አትሮኖስ
279K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ዴርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ፀደይና ዘሚካኤል ዶ/ሩን ለማግኘት ቦንጋ ከተማ ይገኛሉ፡፡ይሄ ጉዞ እንደዚህ አልነበረም የታሰበው፡፡ሚካኤልና እሷ ነበሩ ለሳምንታት አብረው ለመሄድ ሲዘጋጁ የነበሩት፡፡ከዛ ዝግጅቱ ሁሉ ተጠናቆ…ሚካኤል ቻርተር አውሮፕላን ተከራይቶ ወደቦንጋ ለመብረር ከአዳማ ተነስተው  አውሮፕላኑ ወደሚገኝበት አዲስ አበባ ሲደርሱ ዘሚካኤል ጠበቃቸው፡፡

ሁለቱም ያልጠቁት ነገር ስለሆነ በጣም ነበር ግራ የተጋቡት፡፡ዘሚካኤል እንደአጋጣሚ ከአዲስአለም ጋር ሲደዋወል ነበር ስለጉዞው የነገረችው፡፡
ለማናቸውም ሰላምታ ሳይሰጥ‹‹ፀዲ ከእኔ ጋር ነው መሄድ ያለብሽ?››አላት፡፡

‹‹ማለት…?ለምን ሲባል?››
‹‹በቃ ካንቺ ጋር መሄድና አብሬሽ መሆን እፈልጋለው››
ሚካኤል እጁን አጣጥፎ በገረሜታ እና በትዝብት እየተከታተላቸው ነው፡፡ፀደይን በተመለከተ እንዲህ ሲሪዬስ በመሆኑ ደስታ ተሰምቶታል፡፡

‹‹አይ…ከሚኪ ጋር ነው የምንሄደው…..አንተን ማስቸገር አልፈልግም››ኮስተር ብላ ተቃወመችው፡፡

እሱም ከእሷ በጠነከረ መኮሳተር‹‹እኔ ደግሞ አልስማማም….በችግርሽ ጊዜ አብሬሽ መሆን እፈልጋለው….የአባትሽን አድራሻ ብታገኚም ባታገኚም አብሬሽ ሆኜ ደስታሽንም ሆነ ሀዘንሽን መካፈል አለብኝ››ብሎ ግግም አለ፡፡

ሚካኤል ፀአዳ ስለ/ዶሩ  እንደዋሸችው ስለሚያውቅ በውስጡ ፈገግ እያለ‹‹ፀዲ አንዴ ላናግርሽ?››አላት፡፡

‹‹ቆይ ጠብቀኝ መጣው››ብላው ከዘሚካኤል ተለየችና ወደሚካኤል ሄደች፡፡

‹‹ፀዲ እሱ አንዴ ከጠመመ እሺ አይልም..››አላት፡፡

‹‹እና ከእሱ ጋር ሄጄ እንዴት ልሆን ነው?››

‹‹አሪፍ ነው እንደውም…ይሄ የእግዚያብሄር የራሱ እቅድ ይሆናል…ሁኔታዎችን እንዳመጣጣቸው ትወጫቸዋለሽ… ከሰውዬው የሆነ ጠቃሚ መረጃ ብናገኝ እንኳን እሱን አስረድቶ ማሳመን ከባድ ነው የሚሆንብን .. በኃላ እንዲህ ነው የተፈጠረው..እንደዛ ነው የሆነው ከምንል ቀጥታ ከፈረሱ አፍ ቢሰማ ነው የሚሻለው››

‹‹አረ ተው ሚኪ..››

‹‹ግድ የለሽም ባንቺ እተማመንብሻለው፡፡››አለና ጉንጮን ስሞ በፈገግታ በመጣበት መኪና ተመልሶ ሄደ፡፡
///
እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነው ሁለቱ  ቦንጋ  ከተማ ሊገኙ የቻሉት፡፡እንደደረሱ ፀደይ ከዘሚካኤል ዞር አለችን የዶ/ሩ ነው ተብሎ በተሰጣት  ስልክ ደውላ ነበር፡፡የዶ/ር ወንድም ነኝ የሚል ሰው ነበር አንስቶ ያዋራት፡፡‹‹ለምን እንደመጣችና ዶ/ርን  ለምን ጉዳይ እንደፈለገችው በአጭሩ ነገረችው፡፡

‹‹ላናግረውና መልሼ ልደውልልሽ ››አለና ስልኩን ዘጋ፡፡ሰውዬው መልሶ እስኪደውል ለሀያ ደቂቃ ተጨንቃ ነበር፡፡‹‹አይ ማግኘት አልፈልግም ቢል ምን አደርጋለው?››የሚልው ሀሳብ ትንፋሽ እስኪያጥራት ድረስ ነበር ያስጨነቃት፡፡ደውሎ ግን አስደሳች ነገር ነው የነገራት፡፡ በፈለጉት ሰዓት መምጣት እንደሚችሉ እና ሊያናግራቸው ፍቃደኛ እንደሆነ ነገራት፡፡ጊዜ ሳያባክኑ ወዲያው ነበር ባጀጃጅ በመከራየት ከከተማው የአንድ ሰዓት መንገድ ወደሚርቅ ገጠር ጉዞ ጀመሩ፡፡

እየሄዱ ሳሉ በገጠሩ ውበት ተደምማ..ዶዶላ ሆኜ አልፎ እልፎ ገጠር ሄድ ነበር..እዛም እንዲህ ውብ ነበር….እና በጣም ነበር ደስተኛ የምሆነው፡፡››

‹‹ገጠር ዘመድ ነበረሽ?››

‹‹አይ የጎደኛዬ ቤተሰቦች ገጠር ነበሩ.. እሱ ነበር ይዞኝ የሚሄደው››

‹‹ጓደኛዬ ስትይ…?››

‹‹የምስር አባት››

ወደራሱ ጎትቶ እያቀፋት‹‹በጣም ነው አይደል የጎዳሽ?››አላት ፡፡

‹‹አዎ!!በፊት በጣም የምጠላውና ባገኘው የምገድለው ይመስለኝ ነበር፡፡››

‹‹አሁንስ?››

‹‹…አሁን ግን  ሙሉ በሙሉ ይቅር ብዬዋለው››አለችው፡፡

‹‹ግን እንዴት በዛ መጠን የምትጠይውን ሰው እንዲህ በቀላሉ ይቅር ማለት ቻልሽ?››ሲል በገረሜታ ጠየቃት፡፡ይህንን ጥያቄ የጠየቃት እሱ በቤተሰቦቹ ላይ የቋጠረውን ቂምና ጥላቻ አሁንም በልቡ ውስጥ ቋጥኝ ሆኖ እያስጨነቀው በመሆኑ እሷ የነገረችውን ነገር ማመን ስላቃተው ነው፡፡

እሷ ግን እርግጠኛ በመሆን ታስረዳው ጀመር….‹‹ምን መሰለህ..በእኔና በእሱ መካከል የተፈጠረው ችገር የዛሬ ስድስት  አመት  የሆነ ነው››

‹‹እና ጊዜ ቁስልን ይፈውሳል በሚለው ብሂል ሄደሽ ነው?››

‹‹አይ እንደእሱ አይደለም…ሳስበው የዛሬ ስድስት አመት የነበረችው ፀደይ አሁን ካለችው ፀደይ ጋር በብዙ ነገር እንደምትለይ ገባኝ..እንደውም አንዳንዴ ያቺ ፀደይ ልክ እንደአንድ የምወዳት ዘመዴ ትናፍቀኛለች…››

እያወራች ያለችው መጀመሪያ ከተነሱበት ሀሳብ ጋር ምንም አልገጣጠም አለው…ቢሆንም በትግስት ማደመጡን ለመቀጠል ወሰነ..
እሷም ቀጠለች‹‹እና አሁን ያለሁት ፀደይ የዛን ጊዜ ባለፍኩበት ሁኔታ ላይ ብሆን ተመሳሳይ ችግር ላይ እወድቃለው..?ብወድቅስ ተመሳሳይ ምላሽ ነው የምሰጠው..?ማለቴ ራሴን ስለማጥፋት አስባለው….?ቤተሰቦቼንና ሀገሬን ጥዬ ወደማላውቀው ከተማ እሰደዳለው…?አንዱንም አላደርግም…፡፡ችግሩን በተለየ መንገድ ነበር የምፈታው…ይሄንን ወደ እሱ ቀየርኩት…አሁን እሱ በህይወት ካለ የሆነች ሴት አፍቅሮ ካስረገዘ በኃላ ደምፁ አጥፍቶ ይሸሻል…?እርግጠኛ ነኝ ቢያንስ እናትዬውን እንኳን ለማግባት ባይፈልግ ልጁን የራስሽ ጉዳይ ብሎ ዞር አይልም፡፡ታዲያ ዛሬ ባገኘውና ጥላቻዬን ባሳውቀው ካዛም አልፌ ልበቀለው ብሞክር ትርጉም ይሰጣል…አይሰጥም..፡፡ምክንያቱም ያ እኔ ማውቀው ልጅ ጠፍቶል… በብዙ ነገር ተቀይሮ በብዙ መከራ ውስጥ አልፎ ብዙ ህይወት ልምዶችን ቀስሞ ሌላ ሰው ሆኖ ነው ማገኘው..እና ሌላ ሰው ባጠፋው ሌላ ሰው የመቅጣት ያህል ነው….ለዛ ነው ይቅር ልለው የወሰንኩት፡፡››

ዘሚካኤል ዝም ነው ያላት…የነገረችውን ጠቅላላ ወደራሱ ህይወት ወስዶ ነው ማሰላሰል የፈለገው…፡፡ከዛሬ ሰባት በፊት የነበረው ዘሚካኤልና አሁን ካለው ዘሚካኤል ፈፅሞ የማይመሳሰል… የተለያየ ፍላጎት ..የተለየ አላማና አመለካከት ያለው ነው ፡፡እና መቶ ፐርሰንት የሚመሳሰሉበት ነገር ቢኖር በስማቸው ነው፡፡እሱንም ቢሆን የአባቱን ስም ስላስቀየረ….መቶ ፐርሰንት ሊባል አይችልም፡፡
//
ከቦንጋ ከተማ የአንድሰዓት እግር መንገድ ሄደው ነው ሰውዬውን ያገኙት፡፡ግዙፉ የሆነ በአረንጎዴ ዛፎችና ተክሎች ተሞላ ውብ ግቢ ነው የገቡት፡፡የሰውዬው ወንድም ነው የተቀበላቸው፡፡ ‹‹ወደማሳ ሄዶል አሁን መምጫው ደርሶል   ግቡና ጠብቁት ››ብሎ ወደግዙፉ የሳር ጎጆ ቤት ይዞቸው ገባ ፡፡ቤቱ ፅድት ያለ ነው፡፡ጥግ ላይ በለአንድ ሜትር የተነጠፈ አልጋ አለ..ከአልጋው አጠገብ ከእንጨት የተሰራ መደርደሪያ አለ..መደርደሪያው ግማሽ በመፅሀፍ ተሞልቷል፡፡ከስር በኩል አንድ መለስተኛ ቴፕ ይታያል፡፡

‹‹ግቡ ››አላቸውን የሚቀመጡበት ወንበር ሰጣቸው፡፡እና መቀመጣቸውን ካረጋገጠ በኃላ ተመልሶ ወጣ፡፡

‹‹አይ ሰውዬው ጥሩ ሁኔታ ላይ ሳይሆን አይቀርም››አላት ዘሚካኤል፡፡

‹‹በምን አወቅክ?››

‹‹አንድ ሰውን እኮ በቤቱ ሁኔታ መገመት ትቺያለሽ..አታይም እንዴ ምንም የቆሸሸ ምንም የትዝረከረከ  ነገር የለም….››

‹‹እንደአፍህ ያድርግልኝ.››አለችው፡፡

ድንገት ዘሚካኤል ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ ተነሳ..ሁኔታው ፀአዳን በጣም አስደነገጣት…እና አብራው ብድግ አለች…የሆነ እባብ ያየ ነው የመሰላት….ተንዳርድሮ ወደአልጋው ተጠጋ ..ከአልጋው በግራ በኩል ባለ መለስተኛ ጠረጴዛ ላይ ብዛት ያላቸው  በፍሬም ያሉ ፎቶዎች ተደርድረውበታል…ቀጥታ ሔደና ተራ በተራ እያነሳ ያያቸው ጀመር….ፀደይ ያልጠበቀችው ነገር ነው ያጋጠማት…ፎቶውን እያየ ወደእሷ ዞረና አፈጠጠባት›

‹‹ይሄ ምንድነው?››
👍496👏2