ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ዝመት አትበለኝ
_______________
ወንድሜን ፊት ለፊት ተሰልፎ እያየሁ
በየትኛው እጄ ቃታ እስባለሁ
ዝመት አትበለኝ በማን እዘምታለሁ
እዛም የሚቆረስ ግማሽ አካሌ ነው
የተንቀዠቀዠው....
የተቅበዘበዘው......
እርካታ ያላገኘው.......
ጀግና ያልተባለው........
እንዴት ወንድም ገዳይ ቃየን እሆናለሁ ?

መታሰቢያነቱ :- |ለቅድስት ሀገር #ኢትዮጵያ

አ.አ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
#ጉባኤው
_____
መስከረም :- ለምን እንደሆነ ጉባኤ የጠራነው
አንዳችንም ሳንቀረ የተሰበሰብነው?
ወርኃ ጥቅምት በቶሎ እንዲገልጠው
ሰብሳቢው መስከረም እድል እሰጣለው

ጥቅምት ፦ አዎን ጋሽ መስከረም የወራቶች አውራ
አመሰግናለሁ ዕድል ስለሰጡኝ እኔ እዳወራ
ያሉት ትክክል ነው አንድም ወር አልቀረም
ችግሩ ጥልቅ ቢሆን ባይሆን የማያከርም
ሁሉንም ወር ቀጥረን እዚህ ተጠራቀምን

ኅዳር ፦ ሁሉም እንደመጣ እናረጋግጥና
ጉባኤው ይጀመር በታላቅ ጦሞና


መስከረም :- ጥሩ መልካም አልከን ወንድማችን ኅዳር
ሁሉም በሥርዓቱ ተሰፍሮ ይቆጠር
መቼም ከተያዘ ወግ አይቀርምና
ኅዳር አንተ ትጉ ብዕርን አውጣና
ቃለ ጉባኤ ያዝ ካፍ ካፍ ልቀምና


ኅዳር :- እሺ ታላቁ ወር የመጀመሪያችን
በሙሉ እጥፋለሁን ሳላስቀር አንዳችን

ጥቅምት :- እኔም ጥቅምት አለው የጉባኤው ድምቀት
ጋሽ መስከረም እርሶ ጉባኤውን ሲመሩት
እቀላጠፋለው ሀሳብ እንዳይነጥፍ
ከአንዱ ወደ ሌላው እያልኩኝ ቅልጥፍጥፍ

ማንም እንዳልቀረ ቢያውቅም ልቦናዬ
ወግ መጠበቅ ነውና ዋነኛው ሥራዬ
ማን ማን እንደመጣ ሊታደም ጉባኤ
አሁን እጠራለሁ እርሶን አስቀድሜ
ጋሽ መስከረምዬ ስዩመ ጉባኤ


ታህሳስ ና ጥር የካቲት መጋቢት
እነዝያውናቸው ሚያዝያ ና ግንቦት
ሰኔም ተገኘታለች ይህች አሳባቂ
የክረምቱን መድርሰ ቀድማ አሳዋቂ
ሐምሌ ና ነሐሴም ጉም ድመና ለበሰው
ጋቢ የደረቡ አዛውንትን መስለው
በቀኘ ይታዩናል ዶፍ ዝናብ አርግዘው

/ ይህን ጊዜ ጉባኤው በሳቅ ይታወካለል /

ሐምሌ ፦ ለአነጋገር ልክ ለከት አብጅለት
ምን ብትንቀን ነው ነፍሰ ጡር ያረከን ?
አለዛ ታርመህ አደብን ካልገዛህ
የያዝነውን ውኃ በአንድነት ለቀን
ጉድ እንዳናረገህ በጎርፍ አሶስደን

መስከረም ፦ ጥቅምት አንተም ተው አንተም ታገስ ሐምሌ
እርምጃ እወስዳለሁ እኔ ግን በግሌ
ሌላ ሆኖ ሳለ መነጋገሪያችን
በንቀርት ላይ ደግፍ ሆነ ችግራችን
ደራሽ ጎርፍ ማዘዝ ይቻለኛል ብለህ
አትኩራ በክብር በተሰጠህ ነገር
ልታቅ ይገባሃል ስለሞቃም ወር
መፎከር አይበጅም ጉልበትን ተማምኖ
ለአንዱ ሲሰጠው እንዲወስድ በትኖ
ለሌላው ይሰጠዋለል እጥፍ ድርብ ሆኖ
አሙቆ አፍልቶ የሚያስቀር አትኖ
አሉባልታ ወሬ ቧልቱን እንተውና
የስብሰባው አላማ ይህ አይደለምና
በቶሎ እንመለስ በቀናው ጎዳና

ታኀሳስ :- በሉ አታንቃቁን በቶሎ ጀምሩ
የተጋረጠብን ችግር ካለም አውሩ
አውርተን እንፍታው ነገሩን ከስሩ

ሚያዝያ :- እኔም እስማማለው በሀሳበ ጥር
ቶሎ ተገልጦልን ሰብሰባው ቢያጥር
ምንድ ነው ምሥጢሩ የመታደማችን
ምን ችግር ገጠመን ከመካከላችን?

መስከረም :- እንግዲህ ለማንሳት ከሥሩ ነገሩን
ብርቱ ችግር መቷል የሚነጣጥለን
አንድነትን ፈቶ ለብቻ የሚያቀረን
ስለዚህ ተወያይተን አውርተን በጋራ
ሀሳብ ለማዳመጥ ጉባኤ ተጠራ


ሰኔ : አረ ሰብሳቢያችን ታላቅ ወንድማችን
ምን ይሆን ነገሩ እንዲህ ያሰጨነቀን
ተነፋፋው እኮ ነገር ሆዴ ገብቶ
እኔ እንደው ወሬ አልችል ንገረን በቶሎ
ሰኔን እያወከኝ ለወሬ የሞትኩ ነኝ
በዘንድው እንኳ ክረምት መጣው ቢለኝ
ቀድሜ ዘረገፍኩ ዝናበ በረከቱን
ገና ሳይጠጋ ዘመነ ክረምቱ
እናማ ንገሩን ነገር ሳታረዝሙ
ብሶ እንዳይገለኝ የወሬ ጥማቱ

መስከረም : -እስቲ ተረጋጊ ሰኔ አትጣደፊ
አንዳንዴ ወሬውን ሰምተሽም እለፊ
ችግርና ሐዘን የገጠሙ ለታ
መቅደም ይገባዋል ሁል ጊዜም እርጋታ

ነሩን ስጀምር ማስረዳት ሀ ብዬ
ሐዘኔ ጥልቅ ነው ይህን በማለቴ
13 ሆነን
በስካሁን ኑሯች በምድረ ኢትዮጲያ
እንዳችን የጌታ ሌሎቻን የ12ቱ ሐዋርያ
ምሳሌዎች ሆነን ኖረናል በአራያ

ጥቅምት :- አፌ ቁርጥ ይበል መስከም ሊቃችን
ምሥጢር አርገህ መሰልከን

መስከረም :-አመሰግናለሁ አክባሪዬ ጥቅምት
ግን ግን ታዝን ነበር ብትታገስ ጥቂት
እንዲሁ ቢያዛልቀን ነበረ በቀና
ዛሬ ግን በዓለም ዕውቀት በዛችና
ዋዜማ ላይ ሆንን ለመለየት ዜና

(ይህን ጊዜ ጉባኤው በጫጫታ ይታወካል ዋዜማ ለመለየት ዜና ሆሆሆ ወዘተ በሚሉ ወሬዎች )


ጷጉሜ :- አንዳችን የጌታ ሌሎቻን የ12ቱሐዋርያ
ምሳሌዎች ሆነን ከኖርን በምድረ በኢትዮጲያ
አሁን ደርሶ የሚለይ ምን ተአምር መጣ?

ግንቦት :- አይ ጷጉሜ የዋህ እህት
የሐዋርያትም ሕብረት ከጌታችን ጋራ
ተፈቶ የለም ወይ በአይሁድ ፉከራ
ፈሪሳዊ ዕውቀት እርሾዎ ሲንሰራፋ
የሥላሴ አምሳል የሰው ልጅም ከፋ
እስካልተቆጠብን ከፈሪሳኢ እርሾ
መፈጠሩ አይቀርም በፍቅር ላይ ቁርሾ

ጷጉሜን :- የሆነውስ ሆኖ እኛን የሚለያይ ምን እርሾ ተገኘ
የሰው ልጅ አይደለን ዘር ቋን ቋ አለየን
ለያይቶ ከፋፍሎ ለብቻ የሚያደርገን ?

መስከረም :- እንግዲህ ጷጉሜያችን ትንሿ እህታችን ችግሩ ይህ ነው
ያንቺ ከኛ ጋራ አብሮ መቆጠር ነው
አንዳንድ ዕውቀት ገባን ታረቀቅን ያሉ
ጷጉሜ ከወራቶች ትቀነስ ነው ያሉ
ጷጉሜ :- ምን ?? አጥብቆ ጠያቂ የእናቱን ሞት ይረዳል አሉ
ለካ ለኔ ኖሯል ስብሰባ የተጠራው
እኔማ መቼ አወኩ እንዲ እንደተጠላው
የሁልሽን ጉለት ሳሟላ ቆይቼ
አንዳንዴ 4 ቀን ሌላ ግዜ 5 ገፋ ሲልም 7 ቀን እኮ የምሆነው
የናንተን ትራፊ በፍቅር ሰብስቤ ነው
እናንተ እዳታንሱ ከ30 ቀናት
ልቃቹም እዳቴዱ ከሰሌዳ ወራት
እራሴን ስቀንስ ሳባዛ ሁልግዜ
አመሰግናለሁ ይህ ከሆነ ደሞዜ
ደግሞም አዝ ኛለው ይዞኛል ትካዜ

(ከቀድሞ የበለጠ ጉባኤው ለሁለት ተከፍሎ በታላቅ ጫጫታ ይታወካል)

አዎ ትቀነስ ! አይ የለም ለምን ሲባል ትቀነሳለች! ትቀነስ! አይ በጭራሽ !ወዘተ)


መስከረም :- ፀጥታ ፀጥታ ጸጥታ ይከበር
በጥሞና ሆነን በተራ እንምከር

(ጫጫታው እየጋለ ይሄዳል ሰብሳቢው መስከረም ቆም ብሎ ያጨበጭባል )
በመካከል የጷጉሜ የለቅሶ ድምጽ ይሰማል /

ጥቅምት :- ጷጉሜ እህታች በቶሎ አትከፊ
ሁሉን የሚቻለውን እርሱን ተደገፊ
ጉባኤው ተማክሮ አልወሰነምና
ፊትሽ እንዳይጨልም በሐምሌ ደመና

መስከረም :- እሺ አሁን ሁሉም በየተራ
ሀሳቡን ይሰጣል ገልጦ እያብራራ
ጥቅምት በሥርዓቱ በቅደም ተከተል ተራ ያሲዝና
ኅዳር ይጥፈዋል ሁሉን በጥሞና
ስለዚህ ወስኑ መክንያትን ይዛችሁ
ትቀነስ ትቀመጥ ጷጉሜን እህታችሁ?

(አሁንም ጫጫታው ይጀምራል )

መስከረም :- ሀሳብ ያለው ብቻ እጁ እያወጣ
ዕድሉን ሰሰጠው መልካም ምክሩን የምጣ
ከዛ በተረፈ ነውና ጉባኤ
ጫጫታን አልፈቅድም የጎንዮሽ ወሬ

ጥቅምት :- አዎን እሺ እዛ ጋር ወርኃ መጋቢት እጁን ስላወጣ
ታላቁ መስከረም ዕድል ይስጡትና ቆንጆ ሀሳብ ያምጣ

መስከረም :- እሺ መልካም ቀጥል

መጋቢት :- አመሰግናለው ሰብሳቢው መስከረም
ዕድል ስለሰጡኝ ከሁሉ በማቅደም
ክብረቴም ይድረሰው ለአሳላፊው ጥቅምት
የኔ እንኳን ሀሳቤ በጷጉሜ ወራችን
አትቀነስ ባይ ነኝ ትሩን ከጎናችን
እርሷ ብትለየን ከመካከላችን
እኩልነት ቀርቶ ይከራል ጠባችን
እኔ በበኩሌ ከ30ው ዕድሜዬ
መቀነስ አልሻም ከየወር ድርሻዬ


መስከረም :- መልካም ሌላ ባለ ሀሳብ

ጥቅምት :- እዛ ጋር ጥግ ላይ ሰኔ እያወጣች ነው

መስከረም :-እስቲ ሰኔ ተንፍሽ

ሰኔ :- አመሰግናለሁ ዕድል በመቸሬ
እኔ አላረዝምም አጭር ነች ነገሬ
ጷጉሜ ትቀነስ ወይ በሚለው ሀሳባችሁ
እኔ እስማማለው አጠቅምም ባካችሁ
ወይ ሞልታ ላትሞላ ይህቺ የቀን ጎደሎ
ውሳኔው ይወሰን ትወገድ በቶሎ

መስከረም : - እሺ ተቀበልንሽ ሰኔ ታዳሚያችን
ግን ግን ለመለየት ሳይሆን መሰባሰባችን
አንድ መሆን ነበር የኛ ዓላማችን
የሆነው ሆነና ሰብሳቢ ነኝና
ሁሉንም ሀሳቦች ልስማ በየፊና
አሁንም ቀጥዬ ዕድልን ልስጣችሁ
ከስካሁኑ ሁሉ የተለየ ሀሳብ ካለ መሃላችሁ
እጅ ክንዳችሁን አሳዮን አጉልታችሁ

ጥቅምት :- በዚ ጥግ ደግሞ ከተደረደሩት
የጥር እጅ እታያል ጋሼ ዕድል ይስጡት

መስከረም :- በል እሺ ተናገር ዕድል ሰጥቻለሁ
የሚያስማማን ሀሳብ ካንተ ዘንድ እሻለው

ጥር :- አመሰግናለሁ ወርሃ መስከረም
እኔም ባጭሩ ነው ነገር አላረዝምም
ትንሽ ሰው ትንሽ ነው ይላሉ ሰዎቹ
ዕውቀት የገባቸው ነገር አዋቆቹ
ማለቴ እነዛ ነጮቹ
ምንድነው ለማለት ባጭሩ የፈለኩ
ምንም አይመስለኝም ጷጉሜንም ብትነኩ
ትቀነስ ካላቹም ትቀነስ ግድ የለም
በኔ ሕልውና ላይ ለውጥን አያመጣም

ጥቅምት :- ጷጉሜን ሀሳብ አላት መስለኝ ቆማለች
ዕድል እንዲሰጣች ፍቃድ ከጅላለች

መስከረም :- እሺ አድምጠናል የጥርን ሀሳብ
ግን እንደታሰበው ውኃ አያነሳም
ጷጉሜ ስለቆመች ዕድልን ፈልጋ
እስቲ እናዳምጣት እንሁን ከእርሷ ጋር


ጷጉሜን :- ለሰው ሀገር ተሽጠው
ወርቅና ዋንጫው ያመጡ ሮጠው
ያናድደኝ ነበር እዚህ ሆኜ ሳየው
ለካ ተገፍተው ነው ፍቅርን ተነፍገው
እንዲህ ካሴራቹ እኔን ለማስቀረት
አብሮ አደግ ጓደኛን መለየት ነውር ከሌለበት
እኔም እሄዳለሁ ፍቅር ወዳለበት

( ብላ ጷጉሜ እያለቀሰች ስብሰባውን እረግጣ ትወጣለች )

ጥር :- ይህው አላልኳቹም ትንሽ ሰው ትንሽ ነው
እረግጣን የወጣች ቢናቅ ነው ጉባኤው

መስከረም :- መቋቋም ካልቻለች የመለየትዜንን
ብትወጣ ገድ የለም
ተገፍታም ተይዛመ ሁለት በደል የለም

(በጣም ተበሳጭቶ ዕድል ሳይሰጠው የካቲት ይነሳና)

የካቲት :- ጷጉሜ አትቀነስም እኔ ቆሜ ሳለሁ
በእርሷ ከመጣችሁ ሞቴን እመርጣለሁ
መኖር እየቻልን ሁላችን ተካተን
በነጭ ዲስኩር ወሬ እንዴት እናምናለን
እስቲ እነርሱ ራሱ ከወራቶቻቸው
በ11ዱ ይቅሩ አንዱን ወር ቀንሰው
ፊደሉ ይቀነስ ወራቱ ይቀነስ
ምን የሚሉት እብደት ምን ዐይነት መቃወስ
ዓለም እየሳቀ በጅጉ እንዳይንቀን
እንቀነስ ስንል በመደመር ዘመን
እግዚአብሔር ለማለት God ን ስትጽፉ
Gን ካቲታል አርጓት ከእውቀት እንዳትነጥፉ
እግዚአብሔር ለማለት ጣዖት እዳጥፉ
ብለው የሚነተርኩን በነጋ በጠባ
የእነርሱ ፊደል ነው ምሥጢር ትርጉሜ አልባ
የኛን ፊደላት ሀሌንታዋ "ሀ " ብናይ
ጊዜ አይበቃኝም ግን ለምሳሌው ለጉባኤው
ሀሌታ ሀ ማለት ብሒል ሀልቱ ለአብ እም ቅድመ ዓለም
የአብ አኗኗሩ የቀደመ ካለም
መክሼ ሆና ሳለ ካሌታዋ ጋር
ሐ መሩሐ ሐ ግን ልዩ ናት በምሥጢር
ሐመ ሞተ በእንአነ ስለኛ ሞተ ብላ የምታመሰጥ
ስለዚህ ወንድሞቼ ሁላችን ሁላችን
የፈረንጅ ነገር ክፉ ምክርን ትተን
የባቶቻችንን ቃል ወንጌል ተምኩዘን
በጭኸወት የማይፈርስ በከንቱ ማላዘን
ባንድነት እንኑር በፍቅር ኢያሪኮ ዙሪያችንን አጥረን

(ጭብጨባው ከዳር እስከዳር አዳራሹን ያናጋዋል

መስከረም :- እድሉን ሳልሰጥህ ያወራህ ቢሆንም
ፍቅርን ስለሰበክ አልቃወምህም
ሰለዚህ እግዚአብሔር ያክብርህ የካቲት አስተዋይ
የአባቶችን ትዕዛዝ አደራ ተቀባይ
ጷጉሜን ርቃ ሳትሄድ በኛ ተበሳጭታ
ይቅርታ ትጠየቅ በክብር ተጠርታ
ጠቡ ይቅርና መናናቅ ተረስቶ
መኖሩ ይሻለላል በአናድነት ተካቶ
ጥቅምት ፍጠንና ይዘአት ና ቶሎ

መስከረም ፦ በመስከረም
ወራት ፦ ስፍራው ሁሉ ለምለም
መስከረም ፦ በጥቅምት
ወራት ፦ አንድ አጥንት
መስከረም ፦ በኅዳር
ወራት ፦ እሸት ከእዳር እዳር
መስከረም ፦ በታህሳስ
ወራት ፦ ጎተራህን አብስ
መስከረም ፦ በጥር
ወራት ፦ ምርትህን አበጥር
መስከረም ፦ የካቲት
ወራት ፦ አዝመራህን ክተት
መስከረም ፦ መጋቢት
ወራት ፦ እረስ ለወደፊት
መስከረም ፦ በሚያዝያ
ወራት ፦ ፀሐይ እዚህ እዛህ
መስከረም ፦ ግንቦት
ወራት ፦ ፀሐይ አናት አናት
መስከረም ፦ በሰኔ
ወራት ፦ ዝናቡን ወደኔ
መስከረም ፦ በሐምሌ
ወራት ፦ ልኑር እነደ አመሌ
መስከረም ፦ በነሐሴ
ወራት ፦ ትንፍስ አለች ነፍሴ
መስከረም ፦ በጷጉሜ
ወራት ፦ እስቲ ልዘጋጀው አዲስ ሕልም አልሜ

(ጭብጨባው ከዳር እስከዳር አዳራሹን ያናጋዋል)
ተፈጸመ
ከ ተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
ሰኔ 19/2014 ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጲያ
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ምዕራፍ :- #14
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ቆይታ :- #13ደቂቃ ከ43ሰከንድ ብቻ
የቦታ ይዞታ :- #3.2mb ብቻ
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ 🙏
_°°°°°°°°°°°___
#እራስህን ፈትሽ

የዛሬ ዓመት አካባቢ ነው ወቅቱ እንደ አሁኑ የሽብር ቡድኑ እና የcovid 19 ስጋት መንግስትን ያስጨነቀበት ወቅት ነው። ምሽት አካባቢ አገልገሎት ጨርሰን ወደ ሰፈር እያመራን ነው። የጸጥታ ኃይሎች (የፌደራል ፖሊሶች) በየ አስፋልቱ መዐዘናት ቆመው አላፊ አግዳዊውን አስቁመው እንደ መፈተሽ ዐይነት ነገር ይሰራሉ።

#እኛም ወደ ሰፈር ለመግባት ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩን በአንዱ አስፋልት ላይ መንገዱን አጥረውት አገኘንና ለመፈተሽ ተበታትነት ወደ ጸጥታ ኃይሎቹ ቀረብን ።እኔ በበኩሌ እጄን ከኪሴ አውጥቼ ወደ ግራና ወደ ቀኝ ዘርግቼ የመስቀል ምልክት ሰርቼ ለመፈተሽ ተዘጋጀው ፊት ለፊቴ ያለው ፖሊስ ግን ምንም የመፈተሽ አዝማሚያ ሳያሳይ የሆነ ነገር ተናገረ ግራ ገባኝና ይህው አልኩት ዝግጁ መሆኔን ለማሳወቅ #እራስህን_ፈትሺ አትሰሚም እንዴ? ሲል ጮክ ብሎ ደገመው አንደኛ እና ሁለተኛ መደብ እንዲሁም ጾታ ነጠላና ብዙ ቁጥር የማይለየው ንግግሩ ከወዴት እንደሆነ ጠቆመኝ ያው የወድሄት ነህ ዘመን ላይ አይደለን ?!
እውነት ለመናገር እራስህን ፈትሽ እንዳለኝ መጀመሪያውኑ ሰምቼዋለው ግን እራሴን ፈትሼ ንጹዑ ነኝ ምንም አልያስኩም ነው የምለው? ወይስ ይህው ሁለት ስለትና አንድ ተቀጣጣይ ፈንጂ ከኋላ ኪሴ ይዣለሁ ብዬ እራሴን እንዳጋልጥ ነው የፈለገው ብዬ ግራ ስለገባኝ ነው።
#እንዴት እራስህን ፈትሽ ሊለኝ ይችላል ብዬ እርግጠኛ ለመሆን ለሦስተኛ ጊዜ በድጋሚ እህህ ልል አሰብኩና ወዲያው ማዳመጫዬን ከማላመጫዬ ሲደባልቀው ስለታየኝ ተውኩት ከዛም የሰማሁትን ግን ያልገባኝን ንግግሩን መተግበር ጀመርኩ ።እራሴን እንደነገሩ ዳባበስኩና ይህው የለም ስለው መንገዱን ከፍቶ እንዳልፍ ፈቀደልኝ።

እስከ ዛሬ ድረስ ማለትም ለ365 ቀናት ከ 91ኬክሮስ ድረስ ፖሊሱን እንደ ሞኝ ቆጥሬ ስስቅ ነበር። ያሳቀኝ ለcovid 19 ተዛማችነት ያሳየውን ጥንቃቄ ከግምት ውስጥ በለማስገባት አይደለም ። በዚህች በራስ ወዳድ ዓለም ሳለን ማን እራሱን ፈትሾ ጥፋተኛ ነኝ ልቀጣ ይገባኛል ሊል ይችላል ቤዬ ስላሰብኩ ነው እንጂ።

#አሁን ግን ዓመቱን ሙሉ ስስቅ የከረምኩት በራሴ መሆኑ ዘግይቶ ገባኝ ።ሰው ለራሱ ታማኝ ከሆነ በፍጹም ለሌላው መታመን አያቅተውም። አንባቢ ሆይ አንተ እራስህን በታማኝነት ስራው ከዛ በብዙ አማኞች ትከበባለህ አንተ ቀድመህ እራስህን ከፈተሽክ ማንም አንተን ሊፈትሽህ አይችልም ቢፈትሽ እንኳ ትርፉ ድካም ብቻ ነው ።ምንም አይገኝብህምና !
“እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።”
|1ኛ #ጴጥ 2፥5

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ጳጉሜ 2/2014 ዓ.ም
Forwarded from Biniam Kalayu
#የገነት ወግ

ከምጽሐት በኃላ ገነት ውስጥ ነው። ቸርነቱ የበዛ መዐቱ የራቀ እግዚአብሔር አምላክ ከሦስት ወጣቶች ሦስት ነገሮች አግኝቶባቸው ገነት አስገባቸው። መቼም እግዚአብሔር አምላክ መንግሥተ ሰማያትን የምታክል ቦታ በጥርኝ ውኃ የሚሸጥ ሞኝ ነጋዴን ይመስላል። #ማቴ10÷41

#ከወጣቶቹ የተገኘባቸው መልካም ነገርም እነኸህ ነበሩ። በአንዱ እምነት በአንዱ ማስተዋል በአንዱ የዋሕነት ነው። ከዚህ የተረፈ የጠለቀ መንፈሳዊ ትጋት የላቸውም በሳምንት አንድ ቀን እሁድ ግጥሚያና ትሬሊንግ ከሌለባቸው ያስቀድሳሉ ከአጽዋማት ሦስቱን መርጠው እንነገሩ ይጦማሉ በቃ ለገነት ዜግነት ያሳጫቸው ይህው ጥቂቱ ጥረታቸው እእና ብዙሁ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው።

#ከገነት በአንዱ ዕለት ታድያ አንደኛው ወጣት እንዲ ይላል " እንተ ገነት ገነት እያልን ስንናፍቃት የነበረችሁ ይችሁ ናትን? እንዴ ጠዋት ቅዳሴ ማታ ውዳሴ እረፍቱ ቆይ መቼ ነው ?
ሌላኛው ወጣት ቀበል አድርጎ ታገስ እስቲ በዚህኮ እረፍቱ ምስጋና ምስጋናው እረፍት ሆኖ ነው የሚኖረው ቢሆንም ግን ጥቂት ማረፋችን አይቀርም ሲል ለማጽናናት ሞከረ
ሦስተኛው ወጣት ግን የሱ ጭንቀት ሌላ እንደሆነ ነገራቸው እንዲህ ሲል እረፍት ብቻውን ምን ያደርጋል? በእረፍት ጊዜያችን ሻምፒዮን ስሊግና ላሊጋን የመሳሰሉት የእግር ኳስ ውድድሮችን መከታተል ካልቻልን

የመጀመሪያው ወጣት ጣልቃ ገብቶ አንተ ደሞ እሱንም ለማየትኮ ቅድሚያ የዕረፍት ጊዜ ሊኖረን ይገባል ማታ ውዳሴ ቀን ቅዳሴ ይህው ከገባን ጀምሮ ስንት ሰንበታት አለፉ በሰንበት እንኳ አናርፍም እኮ አለ ምርር ብሎ

#ለምን ካልሆነ እዚሁ ገነት ውስጥ wi fi እንዲገባ ና ለእያንዳንዳችን እስማርት ስልኮች እንዲታደሉን አናደርግም ከዛ በቃ ላሊጋ በል ሻምፒዮን ስሊግ በል በቃ ሁሉ በእጃችን ሆነ ማለት ነው በተጨማሪም ማኅበራዊ ድኅረ ገጾችን ከፍተን ምድር ካሉ ዘመዶቻችን ጋር ያለ ገደብ እንገናኝ ከናፍቆታቸውም እንገላገላለን አይመስላችሁም? ሲል ሀሳብ አቀረበ

ሁለተኛው ወጣት ድንገት ሳይታሰብ ገብቶ አይመስለንም ሲል አንቧረቀበት ጭራሽ ገነት ውስጥ ዋይ ፋይ ? ጭራሽ ገነት ውስጥ እስማርት ስልክ ? ገነትን ገነት ያሰኙት እኮ የነዚህ ነገር አለመኖር ነው አለዚያማ ከምድር በምን ተሻለ ሆሆሆሆ

#ሦስተኛው ወጣት ፈጠን ብሎ ምን ችግር አለው በምድር ሳለን ትዝ አይላችሁም ካህኑ በስማርት ስልክ ተደግፎ ተንስዑ ሲል ዲያቆኑት ቢሆን እያንዳንዱን የመቅደስ እንቅስቃሴ እየቀረጸ እዛው ማኅበራዊ ድኅረ ገጾች ላይ ሲለቅ አላያችሁም? ስለዚህ ብዙ ችግር ያለው አይመስለኝም አለ

እናንተ ሰዎች ያ በምድር ነው ሆኖም ትክክል ነው ማለት አይደለም።ምክንያቱም የምድሪቱ ቤተ ክርስቲያን የሰማያዊቱ ለዚህች ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናትና። (camera man) ቀራጭነትና ድቁና ፈሪሳዊነትና ክህነት አብረው አይሄዱም። ግማሽ መላጣ ግማሽ ጎፈሬ ብርሃንና ጽልመት እንዴት አንድ ይሆናሉ? ብንችል ለምድር ሰዎች እንጸልይላቸው እንዴት የነርሱን ስዕተት እዚህ እንደግማለን።

#አንዱ ወጣት የሆነ መላ ብልጭ ያለለት በሚመስል ሆናቴ ፍክት ብሎ ቆይ ከዚህ ሁሉ ጭንቅ ለምን ከገነት አንወጣም ?
ሌላኛው ወጣት ከዛስ ? ሲዖል ጥገኝነት እንጠይቅ?
አንተ ባክህ አቀልድ
በቃ ማለቴ ወደ ቀደመ ኑሯችን ወደ ምድር መልሱን ለምን አንላቸውም ???
ይቻላል እንዴ ? ገነትኮ ካገኙ ማጣት ከገቡ መውጣት የለም ማነው የሚያሶጣን?
ቀላልኮነው ለምን ገነት ውስጥ ያልተፈቀደ ነገር ለምን አናደርግም ከዛ በቃ በራሳቸው ጊዜ ያስወጡናል
አረ ባካችሁ ጓደኞቼ ምን ሆናችዋል? አዳምና ሔዋን በገነት ያልተፈቀደውን አድርገው ከገነት ሲባረሩ የምትገለባበጥ የኪሩቤል ሰይፍም ተመዞባቸው ነበር በኛ ደግሞ ይወድቅብን ይሆናል ማን ያውቃል ።
ማለት ገነት ሰይፍ አለ ? ታድያ ሰይፍ ካለ wifi ቢኖር ምን ችግር አለ? ቢያን አመስግነን ቀድሰን አወድሰን ስንጨርስ ትንሽ እንደበርበት ነበር እኮ ።

#ይህን ሲነጋገሩ ከቀደሙት ደጋግ አባቶች አንዱ በለወሳስ የምስጋና ውዳሴ እያቀረበ ወደ ወደ መንበረ መንግሥት ሲጓዝ አያቸው ከንግግራቸውም ያሉበት ቦታ እንዳልተመቻቸውና መውጣት እንደሚሹ ተረዳ መንገዱንም ገታ አድርጎ ወደ ወጣቶቹ ተጠግቶ ሰላምታ ሰጣቸው።
ከግርማ ሞገሱና ከንግግሩ ለዛ ተደመሙ የተነጋገሩትን አንዲቱንም ቃል ባልሰማን ብለውም ተመኙ። ያ ሰው ግን ያለ ዕውቀት እንደተናገሩ ያውቃልና እያለዛዘበ ጠየቃቸው ልጆች ምን ሆናችኋል የምረዳችሁ ነገር አለ አላቸው እነርሱ ግን ለማስቀየስ ተጠቃቀሱና አይ የለም አሉት በጋራ። መልካም ብሎ ጥሏቸው ጉዞዎን ሊቀጥል ሲል ግን አንደኛው ወጣት ግን አንተ ማነህ? ሲል የገነት ጠባቂ ጥጦስን የጠየቀውን ጥያቄ አቀረበለት አብርሃም ነህን አለው ያም ሰው ዝም አለ እሽ ሙሴ ነህን አለው ያ ሰው አለመለሰለትም በቃ ቅዱስ ጳውሎስ ነህን መሆን አለብህ አለው በጥያቄው ሳይሰለች ነኝም አይደለውምም ሳይለው እርሱ ይቆየኝ

ወጣትነት አስቸጋሪ ነው እኔም ወጣት ሳለው ብዙ ጠባያት እየተፈራረቁ አስቸግረውኝ ነበር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት በእናቱ አማላጅነት ሁሉም አልፌያቸው እዚህ ደርሻለው ከፈለጋችሁ ከልምዴ በማካፈል ልረዳችሁ እችላለሁ አላቸው። ካልሆነ ግን በሉ በደህና ዋሉ ብሎ ፊቱን አዙሮ መንገዱን ቀጠለ በእውኑ ግን ጥሏቸው ሊሄድ ልቡ አልወደደም ነበር

#ቢያንስ ከልምዱና ከዕውቀቱ ሊያካፍለን ይችላል በገነት ብዙ ስለቆየ መግቢያ መውጫውንም ሊነግረን ይችላል ለምን ሀሳባችንን አንነግረውም ተባባሉ በለወሳስ ቀስ ብለው። ከዛም አንደኛው ፈጠን ብሎ አባት አባቴ አንዴ ቆይ ብሎ ከኋላ ከተል እያለ ተጣራ አንድ ጊዜ አባቴ ሁለት ደቂቃ ይኖሮታል እባካችሁ ለምስጋና ወደ መንበረ መንግሥት እየሄድኩ ነው ከፈለጋችሁ ግን አብራችሁኝ እየሄዳችሁ የፈለጋችሁትን ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ አላቸው። እሺ ይሁን አብረኖት እንሄዳለን ብቻ እርሶ መፍትኤ ብቻ ይስጡን መፍትኤስ ከእግዚአብሔር ነው ግን ምን ገጠማችሁ ?

አንደኛው እጆቹን እያፍተለተለ በእግሮቹም ወደፊት አብሯቸው እየተራመደ ይህውሎት አባ እኛ የገነት ኑሮ ሰልችቶናል ወደ ቀደመ ቦታችን ወደ መሬት መመለስ እስፈልጋለን አለ ሁለቱ ሀሳቡን በመደገፍ በአውንታ ጭንቅላታቸውን አነቃነቁ ያ ባለ ግርማ ሞገስ ሰው ግን ፈገግ አለና ለአህያ ማር አይጥማት አሉ ሲል ተረተባቸው ቀጥሎም እርሷስ ሳያቀምሷት ነው አይጥማትም እያሉ የሚያሟት እናተ ቀምሳችሁ ሳለ እንዴት ሳይጥማችሁ ቀረ ለመሆኑ ገነት ምን ጎደለ?

#አንዱ ቀበል አድርጎ ሻምፒዮ ሲሊግ የለ ፤ ላሊጋ የለ ፤ facebook የለ ፤ instageram የለ ፤ ጠዋት ቅዳሴ ማታ ውዳሴ ይሰለቻልኮ አባ

አይ ልጆቼ ይህ ነው ጭንቀታችሁ ይህን እናንተ ያያችሁትን እኮ ብዙዎች ሊያዮት ወደው ሊያዮት አልቻሉም እስራኤል የሰማይ መና ሰለችን ሥጋ አማረን ቢሉ መና ("ና"ይላላ) ሆነው ቀሩ። የተመኙት ሥጋ ተሰጣቸው ከአፋቸው ከተው እንደቀመሱትም ሁሉም እረግፈው ሞቱ ቦታዋም እስከዛሬ ድረስ የምኞት መቃብር ተብላ እየተጠራች ነው። ምነው ከሕይወት ይልቅ የምኞት መቃብርን ሻታችሁ ከመና ይልቅ መና መሆንን ወደደዳችሁ?
#እናንተኮ ገነትን እንዲ የጠላችዋት አስቀድማችሁም ስላሎደዳችዋት ነው ።አስቀድማችሁ በምድር ሳላችሁ ብትወዷት ኖሮ ዛሬ ባልሰለቻችሁ ነበር።
እንዴ አባ በምድር ሳለን ገነትን የት አገኝተናት ጠላና እሷ ያለችሁ እዚህ የት ተገናንተን አባ አል አንደኛው ንግግራቸው ድፍን ቅል ሆኖበት ያ ሰው ግን አብራቹ ነበረች እንጂ። ምድራዊቷ ቤተ ክርስቲያን ዕለት ዕለተ ታስቀድሱ ነበር ? ትቆርቡ ነበር?ማኅሌቷን ሰዓታቷን ትካፈሉ ነበር?
አይ አባ አልፎ አልፎ ግጥሚያና ትሬሊንግ ከሌላን እናስቀድሳለን በየ5ዓመቱም እንቆርባለን ሰዓታትም ቢሆን እግር ካደረሰን መቆሚያ ተደግፈን ጥቂት እንቆማለን።

#እሱንኮነው የምላችሁ እናንተ የሥጋ ትሬሊንግ እንጂ የመንፈስ ትሬሊንግ አድርጋችሁ አታውቁም በምድራዊቷ ገነት በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ልምምዳችሁን በአግባቡ ስላልተለማመዳችሁ ሰማያዊቷ ገነት ሰለቸቻችሁ እናንተ ብቻ አይደላችሁም ብዙዎች በቤተመቅደሱ ሥርዓት ዝለው በሰማይ ገነት የሚበረቱ ይመስላቸዋል እንዲያ ግን አይደለም እግዚአብሔር ቸርነቱ በዝቶ ያለ ብዙ ትሩፋትና ድካም በየ ጥቂቱ ምሮ ሁሉንም ሰው ገነት ቢያስገባ እንኳን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብዙዎች ገነትን ይሰለቹና ካሎጣን ማለታቸው አይቀርም ምክንያቱም በምድር አልተለማመዷትምና ።

የዓለሙ ጫጫታና ውክቢያ አንዱን ቀራጭ ሌላውን ፈሪሳዊ አድርጎ እየጎተተ ያስቀረዋልና መልካም እንድትሆን በሚል ሰበብ የተሸከምከው በግ ውሻ ነው ጣለው እያሉ መልካሚቱን ቤተ ክርስቲያን ጥሎ ለሰማያዊቱ ገነት የተገባ ሆኖ እንዳይገኝም የልምዱን ጊዜ ከማያምኑ ጋር እንዲያጠፈ ይገደዳል ።በዚህ ዓይነት ታድያ ሦስት ሰዓት ቆሞ ማስቀደስ ጭንቅ የሚሆንበት እንዴት 24ሰዓት ከቅዱሳኑ ጋር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ለማለት ይቻለዋል።
#እግዚአብሔርምኮ ጸጋ የሚሰጠው በጣሩበት በለፉበት በወጡበት በወረዱበት በዋሉበት እኮ ነው "..እንበለ ድካም ወጻሕማ ኢይትረከብ ጸጋ እግዚአብሔር..."ያለ ድካምና ልፋት የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲሁ አትሰጥም እዲል መጽሐፉ። ገባችሁ እንዴ ልጆቼ ሲሉ ጠየቋቸው ሦስቱም በአውንታ አገታቸውን ነቀነቁ። ስለዚህ አሁን ምን አሰባችሁ በገነት መኖር ወይስ ከገነት መውጣት? ሁሉም በአንድላይ በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው የሚል ሀሳብ መጣላቸውና ካቀረቀሩበት ቀና ሲሉ እራሳቸውን ከምስጋናው ከተማ ከውዳሴ ሀገር ከመንበረ መንግሥት አገኙና መሰልቸት በማያገኘው መንፈስ ደስ እያላቸው ለምስጋና ገቡ።
..............ይቆየን።
አ.አ አበባ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
መስከረም 1/1/2015 ዓ.ም
#በቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ " #ራስ " የክብር የበላይነትን የልዕልና መገለጫ ነው። ቤተ ክርስቲያናችንም ርዕሰ ዕሩሳን ክርስቶስ ርዕሳተ ደናግል ድንግል ማርያም ርዕሰ ነቢያት ሙሴ፣ ርዕሰ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ርዕሰ ባሕታዊያን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እያለች ታስተምራለች።
በሀገራች ታሪክም ከሥልጣን ማዕረጋት መካከል የራስነት ማዕረግ የተለመደ ነው። ራስ ተፈሪ፣ ራስ አሊ ፣ራስ መኮንን እንደሚባለው ። ዛሬ ዛሬ ግን ይህ ስም የዘፈን ናዝራዊያን የሆኑ ሰዎች ፀጉራቸውን በማስረዘም ራስ(ራስታ) ተብለው የጨለማው ዓለም ገዢ ኤሮድስን ለማስደሰት የሚዘፍኑ የዘማዊያን መጠሪያ ሆኗል።
#ሄሮድስ የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት ሄሮድያዳን ያገባት ዘንድ ፈለገ ዮሐንስ ግን እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም አለው። ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው። አሳስሮት በወህኒ(እስር ቤት) ዘጋበት፤ ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤ ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ እንዲሰጣት በመሐላ ተስፋ አደረገላት።
እርስዋም በእናትዋ ተመክራ፦ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በዚህ በወጭት ስጠኝ አለችው። ንጉሡም አዘነ፥ ነገር ግን ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ተቀምጠው ስላሉት ሰዎች እንዲሰጡአት አዘዘ፤ ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ አስቆረጠው።
#ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፥ ወደ እናትዋም ወሰደችው ። እናቷ የሄሮድያዳ የነቢዮን ራስ በወጪት ይዛ ምላሱን ወደ ውጪ አውጥታ አንቺ ነሽ የንጉሥ ሚስት ሆኜ ንግሥት እንዳልባል ያደረግሽኝ እያለች በወስፌ ትወጋው ትጠቀጥቀው ነበር የነቢዩ እራስም ክንፍ አውጥታ በራ ሄዳ ለ15 ዓመታት ዞራ ወንጌልን ሰብካለች #ማቴ 14÷3-12
አንባቢ ሆይ ዘፈንን ዕርም ብለህ ተው። ዘፋኞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አይገቡምና #ገላ 5÷16 ደግሞ እኔ አልዘፍንም የሚዘፍኑትን እሰማለው፣ዐያለው እንጂ አልክን ? ሄሮድስን ለዘፉኝ ወለታ የነቢይ ራስን እንዲሰጥ ያደረገው ዘፈን መስማትና ማየቱ አይደለምን? ሄሮድስ ቅዱስ ዮሐንስን የመሰለ ርዕሰ ያጣው ዘፈንን በማየቱና በመስማቱ ነው። ዘፉኝ ካየህ ዘፈን ከሰማህ እራስህን ታጣዋለህ ራስ ክርስቶስን ነው ነውና እራስህን ጠብቅ ።
#ራስ የአካል ሁሉ መዲና ናት አካል ያለ ራስ ምንም ነው ወይም በድን ነው እራስ ግን ያለ አካል ሕያው ሆኖ መቆም ይቻለዋል። ለዚህም የነቢዮ ዮሐንስ ራስ ሆነኛ ምስክር ናት ከአካል ከተለየች በኋላ 15 ዓመት ዞራ አስተምራለችና። መጋቢ አዲስ የኔታ እሸቱ እንዳሉት የሰው ዋነኛ መገለጫው ራስ ነው ሰው ለመታወቂያ የሚያገለግል ፎቶግራፍ እንኳን የሚነሳው ከአንገቱ በላይ ያለውን የራሱን አካል ነው እንጂ እግሩን ወይም ደረቱን አይደለም።
ዋና ዋና ስብአዊ ተግባራት የሚፈጸሙትም እራስ ላይ ባሉ ልዮ ልዮ ባለ ድርሻ አካላት ነው። እነማ ቢሉ ዐይን ፣ጀሮ፣ አፍንጫ ፣አፍ /ምላስ። ገድለ ጊዮርጊስ ደግሞ አዳሪ በማኅደሩ ማኅደሩም በአዳሪው የመጥራት የመጻሕፍት ልማድን ተጠቅሞ ዐይን ፣ጀሮ፣ አፍንጫ ፣አፍ /ምላስ በማደሪያቸው በራስ ቅል አማካኝነት ራስ ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ ይላል። ግሩም ነው ! ዳዊት የጎልያድን ራስ ቆረጠ ሲባል ዐይን ፣ጀሮ፣ አፍንጫ ፣አፍ /ምላስ ን አልነካም ማለት አይደለም እነርሱም በራስ ያሉ ናቸውና እነርሱም ተቆረጡ ማለት ጭምር ነው።
#እንደ እባብ ልባሞች ሁኑ በማለት የእባብ ልባምነቱ የተገለጠበት ዋነኛ ምክንያትም እባባ ከአካላቱ ሁሉ እራሱን (ጭንቅላቱን) ከምት ከዱላ መጠበቁ ነው። ወገቡ ጢቆረጥ አይሞትም ጭራው ቢበጠስ እስትንፋሱ አይቋረጥም ጭንቅላቱን ከተመታ ግን ሕያውነቱ ያከትማል ስለሆነም ጥንቅላቱን ወይም የራስ ቅሉን በከፍተኛ ጥንቃቄ ከምት ይጠብቃል። እባብን ልባም ካሰኚት ጠባዮቹ አንዱ እራሱን መጠበቁ ነው ።
እራስ የተባለች ሃይማኖት ነች ሃይማኖቱ በምንፍቅና ሀሳብ የተመታ ሰውም ምንም ምግባር ትሩፋት ቢኖረው ዋጋ የለውም የሞተ ነው እራሳችሁ የሆነች ሃይማኖታችሁን ከመናፍቃን ጥርጥር ከአሕዛብ ክሕደት ጠብቋት ሲል ነው።
#ሐዋርያው ሃይማኖቴን ጠብቄያለው ማለቱ እራሴን ጠብቂያለው በክፉዎች ምክር አልሃድኩም በኃጢያተኞችም መንገድ አልቆምኩም በዋዘኞችም ወንበር አልተቀመጥኩም ማለቱ ነው። 2ኛ ጢሞ 4፥7 መዝ1÷1 “በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።” #ማቴ 7፥6

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
መስከረም ፪ቀን ፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም