትጠይቀኝ። እባክህ ሰርጉን አትሂድ?” ማለት ብቻ ነበር የመጣልኝ ሀሳብ
“እሺ።” አለ እንደዘበት። ከዛም ያልሰጠሁትን እጄን ፈልቅቆ እየማለ “ ይኸው !ቦስ ይቅርታ ራሔል ሙች! አልሄድም። ከፈለግሽ በቤተሰብሽ ኬዝም አልገባም። ያ የሚያስደስትሽ ከሆነ ምክንያትሽንም ማወቅ አልፈልግም። ራስሽ ፈልገሽ እስካልነገርሽኝ ድጋሚ አልጠይቅሽም። ግን አንድ እንድታደርጊልኝ የምፈልገው ነገር አለ!” እያለኝ ስልኬ ጠራ። ከቤት ነው። አንስቼው ስለእማዬ በሰማሁት ነገር እግሮቼ ዛሉብኝ። የብርትኳን ቢላዋ አንስታ ታፋዋ ላይ ሰክታለች። ሰራተኛዋ እየተርበተበተች ነው የነገረችኝ። ስለእማዬ በሰማሁ ቅፅበት ፍትህን ረስቼዋለሁ።
“ምንድነው እሱ? ምንድነው? እናትሽ ምን ሆነው ነው?” አፌ ቃላት መትፋት አቃተው። ምንም አላስፈቀደኝምም። አልጠየቀኝምም። ስልኬን አንስቶ መልሶ ደወለ። ልሄድ ቆሚያለሁ። ግን መንቀሳቀስ ከበደኝ። ከሰራተኛዋ ጋር እያወራ እንደሆነ አውቃለሁ። ግን አልሰማውም። ኮቴንና ቦርሳዬን ሰብስቦ እጄን መንጭቆ ይዞኝ ሲወጣ እግሬን ለመራመድ ማዘዜን ባላውቅም ተከትዬው መኪናው ጋር ደርሻለሁ። በሩን ከፍቶ መኪናው ውስጥ ሲያስገባኝ፣ ስንሄድ፣ ከሰራተኛዋ ጋር ሲደዋወል፣ እቤት ይዞኝ ሲገባ… …… ጆሮዬ ጭውውውውው ይልብኛል። ጭንቅላቴ የሆነ ከባድ ነገር እንደተጫነብኝ ለአንገቴ ከብዶታል።
🌑ይቀጥላል➡️
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ የኔ ምርጦች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ Like 👍👍 እያደረጉ

👍8👏1
#የወላድ_አንጀት
:
ሀገር ስታነጥስ፣
ከአንገቷ ፤ጉንብስ!
ከወገቧ -- ቅንጥስ!
ስትል ደፋ ቀና
ታፍጋ ተፋፍና፣
:
እራሱ ለኩሶ
እራሱ ነስንሶ
እራሱው አጢሶ፣
ጡት ነካሹ ልጇ
"ይማርሽ!" ሲል ደርሶ፣
:
አወይ እናትነት፣
አወይ ቅድስና
አወይ የዋህነት!
:
ጨክናም አትጨክን
ችላም አትበረታ
"ያኑርህ!" ትላለች
ባገኘችው ፋታ !!!
🔘በርናባስ ከበደ🔘
:
ሀገር ስታነጥስ፣
ከአንገቷ ፤ጉንብስ!
ከወገቧ -- ቅንጥስ!
ስትል ደፋ ቀና
ታፍጋ ተፋፍና፣
:
እራሱ ለኩሶ
እራሱ ነስንሶ
እራሱው አጢሶ፣
ጡት ነካሹ ልጇ
"ይማርሽ!" ሲል ደርሶ፣
:
አወይ እናትነት፣
አወይ ቅድስና
አወይ የዋህነት!
:
ጨክናም አትጨክን
ችላም አትበረታ
"ያኑርህ!" ትላለች
ባገኘችው ፋታ !!!
🔘በርናባስ ከበደ🔘
👍1