ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
የብዙ ቅዱሳን ማረፊያና መፍለቂያ #የቅዱሳን_ወደብ_ሀገረ_እግዚአብሔር_ኢትዮጵያ

#ልዮ ልዮ ወደቦቻችንን አተናል የቅዱሳን ማደሪያ ወደብ መሆናችንን ካጣን ግን ከቀድሞ ይልቅ አሁን ይብስብናል።

#ኢትዮጵያ_የብዙ_ቅዱሳን_ወደብና_የክርስቲያኖች_ደሴት_ናት !
ከተራ #ዘኢትዮጵያ
_______
#ሳቢ ያልቅ ይ እንጂ ሐሳብ አያልቅም! ስለዚህ ሀሳብ ቦይ እስካገኘ ድረስ ፈሶ
የማያልቅ ወንዝ ነው ። ይልቁኑ መነሻቸው በምድር የማይታወቁ ገነታዊ የሆኑ ወንዞች ለዚህ
ጥሩ ማሳያዎች ናቸው።
ሀገራችን ሁል ጊዜ የጥምቀት በዓልን ምክንያት አድርጋ ዋዜማውን ማለትም ጥር 10 ቀንን
" ከተራ " ብላ ታቦት ከመንበሩ አንስታ ድንኳን ወደ ተተከለበት የታቆረ ፣የተከተረ፣የተገደበ
ውኃ ወዳለበት ሥፍራ ይዛ በመሄድ በልልታና በግርግርታ በድምቀት ከምዕመኞቿ ጋር
ታከብረዋለች ። ኢያሱ 3÷3
#ይህንንም ማድረጓ አምላካችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ መጥቶ
ያጥምቀኝ ሳይል ወደ ባሪያው ወደ ዮሐንስ በትሕትና ሄዶ መጠመቁን ለማሰብ ነው።
የትሕትና አባት ! ይህን በማድረግ ባያስተምረን ኖሮ ዛሬ ካህናቱ ቤታችን መጥተው
ያጥምቁን ባልን ነበር። ከተራ የቃሉ ትርጉም መገደብ ፣ በአንድ ቦታ መርጋት (ለፈሳሽ
ነገር)፣ መታቆር ፣መቆም ወይም ማቆም የሚል ነው።
ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ " እነሆ ውኃ ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው? " ብላ
ከተጠመቀችበት ጊዜ አንስቶ ይህው ዛሬ ድረስ ምሥጢረ ጥምቀትን በሚገባ ለልጆቿ
ስታስተምርና ሥርዓቱንም ስትፈጽም ኖራለች ። ወደ ፊትም ትኖራለች። # ሐዋ 8÷36
#ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የጥምቀትን በዓል ማክበር የጀመረችሁ በኩረ ጳጳሳት ዘኢትዮጲያ
የሚባሉት " ፍሬ ምናጦስ" ወይም ሕዝቡ ከፍቅሩ ጽናት የተነሳ ፊደል ቀርጾ ንባብ አደላድሎ
የድንቁርናን ጽልመት ገፏልናልና ብለው " አቡነ ሠላማ ከሳቴ ብርሃን " /የሠላም አባት
ብርሃንን የሚገልጥ / እያሉ ይጠሯቸው በነበሩት በመጀመሪያው ታላቅ ጳጳሳችን ትዕዛዝና
መመሪያ ነበር።
ከዛ በመቀጠል እነ አፄ ገብረ መስቀል፣ እነ አፄ ናዖድ እና አፄ ዘርዓ ያዕቆብ የመሳሰሉት
ቅዱሳን ነገሥታት ይህ ደገኛ የጥምቀት በዓል በአደባባይ እንዲከበር አድርገውታል።
ዛሬ ዛሬ እነዚህን የመሰሉ ቅድስናን ከንግሥና አስተባብረው የያዙ መሪዎችን በማጣቷ
ባህሏን ፣ወጓን፣ ሃይማኖቷን ፣ትውፊቷ ፣ሥርዓቷን በአደባባይ ወጥታ እንዳታከብር ጫና
እያሳደሩባት ትገኛለች።
#እርሷ ግን ተስፋዋ እግዚአብሔር ነውና ዛሬም ወደ ዮርዳኖስን መውረዷን አላቆመችም ።
አንድነት ይዛለች ፣ ፍቅር ከትራለች ፣ ሠላም ጸንሳለች መለያት እንዳያጨነግፋት፣ አጥንት
ቆጣሪነት እንዳይበትናት እንጠንቀቅላት።
ይህ ሀገራዊ ከተራ ከመንፈሳዊ ክትረት ምሳሌነት አልፎ በየ ቤታችን መብራትና እራት ሆኖ
የሚመጣ የብልጥግናችን ቀንዲል ነው። ከተራውን ከተራ ነገሮች ሁሉ ወጥተን በአንድነት
የምንረጨው ጥሩ ውኃ ያድርግልን። # ሕዝ 36÷25
"ሃይማኖት፣ ብሔር፣ዘር የማይለኝ ሰናይ ከተራ... #ዓባይ !"
ኃ/ማርያም
አ.አ ኢትዮጵያ
10/2013ዓ.ም
" #ኢትዮጵያ እኮ ሠላም ብታገኝ ጠንካራ የምትሆን ሀገር ናት" ቤተ እስራላዊው #አባ ዮናታን /ሚተራሊዮን /
ዝመት አትበለኝ
_______________
ወንድሜን ፊት ለፊት ተሰልፎ እያየሁ
በየትኛው እጄ ቃታ እስባለሁ
ዝመት አትበለኝ በማን እዘምታለሁ
እዛም የሚቆረስ ግማሽ አካሌ ነው
የተንቀዠቀዠው....
የተቅበዘበዘው......
እርካታ ያላገኘው.......
ጀግና ያልተባለው........
እንዴት ወንድም ገዳይ ቃየን እሆናለሁ ?

መታሰቢያነቱ :- |ለቅድስት ሀገር #ኢትዮጵያ

አ.አ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም