አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሁቱትሲ


#ምዕራፍ_አስራ_አምስት


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#ወደ_አማጽያኑ_የሚወስደው_መንገድ


በነሃሴ መጨረሻ በአንድ ሞቃት ከሰዓት በኋላ የፈረንሳዩ መኰንን ምሽጉን ለቀን ልንሄድ እንደሆነ ነገረኝ፡፡ ዘመቻ ቱርኮይዝ ተጠናቀቀ፣ ስለሆነም ፈረንሳውያኑ ከሩዋንዳ ለመውጣት ይዘገጃጃሉ፡፡ ‹‹ምሽጋችንን ዛሬ እንዘጋለን›› አለኝ፡፡ ‹‹በሁለት ሰዓታት ውስጥ ሁሉም ሰው ይህን ምሽግ ለቆ እንዲወጣ ይዘገጃጅ፡፡››
‹‹የት ነው የምንሄደው?›› ስል ጠየቅሁት፡፡ ‹‹እዚህ ሰላሳ ሰዎች አሉ… የት ሂዱ ልበላቸው? ቤት የለንም!›› በድንገተኛው ዜና ተገረምኩ፡፡
‹‹ሁላችሁንም ከቱትሲ ወታደሮች ጋር እንድትቆዩ ልንወስዳችሁ ነው፡፡ ሩአግ ወደ አካባቢው የተጠጋ ሲሆን ካለንበት ስፍራ የተወሰኑ ኪሎሜትሮች ራቅ ብሎም ምሽግ
አቋቁሟል፡፡ እዚያ ወስደን ለእነርሱ እንሰጣችኋለን፡፡ ከራሳችሁ ሰዎች ጋር መሆኑ ይሻላችኋል፡፡››
የቱትሲ ወታደሮቹ በመጨረሻ ወደኛ እየተዋጉ መምጣታቸውንና ኢንተርሃምዌዎችን ከሀገር እያስወጡ መሆናቸውን በመስማቴ ተደሰትኩ፡፡ ጀግናችን፣ የሩአጉ መሪ ፖል ካጋሜ፣ በኪጋሊ አዲስ መንግሥት ማቋቋሙን ሳይቀር ሰማሁ፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን በመጨረሻም ሰላም አገኘን - ያች ቀን ደረሰች፤ የዘር ጭፍጨፋው መቆሙ ነው!
መሄዳችን መሆኑን በምሽጉ እየተዘዋወርኩ ለእያንዳንዱ ሰው ተናገርኩ፡፡ በቅርቡ ከመጡት አንዳንዶቹ ተጠራጠሩ፤ ፈረንሳውያኑ የማይታመኑና የስደተኛ መጠለያውን ያዘጋጁትም የዘር ጭፍጨፋውን ያስተባበሩትን ሁቱዎች በኪቩ ሐይቅ የማሻገርና ከሩዋንዳ በደኅና የማስወጣት እውነተኛ ተልዕኳቸውን ለመሸፈን እንደ ሰብዓዊ መከላከያ አድርገው ለመጠቀም ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡
‹‹ይህን እንኳን አላምንም›› አልኳቸው፡፡ ‹‹ፈረንሳውያኑ ለሳምንታት በደኅና ይዘውን ከርመዋል፤ ነጻ ሊያወጡንም ትንሽ ነው የቀራቸው! እናደርጋለን ያሉትን ሁሉ እያደረጉልን ነው፡፡››
በተጠንቀቅ ስለሆንን ለመዘገጃጀት ጊዜ አልወሰደብንም፡፡ ጓዝ ብሎ ነገር ያለው ስደተኛ የለም፡፡ በመሆኑም የምንሸክፈው ኮተት የለንም፡፡ ያሉኝን ጥቂት ንብረቶች ሰባሰብኩ - የቄስ ሙሪንዚ ልጅ የሰጠችኝን ሹራቤንና ፎጣዬን፣ ፒየር የሰጠኝን ሁለት መጻሕፍትና የተወሰኑ ወታደሮቹ የሰጡኝን ትርፍ ሳሙናዎችና ቲሸርቶችን በከረጢት አደረግሁ፡፡ ይህን ሳደርግ ግን እናቴ ገዳዮቹ በቤታችን አካባቢ እንደተሰበሰቡ እቃዎቿን በሻንጣዎች ስትከት የነበረው ትዝ አለኝና ካለፈው ሕይወቴ እቃዎችን ወደ አዲሱ ሕይወቴ ማንኳተት እንደሌለብኝ ወሰንኩ፡፡ በሁለቱ ሕይወቶቼ መካከል ንጹሕ መለያያ ለማድረግ ወሰንኩ፡፡ ከረጢቱን አንድ ሌላ ምስኪን ቤት-አልባ ቱትሲ ያገኘው ዘንድ በመመኘት ወደ መማሪያ ክፍሉ ወስጄ ጥጋት ላይ ተውኩት፡፡ ልሄድ ዘወር ስል በሩ ላይ ከቆመው ከፒየር ጋር ድንገት ግጥምጥም አልን፡፡ በሐዘኔታ አየኝና አንዲት ወረቀት ሰጠኝ፡፡ ‹‹እንዲያው ምናልባት ሐሳብሽን ከቀየርሽ ይህ የፈረንሳዩ አድራሻዬ ነው፡፡ በጣም እናፍቅሻለሁ፤ በልቤም አኖርሻለሁ፡፡ አምላክ በደኅና እንዲያቆይሽ እጸልያለሁ፡፡››
‹‹በል ደኅና ሁን ፒየር፡፡ እግዚአብሔር ይባርክህ›› ብልም እርሱ ግን ምላሼን እንኳን ሳይሰማ ሄዶ ኖሯል፡፡

በተሸከርካሪው ኋላ ላይ ለመውጣት የመጨረሻዋ ነኝ፡፡ የኋላ መዝጊያው ገጭ ብሎ ሲዘጋ የሸራ ከለላው እኛን ለመደበቅ ቁልቁል ተጋረደ፤ ተሽከርካሪውም ወደፊት ተንቀሳቀሰ፡፡ መቼም አሳልፌ የማልሰጠው ንብረቴን፣ አባቴ የሰጠኝን መቁጠሪያዬን፣ አወጣሁና ጸሎቴን አደረስኩበት፡፡ እግዚአብሔርን በአዲሱ መንገዳችን እንዲባርከንና ወደ ቱትሲ ወታደሮቹ በደኅና እንዲያደርሰን ጠየቅሁት፡፡
ተሸከርካሪው በግማሽ ክብ ቅርጽ የተደረደሩትን ብረት-ለበስ ተሸከርካሪዎችና ቁልቁል ጥርጊያ መንገዱን አልፎ ወደ ገዳዮች ባሕር ሰጠመ! ሸራው ላይ ባለች ትንሽ ቀዳዳ አጮልቄ በሺዎች የሚቆጠሩ ሁቱዎች በዋናው መንገድ ወደ ኪቩ ሐይቅ ሲተሙ አየሁ - ከመካከላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩት የኢንተርሃምዌን የደንብ ልብስ ለብሰው ገጀራ ይዘዋል፡፡
‹‹ወይ አምላኬ›› አልኩ ተሸከርካሪው ላይ እንደገና ወድቄ፡፡ ‹‹ድጋሚ አያምጣው!›› ሁቱዎቹ መንገድ እንዲለቁና እንዲያሳልፉን የተሸከርካሪውን ጡሩንባ እየነፋን በተጨናነቀው መንገድ እናዘግም ገባን፡፡ ኢንተርሃምዌዎቹ ካስቆሙን ወይም ተሸከርካሪያችን ከተበላሸ በደቂቃዎች ውስጥ ይረባረቡብናል፡፡ መታጠቢያ ቤቱን ለቅቄ ከወጣሁ ወዲህ ይህን ያህል ፈርቼ አላውቅም፡፡
‹‹እባክህ አምላኬ›› ስል ጸለይኩ፡፡ ‹‹ይህን ያህል አምጥተኸናል - አሁን ቀሪውንም ጎዳና ውሰደን! እነዚህን ገዳዮችም አሳውርልን … እዚህ ተሸከርካሪ ጀርባ ላይ እንዲያዩ አታድርጋቸው፡፡ መሐሪው ጌታ ሆይ! ከነዚህ ጥላቻ ከተሞላባቸው ዓይኖቻቸው ሰውረን!››
ወደ ሩአግ ምሽግ ከሚወስደን መንገዳችን ከግማሽ በላይ እንደሄድን ተሸከርካሪው ቆመ፡፡ ፈረንሳዊው መኰንን ወደ ኋላ መጥቶ ሸራውን ገለጠና ‹‹በአካባቢው ተኩስ አለ የሚል ወሬ ደርሶናል፤ ስለሆነም በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ተኩስን የማስቆም ግዴታ አለብን፡፡ ስለዚህ ልንመለስ ስለሆነ የግድ እዚህ መውረድ አለባችሁ፡፡›› አሳስቼ የሰማሁት መሰለኝ፡፡ ‹‹መልሰህ ትወስደናለህ ማለት ነው፣ አይደል?››
‹‹አይ፣ መጠለያውን ልንዘጋው ስለሆነ ብትመለሱም የምታርፉበት ስፍራ የለም፡፡ እዚህ መውረድ አለባችሁ… አሁኑኑ፡፡ ይቅርታ እንግዲህ ኢማኪዩሌ፡፡›› ባለፉት ጥቂት ሳምንታት መኰንኑን በደንብ አውቄዋለሁ፡፡ ሁቱ ገዳዮችን ስለሚጠላ ቱትሲዎችን በተቻለው መጠን ለመርዳት እንደሚፈልግ ተናግሯል፤ ስለሆነም በታጠቁ ኢንተርሃምዌዎች እጅ ሊጥለን ነው ብዬ ላምን አልቻልኩም፡፡ እርሱን ለማሳመን ከተሽከርካሪው ወረድኩ፡፡ ‹‹እባክህ፣ መኰንን ሆይ፣ እዚህ ከተውከን ምን እንደሚከሰትብን ከማንም በላይ ታውቃለህ፡፡ በዙሪያችን ገዳዮቹ እያንዣበቡ ነው! እባክህ ተለመነኝ … የሩአግ ምሽግ ከዚህ በኋላ ግፋ ቢል አንድ ኪሎሜትር ስለሚርቅ እባክህ እዚያ አድርሰን፤ አሊያም መልሰህ ውሰደን … እዚህ ለእርድ አትተወን!››
‹‹ይቅርታ ኢማኪዩሌ፡፡ ትዕዛዝ አለብኝ፡፡››
‹‹እባክህ መኰንን ብትወስደን ምናለ!››
‹‹አይ! ሰዎችሽን አውርጅልኝ፡፡ መሄድ አለብን፡፡››
አንድ ደርዘን ገደማ ኢንተርሃምዌዎች አሥር ጫማ በሚሆን ርቀት እየተከታተሉን፣ የምንነጋገረውን እየሰሙና ፍላጎታቸው በጣም አይሎ ስለቆሙ እየተከሰተ ያለውን ነገር ልናምን አልቻልንም፡፡ ጨነቀኝ፤ መሬቷም ዞረችብኝ፣ ለአንድ አፍታ እንኳን የማየው ነገር የቁጡ ፊቶችን ብዥታ ሆነ፡፡ ራሴን በተሸከርካሪው አንድ ጎን ላይ አረጋግቼ ቆሜ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሬት ላይ ያሉትን አስከሬኖች ምንነት አወቅሁ - መንገዱን ተከትሎ ዓይኔ እስከሚያየው ድረስ ሳማትር አስከሬኖች በየቦታው ወድቀዋል፡፡
መኰንኑን ቀና ብዬ አይቼ በዓይኖቼ ለመጨረሻ ጊዜ ተለማመጥኩት፡፡ ረብ-አልባ ነው - ወይ ፍንክች አለ፡፡ ምናልባት ቄሱና ሌሎቹ ስለ ፈረንሳውያኑ የተናገሩት ልክ ነው ማለት ነው፡፡ እውነት እዚህ የመጡት ገዳዮቹን ለመርዳት ይሆን? ይኸው በእርግጠኝነት ለሞት ሊተዉን ነው፡፡
ለጓደኞቼ ‹‹ኑ ውረዱ›› አልኳቸው፡፡ ‹‹ሁላችሁም ውረዱ … ፈረንጆቹ እዚህ ትተውን ሊሄዱ ነው፡፡››
#አላገባህም


#ምዕራፍ_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁ_ገመቹ

/////

በማግስቱ አቶ ቅጣው እንደተለመደው ጭለማና ድፍን በሆነው የእስር ክፍሉ በሰንሰለት እጅና እግራቸው እንደተጠፈረ  ኩርምት ብለው  በትካዜ ላይ እያሉ  የበራፍ መኳኳት ድምፅ ሰሙ የገመቱት ትንሽዬዋ መስኮት መሳይ ቀዳዳ ተከፍታ የእለቱ የምግብ ኮታቸው ይወረወርልኛል ብለው ነበር …ግን ትልቁ በራፍ ተከፈተ….ወዲያው ብርሀን ሾልኮ ወደክፍሉ ገባና አይናቸው ላይ አንፀባረቀባቸው፡፡አይናቸውን ጨፈኑ..ከዛ ገለጡ… አሁንም ጨፈኑ እንደዛ እያደረጉ ካለማመዱት በኋላ ገልጠው ምን እየተካሄደ እንደሆነ ሲያስተውሉ ከክፍሉ ይዘዋቸው ሊወጡ እንደሆነ ገባቸው..፡፡አንድ ጠባቂ ክላሹን እንዳቀባበለ ውጭ በራፍ ላይ ሲታያቸው አንደኛው ደግሞ እንደተለመደው ወደውስጥ ገባና ሰነሰለቱን ከመሬት ከተቀበረው ብረት ጋር የተያያዘውን ብረት ይፈታል ብለው ሲጠብቁ ከእግራቸው ጋር የተያያዘውን ሰንሰለት ፈታውና አላቀቀው…ከዛ ወደላይ ቀና ብሎ በእጃቸው ላይ የተሳረውን ሰንሰለት በተመሳሳይ ፈታና እዛው ወለሉ ላይ ሲወረውረው የፈጠረው የቅልጭልጭልታ ድምፅ በጆሮቸው ገብቶ አእመሮቸውን አተረማመሰው…‹‹ወደ መገደያዬ ሊወስዱኝ ነው እንዴ?››ሲሉ አሰቡ…..በመጀመሪያ በጣም ቅር አላቸው፡፡ከዛ ግን‹‹እንደውም ግልግል ነው…አሁንስ በህይወት እየኖርኩ ነው ይባላል …?

ከሞት ወደሞት መሄዱ ምኑ ያስፈራል?››ሲሉ አሰቡ፡፡ፊት ለፊታቸው ያለው ፖሊስ ከኪሱ ሌላ የሚያብረቀርቅ ካቴና  ከጃኬት ኪሱ አወጣና እጃቸው ላይ ካደረገላቸው በኃላ

‹‹አቶ ቅጣው..ቀጥል እንሂድ..››አላቸው…፡፡

‹‹ለምን..?ወዴየት?› የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ሳይጠይቅ በዝምታ ፊቱን ወደበራፉ አዞረና እርምጃውን ቀጠለ…ሰውነቱ  የዶሮ ላባ ያህል ቀለለው…ላለፉት ስድስት ወር እንዛ አስጠሊታ ድምፅ ያላቸው የዛጉ ሰንሰለቶች ከእግሩና ከእጁ ጋር ተላቀው ስለማያውቁ በተንቀሳቀሰ ቁጥር እንሱንም ይዞ ይንቀሳቀስ ስለነበረ እንደራሱ አካል ያያቸው ከጀመረ ሰነባብቶል…እና አሁን የሆነ የአካሉን ክፍል ቆርጠው እንዳስቀሩበት ነው የተሰማው..ከክፍሉ ይዘውት ወጡ ፡፡በኮሪደሩ ይዘውት ከተጓዙ በኋላ ለመጀመሪየ ጊዜ ከዛ ቀፋፊና መቀብር መሳይ ህንፃ ሙሉ በሙሉ ይዘውት ወጡና የውጭን ብርሀን እንዲያይ አደረጉት፡፡በመጀመሪያ ጭው አለበት…ከዛ እንደምንም አይኑን አጨንቁሮ አካባቢውን ለመቃኘት ሞከረ..ዛፎች ይታዩታል….አረንጓዴ ሳር የለበሰ ሜዳ ..ከዛፍ ዛፍ እየበረሩ የሚታዩ ወፎች…በግዙፍ አጥር  የተከበበ አነስታኛ ሜዳ…ሜዳውን ሞልተው  ኳስ የሚጫወቱና ስፖርት ሚሰሩ  እናም ደግሞ አፍ ለአፈ ገጥመው የሚያወሩ ቢጫ ቱታ የለበሱ መአት እስረኞች..ከሁሉም በላይ እምክ እምክ የማይልና የማያፍን ንፅህ የተፈጥሮ አየር በአፍንጫው ሲስብ …በቃ ከመቃብር የወጣ አይነት ስሜት ነው የተሰማው….እንባውን ከትሮ ማቆየት ስለተሳነው አለቀሰ…

‹‹እዛ ጨለማና የታመቀ ክፍል ውስጥ በህይወት ከመቆየት እዚህ በተፈጥሮ ፀጋ በተሸሞነሞነ ንፅህ አየር ውስጥ ሞቶ መቀበር ይሻላል››ሲል አሰበ፡፡

ከፊት እየመራው ያለው ፖሊስ‹‹ቀጥል አቶ ቅጣው››ሲል እንዲከተለው አዘዘው፡፡ ሌለኛው ፖሊስ ከኋላ ክላሹን እንደደቀነበት በሁለት ህንፃዎች መካከል ባለች ጠባብ መንገድ እየመራ ወሰደው.. በቆርቆሮ የተሰሩ ብዙ ክፍል ያሉበት ክፍል ጋር ሲደርስ ቆመ …ይሄን የቆርቆሮ ቤት ያውቀዋል….እስረኞች በእያንዳንዱ ክፍል አምስትና ስድስት እየሆኑ በሳምንት አንድ ቀን ሰውነታቸውን የሚታጠቡበት ክፍል ነው፡፡ከበርካታ ወራት በፊት እሱም እንደማንኛውም እስረኛ በሳምንት አንድ ቀን የመታጠብ ወርቃማ እድል ነበረው…አሁን ግን ሰውነቱ ውሀ ከነካው ስድስት ወር ከማለፉ የተነሳ የሰውነቱ ቀለም ሙሉ በሙሉ ተቀይሮል …አካላቱ ላይ የተለደፈው ቆሻሻ በውሀና ሳሙና  ሳይሆን በቢላዋ እየተቀረፈ እየተቀረፈ ካልተነሳ የሚፀዳ አይመስልም፡

አንድ ሌላ ፖሊስ በፔስታል የሆነ ነገር ይዞ በራፍ ላይ እየጠበቃቸው ነበር፡፡መድረሳቸውን ሲያይ አንደኛውን ክፍል ከፈተና ..ይሄው መቀየሬያ ልብሱ እዚህ ውስጥ አለ..ልጅህ ነው ያመጣልህ….ሌላውን ክፍል ድርስ እናመጣልሀለን..ሳሙናም ይሄው አለና›› ለፖሊሱ አስረክቦ ሄደ፡፡

‹‹አቶ ቅጣው ያልሆነ ነገር ለመስራት ፈፅሞ  እንዳትሞክር….ይሄው ሳሙና …  ሰውነትህን ታጠብና ልብስ ቀይር….››አለው

‹‹ለምን ግን?››ሲል መጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ጠየቀ፡፡

ፖሊሱ እጁ ላይ ያጠለቀለትን ካቴና እየፈታ‹‹ለምን ማለት ..ምኑ?››ሲል ጥያቄው እንዳልገባው በሚገልፅ ሁኔታ መልሶ ጠየቀው፡፡

‹‹መታጠቤና ..ልብስ መቀየሬ?››

‹‹ምነው አሁን ያለህበት ሁኔታ ተመችቶሀል እንዴ?ማጥ ውስጥ ሲንከባለል የከረመ ከርከሮ እኮ ነው የምትመስለው …ለማንኛውም ለምን እንድታጠብ እንደተፈቀደልህ አናውቅም…እኛ የታዘዝነውን እያደረግን ነው…ስራችንን እንድንሰራ ተባበረን..እንካ ልብሱንና ሳሙናውን… ይዘህ ግባ››አለው።

እንዳው በግዴለሽነት ተቀበለውና ወደውስጥ በዝግታ ገብቶ በራፉን ከውስጥ ሊዘጋው ሲል…ፖሊሱ ፈጠን አለና‹‹አይ አትዝጋው…..ክፍት ይሁን …ከእይታችን ውጭ መሆን የለብህም››የሚል ትእዛዝ ሰጠው፡፡

በግዴለሽነት በራፉን መልሶ በልቅጦ ወደውስጥ ገባ…ልብስ የያዘውን ፔስታል በአንዱ የግድግዳው ኮርነር ጋር አስቀምጦ ሳሙናውን ብቻ ይዞ ቀጥታ ሻወር ወደላበት ቦታ ሄደ… ውሀውን እስከመጨረሻ  ከፈተውና ውስጡ ቆመ…ውጭ ሆነው በትኩረት እየተከታተሉት ያሉት ሁለት ፖሊሶች በገረሜታ ምን እየሰራነው? ብለው እየተገረሙበት ነበር፡፡ለሀያ ደቂቃ አልተነቃነቀም…ውሀው እየተንፎለፎለ በላዩ ላይ ሲወርድ ከለበሰው ልብስ ላይም ሆነ ከገላው ላይ እየተቀረፈ የሚወርደው ቆሻሻ  ለሚያየው ሰው ይዘገንናል..በኋላ ግራ ሲገባቸው አንደኛው ፖሊስ ወደውስጥ ገባና ወደእሱ ተጠግቶ

‹አቶ ቅጣው ..ቅጣው …››ውሀውን  ዘጋው ሲል ጠየቀው…ከገባበት ጥልቅ ሰመመን የነቃ የሚመስለው ቅጣው‹‹አቤት በቃ ልውጣ እንዴ?››ሲል ጠየቀ፡፡

‹‹አይ እሱ እስከፈለግክ መታጠብ ትችላለህ..ግን በስርአት አድርገው፡››

‹‹በስርአት ማለት?››ተደነጋገረ፡፡

ሳሙናው እኮ በእጅህ እንደያዝከው ሟሙቶ ሊያልቅ ነው..የለበስከውን ቀፋፊ እና ቡትቶ ልብስ አውጥተህ ጣልና ሰውነትህን ሳሙና እየመታህ በትክክል ታጠብ››

‹‹እ..ገባኝ..እሺ›› ብሎ ልብሶቹን አወላለቀና ከእሱ አርቆ በመወርወር ርቃኑን ቆመና ሻወሩን በድጋሚ ከፈተ…ከዛ ከፀጉሩ በመጀመር ሙሉ ሰውነቱን ሳሙና በመለቅለቅ መታጠብ ጀመረ…ምን አልባትም አምስት ስድስት ጊዜ ደጋግሞ ሳሙና በመለቅለቅ ለወራት በሰውነቱ ተጠቅጥቆ የተከማቸውን ቆሻሻ በተቻለው መልኩ ለማስለቀቅ ጣረ… ከዛ…ቧንቧውን ዘጋና ቀጥታ ወደፔስታሉ በመሄድ ውስጡ ያለውን ልብስ ተራ በተራ እያወጣ በመመልከት  ለበሰ…ሁሉም ልብሶች ምርጥና አዲስ ሲሆኑ ለእሱ ግን ሰፍተውታል ….‹‹ምን አልባትም በጣም ከመክሳቴ የተነሳ ለእኔ በልኬ የሚሆን ልብስ ገበያ ላይ ስለሌለ ይሆናል ይሄን ያመጡልኝ››ሲል አሰበና በመጨረሻ ካልሲውንና ጫማውን አድርጎ ወደ ፖሊሶቹ ሄደ….በራፉ ላይ ተቀበሉትና በእጁ ላይ ካቴናውን መልሰው አጠለቁለትና በሌላ አቅጣጫ ይዘውት ሄዱ…አሁንም የወሰዱትን ቦታ ገና እንዳየው ነው ያወቀው›..የእስረኞች ፀጉር ማስተካከያ ቦታ ነው፡፡

‹‹ሽፈራው በል ቆንጆ አድርገህ አስተካክለው››ፖሊሱ ፀጉር አስተካካዩን አዘዘው፡፡

‹‹እንዴ ቅጣው..?እንዴት ነህ..?ሰላም ነህ?››ፀጉር አስተካካዩ በገረሜታ ተቀበለው፡፡
👍6610🥰2