አትሮኖስ
282K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
489 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አላገባህም


#ምዕራፍ_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁ_ገመቹ

/////

በማግስቱ አቶ ቅጣው እንደተለመደው ጭለማና ድፍን በሆነው የእስር ክፍሉ በሰንሰለት እጅና እግራቸው እንደተጠፈረ  ኩርምት ብለው  በትካዜ ላይ እያሉ  የበራፍ መኳኳት ድምፅ ሰሙ የገመቱት ትንሽዬዋ መስኮት መሳይ ቀዳዳ ተከፍታ የእለቱ የምግብ ኮታቸው ይወረወርልኛል ብለው ነበር …ግን ትልቁ በራፍ ተከፈተ….ወዲያው ብርሀን ሾልኮ ወደክፍሉ ገባና አይናቸው ላይ አንፀባረቀባቸው፡፡አይናቸውን ጨፈኑ..ከዛ ገለጡ… አሁንም ጨፈኑ እንደዛ እያደረጉ ካለማመዱት በኋላ ገልጠው ምን እየተካሄደ እንደሆነ ሲያስተውሉ ከክፍሉ ይዘዋቸው ሊወጡ እንደሆነ ገባቸው..፡፡አንድ ጠባቂ ክላሹን እንዳቀባበለ ውጭ በራፍ ላይ ሲታያቸው አንደኛው ደግሞ እንደተለመደው ወደውስጥ ገባና ሰነሰለቱን ከመሬት ከተቀበረው ብረት ጋር የተያያዘውን ብረት ይፈታል ብለው ሲጠብቁ ከእግራቸው ጋር የተያያዘውን ሰንሰለት ፈታውና አላቀቀው…ከዛ ወደላይ ቀና ብሎ በእጃቸው ላይ የተሳረውን ሰንሰለት በተመሳሳይ ፈታና እዛው ወለሉ ላይ ሲወረውረው የፈጠረው የቅልጭልጭልታ ድምፅ በጆሮቸው ገብቶ አእመሮቸውን አተረማመሰው…‹‹ወደ መገደያዬ ሊወስዱኝ ነው እንዴ?››ሲሉ አሰቡ…..በመጀመሪያ በጣም ቅር አላቸው፡፡ከዛ ግን‹‹እንደውም ግልግል ነው…አሁንስ በህይወት እየኖርኩ ነው ይባላል …?

ከሞት ወደሞት መሄዱ ምኑ ያስፈራል?››ሲሉ አሰቡ፡፡ፊት ለፊታቸው ያለው ፖሊስ ከኪሱ ሌላ የሚያብረቀርቅ ካቴና  ከጃኬት ኪሱ አወጣና እጃቸው ላይ ካደረገላቸው በኃላ

‹‹አቶ ቅጣው..ቀጥል እንሂድ..››አላቸው…፡፡

‹‹ለምን..?ወዴየት?› የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ሳይጠይቅ በዝምታ ፊቱን ወደበራፉ አዞረና እርምጃውን ቀጠለ…ሰውነቱ  የዶሮ ላባ ያህል ቀለለው…ላለፉት ስድስት ወር እንዛ አስጠሊታ ድምፅ ያላቸው የዛጉ ሰንሰለቶች ከእግሩና ከእጁ ጋር ተላቀው ስለማያውቁ በተንቀሳቀሰ ቁጥር እንሱንም ይዞ ይንቀሳቀስ ስለነበረ እንደራሱ አካል ያያቸው ከጀመረ ሰነባብቶል…እና አሁን የሆነ የአካሉን ክፍል ቆርጠው እንዳስቀሩበት ነው የተሰማው..ከክፍሉ ይዘውት ወጡ ፡፡በኮሪደሩ ይዘውት ከተጓዙ በኋላ ለመጀመሪየ ጊዜ ከዛ ቀፋፊና መቀብር መሳይ ህንፃ ሙሉ በሙሉ ይዘውት ወጡና የውጭን ብርሀን እንዲያይ አደረጉት፡፡በመጀመሪያ ጭው አለበት…ከዛ እንደምንም አይኑን አጨንቁሮ አካባቢውን ለመቃኘት ሞከረ..ዛፎች ይታዩታል….አረንጓዴ ሳር የለበሰ ሜዳ ..ከዛፍ ዛፍ እየበረሩ የሚታዩ ወፎች…በግዙፍ አጥር  የተከበበ አነስታኛ ሜዳ…ሜዳውን ሞልተው  ኳስ የሚጫወቱና ስፖርት ሚሰሩ  እናም ደግሞ አፍ ለአፈ ገጥመው የሚያወሩ ቢጫ ቱታ የለበሱ መአት እስረኞች..ከሁሉም በላይ እምክ እምክ የማይልና የማያፍን ንፅህ የተፈጥሮ አየር በአፍንጫው ሲስብ …በቃ ከመቃብር የወጣ አይነት ስሜት ነው የተሰማው….እንባውን ከትሮ ማቆየት ስለተሳነው አለቀሰ…

‹‹እዛ ጨለማና የታመቀ ክፍል ውስጥ በህይወት ከመቆየት እዚህ በተፈጥሮ ፀጋ በተሸሞነሞነ ንፅህ አየር ውስጥ ሞቶ መቀበር ይሻላል››ሲል አሰበ፡፡

ከፊት እየመራው ያለው ፖሊስ‹‹ቀጥል አቶ ቅጣው››ሲል እንዲከተለው አዘዘው፡፡ ሌለኛው ፖሊስ ከኋላ ክላሹን እንደደቀነበት በሁለት ህንፃዎች መካከል ባለች ጠባብ መንገድ እየመራ ወሰደው.. በቆርቆሮ የተሰሩ ብዙ ክፍል ያሉበት ክፍል ጋር ሲደርስ ቆመ …ይሄን የቆርቆሮ ቤት ያውቀዋል….እስረኞች በእያንዳንዱ ክፍል አምስትና ስድስት እየሆኑ በሳምንት አንድ ቀን ሰውነታቸውን የሚታጠቡበት ክፍል ነው፡፡ከበርካታ ወራት በፊት እሱም እንደማንኛውም እስረኛ በሳምንት አንድ ቀን የመታጠብ ወርቃማ እድል ነበረው…አሁን ግን ሰውነቱ ውሀ ከነካው ስድስት ወር ከማለፉ የተነሳ የሰውነቱ ቀለም ሙሉ በሙሉ ተቀይሮል …አካላቱ ላይ የተለደፈው ቆሻሻ በውሀና ሳሙና  ሳይሆን በቢላዋ እየተቀረፈ እየተቀረፈ ካልተነሳ የሚፀዳ አይመስልም፡

አንድ ሌላ ፖሊስ በፔስታል የሆነ ነገር ይዞ በራፍ ላይ እየጠበቃቸው ነበር፡፡መድረሳቸውን ሲያይ አንደኛውን ክፍል ከፈተና ..ይሄው መቀየሬያ ልብሱ እዚህ ውስጥ አለ..ልጅህ ነው ያመጣልህ….ሌላውን ክፍል ድርስ እናመጣልሀለን..ሳሙናም ይሄው አለና›› ለፖሊሱ አስረክቦ ሄደ፡፡

‹‹አቶ ቅጣው ያልሆነ ነገር ለመስራት ፈፅሞ  እንዳትሞክር….ይሄው ሳሙና …  ሰውነትህን ታጠብና ልብስ ቀይር….››አለው

‹‹ለምን ግን?››ሲል መጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ጠየቀ፡፡

ፖሊሱ እጁ ላይ ያጠለቀለትን ካቴና እየፈታ‹‹ለምን ማለት ..ምኑ?››ሲል ጥያቄው እንዳልገባው በሚገልፅ ሁኔታ መልሶ ጠየቀው፡፡

‹‹መታጠቤና ..ልብስ መቀየሬ?››

‹‹ምነው አሁን ያለህበት ሁኔታ ተመችቶሀል እንዴ?ማጥ ውስጥ ሲንከባለል የከረመ ከርከሮ እኮ ነው የምትመስለው …ለማንኛውም ለምን እንድታጠብ እንደተፈቀደልህ አናውቅም…እኛ የታዘዝነውን እያደረግን ነው…ስራችንን እንድንሰራ ተባበረን..እንካ ልብሱንና ሳሙናውን… ይዘህ ግባ››አለው።

እንዳው በግዴለሽነት ተቀበለውና ወደውስጥ በዝግታ ገብቶ በራፉን ከውስጥ ሊዘጋው ሲል…ፖሊሱ ፈጠን አለና‹‹አይ አትዝጋው…..ክፍት ይሁን …ከእይታችን ውጭ መሆን የለብህም››የሚል ትእዛዝ ሰጠው፡፡

በግዴለሽነት በራፉን መልሶ በልቅጦ ወደውስጥ ገባ…ልብስ የያዘውን ፔስታል በአንዱ የግድግዳው ኮርነር ጋር አስቀምጦ ሳሙናውን ብቻ ይዞ ቀጥታ ሻወር ወደላበት ቦታ ሄደ… ውሀውን እስከመጨረሻ  ከፈተውና ውስጡ ቆመ…ውጭ ሆነው በትኩረት እየተከታተሉት ያሉት ሁለት ፖሊሶች በገረሜታ ምን እየሰራነው? ብለው እየተገረሙበት ነበር፡፡ለሀያ ደቂቃ አልተነቃነቀም…ውሀው እየተንፎለፎለ በላዩ ላይ ሲወርድ ከለበሰው ልብስ ላይም ሆነ ከገላው ላይ እየተቀረፈ የሚወርደው ቆሻሻ  ለሚያየው ሰው ይዘገንናል..በኋላ ግራ ሲገባቸው አንደኛው ፖሊስ ወደውስጥ ገባና ወደእሱ ተጠግቶ

‹አቶ ቅጣው ..ቅጣው …››ውሀውን  ዘጋው ሲል ጠየቀው…ከገባበት ጥልቅ ሰመመን የነቃ የሚመስለው ቅጣው‹‹አቤት በቃ ልውጣ እንዴ?››ሲል ጠየቀ፡፡

‹‹አይ እሱ እስከፈለግክ መታጠብ ትችላለህ..ግን በስርአት አድርገው፡››

‹‹በስርአት ማለት?››ተደነጋገረ፡፡

ሳሙናው እኮ በእጅህ እንደያዝከው ሟሙቶ ሊያልቅ ነው..የለበስከውን ቀፋፊ እና ቡትቶ ልብስ አውጥተህ ጣልና ሰውነትህን ሳሙና እየመታህ በትክክል ታጠብ››

‹‹እ..ገባኝ..እሺ›› ብሎ ልብሶቹን አወላለቀና ከእሱ አርቆ በመወርወር ርቃኑን ቆመና ሻወሩን በድጋሚ ከፈተ…ከዛ ከፀጉሩ በመጀመር ሙሉ ሰውነቱን ሳሙና በመለቅለቅ መታጠብ ጀመረ…ምን አልባትም አምስት ስድስት ጊዜ ደጋግሞ ሳሙና በመለቅለቅ ለወራት በሰውነቱ ተጠቅጥቆ የተከማቸውን ቆሻሻ በተቻለው መልኩ ለማስለቀቅ ጣረ… ከዛ…ቧንቧውን ዘጋና ቀጥታ ወደፔስታሉ በመሄድ ውስጡ ያለውን ልብስ ተራ በተራ እያወጣ በመመልከት  ለበሰ…ሁሉም ልብሶች ምርጥና አዲስ ሲሆኑ ለእሱ ግን ሰፍተውታል ….‹‹ምን አልባትም በጣም ከመክሳቴ የተነሳ ለእኔ በልኬ የሚሆን ልብስ ገበያ ላይ ስለሌለ ይሆናል ይሄን ያመጡልኝ››ሲል አሰበና በመጨረሻ ካልሲውንና ጫማውን አድርጎ ወደ ፖሊሶቹ ሄደ….በራፉ ላይ ተቀበሉትና በእጁ ላይ ካቴናውን መልሰው አጠለቁለትና በሌላ አቅጣጫ ይዘውት ሄዱ…አሁንም የወሰዱትን ቦታ ገና እንዳየው ነው ያወቀው›..የእስረኞች ፀጉር ማስተካከያ ቦታ ነው፡፡

‹‹ሽፈራው በል ቆንጆ አድርገህ አስተካክለው››ፖሊሱ ፀጉር አስተካካዩን አዘዘው፡፡

‹‹እንዴ ቅጣው..?እንዴት ነህ..?ሰላም ነህ?››ፀጉር አስተካካዩ በገረሜታ ተቀበለው፡፡
👍6610🥰2
‹‹አለው››አጭር መልስ ሰጠው፡፡

ከዚህ ፀጉር አስተካካይ እስረኛ ጋር በደንብ ይተዋወቃል..ግን ደግሞ ናፍቀሀኛል ብሎ ዘሎ ሊጠመጠምበት አይችልም… እንደዛ አይነት ሞራል የለውም፡፡ለሰዎችም ሆነ ለጠቅላላው አለም ያለው ጉጉትና ትርጉም ከተዛባ ሰነባብቷል፡፡

ከነካቴናው የጸጉር  ማስተካከያው  ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ተቀመጠ….መሳሪያ የያዘው ፖሊስ በራፍ ላይ ሲቀር አንደኛው ተከትሎት ገባና ሌላ ወንበር ላይ ጠቀመጠ፡፡

ሽፈራው  ልብስ እያለበሰው‹‹ወይ ቅጣው….ለአመታት ባዕት የዘጋ ባህታዊ መስለህ የለም እንዴ?››የሚል አስተያየት ሰጠ፡፡

‹‹ሽፈራው  ወሬህን አቁምና ስራህን ስራ››ፖሊሱ አስጠነቀቀው፡፡

‹‹እሺ ..ይሄ ጸጉር ማሽኔን ስለሚሰብረው መጀመሪያ በመቀስ ልቀንሰው››

‹‹እንደፈለክ አድርግ..ብቻ ሰው አስመስለው››

‹‹ስትገድሉኝ ቀረፃ አለው እንዴ?››ቅጣው ወደፖሊሱ ዞሮ ጠየቀ፡፡

‹‹ማለት?››

‹‹ለመግደል ሰው ማስመር ጥቅሙ ምንድነው ብዬ ነዋ…ይቅርታ አንተን ላበሳጭህ ፈልጌ ሳይሆን  ስላልገባኝ ነው?›

‹‹ስውዬ እኛ ቀጥሎ በአንተ ላይ ስለሚሆነው ነገር ምንም የምናውቀው ነገር የለም…አድርጉ የተባልነውን እያደረግን ነው…..››

‹‹እሺ..ችግር የለውም የሚሆነውን በትእግስት በመጠበቅ  ማየት እችላለው››

ፀጉሩንና ፂሙን ለማስተካከል 40 ደቂቃ ወሰደበት…..እራሱን በመስታወት ሲያይ ከአመታት በፊት የሚያውቀውንና ትንሽ ትንሽ የሚያስታውሰውን  ሰው ምስል እያየ ያለ ነው መሰለው፡፡

‹‹አሁን መሄድ እንችላለን››
አሉና እየመሩት  ወደ አስጠሊታ ህንጻ ይዘውት ሄዱ፤ ግን ደግሞ  ወደምድር ቤት ሳይሆን በፊት ለፊት የመጀመሪያ ፎቅ ላይ ወደ ሚገኘው የኩማንደሩ ቢሮ ነው የተወሰደው፡፡አሁን እርግጠኛ ሆነ..‹‹በቃ ዛሬ ወይም ነገ የሞት ቅጣቱ ተፈጻሚ እንዲሆን መወሰኑን ሊነግሩኝና ለሞቴ ሊያዘጋጁኝ  ነው፡፡››ሲል አሰበ፡፡ፖሊሶቹ ኩማንደሩ ቢሮ አስገቡትና ለኮማንደሩ አስረክበውት ውጭ  በረንዳ ላይ  ሆነው በቀጣይ የሚሰጣቸውን ትዕዛዝ መጠባበቅ ጀመሩ፡፡

‹‹ቅጣው …ተቀመጥ….››
ትናንትና ልጁን ለማግኘት ታሽጎበት ከነበረ ጭለማ ምድር ቤት ሾልኮ የመጣበትን የኋላ በራፍ  በትዝብት እየተመለከተ በዝግታ እየተራመደ ኩማደሩ ፊት ለፊት ተቀመጠ፡፡ከዛም ኮማንደሩ ምንም ነገር ከመናገራቸው በፊት‹‹መቼ ነው?››ሲል ጥያቄውን ጠየቀ፡፡

ኮሚሽነሩ ግራ ተጋባ

‹‹ምኑ?››

‹‹የምገደልበት ቀን…ዘሬ ነው ነገ….?ከዛ በፊት ልጇቼን ማናገር እፈልጋለው››

ኩማንደሩ  ፈገግ አሉና ‹‹መቼ ይሁንልህ ….?››ሲሉ በፈገግታ ጠየቁት፡፡

‹‹መቼም ቢሆን ችግር የለብኝም ….እንደውም ቶሎ መሆኑን እፈልገዋለው..ግን  እንዳልኩት ለመጨረሻ ጊዜ ልጆቼን ማናገር ብችል ደስ ይለኛል…የመጨረሻ ምኞቴ ይህ ብቻ ነው፡፡››

‹‹ማነው እንደዛ አይነት ነገር በአእምሮህ ያስቀመጠው?››

‹‹ማንም…ያለወትሮችሁ ስታሰማማሩኝ..ከዛ ውጭ ምን ሊሆን ይችላል ብዬ ላስብ?፡፡››

‹‹አሳምረን ልንገድልህ መስሎህ ነው?››ተንከትክተው ሳቁ‹‹ተሳስተሀል….አሁን የጠራሁህ..ላስጠነቅቅህ ነው፡፡ሰንሰለትህን ከላይህ ላይ አውልቀናል .ለጊዜው ከሌሎች እስረኞች ጋር ልንቀላቅልህ ባንችልም የተሻለ ክፍልም ቀይረንልሀል….ግን እንደባለፈው አይነት የማምለጥ  ወይም የመረበሽና የእስርቤቱን ህግ የመፃረር ጥቂት ሙከራ ብታደርግ መልሰን ወደዛ ጨለማና ቀፋፊ ክፍል እንጥልሀለን..እናም እስከወዲያኛው እንረሳሀለን››ሲሉ አስፈራሩት፡፡

‹‹ገብቶኛል››
‹‹በቃ ይሄው ነው…..በጣም ጥሩ ልጅ ነው ያለህ››

‹‹ማ ..ሚካኤል ነው?››

‹‹አዎ ሚካኤል…ምነው ሌላም ልጅ አለህ እንዴ?››

‹‹አዎ የሚካኤል መንታ ወንድም አለ… ዘሚካኤል ይባላል ….ዘፋኝና አርቲስት ነው…ግን እሱ እኔን  ማግኘትም ሆነ ..ስለእኔ መስማት አይፈልግም››ሲል በቁጭትና በናፍቆት ተናገረ፡፡

ኩማንደሩ በአድናቆት አፉቸውን ከፈቱ‹እንዴ…!!ዘሚኬኤል ይሄ የምናውቀው…. ስልካቸውን  አወጡና ዩቲዩብ በመክፈት ፈለግ ፈለግ አድርገው የዘሚካኤልን አንዱን ዘፈን በመክፈት  ከተቀመጡበት ተነስተው ወደእሱ ሄዱና 

‹‹ይሄ እንዳይሆን?››

‹‹አዎ እራሱ ነው….የእኔ ልጅ ነው››በኩራትና በእፍረት መሀከል በሚዋልል ስሜት አረጋገጡ፡፡

‹‹ይገርማል ..ሴት ልጄ እንዴት ትወደዋለች መሰለህ….?.ብዙ ህዝብ የሚወደው በጣም ጎበዝ ልጅ እኮ ነው ያለህ››

‹‹አዎ ጥሩ ልጅ ነው..እንዳልኩህ ግን ከሚካኤል የተለየ ፀባይ ነው ያለው ..እልከኛ ነው….እና እኔን ለማየት ሆነ ስለእኔ ለመስማት አይፈልግም….ለማንኛውም ሚካኤልን መልሼ የማግኘት እድል ያለኝ ይመስልሀል?፡፡››

‹‹ነገርኩህ እኮ …አንተ ብቻ የእስር ቤቱን ህግና  ደንብ አክብረህ ቆይ….እኔ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የተቻለኝን እጥራለው…እንዳልኩህ ይሄን ሁሉ እንዲሆን ከፍታኛውን ጥረት የጣረው ልጅህ ነው..በል አሁን ፖሊሶቹ ወደ አዲሱ ክፍልህ ይወስዱሀል››

ለአዲሱ ክፍል ሳይሆን ልጁን ዳግመኛ የማግኘት እድል እንዳለው በመስማት በጣም ተደስቶ‹‹አመሰግናለው….ኩማንደር››በማለት ከተቀመጠበት ተነሳና  ቆመ…ኮሚሽነሩ መጥሪያውን ሲጫኑ ፖሊሱ የቢሮውን በር ከፍቶ ወደውስጥ ገባ…ሳጂን እስረኛውን ወደተዘጋጀለት አዲሱ ክፍል ወሰዱት››

‹‹እሺ ኮሚሽር››በማለት ፖሊሱ እስረኛውን ይዞት ወጣ፡
         
ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe ቤተሰቦች please 🙏

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏47👍354
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

አዲስ አለም በራሷ መኪና ግን ሹፌር እየነዳላት  ከአዳማ ወደአዲስ አበባ እየተጓዘች ነው፡፡

የተቀመጠችው ከኋላ ወንበር ላይ ሲሆን ከግራዋ የራሷ ልጅ ቅዱስ ሲኖር ከግራዋ ደግሞ የፀአዳ ልጅ ምሰር ትገኛለች፡፡

አዲስአለም ወደአዲስ አበባ የምትሄደው እናቷን ለመጠየቅ ነው፡፡ይሄ ቤተሰቦቾ አዳማ ለቀው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ  በወር ወይም በሁለት ወር አንዴ የምታርገው ነገር ስለሆነ ማንም ለምን እንዴት ብሎ የሚጠይቃት የለም፡፡ምስርን በምን ሰበብ አስፈቅዳ ከእሷ ጋር ይዛት እንደምትመጣ ግን ግራ ገብቷት ነበር፡፡ማታ ነበር ፀአዳ ጋር የደወለች፡፡

‹‹እሺ ጓደኛዬ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ ምነው ቀን ተገናኝተን ነበር እኮ..በዚህ መሀከል ምን ትሆናለች ብለሽ አሰብሽ?››.

‹‹አንቺ ደግሞ ከአፍሽ ቀና ነገር ቢወጣ ምን አለበት?››

‹‹በይ አሁን ምን ፈልገሽ ነው ወደገደለው ግቢ….››

‹‹በእናትሽ ነገ እነማዬ ጋር አብረን እንሂድ››

‹‹ነገ ››

‹‹አዎ ነገ››

‹‹ያምሻል እንዴ…?ስንት ስራ እንዳለብኝ  ስነግርሽ ውዬ እንዴት የማልችለውን ነገር ትጠይቂኛለሽ?››

‹‹ውይ ለካ ስራ አለብሽ..ብቻዬን መሄድ እኮ ደብሮኝ ነው››

ብቻሽን መሄድ ከደበረሽ  ታዛዥ እና ጣፋጭ የሆነ ምርጥ ባል አለሽ እሱን አስከትለሽ ሂጂ››

‹‹አንቺ እየሰማሽ እኮ ነው››

‹‹ላውድ ላይ አድርሽ ነው እንዴት የምታወሪኝ… አንቺ እኮ ቅሌታም ነሽ….ለነገሩ ሚኪን በተመለከተ መጥፎ ነገር እንደማልናገር እርግጠኛ ስለሆንኩ እንደፈልገሽ››

‹‹መጥፎ ነገር እንደማትናገሪ እኔም ምስክር ነኝ … ውሸት ግን ትናገሪያለሽ..ምን አልባት እንዳልሺው ጣፋጭ ሊሆን ይችላል ታዛዣ ግን አይደለም..ልክ እንደአንቺው ስራ አለኝ አልችልም የሚል መልስ ነው የሰጠኝ››

‹‹በቃ ከልጅሽ ጋር ሒጂ››

‹‹ወይ እንደውም ተውት ከልጆቼ ጋ ሄዳለው…ምስርን ቆንጆ አድርገሽ አሳምሪያትና ወደስራ ስትሄጂ ይዘሻት ውጭ.. በዛው መጥቼ ወስዳታለው››

‹‹ምን እያልሽ ነው?››ፀአዳ እንደመበሳጨት አለች፡፡

‹‹የራስሽው ምክር እኮ ነው፡፡ልጆቹን ይዤ ሄድና ዘና እንላለን…እናንተም ካለልጆቻችሁ ይድላችሁ…እሁድ ማታ ተመልሰን እንመጣለን፡፡››

‹‹አንቺ እኮ የሆነ መዠገር ነገር ነሽ…እኔ ለራሴ ስንት ስራ አለብኝ..?ገና አሁን እሷን ሰውነቷን ሳጥብ..ፀጉሯን ሰሰራ….››

አላስጨረሰቻትም፡፡‹‹በቃ…ጥዋት ሁለት ተኩል አካባቢ ስራ ቦታሽ እመጣና ወስዳታለው..ደህና እደሪ..እወድሻለው፡፡››ብላት ስልኳን ዘጋችው፡፡እንዳለችውም ጥዋት ስትሄድ ፀአዳ ከነንጭንጯ ልጇን ምስርን አስባና አሳምራ ነበር የጠበቀቻት፡፡

‹‹ውይ ጎደኛዬ ንዴት እንደሸወድኩሽ ስታውቂ እንዴት ትናደጂ ይሆን?›› ብላ አሰበችና ብቻዋን ፈገግ አለች፡፡

ሹፌሩ ጎሮ አካባቢ የሚገኘው የቤተሰቦቾ ቤት ካደረሳት በኃላ  ሚካኤል እንዲገዛለት ያዘዘው ዕቃዎች ስለሉ ወደመርካቶ ለመሄድ ተዘጋጀ….

‹‹በቃ ነገ አስር ሰዓት አካባቢ እዚህ ድረስ ››አለችው አዲስ፡፡

‹‹እዚህ የምትንቀሳቀሺበት አይቸግርሽም?››

‹‹ችግር የለውም..የትም የመውጣት እቅድ የለኝም…ምን አልባት የምወጣም ከሆነ ራይድ እጠቀማለው››አለችና ሸኘችው፡፡

ከዛ ልጆቹን ወደቤት አስገብታ እናቷን በቅጡ እንኳን ሰላም ሳትል ነው ወደጓሮ ሄዳ ስልክ የደወለችው፡፡ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ‹‹እንዴት ነህ ዘሚካኤል?››

‹‹ሰላም ነኝ..ግን አልተሳካልኝም ብለሽ እንዳታበሳጪኝ››

‹‹አረ ተሳክቶልኛል…መጥተናል እማዬ ቤት ነው ያለነው፡፡››

‹‹በጣም ጎበዝ…..በቃ ጎሮ አካባቢ ነው ያልሺኝ፡፡››

‹‹አዎ… ትክክለኛ አድራሻውን በሚሴጅ ልክልሀለው››

‹‹በቃ..በአንድ ሰዓት ውስጥ እመጣለው››

‹‹ጥሩ ነው..እኛም ገና አሁን መድረሳችን ስለሆነ እስከዛ ከእማዬ ጋ እንጫወታለን…በል ቻው››

‹‹አዲስ በጣም አመሰግናለው…ቻው››

ስልኩ ተዘጋ ፣፣እሷ ግን ፈዛ ቀረች…ከዘሚካኤል ጋር በዚህ መጠን መቀራረብ መቻሏ የተአምር ያህል ነው….ለዘመናት ስታልመውና ስትመኘው የነበረ ነገር ነው፡፡ግን በዚህ መንገድ ይሆናል ብላ ፈፅሞ ሀሳብ አልነበራትም..እሱ የእሷን የልብ ጓደኛ አፍቅሮ እሷ ደግሞ እሱን ከሚያፈቅራት ልጅ ጋር ለማቀራረብ ስትጥር….በራሷ ድርጊት ፈገግ አለች፡፡

‹‹ምን አለበት…. ለሚያፈቅሩት ሰው የሚያፈቅረውን ነገር እዲያገኝ መርዳት ትንሽ ህመም ቢኖረውም ግን ደግሞ ደስ የሚል ስሜት አለው፡፡››አለችና ለስሜቷ ድጋፍ ለመስጠት ሞከረች…የባሏ ሚካኤል ምስል በድንገት መጥቶ አየሩን ሞላው‹‹ፍቅሬ ምን እያሰብሽ ነው…?የገዛ ወንድሜን!!!››ብሎ በሀዘን በተሰበረ ስሜት ሲወቅሳት አየች፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ይሄ እኮ ያለፈ ታሪክ ነው….ታውቃለህ እሱን ለማግኘት ስትጥር ነበር ከአንተ ጋር የተቀራረብኩት…ከዛ እሱም ሀገር ጥሎ ጠፋ አንተም ለእኔ ምርጥና ተወዳጅ ሆንክልኝ..እናም  በሙሉ ልቤም ወድጄ አገባሁህ››

‹‹ግን ስታገቢኝ…ወደሽ ነው..ወይስ አፍቅረሺኝ?››

‹‹አይ አንተ ደግሞ ምን ቃላት ትመነዝራለህ….ለማንኛውም..የእሱ ያለፈ የአፍላ የወጣትነት ስሜት ነው..አሁን እየቀረብኩትና እየረዳሁት ያለሁት ያንተ ወንድም ስለሆነ ብቻ ነው››

‹‹እንዴ…!!ምንድነው  ጓሮ ተደብቀሽ ብቻሽን ምታወሪው?››የእናትዬው የመገረም ንግግር ነበር ከገባችበት ቅዠት መሰል ሀሳብ አባኖ ያወጣት፡፡

‹‹አይ እማዬ ..ምንም አይደል ..የሆነ ነገር እያሰብኩ ነበር››

‹‹የሆነ ነገር..ምነው ከሚካኤል ጋር ተጣላችሁ እንዴ?››

‹‹ወይ እማዬ ምንድነው የምታወሪው..?ከሚካኤል ጋር ለምንድነው የምጣለው?››

‹‹ባልና ሚስት ለምንድነው የሚጣሉት?››

‹‹እኔ እንጃ..እኔና ሚኪ ስንጣለ አይተሸን ታውቂያለሽ?››

‹‹እሱ መልካምና ታጋሽ ባል ስለሆነ ነዋ…እንጂማ እንደአንቺ መመነጫጨቅ ቢሆን… ››እናትዬው ነግግሯን ሳታገባድድ አንጠልጥላ ተወችው፡፡

‹‹እማዬ ደግሞ… የእኔ እናት ነሽ  የእሱ?››

‹‹የሁለታችሁም…ባሌ ነው ብለሽ አምጥተሸ ካስተዋወቅሺኝ ቀን ጀምሮ እኮ ልክ እንደአንቺ እሱም ልጄ ሆኗል…በዛ ላይ አሁን ወርቅ የሆነ የልጅ ልጅ ሰጥቶኛል…በይ አሁን ነይ ግቢ ቁርስ ቀርቧል…››አሏትና ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ፡፡ 

ዘሚካኤል እንዳለውም ከአንድ ሰዓት በኃላ በራፍ ላይ ደርሶ ደወለላቸው፡፡ተዘጋጅታ ስትጠብቀው ስለነበረ ወዲያውኑ ነው ልጆቹን ይዛ የወጣችው፡፡ከግዙፉ ሀመር መኪናው ወርዶ በራፍን ከፍቶ ቆሞ እየጠበቃቸው ነበር…የስድስት አመቷ ምስር እንዳየችው ደነገጠች…..መጀመሪያ የት እንደምታውቀው ነበር ግራ የገባት..ከዛ የምትወደው ዘፋኝና ተዋናይ መሆኑን ስታውቅ ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት እየተንደረደረች ወደ እሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ከቆመበት እጆቹን ዘርግቶ ወደእሷ ተንቀሳቀሰ…እቅፉ ውስጥ ወደቀች.. ጭምቅ አድርጎ አቀፋትና በአየር ላይ አንጠለጠላት..የምስርን ድርጊት ያየው ቅዱስ እጆቹን ከእናቱ እጅ አስለቅቆ ኩስ ኩስ እያለ ምስር እንዳደረገችው ወደዘሚካኤል ሮጠ….አዲስአለም በልጆቹ ያልተጠበቀ ድርጊት  በድንጋጤ አፏን ከፈተች ….ሚካኤል ቅዱስ ስሩ ሲደርስ ምስርን ወደአንዱ እጁ አዘዋወራትና ጎንበስ ብሎ ቅዱስን አቅፎ ወደላይ አነሳውና ጉንጮቹን እያገላበጠ ሳመው…..በዚህ ጊዜ አዲስ አለም ከመደነቅ ሳትወጣ ስራቸው ደርሳ ነበር፡፡

‹‹ቆይ ከእነዚህ ልጆች ጋር ከዚህ በፊት ትተዋወቁ ነበር እንዴ?››

ጉንጮቾን እያገላበጠ ሰማት..ትንፋሹ ልክ ሰው ፊት ላይ እደሚበትን አደንዛዥ ዕፅ ኃይል አለው…
👍6612
‹‹ቅዱስን የሰርጉ ቀን ፀዲ አስተዋውቀናለች፣ከምስር ጋ ግን አሁን ነው የተዋወቅነው››

‹‹ምስር ማነው ታውቂዋለሽ?››

‹‹አዎ ሄኖክም ነው….ብርሀንም ነው…ዘሚካኤልም ነው››

በሳቅ ተንከተከቱ…የጠራቸው ተዋናይ ሆኖ የተጫወታቸውን ፊልሞች ላይ ያሉትን የገፀባህሪያቱን ስም ነው››

‹‹ተምታቶባታል ማለት ነው››አለች አዲስ፡፡

‹‹አይ ትክክል ነች..የተጫወትኳቸውን ፊልሞች ላይ የነበሩኝን ስሞች ነው የዘረዘረችው››

‹‹ነው እንዴ..?››አዲስአለም የእሷን ያህል ባለማወቆ እፍረት ተሰማት…፡፡

አዲስአለም ግራ ቀኙን ካየች በኋላ‹‹በሉ ወደመኪና ውስጥ እንግባ ..ሰው ሁሉ እያፈጠጠብን ነው››አለች፡፡

‹‹ያው ከእኔጋ እስከሆንሽ ደረስ እንዲህ አይነት ነገሮች የተለመዱ ናቸው …››አለና ልጆቹን እንዳቀፈ የኋላውን ወንበር ላይ አስቀመጣቸው፡፡..አዲስ አለምም ልጇቹን ተከትላ ገባች፡በራፉን ዘጋና ወደሹፌረ ወንበር ዞረና ገብቶ መንዳት ጀመረ፡፡

‹‹ቅዱስን እኮ ያየኸው አልመሰለኝም ነበር››

‹‹የሰርጉ ቀን ፀዲ ይዛው መጥታ አስተዋውቃኝ ነበር….ግን ሳየው ደንግጬ ሰልነበረ ተቀብያት እንኳን አላቀፍኩትም ነበር…እና ከተለየሁት በኋላ በጣም ሲፀፅተኝ ነበር››

‹‹ይሄው አሁን በግላጭ አግኝተኀዋል ምንም የሚፀፅት ነገር የለም..››

‹‹ህፃን ስለሆነ ነው ይቅር ብሎ ያናገረኝ…ትልቅ ሰው ቢሆን ይሄኔ ቂም ይዞብኝ እየገላመጠኝ ነበር››
///
ቀጥታ ወደቤት ነበር የወሰዳቸው፡፡ቤቱ ።ተአምስተኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ ባለአራት መኝታ ቤት ግዙፍ አፓርታማ ነበር፡፡ክፍት ሆኖ ነበር የጠበቃቸው…፡፡

‹‹እንዴ ቤት ሰው አለ እንዴ?››ሥትል ጠየቀችው፡፡

‹‹እንዴ ብቸኛ ነው አሉሽ እንዴ?››

‹‹እሱማ አርቲስት እንዴት ብቸኛ ይሆናል…››ስትል መለሰችለት፡፡ወደውስጥ ዘልቀው ሲገቡ ነጭ የሼፍ ልብስ የለበሰች አንድ ልጅ እግር ወጣት ከኪችን ወጣችና ተቀበለቻቸው….ገብተው ሳሎን ተቀመጡ….አዲስ አለም ቤቱን ከጠበቀችው በላይ ውብ እና ዘመናዊ ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡ሶፋውን ጨምሮ እያንዳንዱ ቤቱ ውስጥ ያሉት  እቃዎች በጠቅላላ ጥራት ያላቸውና   እጅግ  ዘመናዊ ብሎም  ውድ ናቸው….

ዘሚካኤል ከፊት ለፊቷ ሲቀመጥ ስሯ የነበረችው ምስር ከተቀመጠችበት ቀስ ብላ ተነሳችና ከጎኑ ተቀመጠች….አዲስአለምና ዘሚካኤል ተያይተው ፈገግ አሉ…ወደራሱ ሳባትና ግንባሯን ሳማትና‹‹እናትሽ ሰለም ነች?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አዎ ሰላም ነች…ስሄድ አንተን እንዳገኘሁህ  እነግራታለው››

‹‹በእውነት..እሷ ታውቀኛለች እንዴ?››

‹‹አዎ ብዙ የአንተን ፊልሞች አብረን አይተናል››

‹‹እንዴት ደስ ይላል..ዘፈኖቼንስ?››

‹‹ዘፈኖችህን እኔ ነኝ የምወዳቸው…እሷ ደስ አይሉም ትላለች….ግን ተሳስታለች››

‹‹አይደል ..አዎ ታሳስታለች…›››አለና በሳቅ ተንከተከተ…አዲስአለምም አብራው ሳቀች፡፡

‹‹ምስር የእሱን ዘፈን መዝፈን ትቺያለሽ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹አዎ›› አለች በደስታ፡፡

‹‹እስኪ አንዱን ዝፈኚልን፡፡››

‹‹የትኛውን?››

‹‹ምትቺይውን››

በልበ ሙሉነት‹‹ ሁሉንም ነው የምችለው አለች፡፡››

አዲስ ወደ ዘሚካኤል ዞራ ‹‹አንተ ምረጥላት፡፡››አለችው፡፡

ከፊት ለፊታቸው ወጣችና ልክ ማይክ እንደያዘ ፕሮፌሽናል ዘፋኝ  እጇን አፏ ላይ ቀስራ፣በሚጣፍጡ ኮልታፋ እደበቷ እየተውረገረገች ታስነካው ጀመር…..ቅዱስም ከእናቱ እቅፍ ተንሸረቶ  ሄደ እና ስሯ እንጣጥ እጣት እያለ ያጅባት ጀመረ…ቤቱ በሳቅና ጫጫታ ተሞላ ፡፡ሁለት ሼፎች እየተጋገዙ የምግብ ጠረጴዛውን በምግብ ሞሉት… ሳቃቸው ሳይቆረጥ ተያይዘው ወደምግብ ጠረጴዛው ሄዱና ከበቡት..አሪፍ የምሳ ግብዛ ነበር፡፡

‹‹ደግሰህ ነው የጠበቅከን… አናመሰግናለን››

‹‹እያሾፍሽ መሆን አለበት..ግብዣው እኮ ላንቺ አይደለም የተዘጋጀው.. ለቅዱስና ለምስር ነው፡፡››

ወደእሷ ዞሮ ጭንቅሏቷን እየዳበሳት‹‹ምስር ምሳ እንዴት ነበር?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹በጣም ይጠፍጣል››ስትል በደስታ እንደፈገገች መለሰችለት፡፡

‹‹ሌላ ቀን እናትሽን ይዘሽ ትመጪያለሽ?››

‹‹እሺ ካለችኝ..ይዣት መጣለሁ››

‹‹እሺ ካላለችሽ ደግሞ….እኔ እናንተ ቤት መጣለው››

‹‹በእውነት ትመጠለህ…በጣም ነው ደስ የሚለኝ..ጓደኞቼን አስተዋውቅሀለው፡፡››

‹‹በእውነት… ፕሮሚስ…››

‹‹ፕሮሚስ፡፡››

‹‹አሁን ቤቴን ላስጎብኛሁና ከዛ ወይ አንድነት ወይ እንጦጦ አዲስ የመረጠችው ቦታ ሄደን ዘና እንላለን…እንዋኛለን..ዣዋዥዌ  እንጫወታለን..››

እያዞረ እንያንዳንዱን ክፍል ለአዲስአለም አሳያትና ከቤት ለመውጣት ተዘጋጁ… ከአሳንሱሩ እንደወጡ ቅዱስን አቅፎ ምስርን በአንድ እጁ ይዞ አዲስአለም ከጎኑ ሆና መኪናው ወደቆመችበት ቦታ እየተጓዘ ሳለ ድንገት ካሜራ የደቀኑና ማይክራፎን በእጅ የጨበጡ ጋዜጠኞች ከበቡት፡፡አዲስ አለም አደነጋገጦ ፖሊስ የከበባት ነው ያመሰለችው፡፡

‹‹ዘሚካኤል የአቀፍከው ልጅ ያንተ ነው…..?››ጋዜጠኛው ጠየቀው፡፡

‹‹አይ አጎቱ ነኝ…››ዘሚካኤል ዘና ብሎ መለሰው፡፡

‹‹ማለት የወንድምህ ልጅ?››

‹‹አይ የእህቴ ልጅ ነው…የእሷ ልጅ ነው››ወደአዲስ አለም እየጠቆመ መለሰለት፡፡

‹‹እሷም…››ጋዜጠኛው ወደምስር እየጠቆመ ጠየቀው፡፡

ጎንበስ አለና በአንድ እጁ አቅፎ ወደላይ አንስቶ ለካሜራ እይታ እያስተካከላት‹‹አይ ይህቺማ የእኔ ልጅ ነች…የምስራች ዘሚካኤል ትባላለች፡፡››

እንደዚህ ሲል እንደልጅቷ የደነገጠና  ግራ የተጋባም ሰው የለም…ትኩር ብላ አየችውና እጆቾን በእገቱ ዙሪየ ጠምጥማ ጉንጮን ሳመችው፡፡ይህ ዳግሞ በልተጠበቀ ሁኔታ ቀረፃውን አሳመረው፡፡

‹‹እስከዛሬ የት ነበረች…?እናትዬውስ ማን ነች?››

‹‹ ከዚህ በላይ  ምንም ማለት አንችልም..ይቅርታ እንቸኩላለን››በማለት ልጆቹን እንዳቀፈ ጋዜጠኞቹን እየገፋቸው   ወደ መኪናው ሄደ፡፡መኪና ውስጥ ተቀምጠው ከቦታው እንደተንቀሳቀሱ፡፡

‹‹በድን ሆና የነበረችው አዲስ በፍራቻና በመደናገጥ ወደምስር እያየች‹‹ምንድነው ያደረከው?››አለችው፡፡

‹‹እኔ እንጃ….ምን እንዳደረኩ እኔም አላውቅም›› ዋሻት….ያደረገውን ነገር ሁሉ ያደረገው በእቅድ እና ሆነ ብሎ ቢሆንም ይሄንን ለእሷ ሊያምንላት አይችልም፡፡

‹‹እንደምንም ብለህ ዜናውን  እንዳያሰራጩት ማድረግ አለብህ››

‹‹እስከአሁን በዩቲዩብ ወይም በሆነ መንገድ ለቀውታል፡፡››ተስፋ አስቆራጭ መልስ መለሰላት፡፡፡

‹‹ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያስገባሀኝ..››አለችው በትልቅ ቅሬታ፡፡

‹‹አይዞሽ..ሁሉ ነገር ይስተካከላል…ምኞቴን እንደገለፅኩ አድርገሽ ቁጠሪው››አለና ወደኃላ በከፊል ዞሮ ‹‹ምስር››ሲል ተጣራ፡፡

‹‹አቤት አባዬ›› 

አሁን በድንጋጤ አፉን የመክፈቱ ተራ የእሱ ነበር….በዚህ ጊዜ ትዕግስቷ ያለቀው አዲስአለም ‹‹ዘሚካኤል አንድ ነገር ላስቸግርህ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ ምን ?የፈለግሽውን››

‹‹ ለዛሬ ጉብኝቱ ይቅርብንና ቃሊቲ መነኸሪያ አድርሰን››

በሰማው ነገር ተደናገጠና መኪናውን ጥግ አስይዞ አቆመና ወደኃላ ዞሮ‹‹ምነው ..ለምን?››ሲል ጠየቃት፡፡

የምትናገረውን ነገር ምስር እንዳትሰማ በመፈለግ ስታቅማማ ተመለከታት..መኪናውን ከፈተና ወረደ…እሷም ከፍታ ወረደችና መኪናውን ተደግፈው ማውራት ጀመሩ፡፡

‹‹ምንድነው አዲስ ንገሪኝ?››

‹‹ፀደይ እንዲህ አይነት ነገሮችን እንደቀልድ ችላ ብላ የምታልፍ ሰው አይደለችም…ይሄ ነገር ተሰራጭቶ እሷ ጆሮ ከመድረሱ በፊት ቀድሜ የተፈጠረውና ላስረዳት ይገባል፡፡››

‹‹ምነው ይሄን ያህል…?››
👍5710😁1
‹‹አዎ..አሁኑኑ ወደአዳማ መመለስ አለብኝ…ፀዲ ጓደኛዬ ብቻ ሳትሆን እህቴም ጭምር ነች…በምንም ነገር ስትጎዳ ማየት አልፈልግም..በተለይ እኔ የመጓዳቷ ምክንያት መሆን አልፈልግም፡፡››

‹‹እዚህ ነገር ውስጥ ስላስገባሁሽ ይቅርታ..ግን አሁኑኑ  ጋዜጠኞችን ሰብስቤ የታናገርኩት ለቀልድ እንደሆነ በመግለፅ ማስተባበል እችላለው ››አላት..አዎ ጥሩ ነው እንደዛ አድርግ ብትለው እንኳን እንደማያደርግ እርግጠኛ ነው…ምስርን ልጄ ብሎ ያወጀው አውቆ ነው..እንደውም አዲስ ያልገባት ጋዜጠኞቹ ድንገት በአጋጣሚ የተከሰቱ ሳይሆን እሱ ሆነ ብሎ እንዲጠብቁት አድርጎ ነው፡፡

ከፀአዳ ጋር ባለው የፍቅር ጦርነት ልጇን ምስርን  ስለተጠቀመባት ትንሽ ፀፀት ቢሰማውም ያደረገውን ነገር ሁሉ ያደረገው ግን ሆነ ብሎ በእቅድ ነው፡፡እሱ ከዱባይ ከመጣ አንድ ሳምንት ቢሆነውም እሷን ግን ፈፅሞ ሊያገኛት አልቻለም….በስልክ ደጋግሞ ቢሞክር ልታነሳለት አልቻለችም….አዳማ ድረስ ከአንዴም ሁለት ቀን ሄዶ ሊያገኛት ቢሞክርም ተደበቀችበት..እና በዚህ ጉዳይ በጣም አበሳጭታዋለች ..እልክም አስገብታዋለች..ለዛ ነው አዲስ እንድታግዘው ያሳመናት፡፡እሷም እንዲህ አይነት ነገር ያደርጋል ብላ ሳላላሰበች በደስታ ነበር የተስማማችው፡፡

‹‹ዘሚካኤል…እየቀለድክ ነው እንዴ..?ስለስድስት አመት ልጅ ስሜት እኮ ነው የምናወራው..አባትሽ ነኝ ስትላት እንዴት እንደተደሰተች አታይም…የዛሬ ልጆችን ታውቃቸዋለህ ለቴክኖሎጆ ቅርብ ስለሆነ መረጃዎች በቀላሉ ይደርሷቸዋል፡፡በዛ ላይ ይህቺ ልጅ ከተወለደች ጀምሮ አባት ምን ማለት እንደሆነ ጣዕሙን አታውቅም….ግን እንደማንኛውም ልጅ የሚወዳትና የሚንከባከባት አባት ስትፈልግና ስትመኝ እንዳደገች እርግጠኛ ነኝ..እና አባትሽ ነኝ ስትላት  አልገባኸህም እንጂ ያንን ክፍተት ሞላልሻለው ነው ያልካት…፡እና ማስተባበሉ ሌላ ችግር ነው የሚያመጣው፡፡አሁን እንዳልኩህ ወደመናኸሪያ ውሰደኝ፡፡››
የሰራው ስህተት ይበልጥ እንዲሰማው አደረገች‹‹እሺ ግቢ፡፡››አለና…ዞሮ ወደመኪናው ገባና መሪውን ጨበጠ፡፡እሷም ገባች፡፡ቀጥታ መኪናውን አዞረና ነዳው፡፡ግን ወደመናኸሪያ ሳይሆን ወደአዳማ ነበር የነዳው፡፡አደረሳቸውና ከፀአዳ ሳይገናኝ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe ቤተሰቦች

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍829🔥1
አትሮኖስ pinned «#አላገባህም ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስድስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ //// አዲስ አለም በራሷ መኪና ግን ሹፌር እየነዳላት  ከአዳማ ወደአዲስ አበባ እየተጓዘች ነው፡፡ የተቀመጠችው ከኋላ ወንበር ላይ ሲሆን ከግራዋ የራሷ ልጅ ቅዱስ ሲኖር ከግራዋ ደግሞ የፀአዳ ልጅ ምሰር ትገኛለች፡፡ አዲስአለም ወደአዲስ አበባ የምትሄደው እናቷን ለመጠየቅ ነው፡፡ይሄ ቤተሰቦቾ አዳማ ለቀው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ…»
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ነው፤ የሆነ የሚንጠጣረር ነገር እያደነቆረው ነው፡፡በመከራ ነው ከእንቅልፉ የነቃው…የበራፉ መጥሪያ ድምፅ መሆኑ አወቀ..ስልኩን ከኮመዲኖ ላይ አነሳና ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ይላል፡፡ያልተለመደ ነገር ነው፡፡በዚህ ሰዓት ማን ነው በራፍን መጥሪያ የሚያንጣርረው?፡፡የፅዳት ሰራተኛዋ እንደማትሆን እርግጠኛ ነው፡፡እሷ አንደኛ በዚህ ሰዓት አትመጣም…ብትመጣም የራሷ የሆነ ቁልፍ ስላላት እሱን የምትቀሰቅስበት ምንም  አይነት ምክንያት የላትም….መኝታውን ለቆ ተነሳና ጋዎኑን ደርቦ መኝታ ቤቱን ለቆ ወጣ፡፡፡ሳሎን ደርሶ በራፉን ሲከፍት..እየተመለከተ ያለው  ፈፅሞ በአእምሮው ያልጠበቀውን ነው፡፡ፊቱን በጥፊ ደረቱን በጡጫ እየቀጠቀጠች ገፍትራ ወደውስጥ አስገብታ ትቦጫጭረው ጀመር….‹‹ምን አድርጌሀለው..?እንዴት በልጄ ስሜት እንደዛ ትጫወታለህ..?ምን አይነት አረመኔ ሰው ብትሆን ነው?፡፡››
እንደዚህ አውሬ የሆነች ሴት በእድሜ ዘመኑ አጋጥሞት  አያውቅም፡፡ፊቱን ከብጭሪያ ለመከላከል ሁለቱን  እጆቹን በፊቱ ዙሪያ አድርጎ ለመከላከል ሞከረ፡፡
‹‹አረ ፀዲ ተረጋጊ….››
‹‹አልረጋጋም..እንዲህ አሳብደሀኝ እንዴት ነው የምረጋጋው…..?ልጄን እንዴት እንዳሳደኩዋት ታውቃለህ…?››መደባደቧን እና ጮኸቷን አላቆረጠችም….እንባዋ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ እየረገፈ ነው፡፡ትናንት የሆነውን ከሰማችበት ደቂቃ ጀመሮ ማልቀሷን አላቆረጠችም… ለሊቱን እንቅልፍ ባይኗ ሳይዞር ስትቃጠልና ስትነፈርቅ ስላደረች የእናቱን ሞት አዲስ እንደተረዳ ሀዘንተኛ አይኖቾ ከማበጣቸውም በላይ ክፍኛ ደፍርሰዋል፡፡
ዘሚካኤል መከላከሉ ብቻ እንደማያዋጣ ገባው፡፡እንደምንም አለና ሁለት እጆቾን ያዘና ስቦ ከሰውነቱ ጋር አጣበቃት፡፡
‹‹ልቀቀኝ..ከዚህ ቀፋፊ ሰውነትህ ጋር መነካካት …..››አላስጨረሳትም የተከፈተ አፏን በአፉ ከደነው….በተቻላት መጠን ተወራጨች…ከእሱ ፈርጣማና የዳበረ ጡንቻ ማምለጥ አልቻችም…ከንፈሩን ነከሰችው….ለቀቃትና..ተስፈንጥራ ወደኃላ ልታመልጥ ስትል መልሶ በመያዝ ሙሉ በሙሉ ከስር ገብቷ ተሸከማት……እንደእፃን ልጅ በእግሯም በእጇም ተወራጨች… ወደሶፋው ይዟት ሄደ…ሶፋው ላይ ሊወረውረኝ ነው ብላ ስትጠብቅ እሷን አጥብቆ እንደያዘ እግሩን ዘረጋና ከሳፋው ላይ አንዱን ትራስ ወደወለሉ አወረደ….በፍጥነት ገለበጣትና እንደህፃን አቅፎ ወደታች በጉልበቱ ተንበረከከ እና ወለሉ ላይ አስተኛት…ሾልካ ከስሩ ለማምለጥ ታገለች… በጥንካሬ ጨምቆ ከወለሉ ላይ አጣበቃትና ጭንቅላቱን ቀና አድርጎ ትራሱ ላይ አስደገፋት …እንዳይጨፈልቃት በመጠንቀቅ እላዩዋ ላይ  ተቀመጠ…የለበሰውን ጋወን አውልቆ ወረወረው….
‹‹ምን ልታደርግ ነው?››አይኗቾ በድንጋጤ ፈጠጡ፡፡
ወደታች ጎንበስ አለና የለበሰችውን ቲሸርት ከግራና ከቀኝ ይዞ ወደታች ተረተረው….የመጨረሻውን ንዴት በመናደዷ ምክንያት ደምስሯ ተግተረተረ‹‹ምን እያደረክ ነው? ልትደፍረኝ ነው እንዴ..?እከስሀለው…ስምህን ነው ያማጠፋው….››የቀራት ብቸኛ መከላከያ ምላሷ ብቻ ነበር….ልታስፈራራው ሞከረች ፡፡ተንጠራራና ሌላ ትራስ አምጥቶ ከጎኗ በማድረግ ከላዬ ላይ ወርዶ ከጓና ተኝቶ ወደራሱ ገለበጣትና አቀፋት፡፡
ከታች እሱ በቁምጣ ሲሆን እሷ ደግሞ ልክ እንደወትሮዋ ጅንስ ሱሪ እንደለበሰች ነው፡፡
‹‹በፈጠሪ ስትበሳጪ እንዴት ነው የምታምሪው?፡፡››
‹‹እያሾፍክብኝ ነው?››
‹‹በፍፅም ..አይገባሽም እንዴ ..?ካንቺ ፍቅር ይዞኛል…ላገባሽ እፈልጋለው››
ምትሰማውን ቃል ማመን አቃታት‹‹ይሄ ደግሞ ሌላ ቀልድ መሆኑ ነው?ሕይወት እንደምትተውነው ተውኔት መሰለህ?››
‹‹እሱ እንዳያያዝሽ ነው …እኔ ግን የተናገርኩት ከልቤ ነው…ከፈለግሽ ዛሬውኑ ሄደን መጋባት እንችላለን…እንደማገባሽ እግጠኛ ስለሆንኩ ነው ምስርን ልጄ ነች ያልኩት፡፡››
‹‹እንዴት እሺ ትለኛልች ብለህ አሳብክ?››
‹‹እንደምትወጂኝ አይኖችሽ ውስጥ ስላነበብኩ››
የተፋቀረ ሁሉ ይጋባል ያለህ ማን ነው….ደግሞ እወቅ እኔ ፍቅር አልፈልግም…አሁን ልቀቀኝ ..ከአንተ እስከወዲያኛው መሸሽና መራቅ ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹አይ ከአኔ ሸሽተሸ ማምለጥ  አትችይም፡፡››
‹‹ልቀቀኝ አልኩ..›› ለመመናጨቅ ሞከረች አጥብቆ ያዛትና ከንፈሯ ላይ በድጋሚ ተጣበቀ… ሳላሳ ሰከንድ ያህል ብቻ ነው መታገል የቻለችው..ከዛ ቀስ በቀስ እየለዘበች…  የእጆቾ ጡንቻዎች እየለሰለሱ ..ከንፈሯቾ ለከንፈሮቹ መልስ እየሰጡ መጡ…እሱን ሲቧጭሩ እና ሲደበድብት የነበሩት ጣቶቹ ጀርባውናና መላ ሰውነቱን ማሻሸት ጀመሩ…ከዛ እሱ ቁምጣውን ሲያወልቅ እሷም በገዛ እጇቾ ጅንስ ሱሪዋን እያወለቀች ነበር….እዛ ግዙፍ የሳሎን ወለል ላይ 30 ለሚሆኑ ደቂቃዎች በፍቅር እየተንከባለሉ እና ከኮርነር  ኮርነር እየተሸከረከሩ በጣር የታጅበው ወሲብ ሲሰሩ በራፉ ክፍት መሆኑን እንኳን አላስተዋሉም ነበር፡፡
ከወሲብ በኃላ አርቃኗን ሆና ‹‹አንተ ምን አይነት አዚም ነው ያለህ ግን?››ስትል ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው የፍቅር አዚም ነዋ››
‹‹አይ አይመስለኝም…..የሆነ  የሚያደነዝዝ አይነት መስተፋቅርማ አለህ…አሁን ሻወር ቤቱን አሳየኝ..››አለችው፡፡
ከተዘረረበት ወለል እየተነሳ ወደእሷ ሄዶ ከስር ተሸክሞ ወደምኝታ ክፍሉ ተሸክሟት ገባ….‹‹ያው ግቢና ታጠቢ››
‹‹እሺ…ቲሸርቴን ቀዳደሀዋል….አሁን ምን ልለብስ ነው?››እያለች ገባች፡፡
‹‹አታስቢ አዘጋጅልሻለው….ግን አብሬሽ ሻወር መውሰድ እፈልጋለው፡፡››
‹‹ስርአት ይዘህ የምትታጠብ ከሆነ ትችላለህ›› አለችው፡፡በደስታ እርቃኑን ገባና ተቀላቀላት…መታጠብ ጀመሩ፡፡ ቃል እንደገባው ግን ስርዓት ይዞ አልታጠበም..እሷም በቃላት አውጥታ አትናገር እንጂ ስርዓት የለሽ መሆኑን ፈልጋው ነበር..ከዛ ሻወር ቤት ለመውጣት አንድ ሰዓት በላይ ነበር የወሰደባቸው፡፡ ከዛ ተያይዘው ሲወጡ ሁለቱም ሰውነታቸውን ማዘዝ እስኪያቅታቸው ዝለው ነበር.. ርቃናቸውን ተያይዘው አልጋ ውስጥ ነው የገቡት…ሁለት ሰው መሆናቸውን መለየት እስኪከብድ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተቃቅፈው ለሞት የተቃረበ እንቅልፍ ውስጥ ገቡ፡፡
///
ተመሳሳይ የበራፍ ተደጋግሞ መንጫረር ነበር ከእንቅልፉ ያባነነው..‹‹ዛሬ ደግሞ ምን ጉድ ነው ?››በማለት እየተነጫነጨ…እንደምንም ነቅቶ ስልኩን ሲመለከት..ከ30 በላይ ሚስኮል ነበረው…ሰዓቱን ሲመለከት 7ሰዓት ተኩል ሆኗል…ማመን አልቻለም፡፡ይሄ ሁሉ ሚስኮል ከማን ነው ብሎ ሲያየው አብዛኛው ከአዲስአለም ነው…ስለፀደይ ተጨንቃ እንደሆነ ገመተ ..አልጋውን ለቆ ሲወርድ ፀደይ እራሷን አታውቅም፡፡
ጋወኑን ቅድም ሳሎን ወለል ላይ ትቶት ስለነበረ….ቁምጣ እና ቲሸርት ለበሰና በድኑን እየጎተተ ወደ ሳሎን ሄዶ በራፉን ሲከፍት ክፍኛ የደነገጠችውና አይኗ  የፈጠጠው አዲስአለም በራፉ ላይ ተገትራለች
‹‹እዚህ አልመጣችም…?ወይኔ ጓደኛዬ….›
‹‹አረ ተረጋጊ..ግቢ ››
ወደውስጥ አስገባትና በራፉን መልሶ ዘግቶ ተመለሰ‹‹እሺ የት ሄደች ይባላል ?አንተ ደግሞ ለምንድነው ስልክህን የማታነሳው?››
‹‹አሁን ተረጋጊና ከተቻለሽ ቆንጆ ምሳ ስሪልን››
‹‹ምን እያወራህ ነው?ፀደይ ጠፍታለች እኮ ነው የምልህ››
👍6014
እጇን እየጎተተ ወደመኝታ ቤት ይዞት ሄደና በራን በስሱ ከፍቶ ወደውስጥ አሳያት.. ወዲያው ጎትቶ ወደኃላ አስቀራት…..እንደዛ ያደረገው እንዴት እንደሆነ ሳያውቅ ፀአዳ ብርድልብሱ ከላዬ ላይ ተገፎ ሙሉ እርቃኗን ተዘርራ መተኛቷን ስለተመለከተ ነው….አዲስአለም ግን የሚበቃትን ያህል አይታ ስለነበር…እየነፈረቀች ስታለቅስ የነበረችው ሴት በሳቅ መንፈርፈር ጀመረች‹‹አረ እንዳትቀሰቅሺያት..ድምፅሽን ቀንሺ ›› በማለት ጎትቶ መልሶ ወደ ሳሎን ይዞት ሄደ፡፡
‹‹አንተ ምን አደረካት?፡፡››
‹‹እሱን ቀስ ብዬ ነግርሻለው…አሁን ግን በጣም ነው የራበኝ..እርግጠኛ ነኝ እሷም እርቧታል…ኪችን ግቢና የሆነ ነገር ስሪልን፡፡››
‹‹እንዴ እውነትህን ነው በጣም ነው እንጂ የራባችሁ ››እያለች ሳቆን ሳታቆርጥ ወደኪችን ገባች፡፡

ፀአዳ  ከእንቅልፎ ነቅታና ልብሷን ለባብሳ ወደሳሎን ስትገባ የምግብ ጠረጴዛው በምግብ ተሞልቶ ነበር፡፡በጣም ደስ እያላት ወደዛው ነው የተንደረደረችው፡፡በርሀብ አንጀቷ እየተገለባበጠ ነበር፡፡ሶፋው ላይ ጋደም ብሎ የእሷን መነሳት ሲጠብቅ የነበረው ዘሚካኤል ም ወደእሷ ሄዳና ተቀላቀላት፡፡
‹‹እርቦሻል እንዴ?››
‹‹በጣም እንጂ…ለመሆኑ ይሄን ሁሉ ምግብ ማን ሰራልህ?››በመደነቅ ጠየቀችው፡፡
‹‹ምን ማለትሽ ነው? ራሴው ነኛ….ባለሞያ እኮ ነኝ››
በጥርጣሪ ቀና ብላ አየችውና  መመገቧን ቀጠለች…ምግቡን አዲስአለም ከሰራችና ካቀራረበች በኃላ እንድትቆይ ቢጠይቃትም‹‹ፀደይ ስትነሳ እኔን ካየች ትሳቀቃለች›› በማለት ነው የሄደችው፡፡
ምግቡን በደንብ እስኪጠግቡ ድረስ እየተጎራረሱ በልተው ተነሱ፡፡ስትጠግብ አዲስአለም ትዝ አለቻት፡ወይኔ ጉዴ አዲስ ይሄኔ  የት ገባች ብላ አብዳለች..››በማለት ልትደውልላት ስልኳን መፈለግ ጀመረች፡፡
‹አታስቢ ..እኔ ጋር ደውላ ነበር….ነግሬታለው፡፡›
‹‹ምን ብለህ ነገርካት?››
‹‹እኔ ጋር እንደሆንሽና ፍቅር እያሰራን እንደሆነ ነዋ፡፡››
‹‹አንተ እኮ አታደርገውም አይባልም..ባለፈውም ጣፈጭ ነች ..ምናምን ብለህ ነግረሀት ነበር፡፡››
‹‹እና እውነቴን ነዋ…በጣም በጣም ጣፋጭ እኮ ነሽ››
አፈጠጠችበት‹‹ተረጋጊ…እኔ ጋር መጥተሸ እየተነጋገርን እንደሆነ እና ቆይተሸ እንደምትደውይላት  ነው የነገርኳት››
‹‹በል አሁን ደህና ሁን…መሄዴ ነው››ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡
‹‹አዳማ ማደርስሽ አኔ ነኝ…..››
‹‹አይሆንም››
‹‹ምነው ታፍሪኛለሽ እንዴ?››
‹‹አይ እዚህ የምቆይበት ጉዳይ አለ….ግብርና ሚኒስቴር መስሪያ ቤት መሄድ አለብኝ፡፡››
‹‹ምነው በሰላም..?ገበሬ ልትሆኚ ነው እንዴ?››
‹‹ብሆን ደስ ይለኝ ነበር..ለጊዜው ግን ሰው ለመፈለግ ነው››
‹‹አልገባኝም››አላት ኮስተር ብሎ፡፡
‹‹ባይገባህም ችግር የለውም….በአጭሩ ከአመታት በፊት እዛ መስሪያ ቤት የሚሰራ ሰው አድራሻ ለመጠየቅ ነው፡፡››
‹‹ምነው ዘመድሽ ነው እንዴ?››ጥርጣሬ ባረበበት ድምፅ ጠየቃት፡፡ፈጥኖ ወደ አእምሮው የመጣው የምስር አባት ነው፡፡ወዲያው ግን ‹‹የእሱን አድራሻ መከላከያ ሚኒስቴር እንጂ ግብረና ሚኒስቴር ምን ይሰራል?›› ሲል አሰበና ተረጋጋ፡፡
እሷም‹‹አጥብቆ ጠያቂ የእናቱን ሞት ይረዳል አሉ››ብላ ተረተችበት፡፡
‹‹እንደአሮጊት ተረት ታበዢያለሽ፤ ለማንኛውም አብረን እንሄዳለን››
በመገረም ‹‹የት?››
‹‹ግብርና ሚኒስቴር ነዋ››
‹‹እሺ አትለኝም ብለህ ነው››
‹‹እውነቴን ነው..የምትፈልጊውን ሰው እኔም በአካል ተገኝቼ መወቅ አለብኝ››
‹‹ጥሩ …በል ተነስ እንሂድ….››ብላ ቀድማ ወደውጭ መራመድ ጀመረች..

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe ቤተሰቦች

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍969
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ


/////
እሱም ጃኬቱን ይዞ  ተከተላት፡፡እራሱ እያሸከረከረ የምትፈልገው መስሪያ ቤት ድረስ ወሰዳት፡፡

‹‹እ…ትጠብቀኛለህ ወይስ ትሄዳለህ?››

‹‹ኸረ በፍፁም.. አብሬሸ እገባለው››

‹‹ተው እዚሁ መኪና ውስጥ ጠብቀኝ..ከአንተ ጋር  የሆነ ቦታ መሄድ እኳ በሴቶች አይን ክፉኛ መገረፍ ነው..ታውቃለህ የሰው አይን ደግሞ ያቃጥላል፡፡››

‹‹አረ ባክሽ…!!!››ሞተሩን አጠፋና ከመኪናው ወረዳ… እሷም ወረደች…ክንዷን ያዘና ወደውስጥ መራመድ ጀመረ..መራመድ አቅቷት እግሯቾ ተሳሰሩባት፡፡ግን ምርጫ አልነበራትም፡፡
ግቢ ውስጥ ገቡና ወደኢንፎሪሜሽን ዴስክ ሲደርሱ እሱን እንግዳ ማረፊያ ወንበር ላይ አስቀጠችውና እሷ ወደዛው አመራች…ከአስር ደቀቂቃ በኃላ ግን አንገቷን ደፍታ ወደእሱ ተመለሰችና ከጎኑ ቁጭ አለች፡፡

‹‹ምነው ፍቅር…አገኘሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አይ ..ጠመሙብኝ …ሰውዬው ከአራት አመት በፊት የዚህ ቢሮ ዳሬክተር ዴሬክቶሬት ነበረ…አሁን የት እንዳለና ቢያንስ ስልኩን እንዲሰጡኝ ነበር የጠየቅኳቸው…››

‹‹ቆይ ሰውዬው ምንሽ ነው?››

‹‹ምኔም አይደለም..ጭራሽም አላውቀውም..ግን ስለአባቴ መረጃ እንዳለው በሆነ መንገድ አውቄለው…እሱን ካገኘው አባቴ ይሙት ይኑር ማወቅ እችላለው፡፡››

የነገረችውን ያለምንም ጥርጣሬ አመናት…አሳዘነችው፡፡‹‹የሰውዬው ስም ማን ነው?››
ሙሉ ስሙን ነገረችው፡፡

‹‹ቆይ እንደውም ተነሽ›› ብሎ እጇን ይዞ ወደኢንፎርሜሽን ዴስኩ መራመድ ጀመረ..እሷ ምን ሊያደርግ እንደሆነ ሳይገባት ዝም ብላ ተጎተተችለት፡፡እንደደረሰ በትንሿ መስኮት ጎንበስ ብሎ ሲመለከት ..ሁለት ልጅ እግር ሴቶች ታዩት

‹‹ጤና ይስጥልኝ?›› ሲላቸው ሁለቱም አፋቸውን ከፍተው ፀጥ አሉት፡፡

‹‹እባካችሁ የሆነ ነገር ላስቸግራችሁ ነበር››

‹‹ምን ፈለክ…?ምን እንርዳህ?››አንደኛዋ ከመቀመጫዋ  ተነስታ በመንሰፍሰፍ ጠየቀችው፡፡

‹‹እሷ እህቴ ነች..ከኃላው ያለችውን ፀአዳን ተመለከተችና‹‹ማንን ነበር ያልሽን?››ስትል  ድጋሚ ጠየቀቻት፡፡

ፀአዳ  ነገረቻት፡፡‹‹ቆይ እስኪ ››አለችና በኋላው በራፍ በመውጣት ወደእነሱ መጣች..እስቲ ተከተሉኝ ጋሽ ይርጋ በደንብ ያውቃሉ፡፡ጋሽ ይርጋ ማለት እዚህ መስሪያ ቤት ለ30አመት የሰሩ የመዝገብት ቤት ሰራተኛ ናቸው፡፡››የምታወራውን እያዳመጡ ከኋላ ተከተሏት‹‹አስቸገርን አይደል..?››አላት፡፡

ወደኃላ ዞራ‹‹‹አረ ችግር የለውም…ለዛውም ላንተ..ባይ ዘወዌ በጣም አድናቂህ ነኝ››አለችው
‹‹አመሰግናለው››ትህትና ባልተለየው የድምፅ ቃና መለሰላት፡፡

ከ10 ደቂቃ በኃላ የሰውየውን ሙሉ አድራሻ ይዘው ከቢሮ ወጡ…መኪና ውስጥ ገብተው መጓዝ እንደጀመሩን‹‹አየሽ አንቺን ሰምቼ ከስርሽ ቀርቼ ቢሆን ኖረ ምን እንደሚያጋጥምሽ ተመልከቺ››አላት በኩራት፡፡

‹‹እሱስ እውነትህን ነው..አድራሻውን እንዲህ በቀላሉ አላገኘውም ነበር›

‹‹እና ሽልማት የለኝም?››

‹‹አለህ..ምን ትፈልገለህ…?መክሰስ ልጋብዝህ?››

‹‹አዎ ግን ቤትሽ››

‹‹ቤትሽ?››ግራ በመጋባት አፍጥጣ አየችው፡፡

‹‹አዎ ምነው ላደርስሽ አይደል…አሁን አስር ተኩልነው… አስራሁለት  ሰዓት ሳይሆን እዛ እንደርሳለን…ከዛ  ቤትሽ መክሰስ ትጋብዢኛለሽ››

‹‹ለምን መክሰስ..እራት ቢሆንልህ አይሻልም….በዛውም ታድራለህ››

በፈገግታ ተሞልቶ‹‹አንቺ እኮ ምርጥ ነሽ…….››ሲል መለሰ

‹‹አረ  አላደርገውም …..ጎረቤቶቼስ ምን ይሉኛል.?.››

‹‹ምንም ይበሉሽ……››

‹‹አይ አይቻልም ከፈለክ ውጭ ልጋብዝህ››

‹‹ውጭ አልፍግም….. ባይሆን እዛ እስክንደርስ አስቢበት››አላት፡

ቀጥታ ወደአዳማ እየነዳ ነው፡፡‹‹አሁን ታዲያ እንዴት ልታደርጊ ነው?››

‹‹ግራ ገብቶኛል..ግን ምን ቢሆን ነው አንድ አመት ሙሉ አማኑኤል ህክምና ላይ የቆየው››

‹‹ያው አማኑኤል ምን ሲኮን ነው የሚቆየው? ጭንቅላቱን አሟት ነዋ….፡፡››መለሰላት፡፡

‹‹ታዲያ ከዛ ሲወጣ ሁሉን ነገር ጣጥሎ ቤተሰቦቹ ጋር ቦንጋ እንደገባ ነው የነገሩን ..እንዴት እንደዛ አይነት ውሳኔ ወሰነ…?ይታይህ በአንድ ወቅት ትልቅ ስልጣን ላይ የነበረ ጉምቱ ባለስልጣን በዛ ላይ ዶ/ር ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ቦንጋ …ከቦንጋም ገጠር  ጠቅልሎ ሲገባ አይገርምም፡፡

‹‹ይገርማል..ግን እደእኔ እንደእኔ የብልህ ውሳኔ ነው የወሰነው ..ይሄ ሰው ጭንቀትና የአእምሮ በሽታ ካለበት ትክክለኛ መረጋጊያ ቦታ ገጠር ነው..ይታይሽ እዚህ አዲስ አበባ እንኳን ለአእመሮ ህመምተኛ ለጤነኛው ሰው ትርምሱና ኳኳታው አስጨናቂ ነው…ይልቅ እኔ ያሳሰበኝ ….አሁን ምን ልታደርጊ ነው?፡፡የሚለው ነው፡፡

‹‹ቦታው ላይ ሄጄ እድሌን ሞክራለው››ስትል በእርግጠኝነት መለሰችለት፡፡

‹‹የእውነት ?››አለ ደነግጦ፡፡

‹‹አዎ….ይሄ እኮ ሲሪዬስ ነገር ነው….››

‹‹አውቃለው ..ግን እዛ ደረስ ሄደሽ ምንም ሊነግርሽ ባይችልስ…..?ማለቴ ከጤናው አንፃር ምንም ነገር ባያስታውስስ?››

‹‹ምንም ይሁን ምን  ሰውዬውን ፊት ለፊት አግኝቼው መሞከር እፈልጋለው….ካለበለዚያ,--እረፍት አላገኝም፡፡››ስትል መለሰችለት፡፡
///
አቶ ቅጣው አዲሱ ክፍሉ በጣም ተመችቶታል…እንደውም በፊት ካለበት ክፍል ጋር ሲነፃፀር ከሲኦል ወደገነት የመዘዋወር አይነት ነው፡፡መኝታ አልጋ ያለው ..በቂ ብርሀን የሚያስገባ ንፁህ ክፍል ነው ያስገቡት፡፡በዛ  ላይ እግሩም ሆነ እጁ ከሰንሰለት እስር ነፃ ስለሆነና ምግብም ሰዓቱን ጠብቆ ስለሚመጣለት ሰውነቱ ተአምራዊ በሆነ መልኩ እያገገመ ነው፡፡ክፍል ውስጥም ቢሆን እንደፈለገው እየተንቀሳቀሰ ቀላል ስፖርቶችን መስራት ችሏል…በዛ ምክንያት መንፈሱም ሆነ አካሉ ልዩ ለውጥ አምጥቷል፡፡
አሁን ቁጭ ብሎ መፅሀፍ ቁዱስ እያነበበ ነው፡፡ይሄንን መፅሀፍ ቅዱስ ከ10 ቀን በፊት ነበር ጠያቂው እና መካሪው መነኩሴ ናቸው አምጥተው የሰጡት፡፡ወዲያው  ግን ማንበብ አልቻለም ነበር…፡፡አይኖቹ ለወራት ጨለማ ክፍል ውስጥ ስለከረሙ በቀላሉ ከብዣታ አገግመው ፊደል እየለቀሙ ለማንበብ ተቸግረው ነበር…ከጥቂት ቀናት ወደዚህ ግን  እንደምንም ለማንበብ ችሏል፡፡
መለኩሴው የመጡ ቀን እንደተለመደው..ጠያቂ አለህ ተብሎ ነበር ከክፍል የተወሰደው፡፡የሚጠብቁት ክፍል ውስጥ ሲገባ እንደወትሮ በሰንሰለት እጅና እግሮቹ ተጠፍሮ የተቀደደ እና የተቦጫጨቀ ልብስ ለብሶ ሳይሆን በተለየ ሁኔታ ነበር፡፡እና በዚህ ሁኔታ ይደነቃሉ ብሎ ጠብቆ የነበረ ቢሆንም መነኩሴው ግን ልክ እንደወትሮ በተመሳሳይ ስሜት ነበር ያተናገሩት
ልጄ ይህ ግንኙነታችን የመጨረሻችን ነው… ልሰናበትህ ነው የመጣውት..›› ሲሉት ከዚ በፊት ተሰምቶት የማያውቀው ብቸኝነት ነው የተሰማው፡፡

‹‹አባ ለምን…?መመላለሱን ሰለቹ እንዴ?››

‹‹አይደለም… ልጄ ልሄድ ነው››

‹‹ወዴት ነው የሚሄዱት?››

‹‹ወደአባቴ…ወደፈጣሪ››

ሌላ ድንጋጤ፣‹‹እንዴ ያሞታል እንዴ?››

ፈገግ አሉ‹‹ አይ ልጄ ወደፈጣሪ ለመሄድ እኮ የግድ መታመም የለብንም…አምላክ በቃ ወደእኔ ና ብሎኛል…የዛሬዋን የመጨረሻ ቀኔ አንተንና ሌሎች ልጆቼን ለመሰናብት ነው የሰጠኝ..መቼስ ፡እሱ ለቸርነቱ ዳርቻ የለው… እኔ ሀጥያተኛውን መሞቻ ቀኔን ነገሮች ለመሰናበቻ ሚሆን ቀን ፈቅዶልኝ…ተመስገን ነው ..ተመስገን፡፡››

መነኩሴው የሚያወሩትን ሊገባው አልቻለም፡፡‹‹አባ እኔ ሞት የተፈረደብኝ ሰው እያለው እርሶ…..››
👍6011😱1
‹‹ልጄ የእኔ እኮ ሞት አይደለም..እረፍት ነው..ወደ አባቴና ወደፈጣሪዬ ነው እኮ የምሄደው … የመሄጃ ቀኔን በናፍቆት እና በጉጉት የምጠብቀው…ለእኔ ሰርጌ ነው፡፡››
ሞቱን እንደዚህ በጉጉት የሚጠብቅ ሰው አጋጥሞት አያውቅም…

‹‹ልጄ አሁን ሰለኔ ማውራቱ ይበቃህ…››.ደረታቸው ላይ አንጠልጥለው ከያዙት ኮሮጆ ውስጥ መፅፍ ቅዱስ አወጡና

‹‹ልጄ ስሰናበትህ ይሄንን ሰጥቼህ ነው የምሄደው፡፡››አሉት፡፡

‹‹እና አንድ መደበኛ ጠያቂዬ እርሷ ነበሩ..አሁን እርሷንም ላጣ ነው እንዴ?፡፡

‹‹አይ ትልቁን ነገር ሰጠሁህ እኮ….እኔም መጥቼ የማወራህ ከመፅሀፉ የተማርኩትን ነው….አሁ ግን ዋናውን የእውቀትና የእውነት ምንጭ ሰጠሁህ..ወር እየጠበቅክ ሳይሆን በፈለክ ጊዜ ገለጥ አድርገህ ከመፀሀፉ ጋር ማውራት ትችላለህ…እመነኝ ሌላ ጠያቂ ባይኖርህም ምንም የሚጎድልብህ ነገር የለም፡፡››

‹‹ይሁን እሺ አባ..እርሷ የእኔን እውነት እንደተረዱልኝ ልጆቼም ቢረዱኝ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር መሰሎት፡፡››

‹‹አይዞህ በጊዜ ሂደት ይረዱሀል…ደግሞ እውነት  እንደውሸት ፈጣን አይደለችም… አስተዋዬች ብቻ ፈልፍው የሚያገኞት ገፀ-በረከት ነች፡፡እውነትን ማንም ያወራታል….በትክክል እውነትን የሚያገኞትና የሚኖሯት ግን ጥቂቶች ናቸው….ምን መሰለህ ልጄ……ስለእውነት መተንተን ከፈላስፎች ዋናኛ ስራዎቸ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የሀይማኖተኞችም ስብከት ማራኪ ርዕስ ነው፡፡የስነምግባር መምህራኖችም የአስተምሮታቸው ማጠንጠኛቸው እውነት ነች፡፡እውነት ማሰብ  …እውነት ማሽተት.. እውነት መንገድ ላይ መጓዝ የሁሉም ምክርና የህይወት መመሪያ ነው፡፡ግን እውነት ምንድ ነው..?የሚባለውን ያህል ተጨባጭ ነውን.?.ሁላችንንም የሚያስማማ አንድ እውነት አለን?፡፡እንደዛ ቢሆን እኮ በአለም ላይ ያሉ፡፡ምስቅልቅሎች በአብዛኛው ባልተከሰቱ ነበር…በአብዛኛው  ደም አፍሳሽ ጦርነቶች የሚከሰቱት ሁለት እውነት አለን ብለው አምርረው በሚያምኑ አካላት ነው፡፡ሁለቱም አለን ለሚሉት እውነት ታማኝ ናቸው….ሁለቱም አለን ለሚሉት እውነት ማሳመኛ ደርዘን በላይ መረጃዎችን በቀላሉ ማቅረብ ይችላሉ…ለዛም ነው እውነታቸውን ከሚተዉ ህይወታቸውን ቢያጡ የሚመርጡት…..ታዲያ እነዚህ የሚዳኛቸው ዳኛ የየትኛውን እውነት ይመርጣል…?.
አሁንም አንተም የእኔን እውነት እንዴት በቀላሉ አልተረዱኝም ብለህ አትብከንከን…አንተ ቨየምታውቀው መረጃዎች እነሱ ጋር የሉም፡፡እውነትን በፍቅር ካላስረዳህ በክርክር ማንንም አታሳምንም፡፡እውነት በትእግስትና በጥበብ ካልታገሰች በመቅረዝ ላይ ወጥታ ማብራት አትችልም፡፡ስለዚህ ትዕግስት አድርግ…ጥበበኛ ሁን!!፡፡

‹‹እርሶስ እወነቶትን ነው….አሁን እዚህ ቁጭ ብዬ ሞቴን እየጠበቅኩ የምቀናው በማን እንደሆነ ያውቃሉ…ውጭ ባሉት ሚሊዬነር ጎደኞቼ አይደለም…በእንደእርሶ አይነት ሀይማነተኛ ሰው ነው፡፡ሀይማኖተኛ መሆን ነው የምፈልገው፡፡

መነኩሴው በቅጣው ንግግር እንደመተከዝ አሉና‹‹ልጄ በሀይማኖተኛ ሰዎች አትቅና…መንገዳቸውንም ለመከተል አትባክን..ይልቅ ፋለጋው አድካሚ ቢሆንም መንፈሳዊ ሰዎችን አስሰህ አግኝ ፣ከእነርሱ እግር ስርም ቁጭ ብለህ ተማር…››
የተናገሩት ነገር ግልፅ አልሆነለትም፡፡ ‹‹መንፈሳዊያኑን ከሀይማኖት ሰዎች እንዴት እንለያቸዋለን?››ሲል ጠየቀ ፡፡

‹‹አስተዋይ ከሆንክ ቀላል ነው…አምስት ደቂቃ ሲያወሩ ብታዳምጥ በቀላሉ ትለያቸዋለህ፡፡ሀይማኖተኛ ሰዎች ስለጠላትና ሴይጣን አብዝተው ያወራሉ…ስለመሰናክልና ዝሙት በዝርዝር ይደሰኩራሉ…፡፡ምንፈሳዊያኑ አንደበት ግን ስለ ፍቅርና ፅድቅ ብቻ ነው የምትሰማው …የሚያስጨንቃቸው ፍፅም መልካምነትና ፍፅም ምሉዕነት ነው፡፡ ሀይማኖተኞቹ ስለሀይማኖታቸው ብቻኛ መዳኛ መንገድ ሲነግሩህ መንፈሳዊያኑ ግን ስለምሉዕነትና ስለሁለንታና ያወሩሀል…ከሀይማኖተኖቹ ጋር ስታወራ ሰለ መርከስህና ስለሀጥያትህ እንድታስብ እና ራስህን በመጠየፍ የፀፀት  ስሜት ውስጥ ገብተህ እንድትሰበር ነው የሚያደርጉህ፡፡   መንፈሳዊያኑ ግን ስለምህረት እና ይቅርታ ነው የሚያወሩህ… ሰው እንድትሆንና ቀና እንድትል ያበረታቱሀል…ውስጥህ የተቀበረው ቅዱሱ ማነነትህ  እንዲበለፅግና እንዲጎለብት ያግዙሀል፡፡ከጥላቻ ርቀህ የፍቅር ምርኮኛ እንድትሆን ያሰለጥኑሀል፡፡ ››

‹‹አሁን ገባኝ…ግን እኔ እነሱ ፈልጎ የማግኘት እድሉ አያኖረኝም››

‹‹ያ እውነት አይደለም፡፡አንተ ብቻ በርትተህ ፈልግ…ፀልይ.. እግያብሄር የቀረውን ያበጃጃል…ለእሱ የሚሳነው ነገር የለም…እስካዛው ግን እዚህ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን መንፈሳዊ ሰዎችን አውራቸው…እነሱ መንገዱን ይመሩሀል…ጥበቡንና መስተዋሉን እንዲኖርህ ያደርጉሀል፡፡በል አሁን ጠባቂዎቹ ሰዓታቹሁ አልቋል ሳይሉን በፊት የመጨረሻ ፀሎታችንን እንፀልይ ብለው… መቀመጫቸውን ለቀው ተንበረከኩ፡፡ቅጣውም መፅሀፉ ቅዱሱን በደረቱ ላይ ለጥፎ እንደያዘ ከጎናቸው ተንበረከከ…..
እንግዲህ ከመነክሴው ጋር ለመጨረሻ ጊዜ የተለያዩት በዛ መንገድና ሁኔታ ነበር፡፡ይሄው አሁን የእስር ቤት ክፍል ውስጥ ሆኖ እሷቸውን እያናፈቁት ነው‹‹የእውነት እንዳሉት ሞተው ይሆን ወይስ …?››የሚል ሀሳብ እየተወዛገበ ነው፡፡እንደምንም እራሱን ከሀሳቡ አራቀና በፅሞና መፅሀፍ ቅዱስን ማንበብን ቀጠለ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe ቤተሰቦች ይሄ ሁሉ ህዝብ እያለ አረ 500

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8110🥰1
አትሮኖስ pinned «#አላገባህም ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስምንት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ ፡ ፡ ///// እሱም ጃኬቱን ይዞ  ተከተላት፡፡እራሱ እያሸከረከረ የምትፈልገው መስሪያ ቤት ድረስ ወሰዳት፡፡ ‹‹እ…ትጠብቀኛለህ ወይስ ትሄዳለህ?›› ‹‹ኸረ በፍፁም.. አብሬሸ እገባለው›› ‹‹ተው እዚሁ መኪና ውስጥ ጠብቀኝ..ከአንተ ጋር  የሆነ ቦታ መሄድ እኳ በሴቶች አይን ክፉኛ መገረፍ ነው..ታውቃለህ የሰው አይን ደግሞ ያቃጥላል፡፡››…»
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ዴርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ፀደይና ዘሚካኤል ዶ/ሩን ለማግኘት ቦንጋ ከተማ ይገኛሉ፡፡ይሄ ጉዞ እንደዚህ አልነበረም የታሰበው፡፡ሚካኤልና እሷ ነበሩ ለሳምንታት አብረው ለመሄድ ሲዘጋጁ የነበሩት፡፡ከዛ ዝግጅቱ ሁሉ ተጠናቆ…ሚካኤል ቻርተር አውሮፕላን ተከራይቶ ወደቦንጋ ለመብረር ከአዳማ ተነስተው  አውሮፕላኑ ወደሚገኝበት አዲስ አበባ ሲደርሱ ዘሚካኤል ጠበቃቸው፡፡

ሁለቱም ያልጠቁት ነገር ስለሆነ በጣም ነበር ግራ የተጋቡት፡፡ዘሚካኤል እንደአጋጣሚ ከአዲስአለም ጋር ሲደዋወል ነበር ስለጉዞው የነገረችው፡፡
ለማናቸውም ሰላምታ ሳይሰጥ‹‹ፀዲ ከእኔ ጋር ነው መሄድ ያለብሽ?››አላት፡፡

‹‹ማለት…?ለምን ሲባል?››
‹‹በቃ ካንቺ ጋር መሄድና አብሬሽ መሆን እፈልጋለው››
ሚካኤል እጁን አጣጥፎ በገረሜታ እና በትዝብት እየተከታተላቸው ነው፡፡ፀደይን በተመለከተ እንዲህ ሲሪዬስ በመሆኑ ደስታ ተሰምቶታል፡፡

‹‹አይ…ከሚኪ ጋር ነው የምንሄደው…..አንተን ማስቸገር አልፈልግም››ኮስተር ብላ ተቃወመችው፡፡

እሱም ከእሷ በጠነከረ መኮሳተር‹‹እኔ ደግሞ አልስማማም….በችግርሽ ጊዜ አብሬሽ መሆን እፈልጋለው….የአባትሽን አድራሻ ብታገኚም ባታገኚም አብሬሽ ሆኜ ደስታሽንም ሆነ ሀዘንሽን መካፈል አለብኝ››ብሎ ግግም አለ፡፡

ሚካኤል ፀአዳ ስለ/ዶሩ  እንደዋሸችው ስለሚያውቅ በውስጡ ፈገግ እያለ‹‹ፀዲ አንዴ ላናግርሽ?››አላት፡፡

‹‹ቆይ ጠብቀኝ መጣው››ብላው ከዘሚካኤል ተለየችና ወደሚካኤል ሄደች፡፡

‹‹ፀዲ እሱ አንዴ ከጠመመ እሺ አይልም..››አላት፡፡

‹‹እና ከእሱ ጋር ሄጄ እንዴት ልሆን ነው?››

‹‹አሪፍ ነው እንደውም…ይሄ የእግዚያብሄር የራሱ እቅድ ይሆናል…ሁኔታዎችን እንዳመጣጣቸው ትወጫቸዋለሽ… ከሰውዬው የሆነ ጠቃሚ መረጃ ብናገኝ እንኳን እሱን አስረድቶ ማሳመን ከባድ ነው የሚሆንብን .. በኃላ እንዲህ ነው የተፈጠረው..እንደዛ ነው የሆነው ከምንል ቀጥታ ከፈረሱ አፍ ቢሰማ ነው የሚሻለው››

‹‹አረ ተው ሚኪ..››

‹‹ግድ የለሽም ባንቺ እተማመንብሻለው፡፡››አለና ጉንጮን ስሞ በፈገግታ በመጣበት መኪና ተመልሶ ሄደ፡፡
///
እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነው ሁለቱ  ቦንጋ  ከተማ ሊገኙ የቻሉት፡፡እንደደረሱ ፀደይ ከዘሚካኤል ዞር አለችን የዶ/ሩ ነው ተብሎ በተሰጣት  ስልክ ደውላ ነበር፡፡የዶ/ር ወንድም ነኝ የሚል ሰው ነበር አንስቶ ያዋራት፡፡‹‹ለምን እንደመጣችና ዶ/ርን  ለምን ጉዳይ እንደፈለገችው በአጭሩ ነገረችው፡፡

‹‹ላናግረውና መልሼ ልደውልልሽ ››አለና ስልኩን ዘጋ፡፡ሰውዬው መልሶ እስኪደውል ለሀያ ደቂቃ ተጨንቃ ነበር፡፡‹‹አይ ማግኘት አልፈልግም ቢል ምን አደርጋለው?››የሚልው ሀሳብ ትንፋሽ እስኪያጥራት ድረስ ነበር ያስጨነቃት፡፡ደውሎ ግን አስደሳች ነገር ነው የነገራት፡፡ በፈለጉት ሰዓት መምጣት እንደሚችሉ እና ሊያናግራቸው ፍቃደኛ እንደሆነ ነገራት፡፡ጊዜ ሳያባክኑ ወዲያው ነበር ባጀጃጅ በመከራየት ከከተማው የአንድ ሰዓት መንገድ ወደሚርቅ ገጠር ጉዞ ጀመሩ፡፡

እየሄዱ ሳሉ በገጠሩ ውበት ተደምማ..ዶዶላ ሆኜ አልፎ እልፎ ገጠር ሄድ ነበር..እዛም እንዲህ ውብ ነበር….እና በጣም ነበር ደስተኛ የምሆነው፡፡››

‹‹ገጠር ዘመድ ነበረሽ?››

‹‹አይ የጎደኛዬ ቤተሰቦች ገጠር ነበሩ.. እሱ ነበር ይዞኝ የሚሄደው››

‹‹ጓደኛዬ ስትይ…?››

‹‹የምስር አባት››

ወደራሱ ጎትቶ እያቀፋት‹‹በጣም ነው አይደል የጎዳሽ?››አላት ፡፡

‹‹አዎ!!በፊት በጣም የምጠላውና ባገኘው የምገድለው ይመስለኝ ነበር፡፡››

‹‹አሁንስ?››

‹‹…አሁን ግን  ሙሉ በሙሉ ይቅር ብዬዋለው››አለችው፡፡

‹‹ግን እንዴት በዛ መጠን የምትጠይውን ሰው እንዲህ በቀላሉ ይቅር ማለት ቻልሽ?››ሲል በገረሜታ ጠየቃት፡፡ይህንን ጥያቄ የጠየቃት እሱ በቤተሰቦቹ ላይ የቋጠረውን ቂምና ጥላቻ አሁንም በልቡ ውስጥ ቋጥኝ ሆኖ እያስጨነቀው በመሆኑ እሷ የነገረችውን ነገር ማመን ስላቃተው ነው፡፡

እሷ ግን እርግጠኛ በመሆን ታስረዳው ጀመር….‹‹ምን መሰለህ..በእኔና በእሱ መካከል የተፈጠረው ችገር የዛሬ ስድስት  አመት  የሆነ ነው››

‹‹እና ጊዜ ቁስልን ይፈውሳል በሚለው ብሂል ሄደሽ ነው?››

‹‹አይ እንደእሱ አይደለም…ሳስበው የዛሬ ስድስት አመት የነበረችው ፀደይ አሁን ካለችው ፀደይ ጋር በብዙ ነገር እንደምትለይ ገባኝ..እንደውም አንዳንዴ ያቺ ፀደይ ልክ እንደአንድ የምወዳት ዘመዴ ትናፍቀኛለች…››

እያወራች ያለችው መጀመሪያ ከተነሱበት ሀሳብ ጋር ምንም አልገጣጠም አለው…ቢሆንም በትግስት ማደመጡን ለመቀጠል ወሰነ..
እሷም ቀጠለች‹‹እና አሁን ያለሁት ፀደይ የዛን ጊዜ ባለፍኩበት ሁኔታ ላይ ብሆን ተመሳሳይ ችግር ላይ እወድቃለው..?ብወድቅስ ተመሳሳይ ምላሽ ነው የምሰጠው..?ማለቴ ራሴን ስለማጥፋት አስባለው….?ቤተሰቦቼንና ሀገሬን ጥዬ ወደማላውቀው ከተማ እሰደዳለው…?አንዱንም አላደርግም…፡፡ችግሩን በተለየ መንገድ ነበር የምፈታው…ይሄንን ወደ እሱ ቀየርኩት…አሁን እሱ በህይወት ካለ የሆነች ሴት አፍቅሮ ካስረገዘ በኃላ ደምፁ አጥፍቶ ይሸሻል…?እርግጠኛ ነኝ ቢያንስ እናትዬውን እንኳን ለማግባት ባይፈልግ ልጁን የራስሽ ጉዳይ ብሎ ዞር አይልም፡፡ታዲያ ዛሬ ባገኘውና ጥላቻዬን ባሳውቀው ካዛም አልፌ ልበቀለው ብሞክር ትርጉም ይሰጣል…አይሰጥም..፡፡ምክንያቱም ያ እኔ ማውቀው ልጅ ጠፍቶል… በብዙ ነገር ተቀይሮ በብዙ መከራ ውስጥ አልፎ ብዙ ህይወት ልምዶችን ቀስሞ ሌላ ሰው ሆኖ ነው ማገኘው..እና ሌላ ሰው ባጠፋው ሌላ ሰው የመቅጣት ያህል ነው….ለዛ ነው ይቅር ልለው የወሰንኩት፡፡››

ዘሚካኤል ዝም ነው ያላት…የነገረችውን ጠቅላላ ወደራሱ ህይወት ወስዶ ነው ማሰላሰል የፈለገው…፡፡ከዛሬ ሰባት በፊት የነበረው ዘሚካኤልና አሁን ካለው ዘሚካኤል ፈፅሞ የማይመሳሰል… የተለያየ ፍላጎት ..የተለየ አላማና አመለካከት ያለው ነው ፡፡እና መቶ ፐርሰንት የሚመሳሰሉበት ነገር ቢኖር በስማቸው ነው፡፡እሱንም ቢሆን የአባቱን ስም ስላስቀየረ….መቶ ፐርሰንት ሊባል አይችልም፡፡
//
ከቦንጋ ከተማ የአንድሰዓት እግር መንገድ ሄደው ነው ሰውዬውን ያገኙት፡፡ግዙፉ የሆነ በአረንጎዴ ዛፎችና ተክሎች ተሞላ ውብ ግቢ ነው የገቡት፡፡የሰውዬው ወንድም ነው የተቀበላቸው፡፡ ‹‹ወደማሳ ሄዶል አሁን መምጫው ደርሶል   ግቡና ጠብቁት ››ብሎ ወደግዙፉ የሳር ጎጆ ቤት ይዞቸው ገባ ፡፡ቤቱ ፅድት ያለ ነው፡፡ጥግ ላይ በለአንድ ሜትር የተነጠፈ አልጋ አለ..ከአልጋው አጠገብ ከእንጨት የተሰራ መደርደሪያ አለ..መደርደሪያው ግማሽ በመፅሀፍ ተሞልቷል፡፡ከስር በኩል አንድ መለስተኛ ቴፕ ይታያል፡፡

‹‹ግቡ ››አላቸውን የሚቀመጡበት ወንበር ሰጣቸው፡፡እና መቀመጣቸውን ካረጋገጠ በኃላ ተመልሶ ወጣ፡፡

‹‹አይ ሰውዬው ጥሩ ሁኔታ ላይ ሳይሆን አይቀርም››አላት ዘሚካኤል፡፡

‹‹በምን አወቅክ?››

‹‹አንድ ሰውን እኮ በቤቱ ሁኔታ መገመት ትቺያለሽ..አታይም እንዴ ምንም የቆሸሸ ምንም የትዝረከረከ  ነገር የለም….››

‹‹እንደአፍህ ያድርግልኝ.››አለችው፡፡

ድንገት ዘሚካኤል ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ ተነሳ..ሁኔታው ፀአዳን በጣም አስደነገጣት…እና አብራው ብድግ አለች…የሆነ እባብ ያየ ነው የመሰላት….ተንዳርድሮ ወደአልጋው ተጠጋ ..ከአልጋው በግራ በኩል ባለ መለስተኛ ጠረጴዛ ላይ ብዛት ያላቸው  በፍሬም ያሉ ፎቶዎች ተደርድረውበታል…ቀጥታ ሔደና ተራ በተራ እያነሳ ያያቸው ጀመር….ፀደይ ያልጠበቀችው ነገር ነው ያጋጠማት…ፎቶውን እያየ ወደእሷ ዞረና አፈጠጠባት›

‹‹ይሄ ምንድነው?››
👍496👏2
‹‹ፎቶ ነዋ››

‹‹እሱማ ፎቶ ነው…..የእናቴና የእህቴ ፎቶ እዚህ ሰውዬ ቤት ምን ይሰራል?››አንቧረቀባት

‹‹ተረጋጋ..አስረዳሀለው››

‹‹እንዴት ነው የምታስረጂኝ……?››የያዘውን ፎቶ አስቀመጠና ሌላ ፎቶ አነሳ‹‹እያት ይህቺ እናቴ ነች…ሌላ የማላውቀው ሰው እየሰማት ነው….ሰውዬው ማን ነው?››

‹‹ዶ/ሩ ነው… ልናገኘው የመጣናው፡፡››

‹‹ምን እየተካሄደ ነው..ይሄ ነገር ፈጽሞ ከአንቺ አባት ጋር የሚገናኝ አይደለም አይደል….?ይሄ የቤተሰቦቼ ጉዳይ ነው?››

ጭንቅላቷን ከፍ ዝቅ በማድረግ አረጋገጠችለት

‹‹እናቴ እንዴት በማላውቀው ሰው ትሳማለች…?.እንዴት ይሄን ሰውዬ ልትስመው ቻለች?››

‹‹በጣም ታፈቅረኝ ስለነበር››የሚል መልስ ከወደ በራፉ ሰሙ..ሁለቱም ዞር ሲሉ እሱን ለማግኘት የመጡት ዶ/ር ለሜቻ በቀለ ሙሉ ገበሬ መስሎ የሰሌን ኮፍያ እና ቦት ጫማ አድርጎ በራፍ ላይ ቆሟል….

‹‹አይ ምንም እየገባኝ አይደለም….?››

‹‹ቁጭ በል አስረዳሀለው..››አለና ወደውስጥ ገብቶ ቀድሞት ተቀመጠ…በፀደይ  ዘሚካኤልን እየጎተተች ይዛው መጣችና አስቀመጠችው…እሷም ተቀመጠችን ስልኳን አውጥታ ሪከርድ ላይ አደረገችና ሰውዬው የሚናገረውን ለመስማት ዝግጁ ሆነች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe ቤተሰቦች ይሄን የምታነቡ ምንያህላቹ subscriber አድርጋችኋል???

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏60👍308😱4
#መሃልይ

ይኅው
ይኅው መጣች
መጣችልኝ
ይህቺት....
...
እሷ ናት
    የዝምታዬ አባራሪ
         የመዝሙሮቼ ባለቤት
እሷ ናት...
    የ ሁከቶቼ እረኛ
        የሰላሞቼ ባለቤት
እሷ ናት.....
አይኗ ውስጥ ጣት አለ
      ትጫወተኛለች
ጣቷ ውስር አይን አለ
     ታባብለኛለች
የኔ ልብ ፒያኖ
    የ'ሷ  ሙዚቀኛ
ስትጫወትብኝ
     እንቅልፍም አይወስደኝ
        ስሜቴ ሲነካ
የመጣች እንደሆን
     ዘማሪ ናት ነፍሴ
የመጣች እንደሆን
      አቀንቃኝ ነው ልቤ
ገላዬም ዳንሰኛ
ነቃ ቀና ካለ አይሆንም ዳተኛ።      ያየችኝ እንደሆን፤
     ዓይኗ ጣት ያበቅላል
የበቀለው ጣቷ
    ዓይኔ ውስጥ ይሰርጋል
የሰረገው ጣቷ
የልቤን ፒያኖ
ሲጫወተው ያድራል።
ይህን እሷ አታውቅም፤
ታአምሯን አታውቅም
እኔም አልነገርኳት፤
ምስጢሩን አላውቅም 

እየመጣች ብቻ ትጫወተኛለች
እየመጣች ብቻ
እኔ ፒያኖ ነኝ እሷ ሙዚቀኛ...

🔘እንዳለ ጊታ ከበደ🔘
😁26👍104😢2
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///

ዘሚካኤል እንግዳው ላይ አፍጥጦ

‹‹አይ ምንም እየገባኝ አይደለም….?››አለ

ሰውዬውም ዘሚካኤል‹‹ቁጭ በል አስረዳሀለው..››አለና ወደውስጥ ገብቶ ቀድሞ ተቀመጠ…

ፀደይ  ዘሚካኤልን እየጎተተች ይዛው መጣችና አስቀመጠችው…እሷም ተቀመጠችን ስልኳን አውጥታ ሪከርድ ላይ አደረገችና ሰውዬው የሚናገረውን ለመስማት ዝግጁ ሆነች፡፡

‹‹ምን ድረስ ታውቃላችሁ?››

‹‹እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም››ዘሚካኤል በትግስተ የለሽነት መለሰ፡፡

ፀደይ ዝም አለች‹‹ጥሩ ከመጀመሪያው ብጀምርላችሁ ችግር የለውም..እኔ እና እናትህ የልጅነት ጓደኛሞች ማለት ፍቅረኛሞች ነበርን…በጣም ነበር የምንዋደደው…..ምንጊዜም ስለመጋባትና ዕድሜ ዘመናችንን ሙሉ አብሮ ስለመኖር ነበር የምናስበው…ከዛ ድንገት አባቴ ወደአሜሪካ መሄድ አለብህ አለኝ…ብዙ ወንድሞቹ እዛ ስላሉ ሀሳቡን ላስቀይረው አልቻልኩም….አባቴን በጣም ነበር የምፈራው..ከዛ ጥያቄውን ተቀብዬ ወደአሜሪካ ሄድኩ…ለካ እሷ በወቅቱ እህትህን ፀንሳ ነበር..፡፡››

‹‹ፀንሳ ማለት …ከማን?››

‹‹ከማን ይሆናል ከእኔ ነዋ››

‹‹እና እህቴ የአንተ ልጅ ነች…?.ምንድነው የምትቀባጥረው?››

‹‹አልቀባጠርኩም..ከፈለክ አባትህን ጠይቀው …ያውቃል…እናትህ እኔ ጥያት ስለሄድኩ በጣም ተበሳጭታብኝ ስለነበር እና በዛ ላይ አርግዛ ስለነበር…ወዲያው አባትህን አገባችው…ስታገባው..ለልጇ አባት ለማግኘት አንጂ አፍቅራው አልነበረም…እሱም ይወዳት ስለነበረ ተንከባከባት….እህትህም በሰባት ወር እንደተወለደች ነበር ያሰበው…የገዛ ልጁ ነበር የምትመስለው….ስለዚህ ትርሲትን  እንደልጁ አሳደጋት..ከዛ አንተ እና ወንድምህ ተወለዳችሁ፡፡እኔም ከሀያ አመት ቆይታ በኃላ ከአሜሪካ ተመለስኩ፡፡ለእሷ የነበረኝ ፍቅር ከውስጤ ስላልበረደ ፈልጌ አገኘኋት…በጣም ተበሳጭታብኝ የነበረ ቢሆንም ታፈቅረኝ ስለነበረ በሂደት ይቅር አለቺኝ…አባትህን  ፈታ እኔን እንድተገባኝ እጨቀጭቃት ጀመር…እሷም ምንም እንኳን ከእኔ ጋር ለመጋባት በጣም ፍላጎት ቢኖራትም እናንተን መበተን ስላልፈለገች በሀሳቤ ልትስማማ አልቻለችም፡፡

እኔም እሷን ትቼ ሌላ ሴት ማግባት ብሞክርም አልቻልኩም..አቃተኝ…ከዛ በቃ አንቺ እሺ ብለሽ ባልሽን ፈተሸ ማታገቢኝ ከሆነ ቢያንስ ልጄን የማግኘት መብት አለኝ..ለልጄ አባቷ እኔ እንደሆንኩ ንገሪያት እያልኩ በዚህ መጨቃጨቅ ጀመርን፡፡እሷም ያንን ማድረግ አልችልም እያለች መከላከል ጀመረች፡፡በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን በድብቅ እየተገናኘን ፍቅራችንን እንወጣ ነበር…

‹‹ለምን ያህል ጊዜ ከአባቴ እየተደበቃችሁ ..እንደዛ አደረጋችሁ?››ግሽግሽ ባለና ጥላቻ በተጫነው ስሜት ጠየቀው፡፡

‹‹አራት ወይም አምስት አመት››መለሰለት

‹‹እና አባቴ ይሄን ሁሉ ታሪክ ሲያውቅ ነዋ ..ቀልቡን ነስቶት ያንን  ወንጀል የፈፀመው?››

‹‹አይ አይደለም…ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ እስከዛሬ ድረስ ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ  አዝናለው..እመነኝ በጉዳዩ በጣም መፀፀት ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገሬን አጥቼበታለው….፡፡ ስራዬን፤ ጤናዬን …ብዙ ብዙ ነገር…ብዙ ጊዜም ራሴን አጥፍቼ ከልጄ ትርሲት እና ከእናትህ ጎን ለመተኛት ሞክሬ ነበር..ግን በሆነ መንገድ እተርፋለው…መጨረሻ ይሄው እንደምታየኝ የአያቴ መንደር መጥቼ በዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ጀመርኩ..ትንሽም ወደእዚህ ከመጣሁ ነው ጤነኛ የሆንኩት››

‹‹ሰውዬ እኔ ያንተን ፀፀት ለመስማተ  ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም..ስለዋናው ጉዳይ ንገረኝ››

‹‹ትዝ ይለኛል ቀኑ እሁድ ነበር….በእለቱ አባትህ ሞጆ የጓደኛው ለቅሶ ስለነበረ መሄዱን እናትህ ስትነግረኝ..መኪናዬን ከአዲስአበባ አስነስቼ አዳማ ሄድኩ ፡፡እናትህን ተቀጣጥረን ስለነበር ቡቲክ አገኘኋት …እሁድ በዛ ላይ ጥዋት  ስለሆነ የገበያ ግር ግር አልነበረም.. ከዛ የተወሰነ ከቆየን በኃላ የተለመደ ጭቅጭቃችንን ጀመርን‹‹ …ለልጄ አባቷ መሆኔን ወይ ቀድመሽ ንገሪያት ወይ እነግራታለው››አልኳት፡፡

‹‹እሷ ቅጣውን በልዩ ሁኔታ ነው የምትወደው …አባትሽ ቅጣው አይደለም ብላት ልጄ በጣም ነው ምትጎዳው››አለቺኝ፡፡

‹‹ብትጎዳም ለጊዜው ነው…ከውሸት ጋር ለዘላለም ከምትኖር እውነቱን አውቃ ለትንሽ ጊዜ ብትጎዳ ይሻልል››አልኳት
በዚህ ጉዳይ ላይ ለ30 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በከረረ ሁኔታ ስንከራከር ቆየን….ከዛ የስልክ ንግግር ድምፅ ነው  ሁለታችንንም ያነቃን….

እህትህ ትርሲት ከባንኮኒው ማዶ … ፊቷ በእንባ ታጥቦ…አይኖቾ ፈጠውና  አውሬ መስላ ቆማለች..ሱቁ ውስጥ ገብታ እዛ የቆመችበት ቦታ መች እንደቆመች አናውቅም..ምን ያህሉን እንደሳማችንም አናውቅም….ከሁኔታዋ እንደሚታው ግን የሚበቃትን ያህል እንደሰማችን ያስታውቃል…ሁለታችንም በርግገን ጎን ለጎን ተጣብቀን ከተቀመጥንበት ተነሳን….

‹‹ለማን እየደወለች ነው?››ሁለታችንም ግራ ተጋባን፡፡ወዲያው ስልኩ ተነሳላትና ማውራት ጀመረች፡፡

‹‹አባዬ  ….ያንተ ልጅ አይደለሁም እንዴ…?እማዬና ውሽማዋ ሲያወሩ ሰማው…አባዬ እኔ ያንተ ልጅ ካልሆንኩ መኖር አልፈልግም…የሌላ ሰው ልጅ መሆን በጣም ነው የሚቀፈኝ…አይ አልጠብቅህም ..በጣም ነው የምወድህ….››አለችና ስልኩን ግድግዳው ላይ ወርውራ ከሱቁ ወጥታ ተፈተለከች፡፡ልንደረስባት ሞከርን ግን ወዲያው ተሰወረችብን፡፡

‹‹ወይኔ ልጄ….ወይኔ ልጄ…››እናትዬው ተርበተበተች....እኔም የምይዝው የምጨብጠው ግራ ገባኝ….ሱቁን ዘጋንና….

‹‹ወደየት ነው የሄደችው?››ስል እናትህን ጠየቅኳት፡፡‹‹እኔ ምናውቃለው..ወደቤት ከሄደች…ሄጄ ልያት››አለችኝ

‹‹በቃ ነይ መኪና ውስጥ ግቢ››ስላት

‹‹እንዴ ..አንድ ላይ ስንሄድ..?››

‹‹አሁን እኮ ነገሮች ተደበላልቀዋል…ምንፈራው ሳይሆን የምንጋፈጠው ነው››አልኳትና እየጎተትኩ መኪናዬ ውስጥ ይዣት ገባው፡፡በየመንገዱ እየፈለግናት…ልትሄድ ትችልበታለች ብላ እናቷ የጠረጠረችበት  አንድ ሁለት ቦታ አቁመን አይተን መጨረሻ ወደቤት ሄድን…መኪናውን ራቅ አድርጌ እንዳቆም አደረገችኝና…‹‹እኔ ገብቼ ልያትና ካለች እነግርሀለው..ከሌለችም ሌላ ቦታ ሄደን እንፈልጋታለን›› ብላኝ ገባች፡፡እኔም በጭንቀት እየተንቆራጠጥኩ መጠበቅ ጀመርኩ…5 ደቂቃ ..10 ደቂቃ አለፈ..ስልኬን አውጥቼ ስደውል እናትህ ሞባይል አይነሳም…ራሴን መቆጣጠር አቃተኝና የሆነው ይሁን ብዬ ወደግቢው ገባው፡፡ሳሎኑ በራፍ እንደተከፈተ ነበር…ስገባ  ልጄ ኮርኒሱ ላይ ተንጠልጥላለች..እናትህ ደግሞ የገዛ ሆዷን ላይ ቢላዋ ሽጣ ተዘርራለች፡፡ይመስለኛል እናትህ ወደቤት ስትገባ እህትህ ተሰቅላ እራሷ አጥፍታ ስታያት ወዲያው አካባቢው ላይ ያገኘችውን ቢላዋ ሆዷ ውሰጥ የሻጠችው ይመስለኛል፡፡

ከዛ ደንዝዤ የምሆነው ጠፋኝ…ምን ላድርግ ..?ልጄን ከተሰቀለችበት ለማውረድ ገመድ መቁረጫ ለመፈለግ ወደውስጥ ገብቼ መቁረጫ ይዤ ስመለስ አባትህ ከውጭ ከሳሎኑ ሲገባ አየሁት፡፡በደመነፍስ ወደ ጎሮ በራፍ ሄድኩ…ዞሬ ከግቢው ወጣሁና መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ደም እንባ እያለቀስኩ ሁኔታዎችን መከታተል ጀምርኩ፡፡ ከዛ አንተና ወንድምህ አንድ አይነት ሰማያዊ የስፖርት ልብስ ለብሳችሁ ወደቤት ስትገቡ ተመለከትኩ፡፡ ከደቂቃዎች በኃላ ፖሊሶች ሰፈሩን ወረሩት…እናንተንም አባታችሁንም ፖሊሶች ይዘዋችሁ ሲሄድ የእናትህንና የእህትህን አስከሬን በአንብላንስ ሲወሰድ ከመንገድ ማዶ መኪናዬ ውስጥ ተቀምጬ እየተመለከትኩ ነበር፡፡ ሁለቱም እራሷቸውን  እንዳጠፉ እርግጠኛ ነኝ፡፡
👍6415
እና በጣም የማስጠላ ፈሪ ሰው ነኝ አይደል…በወቅቱ  ትልቅ ስልጣን ላይ ነበርኩ..ከዚህ ወንጀል ጋር ስሜ ቢያያዝ ምንድነው የሚገጥመኝ? ብዬ ፈራው…አባትህ እንደገደለ ሲያምን ..የሞት ፍርድ ሲፈረድበት ሁሉ ዝም ብዬ ተመለከትኩ…ከሰውዬው አይኖች እንባ እየረገፈ ነው፡፡‹‹እና ምን መሰለህ….››ዶ/ሩ የዘሚካኤልን መቀያየር ሲመለከት ንግግሩን አቆመ፡፡

ዘሚካኤል ወደኃላው ክንብል ብሎ ወደቀ…ፀአዳ እና ዶክተሩ በድንጋጤ ተባብረው አነሱትና  አልጋ ላይ አስተኝተው ውሀ በተነከረ ጨርቅ ጭንቅላቱንና ልቡን ያቀዘቅዙለት ጀመረ….ቀስ በቀስ ከገባበት ጭልጥ ያለ ሰመመን እየነቃ መጣ…ራሱን በደንብ ሲያውቅ በመጀመሪያ ያደረገው ነገር…ከተኛበት ተስፍንጥሮ በመነሳት የሰውዬውን አንገት አንቆ በቴስታ መነረት ነበር…..

ከአንድ ሰዓት  በኃላ ፀአዳና ዘሚካኤል ወደአዲስ አበባ የመልስ ጉዞ ለማድረግ በተከራዩት የቻርተር አውሮፕላን ውስጥ ገብተው ፓይለቱ የአውሮፕላኗን ሞተር አስነስቶ አየር ላይ አስኪሰቅላት ድረስ እየተጠባበቁ ነው…ዘሚካኤል አሁን ድረስ በድኑ ነው ያለው….እንደጣኦት ያመልካትና ይወዳት የነበረችው እናቱ እንደዛ አይነት ሰው መሆኗን ሲያውቅ ከመሸማቀቁ የተነሳ የሚደበቅበት ጥጋት ነው ያጣው….በእናቱ ከመመካቱ የተነሳ ሀጥያተኛና  ጨካኝ ነው ብሎ የሚያስበውን  የአባቱን ስም ከስሙ ቀጥሎ መጠራቱን ተጠይፎ  እንዲፋቅ በማደረግ የእናቱ ስም እንደአባት አድርጎ መጠቀም ከጀመረ አመታት አልፎታል፡፡

ምንም ጥፋት የሌለበትን እና የዚህ ሁሉ በደል ዋና ተጠቂ የሆነው አባቱን በዛን ወቅት ሊገድለው ሁሉ ነበር… ከዛ በኋላም ወንድሙንና አባቱን ሲጠየፍና ሲራገም ነው የኖረው..‹‹ አሁን እኔ ምን አይነት ፍጡር ነኝ?››ሲል እራሱን ተጠየፈው፡፡‹‹እንዴት የወንድሜን ያህል ማስተዋልና መረጋጋት ያቅተኛል…?››ለራሱ ያለው ግምት ወረደበት፡፡

ፀአዳ ….ሚካኤልና  አዲስ አለም በየተራ እየደወሉ እያጨናነቋት ነው….አንስታ ምን እንደምትላቸው ስላልገባት ለማንሳት አልደፈረችም….ከዛ ይልቅ አሁን ወደ አዲስአበባ ሊመለሱ ሄሊኮፍረተር ውስጥ መግባታቸውና እና ስልኩን ማናገር እንደማትችል ገልጻ
ከዶ/ር ጋር ያደረጉትን ውይይት የሰውዬውን ንዛዜ የመሰለ አስገራሚ ትያትራዊ  ገለፃ በቴሌግራም ለሚካኤል ላከችለትና ስልኳን ዘጋችው፡፡

‹‹ፀዲ …እኔን እንዳትወጂኝ እሺ……የማንም ሰው ፍቅር አይገባኝም››አላት እየነፈረቀ፡፡

ወደእሱ ይበልጥ ተጠጋችና.. አቀፈችው፡፡እየነፈረቀ ንግግሩን ቀጠለ‹‹እኔ ሁል ጊዜ ከእኔ ለመሸሽ ስትሞክሪና እንድተውሽ ስትጨቀጭቂኝ…ይህቺ ልጅ ያማታል እንዴ? እንዴት  ጨክና  እኔን የመሰለ ሰው አልፈልግም ልትል ቻለች ? ››እያልኩ  እገረም ነበር..ለካ አንቺ ብልህ ስለሆንሽ ደካማነቴና እንጭጭ የሆነ አስተሳሰቤን በግልፅ ስላወቅሽ እንደማልመጥንሽ ተረድተሸ ነው፡፡›

‹‹አረ አንተ ሰው  ምኑን ከምን እያገናኘህ ነው….?እባክህ የእኔ ቆንጆ ራስህን አታሰቃይ..የሆነው ሁሉ ሆኗል….ይልቅ ራስህን አረጋጋና በቀጣይ የሚስተካከሉ ነገሮችን ማስተካከሉ ላይ ትኩረት ማድረግ ነው››

‹‹አልገባሽም እንዴ..?ምንም የሚስተካከል ነገር የለም….ይሄንን ዜና ወንድሜ ካወቀ በኃላ እንዴት እንደሚጠየፈኝ አስበሽዋል..?አባቴንማ ተይው ይሄኔ  ልጁ መሆኔንም ዘንግቷል..››

‹‹አይ …ይሄንን ጉዳይ እንድናጣራ እኮ ፍንጩን ለሚኪ የሰጡት አባትህ ናቸው…. ምክንያታቸው ደግሞ ከመሞቴ በፊት ልጄ እንደጠላኝ መሞት አልፈልግም…..ከመሞቴ በፊት እውነቱን አውቆ አንዴ አይኑን አይቼውና አቅፌው ልሰናበተው እፈልጋለው…ብለው ነው፡፡አንተን ለማግኘት ስለሚፈልጉ ነው፡፡››

‹‹ተይ ፀዲ.. አኔን ለማፅናናት ብለሽ ነው፡፡››

‹‹አይደለም…እውነቴን ነው…ለማንኛውም አሁን ሁሉንም ረስተህ ለመረጋጋት ሞክር፡፡››ስትለው የሂሊኮፕተሯ ሞተር መንኳኳት ጀመረ፡፡
///
ዘሚካኤል አፓርታማ ሲደርሱ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡አሳንሱሩን ተጠቅመው ወደላይ ወጡ…ሲደርሱ በራፉ ክፍት ነው፡፡መጥሪያውን ተጭነው ሲከፈት አዲስ አለም ሚካኤልና ቅድስ እየጠበቋቸው ነበር….ሁሉም ዘሚካኤል ላይ ተጠመጠሙበት…ሁለቱ ወንድማማቾች ለመላቀቅ በርካታ ደቂቃዎች ወሰደባቸው…ህፃኑ ቅዱስ ተጨንቆ እስኪያለቅስ ሁሉም እየተንሰቀሰቁ ተላቀሱ…ቤቱ አዲስ ሬሳ የወጣበት ቤት ነው የመሰለው፡፡
///
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አዲስ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ አንተስ?››

‹‹እኔ በጣም ደህና ነኝ…ሚካኤል ይደውልልኛል ብዬ እየጠበቅኩ ነበር፡፡››

‹‹ይደውልልሀል..አሁን ኩማንደሩ ቀጥሮት ሊያገኘው ሄዶል …ከእሱ እንደጨረሰ እርግጠኛ ነኝ ይደውልልሀል፡፡…አታስብ ኩማንደሩ ደግሞ ያንተ አድናቂ ስለሆነ ከአባታችሁ እንድትገናኙ ሁኔታውን ያመቻቻል….በዛ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው

‹‹ጥሩ ታዲያ አንቺ ሰላም ነሽ?››

‹‹በጣም ሰላም ነኝ…ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ  ነበር››

‹‹ምን?››

‹‹ከፀዲ ጋር እንዴት ናችሁ?››

ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኃላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››

‹‹ግልፅ ሆነህ ንገረኝ…ስለእሷ ምን ታስባለህ..ማለቴ አሁንም በፊት እንደነገርከኝ ታፈቅራታለህ?››

‹‹እንዴ!እንዴት በአንድ ወር ፍቅሩ ይተናል ብለሽ አሰብሽ? እንደውም ጥሩ ነገር አነሳሽልኝ…የሆነ ቀን አመቻችቼ ካንቺ ጋር መነጋገር እፈልግ ነበር..እኔ ላገባት እፍልጋለው..በቅርብ ቀን..እና እንዴት ጠይቄ ላሳምናት የሚለውን ከእኔ ይልቅ አንቺ ስለምታውቂ እንድታማክሪኝ እፈልጋለው፡፡››

‹‹እንግዲያው እንደዛ ከሆነ ሳይረፍድብህ ፍጠን››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ያንተን ልጅ አርግዛለች..››
የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››

‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል  ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ  ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል  ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡

መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኃላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››

‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡

የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ  መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe ቤተሰቦች ይሄን የምታነቡ ምንያህላቹ subscriber አድርጋችኋል???

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍13217👏3
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡

የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አዲስ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ አንተስ?››

‹‹እኔ በጣም ደህና ነኝ…ሚካኤል ይደውልልኛል ብዬ እየጠበቅኩ ነበር፡፡››

‹‹ይደውልልሀል..አሁን ኩማንደሩ ቀጥሮት ሊያገኘው ሄዶል …ከእሱ እንደጨረሰ እርግጠኛ ነኝ ይደውልልሀል፡፡…አታስብ ኩማንደሩ ደግሞ ያንተ አድናቂ ስለሆነ ከአባታችሁ እንድትገናኙ ሁኔታውን ያመቻቻል….በዛ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው

‹‹ጥሩ ታዲያ አንቺ ሰላም ነሽ?››

‹‹በጣም ሰላም ነኝ…ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ  ነበር››

‹‹ምን?››

‹‹ከፀዲ ጋር እንዴት ናችሁ?››

ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኋላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡

ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››

‹‹ግልፅ ሆነህ ንገረኝ…ስለእሷ ምን ታስባለህ..ማለቴ አሁንም በፊት እንደነገርከኝ ታፈቅራታለህ?››

‹‹እንዴ!እንዴት በአንድ ወር ፍቅሩ ይተናል ብለሽ አሰብሽ? እንደውም ጥሩ ነገር አነሳሽልኝ…የሆነ ቀን አመቻችቼ ካንቺ ጋር መነጋገር እፈልግ ነበር..እኔ ላገባት እፍልጋለው..በቅርብ ቀን..እና እንዴት ጠይቄ ላሳምናት የሚለውን ከእኔ ይልቅ አንቺ ስለምታውቂ እንድታማክሪኝ እፈልጋለው፡፡››

‹‹እንግዲያው እንደዛ ከሆነ ሳይረፍድብህ ፍጠን››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ያንተን ልጅ አርግዛለች..››

የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…

‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››

‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡

በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል  ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ  ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል  ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኋላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››

‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በበቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡

የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ  መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡

ፀአዳ ቤት ሲደርስ በራፏ ዝግ ነበር..ሊደውልላት አልፈለገም ፡፡ሻንጣውን አወረደና በራፏ በረንዳ ላይ አድርጎ እሱ መኪናው ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ጀመረ…ከምሽቱ አንድ ሰአት ስትመጣ እሱ መኪና ውስጥ ሻንጣው በረንዳ ላይ ሆኖ ስታየው ፍፁም ነው ግራ የተጋባችው…ምስር  እሱ መሆኑን ስታውቅ ከእናቷ ተነጥላ ወደእሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ፈጥኖ ከመኪናው ወረደና እጇቹን እንደክንፍ ዘርግቶ ጠበቃት…ተጠምጥማበት በደስታ ጉንጩን ትስመው ጀመር…
ወደቤት እንደገቡ ፀደይ‹‹ምንድነው ጉዱ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምንም ..ለጥቂት ሳምንታት እረፍት ስለሆንኩ እዚህ ከእናንተ ጋር ለመቆየት ወስኜ ነው፡፡››

‹‹እዚህ ከእኛ ጋር?››

‹‹አዎ ከእናንተ ጋር››
ህፃኖ ምስር ‹‹ታድለን…ታድለን›› እያለች መጨፈር ጀመረች፡፡

ፀአዳ ልጇ ምስር ፊት ምንም ማለት አልቻለችም.‹‹እንግዲያው እደቤትህ ዘና በል…እኔ ልብስ ልቀይር ››አለችና መኝታ ቤት ገባች፡፡ከዛ እራት ሰርታ በሉና ከሶስት ሰዓት በኃላ ምስርን አስተኝተው ነበር እንደአዲስ ጭቅጭቁን የጀመሩት፡፡

‹‹ምን እየሰራህ ነው?››

‹‹እንደምታገቢኝ ቃል ገብተሸ ቀለበት እስክታስሪልኝ ድረስ ከዚህ ቤት ወጥቼ ወደቤቴ አልመለስም››ሲል ቁርጡን ፍርጥም ብሎ ነገራት፡

‹‹ጭራሽ ማግባት? እየቀለድክ ነው፡፡››

‹‹በፍፅም …ብቀልድ ነው እንደዚህ አይነት እርምጃ የወሰድኩት፡፡››

‹‹ስማ..እኔ ካንተ ጋብቻ ፍቅር ምናምን አልፈልግም››

‹‹ታዲያ ምንድንው ምትፈልጊው?››

ትኩር ብላ አየችው….
‹‹ንገሪኝ ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው….. ?››

‹‹ካንተ ወሲብ ብቻ ይበቃኛል….ማለቴ እስከአሁን የደረግነውን ለማለት ነው …ደግሞ  አሁንም እናድረግ እያልኩህ አይደለም፡፡››

በንግግሯ ሆድን እስኪያመው ሳቀ…በመሀል ስልክ ተደወለለት ..ከወንድሙ ነበር…በጉጉት አነሳው‹‹እሺ ሚካኤል ደህና አመሸህ?››

‹‹ሰላም ነኝ…ነገ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ አዳማ መገኘት ትችላለህ?››

‹‹ምነው ?አባዬን እንድናገኝ ፈቀዱልን እንዴ?››

‹‹አዎ በጣም ደስ የሚለው ደግሞ አንድ ላይ እንድናገኘው ነው ያመቻቹልን ቅር ካላለህ አዲስንና ቅዱስንም ይዘናቸው እንሄዳለን››

‹‹አረ ቅር አይለኝም ጥሩ ሀሳብ …ግን አባዬ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ የሚሆን ይመስልሀል?››ሰሞኑን ሲብሰለሰልበት የነበረውን ስጋቱን አንስቶ ጠየቀው፡፡

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከመሞቱ በፊት ማግኘት የሚፈልገው ብቸኛ ነገር እኮ አንተን ማናገር ነው…በደስታ  ነው የሚያነባው….እንኳን በአካል አግኝተሀው አባዬ ብለህ ስጠራው ሰምቶ ይቅርና ባለፈው ፎቶህን ሳሳየው እንዴት እያገላበጠ ሲስምና ሲያለቅስ እንደነበረ እኔ ነኝ የማውቀው…በል በዛ እርግጠኛ ሁን..ምንም አትጨናነቅ፡፡››

‹‹ምን ያስፈልገዋል…?ማለት ምን ይዤለት ልሂድ?››

‹‹የሚያስፈልገወን ነገር ሁሉ አዘጋጅተናል…አንተ ደግሞ ሚፈልገውን ነገር እንጠይቀውና በሚቀጥለው ዙር ትወስድለታለህ…ደግሞ ደስ የሚለው ከቦንጋ ያመጣችሁትን ከዶ/ሩ ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ለኩማንደሩ አሰምቼው በጣም ነው ያዘነው..እናም አባዬን ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር ወስነዋል…››

‹‹በጣም የሚያስደስት ነገር ነው እየነገርከኝ ያለሀው..ወንድሜ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንክ ታውቃለህ አይደል… በጣም ነው የምኮራብህ፡፡››

ሚካኤልም እንባ እየተናነቀው‹‹እኔም በጣም ነው የምኮራብህ››አለው

‹‹በቃ እሺ …...ሶስት ሰዓት ነው ያልከኝ አይደል?፡፡››

‹‹አዎ…መድረስ ትችላለህ አይደል…?››

‹‹በደንብ እንጂ ሁለት ተኩል ደርሼ ደውልልሀለው››

‹‹ጥሩ በቃ ደህና እደር››ስልኩን ዘጋ፡፡

ንግግራቸውን ሁሉ በገረሜታ ስትሰማ የነበረችው ፀደይ‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ሁለት ተኩል ትደርሳለህ?››ስትል በፈገግታ አሾፈችበት፡፡

‹‹ትቆጪኛለሽ ብዬ ነው እንጂ እዚህ ነኝ ልለው ነበረ››

‹‹ልፋ ቢልህ ነው ….ግን ለእናንተ ደስ ብሎኛል››

‹‹ማለት?››

‹‹አንተና ወንድምህ እንዲህ እየተደዋወላችሁ በሰላም ማውራት መቻላችሁ ትልቅ ነገር ነው…አረ እንደውም ከመነጋጋርም አልፋችሁ መሞጋገስ ጀምራችኃል››

‹‹እድሜ ለአንቺ ….ባንቺ ቀናነትና ጥረት ነው ለዚህ የበቃነው….››

‹‹እኔን ማሞገሱን እንኳን ለሌላ ጊዜ አቆየው..በነገራችን ላይ የአባትህ ጉዳይ ላይ  ይግባኝ ለመጠየቅ ሚቻል ከአሆነ አንድ ጎበዝ ጠበቃ አግኝኝቼ ሁኔታውን አስረድቼው ነበር….››

‹‹በእውነት ..ታዲያ ምን አለሽ?››
👍6721👎1👏1
‹‹ምንም ነገር ከማለቴ በፊት ዶ/ር ለሜቻን ማናገር አለብኝ..አለኝ..እስኪ የሚቻል ከሆነ  በስልክ ላገናኛቸው አስቤለው…ቆይ አንደውም እስኪ ልደውልና ላናግረው››

‹‹ማንን ጠበቃውን..?››

‹‹አይ ዶክተሩን››አለችና ስልኳን አንስታ ቦንጋ የሚገኘው ደ/ር ለሜቻ ቁጥር ላይ ደወለች  ፡፡

ከበርካታ ጥሪዎች በኃላ ሰልችቷት ልትዘጋው ስትል ተነሳ‹‹ሄሎ…ፀደይ ነኝ..ባለፈው… ››

‹‹አውቄሻለው….ወንድሙ ነኝ››የሚል መልስ አገኘች፡፡

‹‹እሺ በምሽት ስለደወልኩ ይቅርታ››

‹‹ምንም አይደል?››የደከመ እና የቀዘቀዘ ድምፅ ነው እየሰማች ያለችው፡፡

‹‹አውቀኸኛል አይደል?››

‹‹አዎ አውቄሻለው… የዘፋኙ ጓደኛ አይደለሽ?››

‹‹አዎ ነኝ..ዶ/ርን ለማናገር ፈልጌ ነበር…ከልተኙ ልታገናኘን ትችላለህ…ለብርቱ ጉዳይ ነው የምፈልጋቸው፡፡››

‹‹አዝናለው አልችልም››

‹‹ችግር የለውም በቃ…ነገ ጥዋት መልሼ ደውላለው…እንደደወልኩ ነገርልኝ››

‹‹አልችልም አልኩሽ እኮ››ፀደይ ድግገርግር አላት

‹‹ማለት…ምን ችግር አለው?››

‹‹ወንድሜ ከሶስት ቀን በፊት እራሱን አጥፍቶል…ዛሬ ቀብሩ ነበር››ሲል ሳግ በተናነቀው ድምፅ አረዳት….ፀደይ ስልኩ ከእጇ ተንሸራቶ ወለሉ ላይ ወደቀ…
ሁኔታዋን በንቃት ሲከታተል የነበረው ዘሚካኤል ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ ተነሳና ስሯ ደርሶ ትከሻዋን እየነካካ ምን እንደተፈጠረ ይጠይቃት ጀመር‹‹ዶ/ሩ እራሱን አጥፍቶ እንደሞተ ነው የነገረኝ››ስትል ነገረችው፡፡

ቀስ አለና አጠገቡ የሚገኝ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ አለ…ይዘን ወይስ ይደሰት ግራ ገባው…እንኳን ሞተም ወይም ነፍስ ይማርም ማለት አልቻለም፡፡

ፀደይ ግን በጣም ነው የደነገጠችው…እንባዋ እስኪረግፍ ድረስ ነው ያዘነችው‹‹ደህና እያገገመ የነበረውን ሰውዬ የተደበቀበት ዋሻ ድረስ ሄደን ቁስሉን ነካካንበትና ለሞት ዳረግነው››ስትል ተፀፀተች፡፡‹‹ለምንድነው ግን አንተ ፍፅም መልካም ነገር ለመስራት በተንቀሳቀስ ቁጥር ሳታውቀው መጥፎ ነገር እንድትሰራ የምትገደደው?››ጥያቄው ለራሷ ይሁን ወይስ ለዘሚካኤል አይታወቅም፡፡

እሱ ግን  የመሰለውን መመለስ ጀመረ‹‹ለዛ እኮ ነው የማይሳሳተው የማይሰራ ሰው ብቻ ነው የሚባለው..በእንቅስቃሴ ላይ ካለሽ የግድ መልካሙንም መጥፎውንም ነገር መስራትሽ አይቀርም…ዋናው ልዩነት አንድ ነገር ስትሰሪ ኢንቴንሽንሽ ምንድነው የሚለው ነው…?በመንገድሽ ላይ ክፍ ተግባራትን ላለመስራት ምን ያህል ተጠንቅቀሻል ?..ግን ደግሞ ምንም ብትጥሪ ከቁጥጥርሽ ውጭ በሆነ መንገድ የማትፈልጊው ነገር መፈጠሩ አይቀርም፡፡››

ከሰውዬው ሀዘን ለማገገም ከአንድ ሰዓት በላይ ወሰደባቸው…አምስት  ሰዓት ሆነ….‹‹በል አሁን እንተኛ..መቼስ ድንገት ነው የመጣሀው እንደምታየው ያለን አንድ መኝታ ቤት ብቻ ነው››አለችው፡፡

‹‹ችግር የለውም …ምለብሰው ልብስ ብቻ ስጪኝ፣ እዚሁ ሶፋ ላይ እተኛለው››አላት፡፡ያልጠበቀችው መልስ ነበር፡፡ብቻዬን ልታስተኚኝ…ምናምን ››ብሎ ይቀውጠዋል ብላ አስባ ነበር፡፡እሱ ግን ምንም አልተቃወማትም..ጭራሽ መጀመሪያውኑ  ከእሷ ጋ ለመተኛት ያሰበ አይመስልም፡፡

‹‹ለምን ከምስር ጋር መኝታ ቤት ገብተህ አትተኛም….እኔ እዚህ…›› አላስጨረሳትም.

‹‹.አይሆንም አልኩሽ እኮ…!!››
ተነሳችና ሚለብሰው ልብስ አምጥታ አስተካከለችለትና ግንባሩን ስማ ወደመኝታ ቤቷ ሄዳች…እጄን ይዞ ጎትቶ ይስመኛል ብላ አስባ ነበር..ግን አላደረገውም….በመገረም ተሞልታ ከልጆ ጎን ተኛችና ስለገጠማት ነገር ማሰላሰል ጀመረች፡፡

‹‹እሺ አሁን ምን ላደርግ ነው?››እራሷን በጥያቄ አስጨነቀች‹‹ምን አደርጋለው…በእቅዴ መሰረት ነው የምሄደው…..ፅንሱን አስወርዳዋለው…ስለዚህ ጉዳይ ማንም እንዲያውቅ አላደርግም..ከዛ ቀስ ብዬ በዘዴ ሻንጣውን ሸክፎ እንደመጣ ሸንጣውን ሸክፎ ወደቤቱ እንዲመለስ አደርገዋለው….››ብላ ወሰነች፡፡

በዚህ ጊዜ ዘሚካኤም እንዴት ከዚህ በላይ እንደሚያጠምዳትና በራሷ ላይም ሆነ በፀነስችው ፅንስ ላይ ምንም እንዳታደርግ ማድረግ እንደሚችል እያሰበ ነው፡፡ሳሎን ተኝቶ መኝታ ቤት ሆና የምትተነፍሰው የእሷ ትንፋሽ የሚሰማው መስሎ እየተሳማው ነው…ሹክክ ብሎ ሄዶ የመኝታ ቤቱን በራፍ ከፍቶ ጉያዋ ውስጥ ተወሽቆ ትንፋሿን ቢሞቅ በጣም ደስ ይለው ነበር…ግን እሷን ለወሲብ ብቻ ሳይሆን ለፍቅርና ለጋብቻ ጭምር እንደሚፈልጋት በተግባር ማሳየት አለበት..ለዛ ደግሞ ይሄ  አንዱ አጋጣሚ ነው፡፡
ስልኩን አነሳና  መልእክት በመፃፍ ከፎቶ ጋር ለሚያውቃቸው ሶስት ጋዜጠኞች በመላክ ተከናንቦ ለመተኛት ሞከረ፡፡

ጥዋት አስራሁለት ሰዓት ተኩል ነው የባነነው፡፡ሶፋውን ለቀቀና ሳሎኑ ውስጥ እየተዘዋረ ሰውነቱን ሲያፍታታ  ከወደኪችን ድምፅ ሰማ ..ቀስ ብሎ ተጠጋና ‹‹ፀዲ››ሲል ተጣራ፡፡

በበራፉ ብቅ አለችና‹‹እንዴ !!ቀሰቀስኩህ እንዴ?››

‹‹አይ በራሴ ነው የተነሳሁት… የተኛሽ እኮ ነው የመሰለኝ፡፡››
‹‹እንዴ የልጅ እናት እኮ ነኝ…ልጄን ቁርስ አብልቼ የምሳ ዕቃዎን ቆጥሬ ወደትምህርት ቤት መላክ አለብኝ..በዛ ላይ ችኮ የሆነ እንግዳ አለብኝ››
‹‹አንቺ እኔ ችኮ…ብሎ ሊይዛት ወደእሷ ሲንደረደር ተፈናጥራ ወደውስጥ ገባች…ተከትሎት ገባ…‹‹አንተ እረፍ ….ምግቡን እንዳታስደፋኝ፡፡››ከኃላ አቀፈና አንገቷን ሳማት…ከንፈሩ እዛው አንገቷ ላይ ተጣብቆ እንዲቆይ ተመኘች…. ግን ‹‹እማዬ ..እማዬ›› ብሎ የሚጣራውን የምስርን ድምፅ ሲሰሙ ሁለቱም በፍጥነት ተላቀቁ….
…..
አንድ ሰዓት ተኩል ሲሆን ምስርን አብረው ወጥተው ሰርቢሶ ድረስ ሸኞትና  ወደቤት ተመለሱ…ቁርስ አቀረበችና  እየተጎራረሱ መብላት ጀመሩ‹‹ቆይ ስራ የለህም እንዴ?››

‹‹ለአንድ ወር ምንም ስራ ላለመስራት አመቻችቼለው…ያሉኝን የስራ ቀጠሮዎች ሁሉ ሰርዣለው፡፡

ተስፋ ቆረጠች…‹‹ጥሩ ነው…ግን ያው እዚህ እንደምታየው ምንም አይመችህም..ቤታችን ጠባብ ነው..አንድ ምኝታ ቤት ብቻ ነው ያለን…..አባትህን ካየህ በኃላ ቆንጆ ምሳ ጋብዝህና ከዛ ወደ አዲስ አበባ እሸኝሀለው፡፡ባይሆን ቅዳሜ እመጣና አንተ ጋር አድራለው››

‹‹አይ …አታስቢ…ሶፋ ላይ መተኛት እንደዚህ እንደሚመች አላውቅም ነበር……በጣም ተመችቶኛል….ደግሞ ትዳር መስዋዕትነት ይጠይቃል….አንቺ ካለሽ እንኳን እንደዚህ አይነት ቤት ገጠር ጎጆ ቤት ውስጥም ቢሆን ይመቸኛል፡፡››

ከእሱ ጋር መከራከር ልብ የሚያቆስል ተግባር ሆኖ ነው ያገኘችው….በቀጣይ ምን  ብዬ ልመልስለት ብላ ስታስብ ስልኳ ጠራ…እሷ ጋር ምትሰራ ልጅ ነች፡፡የስራ ጉዳይ ነው ብላ ችላ አለችው፡፡ደግሞ ተደወለ..አነሳችው፡፡

‹‹ፀዲ እንኳን ደስ ያለሽ››
ግራ ተጋባች‹‹ለምኑ?››

‹‹ምን አገር ምድሩ የሰማውን ነገር እኔን እንዴት ትደብቂኛለሽ?››

‹‹ምኑን ነው የምደብቅሽ?››

‹‹ለማንኛውም..ለባሉም ለልጁም እንኳን ደስ ያለሽ..ግን ድል ያለ ድግስ እፈልጋለን››

ስልኩን ጠረቀመችባት…..ዘሚካኤልን አፍጥጣ አየችው….እሱ እየሆነ የለው ነገር ስለገባው ብዙም አልተደናገጠም….ወዲያው መልሶ ስልኳ ጠራ…ሌላ የምታውቃት ሴት ነች…አነሳችው፡፡

ሰላምም ሳትላት ቀጥታ ወደጉዳዩ ገባች‹‹አንቺ …ያንን የመሰለ አርቲስት አፈሺው አይደል….?አንኳንም ደስ ያለሽ….ሰርጉን እንዳትረሺን››

‹‹ምንድነው ?የምን ሰርግ››

‹‹እንዴ ዪቲዩብና ፌስ ብክ ጠቅላላ በአንቺና በእጮኛሽ ፎቶ ተጥለቅልቆ የለ እንዴ››ስልኩን ጠረቀመችና ፌስ ብኩ ከፈተች..፡፡
👍5814😢2
ታዋቂው ዘፋኝና የፊልም አክተር ዘሚካኤል በመጨረሻ ሊያገባ እንደሆነ ተናገረ፡፡
ይህቺ በምስሉ ላይ የምትታየው የአዳማ ልጅ በጠም እንዳፈቀራትና በቅርብ ሊጋቡ እንደሆነ …እንደፀነሰችለት ሲያውቅ በደስታ  ሻንጣውን ሸክፎ እቤቷ እንደገባና በቅርብ ከተጋቡ በኋላ ተነጋግረው ኑሮቸውን ወደአዲስአበባ እንደሚያዘዋውሩ ይገልጻል…ከፅሁፉ ጋር የተያያዘው ፎቶ ቦንጋ በሄዱ ጊዜ ተቃቅፈው እየተሳሳሙ እንደቀልድ የተነሱት ፎቶ ነው፡፡

እየተረተረች ስታይ…..ማህበራዊ ሚዲያውን ጠቅላላ አደበላለቆታል፡፡የዜናው ምንጭ የራሱ የገዛ የፌስ ቡክና የኢንስታግራም ገፅ ነው፡፡

‹‹ምንድነው ይሄ…?አንተ እንደዚህ ብለሀል እንዴ..?ብላ ስልኳን አቀበለችው..ተቀብሎ አየት አደረገና .‹‹.አዎ…››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹የምን ልጅ ነው?››

‹‹አረባክሽ….?››

ከመበሳጨቷ የተነሳ መናገር አንኳን አቃታት‹‹ግን የእውነት አእምሮ ጤነኛ ነው….ሁል ጊዜ ለምን እራስህን ብቻ ታዳምጣለህ…?ይሄንን ነገር ለማድረግ ከማሰብህ በፊት እሷስ ምን ታስባለች…..?ብለህ አታስብም፡፡››

‹‹አንቺስ ልጄን ለማስወረድ ከመነሳትሽ በፊት ስለዚህ ጉዳይ እሱስ መስማት የለበትም ወይ…?ብለሽ አታስቢም፡፡››

‹‹እና በቀል መሆኑ ነው…?››

‹‹አይ በቀል ሳይሆን ነገሮችን ወደትክክለኛ መስመር እንዲገቡ እያስተካከልኩ ነው፡፡በነገራችን ላይ  በሚቀጥለው ሳምንት ወደቤተሰቦችሽ የምልካቸውን ሽማግሌዎች አዘጋጅቼለው..ድንገት እንዳይሆንባቸው አሁኑኑ ደውለሽ ለወላጆችሽ ንገሪያቸው፡፡››
ከተቀመጠችበት ተነሳች…መልሳ ቁጭ አለች…ከንደገና ተነሳች‹‹ይሄውልህ ምን አይነት ክፉ ሰው ያልሆነ ነገር ነግሮህ እንዳሳሳተህ አላውቅም..እኔ ምንም ልጅ አልፀነስኩም…ልጅ ሚባል በማህፀኔ የለም››

‹‹እሺ ቀላል ነው..››ኪሱ ገባና የእርግዝና መመርመሪያ አውጥቶ ጠረጴዛ ላይ አደረገና›› በቃ መሳሳቴን አሳምኚኝ… አይኔ እያየ ያው ተጠቀሚና አለማርገዝሽን አሳይኝ፡፡››

‹‹አላደርገውም….››መመርመሪያውን አነሳችና ሰባብራ ወደውጭ ወረወረች..ተንከትክቶ ሳቀ…‹‹አየሽ  እኔ አልተሳሳትኩም…..ልጄን ምንም ነገር ማድረግ አትቺይም…ታፈቅሪኛለሽ አፈቅርሻለው..እናም እንጋባለን››

‹‹እኔ ካንተ ፍቅር አልፈልግም አልኩህ…..››

‹‹እና…››

..ልትመልስለት አፏን ስትከፍት የዘሚካኤል ስልክ ጠራ….ስልኩን አነሳው፡፡

‹‹ደህና አደርክ ወንድሜ?››

‹‹ደህና  ነኝ..ደረስክ እንዴ?››

ደርሼለው…..ሰአት ገና ስለሆነ ፀዲ ጋር ጎራ አልኩ..እኔም ከእናንተ ጋር እሄዳለው እያለችኝ ነው››

‹‹በጣም ጥሩ እኔም እንደዛ አስቤ ልደውልላት ነበር……እና አሁን የት ናችሁ?፡፡››

‹‹እሷ ቤት››

በቃ አዲስንና ቅዱስን ይዣ  እመጣለው..እዛ ጠብቁኝ.. ከ30 ደቂቃ በኃላ እደርሳለው…ሁላችንም ተያይዘን እንሄዳለን፡፡

ፀደይ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጋ ሶፋው ላይ ሄዳ ተቀመጠች፡፡

‹‹ሰማሽ አይደል..ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ ብሎል….አንቺም መገኘት አለብሽ…ይልፋትሽን ውጤት ማየት ይገባሻል….በዛ ላይ አባቴ ምራቱንና የወደፊት የልጅ ልጁንም መተዋወቅ አለበት፡፡

‹‹በጣም ሟዛዛ ሰው ነህ ..ታውቃለህ አይደል?፡፡››

‹‹አዎ አውቃለው..››አለና ከጎኗ ተቀመጠ…ፈራ ተባ እያለ ወደራሱ ጎትቶ ደረቱ ላይ ለጠፋት..እጅ በመስጠት መንፈስ  ቀና ብላ አይን አይኑን ማየት ጀመረች፡፡ወደታች ዝቅ አለና ከንፈሯ ላይ ተጣበቀ…..እጇቾን በአንገቱ ዙሪያ ጠመጠመች….ከተቀመጠችበት ተነሳችና እላዩ ላይ ተቀመጠችበት…..የለበሰችውን ልብስ ማውለቅ ጀመረ…ሁለቱም ያለቻቸውን ጥቂት ደቂቃ በጥድፊያ ሊጠቀሙባት የቸኮሉ ይመስላሉ….እርስ በርስ እንደተቃቀፉ ወለሉ ላይ ወደቁ….‹‹እኔ እኮ  ከአንተ  ፍቅር አልፈልግም…..››ስትል ቃተተች

ተፈፀመ

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe ቤተሰቦች ይሄን የምታነቡ ምንያህላቹ subscriber አድርጋችኋል??? በቅርብ በሌላ ታሪክ እንገናኛለን እስከዛው #Subscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍11326😁13🤔10🥰2
አትሮኖስ pinned «#አላገባህም ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ /// ዘሚካኤል እንግዳው ላይ አፍጥጦ ‹‹አይ ምንም እየገባኝ አይደለም….?››አለ ሰውዬውም ዘሚካኤል‹‹ቁጭ በል አስረዳሀለው..››አለና ወደውስጥ ገብቶ ቀድሞ ተቀመጠ… ፀደይ  ዘሚካኤልን እየጎተተች ይዛው መጣችና አስቀመጠችው…እሷም ተቀመጠችን ስልኳን አውጥታ ሪከርድ ላይ አደረገችና ሰውዬው የሚናገረውን ለመስማት ዝግጁ ሆነች፡፡ ‹‹ምን…»