ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
#ጉባኤው
_____
መስከረም :- ለምን እንደሆነ ጉባኤ የጠራነው
አንዳችንም ሳንቀረ የተሰበሰብነው?
ወርኃ ጥቅምት በቶሎ እንዲገልጠው
ሰብሳቢው መስከረም እድል እሰጣለው

ጥቅምት ፦ አዎን ጋሽ መስከረም የወራቶች አውራ
አመሰግናለሁ ዕድል ስለሰጡኝ እኔ እዳወራ
ያሉት ትክክል ነው አንድም ወር አልቀረም
ችግሩ ጥልቅ ቢሆን ባይሆን የማያከርም
ሁሉንም ወር ቀጥረን እዚህ ተጠራቀምን

ኅዳር ፦ ሁሉም እንደመጣ እናረጋግጥና
ጉባኤው ይጀመር በታላቅ ጦሞና


መስከረም :- ጥሩ መልካም አልከን ወንድማችን ኅዳር
ሁሉም በሥርዓቱ ተሰፍሮ ይቆጠር
መቼም ከተያዘ ወግ አይቀርምና
ኅዳር አንተ ትጉ ብዕርን አውጣና
ቃለ ጉባኤ ያዝ ካፍ ካፍ ልቀምና


ኅዳር :- እሺ ታላቁ ወር የመጀመሪያችን
በሙሉ እጥፋለሁን ሳላስቀር አንዳችን

ጥቅምት :- እኔም ጥቅምት አለው የጉባኤው ድምቀት
ጋሽ መስከረም እርሶ ጉባኤውን ሲመሩት
እቀላጠፋለው ሀሳብ እንዳይነጥፍ
ከአንዱ ወደ ሌላው እያልኩኝ ቅልጥፍጥፍ

ማንም እንዳልቀረ ቢያውቅም ልቦናዬ
ወግ መጠበቅ ነውና ዋነኛው ሥራዬ
ማን ማን እንደመጣ ሊታደም ጉባኤ
አሁን እጠራለሁ እርሶን አስቀድሜ
ጋሽ መስከረምዬ ስዩመ ጉባኤ


ታህሳስ ና ጥር የካቲት መጋቢት
እነዝያውናቸው ሚያዝያ ና ግንቦት
ሰኔም ተገኘታለች ይህች አሳባቂ
የክረምቱን መድርሰ ቀድማ አሳዋቂ
ሐምሌ ና ነሐሴም ጉም ድመና ለበሰው
ጋቢ የደረቡ አዛውንትን መስለው
በቀኘ ይታዩናል ዶፍ ዝናብ አርግዘው

/ ይህን ጊዜ ጉባኤው በሳቅ ይታወካለል /

ሐምሌ ፦ ለአነጋገር ልክ ለከት አብጅለት
ምን ብትንቀን ነው ነፍሰ ጡር ያረከን ?
አለዛ ታርመህ አደብን ካልገዛህ
የያዝነውን ውኃ በአንድነት ለቀን
ጉድ እንዳናረገህ በጎርፍ አሶስደን

መስከረም ፦ ጥቅምት አንተም ተው አንተም ታገስ ሐምሌ
እርምጃ እወስዳለሁ እኔ ግን በግሌ
ሌላ ሆኖ ሳለ መነጋገሪያችን
በንቀርት ላይ ደግፍ ሆነ ችግራችን
ደራሽ ጎርፍ ማዘዝ ይቻለኛል ብለህ
አትኩራ በክብር በተሰጠህ ነገር
ልታቅ ይገባሃል ስለሞቃም ወር
መፎከር አይበጅም ጉልበትን ተማምኖ
ለአንዱ ሲሰጠው እንዲወስድ በትኖ
ለሌላው ይሰጠዋለል እጥፍ ድርብ ሆኖ
አሙቆ አፍልቶ የሚያስቀር አትኖ
አሉባልታ ወሬ ቧልቱን እንተውና
የስብሰባው አላማ ይህ አይደለምና
በቶሎ እንመለስ በቀናው ጎዳና

ታኀሳስ :- በሉ አታንቃቁን በቶሎ ጀምሩ
የተጋረጠብን ችግር ካለም አውሩ
አውርተን እንፍታው ነገሩን ከስሩ

ሚያዝያ :- እኔም እስማማለው በሀሳበ ጥር
ቶሎ ተገልጦልን ሰብሰባው ቢያጥር
ምንድ ነው ምሥጢሩ የመታደማችን
ምን ችግር ገጠመን ከመካከላችን?

መስከረም :- እንግዲህ ለማንሳት ከሥሩ ነገሩን
ብርቱ ችግር መቷል የሚነጣጥለን
አንድነትን ፈቶ ለብቻ የሚያቀረን
ስለዚህ ተወያይተን አውርተን በጋራ
ሀሳብ ለማዳመጥ ጉባኤ ተጠራ


ሰኔ : አረ ሰብሳቢያችን ታላቅ ወንድማችን
ምን ይሆን ነገሩ እንዲህ ያሰጨነቀን
ተነፋፋው እኮ ነገር ሆዴ ገብቶ
እኔ እንደው ወሬ አልችል ንገረን በቶሎ
ሰኔን እያወከኝ ለወሬ የሞትኩ ነኝ
በዘንድው እንኳ ክረምት መጣው ቢለኝ
ቀድሜ ዘረገፍኩ ዝናበ በረከቱን
ገና ሳይጠጋ ዘመነ ክረምቱ
እናማ ንገሩን ነገር ሳታረዝሙ
ብሶ እንዳይገለኝ የወሬ ጥማቱ

መስከረም : -እስቲ ተረጋጊ ሰኔ አትጣደፊ
አንዳንዴ ወሬውን ሰምተሽም እለፊ
ችግርና ሐዘን የገጠሙ ለታ
መቅደም ይገባዋል ሁል ጊዜም እርጋታ

ነሩን ስጀምር ማስረዳት ሀ ብዬ
ሐዘኔ ጥልቅ ነው ይህን በማለቴ
13 ሆነን
በስካሁን ኑሯች በምድረ ኢትዮጲያ
እንዳችን የጌታ ሌሎቻን የ12ቱ ሐዋርያ
ምሳሌዎች ሆነን ኖረናል በአራያ

ጥቅምት :- አፌ ቁርጥ ይበል መስከም ሊቃችን
ምሥጢር አርገህ መሰልከን

መስከረም :-አመሰግናለሁ አክባሪዬ ጥቅምት
ግን ግን ታዝን ነበር ብትታገስ ጥቂት
እንዲሁ ቢያዛልቀን ነበረ በቀና
ዛሬ ግን በዓለም ዕውቀት በዛችና
ዋዜማ ላይ ሆንን ለመለየት ዜና

(ይህን ጊዜ ጉባኤው በጫጫታ ይታወካል ዋዜማ ለመለየት ዜና ሆሆሆ ወዘተ በሚሉ ወሬዎች )


ጷጉሜ :- አንዳችን የጌታ ሌሎቻን የ12ቱሐዋርያ
ምሳሌዎች ሆነን ከኖርን በምድረ በኢትዮጲያ
አሁን ደርሶ የሚለይ ምን ተአምር መጣ?

ግንቦት :- አይ ጷጉሜ የዋህ እህት
የሐዋርያትም ሕብረት ከጌታችን ጋራ
ተፈቶ የለም ወይ በአይሁድ ፉከራ
ፈሪሳዊ ዕውቀት እርሾዎ ሲንሰራፋ
የሥላሴ አምሳል የሰው ልጅም ከፋ
እስካልተቆጠብን ከፈሪሳኢ እርሾ
መፈጠሩ አይቀርም በፍቅር ላይ ቁርሾ

ጷጉሜን :- የሆነውስ ሆኖ እኛን የሚለያይ ምን እርሾ ተገኘ
የሰው ልጅ አይደለን ዘር ቋን ቋ አለየን
ለያይቶ ከፋፍሎ ለብቻ የሚያደርገን ?

መስከረም :- እንግዲህ ጷጉሜያችን ትንሿ እህታችን ችግሩ ይህ ነው
ያንቺ ከኛ ጋራ አብሮ መቆጠር ነው
አንዳንድ ዕውቀት ገባን ታረቀቅን ያሉ
ጷጉሜ ከወራቶች ትቀነስ ነው ያሉ