አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
489 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የሚፈልጉትን_አይፈልጉትም

#አጭር_ታሪክ


ግልጽ ሰው እወዳለሁ አለችው

ህይወቱን ግልጽ ነገራት ጠላችው

ቀላል ሰው ደስ ይለኛል አለችው

ቀለል ሲል ረከሰባት ሸሸችው

ኩሩ ሰው ምርጫዬ  ነው ስትለው ኮራ አለ

ጠበርክ ብላው ሄደች።

የተረጋጋ ሰው  እወዳለሁ አለችው

ሲረጋጋ ተንቀራፈፍቅ ብላው ሄደች

የማይጨቃጨቅ ሰው ነው ምርጫዬ አለች

ስህተቷን ሲያልፋት ባትወደኝ ነው ግድ ያለሰጠህ አለችው

አስሬ መገናኘት መደዋወል ምናምን አልወድም አልችው።

መደወሉን ሲቀንስ ብትፈልገኝ ኖሮ ይሄንንም ብልህ ገፍተህ ትመጣ ትደውል ነበር። በቃኸኝ አለችው።


ምን እንዳጠፋ አሰበ።

እስካሁን አልገባውም።

ለአባቱ ነገረው ሁሉንም። አባቱ መለሰለት።

"ሰው ወዳለሁ ያለው ሁሉ አይኮንለትም።

ያለውን ሁሉ የምደረግለት ለአምላክህ ነው።

ሰው እኮ የፈለገውን ነገር ገና መፈለጉን አርግጠኛ አደለም።

የሚወደውን ነገር ለይቶ ያልጨረሰ ፍጡር ነው።

በተለይ  እነሱ ወጣቶቹ የሚፈልጉትን ራሱ በቅጡ አይፈልጉትም"

"ምን ልሁንላት?"

"ራስህን ሁንላት!
የምትልህን ትተህ የማትልህን ሁንላት።
ሴቶች ከንግግራቸው ጋ ሩቅ ናቸው።
ያሉህን ትተህ ያላሉህን ስማቸው"

የልጁ ስልክ ጮኸ። እሷ ናት።

~    ~      ~      ~  

💧ኤልያስ ሽታኹን💧
👍55🔥87👏1
"ሁሌ ባገኝህ አይሰለቸኝም" አለችው

"እውነትሽ ነው"

"አዎ ገና መተዋወቃችን ቢሆንም ደጋግሜ ላገኝህ እፈልጋለሁ"

ዝም ተባባሉ ረጅም ሰዓት።

"እኔ ምልህ ህይወት ላንተ  ምንድነው አለችው?"

"ቀይሮ መድገም ነው" አላት

"ማለት"

"አሁን የሆነች ተራ ካፌ ቡና ትጠጪያለሽ ሲኖርሽ ሸራተን ነው ራሱን ቡና

አሁን  አንድ ክፍል ቤትሽ ውሰጥ ትተኛለሽ
ሲኖርሽ አስር ክፍል ያለው ግን አንዱ ክፍል ብቻ ራሱን እንቅልፍ ትተኛለሽ

ደሀ ሆነሽ አረቄ ነው
ሀብታም ስትሆኚ ውስኪ ነው ቀይሮ መድገም

ሰው ለምን ይመስለሻል አንድ ደብር ደጋግሞ ከመሳለም ደብር የሚቀያይረው ቦታ ቀይሮ ጸሎት ለመድገም ነው።

በፊት የሆነ ልጅ ትወጃለሽ ስትለያይ
ልጅ የሆነ ትወጃለሽ 
ያንኑ መውደድ ቀይሮ ነው መድገም ነው

የሆነ ዘፈን በሌላ ዘፈን ዘፋኝ ቀይሮ መድገም

የምታውቂውን ስብከት በሌላ ሰባኪ ወይም ቄስ ቀይሮ መድገም 

በኢኮኖሚ ክላስ መሄድ ዝነኛ ስትሆኚ እዛው ፕሌን ውስጥ ቢዝነስ ክላስ ሆኖ ወንበር ቀይሮ በረራ መድገም

ሰው ሁሉ ገንዘብ የሚፈልገው የነበረውን ነገር ቀይሮ ለመድገም ነው።"

የሆነ ነገሯ ተዛባባት።

"በቃ የዘመኑን ከቨር ሙዚቃ ታውቂያለሽ?"

"አዎ" አለችው

"የኛ ሰው ህይወት እንደዛ ነው
የህይወት ከቨር በይው።
የሆነ የሆነ ነገር ቀንጭጮቦ መምጣት ቀጣጥሎ ማዜም
ቀያይሮ መድገም..."


"የሚቀጥለው አመት እደውልልሀለሁ" አለችው


💧ኤልያስ ሽታሁን💧
👍577🔥2
የምታውቁት ሰው ሲጠላችሁ
የማታውቁት ነው የሚያነሳችሁ!

ቅዱስ ዮሴፍ የሚያውቁት
ወንድሞቹ ሸጡት

የማያውቁት ግብፆች አነገሱት!

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍506🥰1
እንዴት እንደመጣሁ እንዳትጠይቂኝ
ለምን
ስለምትናፍንቂኝ፡፡
አውቀዋለሁኛ
አንድ የበደለሽ ሰው ናፍቀሺኛል ቢልሽ
ላንቺ
ፌዝ ነው የሚመስልሽ


ግን ናፍቀሽኛል፡፡

አዎ
በድያለሁ በግፍ
ደግሞም
ናፍቀሽኛል በእጥፍ፡፡
ማርያምን የምሬን በዝቷል መናፈቄ
የትም እገኛለሁ
የትም እስቀለሁ ግን ያለቅሳል ሳቄ፡፡
ብራመድ በሀገሩ
                     ብክንፍ እንኳ ብበር
ተከፍቶ አያለሁ ቆለፍኩት ያልኩት በር፡፡
ቀን የከረቸምኩት
ሌት በምን ከፈትኩት?
በለሊትሽ መጣሁ
አለሜን ስላጣሁ
ከትናንት የባሰ እንደማጣሽ ሳስብ
በደሌን አየሁት እጥፍ መውደድ ሲስብ
አንቺዬዋ ወዴ
የበደለ ሁሉ አይናፍቅም እንዴ...
ማቀፍ እንኳ ባልችል ምረት  ባለምንም
አትሳቂብኝ እንጂ
ግጥሙን እያነበብኩ ናፍቀሽኝ አሁንም፡፡
ፀሀይዋን ከተትኳት
አይንሽን ለማየት ከቤቴ እየወጣሁ 
የበደለ አይኔን እንዳታይኝ ብዬ
                    በጨለማ መጣሁ፡፡
ደረስኩኝ ከደጅሽ መፍራቴ በነነ
እሰይ አገኘሁሽ ናፍቆቴ ሰው ሆነ፡፡
እከንፋለሁ ይኸው ስደርስም አልሳምሺኝ
አጃኢብ ሰው መሆን
ሳጠፋ ጊዜ ነው ጭራሽ የናፈቅሽኝ፡፡
አጥፍቻለሁ አዎ መውደዴን ቀብሬ
አትሳቂብኝ እንጂ
ልክ ስበድልሽ ጨመረብኝ ፍቅሬ፡፡
:
:
:
ናፈቅሽኝ፡፡
        
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
39👍18🥰2
(አንቺ ተኝተሽ እስክትነቂ የተፃፈ)

ሰርቄ ልቀፍሽ ሰርቄ ልሳምሽ
ከባልሽ በፊት ነው ልቤ የሚያስብሽ
ወድጄ መሰለሽ
የሳሙትን ከንፈር በሌላ ሲወዛ
ያሳደጉትን ነፍስ በስጋ ሲገዛ
መታዘብ ያበሽቃል

ቱ ቱ ቱ

እኔ ጋር ስትመጪ መብሸቄ ይወድቃል፡፡
ባልሽን እርሺልኝ
መንትፌ ልቀፍሽ
ደብቄሽ እቀፊኝ
ጨለማን ስናስስ
ከብርሀን ስፊኝ፡፡
መስረቅ ቢሆን ሀጢያት በሰው የሚያስነቅፍ
እንዴትም አልሰማ ጆሮዬ ካንቺ እቅፍ፡፡
እቅፍቅፍ ...
እጥምጥም  ትጥምጥም
ሞቴ ባንቺ ሲጥም፡፡
አበጀሁ  ሰረቅኩሽ

እምጿ!!!!!

ይኸው ሳምኩሽ፡፡
እሰይ እዘርፉለሁ
እሬሳ እስከምሆን
ማነው  የሚያውቅልኝ
ባልሽስ ራሱ ከኔ ዘርፎሽ ቢሆን?
እረ....
ትዳር በቀደመ::
ይቀድመኝ
ግድ የለኝ፡፡
የሰው ነሽ እያልኩኝ ኑሪልኝ ከእቅፌ
እንኳንና ሞቴ አይመጣም እንቅልፌ፡፡
ሰርቄ ልቀፍሽ ሰርቄ ልሳምሽ
ከባልሽ በፊት ነው ልቤ የሚያስብሽ
በይ
ደርቢ እንዳይበርድሽ፡፡
        ----------///////----------

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍253👎3🥰1
#አጭር_ታሪክ

አንድ በእድሜ የገፋ አናፂ ፣ ጡረታ ሊወጣ ሲቃረብ የመጨረሻውን ቤት እንዲሠራ ተጠየቀ።

ደክሞት ስለነበረ ለማረፍ ጓጉቶ ርካሽ ቁሳቁሶችን ተጠቅሞ ስራውን በችኮላ ጨረሰ...

ሲጨርስ አሰሪው

''ይህ ቤትህ ነው ለአመታት ያገለገለልክበት ስጦታ'' ብሎ ቁልፉን ሰጠው። አናፂው ደንግጦ በግዴለሽነቱ ተፀፀተ። የራሱን ቤት የገነባው በደካማ ሁኔታ ነበር።
/////////
ዛሬ የምትሰራው ስራ ነገ የምትኖረውን ህይወት ይቀርፃል። ሁልጊዜ ጥሩውን ነገር ስራ!
👍57
#እቀናለሁ_አዎ

አጥንት ያነቅዛል ሲል ባይገባንም ውሉ
ቅናት ይሉት ነገር ተሰጥቷል ለሁሉ፡፡

#አዎን_እቀናለሁ
ያልቀኑበት ነገር ሲነጠቅ ስላየሁ፡፡
ብቻ ወድሽ የለ እኔ ምን አውቅና
ራሴን የማገኝ በሆንሽው ስቀና፡፡
ይኸውልሽ ጉዴ
ከከንፈርሽ በታች
ባለው ጥቁር ነጥብ ስቀና እያየሽኝ
እንደማላቅ ነገር ማርያም ስማኝ አልሽኝ፡፡

ለምን
ለምን ከንፈርሽ ጋር
ለምን አንቺን መርጣ
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን ሳመችሽ ስል ብዬ ደፋ ቀና
አትፍረጂ  ፍቅሬ
አፍቃሪ አይመርጥም በፍቅሩ ሲቀና፡፡
ለምን

እኔ ምን አቃለሁ ብቻ ወድሻለሁ!!!

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍29🥰165
በውሃ ላይ እርፍ
ያንቺን ገድል ልጽፍ....

(ላይሆንልኝ)

ቀለም ቢሆን ላይጽፍሽ ያንቺን ቁንጅና
የነፍስሸን ፊደል ላይችለው መሬት ብራና....
መታገሌ
መጃጃሌ፡፡
እንደው
ድከም ያለው
አንቺን የወደደ አንቺን የተመኘ
ተሞኘ፡፡

ሁሉን ትቼ ኖሬ ልጽፍሽ ከምጥር
በቃሌ ባጠናሽ እንደመንፈስ ምስጢር፡፡
(ይሻላል)
በቃሌ ወደድኩሽ
በቃሌ ናፈቅኩሽ
አይገርምሽም?
በቃል እየያዙ በቃል አለመጻፍ
ምንም አለማለት እያለ ምላስ አፍ
በቃል ብወድሽም
በቃል ባሰብሽም
ቃል ግን አይጽፍሽም፡፡

(አይገርምሽም?)


🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍21
ዝም በይ ዝም በይ
ገና ጨለማ ነው በዚህ ምድር ሰማይ
አንቺ ቃል ካወጣሽ ትወጣለች ፀሀይ::
ፀሀይ ወጣች ማለት
ካንቺ ጋር መለየት፡፡
ካንቺ ከመለየት ከመሸሽ ከመልክሽ
ፀሀይ ገብታ ትቅር ቃል አታውጪ ባክሽ፡፡
እንደኤልያስ ቃል ሰማይ እንዳዘዘ
ባንቺ ዝም ማለት ብርሃን ተያዘ፡፡
(እሰይ)
ያዥልኝ ያን ፀሀይ ያዣት ያችን ጀንበር
እስከዛሬስ ቢሆን
አንቺ ባታወሪ መች ታበራ ነበር?
አሁን
በዚህ ምሽት
ከኔ ተደባልቀሽ
ከኔ ተቀላቅለሽ
ከኔ ጋር ተራምደሽ
የሕይወትን ጣጣ ከኔ ጋር ተሻግረሽ
ፀሀይን አታውጫት አንድ ቃል ተናግረሽ፡፡
(ስወድሽ)
ባለችበት ትቅር አይንጋ ዘላለም
አይንጋ ዘላለም ባለችበት ትቅር
ብርሃን አያሻውም ሰው ካወረው ፍቅር፡፡
ዝም በይ ዝም በይ
ገና ጨለማ ነው በዚህ ምድር ሰማይ
አንቺ ቃል ካወጣሽ ትወጣለች ፀሀይ፡፡

(አታውሪ በዝምታሽ አብሪ)

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍216
የአምላክን ትዕዛዝ ልቤ እሺ ቢልም
ካንቺ ጋር የሆንኩት ሀጢያት አይባልም፡፡
ደብር የመሳለም ያህል
እንደ ትጉህ ገበሬ እህል
ሙሉ ነሽ
ልክ ነሽ፡፡
እናማ
ነይማ
መሳት
መሳሳት
ባንቺ ካለ
ፅድቅ ይሉት ገነት የት አለ?
ካንቺ አበላልጬ ገነትን ባልሽርም
አንቺን ያህል ቆንጆ ችዬ አለሸሞሽርም፡፡፡
የንፅህናሽ ልክ ገዝፎ ከምሳሌ
ያልታየ ገፄ ነሽ መሀሌ ማህሌይ፡፡

እቴ ባአንቺ መቅደስ
ወረብም አያፀድቅም ካንቺ ከመደነስ፡፡
የአምላክን ትዕዛዝ ልቤ እሺ ቢልም
ካንቺ ጋር የሆንኩት ሀጢያት አይባልም፡፡
(ለኔ)
ነውር እንደሆነ
ነውር እንደሆነ የእብድ እሳትን ማጥፋት
ነውር እንደሆነ ለማኝ ላይ መትፋት
ነውር እንደሆነ መሽናት ቤተስኪያን ዳር
ነውር እንደሆነ  ያለእድሜ መዳር
ነውር እንደሆነ
ኪዳነውልድን ትቶ ቃል አውቃለሁ ማለት
ነውር እንደሆነ
ረስቶ መቀመጥ የግሸንን ስለት
ነውር እንደሆነ
በጁምኣ መሀል ሶላትን ማቋረጥ
ነውር እንደሆነ
በቆሞስ ወንበር ላይ ጉብ ብሎ መቀመጥ
እንደዚያ ነውር ነው አንቺን  አለመሳም
የወደደ ሲያብድ ለነገው አይሳሳም፡፡
አልሳሳም ለነገ አልሳሳም ለተስፋ
ትዕዛዝ አይባልም
ፅድቅ የሚሉት ምስጢር ፍቅርን ከገፋ፡፡

ናፈቅሽኝ።

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍255👎5🥰2😱2
ኢትዮጵያ በራሷ ገዳይ ነገር አላት እንዴ?
ድንቄም ትርጓሜ
ቅኔና ዝማሜ
ድንቄም ሶላት አዛን
ሁሌ መለካካት ሁል ጊዜ ሚዛን፡፡
ድንቄም ሀዘን  ዕንባ
ሞትን ሰው ካረባ፡፡፡
አይ ቀስተደመና
ምደረ መና፡፡
ድንቄም ገዳም
እየተናከሰ አደምና አዳም፡፡
ድንቄም ገዳ
እንደወይን ግብዣ ደም እየተቀዳ፡፡
ድንቄም አክሱም አወይ ላሊበላ
እንደቅርጫ ስጋ ሰው እየተባላ፡፡
አይ አይ
ዋይ ዋይ፡፡
አይ እድገት
አይ ሰላም
በሰማይ አለኝ ላም፡፡
አወየው ሶፍ ዑመር
ሞት በሰው ቢከመር፡፡
አወይ አልነጃሺ
ስንቱን ተቀብሎ ዛሬ እሱ ቢሸሽ፡፡
(አናሳዝንም)
አይ ሸገር ፊነፊኔ
ለወያኔም ወይኔ
ለ..... ወይኔ፡፡
የዘሬ ያንዘርዝረኝ እንደተባባለነው
ይኸው....
ህይወት ድፍን ሲሆን በሞት ዘረዘርነው፡፡
ደሞ አለን በለኝ ተስፋና ዕድሉ
ታሪክና ባህል
ሲቆም አያምርበት ሰው እየገደሉ፡፡
አናሳዝንም???

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍23🔥98😢2
አንቺን እንዲሰጠኝ ሆንኩኝ አምላክ ለማኝ
ጧፍ መባ ገዛሁ ልሰጠው ከሰማኝ፡፡
አንቺዬ
ፀሎቴን ሳልጨርስ ብትይ እመጣለሁ
እኔ እኮ ሞኝ ነኝ
ፈጣሪዬን ትቼ እጠብቅሻለሁ፡፡
እጠብቅሻለሁ
በተገተርኩበት
እጠብቅሻለሁ
በተፈጠረኩበት፡፡
ጊዜ አይፈራረቅ አይጮኹም አእዋፍ
አንቺን ስጠብቅሽ
ለኮስኩት ጨክኜ ለስለት እንዲሆን የገዛሁት ጧፍ፡፡
ትመጫለሽ አይደል?


🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍209🔥2
የጨነቀው ሁሉ
"ማርያም ማርያም" ይላል ምጥም እንዳያቄም
በማን ስም ወለዱሽ ሀናና ኢያቄም?

~     ~     ~     ~       ~     ~

ቤት የለውምና
አዳም ወጥቶ ቀርቶ ከፈጣሪ ደጁ
ምንድነው ሚስጥሩ?
ቤት አትልተወለዱም እናትና ልጁ።


መስዋዕቱ ቀረ ርግብና ዋኖስ
ልጇን ልትሰጥ ነው እናት ከሊባኖስ።

የሊባኖስ ዝግባ ንፋስ የማይገፋው
ማርያም ስትወለድ እግዜር ዙፋን ሰፋው።


እመብዙሃኗ
የሄኖክ የራስ ወርቅ ኢሳይያስ ትንቢቱ
የዳዊት የልጅ ልጅ  የኖኅ መርከቢቱ።


ምስጢሩ ነችና  ሰምና ወርቅ ቃል
ቀራንዮን ያየ ሊባኖስን ያውቃል።


የጨነቀው ሁሉ
"ማርያም ማርያም" ይላል ምጥም እንዳያቄም
በማን ስም ወለዱሽ ሀናና ኢያቄም?

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
56👍11🥰3🔥1
#ፀሎተ_ግንቦት

ለተቀረው አመት...ደግሞም እስካመቱ
አንድ ሲል ልደታ...ዘጠኝ ሲል ወራቱ
ቅዬው ሲሰበሰብ ...
ላድባር የሚጀ'በት ፥ ሸክፎ ከቤቱ
ዛሬ ያልጠገብ ፥  አይኑና ፣ አንጀቱ
በማጣት ይታሻል...ጓዳና ፣ ማጀቱ
እንዲለን ልማዱ...
ጋን..እጋን ሲጋባ...መብሉ ሲመሰኳ
ማቲ ሲተራመስ ...ጨዋታው ሲውኳኳ
ቡኑ ሲከታትም ...ጢሱ ሲትጎለጎል
አጥንት ፣ ጉልጥምቱ ...ከሳቱ ሲታጎል
እንኳንስ ያዳም ከርስ...ያሞራው ሲረካ
ይህን የለመደ ...
ለላመት ድረሱ ፥ ብሎ ይመርቃል ፥ ሆድና መለይካ።
ልማድ መጥፎ ህመም ...
ሲነጠሉ ግዜ ..  ትዝታው በሽታ
የቀረ ለት ያማል...
ቀን በቀኑ ሲደርስ ...ክርሚያው በሽውታ
የሰው ልደት እንኳ ፥ ሲኮስስ ይከፋል ፥ እንኳን #ያዛኝቷ
እናም .... #እመቤቴ
ልማድሽ እንዳይቀር... #እመብርሀኒቱ
በለትሽ ምህላ ፥ እንዲሽር ፍጥረቱ
እንዳምና እንድንውል ፥ ለቀጣይ ለፊቱ
ጠርገሽ ወድያ ይጣል ...ነቀርሳ ልክፍቱ ።          

   🔘አብርሀም_ተክሉ🔘
🥰24👍113👏3
#ሀና_እና_እያቄም

ልጅ ቢሰጠን ብለው ቢያስገቡ ስለትን፣ እግዚአብሔር ሰጣቸው የእግዚአብሔር እናትን።

ሚካኤል ፣ ገብርኤል ፣ ዑራኤል …)

ስላሴ መንበር ፊት
ሰርክ የሚላላኩት፣
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው የሚያመልኩት።

(አምላክ ሰው)

እንደሚሆን ያኔ ትንቢቱን የሚያምኑ፣ ማርያም ስትወለድ እርግጠኛ ሆኑ።

ከአምላክ የራቁት፣
መዳን የናፈቁት፣
ከገነት ቤታቸው የወጡት በራቁት።

( አዳም እና ሄዋን )

ስትወለድ ቢያዩ ድንግል ከሊባኖስ፣
ከሲኦል ታያቸው የድህነት ፋኖስ።
👍4130
#የባርነት_አዚም

ኑ ባንዲራ እንሰቀል አንድ ላይ እናዚም፡፡
ኑ  ሰነደቅ እንስቀል
በሰው ስም ይነገድ በሰው ስም ይሸቀል፡፡

ቁስልን በማከክ ባይሽርም ህመሙ
ሀበሻን ግን ስሚው
ጥፍርን ሲለምን ለቁስል ለደሙ፡፡
"እከክ የሰጠ አምላክ
ጥፍርን ደግሞ ይላክ::"
እያለ የሚኖር
ብሂል ነው ሀበሻ ያውም ቃል አጋኖ
ሞኝ ሆኖ  አየደለም
ኑሮ ሆነበት ነው መቁሰል ደምቡ ሆኖ፡፡
መቁሰል የለመደ የሀበሻ ገላ
ጥፍር ይለምናል ማከክ ላይሆን መላ::
ግን ምን ታደርጊዋለሽ?
ደዌ ነፍስ
ደዌ ስጋ
ደዌ መንፈስ
ተጣብቆት ሰንብቶ
ባይሽርም በኮሶ ባይሽርም ባረቄው
መቁስል ስለማይቆሞ ጥፍር ነው ጥያቄው፡፡
ጥፍር
ጥፍር
(ጠብቆም ይነበብልኝ)
ጥፍር
እስር
እስርስር
ጥፍርፍር::
ጥፍር
ለእከክ የጠየቅነው ደግሞ ሲወጣልን
የፀብ አምሮታችን ይኸው ተነሳልን
ጥፍር
ጥፍር
ጥፍር
አንድም ለቁስላችን
አንድም ለፀባችን፡፡
ሀበሻ ብልጥ ነው የመቁሰል ዘመኑ ስለማያበቃ
የሰርክ  ልመናው ጥፍር ሆነ በቃ፡፡
  
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍207👎1
#እኔ
በፀጉሮችሽ መሐል እልፍ ፂም ባገኝም
የት ነበረች ብዬ ሳስብ አልገኝም

#እኔ
የሺ ወንድ ጠረን ብስብም ከአንገትሽ
እከራከራለሁ አይደለም ካንጀትሽ

#እኔ
በጡቶችሽ ጫፎች እያየሁ አሻራ
እጠርግልሻለሁ ቆጥሬ እንዳቧራ
ይልቅስ የእኔ
ስጋቴ
ፍርሃቴ
ያ ሁሉ ተባዕት እንዳያስጨንቁሽ
ያ ሁሉ ተባዕት ቀምሰው እንዳይርቁሽ
የሚያብሰከሰከኝ ሲስሙ እንዳያንቁሽ
(ነበር)

#እኔ
ሁሉን ደስታ አይተሽ
እንደፀሀይ ገላ ሙቀሽ
ስትጨርሺ
እንዳላይሽ አዝነሽ
እንዳንላይሽ ደርቀሽ
(ነበር)
እንጂ
ያዘንሽ ቀንም ከአጠገብሽ አለሁ
የደስታሽን ቀብር አብሬ እውላለሁ
ያንቺን የሀዘን ቀን እንደኔ ቆጥሬ
እንጀመር እላለሁ መውደድን ከዛሬ
ከዛሬ
ከአሁን
ከቅፅበት
ህይወት ስታበቃ እኛ እንጀምረበት
እላለሁ፡፡
እላለሁ
እንዳዲስ እንጀምር እንዳልተለመደው
ይሰፋል እላለሁ የተቀዳደደው
ይፀናል እላለሁ የተንገዳገደው
እላለሁ፡፡
እንደማቱሳላ
አኑረኝ
ቀኔን ሳላሰላ
አክርመኝ፡፡
ላቧን እስክትጨርስ
በወንድ እንክትርስ
ዓይኗ እስከሚሟሟ
እስከሚደባለቅ እውንና ህልሟ
አኑረኝ እላለሁ
አክረመኝ እላለሁ
እድሜ ስጠኝ ብዬ እለማመናለሁ
ለምን
ሁሉም የጣለሽ ቀን እኔ አነሳሻለሁ፡፡
(እስከዛ ግን አለሁ)

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3215🔥3
......የሚጠብቀን ባያንቀላፋም
<ኳ!> ባለ ቁጥር መንቃት አይከፋም...

🔘red-8🔘
👍354😢2
እግዜሄር የጨበጣቸው ''ሳያቅፈን'' ብለው ሲቆጡ

እግዚሄር ያቀፋቸው
እልፍኙ ገብተን ካልበላን- ብለው በኩርፊያ ሲመጡ

የግዚያብሄር እልፍኝ የገቡት

እንጀራ ሳይሰጠን ብለው-ቂም ዘግነው ይዘው ሲወጡ

ባይ ..ደነቀኝ....ባይ ገረመኝ..

ምናለ እኔን ላ'ንድዜ
ገላምጦኝ ደስታ ቢገድለኝ።

🔘red-8🔘
🥰41👍1713
#አምስቱ_የስሜት_ህዋሳት_ስንት_ናቸው?

.
እኔና እሷ ሳንፋቀር..
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ የምናውቀው አምስት ነገር
በአይናችን እናያለን
በእጃችን እንዳስሳለን
በምላሳችን እንቀምሳለን
በጆሯችን እንሰማለን
ባፍንጫችን እናሸታለን ፣ የሚል ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንፋቀር..
ካንደበቷ ቃል ሳይወጣ ፣ በዝምታ ስትናገር
የከንፈሯን ንቅናቄ
እያየሁኝ የምሰማት ፣ ያለችኝን አንዳች ነገር.
አይን ማለት
በዚያ ሰአት ፥ መስሚያ ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንጣላ
ስለጃችን ከተማርነው ፤ ከመዳሰስ ስሜት ሌላ
ሌላ ስሜት ተፈጥሮብኝ ፥ ያንደበቴን ቃል ሰስቼ
አነዳች ነገር ስናገራት ፤ የመሀል ጣቴን አውጥቼ
ስድብ መሆኑ ሲገባት
ምላሷን ስታወጣብኝ
ስላቅ መሆኑ ሚገባኝ
እጅ ማለት ሌላ ስሜት ፥ ምላስ ማለት ሌላ ነገር
መቅመስ መዳበስ ያልሆነ ፥ ያልተማርነው ነገር ነበር፡፡
ብቻ
ብቻ
እኔና እሷ ስንጣላ ፥ እኔና እሷ ስንፋቀር
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ ብንማርም አምስት ነገር
እኛ ኖረን ያሳለፍነው ፥ ቁጥር አልባ ስሜት ነበር፡፡

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍389👏2