Forwarded from እውነት አርነት ያወጣል (ቴዎድሮስ)
ዳንኤል ክብረት በ2011 ለንባብ ባበቃው "ኢትዮጵያዊው ሱራፊ" ላይ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት የሚባል የለም የሚል ሐሳብ ሲያቀርብ ይታያል፡፡ ለዚህም ‹‹ #የሄደም #የተመለሰም #ሰሎሞናዊ #መንግሥት #የለም፡፡… ከእስራኤል ዘር ጋር ማገናኘት የሕዝባችን ባህል መሆኑን የምናየው በታሪክ ነገሥታቱ ብቻ ሳይሆን በገድለ ቅዱሳኑም ይህንኑ ባህል ማገኘታችን ነው፡፡ በባህላዊው የዘር ቈጠራ ውስጥም አለ፡፡ #ስለዚህም #ነገሥታቱን #‹ሰሎሞናዊ› #የሆነና #ያልሆነ #ብሎ #መከፋፈሉ #አዋጪ #አይደለም›› (ገጽ 27) በሚል ያሰፈረውን መመልከት ይቻላል፡፡
ታዲያ ከሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት ጋር በተያያዘ ስመ ገናና የሆነው ክብረ ነገሥት ለምን ተጻፈ? የሚል ጥያቄ ቢነሣ ዳንኤል የሚከተለውን መልስ ይሰጣል፡-
#"...ለዐዲሱ #የይኩኖ #አምላክ #ሥርወ #መንግሥት #ታሪካዊ፣ #ሃይማኖታዊ #መደላድል #መፍጠር… የዐረብ ምንጮችን መሠረት አደርጎ በቃላዊ መረጃዎችና በተራረፉ የጸሑፍ መዛግብት ላይ ተንተርሶ የተዘጋጀ #አገራዊ #መጽሐፍ #ነው፡፡… ሁለተኛው ዓላማው ለኢትዮጵያ ነገሥታት የማንነት መሠረት መስጠት ነው፡፡ ንግሥናን ከእስራኤል ዘር በሚገኝ የዘር ተዋርዶ ብቻ እንዲሆን የሕግ መሠረት አስቀመጠ፡፡ ‹ሰሎሞናዊ› የሚለውም ሐሳብ በሚገባ ጎልቶ ወጣ፡፡ ይኩኖ አምላክም የሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት መላሽ ተባለ፡፡… ንቡረ ዕድ ይስሐቅና የዘመኑ ሊቃውንት ክብረ ነገሥትን የተረጎሙበት አንዱ ምክንያት ለኢትዮጵያ ዐዲስ ማንነትን ለመስጠት ነው፡፡ ያችኛዋ እስራኤል ፈረሳለች፣ ክርስትናንም አልተቀበለችም፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ዐዲሷ እስራኤል ናት፡፡ በመሆኑም ለእስራኤል የተሰጠው ቃል ኪዳን ለኢትዮጵያ ተላልፏል፣ ይህም በሰሎሞንና በንግሥት ሳባ በኩል ተፈጽሟል፡፡ የቃል ኪዳኑ ታቦትም በኢትዮጵያ ነው፡፡ ስለዚህ #ኢትዮጵያ #የአፍሪካ #ጽዮን #ናት #የሚለውን #ለመመሥረት #ነው (ገጽ 25 እና 302 የግርጌ ማስታወሻ 804 እና 325)፡፡
በዚህ በዳንኤል እምነትና ምስክርነት መሠረት ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት የሚባል ከሌለ፣ ክብረ መንግሥትም ለሌላ ዓላማ ከተጻፈ የሰሎሞን ልጅ ነው የሚባለው የቀዳማዊ ምኒልክ ታሪክ እና በእሱ አማካይነት ወደ ሀገራችን መጥቷል የሚባለው ታቦት ታሪክ ውሃ በላው ማለት ነዋ!!!???
https://tttttt.me/tewoderosdemelash/586

Telegram
ቴዎድሮስ ደመላሽ
ዳንኤል ክብረት በ2011 ለንባብ ባበቃው "ኢትዮጵያዊው ሱራፊ" ላይ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት የሚባል የለም የሚል ሐሳብ ሲያቀርብ ይታያል፡፡ ለዚህም ‹‹ #የሄደም #የተመለሰም #ሰሎሞናዊ #መንግሥት #የለም፡፡… ከእስራኤል ዘር ጋር ማገናኘት የሕዝባችን ባህል መሆኑን የምናየው በታሪክ ነገሥታቱ ብቻ ሳይሆን በገድለ ቅዱሳኑም ይህንኑ ባህል ማገኘታችን ነው፡፡ በባህላዊው የዘር ቈጠራ ውስጥም አለ፡፡ #ስለዚህም…