#አላገባህም
፡
፡
#ምዕራፍ_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁ_ገመቹ
/////
በማግስቱ አቶ ቅጣው እንደተለመደው ጭለማና ድፍን በሆነው የእስር ክፍሉ በሰንሰለት እጅና እግራቸው እንደተጠፈረ ኩርምት ብለው በትካዜ ላይ እያሉ የበራፍ መኳኳት ድምፅ ሰሙ የገመቱት ትንሽዬዋ መስኮት መሳይ ቀዳዳ ተከፍታ የእለቱ የምግብ ኮታቸው ይወረወርልኛል ብለው ነበር …ግን ትልቁ በራፍ ተከፈተ….ወዲያው ብርሀን ሾልኮ ወደክፍሉ ገባና አይናቸው ላይ አንፀባረቀባቸው፡፡አይናቸውን ጨፈኑ..ከዛ ገለጡ… አሁንም ጨፈኑ እንደዛ እያደረጉ ካለማመዱት በኋላ ገልጠው ምን እየተካሄደ እንደሆነ ሲያስተውሉ ከክፍሉ ይዘዋቸው ሊወጡ እንደሆነ ገባቸው..፡፡አንድ ጠባቂ ክላሹን እንዳቀባበለ ውጭ በራፍ ላይ ሲታያቸው አንደኛው ደግሞ እንደተለመደው ወደውስጥ ገባና ሰነሰለቱን ከመሬት ከተቀበረው ብረት ጋር የተያያዘውን ብረት ይፈታል ብለው ሲጠብቁ ከእግራቸው ጋር የተያያዘውን ሰንሰለት ፈታውና አላቀቀው…ከዛ ወደላይ ቀና ብሎ በእጃቸው ላይ የተሳረውን ሰንሰለት በተመሳሳይ ፈታና እዛው ወለሉ ላይ ሲወረውረው የፈጠረው የቅልጭልጭልታ ድምፅ በጆሮቸው ገብቶ አእመሮቸውን አተረማመሰው…‹‹ወደ መገደያዬ ሊወስዱኝ ነው እንዴ?››ሲሉ አሰቡ…..በመጀመሪያ በጣም ቅር አላቸው፡፡ከዛ ግን‹‹እንደውም ግልግል ነው…አሁንስ በህይወት እየኖርኩ ነው ይባላል …?
ከሞት ወደሞት መሄዱ ምኑ ያስፈራል?››ሲሉ አሰቡ፡፡ፊት ለፊታቸው ያለው ፖሊስ ከኪሱ ሌላ የሚያብረቀርቅ ካቴና ከጃኬት ኪሱ አወጣና እጃቸው ላይ ካደረገላቸው በኃላ
‹‹አቶ ቅጣው..ቀጥል እንሂድ..››አላቸው…፡፡
‹‹ለምን..?ወዴየት?› የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ሳይጠይቅ በዝምታ ፊቱን ወደበራፉ አዞረና እርምጃውን ቀጠለ…ሰውነቱ የዶሮ ላባ ያህል ቀለለው…ላለፉት ስድስት ወር እንዛ አስጠሊታ ድምፅ ያላቸው የዛጉ ሰንሰለቶች ከእግሩና ከእጁ ጋር ተላቀው ስለማያውቁ በተንቀሳቀሰ ቁጥር እንሱንም ይዞ ይንቀሳቀስ ስለነበረ እንደራሱ አካል ያያቸው ከጀመረ ሰነባብቶል…እና አሁን የሆነ የአካሉን ክፍል ቆርጠው እንዳስቀሩበት ነው የተሰማው..ከክፍሉ ይዘውት ወጡ ፡፡በኮሪደሩ ይዘውት ከተጓዙ በኋላ ለመጀመሪየ ጊዜ ከዛ ቀፋፊና መቀብር መሳይ ህንፃ ሙሉ በሙሉ ይዘውት ወጡና የውጭን ብርሀን እንዲያይ አደረጉት፡፡በመጀመሪያ ጭው አለበት…ከዛ እንደምንም አይኑን አጨንቁሮ አካባቢውን ለመቃኘት ሞከረ..ዛፎች ይታዩታል….አረንጓዴ ሳር የለበሰ ሜዳ ..ከዛፍ ዛፍ እየበረሩ የሚታዩ ወፎች…በግዙፍ አጥር የተከበበ አነስታኛ ሜዳ…ሜዳውን ሞልተው ኳስ የሚጫወቱና ስፖርት ሚሰሩ እናም ደግሞ አፍ ለአፈ ገጥመው የሚያወሩ ቢጫ ቱታ የለበሱ መአት እስረኞች..ከሁሉም በላይ እምክ እምክ የማይልና የማያፍን ንፅህ የተፈጥሮ አየር በአፍንጫው ሲስብ …በቃ ከመቃብር የወጣ አይነት ስሜት ነው የተሰማው….እንባውን ከትሮ ማቆየት ስለተሳነው አለቀሰ…
‹‹እዛ ጨለማና የታመቀ ክፍል ውስጥ በህይወት ከመቆየት እዚህ በተፈጥሮ ፀጋ በተሸሞነሞነ ንፅህ አየር ውስጥ ሞቶ መቀበር ይሻላል››ሲል አሰበ፡፡
ከፊት እየመራው ያለው ፖሊስ‹‹ቀጥል አቶ ቅጣው››ሲል እንዲከተለው አዘዘው፡፡ ሌለኛው ፖሊስ ከኋላ ክላሹን እንደደቀነበት በሁለት ህንፃዎች መካከል ባለች ጠባብ መንገድ እየመራ ወሰደው.. በቆርቆሮ የተሰሩ ብዙ ክፍል ያሉበት ክፍል ጋር ሲደርስ ቆመ …ይሄን የቆርቆሮ ቤት ያውቀዋል….እስረኞች በእያንዳንዱ ክፍል አምስትና ስድስት እየሆኑ በሳምንት አንድ ቀን ሰውነታቸውን የሚታጠቡበት ክፍል ነው፡፡ከበርካታ ወራት በፊት እሱም እንደማንኛውም እስረኛ በሳምንት አንድ ቀን የመታጠብ ወርቃማ እድል ነበረው…አሁን ግን ሰውነቱ ውሀ ከነካው ስድስት ወር ከማለፉ የተነሳ የሰውነቱ ቀለም ሙሉ በሙሉ ተቀይሮል …አካላቱ ላይ የተለደፈው ቆሻሻ በውሀና ሳሙና ሳይሆን በቢላዋ እየተቀረፈ እየተቀረፈ ካልተነሳ የሚፀዳ አይመስልም፡
አንድ ሌላ ፖሊስ በፔስታል የሆነ ነገር ይዞ በራፍ ላይ እየጠበቃቸው ነበር፡፡መድረሳቸውን ሲያይ አንደኛውን ክፍል ከፈተና ..ይሄው መቀየሬያ ልብሱ እዚህ ውስጥ አለ..ልጅህ ነው ያመጣልህ….ሌላውን ክፍል ድርስ እናመጣልሀለን..ሳሙናም ይሄው አለና›› ለፖሊሱ አስረክቦ ሄደ፡፡
‹‹አቶ ቅጣው ያልሆነ ነገር ለመስራት ፈፅሞ እንዳትሞክር….ይሄው ሳሙና … ሰውነትህን ታጠብና ልብስ ቀይር….››አለው
‹‹ለምን ግን?››ሲል መጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ጠየቀ፡፡
ፖሊሱ እጁ ላይ ያጠለቀለትን ካቴና እየፈታ‹‹ለምን ማለት ..ምኑ?››ሲል ጥያቄው እንዳልገባው በሚገልፅ ሁኔታ መልሶ ጠየቀው፡፡
‹‹መታጠቤና ..ልብስ መቀየሬ?››
‹‹ምነው አሁን ያለህበት ሁኔታ ተመችቶሀል እንዴ?ማጥ ውስጥ ሲንከባለል የከረመ ከርከሮ እኮ ነው የምትመስለው …ለማንኛውም ለምን እንድታጠብ እንደተፈቀደልህ አናውቅም…እኛ የታዘዝነውን እያደረግን ነው…ስራችንን እንድንሰራ ተባበረን..እንካ ልብሱንና ሳሙናውን… ይዘህ ግባ››አለው።
እንዳው በግዴለሽነት ተቀበለውና ወደውስጥ በዝግታ ገብቶ በራፉን ከውስጥ ሊዘጋው ሲል…ፖሊሱ ፈጠን አለና‹‹አይ አትዝጋው…..ክፍት ይሁን …ከእይታችን ውጭ መሆን የለብህም››የሚል ትእዛዝ ሰጠው፡፡
በግዴለሽነት በራፉን መልሶ በልቅጦ ወደውስጥ ገባ…ልብስ የያዘውን ፔስታል በአንዱ የግድግዳው ኮርነር ጋር አስቀምጦ ሳሙናውን ብቻ ይዞ ቀጥታ ሻወር ወደላበት ቦታ ሄደ… ውሀውን እስከመጨረሻ ከፈተውና ውስጡ ቆመ…ውጭ ሆነው በትኩረት እየተከታተሉት ያሉት ሁለት ፖሊሶች በገረሜታ ምን እየሰራነው? ብለው እየተገረሙበት ነበር፡፡ለሀያ ደቂቃ አልተነቃነቀም…ውሀው እየተንፎለፎለ በላዩ ላይ ሲወርድ ከለበሰው ልብስ ላይም ሆነ ከገላው ላይ እየተቀረፈ የሚወርደው ቆሻሻ ለሚያየው ሰው ይዘገንናል..በኋላ ግራ ሲገባቸው አንደኛው ፖሊስ ወደውስጥ ገባና ወደእሱ ተጠግቶ
‹አቶ ቅጣው ..ቅጣው …››ውሀውን ዘጋው ሲል ጠየቀው…ከገባበት ጥልቅ ሰመመን የነቃ የሚመስለው ቅጣው‹‹አቤት በቃ ልውጣ እንዴ?››ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹አይ እሱ እስከፈለግክ መታጠብ ትችላለህ..ግን በስርአት አድርገው፡››
‹‹በስርአት ማለት?››ተደነጋገረ፡፡
ሳሙናው እኮ በእጅህ እንደያዝከው ሟሙቶ ሊያልቅ ነው..የለበስከውን ቀፋፊ እና ቡትቶ ልብስ አውጥተህ ጣልና ሰውነትህን ሳሙና እየመታህ በትክክል ታጠብ››
‹‹እ..ገባኝ..እሺ›› ብሎ ልብሶቹን አወላለቀና ከእሱ አርቆ በመወርወር ርቃኑን ቆመና ሻወሩን በድጋሚ ከፈተ…ከዛ ከፀጉሩ በመጀመር ሙሉ ሰውነቱን ሳሙና በመለቅለቅ መታጠብ ጀመረ…ምን አልባትም አምስት ስድስት ጊዜ ደጋግሞ ሳሙና በመለቅለቅ ለወራት በሰውነቱ ተጠቅጥቆ የተከማቸውን ቆሻሻ በተቻለው መልኩ ለማስለቀቅ ጣረ… ከዛ…ቧንቧውን ዘጋና ቀጥታ ወደፔስታሉ በመሄድ ውስጡ ያለውን ልብስ ተራ በተራ እያወጣ በመመልከት ለበሰ…ሁሉም ልብሶች ምርጥና አዲስ ሲሆኑ ለእሱ ግን ሰፍተውታል ….‹‹ምን አልባትም በጣም ከመክሳቴ የተነሳ ለእኔ በልኬ የሚሆን ልብስ ገበያ ላይ ስለሌለ ይሆናል ይሄን ያመጡልኝ››ሲል አሰበና በመጨረሻ ካልሲውንና ጫማውን አድርጎ ወደ ፖሊሶቹ ሄደ….በራፉ ላይ ተቀበሉትና በእጁ ላይ ካቴናውን መልሰው አጠለቁለትና በሌላ አቅጣጫ ይዘውት ሄዱ…አሁንም የወሰዱትን ቦታ ገና እንዳየው ነው ያወቀው›..የእስረኞች ፀጉር ማስተካከያ ቦታ ነው፡፡
‹‹ሽፈራው በል ቆንጆ አድርገህ አስተካክለው››ፖሊሱ ፀጉር አስተካካዩን አዘዘው፡፡
‹‹እንዴ ቅጣው..?እንዴት ነህ..?ሰላም ነህ?››ፀጉር አስተካካዩ በገረሜታ ተቀበለው፡፡

👍66❤10🥰2