ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የአድዋ_ተራሮች ትዝብት
_____

ቲሺ ምናለ ከዚህ ንበር ትንሽ ቀቅ ብዬ በተፈጠርኩ ካድማሱ ባሻገር እንደ ሰንሰለት ከተያያዙት ከአድዋ ተራሮች በመጠኑ ተለቅ የሚለው የአንዱ ተራራ የምሬት ንግግር ነበር

#እንዴ ይህ እኮ እኛ የተፈጠርንበትን የነጻነት ጀንበር የተፈነጠቀበት የኢትዮጱያ መሬት ነው ይህን መሬት ስንቱ ተራራ ሊፈጠርበት እንደሚመኝ እረስተህው ነው ።

ሌላኛው ከግራ ያለው ተራራ ቀበል አርጎ የዓለምና የአፍሪካ ስመ ጥር ተራሮች ኤቨረስትና ኪሊማንጃሮ እራሳቸው ረጃጅሞች ስመ ጥር ተራራሮች ሆነው ከሚታወቁ ይልቅ እዚህ ቦታ ተፈጥረው የጥቁር ሕዝብ ድልን የሰውልጅ እኩልነት የነጻነት ቀንዲል መለኮሰን ዕብሪተኝነት አንገት ሲደፈ ጨዋነት ሲረታ ቢያዮና የጀግኞች የዐይን መስክር ቢሆኑ የበለጠ ደስተኛ ይሆኑ ነበር። አንተ እዚህ በመፈጠረህ ታማርራለህ

#ግዙፉ ተራራ ከመካከላቸው ሆኖ ዐይ የልጅ ነገር እሱ መቼ ጠፋኝ " ለቀባሪው አረዱት አሉ " እናንተ በዚህች ምድር ከመፈጠራችሁ በፊት እኔ ቀድሜ ነበርኩ አድዋ ጦርነት እራሱ ከእናንተ የተሻለ ቁመናና ርዝመት ያለኝ በመሆኔ ከናንተ በተሻለ የጦርነቱን ሙሉ እንቅስቃሴ ለማየት ታድያለው የአባ ነብሶ ድፍረት መድፉን ለብቻ ሲያጓራው ፣የገበየው ደረት ደልብጦ መግባት ፣የጣይቱ ብልሐት፣ የምኒልክ ጽናት የሰማዕቱ እርዳታ ሁለም እንደ ትላንትና ሆኖ በሐይኔ ሕሊናዬ ተሰሎ ተቀምጧል መቼም ልረሳው አልችልም ያቺ የኃላ ደጀን የነበረች አዝማሪ ጻድቄ እራሱ ሳትቀር ከነ ግጥሞቿና ከነ አበረታች መሰንቆዋ የዕለት ለዕለት ትዝታዬ ነች እንዲያውም አንድ ጊዜ ጠላት በአድዋ ሥላሴ በኩል ገፍቶ ሲያይል "የአድዋን ሥላሴ ጠላት አረከሰው ገበየው በሞቴ ግባና ቀድሰው " ብላ ገጥማ ነበር።
ታድያ ይህን ያክል የምታስታውሰው ከሆነ ምን ቢመር ነው ከዚህች የነጻነት ድንበር ውጪ መፈጠርን የፈለክ? ሆ ሰው እንዴት ሰው አልኩ እንዴ ተራራ እንዴት በተመረጠ መሬት በነፃነት ሀገር ተፈጥሮ ሲያበቃ ለምን በዚህ የነፃነት ሀገር ተፈጠርኩ ብሎእንዴት በከንቱ ያማርራል?
#በከንቱ_አይደለም ማማረሬ እውነት ይዤ እንጂ ። በግራና በቀኝ ያሉት በመጠናቸው አነስ የሚሉት ተራሮች በተመሳሳይ ሰዓትና ቃል ማለት አልገባንም? አሉ።

ከመካከላቸው መሆኑ እንደፈለጉ ጥያቄ እየጠየቁ እንደ ገና ዳቦ በጥያቄ ሊጠብሱት የተዘጋጁ አስመስሏቸዋል። ከዛ አንደኛው ተራራ ከአድመኝነት መንፈስ ወጣ ለማለት ብሎ ሀሳቡን ለመረዳት ትንሽ ፋታ ከወሰደ በኋላ እስቲ በል ንገረን ምንድነው ይህን ያክል ቁጭት አሳድሮ የተፈጠርክበትን የነፃነት ምድር ለመጸየፍ ያበቃህ? ሲል በእርጋታ ጠየቀው
እሳት አመድ ወልዶ ሳይ እንዴት የቁጭት ቆፈን አይውረሰኝ? በዕድሜ አንጋፈ አዛውንት የሚመስለው ተራራ ሳግ እየተናነቀው እንዳይታወቅበት ጉረሮውን እያጸዳ ቀስ ብሎ ቁጭቱን ሊያስረዳቸው ጀመር።
#በዚህ ቦታ በኖርኩበት በእስኳሁኑ ዕድሜ እንዲህ ዐይነት ውርደትና መሸማቀቅ ደርሶብኝ አያውቅም ። ጥንት ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ጠላትን በዚህ ሥፈራ ድል ሲነሱ ለ ሀገር ለድንበር ለሃይማኖት ለአንድነት ለአንድ ሕዝብ ብለው ዋጋ ፍለው ደም አፍስሰው ሥጋ ቆርሰው አጥንት ገብረው ባለፉበት በዚሁ ሥፍራ በገደሉበት ሥፍራ ሲገዳደሉ ነጻ በወጡበት ሰፈር ምርኮ ሲገቡ ድል በነሱበት ሀገር ድል ሲነሳሱ ከማየት ሌላ ምን ውርደት አለ? የዘንድሮስ አድዋ ፋሽሽት ኢጣሊያንን ወይስ የእናት ልጅ ወንድምን ድን የነሳንበት በዓል ነው ብለው ሊያከብሩት ነው ?

የጀግኖች ደም ዋጋ ቢስ ሲሆን ከማየት ሌላ ምን አስቆጪ ነገርስ ይኖራል ? እነሱስ አንዴ ለሀገር ለድንበር ለነፃነትና ለሃይማኖት የሚገባቸውን ዋጋ ከፍለው በክብር አርፈዋል ይብላኝ እንጂ ለኔ ሞት ወስዶ ለማይገላግለኝ ግዑዝ ነው ይሉኛል ምንም የማይሰማኝ ንግግሬን ማድመጥ ያልቻሉ እነሱ መሆናቸው ማን በነሱ ቋንቋ በነገረልኝ

#ያኔ ቋንቋ ብሔር ዘር ሳይለያቸው እንደ አንድ ልብ መካሪ አንደ አንድ ቃል ተናጋረ ሆነው ጠላትን ያስጨነቁ ዛሬ ብሔሬ ቋንቋዬ ተባብለው ሲተላለቁ በዚሁ ሥፍራ ሳይ ለምን አልበግን

ደሞኮ ቋንቋውም ቢሆን በቅጡ የአባቶቻቸውን ቋንቋ አቀላጥፈው አያውቁትም ሁሉም ባለ ቋንቋ ነኝ ባይ ከእንግሊዘኛ ሳያዳቅል ማን በቅጡ የሚናገራቸው አለ እስቲ ቆንጆ ኦሮምኛ ተናጋሪ አምጡልኝ እስቲ ንጹሑ አማርኛ አንደበት ያለው ፈልጉልኝ እስቲ ትግርኛን አቀላጥፎ የሚያወራ የሰሜን ሰው ፈልጉልን የለም አታገኙም ። ለመጠፋፋትና ለመገዳደል ሲሆን ግን ብሔሬ ቋንቋዬ ይባልልኛል አስቀድመህ በቅጡ ውረስወ እስቲ ።

#ሁለቱ ተራሮች ምንም ሊመልሱለት አልቻሉም ከልብ ያልኖረ እውነት ከየት ይገለጣል።

እሱማ እውነትህን ነው በሚል በተጸጸተ አስተያየት ከግራም ከቀኝም ተመለከቱት

የላሊበላ መቅደስ ሰሪዎች እናንተ አይደላችሁም ቢሆንማ ኖሮ ሌላም አስደማሚ የኪነ ሕንጻ አብዝታችሁ ሰርታችሁ ከድኅነት አረንቋ በወጣችሁ ነበር የሚሉን የቀደመ ሥልጣኔያችንን ሊያስክዱን የሚዳዱ የነጭ እባቦች ከንፈር አደዋም የናንተ የኢትዮጵያዊያዊያን ድል አይደለም ቢሆንማ ዛሬ አንድነታችሁን ምን ፈታው መተባበራችሁን ማን ወሰደው ቢሉን ምን እንመልስ ይሆን?
በዚህ የመበላላት መንፈስ ውስጥ ሆነን የአፍሪካዊያን የነፃነት ቀንዲል የተለኮሰው ከዚህ ሀገር በነዚህ ተራሮች ሥር ነው ቢባል ማን ያምናል?

#አንዱ ወጣት እግር የሆነ ተራራ ይህማ አይሆንም እኔ አንደበት አውጥቼ እንደ ቢታንያ ድንጋይ አድዋ የኢትዮጵያዊያን ድል ነው ስል ጮክ ብዬ እመሰክራለዋ ሲል ሌላላው ቀበል አርጎ አዎ እኔም ዝም አልልም አድዋ ከኢትዮጵያ ምድር የተገኘ የጥቁር ሕዝበ ሁሉ ድል ነው ሲል አሳቡን ተጋራው
አንጋፈው ተራራ ግን ከሰማይ ደመናትን ሰብስቦ እንደ ጋቢ ተከናንቦ ጆሮ ዳባ ልበስ በሚል በሽሙጥ ተከናነበ ቀጠል አርጎም አንድነቱና ህብረቱ እንዲመጣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ካልጣረ እመሆኝ ወደፊት እኔ እንዳልኳችሁ ሳይሆን አይቀርም በርግጥ ሁሉም ነገር ከትምህት ቤት መማር አይቻልም የዕድሜ ባለ ፀጋ ሲነግራችሁ ግን እህ ብላችሁ ብሰሙ መልካም ነው ዕድሜ እዚህች ዮኒቨርስ ላይ ያልተገነባና የማይገነባ ትልቅ ዮኒቨርስቲ ነው ።

እናንተ ይህ ትላላችሁ አክሱም፣ ጀጎል፣ አባይ ፣ጣና ሁሉ ሳይቀር ከሀገር ሊወጡ ሲሉ አገኘዋቸውና ስለምን ይህችን ምድር ለቃችሁ ትወጣላችሁ ስል ሞገትኳቸው ሲሉ የነበሩ ኢትዮጵያ አብጠርጥረው ያውቋታል የሚባሉ ለምድ የከበዱ ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ዛሬ መሀመድ ግራኝ ወራሪአይደለም ሲሉ እየተደመጡ ነው ተደምጠዋል ምን ያርጉ ሥልጣን ወደ ሐሰት ዘወረቻቸው ። ታድያ ግራኝ ወራሪ ካልሆነ አርበኛ ነውንን? አምባ ሳደር ነውን? ወይ ብሔራዊ ጀግናችን ነው? በዚህ ዓይነትኮ ወደፊት ዐውልት ይቁምለት መንገድ ይሰየምለት መባሉ አይቀሬ ነው ። በዕድሜ የምታንሱኝ ልጆቼና ወንድሞቼ ይህ አበክራችሁ ስሙኝ በልባችሁም ጽላት ጽፋችሁ አኑሩት እውነት ሁል ጊዜም እውነት ነች ለማቻቻልና ሚዛን ለመጠበቅ አልያም ዲሞክራት ለመሆን ብለህ ልትሸፉፍናት መልኳን አጥፍተህ ልታጠይማት አትችልም ። መሀመድ ግራኝ ሀገር ያፈረሰ ሃይማኖት ያጠፈ ወራሪ ነው። ግራኝ ወራሪ አይደለም ካልን 11 ሚሊየን አይሁዳዊያንን በዘራቸው ምክንያት የጨፈጨፋቸው ኢትለር ቅዱስ ነው ሀገሩም ከደጋጎቹ ሀገር ከመንግሥተ ሠማይ ነው ማለት ነው
#የገነት ወግ

ከምጽሐት በኃላ ገነት ውስጥ ነው። ቸርነቱ የበዛ መዐቱ የራቀ እግዚአብሔር አምላክ ከሦስት ወጣቶች ሦስት ነገሮች አግኝቶባቸው ገነት አስገባቸው። መቼም እግዚአብሔር አምላክ መንግሥተ ሰማያትን የምታክል ቦታ በጥርኝ ውኃ የሚሸጥ ሞኝ ነጋዴን ይመስላል። #ማቴ10÷41

#ከወጣቶቹ የተገኘባቸው መልካም ነገርም እነኸህ ነበሩ። በአንዱ እምነት በአንዱ ማስተዋል በአንዱ የዋሕነት ነው። ከዚህ የተረፈ የጠለቀ መንፈሳዊ ትጋት የላቸውም በሳምንት አንድ ቀን እሁድ ግጥሚያና ትሬሊንግ ከሌለባቸው ያስቀድሳሉ ከአጽዋማት ሦስቱን መርጠው እንነገሩ ይጦማሉ በቃ ለገነት ዜግነት ያሳጫቸው ይህው ጥቂቱ ጥረታቸው እእና ብዙሁ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው።

#ከገነት በአንዱ ዕለት ታድያ አንደኛው ወጣት እንዲ ይላል " እንተ ገነት ገነት እያልን ስንናፍቃት የነበረችሁ ይችሁ ናትን? እንዴ ጠዋት ቅዳሴ ማታ ውዳሴ እረፍቱ ቆይ መቼ ነው ?
ሌላኛው ወጣት ቀበል አድርጎ ታገስ እስቲ በዚህኮ እረፍቱ ምስጋና ምስጋናው እረፍት ሆኖ ነው የሚኖረው ቢሆንም ግን ጥቂት ማረፋችን አይቀርም ሲል ለማጽናናት ሞከረ
ሦስተኛው ወጣት ግን የሱ ጭንቀት ሌላ እንደሆነ ነገራቸው እንዲህ ሲል እረፍት ብቻውን ምን ያደርጋል? በእረፍት ጊዜያችን ሻምፒዮን ስሊግና ላሊጋን የመሳሰሉት የእግር ኳስ ውድድሮችን መከታተል ካልቻልን

የመጀመሪያው ወጣት ጣልቃ ገብቶ አንተ ደሞ እሱንም ለማየትኮ ቅድሚያ የዕረፍት ጊዜ ሊኖረን ይገባል ማታ ውዳሴ ቀን ቅዳሴ ይህው ከገባን ጀምሮ ስንት ሰንበታት አለፉ በሰንበት እንኳ አናርፍም እኮ አለ ምርር ብሎ

#ለምን ካልሆነ እዚሁ ገነት ውስጥ wi fi እንዲገባ ና ለእያንዳንዳችን እስማርት ስልኮች እንዲታደሉን አናደርግም ከዛ በቃ ላሊጋ በል ሻምፒዮን ስሊግ በል በቃ ሁሉ በእጃችን ሆነ ማለት ነው በተጨማሪም ማኅበራዊ ድኅረ ገጾችን ከፍተን ምድር ካሉ ዘመዶቻችን ጋር ያለ ገደብ እንገናኝ ከናፍቆታቸውም እንገላገላለን አይመስላችሁም? ሲል ሀሳብ አቀረበ

ሁለተኛው ወጣት ድንገት ሳይታሰብ ገብቶ አይመስለንም ሲል አንቧረቀበት ጭራሽ ገነት ውስጥ ዋይ ፋይ ? ጭራሽ ገነት ውስጥ እስማርት ስልክ ? ገነትን ገነት ያሰኙት እኮ የነዚህ ነገር አለመኖር ነው አለዚያማ ከምድር በምን ተሻለ ሆሆሆሆ

#ሦስተኛው ወጣት ፈጠን ብሎ ምን ችግር አለው በምድር ሳለን ትዝ አይላችሁም ካህኑ በስማርት ስልክ ተደግፎ ተንስዑ ሲል ዲያቆኑት ቢሆን እያንዳንዱን የመቅደስ እንቅስቃሴ እየቀረጸ እዛው ማኅበራዊ ድኅረ ገጾች ላይ ሲለቅ አላያችሁም? ስለዚህ ብዙ ችግር ያለው አይመስለኝም አለ

እናንተ ሰዎች ያ በምድር ነው ሆኖም ትክክል ነው ማለት አይደለም።ምክንያቱም የምድሪቱ ቤተ ክርስቲያን የሰማያዊቱ ለዚህች ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናትና። (camera man) ቀራጭነትና ድቁና ፈሪሳዊነትና ክህነት አብረው አይሄዱም። ግማሽ መላጣ ግማሽ ጎፈሬ ብርሃንና ጽልመት እንዴት አንድ ይሆናሉ? ብንችል ለምድር ሰዎች እንጸልይላቸው እንዴት የነርሱን ስዕተት እዚህ እንደግማለን።

#አንዱ ወጣት የሆነ መላ ብልጭ ያለለት በሚመስል ሆናቴ ፍክት ብሎ ቆይ ከዚህ ሁሉ ጭንቅ ለምን ከገነት አንወጣም ?
ሌላኛው ወጣት ከዛስ ? ሲዖል ጥገኝነት እንጠይቅ?
አንተ ባክህ አቀልድ
በቃ ማለቴ ወደ ቀደመ ኑሯችን ወደ ምድር መልሱን ለምን አንላቸውም ???
ይቻላል እንዴ ? ገነትኮ ካገኙ ማጣት ከገቡ መውጣት የለም ማነው የሚያሶጣን?
ቀላልኮነው ለምን ገነት ውስጥ ያልተፈቀደ ነገር ለምን አናደርግም ከዛ በቃ በራሳቸው ጊዜ ያስወጡናል
አረ ባካችሁ ጓደኞቼ ምን ሆናችዋል? አዳምና ሔዋን በገነት ያልተፈቀደውን አድርገው ከገነት ሲባረሩ የምትገለባበጥ የኪሩቤል ሰይፍም ተመዞባቸው ነበር በኛ ደግሞ ይወድቅብን ይሆናል ማን ያውቃል ።
ማለት ገነት ሰይፍ አለ ? ታድያ ሰይፍ ካለ wifi ቢኖር ምን ችግር አለ? ቢያን አመስግነን ቀድሰን አወድሰን ስንጨርስ ትንሽ እንደበርበት ነበር እኮ ።

#ይህን ሲነጋገሩ ከቀደሙት ደጋግ አባቶች አንዱ በለወሳስ የምስጋና ውዳሴ እያቀረበ ወደ ወደ መንበረ መንግሥት ሲጓዝ አያቸው ከንግግራቸውም ያሉበት ቦታ እንዳልተመቻቸውና መውጣት እንደሚሹ ተረዳ መንገዱንም ገታ አድርጎ ወደ ወጣቶቹ ተጠግቶ ሰላምታ ሰጣቸው።
ከግርማ ሞገሱና ከንግግሩ ለዛ ተደመሙ የተነጋገሩትን አንዲቱንም ቃል ባልሰማን ብለውም ተመኙ። ያ ሰው ግን ያለ ዕውቀት እንደተናገሩ ያውቃልና እያለዛዘበ ጠየቃቸው ልጆች ምን ሆናችኋል የምረዳችሁ ነገር አለ አላቸው እነርሱ ግን ለማስቀየስ ተጠቃቀሱና አይ የለም አሉት በጋራ። መልካም ብሎ ጥሏቸው ጉዞዎን ሊቀጥል ሲል ግን አንደኛው ወጣት ግን አንተ ማነህ? ሲል የገነት ጠባቂ ጥጦስን የጠየቀውን ጥያቄ አቀረበለት አብርሃም ነህን አለው ያም ሰው ዝም አለ እሽ ሙሴ ነህን አለው ያ ሰው አለመለሰለትም በቃ ቅዱስ ጳውሎስ ነህን መሆን አለብህ አለው በጥያቄው ሳይሰለች ነኝም አይደለውምም ሳይለው እርሱ ይቆየኝ

ወጣትነት አስቸጋሪ ነው እኔም ወጣት ሳለው ብዙ ጠባያት እየተፈራረቁ አስቸግረውኝ ነበር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት በእናቱ አማላጅነት ሁሉም አልፌያቸው እዚህ ደርሻለው ከፈለጋችሁ ከልምዴ በማካፈል ልረዳችሁ እችላለሁ አላቸው። ካልሆነ ግን በሉ በደህና ዋሉ ብሎ ፊቱን አዙሮ መንገዱን ቀጠለ በእውኑ ግን ጥሏቸው ሊሄድ ልቡ አልወደደም ነበር

#ቢያንስ ከልምዱና ከዕውቀቱ ሊያካፍለን ይችላል በገነት ብዙ ስለቆየ መግቢያ መውጫውንም ሊነግረን ይችላል ለምን ሀሳባችንን አንነግረውም ተባባሉ በለወሳስ ቀስ ብለው። ከዛም አንደኛው ፈጠን ብሎ አባት አባቴ አንዴ ቆይ ብሎ ከኋላ ከተል እያለ ተጣራ አንድ ጊዜ አባቴ ሁለት ደቂቃ ይኖሮታል እባካችሁ ለምስጋና ወደ መንበረ መንግሥት እየሄድኩ ነው ከፈለጋችሁ ግን አብራችሁኝ እየሄዳችሁ የፈለጋችሁትን ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ አላቸው። እሺ ይሁን አብረኖት እንሄዳለን ብቻ እርሶ መፍትኤ ብቻ ይስጡን መፍትኤስ ከእግዚአብሔር ነው ግን ምን ገጠማችሁ ?

አንደኛው እጆቹን እያፍተለተለ በእግሮቹም ወደፊት አብሯቸው እየተራመደ ይህውሎት አባ እኛ የገነት ኑሮ ሰልችቶናል ወደ ቀደመ ቦታችን ወደ መሬት መመለስ እስፈልጋለን አለ ሁለቱ ሀሳቡን በመደገፍ በአውንታ ጭንቅላታቸውን አነቃነቁ ያ ባለ ግርማ ሞገስ ሰው ግን ፈገግ አለና ለአህያ ማር አይጥማት አሉ ሲል ተረተባቸው ቀጥሎም እርሷስ ሳያቀምሷት ነው አይጥማትም እያሉ የሚያሟት እናተ ቀምሳችሁ ሳለ እንዴት ሳይጥማችሁ ቀረ ለመሆኑ ገነት ምን ጎደለ?

#አንዱ ቀበል አድርጎ ሻምፒዮ ሲሊግ የለ ፤ ላሊጋ የለ ፤ facebook የለ ፤ instageram የለ ፤ ጠዋት ቅዳሴ ማታ ውዳሴ ይሰለቻልኮ አባ

አይ ልጆቼ ይህ ነው ጭንቀታችሁ ይህን እናንተ ያያችሁትን እኮ ብዙዎች ሊያዮት ወደው ሊያዮት አልቻሉም እስራኤል የሰማይ መና ሰለችን ሥጋ አማረን ቢሉ መና ("ና"ይላላ) ሆነው ቀሩ። የተመኙት ሥጋ ተሰጣቸው ከአፋቸው ከተው እንደቀመሱትም ሁሉም እረግፈው ሞቱ ቦታዋም እስከዛሬ ድረስ የምኞት መቃብር ተብላ እየተጠራች ነው። ምነው ከሕይወት ይልቅ የምኞት መቃብርን ሻታችሁ ከመና ይልቅ መና መሆንን ወደደዳችሁ?