ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#እራስህን ፈትሽ

የዛሬ ዓመት አካባቢ ነው ወቅቱ እንደ አሁኑ የሽብር ቡድኑ እና የcovid 19 ስጋት መንግስትን ያስጨነቀበት ወቅት ነው። ምሽት አካባቢ አገልገሎት ጨርሰን ወደ ሰፈር እያመራን ነው። የጸጥታ ኃይሎች (የፌደራል ፖሊሶች) በየ አስፋልቱ መዐዘናት ቆመው አላፊ አግዳዊውን አስቁመው እንደ መፈተሽ ዐይነት ነገር ይሰራሉ።

#እኛም ወደ ሰፈር ለመግባት ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩን በአንዱ አስፋልት ላይ መንገዱን አጥረውት አገኘንና ለመፈተሽ ተበታትነት ወደ ጸጥታ ኃይሎቹ ቀረብን ።እኔ በበኩሌ እጄን ከኪሴ አውጥቼ ወደ ግራና ወደ ቀኝ ዘርግቼ የመስቀል ምልክት ሰርቼ ለመፈተሽ ተዘጋጀው ፊት ለፊቴ ያለው ፖሊስ ግን ምንም የመፈተሽ አዝማሚያ ሳያሳይ የሆነ ነገር ተናገረ ግራ ገባኝና ይህው አልኩት ዝግጁ መሆኔን ለማሳወቅ #እራስህን_ፈትሺ አትሰሚም እንዴ? ሲል ጮክ ብሎ ደገመው አንደኛ እና ሁለተኛ መደብ እንዲሁም ጾታ ነጠላና ብዙ ቁጥር የማይለየው ንግግሩ ከወዴት እንደሆነ ጠቆመኝ ያው የወድሄት ነህ ዘመን ላይ አይደለን ?!
እውነት ለመናገር እራስህን ፈትሽ እንዳለኝ መጀመሪያውኑ ሰምቼዋለው ግን እራሴን ፈትሼ ንጹዑ ነኝ ምንም አልያስኩም ነው የምለው? ወይስ ይህው ሁለት ስለትና አንድ ተቀጣጣይ ፈንጂ ከኋላ ኪሴ ይዣለሁ ብዬ እራሴን እንዳጋልጥ ነው የፈለገው ብዬ ግራ ስለገባኝ ነው።
#እንዴት እራስህን ፈትሽ ሊለኝ ይችላል ብዬ እርግጠኛ ለመሆን ለሦስተኛ ጊዜ በድጋሚ እህህ ልል አሰብኩና ወዲያው ማዳመጫዬን ከማላመጫዬ ሲደባልቀው ስለታየኝ ተውኩት ከዛም የሰማሁትን ግን ያልገባኝን ንግግሩን መተግበር ጀመርኩ ።እራሴን እንደነገሩ ዳባበስኩና ይህው የለም ስለው መንገዱን ከፍቶ እንዳልፍ ፈቀደልኝ።

እስከ ዛሬ ድረስ ማለትም ለ365 ቀናት ከ 91ኬክሮስ ድረስ ፖሊሱን እንደ ሞኝ ቆጥሬ ስስቅ ነበር። ያሳቀኝ ለcovid 19 ተዛማችነት ያሳየውን ጥንቃቄ ከግምት ውስጥ በለማስገባት አይደለም ። በዚህች በራስ ወዳድ ዓለም ሳለን ማን እራሱን ፈትሾ ጥፋተኛ ነኝ ልቀጣ ይገባኛል ሊል ይችላል ቤዬ ስላሰብኩ ነው እንጂ።

#አሁን ግን ዓመቱን ሙሉ ስስቅ የከረምኩት በራሴ መሆኑ ዘግይቶ ገባኝ ።ሰው ለራሱ ታማኝ ከሆነ በፍጹም ለሌላው መታመን አያቅተውም። አንባቢ ሆይ አንተ እራስህን በታማኝነት ስራው ከዛ በብዙ አማኞች ትከበባለህ አንተ ቀድመህ እራስህን ከፈተሽክ ማንም አንተን ሊፈትሽህ አይችልም ቢፈትሽ እንኳ ትርፉ ድካም ብቻ ነው ።ምንም አይገኝብህምና !
“እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።”
|1ኛ #ጴጥ 2፥5

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ጳጉሜ 2/2014 ዓ.ም