ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ነብዩ ሙሓመድን ሶስት አመት ዘግይቶ የገደለው መርዝ "ከነ ስሙ" ላሳውቃቹ!!!

Solving Mystery: ሙሓመድ ከ ሶስት አመት በኋላ ስለሞተ የገደለው መርዙ አይደለም ለምትሉ ሙስሊሞች👇👇

በ መጀመሪያ ደረጃ ነብዪ ሙሓመድ ተመርዞ ቢሞቱ የ አምላክ ነብይ ላለመሆናቸው ማስረጃ ነውን??

መልስ ከመስጠቴ በፊት ቀጥሎ ያለውን ሓዲዝ ላስነብባቹ።

ሳሂህ ሙስሊም መፅሓፍ 26 ሓዲዝ ቁጥር 5430

"አናስ ዘግቦታል፦ አንዲት አይሁድ ሴት ወደ አላህ መልዕክተኛ(ﷺ) የተመረዘ ስጋ ይዛ መጣች። የ መርዙም ስሜት ሲሰማቸው አስጠሯት እና ጠየቋት። እሷም እንዲህ ብላ መለሰች፤ "እርሶን ለመግደል ፈልጌ ነው"።ነብዩም እንዲህ አሉ፤ "#አላህ #ይህንን #እንድታደርጊ #ስልጣን #አይሰጥሽም።…"

ልብ በሉ፣ አላህ ለ አይሁዳዊቷ ልጅ ነብዩን እንድትገድል ስልጠን እንደማይሰጣት የተናገሩት ነብዩ እራሳቸው ናቸው። ስለዚህ ለ ቅድሙ ጥያቄያችን መልስ የሚሆነው፦ነብዩ በ ገዛ አንደበታቸው "ከዚህ መርዝ አልሞትም" ብለው ስለተናገሩ፣ ከመርዙ ከሞቱ የአምላክ ነብይ የመሆናቸው ነገር ጥያቄ ውስጥ ይገባል ማለት ነው።

የሚቀጥለው ጥያቄ፣ ነብዩ ከ አይሁዳዊቷ ልጅ እጅ በቡሉት መርዝ ነው የሞቱት?? ሲሆን መልሱ "#አዎ" ይሆናል።

ማስረጃዎቻችን፦

1. ነብዩ እራሳቸው በሞቱበት እለት ለስቃያቸውና ለ ሞታቸው ምክኒያት የሆነው በ ኸይባር ከዚህች አይሁዳዊት ልጅ እጅ የበሉት መርዝ እንደሆነ መናገራቸው።

ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅጽ 5፣ መፅሓፍ 59፣ ሓዲዝ 713
Narrated 'Aisha: The Prophet in his ailment in which he died, used to say, "O 'Aisha! I still feel the pain caused by the food i ate at Khaibar,and at this time, I feel as if my Aorta is being cut off FROM THAT POISON"
አይሻ ዘግባለች፦ ነብዩ ታመው በሞቱበት እለት እንዲህ እያሉ ይናገሩ ነበር፤ "ኦ አይሻ! እስከዛሬ ቀን ድረስ በ ኽይበር ከበላሁት ምግብ የሚሰማኝ የሕመም ስሜት አለኝ፤ ከበላሁትም መርዝ አሁን ትልቁ የልብ የደም ቱቦዬ (AORTA) እየተቆረጠ እንዳለ አይነት ስሜት ይሰማኛል..." አሉ።

2. ነብዩ የሞቱት ከተመረዙ ከ 3 አመት በኊላ ነው። ታድያስ 3 አመት ቆይቶ የሚገድል መርዝ አለ???
መልሱ በሚገርም ሁኔታ #አዎ ነው። ተከታተሉኝ!!!

ኦርጋኖፎስፌት (Organophosphates) ይባላሉ። ምንነታቸውንና የሚያመጡትን ውጤት (effect) ከነብዩ አሟሟት ሁኔታ ጋራ እያነፃፀርኩ አቀርብላቹሃለው።

ኦርጋኖፎስፌቶች ምንድናቸው??ስራቸውስ እንዴት ነው??
----------------------------------------------------------

ኦርጋኖፎስፌቶች ከ ካርቦንና ከ ፎስፈረስ የተሰሩ ኬሚካሎች ሲሆኑ "acetylcholinestrase" (አሴታይልኮሊን ኢስትሬስ) የተባሉ ኤንዛይሞችን በመጣበቅ ስራቸውን በትክክል እንዳይሰሩ ያደርጋል። እነኚህ ኤንዛይሞች በተፈጥሮያቸው፣ ሌላ"አሴታይልኮሊን" (acetylcholine) የሚባል በነርቮች መካከልና በነርቭ እና በ ጡንጫዎች ሴል መኻከል   (synapse, and neuro-muscular junction) የሚገኙትን መቆጣጠር ሲሆን በ ኦርጋኖፎስፌቶች ሲጠቁ ግን ይሄንን መስራት ያቅታቸወል። በ ሰውነት ላይ የሚያመጡትም ችግሮች በ ጊዜ አንፃር ለሶስት ይከፈላሉ።

1. Acute Toxicity( በ ቅጽበት( ጊዜ ሳይፈጅ)የሚያደርሱት ችግር)
 አንድ ሰው ተለቅ ያለ የ ኦርጋኖፎስፌት ዶዝ ቢወስድ የሚከተሉ ምልክቶችን ያሳያል።
ሀ. ሙስካሪንክ ምልክቶች፦ ማንባት፣ሽንት አለመቆጣጠር፣ማስታወክ፣ትንፋሽ ማጠር..ወዘተ

ለ. ኒኮቲንክ ምልክቶች፦የ ጡንቻዎች መዳከም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ እራስን መሳት
ልብ በል፤አንድ ሰው ከ ሁለቱ ምልክቶች አንዱን ብቻ ማሳየት ይችላል

አሁን፣ ነብዩ ሙሓመድ ሲመረዙ ከሳቸው ጋራ የተመረዘ ሰው ነበር። ሰውዬውም ይህንን የ ኒኮቲንክ ምልክቶችን አሳይቶ ሞቷል።

ኢብን ሳዓድ ገጽ 252-253፦ ነብዩ ከተመረዘው ስጋ ትንሽ (piece) ወሰዱ።  "ቢሽር ኢብኑ አል ባራ" የሚባልም የ ነብዩ ተከታይ ይሄን አይቶ ምግቡን ምብላቱን ቀጠለ። ነብዩ ቁራሿን ሲበሉ እሱ መብላቱን ቀጠለበት። #ሌሎችም በሉ።ከዛ ነብዩ እንዲህ ብለው ጮሁ፤ "እጃቹን ሰብስቡ፤ይህ የበጉ ታፋ እንደተመረዘ ነግሮኛልና።" ቢሽርም እንዲህ አለ፤ "እርሶን ባከበረው በ አላህ ስም እምላለው፣ ምግቡ እንደተመረዘ ልክ የራሴን ስውስድ ነው ያወቅኩት፤ነገር ግን ይ እርሶን(ነብዩ) ማዕድ አላበላሽም ብዬ መብላቴን ቀጠልኩ።...ቢሽርም ከቦታው #መነሳት #አልቻለም ቀለሙም መቀየር ጀመረ"

i. ቢሽር መነሳት ለምን አልቻለም?? የ ጡንቻው መድከም( ኒኮትኒክ ኢፌክት)
ii.ለምንስ ቀለሙ ተቀየረ? ትንፋሽ እጥረት( respiratory failure) ፣ ልብ በሉ አንድ ሰው ወደ ሠውነት ክፍሉ በቂ ኦክሲጂን ካልሔደ "cyanosis" "የ ሰውነት ወደ ሰማያዊ መቀየር ባህሪ ያሳያል።  ኒኮትኒክ ምልክት።
iii. ነብዩስ ለምን እንደ ብሽር ቶሎ አልሞቱም፦ ምክኒያቱም ቢሽር የወሰደው ዶዝ ከ ነብዩ በላይ ነው። ልብ በሉ ነብዩ የወሰዱት አንድ ቁራጭ ብቻ ነው። በተጨማሪም ሌሎችም ሰዎች ከነሱ ጋር የበሉ ነበሩ። ግን "እነሱም ሞቱ" የሚል የለም። ስለዚህ የነብዩ መኖር ተኣምር አይደለም።

2. intermediate effect

ቀጥለህ አንብብ...