Forwarded from እውነት አርነት ያወጣል (ቴዎድሮስ)
ሰሞኑን ድርሳነ ማርያም የተሰኘ መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር፡፡ መጽሐፉ ውስጥ የተለያዩ አስገራሚ ነገሮችን ያነበብኩ ቢሆንም አሁን ያነበብኩትን ግን ለወገኖቼ ማካፈል እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡
በአንዳንዶች እንደሚታመነው ለማርያም ዐስራት ተደርጋ የተሰጠች አገር አለች፡፡ ድርሳነ ማርያም ስለዚህ ሁኔታ እንዲህ ነው ያሰፈረው፡-
"ዐሥራት ትሆነኝ ዘንድ አንዲትን አገር ስጠኝ አለችው፡፡ አዜቡ ይሁንሽ አላት፡፡ ክርስቲያን ነውን? አልሁት፡፡ #አሁን #ክርስቲያን #አልሆኑም #ብዙዎቹ #ለአውሬ፣ #ለድንጋይ #የሚሰግዱ #ናቸው እንጂ፡፡ ከዚህ በሁላ ግን ክርስቲያን ይሆናሉ፡፡ በስሜ ማመናቸውም እንደፀሐይ ያበራል፡፡ በስምሽም ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ይሠራሉ፡፡ #ይህ #ቦታም #አክሱም #የሚባለው #ነው..." (ድርሳነ ማርያም ገጽ 130)
ከዚህ ውስጥ ሦስት ነጥቦችን ላሳያችሁ፡-
1) አንዳንዶች እንደሚያምኑት አስራት ተደርጋ የተሰጠችው ኢትዮጵያ ናት፡፡ መጽሐፉ ላይ በሰፈረው መሠረት ኢትዮጵያ ልትሆን የምትችለው አክሱም ናት፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አሁን ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራት አገር ለማርያም አስራት ተደርጋ ተሰጥታለች የሚለው ስሕተት ነው ማለት ነው፡፡
2) ሌላው እስከዛሬ ጣዖት አምልከን አናውቅም የሚለው ነው፡፡ በድርሳኑ መሠረት ጣዖት ይመለክ የነበረ መሆኑን፡የተናገረው ራሱ ጌታችን ነው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር ውጪ ምንም አምልካ አታውቅም የሚለውም ስሕተት ነው ማለት ነው፡፡
3) ክርስትና ወደ እኛ ጋር የመጣው በጀንደረባው ነው የሚለውም በዚህ ጽሑፍ መሠረት እሳት የነካው ላስቲክ ሆነ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ጀንረባው፡ክርስትና እንዳመጣ የሚታመነው በ34 ዓ.ም. ነው፡፡ ድርሳኑ ላይ የሰፈረው ታሪክ የሰፈረው ማርያም ከሞተች በሁላ ነው፡፡ ይህ ማለት ጀንደረባው ክርስቲያን ከሆነ፡ከብዙ ዓመታት በሁላ ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ ገና ለክርስትና ሩቅ ነበረች እያለን ነው፡፡
ይህ ሁሉ የእኔ ሐሳብ አይደለም፡፡ ከመጽሐፉ ላይ ያለውን ነው ግልጽ ያደረኩት፡፡
https://tttttt.me/tewoderosdemelash/381

Telegram
ቴዎድሮስ ደመላሽ
ሰሞኑን ድርሳነ ማርያም የተሰኘ መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር፡፡ መጽሐፉ ውስጥ የተለያዩ አስገራሚ ነገሮችን ያነበብኩ ቢሆንም አሁን ያነበብኩትን ግን ለወገኖቼ ማካፈል እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡
በአንዳንዶች እንደሚታመነው ለማርያም ዐስራት ተደርጋ የተሰጠች አገር አለች፡፡ ድርሳነ ማርያም ስለዚህ ሁኔታ እንዲህ ነው ያሰፈረው፡-
"ዐሥራት ትሆነኝ ዘንድ አንዲትን አገር ስጠኝ አለችው፡፡ አዜቡ ይሁንሽ አላት፡፡ ክርስቲያን…