ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
🤔እውነት እየሱስ የተላከው ለእስራኤል ሕዝብ ብቻ ነውን??🤔

እስልምና እና ሙሓመዳውያን የ ጀርባ አጥንት የሌለው ሙግት ይዞ መቅረብ የጀመሩት አብዛኞቻችን እንደምናስበው ከ "ዘመነ አህመድ ዲዳት" ወዲህ ሳይሆን ልክ ሙሓመድ "ጅብሪልን አየሁ" ብሎ ማንነቱ እንኲን የማይታወቅና  የሞት ያህል እስኪሰማው ድረስ ሙሓመድን ከ ድንጋይ ጋር ጨፍልቆ በመያዝ  ያሰቃየውን ፍጡር  ማየት ከጀመረ ወዲህ እንደሆነ የ እስልምና መጽሓፎች ሕያው ምስክር ናቸው። ሙግቶቹን በየጊዜው አንድ በ አንድ እያየን የምንሔድ ሲሆን ዛሬ የ ሙሓመድ ፍሬዎች ከሚያነሱያቸው ነጥቦች አንዱን እናያለን።

እንግዲህ ሙሓመዳውያን እየሱስ የ አለም ሁሉ አዳኝ ሳይሆን ለ እስራኤል ብቻ የተላከ ነብይ ለመሆኑ ቀጥሎ ያለውን ጥቅስ ይጠቀማሉ።

" እርሱም መልሶ። ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 15:24)

መልሶቻችን፦

የ እስራኤል ህዝብ በ እግዚያብሔር ዘንድ የተመረጠ ህዝብ መሆኑን መፅሓፍ ቅዱስ ቢቻ ሳይሆን ቁርዓንም ይመሰክራል።ለምሳሌ፣

ሱራቱል በቅራ 2:47
"የእስራኤል ልጆች ሆይ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬንና እኔም በዓለማት ላይ ያበለጥኳችሁ (አባቶቻችሁን በጊዜያቸው ከነበሩት ዓለማት ያበለጥኩዋቸው) መኾኔን አስታውሱ፡፡'

"O Children of Israel, remember My favor that I have bestowed upon you and that I preferred you over the worlds."
 
 የ እየሱስን ተልዕኮ ለ ሁለት ከፍለን እናያለን።
1. የማዳን ስራው በ መስቀል ላይ ሳይፈፀም
2. የ ማዳን ስራው በ መስቀል ላይ ከተፈፀመ በኊላ

1. የ ማዳን ስራው ከመሰራቱ በፊት እየሱስ እስራኤላውያን የተመረጡ የ ኪዳን ልጆች ስለሆኑ እንደ ልዩ መብት "previlage"   አስቀድሞ ከ ማንም በፊት እነሱን ማስተማር  እቅዱ ነው።

ማስረጃ፦
" እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም። በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ።"
ለእናንተ #አስቀድሞ #እግዚአብሔር #ብላቴናውን #አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።
(የሐዋርያት ሥራ 3:25-26)

ስለዚህ ምድር ላይ በሚመላለስበት ጊዜ ክርስቶስ የሚያስተምረው ይሄ የተመረጠ ህዝብን ነው ማለት ነው።  ሌሎችን ቢያስተምርም የ እስራኤልን አምላክ ከ ጥንት ጅምሮ ስለማያውቁና ስለማይረዱት ለ ተልዕኮው( አምነው ተረድተውም አለምን ሁሉ የማዳረስ) ውጤታማነት አይረዳውም። ስለዚህ መጀመሪያ አስቀድሞ ሕዝቡን ማስተማር በ መቀጠል ደግሞ በነሱ በኩል አለምን ማድረስ እቅዱ ሆኖ እናገኘዋለን።

ዋናው ጥያቄ፤ የ እየሱስ የ ማዳን ስራ ለ እስራኤል ብቻ ነውን??? የ ሚል ሲሆን፣ መልሱ #አይደልም ነው። እየሱስ አንድም ቦታ
 " በኔ የሚገኘው ድነት ለ ኢስራኤል ብቻ ነው" አላለም።

ይልቁንስ በ ክርስቶስ የሚገኘው ድነት ለ አለም ሁሉ መሆኑን የምንረዳው የተልዕኮው ሁለተኛ ክፍል ላይ  ፦
1: እየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምራቸው ከነገራቸው ጥቅሶች
2.እየሱስ ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት ወደ አለም ሁሉ መላክ ሲጀምር መሆኑን መፅሓፍ ቅዱስ ግልጽ ነው።

1. " በእርሱ የሚያምን #ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ #ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:16)

2." እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥"በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት #ከኢየሩሳሌም ጀምሮ #በአሕዛብ #ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።"
(የሉቃስ ወንጌል 24:46-47)

3." ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም #እስከ #ምድር #ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።"
(የሐዋርያት ሥራ 1:8)
4." ኢየሱስም። ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤"" ሕያው የሆነም #የሚያምንብኝም #ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።"" እርስዋም። አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ #ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 11:25-27)

5. " ሰዎች #ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:3-4)

6." ራሱንም #ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:6)

ቁርዓንስ ምን ይላል???

ሱረቱል መሪየም 19:21
አላት (ነገሩ) እንደዚህሽ ነው ፤ ጌታሽ ፦ እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፤ ለሰዎችም ታምር፣ ከኛም ችሮታ(ምህረት=mercy) ልናደርገው (ይህንን ሠራን) የተፈረደም ነገር ነዉ አለ፤ (ነፋባትም)።

He said, "Thus [it will be]; your Lord says, 'It is easy for Me, and We will make him a sign to the people and a mercy from Us. And it is a matter [already] decreed.' "

ልብ በሉ ቁርዓን እራሱ እየሱስን "ለ ሰዎች ምህረት ልናደርገው" ይላል እንጂ "ለ ኢስራኤል" አይልም!!!!

ስለዚህ ሙስሊሞች "እየሱስ ለናንተም ሞቷል" ሞትንም አሸንፎ ተነስቷል። ሙሓመድ ግን ለራሱም መዳኑን እርግጠኛ አልነበረም( Sahih al-Bukhari, Volume 5, Book 58, Number 266,  ቁርአን 46:8,9) ። ስለዚህ ከዘላለም ጥፋት 'ይዳን አይዳን' የማይታወቅ
ነብይ ከመከተል "የሞትና የ ሲኦል መክፈቸ በ እጄ ነው" ያለውን ክርስቶስን ተከተሉ ጥሪያችን ነው!!
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified