ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ግራንቪል ሻርፕ በ ቲቶ 2:13

የ ሙሓመዳውያን ኡሥታዞች ከ ስላሴ ትምህርት ተቃዋሚያን ፅሁፍ በሚቃርሙት የተሳሳተ መረጃና እጅጉን አሳፋሪ በሆነ አለመረዳትና አለማወቅ የክርስቶስን አምላክነት ለመቃወም በ ፅሁፎቻቸው እራሳችውን ማዋረድና ማውረድ ከጀመሩ ሰንብቷል። ከነኚህ ትችህቶች ውስጥ ዛሬ የምናየው ቲቶ 2:13 ላይ የተነሱትን ይሆናል።

" ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም #የታላቁን #የአምላካችንንና #የመድኃኒታችንን #የኢየሱስ #ክርስቶስን ክብር #መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤"
(ወደ ቲቶ 2:12-13)
προσδεχόμενοι τὴν μακαρίαν ἐλπίδα καὶ ἐπιφάνειαν τῆς δόξης τοῦ μεγάλου #θεοῦ καὶ #σωτῆρος ἡμῶν #Χριστοῦ #Ἰησοῦ,

while we wait for the blessed hope—the appearing of the glory of our great #God and #Savior, #Jesus Christ ( tou megaluo #Theou kai #Soteros hemon Christou 'Iesou)

ከላይ እንዳነበባችሁት ክፍሉ እየሱስን # θεοῦ God ወይም #እግዚያብሔር ብሎ እየጠራ እንደሆነ ግልፅ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ከንቱ ተቺዎች "θεοῦ" የሚለው ለ እየሱስ ሳይሆን #ለአብ ነው ብሎ ሙግት አቅርቧል። ሙግቱም አንድ የ ግሪክ ቋንቋ ምሁር (Scholar)፣ ስሙም "ግራንቪል ሻርፕ" የተባለ ሰው ባስቀመጠው የ ሰዋሰው ሕግ ላይ የተመሰረተ ነው። ይሁን እንጂ ይህንን ሙግት ያቀረበው 'ተቺ'፥ ሕጉንና ቲቶ 2:13'ን  አንድ ላይ ቢያጠና ኖሮ፣ ክፍሉ እንዲያውም የ ክርስቶስን አምላክነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ስለሚረዳ አፉን ይዞ ቁጭ ይል ነበር። የሚገርመው ግራምቪል እራሱ ሕጉን ተጠቅሞ ቲቶ 2:13 እየሱስ አምላክ መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ፅፏል።

1ኛው የ ግራንቪል ሕግ ምን ይላል??

“When the copulative kai connects two nouns of the same case, [viz. nouns (either substantive or adjective, or participles) of personal description, respecting office, dignity, affinity, or connexion, and attributes, properties, or qualities, good or ill], if the article ho, or any of its cases, precedes the first of the said nouns or participles, and is not repeated before the second noun or participle, the latter always relates to the same person that is expressed or described by the first noun or participle”

καὶ(kai, 'እና') የተሰኘች መስተፃምር ሁለት ተመሳሳይ ሙያ ያላቸውን ስሞች ለማያያዝ ስትገባና ከመጀመሪያው ስም በፊት ho ወይም τοῦ ("The") የሚለው definite article ከገባ  ግን ሁለተኛው ስም(noun) በፊት ሳይገባ ከቀረ እነኚህ ሁለቱ ስሞች የሚናገሩት(የሚገልፁት) ስለ አንድ ሰው ነው።
(Remarks on the Uses of the Definitive Article, 3)
(ይህንን ካላሟላ ግን ሁለት የተለያዩ አካላትን ለመግለፅ ነው የሚለው ሙግት ከዚህ የመጣ ነው፤ሁል ግዜ ትክክል ባይሆንም)

ይሁን እንጂ ይሄ ሕግ ከላይ የተገለፀውን የ አርፍተ ነገር አወቃቀር ለሚያሟሉ  ሁሉ ይሰራል ማለት #አይደለም። ሕጉ የሚሰራው ቀጥለን ይምንዘረዝራቸውን ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟሉ #ብቻ ነው።

1. ስሞቹ ሕልውና ላላቸው (ለሰው, ለ አምላክ) ብቸ የተጠቀሙ መሆን አለባቸው (they must refer to a person;not a thing)

2. የተፀውኦ ስም (Proper name) መሆን #የለባቸውም

3. ተመሳሳይ ሙያ መሆን አለባቸው (The same case)

4. ነጠላ መሆን አለባቸው (singular in number)

ዋቢ መፅሓፍት

ሀ. A Reexamination of the Granville Sharp rule by Daniel B.Wallace, Ph.D. Associate professor of New Testament Studies;

ለ. Wallace, Greek Grammar, 280-290

ሐ. Robertson, Grammar, 785-90

ስለዚህ በዚህ ሕግ መሰረት ቲቶ 2:13 "እየሱስ አምላክ ነው" ይላል?? መልሱን የምንሰጠው ክፍሉ የ ግራንቪልን ሕግ ሙሉ ለሙሉ ማሟላቱን ነጥብ በ ነጥብ እያየን ይሆናል።

1. 'tou' 'The' የሚለውን definite article የተጠቀመው በ መጀመሪየ ስም ላይ ብቻ ነውን?
መልስ- #አዎ
#tou megaluo #Theou kai #Soteros hemon Christou 'Iesou (ቲቶ 2:13)
θεοῦ(Theou, አምላክ, God) የሚለው የመጀመሪያ ስም ሲሆን σωτῆρος(Soteros, አዳኝ ወይም መድሃኒት, saviour) ሁለተኛ ስም ነው። tou' የሚለው የገባው በ θεοῦ ፊትለፊት ብቻ ነው።

2. ስሞቹ የተጠቀሙት(Theou እና Soteros) "ህልውና ላለው( personal) ነውን??
መልስ፦አዎ። ምክንኒያቱም ሁለቱም እየሱስን ለመግለፅ ነው የገቡት።
"..የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን #የኢየሱስ #ክርስቶስን.."

3. θεοῦ እና σωτῆρος ሁለቱም የተፀውኦ ስም (Proper name) #አይደሉም። ስለዚህ አሁንም ክፍሉ 2ኛውን  ቅድመ ሁኔታ ያሟላል ማለት ነው።

4. θεοῦ እና σωτῆρος ተመሳሳይ ሙያ ናቸውንህ??

θεοῦ=Noun #Genetive masculine singular
σωτῆρος=Noun #Genetive masculine Singular
ስለዚህ መልሱ "አዎ! ሁለቱም ተመሳሳይ ሙያ ናቸው።"

5. θεοῦ እና σωτῆρος ሁለቱም #ነጠላ (singular) ናቸው። ስለዚህ የመጨረሻውንም ቅድመ ሁኔታ ያሟላል።

ስለዚህ፤ ቲቶ 2:13 ሁሉንም የ ግራንቪል የ ሰዋሰው ሕግ ያሟላል። ማለትም θεοῦ እና σωτῆρος ( God and saviour, አምላካችንና መድሓኒታችን) ብሎ የተቀመጠው ሁለቱም #እየሱስን ለመግለፅ ነው ማለት ነው። ስለዚህ እየሱስ 'አምላክ" እና "መድሃኒት" ነው ማለት ነው።

ሙስሊሙ 'ተቺ"ይህንን ክፍል ለማክሸፍ የተጠቀማቸው ጥቅሶች ሁለት ናቸው።

1. ማቴ 21:12 ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ *የሚሸጡትን* እና *የሚገዙትን* ሁሉ አወጣ። "እነኚህ ሁለቱ ስሞች የተለያዩ ሰዎችን ይገልፃሉ" ብሎ ፅፏል።

ይሄ ክፍል በ አረፍተ ነገር አወቃቀሩ ቲቶ 2:13ን ቢመስልም (τοὺς πωλοῦντας καὶ ἀγοράζοντας*Those selling and buying) ግን ቅድመሁኔታዎችን ስለማያሟላ ውድቅ ነው። ምክኒያቱም "የሚሸጡትን* እና *የሚገዙትን" የሚሉ ሁለቱም ቃላት #ነጠላ አይደሉም።የ ግራምቪልን ሕግ አያሟሉም። ስለዚህ ክፍሉን እንደማስረጃ ማቅረብ በራሱ አሳፋሪ ነው።

2. ኤፌሶን 2:20 *በሐዋርያት* እና *በነቢያት* መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥

አሁንም በዚህ ክፍል "በሐዋርያት* እና *በነቢያት"  የተባሉት ሁለቱም ብዛትን የሚያሳዩ እንጂ ነጠላ አይደሉም። ስለዚህ አሁንም ማስረጃው የ ግራንቪልን ሕግ ስለማያሟላ  ውድቅ ይሆናል
@Jesuscrucified