አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_ስድስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍስሀ
===
ስልኬን አነሳውና ደወልኩ አስተዳደሩ ቢሮ
‹‹…ሄሎ የሴት ድምጽ ነው››
‹‹ማነች ፀሀፊዋን ቢሮ ባስቸኮይ ነይ በያት››
‹‹ፀሀፊዋ ነኝ››
‹‹እንግዲያው ቶሎ ነይ…ከአለቃሽ ጋር..አሁኑኑ ››ጆሮዋ ላይ ጠረቀምኩባት…ልክ አስገባቸዋለው..ሁለቱንም ለድፍረታቸው ተገቢውን ትምህርት ሰጪ ቅጣት ያገኟታል…
እኛ ኢትዬጵያውያን ለወሬ ያለን ፍቅር ለራሳችን ካለን ፍቅር በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡እንደህዝብ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ ተምረዋል በሚባሉት የህብረተሰብ ደረጃ ጨምር የ<critical thinking >ልምምድ የለንም… የሰማነውን ወሬ ‹‹ለምን?›› ‹‹እንዴት?›› ‹‹የት?›› ‹‹ መቼ?›› ብለን በመጠየቅ የነገሩን ብልት በታትነን ለማየት የምናደርገው ጥረት ለዜሮ የቀረበ ነው፡፡የሰማነውን ወሬ ወይም መረጃ በዚህ መጠን መመርመር ደግሞ የመረጃዎችን ጥራት ለመጨመር..እርግጠኝነቱን አስተማማኝ ለማድረግ እና እወነተኝነቱን በአስተማማኝ መንገድ ለማረጋገጥ ወሳኝ መንገዶች ናቸው፡፡ ሰምተን ሳንጨርስ ለሌላው መናገር እንጀምራለን፡፡
መጡ‹‹ዝጉትና ቁጭ በሉ…››
ፊት ለፊት ተቀመጡ
‹‹ምን እየተሰራ ነው አቶ ሰይፉ››
‹‹ምን አጠፋን ጌታዬ…››በሚርበተበት አንደበት
‹‹እንደዚህች አይነት ሰራተኛ ይልኩብኛል…ነው ወይስ ይህንን እንድታደርግ እርሶ ነዎት የላኳት››
በቆሪጥ የእሷን መርበትበት ለማየት አይኖቼን ወደእሷ ስልክ ጭራሽ የምለውንም እየሰማች አይመስልም…ዘና ብላ የእጆቾን ጣቶች እየዘረጋችና እያጠፈች ከራሷ ጋር ትጫወታለች፡፡
<አረ እኔ…ለመሆኑ ምን አጠፋች?››
<በቃ ቡኃላ አናግሮታለው ከእሷ ጋር ልጨርስ> አመሰግናለው››
‹‹እሺ አቶ ፍሰሀ››ሹክክ ብለው ወጥተው ሄዱ…
ምን ልበላት እንድትደነግጥ እንዴት ልጩህባት እያልኩ በውስጤ ቃላት ስምርጥ
‹‹አንድ ነገር ልምከርህ›› አለቺኝ….
ይህቺ ልጅማ ጤነኛ አይደለችም…‹‹ምን አልሺኝ››
በምንም አይነት ሁኔታ ተራ ሰራተኞች ፊት የማናጅመንት አባላቶችህን እንዲህ ዝቅ አድርገህ አትናገር..ስህተት ቢሰሩም ጥፋት ቢኖርባቸውም ብቻቸውን ጠርተህ ነው ማነጋገር ያለብህ..ምክንያቱም አንተ ስታበሻቕጣቸው ያየ የበታች ሰራተኛ በትክክል ሊታዘዛቸው አይችልም. ያ ደግሞ ዞሮ ዞሮ የካማፓኒውን እፊሸንሲ ያወርደዋል…ያ ማለት ደግሞ ዞሮ ዞሮ በሰተመጨረሻ ያንተኑ አፈፃፀም ነው የሚጎዳው››
‹‹ጨረሽ››
‹‹አዎ ጨርሼያለው…ለምንድነበር የፈለከኝ?››
‹‹ማን ስለሆንሽ ነው ያለዘዝኩሽንን የሰራሽው?››
‹‹ምነው..? ላግዝህ ብዬ ነው››
‹‹ማን ስለሆንሽ ነው ምታግዤኝ?››
<አንድ ሰውን ለማገዝ እኮ ማንም መሆንን አይጠይቅም …ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው..››
ባክሽ አትቀባጥሪ ..ያ ሽማጊሌ ነው አይደል እንዲህ እንድታደርጊ የነገረሽ?..››…..በጥቂት ቀን ውስጥ ማን መሆኔን አሳየዋለው..አንቺ ግን ለእንጀራሽ ስትይ አደብ ግዤ>>
<<አንተም ለካንፓኒው ህልውና ሆነ ለራስህ የስራ ስኬት ስትል ምክሬን ስማ…..ደግሞ ለሽማግሌው ክብር ይኑርህ..ቅድም በስልክ ስታበሻቅጣቸው ላብ ሲያሰምጣቸው ነበረ…ለእሳቸው ሳይሆን ለራስህ ስትል አክብራቸው ..ደህና ሁን..››ብላኝ መቀመጫዋን ለቃ ወጥታ በራፍን በላዬ ላይ ዘግታ ሄደች…
አሁን አልተናደድኩም ..በጣም ደነገጥኩ…..ምንድነች ይህቺ ልጅ ..?ማንን ተማምና ነው እንዲህ መስመር የለቀቀችው…?እራሴን አመመኝ …ከዚህ በላይ ማሰብ ስላልቻልኩ ቢሮዬን ለቅቄ ወጣው ..ልጠጣና ልረሳት..እና ነገ አባርራታለው››
===
በጥዋት እንደገባው…አስጠራዋት….
‹‹እሺ ይህቺን ደብዳቤ ፃፊልኝ››
ቃል ሳትተነፍስ ተቀበለቺኝና ላፓቶፑ ፊትለፊት ተቀመጠችና መፀፋ ጀመረች…እየተከታተልኳት ነው….ስትባሳጭ ስትደነግጥ ለማየት ነበር በትኩረት እየተከታተልኮት የነበረው…ምንም አይነት የስሜት ለውጥ አልታየባትም …ደብዳቤው ስለ እሷ እንደሆነ አልገባትም ማለት ነው…ስሞን እያነበበች እንዴት አይገባትም…..?
‹‹ለወ/ሪት ፌናን ገመዳ
ጉዳዩ ፡ከስራ መሰናበትን ይመለከታል፡፡
ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ካምፓኒውን ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ አንድአንድ ለውጦች ማድረግ የግድ አስፈላጊ ስለሆነና ለለውጡ የሚመጥኑ ሰራተኞችና ማሰማራት የግድ በመሆኑ ይህ ደብዳቤ ከደረሶት ቀን አንስቶ ከስራ የተሰበናበቱ መሆንን አሳውቃለው፡፡
‹ከሰላምታ ጋር›
ፍሰሀ
ዋና ስራ አስኪያጅ
**
ይንን ነበር እንድትጽፍ የሰጠዋት..ለትዕቢተኛ እና ለስረአት አልበኛ ምህረት እንደሌለኝ እሷንም ሆነ ቀሪ ሰራተኞችን ማስተማር እፈልጋለው..እርግጥ የሰራችው ስራ ስህተት መሆኑን ተረድታ ይቅርታ ከጠየቀቺኝ ..በመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ልምራት እችላለው..አሁን ሳያት ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ማሰቧን የሚጠቁም ምንም አይነት ምልክት አላየውም፡፡
‹‹ጨርሼያለው ፕሪንት ላድርገው››አለችኝ ጭራሽ የደሞዝ ማሻሻያ ደብዳቤ እንደደረሰው ሰራተኛ ፈገግ ብላ
‹‹አዎ አድርጊውና ልፈርም››
አዘዘችና ወደሚቀጥለው ክፍል ሄደች..ፕሪንተሩ ያለው የሚቀጥለው ክፍል ነው፡፡
ይዛ መጣችና አቀበለቺኝ… ልትወጣ ስትል‹‹ቆይ ልፈርምና መዝገብ ቤት ትወስጂዋለሽ››አልኳት ቆማ ትጠብቀኝ ጀመር..
በዚህ አይነት ስሜት ውስጥም እያለው የተመዘዘ ቁመቷን አለማድነቅ አልቻልኩም…..
ከመፈረሜ በፊት ማንበብ ጀመርኩ…‹‹እንዴ ምንድነው የጻፍሺው…?››እስኪ የሰጠውሽን ረቂቅ ስጪኝ…ወረቀቱን ልታነሳ ጎንበስ ስታል ጡቷቾ ተጋልጠው እይታዬ ውስጥ ገቡ..እርግጠኛ ነኝ ጡት ማስያዥ አላደረገችም….ብታደርግማ ይሄን ሁሉ የጡቶን ክፍል በግልፅ ማየት አልችልም ነበር……ከጠረጳዛው ላይ አነሳችና ሰጠቺኝ….
ከስራ መሰናበትን ይመለከታል ነው የሚለው..አንቺ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ መስጠትን ይመለከታ ብለሽ ነው የጻፍሺው…
ዝም ብለህ በፀባይ ብትጠይቀኝ ኖሮ ከነገ ጀምሮ ቀርልህ ነበር….ግን ነገም በሌላ ሰራተኛ ላይ ተመሳሳዩን ላርግ ስለምትል ህጉን እያስተማርኩህ ነው…‹‹ዝም ብለህ በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ሰራተኛ ማባረር አትችልም….አንደኛ ይሄን ስራ ያንተ ሳይሆን የአስተዳደሩ ስለሆነ ለእሳቸው ብትተውላቸው….በስልጣንህ ተመክተህ አይ እኔ መስራት አለብኝ የምትል ከሆነ ደግሞ አንደኛ የሀገሪቱን የአሰሪና ሰራተኛ ህግ ሁለተኛ ሰራተኞች ከካንፓኒው ጋር የገቡትን የቅጥር ውል አንብበህ በውሉ ላይ በሰፈረው ህግ እና ደንብ መሰረት ነው እርምጃ መውሰድ የምትችለው…እንደ አንድ ማናጀር ሰውን ሳይሆን ኮንትራትን ነው ማስተዳደር ያለብህ …
በቃ ውጪልኝ..ደብዳቤውን ቀዳድጄ ቅርጫት ውስጥ ከተትኩና ቤሮውን ለቅቄ ወጣው ..በዚህ ስሜት ሌላ ምንም አይነት ስራ መስራት አልችልም….
ምን እየሆንኩ ነው…..አንድ ተራ ፀሀፊ መስመር ማስገባት ያልቻልኩ ሌሎቹን ምክትል ስራአስኪያጁን ጨምሮ የየክፍል ሀላፊዎች እንዴት አድርጌ ልመራ ነው…?አካሄዴንማ ማስተካከል አለብኝ...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን መልካም ምሽት🙏
👍1
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_ሰባት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


❤️ፌናን
===
ጥሎብኝ ውበት አድናቂ ነኝ፡፡ውበት ግን ምንድነው…?እኔ እንጃ ፡፡በስሜት ህዋሳታችን ተጠቅመን ወደ ውስጣችን ያስገባነው መረጀ ልባችን እና አዕምሮአችን ላይ በእኩል ጊዜ ሲደርስ እና መልሶ ወደ ስሜት ህዋሳታችን በመመለስ እንድንፈግ ወይም እንድንስቅ.. ወይ ደግሞ ጆሮአችን እንዲቆም ወይ ደግሞ በእግር ጥፍራችን የሚያቆም አይነት መደመም ላይ ሚጥለን ነገር ሲሆን ውበት ሚለውን ቃልን ልንጠቀም እንገደዳለን ፡፡
===
የእኔ ነገር … አሁን ስለውበት የእኔን ፍልስፍናዊ እሳቤ ልተነትንላችሁ ፈልጌ ሳይሆን ስለአዲሱ አለቃችን
ልነግራችሁ ስለፈለኩ ነው እንደዚህ ዙሪያ ጥምዝ ምሽከረከረው፡፡
ልጁ በጣም ያምራል…. በቃ የሆነ አትኩረው እንዲያዩት የሚያስገድድ ማግኔት ነገር ግንባሩ ላይ አለው…ለሆነ ሰከንዶች ያህል ደግሞ አትኩረው ሲያዩት አይን ደክም እንዲል ወይም እንዲርገበገብ የሚያደርግ አዚም አለበት….አዎ በአቅራቢያው ሲሆኑ ደግሞ ልብ በደቂቃ መምታት ከሚገባት ምት ወይም ማሰማት ከሚገባት ድውድውታ በሆነ ፐርሰንት እንዲጨምር የሚያደርግ ስውር ኃይል አለው፡፡
ጅኔራላይዝድ አረኩት አይደል…ይሄ ስሜት ስለአዲሱ ሀለቃዬን በተመለከተ እኔን የተሰማኝ ነው እንጂ የቢሮ
ሴት ሁሉ እንደዚህ እያሰባል ወይም እንዲህ ይሰማዋል ልላችሁ አይደለም….
ግን ገና ግማሽ ብስል ግማሽ ጥሬ ነገር ነው…ሙሉበሙሉ ለመብሰል ብዙ እንጨት መፍጀቱ አይቀርም… የዕውቀት ችግር የለበትም ….ያለበት የልምድ ችግር ነው፡፡ደግሞ ነፍሱ በፍራቻ እየተንፈራፈረች መሆኗን በደንብ ያስታውቅበታል…እርግጥ ይሄንን ከእኔ በስተቀር ያወቀበት ሰው የለም…ሌላው የቢሮ ሰራተኞች ስለኃይለኝነቱ….ተቆጪና ተናዳጅ ስለመሆኑ ብቻ ነው የሚያወሩት…..
አንደኛ ቁጣውም ሆነ ጩኸቱ አርቴፊሻል መሆኑን ከንግግሩ ድምጸት እና ከሰውነቱ እንቅስቃሴ በቀላሉ መረዳት ይቻላል…… ኃይለኛና ተፈሪ ለመሆን እየጣረ ነው..ሀይለኛ እና ተፈሪ መሆን የፈለገው ደግሞ ይህንን ካምፓኒ በትክክል መምራት እንደሚችል እራሱን አላሳመነም….ግን ደግሞ ሌሎቹን በቁጣና በማስፈራራትና ሊያሳምን እየጣረ ነው… እያደረገ ያለው ይሄንን ነው….፡፡ግን በዚህ መንገድ ፍጽም አይሳካለትም… ምክንያቱም ቀድሞ እራሱን መሳማን ሳይችል እንዴት ነው ሌላውን ሊያሳምን የሚችለው…?ይሄ የብዙ ሰዎች ባህሪ ነው..ሁልጊዜ የሌላው ፀባይ እንዲስታካከል..ሌላው ሰው እንዲለወጥ…ሌላው ሰው ወንጀል መስራት እንዲያቆም..እነዛ ብድኖች ከሙስና እራሳቸውን እንዲያቅብና ሀቀኛ ዜጋ እንዲሆኑ በፍትህ ታጋይ ስም እንጠይቃለን… ዜጋ ሁሉ በሀቀኝነት ለሀገር ተገቢውን ግብር እንዲከፍል እንፈልጋለን..ለዛም ባለማሰላስ ብዙዎቻችን እንጮኸለን…እንጽፋለን፡፡ግን የጥያቄያችን መንገድ የተሳሳተ ነው……እኛስ እራሳችንን ሀቀኛ ለማድረግ ወስነናል ወይ .. …?እኛስ በገዛ ቤታችን ዲሞክራሲ ለማስፋት መስራት ጀምረናል ወይ……?በዚህ አመት ገቢያችንን ሳንደብቅ ለመንግስት ተገቢውን ግብር ለመክፈል ወስነናል..…?ከቀበሌ መታወቂያ ለማውጣት ስንል የእጅ መንሻ አንከፍልም ለማለት ቁርጠኞች ነን ወይ……?
ሁላችንም በዛ መንገድ አይደለም የምናሰበው..ጉዞችን ወደ ውጤት የሚመራን አይነት አይደለም…ሌላውን ሰው የሆነ ነገር እንዲያደርግ ለማበረታታት ውጤታማው ዘዴ መጀመሪያ አድርጎ በተግባር ማሳየት ብቻ ነው….እና ይሄ አለቃዬ እራሱ ውስጡን ሳያሳምን ሰራተኞቹን በግድ እንደዛ አስቡ እያላቸው ነው…ቢሆንም እኔ እረዳዋለው…ይሄንን ካምፓኔ በብቃት የመምራት ችሎታ እንዳለው ውስጡ እንዲያምን አደርገዋለው…ግን ለምን እረዳዋለው…? እኔ እንጃ ..እንደውም እሱን ከመርዳት ይልቃ ላለመርዳት በቂ ምክንያ ነበረኝ….ምን አይነት ምክንያት…? ካላችሁኝ አሁን አልነግራችሁም….በደፈናው ግን ይሄን ካምፓኒ የመምራት ጉዳይ ባይሳክለት እኔ ተጠቃሚ ነኝ፡፡
ይሄን ሁሉ ምስቅልቅል ሀሳብ እያብሰለሰልኩ ያለውት ቢሮዬ ቁጭ ብዬ ነው….ሀሳቤን የገታውት አቶ ሰይፉ ከውጭ እያለከለኩ መጥተው በመሰላቸት መንፈስ ወንበራቸው ላይ ዝርፍጥ ብለው ረጅም የእፎይታ ትንፋሽ ሲተነፍሱ ሳይ ነው ፡፡
‹‹ምነው ጋሼ…?››እኔም ደንግጬ ጠየቅኳቸወ
‹‹ባክሽ ከእዚህ ልጅ ጋር እንዴት እንደምሰራ ግራ እየገባኝ ነው››
‹‹አይዞት ጋሼ …ጥቂት ጊዜ ነው… ይስተካከላል፡፡››
‹‹አይመስለኝም….ጡረታ መውጫ ጊዜዬ ደርሷል መሰለኝ››
‹‹አይ… ይሄን አይነት መሸነፍማ ከርሶ አልጠብቅም…አሁን ምን ተፈጠረ…?››
‹‹የሰራተኞች አመታዊ በዓል ለማክበር የተበጀተውን በጀት አላፀድቅም አለ››
‹‹ለምን አለ……?››
‹‹ብክነት ነው የሚል አመለካከት ነው ያለው…ይሄንን በዓል ላለፉት አስር አመት ስናከብር ቆይተናል.. ሰራተኞቻችን ከልጅ እስከ አዋቂው ይሄንን ቀን ልክ እንደ ሀይማኖታዊ ክብረበዓል ነው። የሚጠብቁት….ለዛውም እኮ በፕሌን ባህር ዳር ነበር ዕቅዱ..ግን ይሄንን ፈርቼ ከባጀቱ ላይ መቶ ሺ ብር ቀንሼ ወደቢሾፍቱ አዘዋውሬ ነበር ያቀረብኩለት››
‹‹እና ቁርጥ አድርጎ አይሆንም አለ…?››በብስጭት ስሜት ለማረጋገጥ ጠየቅኳቸው
‹‹አዎ ብሏል…››
‹‹የበጀቱን ሰነድ ይስጡኝ››
‹‹ምን ይረባሻል…?››
‹‹አስፈርመዋለዋ››
‹‹ጭራሽ አንቺ……?እንዴት እንደሚጠላሽ አታውቂም እንዴ……?እንድትባረሪ እንደሚፈልግ እኮ ነግሮኛል››
‹‹አውቃለው …እኔን በተመለከተ ባለው ስሜት ላይ ግራ መጋባት ውስጥ ስላለ ነው እንጂ አይጠላኝም …እንደውም ተቃራኒውን ነው…››
‹‹አይ አንቺ ልጅ…አንዴት እንደተንገሸገሸብሽ ስላላየሽ ነው….››
ከመቀመጫዬ ተነሳውን ወደ እሷቸው ወንበር ተጠጋው
‹‹ስጡኝ››
‹‹ቀዳዶ ፊትሽ ላይ እንደሚበትነው እያስጠነቀኩሽ ነው…በዛ ላይ ባንቺ የተነሳ ዳግመኛ እንዲናገረኝ አልፈልግም››
‹‹ግድ የሎትም… እርሶ ሳያዩ ከጠረጵዛ ላይ እንደወሰድኩት ነገረዋለው…››ብዬ እራሴው ወረቀቱን አነሳውና ቢሮውን ለቅቄ ወጣው…
እንደደረስኩ እንግዳ እያስተናገደ መሆኑን ፀሀፊው ስለነገረቺኝ ቁጭ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ..በነገራችን ላይ ፀሀፊው ከሄደችበት ለቅሶ ተመልሳለች…ከ7 ደቂቃ ቡኃላ ባለጉዳዩ ሲወጣ በዝግታ አንኳኩቼ ገባው….በተቀመጠበት ወንበር ወደኃላ ተለጥጦ ሲያዛጋ ነበር የደረስኩት….በራፉን ዘግቼ ወደወንበሩ በመሄድ ቁጨ አልኩ …ማዛጋቱን ጨረሰና እንደመስተካከል ብሎ ለሆነ ሰከናዶች ያህል ዝም ብሎ በገረሜታ ሲያየኝ ከቆየ ቡኃላ
‹‹ምነው የስራ መልቀቂያ ልታስገቢ ነው እንዴ የመጣሽው……?››አለኝ...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_ስምንት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


❤️ፌናን
===
‹‹ምነው የስራ መልቀቂያ ልታስገቢ ነው እንዴ የመጣሽው……?››አለኝ
‹‹አይ አይደለም››
‹‹እና ታዲያ እኔ እንደሆነ አልጠራውሽም …ልጠራሽ የምችልበት ምክንያትም የለኝም .. መልክ መልካምነት ከልዩ ስነምግባር ጋር አሞልቶ የሰጣት ፀሀፊዬ መጥታ ገላግላኛለች….››አለኝ የአሹሙር ለዛ ባለው ንግግር
‹‹በጣም ደስ ይላል…እወነትህን ነው ትሁትና ምርጥ ልጅ ነች..በነገራችን ላይ ከባሏ ጋር አብረን ነው የተማርነው …እሱን ብታየው ደግሞ ዋው.. የሚያሰኝ ውበት ያለው አፍ አስከፋች ሸበላ ልጅ ነው፡፡››አልኩት
የተኮስኩት የነገር ጥይት በትክክል አዕምሮውን መቶታል …በግርምትም በንዴትም አይኖቹን በልጥጦ ‹‹ስለስራ እኮ ነው እያወራሁሽ ያለሁት..ፀሀፊዬ ጎበዝ ሰራተኛ ነች ተስማማታኛለች ነው ያልኩሽ..ስለባሏ ውበት በዚህ አይነት ግነት ለእኔ መንገሩ ለምን አስፈለገ……?››
‹‹አይ እንዲሁ ለጠቅላላ ዕውቀት ያህል ነው…በዛውም እኔም የእሷ አድናቂ መሆኔን እንድታውቅ ፈልጌ ነው››
‹‹የእሷ ወይስ የባሏ…?››መልሶ ተኮሰብኝ
‹‹የሁለቱም››
‹‹እሺ አሁን ለምን መጣሽ…?ስራ እየተዉ በየቢሮው መዞር የስነምግባር ብልሹነት መሆኑን አታውቂም? ››
‹‹አውቃልው ግን አመጣጤ ስታዛጋ ሰምቼ ነው …አስር ደቂቃ ካለህ እዚህ ፊት ለፊታችን ካለ ካፌ አሪፍ የጀበና ቡና ስላለ ልጋብዝህ ስለፈለኩ ነው››
‹‹ምን…?››አደነጋገጡ አብረን እንደር ያልኩት ነው ያስመሰለው…
‹‹ምነው..…?አስር ደቂቃ እኮ ነው›››
‹‹አይ ይቅርብኝ ቡና አልጠጣም…››
‹‹ማኪያቶ ግን ትጠጣለህ…››
….ምንም ሳይለኝ ከመቀመጫው ተነሳና ጃኬቱን ከማንጠልጠያ ላይ በማንሳት እየለበሰ በተቀመጥኩበት ጥሎኝ ቢሮውን ትቶ ወጣ…. ከኃላ ተከተልኩት…እርምጃዬን ከእሱ ማስተካከል አልቻልኩት…. ሊፍት ውስጥ ቀድሞ ገባ ተከትዬው ገባው…ልክ ከረሜላ ከአፉ የነጠቁት ህፃን ይመስል ለንቦጩን ጥሏል….በውስጤ የታፈነውን ሳቅ እንዳያመልጠኝ የተጨነቅኩትን ጭንቀት ልገልጽላችሁ አልችልም፡፡
ከህንፃው ወጥተን መንገዱን እንደያዝን እርምጃዬን ከእርምጃው አስተካከልኩ…ስጠመዘዝ ተጠመዘዘና ተከትሎኝ ካፌ ገባ…
‹‹ምን ይምጣልህ ……?››ወንበር ይዘን እንደተቀመጥን ጠየቅኩት
‹‹ምን አገባሽ›› አለና አስተናጋጇን ጠርቶ ማኪያቶ አዘዘ እኔ የጀበና ቡና አዘዝኩ
‹‹አሁን በትክክል ወስኜያለው››
‹‹ምኑን…? ›››አልኩት
እዚህ ካምፓኒ እግሬ እንደረገጠ አንቺን ለማባረር መወሰኔ ቀድሞውንም ትክክለኛ ውሳኔ ነበር….አሁንም ቢሆን ስራዬን በትክክል ለመሳራት ቅድሚያ ማድረግ ያለብኝ አንቺን ማሰናበት ነው…ደግሞ በመከርሺኝ መሰረት የአሰሪና ሰራተኛ ህጉን አንብቤዋለው..እናም በውል ስምምነታችን መሰረት አሁን እንደገባን የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ እንዲደርስሽ አደርጋለው…ከዛ ደግሞ የወር እረፍት ትሞያለሽ…ከዛ ከፊቴ ገላል አደረግኩሽ ማለት ነው..ከዛ ጊዜሽ ሲያልቅ ደሞዝሽም ሆነ ሌሎች የሚገባሽን ጥቅማ ጥቅሞች ባለሽበት ይላክልሻል… አይዞሽ አትጨነቂ እኔ እንዳአንቺ አይደለውም የስራ ልምድሽ ላይ የማቃቸውን ስርዓት አልበኝነትሽን እና ታዛዤ አለመሆንሽን አልፅፍብሽም…››አለኝ…. አገኘውሽ የሚል የአሸናፊነት ኩራት ባለው ንግግር…
‹‹በነገራን ላይ የሥራ ልምድ ስትል በዚህች ሀገር ለአንድ ሰራተኛ የሚሠጥ የስራ ልምድ ማስረጃ ከሰውዬው ብቃት ጋር ሃማሳ ፐርሰንት እንኳን ተመሳሳይነት ካለው በጣም ጥሩ ነው….አንድ ሰው ስራ ለመቀጠር አምስት የስራ ልምዶች ይዞ ከመጣ በእርግጠኝነት ሶስቱ ፎርጂድ ይሆናል..የቀረው ደግሞ የሶሻሊስት ፓርቲ መፈክር ይመስል በብቃታቸው የተመሰከረላቸው…በችሎታቸው ወደርአልባ..በፀባያቸው ምስጉን የሚሉ ግነቶች የታጨቁበት በቃ ምን ልበልህ እንደውም በብዙ መስሪያ ቤቶች ደብዳው አንዴ ይፃፍል ሰራተኛው የስራ ልምድ ሲጠይቅ ስም እና የደሞዝ መጠን የሚገልፀው ቁጥር ብቻ እየተቀየረ ነው ፕሪንት በማድረግ የሚሰጠው…...እና ይሄ የስራ ልምድን ዓላማ ማርከስና ሀገርንም መግደል …ሰውዬው ገብቶ በለቀቀባቸው መስሪያ ቤቶች ሁሉ በተመሳሰሳይ ሁኔታ ስለጀግንነቱ ብቻ የሚያትት ልብ ወለዳዊ ምስክርነት የሚሠጠው ከሆነ ለምን ብሎ እራሱን ያሻሸላል……?እና ለማለት የፈለኩት አንተ ምርጥ ሀለቃ ስለሆንክ ያልከውን አታደርግም… ስለእኔ በትክክል የሆንኩትን እና ያልሆንኩትን..የምችለውንና የሚጎድለኝን በትክክል በመዘርዘር ነው የምትሸኘኝ…ጉድለቴን መፃፍህ እኮ የሚቀጥረኝ መስሪያ ቤት በመጀመሪያውኑ ስለእኔ እውነቱን አውቆት እንዲቀጥረኝና እና ጉድለቴንም እንዳሻሽል ስልጣና በማመቻቸት እንዲያግዘኝ ቅድሚያ መረጃ ይሰጠዋል፡፡
‹‹እሺ እንዳልሺን አደርጋለው…ስርዓት አልበኝነትሽን እና ወደ ላይ ያለአቅምሽ በመንጠራራት ሚስተካከልሽ እንደሌላ ቦልድ ተደርጎ እንዲፀፍልኝ አደርጋለው››አለኝ…. በዚህ ጊዜ ያዘዝነው ቡናና ማኪያቶ መጥቶልን ነበር….
‹‹አመሰግናው..ግን ከመባረሬ በፊት አንድ ነገር እንድታደርግልኘ እፈልጋለው››
‹‹ጠይቂኝ..››
‹‹ይሄንን ፈርምና ለመጨረሻ ጊዜ ዘና ብዬ ሁላችሁንም ተሰናብቼ ልልቀቅ..››ወረቀቱን አቀበልኩት…ገልጦ አየውና እስከዛሬ ካፈጠጠብኝ በላይ አፈጠጠብኝ…
‹‹ደግሞ ከአቶ ሰይፉ ሰርቄ ነው ያመጣሁት ..ለእሳቸወ ከነገርክብኝ አለቀልኝ››
‹‹ስንቴ ነው የሚያልቅልሽ……?ከእዚህ ካማፓኒ እህል ውሀሽ እኮ ተበጥሶል….ምንም የቀረሽ ነገር የለም››
‹‹ቢሆንም ..››
‹‹በይ ከሰረቅሽበት ቦታ መልሺ››ብሎ ወረቀቱን መልሶ አስታቀፈኝ
‹‹ይሄውልህ ..ይሄንን መፈረም ከማንም በላይ ላንተ ነው የሚጠቅምህ..››
‹‹እንዴት ብሎ ነው ሁለት ቀን ስራ መፍታት እና 3 መቶ ሺ ብር ማውጣት ሊጠቅመኝ የሚችለው……?››
‹‹አንደኛ ይሄ ለአስር አመት በካምፓኒው የቆየ ልምድ ነው፤ለዛውም ውጤታማ ልምድ፡፡ የካምፓኒውን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግባና ተመልከት …ምንጊዜም ከዚህ ዝግጅትና መዝናናት ቡኃላ ባሉ ሶስትና አራት ተከታታይ ወራቶች የእያንደንዱ ሰራተኛ የስራ አፈፃፀም ውጤት በሚገርም መጠን ነው የሚያድገው..የሄንን ያወጣሀውን 3 መቶ ሺ ብር በአንድ ወር ውስጥ እጥፍ ሆኖ ይመለሳልሀል፡፡ በአመታዊ ክብረ በዓሉ ካምፓኒው ከደሞዛቸው ውጭ በሆነ ብር የሆነ ነገር ስላደረጋቸው.የእኔነት ስሜት እንዲያድርባቸው ያደርጋል…፡፡፡ሁለተኛ ሰው በስራ በጣም ውጤታማ የሚሆነው በጣም ዘና ባለበት ጊዜ ነው…ለቀናትም ቢሆን ወደ ሆነ ሀገር ሄደው አየር መቀየራቸው ፤ ያላዩትን ነገር ማየታቸው መንፈሳቸው እንዲታደስ የስራ መነሳሳታቸው እዲጨምር እና ለህይወት ያላቸውም ጉጉት እንዲያንሰራራ ያደርጋል…፡፡ሌላው ያው ሰው ሆኖ መቼስ አንድ ላይ ሲሳራ በተለያየ ምክንያት የተጋጨ የተኮረፈ ይኖራል.. ልክ እደእኔና አንተ ማለት ነው..አንድ ላይ እየሰሩ ደግሞ ቅሬታ ውስጥ መግባት የስራ ጥራትንና ውጤትን በጣም እደሚቀንስ የታወቀ ነው፣እና እንዚህ አይነት ሰዎች ከስራ መንፈስ ውጭ ሆነው እንዲህ አይነት ቦታ ሲሄዱ መንፈሳቸው ከውጥረት የራቀና ዘና ለማለትም ዝግጁ ስለሚሆን ሁሉም ከገባበት ቅሬታ በቀላሉ ይወጣና እርስበርስ ይቅር ይባባላል፡፡ ሌላው በስራ ብቻ የሚተዋወቅ እና ግንኙነቱ በአየር ላይ የሆነ ሰው ግንኑነቱን በአንድ እስቴፕ ያሳድጋል…የተሸለ መግባባት እና አንዱ የአንደን ድክመት እና ጥንካሬ በተወሰነ መልኩ ለመረዳት እድል ያመቻችለታል… አንዳችን ያንዳችንን ፀባይ ፤ ድክመትና ጥንካሬ ማወቃችን እርስ በርስ ለመረዳዳት ተከባብረን እና ተደማምጠን ውጤታማ ለመሆን ያግዘናል...
👍7
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_ዘጠኝ



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


...ቀኑ እሁድ እንደመሆኑ ከእንቅልፌ የተነሳውት አረፋፍጄ ነው….አባቴ ክንዱን ከአንገቴ ዙሪያ እንዴት አድርጎ አውጥቶ፤ከደረቱ ላይ እንዴት አንሸራቶ ከስሬ እንደተነሳ አለውቅም…ከሰራተኞቻችን አንዷ ነች የቀሰቀሰቺኝ፡
‹‹ምነው ትንሽ ልተኛ››ተነጫነጭኩባት
‹‹ጋሼ ለቁርስ እየጠበቁሽ ነው..ቀስቅሺያት ብለውኝ ነው…ካለበለዚያ ጥዬሽ መውጣቴ ነው ብለውሻል››
‹‹እንዳታደርገው… መጣው ጠብቀኝ በይው…››አልኩና ተስፈንጥሬ አልጋዬን ለቅቄ ወረድኩ…..የለበስኩትን ቢጃማ እያወለቅኩና ወለል ላይ እየጣልኩ ወደሻወር ቤት ገባው.፡፡ ሰውነቴን ታጥቤ ለእርፍት ቀን የሚሆን ቀለል ያለ ልብስ ለብሼ ቁርስ ቦታ ለመድረስ ከ15 ደቂቃ በላይ ፈጀቶብኛል…አባቴ ፊት ለፊት በረንዳ ላይ ተቀምጦ መጽሀፍ እያነበበ ነበር…..
ከሶስት ቀን በፊት እንደተለየኝ በሚያስመስል ጥልቅ ስሜት ጉንጬን ሙጭሙጭ አድርጌ ሳምኩትና ከጎኑ ካለው ባዶ ወንበር ላይ ተቀመጥኩ….
‹‹በለሊት ምነው ተነሳህ…?››
‹‹በለሊት እንደምነሳ ሁሌ ታውቂያለሽ…እኔ እያየዋት ያልወጣችን ፀሀይ ቀኑን ሙሉ ምቾት ስትነሳኝ ነው የምትውለው…እንኳን በሰላም ወጣሽ ብዬ በደስታ መቀበል እና ማታ ደግሞ በሰላም ወደማደሪያሽ ግቢ ብዬ መሸኘት ለመኖር ያለኝ ጉጉቴን ይጨምርልኛል..ፀሀይ ለእኔ ያንቺ ተምሳሌት ነች፤እኩል ነው የምወዳችሁ……››
‹‹እንዴ አባ..እኔን ከፀሀይ እኩል ብቻ…እኔ እኮ ከራስህ እኩል የምትወደኝ ይመስለኝ ነበር….…?››
‹‹ለማለት የፈለኩት በትክክል ገብቶሻል…አንቺን ከእኔ እኩል መውደድ አንቺን ማሳነስ ነው…አንቺ ማለት በጣም የተስተካከለው እኔ ማለት ነሽ..አንቺ የእኔ በጣም ጥሩ ጎን ከእናትሽ ጥሩ ጎን ጋር አንድ ላይ ተቀይጦ ሲዋሀድ ማለት ነሽ…..የሁለታችንም ስህተት ሲታረም ንጥር ያለ ንጽህ እውነት ይወጣዋል… ያ እውነት ማለት ደግሞ አንቺ ነሽ…እና አንቺን ከእኔ እኩል ሳይሆን ከእኔ በላይ ነው የምወድሽ….››
ሳይቸግረኝ ቆስቁሼው በጥዋት በጣፍጭና አቅላጭ ንግግሩ እንባዬን አስመጣው…‹‹የእኔ ልዩ አባት››ብዬ ተንጠራርቼ ሳምኩት
ቁርሱ ቀረበልን እና በ10 ደቂቃ ውስጥ እያወራን በልተን ጨረስን……
‹‹አሁን መሄድ እንችላለን…?፡፡››አለኝ
‹‹አዎ ….››ብዬ ከመቀመጫዬ ተነሳውና ወደገራዥ በመሄድ የአባዬን መኪና በማውጣት እሱን ከጎኔ አስቀምጬ ከግቢው ወጣን…እኔና አባቴ እሁድን ተአምር የሚመስል አጋጣሚ ካልተፈጠረ እና አንዳችን የግድ ለብቻችን የምንሄድበት ቦታ ካልገጠመን በስተቀር አንለያይም…ለምሳሌ የእሱ ጓደኛ ጋር ለቅሶ ቢኖርና መሄድ የግድ ቢሆንበት አወቅኳቸውም አላወቅኳቸውም አብረን ነው የምንሄደው…ሰርግ እና ድግስ ተውት ከነባለቤቱ በሚለው ቦታ ባለቤቱን ወክዬ ሁሌ የምሄደው እኔ ነኝ
ከአራት ሰዓት እስከ ስምንት ሰዓት ያለው ፕሮግራማችን ከሞላ ጎደል ሁሌ ተመሳሳይ ነው….በመጀመሪያ ሆስፒታል ነው የምንሄደው…ሆስፒታሉ እንደየሁኔታው ሊለያይ ይችልላ…ግን የትኛውም ሆስፒታል ይሁን ብቻ አንዱ ጋር እንሄዳለን…..ከዛ በተቻለን መጠን የታመሙትን በየክፍሉ እየገባን መጠየቅ እንጀምራለን..ከዛ ቡኃላ በጥየቃችን ወቅት ምንም አስታማሚ የሌላቸውን አዛውንት..ወይም እናቷን የምታስታምም የዘጠኝ ዓመት ልጅ…መድሀኒት መግዣ ብር ያጣ ስንት ወንዘ አቋርጦ ከክፍለሀገር የመጣ ገበሬ …ብቻ ብዙ ብዙ ታሪክ ያላቸው ሰዎች ያጋጥሙናል….ከዛ አባቴ ይዞ የመጣውን ብር እንደየ ችግራቸው ከባድነትና እንደሚያስፈልጋቸው የብር መጠን ያከፋፍላቸዋል…
አንዳንዴ በሁኔታው ስደመም‹‹አባ ልዩ ሰው እኮ ነህ…ሰው ጤናውን ለማስመለስ በሚያደርገው ጥረት ገንዘብ ሲቸግረው…. ህክምናውን አግኝቶ መድሀኒት መግዣ ሲያጣ የሚሰማው ሀዘንና መሸማቀቅ .. በዛ ሰዓት ደግሞ አንተ ደርሰህ አይዞችሁ ስትላቸው የሚሰማቸው ደስታና እፎይታ …››ብዬ ላደንቀውም ላመሰግነውም ሞክራለው….
‹‹እኔ እኮ ምንም አላደረኩላቸውም..ደላላ በይኝ››ይለኛል
‹‹አልገባኝም››
‹‹ደላላ ማለት የሆነ ገዢን ከሻጭ አገናኝቶ ኮሚሽን የሚቀበል እና ባገኘው ኮሚሽን ደስተኛ የሚሆን ሰው አይደል…?እኔም ችግር ላይ ባሉ ሰዎች እና በእናትሽ መካከል አገናኝ ድልድይ በይኝ..ዋናዋ ተመስጋኝ ባለብሯ እናትሽ ነች፡፡ እኔ ከእሷ ብሩን እቀበላለው መጥቼ ልቤ በፈቀደው መንገድ እየመደብኩ አከፋፍላለው… የድለላዬን ዋጋ ሰዎቹ የማይገባኝን አይነት ሙገሳና ፤ መንግሰተ ሰማያት መሬት ለመግዛት የሚያስችለኝን አይነት ምርቃት ያሸክሙኛል..››ይለኛል
‹‹አይ አባ..እናቴ እኮ ብሩን ለሰዎቹ ብላ ሳይሆን አንተን ለማስደሰት ስትል ነው የምትሰጥህ…ለምሳሌ ይሄንን ብር ከጓደኞችህ ጋር ውስኪ ለመራጨት ብትጠቀምበትም እሷ ደንታዋ አይደለም…አረ ውሽማ ኖሮህ ለእሷም ብትሰጣት እንኳን ምንም የሚመስላት አይመስለኝም ….ደግሞ ማላውቅ እንዳይመስልህ››
‹‹ምኑን…? ››
‹‹ይሄንን ባህሪህን ከእናቴም ከመገናኘትህ በፊት ፤ ምንም ብር ባልነበረህም ጊዜ በዝርዝር ሳንቲሞች ደረቅ ዳቦ እየገዛህ በሽተኞችን እንደምትጠይቅ አዎቃለው..››
‹‹እሱስ ትክክል ነሽ›› ብሎ ትክዝ ይላል፡፡››
===
አባቴ ዝም ብሎ አይደለም የዚህ ባህሪ ባለቤት የሆነው…ታሪኩን እሱ ለእናቴ ነግሯት እሷ ደግሞ ለእኔ ነግራኛላች… እኔ ደግሞ አሁን አጠር አድርጌ ለእናንተ ልንገራችሁ…
አባቴ የአጄ ልጅ ነው፡፡አጄ በሻሸመኔ እና በአላባ መካከል የምትገኝ መለስተኛ ከተማ ነች ፡፡ለእናትና አባቱ አንድ ብቸኛ ልጅ ነበር.፡፡አባትዬው ህፃን ሳለ ነበር የሞቱት፡፡እናትዬው ግን አባት አልባ መሆኑን እንዳይሰማው ፊታቸው በማድያት እስኪሸፈን፤ ወገባቸው ያለእድሜያቸው እስኪጎብጥ እንደወንድ እያረሱ..እንደሴት እየፈተሉ ፤እንደገበሬ እያመረቱ ፤እደ ነጋዴ እየቸረቸሩ ምንም ሳይጎድልበት እስተማሩት ..እሱም ልፋታቸውን መሬት እንዲበተን አላደረገም… ጥሩ ውጤት አምጥቶ ዩኒቨርሲቲ ገባ፡፡ሁሉም ነገር መልካም ሆኖ ከቀጠለ ቡኃላ የመጨረሻ የመመረቂያው አመት ላይ ያልተጠበቀ ጨለማ ነገር ተፈጠረ….
ለእናቴ ደረስኩላት ብሎ ፈንጠዝያ ላይ ባለበት ጊዜ…..የአለምን ሁሉ ጥሩ ነገር በሚገባት መጠን ለአናቴ አደርግላታለው ብሎ በጉጉት በሚናጥበት ጊዜ ፡፤ እናቴን ስንድ እመቤት አድርጌ በምቾትና በድሎት እንድትኖር አደርጋታለው ብሎ ዝግጅት ላይ ባለበት ጊዜ በአስቸኳይ ድረስ ተብሎ ከዩኒቨርሲቲ ተጠራ…ሲደርስ እናቱ በሞትና በህይወት መካከል ስታጣጥር ነበር የደረሰው….ከዛ ያደረገው የአካባቢው ሰዎች ባዋጡት እና እናትዬውም እጅ ላይ በነበረች ጥቂት ገንዘብ ለተሻለ ህክምን ወደሻሸመኔ ሆስፒታል ይዞቸው መሄድ ነበር…በምርመራው የበሽታቸው አይነት ተለይቶ መድሀኒት ይታዘዝላቸዋል …ሶስት መድሀኒት 950 ብር…ያ ብር ከየት ይምጣ..…?አቅም ያላቸው የአባቱም ሆኑ የእናቱ ዘመዶች ጋር እየደወለም እራሱም በአካል እየሄደ እደጅ ቢጠና ከአስርና ከሃያ ብር በላይ ሊሰጠው የሚችል አዛኝ ልብ ያለው ሰው ማግኘት አልቻለም..ከዛ የመጨረሻ አማራጭ በሽተኛ እናቱን አስፓልት ዳር አስተኝቶ እናቴን አድኑልኝ እያለ ምድሀኒት መግዣ መለመን ነበር…ግን የተፈላገው ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ብር ከማግኘቱ በፊት እዛው አስፓልት ላይ እናቱ ትሞትበታላች…ያ አባቴ ሙሉ በሙሉ የተቀየረበት ወቅት ነበር..ለገንዘብም ለህይወትም የነበረው ምልከታ ከስር መሰረቱ የተደረማመሰበት …ያ ወቅት አባቴ ዘመድ አልባ ብቸኛ ሰው እንደሆነ የተቀበለበት ጊዜ ነበር…
ትምህርቱን አጠናቆ ወደሀገሩ አልተመለሰም ….ዝም ብሎ ወደማያውቀው አዲስ አበባ ዲግሪውን
👍1
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስር



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


...‹‹ዛሬ የት እንሂድ…?›› አልኩት አባቴን ስምንት ሰዓት ከሩብ አካባቢ….
መኪና ውስጥ ገብተን እኔ እየነዳው ነው እያወራን ያለነው….
‹‹እኔ ምንም በውስጤ የለም…አረጀው መሰለኝ የመዝናኛ አይነቶች እየጠፉብኝ ነው፡፡››
‹‹የእኔ አባትማ እንዲህ በቀላሉ አያረጅም …ገና እኔና እናቴ ድል አድርገን ደግሰን ልጃገረድ ነው የምንድርህ››
‹‹አይ እብድ የሆንሽ ልጅ…በሚስት ላይ ሚስት ወንጀል እንደሆነ አታውቂም…››
‹‹አይ እናቴንማ ሚስቴ ብለህ መጥራቱን አቁም …አሁን መጨረሻ ውሳኔ ላይ ደርሼያለው…››
‹‹ምን አይነት ውሳኔ…?››
‹‹አሁን የጤናዋ ጉዳይ መስመር እስኪይዝ ነው እንጂ ወይ እንደገና ታግባህ ወይ ደግሞ በፍቃዷ ትልቀቅህና ልዳርህ››
ፈገግ አለና‹‹…አሁን ይሄን ምን አሳሰበሽ…?›
‹‹ለምን አላስብም አባ……? ደግሞ አሁን አይደለም …ሁሌ እኮ ነው ሚያንገበግበኝ…በዚህ ጉዳይ ላይ የሆነ ነገር ብትለኝ ደስ ይለኛል….››
‹‹ምን እንድልሽ ነው የምትፈልጊው……?››
‹‹እኔ እንጃ…እናቴን ለምን አልተውካትም……?መቼስ ለብሯ ስትል አብረሀት እንዳልቆየህ አውቃለሁ…አንተ በቁስ ፍቅር ልትሸነፍ ምትችል ሰው አይደለህም …››
‹‹ለምን ጥያቄውን ገልብጠሸ አልጠየቅሺኝም…?››
‹‹እንዴት ብዬ……?››
‹‹ለምን እናቴ አንተን ጥላህ አልሄደችም..…?ለምን እንደዛ ማድረግ ተሳናት……? ሀብታም ነች፤ቆንጆ ነች፤የተማረች እና ብልህ ነች ከንተ ጋር ለምን ኑሮዋን መቀጠል ፈለገች……?ለምን ከቤቷ አንተን አስወጥታ ሌላ የሚመጥናትን ባል አላገባችም ብለሽ አልጠየቅሺም….…?ለምን….…?››
‹‹ሚመጥናትን!! …?ጭራሽ አንተ ለእሷ መመጠን አቅቶህ…? አረ አታስቀኝ ....አንተ እኮ ሁሌ ባል ለመሆን ዝግጁ ነህ…አንተ እንከን አልባ ሰው ነህ…እሷ ነች ሀብት አሳዳጇ..እሷ ነች ቤቱን እርግፍ አድርጋ የአደባባይ ሴት የሆነችው…እሷ ነች…››
‹‹በይ ይብቃሽ ልጄ…ሁል ግዜ ስለምንወዳቸው ሰዎች ያለን ምልከታ ስለእነሱ እወነቱን እንዳናይ እያየንም እንኳን አምነን እንዳንቀበል ጥቁር መጋረጃ ይሆንብናል…ላንቺ አባትሽ ምንም ጉድፍ የለበትም…ያንቺን አባት የሚመስል ሰው በዚህ ምድር ላይ አልተፈጠረም…የዚህ ዓለም ቆነጃጅቶች ሁሉ አባትሽን ለማግኘት ቢደባደብና ቢቦጫጨቁ ተገቢ ነው…..አይደል..…?እንደዛ አይደል የምታስቢው..…?››
‹‹ምነው ባስብ ታዲያ ተሳሳትኩ……?.››
‹‹አዎ ተሳስተሸል..፡፡ባልና ሚስት በሆነ ነገር አልተስማሙም ማለት ጎጆቸውን ማፍረስ አለባቸው ማለት አይደለም…ደግሞ ልጄ አንድ ነገር ልነግርሽ እፈልጋለው.. ትዳርና ሀገር ውስብስብ ናቸው፡፡ትዳር ይዘሽ ልጆች ወልደሽ እና ንብረት አፍርተሸ ረጅም አመት ኖርሽ ማለት ሁሉ ነገር ገነታዊ ነው ማለት አይደለም…የሆነ ነገር ለማግኘት ሁሌ መክፈል ያለብሽ የሆነ መስዋዕትነት አለ…ባልሽ በምንም አይነት ሁኔታ መቶ ፐርሰንት አንቺ ወደምትወጂው ወይም አንቺ ወደምትጓዢበት የህይወት መንገድ ሊጓዝ አይችልም…እንደዛ እንዲያደርግ አደረግሽ ማለት ማነቱን አጠፋሺው ማለት ነው…ማንም ሰው ደግሞ የራሱን ማንነት እስከወዲያኛው ማጣት ስለማይፈልግ የሆነ ቀን ማንነቱን ለማስመለስ መንፈራገጡ አይቀርም ..ያ ደግሞ እቤት ወደመሰነጣጠቅ እና ወደማፍረሰ ያመራል…፡፡
አየሽ ባልና ሚስት ቃልኪዳናቸውን አክብረው እስከወዲያኛው ለመኖር አንድ ነገር ላይ ብቻ ነው እኩል መስማማት ሚገባቸው ‹‹ጎጆችን የጋራችን ነው… የጓጇችንን ህልውና ሁለታችንም እኩል እንፈልገዋለን… ለዛም ስንል ሁል ጊዜ በጋራ ሆነ በየግላችን የተቻለንን እንጥራለን..…››ይሄ ነው ወሳኙ ጉዳይ… ቃላቸውን ለማክበር ሲሉ ይከባበራሉ..ይሄንን ቃል ለማክበር ሲሉ ይደማመጣሉ፣ይሄንን እውን ለማድረግ ሲሉ ሁሌ ሳይሰለቻቸው ይቅር ይባባላሉ….ለጎጇቸው ህልውና ሲሉ ሰጥቶ በመቀበል ፤ተሸንፎም ጭምር በማሸነፍ እኩል ይጥራሉ….
እና ትዳር ቀላል ነገር አይደለም…ባልና ሚስት ተባብሎ እጅ ለእጅ በመያያዝ በየድግስ ቤቱ ከመሄድ በላይ ነው፣ባልና ሚስት መሆን አንድ መሶብ ከመብላት እና አንድ አልጋ ከመጋራትም በላይ ነው…
ይሄን ጌዜ ከተማውን ለቀን ቃሊቲ ኬላ ጋር ደርሰናል..…እየነዳው ያለውት ወደ ዱከም ነው..አባቴ ጥሬ ስጋ ይወዳል..ዱከም ደግሞ በጥሬ ስጋ የምታውቁት ነው…አባቴ ንግግሩን ቀጥሏል፡፡
ትዳር የሚባለው ተቋም ሀገር ከሚባለው የጋራ ቤት ጋር ይመሳሰላል…አንድ ሀገር ውስጥም በጋራ ለመኖር ሀገሬን እወዳለው ብቻ ማለት በቂ አይደለም..ለሀገሬ ስል ሌላው ወገኔ የማይፈልገውን ግማሽ ፍላጎቴን በውስጤ ማክሰምን ይጠይቃል…፡፡በሀገርሽ መጮኸ ሲያምርሽ መጮኸ ትችያለሽ….ጩኸትሽ ግን ህፃናቶች አስደንግጦ ችግር ላይ አለመጣሉን እርግጠኛ መሆንና ለሌላውም መጠንቀቅን ይጠይቃል…፡፡የጋራ በሆነ ሀገር ውስጥ ሙሉ ነፃነት ሚባል ነገር የለም…ያንቺ ነፃነት የእኔ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ ገደብ ይበጅለታል … ህግ የሚባል ገደብ…፡፡ስለዚህ በጋራ ሀገር ውስጥ የጋራ የሆነ ህግ ማክበር ስንችል ነው የጋራ የሆነች ሀገራችንን ህልውና ማስጠበቅ የምንችለው…ሀገራችን እንወዳለን ምንለው በትክክል የሚሰራው በዚህ መንገድ ብቻ ስንጓዝ ነው…ካለበለዚያ እንደፈለኩ ካልተንፈራገጥኩ ምል ከሆነ ስንፈራገጥ የሌላውን ሰው አፍንጫ ላጣምም ስለምችል ችግር መፍጠሬ አይቀርም ፤እራሴ አብኩቼ እራሴ ካልጋገርኩ አይጣፍጥም የምል ከሆነ አይደለም በጋራ ሀገር በጋራ ቤት ውስጥም ከቤተሰቦቼ ጋር መኖር አልችልም… …ሀገሩን የሚወድ ዲሞክራት ሰው እቤቱ ለተደገሰ ሰርግ የሚከፍተውን የሰርግ ዘፈን የጎራቤቱን የሀዘን ሙሾ አለመረበሹን ማረጋገጥ እና መጠንቀቅ እንዳለበት በደንብ ማወቅ አለበት….
ከየትኛው ሀሳብ ተነስተን ምን ውስጥ ገባን….አባቴ ሁሌ እንዴህ ነው….አንድ ነጠላ ስለቤተሰብ የተነሳችን ሀሳብ ለጥጦ ለጥጦ ሀገራዊና አለማቀፋዊ ጉዳይ ማድረግ የተካነበት ነው…...
አሁን ገላን ደርሰናል … የመኪናዋ ነዳጅ አስተማማኝ ስላልሆነ መኪናዬን ወደቀኝ ጠመዘዝኩና ወደ ነዳጅ ማደያ ገባው …. አስተካክዬ በማቆም ሞተሩን አጣፋውና ጋቢናውን ከፍቼ ከመኪናው ወረድኩ ..ነዳጁን እስኪሞላ ውሀ ስለጠማኝ ለመግዛት ወደሱፐር ማርኬት ነው ሄድኩት ….ምፈልገውን ገዝቼ ወደመኪናዬ ስመለስ ግማሽ መንገድ ላይ ከፊቴ ማን ገጭ ቢል ጥሩ መሰላችሁ ….?እስኪ ገምቱ …?አለቃዬ…አቤት የደነገጥኩት ድንጋጤ…በትምህርት ሰዓት ፎርፋ ሆቴል ቁጭ ብላ ስትዝናና አባቷ እይታ ውስጥ የገባች ልጃገረድ ነው የመሰልኩት…
‹‹ደግሞ እዚህ ምን ትሰሪያለሽ..…?››እጁን ለሰላምታ እየዘረጋልኝ
የዘረጋልኝን ከሶፍት የለሰለሰ የሴት የመሰለ እጁን እየጨበጥኩ..በዛውም ይሄ እጅ ገላዬ ላይ አርፎ ቢዳብሰኝ ምን ሊሰማኝ እደሚችል እየገመትኩ ‹‹ወደዱከም እየሄድን ..ነዳጅ እየሞላው ነው…›› ብዬ መለስኩለት ..በእጄ ወደመኪናችን እየጠቆምኩ
ግራ እንደማጋባትም እያለ‹‹ማለት…? ከማን ጋር……?››እንዴ!! እንደቦይ ፍሬንዴ እኮ ነው ኮስተር ብሎ እየጠየቀኝ ያለው
‹‹የትርፍ ጊዜ ስራ ከሚያሰሩኝ ከአለቃዬ ጋር …በእረፍት ቀናቸው መኪና ስላማይነዱ እኔነኝ ምሾፍርላቸው… ››ውሸቱን ከየት እንደመጣልኝ አላውቅም… ቀባጠርኩ…
‹‹አንቺ የእረፍት ቀንሽ አይደለ እንዴ……?ደግሞ መኪና መንዳት እደምትቺይ አልነገርሺኝም››
‹‹አልጠየቅከኝም እንጂ ብትጠይቀኝ እንገርህ ነበር……የእረፍት ቀንሽ ላልከው ደግሞ ደሀ እረፍት ቀን አያስፈልገውም..በዛ ላይ እንደምታየው ሰውዬዬ ጮማ ናቸው…አንተ ልታባርረኝ አይደል እሷቸው ናቸው
👍1
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_አንድ



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍስሀ

ምን ነካኝ..? የዓመታት ፍቅረኛዬን
ከወንድ ጋር ስትዳራ እጅ ከፍንጅ የያዝኳት አይነት ስሜት ነው የተሰማኝ…የሆነ ውስጥ አንጀትን የሚያላውስ አይነት የመረበሽ ስሜት…የሆነ ልብን ድክም የሚያደርግ አይነት የፍርሀት ስሜት…የሆነ ያሳደጋችኃት ለማዳ ወፍ ከእጃችሁ አምልጣ ሰማዩ ተንሳፋ አድማሱን ሰንጥቃ ስትበርባችሁ በዛው ትቀር ይሆን.? ብላችሁ ስትሰጉ የሚሰማችሁ አይነት የእጦት ስሜት …
ሱፐር ማርኬት ልገዛ የመጣውትን ዕቃ ስለጠፋኝ እንደፈዘዝኩ ዝም ብዬ ባዶዬን ነው ወደመኪናዬ የተመለስኩ…... መኪናዬ ውስጥ ገባውና ሞተሩን አስነስቼ የመኪናዋን አፍንጫ ወደ አዲስአባ መለስኩት……
‹‹እንዴ ምን እየሆንክ ነው.?››
‹‹ይቅርታ ለስራ ጉዳይ ስለተደወለልኝ መመለስ አለብን››
‹‹እርግጠኛ ነህ.?››አለቺኝ….
‹‹ማነች እንደዛ ያለችህ.?›› እንዳትሉኝ…ፍቅረኛዬ ነች…ሳሮን ተስፋሁን ትባላለች፡፡አብረን ከሆን አንድ አመት አስቆጥረናል…የዛሬ አመት ለቫኬሽን ከውጭ የመጣው ጊዜ ነበር የተዋወቅነው…አንድ ወር እዚህ ስቆይ አብራኝ ነበረች..ከዛ ለትምህርቴ ወደውጭ ከተመለስኩ ቡኃላም በስልኩም በስካይፒውም ፍቅራችንን እንዲቀጥል ማድረግ ችለናል….አሁን ጨርሼ ከመጣው ቡኃላም እንደዛው…ዛሬ ወደ ደብረዘይት ለአዳር እየሄድን ነበር…. ዘና ብለን ለነገ ስራ በማለዳ ለመመለስ አቅደን ….ግን ይሄው ከቁጥጥር ውጭ በሆነ አደፍራሽ ስሜት ወደ አዲስአባ እየተመለስኩ ነው…..
‹‹እርግጠኛ ነህ ስትይ ….ምን ለማለት ነው.?››ጅራፍ ራሱ ገርፎ እራሱ ይጮኸል ይባላል ..ተቆጣሇት
‹‹የተደወለልህን ስልክ ታሰየኛለህ….?››
‹‹ማለት.? ››
‹‹ስከታተልህ ነበር …ምንም አይነት ስልክ ስታናግር አላየውም..ልጅቷ ማነች...?››
‹‹የቷ ልጅ.?››የምትለው ያልገባኘኝ መስዬ ጠየቅኳት
‹‹እንደዛ ያፈዘዘችህ ነቻ…ለዘመናት የጠፋችብህን ፍቅረኛህን በአጋጣሚ ያገኘህ ነው እኮ የምትመስለው….››
‹‹አትቀባጥሪ….››
‹‹አልተሳሳትኩም ማለት ነው….እንደው ወንዶች ሰትባሉ..››
‹‹በናትሽ አሁን ዝም ልትይልኝ ትቺያለሽ ..ምንም ነገር የመናገር ሙድ ላይ አይደለውም…››
‹‹እንግዲያውም አውርደኝ….››
‹‹የትነው ማወርድሽ.?››ገርሞኝ
‹‹እዚሁ አውርደኝ… ብቻዬን በትራንስፖርት ሄጄ አድሬ መጣለሁ…በስንት ዘዴ እና ውትወታ ቤተሰቤን አሳምኜ ያገኘውትን ከቤት ውጭ የማደር ዕድል ላባክነው አልፈልግም….››
‹‹እወነትሽን ባልሆነ.?››
‹‹እወነቴን ነው ..አውርደኝ አልኩህ እኮ…››አንቧረቀችብኝ
‹‹ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው ››ይላል የሀገሬ ሰው….ዳር ይዤ ፍሬኑን ጠርቅሜ ያዝኩና አቆምኩላት… ኮስሞቲኮቾን እና ቅያሬ ልብሶቾን ያጨቀችበትን ቦርሳዋን አንጠልጥላ ወረደች…ኪሴ ገባውና ለመዝናናት ይዥው የነበረ ከእሽጉ ያልተፈታ አምስት ሺ ብር እግሯ ስር ወረወርኩላትና መኪናዬን አስፈንጥሬ ተፈተለኩ……
ከዛ አዳሬን አትጠይቁኝ…ጥዋት አንድ ሰዓት ተኩል ቢሮ ነበርኩ..ስደርስ ፅዳቶች እንኳን ስራቸውን አላጠናቀቁም ነበር… አግኝቼ እስካናግራት ቸኩያለው አይገልፀውም…ደግሞ ሳይቸግረኝ ቅዳሜ ለት ከስራ መሰናበቷን የሚገልፅ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፈርሜ ነበር….እርግጥ ከሰዓት ሰራተኞች ከወጡ ቡኃላ ስለፈረምኩ ዛሬ ነው የሚደርሳት…ግን እንዴት አድርጌ ማስተካከል እችላለው.. .?መዝገብ ቤት የሚሰሩት አስተዳዳሪውም ጭምር ደብዳቤውን አይተውታል… በውሳኔው የሚዋልል አሐቃ ደግሞ ማንም አያከብረውም….እንደዛ እንዲያስቡኝ ፈፅሞ አልፈልግም….፡፡ ግን ደግሞ የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ…፡፡ብትከሰኝ ጥሩ ነው.. ግን እንዴት ጥሩ ሊሆን ይችላል...?አውቄ ልሸነፍላት ማለት ነው.? ….እሱም ሌላ ጣጣ አለው..‹ በክስ አሸንፍው ተመለሰች› መባሉ ሌላ ውድቀት ነው….አዳሜ ትንሽ በነካዋት ቁጥር ወደክስ እንድትበር መንገድ ማሳየት ነው….፡፡ይልቅ ይቅርታ እዲደረግላት ደብዳቤ ብታስገባ ጥሩ ነው…፡፡አዎ እንደዛ እድታደርግ በዘዴ አግባባታለው…ግን ሳስበው እሷ እንደዛ አታርግም …በፍጽም አንገቷን እንዲህ በቀላሉ የምትደፋ አይነት ልጅ አይደለችም ….
የባጥ የቆጡን ሳስብ 3 ሰዓት ሆነ ..ፀሀፊዬን ጠራዋትና ፌናንን እንድትጠራልኝ ነገርኳት…. ደወለችና….እንዳልገባች ነገረችኝ››
‹‹ምን ማለት ነው … 3 ሰዓት ድረስ አለመግባት….?››ፀሀፊዬ ላይ ነው የጮህኩት
‹‹እኔ እንጃ...?በሞባይሏ ልደውልላት››አለቺኝ እየተሸቆጠቆጠች…፡፡
‹‹አይ ተያት ..እሷን በተመለከተ የተፃፈ ደብዳቤ ከመዝገብ ቤት ታስመጪልኛለሽ.?››
‹‹ቆይ እኔ እራሴ ላምጣ ››ብላ ሄደች
ከሶስት ደቂቃ ቡኃላ ተመልሳ መጣችና ደብዳቤውን እየሰጠቺኝ ‹‹…ያመጣውት ቀሪው ነው ..ዋናውን ፈርማ ወስዳዋለች››አለቺኝ
‹‹ማን ነች የወሰደችው.?››..ሳላስበው ከመቀመጫዬ ተነሳው
‹‹ፌናን ነቻ››
‹‹ምን ጊዜ ወሰደች….? ቅዳሜ ከሰዓት ነበር እኮ የፈረምኩት …ለማንኛው አመሰግናለው..››ብዬ ፀሀፊዋን ሸኘዋትና አስተዳዳሪው ጋር ደወልኩ
‹ደህና አደርክ አቶ ፍሰሀ››
‹‹ሰላም ነኝ..ፌናንን ፈልጌያት ነበር››ቀጥታ ወደ ጉዳዬ ገባው….
‹‹አልገባችም ››
‹‹አልገባኝም ማለት.?››
‹‹ምትገባ አይመስለኝም …..ያው የተሰናበተችበትን ደብዳቤ ወስዳለች..››
‹‹ትውሰዳ..ዝም ብላ ደብዳቤ ተቀብላ መቅረት ትችላለች እንዴ...?ፎርማሊቲ ምናምን ሚባል ነገር የለም….?››
‹‹አይ ፍቃድ ሞልታለች..እንደዛ እንዲሆን መሰለኝ የተነጋገርነው››
‹‹ከምኔው እንዲህ ተዋክባ ሞላችው.?››
‹‹እኔም አልገባኝ አቶ ፍሰሀ …ደብዳቤውን ጥዋት ስገባ ጠረጳዛዬ ላይ ነው ያገኘውት››አሉኝ እየታዘብኝ መሆኑን በሚያሳብቅባቸው ቃና….
ስልኩን በንዴት ጆሮቸው ላይ ጠረቀምኩት ..እስቲ እሳቸው ምን አደረጉኝ…..
…..መልሼ የጠረጳዛውን መጥሪያ ተጫንኩ…ፀሀፊዬ መጣች…‹‹አቤት ፈለከኝ››
===
‹‹ደውይላት… ሞባይሏ ላይ ደውይላት …››ተመልሳ ሄደችና ሞባይሏን ይዛ መጥታ እያየዋት መሞከር ጀመረች… ትግስቴን በሚፈታተን ሁኔታ ደግማ ደጋግማ ሞከረች…‹‹ጥሪ አይቀበልም ነው ሚለው..ሁለቱም ሲሞ አይሰራም››
‹‹የቤት ወይም የጓደኛ ስልክ የላትም.?››
‹‹እኔ አላውቅም ..ወይ የሚያውቅ ሰው ካለ ልጠይቅልህ….?››ግራ ግብትብት ያላት ፀሀፊዬ መፍትሔ ያለችወን ሀሳብ አመጣች…››
‹‹አይ ተይው..አመሰግናለው…››ሸኘዋት
‹‹ምን እሆንኩ ነው ….?እዚህ ቢሮ ስራ ከጀማርኩ ሁለት ሳምንቴ ነው…፡፡በሁለት ሳምንት ብቻ የማውቃት ሴት እንዴት እንዲህ ውስጤን የማተረማመስ አቅም ኖራት….?ነው ወይስ ከእኔ ዕውቅና ውጭ ለዘማናት በውስጤ በስውር የኖረችበት የተፈጥሮ ምትሀታዊ ሚስጥር ይኖር ይሆን...?አይ እንደዛም አይሆንም አሁን እሷን መፈለግ ነው ወይስ በድያታለው ብዬ ስላሰብኩ መፀፀት የወለደው የጥፋተኝነት ስሜት ነው እንዲህ የሚያደርገኝ….?.በቃ አንዴ ላግኛትና አዋርቻት ይቅርታ ከጠየቅኳት ቡኃላ ይሄ ስሜት ይተወኛል…፡፡አዎ እርግጠኛ ነኝ ይተወኛል…››እራሴን ለማፅናናት ብዙ ጣርኩ…መልሼ የጠረጳዛዬን መጥሬያ አንጫረርኩ..የፈረደባት ፀሀፊዬ በፍጥነት መጣች
‹‹ፋይሎን ታመጪልኝ.?››››
‹‹የማንን.?››
‹‹ሌላ የማን ይሆናል .. .?የፌናንን ነዋ››
…‹‹እሺ›› ብላ ሹክክ ብላ ወጥታ ሄደች
‹‹ሰውዬው አረ ተረጋጋ….አሁን ይህቺ ምስኪን ምን አደረገችህ ….?›› እራሴን ለመገሰጽ ሞከርኩ…ይዛልኝ መጣችና አስረክባኝ ወደ ቦታዋ ተመለሰች …
‹‹ፋይሏን ገልጬ ማየት ጀመርኩ…ዝም ብሎ ስሜቴ ስለገፋፋኝ ወይንም ግራ
😁2👍1👏1
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ሁለት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍስሀ
መፅሃፍ መደብሩ ቆሜያለሁ ነገረ ስራዋን በአትኩሮት እየተከታተልኩ ነው፡፡
ገዢው የሆነ መፃፍ ርዕስ ነገሯት
‹‹እንደዚህ የሚባል መጽሀፍ አለሽ.?››ጠየቃት
‹‹አለኝ ግን ለምን ፈለግከው?››
‹‹አልገባኝም?ልገዛሽ ነዋ.?››
‹‹እሱማ ልትገዛኝ ነው ?ለምን መጽሀፉን ልትገዛው ፈለክ ነው ጥያቄዬ?››
‹‹ለምንስ ብፈልገው አንቺ ምን ይመለከትሻል ?ካለሽ ሽጪልኝ ከሌለሽ የለኝም በይ››
‹‹ስኳር ወይ ሳሙና አይደለም የምትገዛው፤ መጽሀፍ ነው..፡፡መጽሀፍቶች ደግሞ ሳያነቡ የሚያነቡ ለመምሰል ታቅፈዋቸው የሚዞሩ ከንቱዎች እጅ እንዲገቡ አልፈልግም በተለይ እንደጠየቅከው ያለ መጽሀፍ……..፡፡ይሄውልህ እዛ አካባቢ በመደዳ መጽሀፍት ቤቶች አሉ ካላቸው ምክንያት ሳይጠይቁ ይሸጡልኸል….ደህና ሁን››ብላ አሰናበተችው፡፡
ሰውዬው በመገረም እያጉረመረመ ጥሏት ሄደ ..ዞር ስትል እኔን አየቺኝ
‹‹እንዴ አለቃ ምን እግር ጣለህ...?መፅሀፍ ልገዛሽ ነው እንዳትለኝ…?››አለች በመጠኑ ፈገግ ብላ
‹‹ለመሆኑ የትኛው የዋህ ነጋዴ ነው ለመክሰር አንቺን እዚህ ያቆመሽ….?››የእወነቴን ነበር የተናገርኩት
‹‹የሚተማመንብኝ››
‹‹እንዲ ደንበኛ እያበሳጨሽ እያባረርሽበት ነው የሚተማመንብሽ…››
ልትመልስልኝ አፎን ስታስተካክል አንድ ሽበት የወረራቸው ደስ የሚል ግርማ ሞገስ ያላቸው ግን ደግሞ ጎስቆል ያሉ አዛውንት ድምጽ በመሀከላችን ገባ ?››
‹‹ደህና ነሽ የእኔ አለም….?››
‹‹ደህና አደሩ..እንዴት ኖት? ጤናዎትስ?››እኔን ከማውቃት ተቃራኒ በሆነ እርብትብት ትህትና እየተፍለቀለቀች እና እየፈገገች በጋለ ሰላምታ ተቀበለቻቸው፡፡ሰው እንዴት እንዲህ ሁለት ገፃ ይኖረዋል?
‹‹….ሰላም ነኝ ልጄ…፡፡ይመስገነው፡፡››
‹‹አኔ እኮ ሲጠፉብኝ ያመሞት መስሎኝ ሰግቼ ነበር››
‹‹አይ ደህና ነኝ.ባለፈው ያስቀመጥሺልኝን መጽሀፍ ልጆቹ ሰጥተውኝ ወስጄ ነበር..እና መጻሀፎ ስለመሰጠቺኝ ከቤት መውጣት አልቻልኩም ለዛ ነው የጠፋሁብሽ››
‹‹ጨረሱት?››
‹‹ጨረሱት..ሁለት ጊዜ ነው ደግሜ ያነበብኩት…አሁንም አንዴ የምደግመው ይመስለኛል..››
‹‹ስለወደዱት ደስ ብሎኛል..አሁንም ያዘጋጀውሏት መጽሀፍ አለች›› ብላ ከተቆለሉት መጽሀፎቶች ጀርባ እጆን ሰደደችና አንድ ልባሱ አርጀት ያለ መጽሀፍት አውጥታ ሰጣቻቸው ፡፡በመንሰፍሰፍ ተቀበሏት እና ርዕሱን አገላብጠው ካነበብ ቡሃላ እሷን ወደ ራሳቸው ጎትተው ግንባሯን ከሳሟት ቡኃላ ‹‹ ስንትነው የእኔ ልጅ .?››ጠየቋት
‹‹ሁለት መቶ ሀምሳ ብር ነው የገዛውሎት››
ቀኝ የካፖርት ኪሳቸው ገቡ…የሆነ ባለአስር ብር ዝርዝር ብሮች አወጡ..የካፖርታቸውን ኪስ ከፈቱና ደረት ኪሳቸው ገቡ ሳንቲም ሳይቀር ያለቸውን ብር ከየኪሳቸው እያወጡ ባንኮኒው ላይ ዘረገፍት.በትኩረተ ስከታተላቸው ነበር…ቢቆጠር ከመቶ ምናንም ብር አይበልጥም ቢያንስ የጠየቀቻቸውን ግማሹን አይሸፍንም
‹‹ልጄ በዚህ ላይ አንቺ ሙይልኝ…››አሏት…የልመና ሳይሆን የትዕዛዝ ቃና ባለው የመተማመን ስሜት
‹‹.አይ ይሄ ልጅ የእርሶ አድናቂ ነው… ገና ሲመጡ አይቶት የሚወስዱትን መፃሀፍን እኔ ነኝ የምከፈለው.. አደራሽን እንዳተቀበያቸው ሲለኝ ነበር..አይደል ፍሰሀ?››አለቺኝ ወደእኔ ቀና ብላ አፍጥጣ እያየቺኝ
‹‹አዎ…እባኮት እልኩና ወደኪሴ ገብቼ ዋሌቴን በማውጣት በግምት አንድ ሺ ምናምን ብር ይመስለኛል አወጣውና ይሄው ብሩ የሚችለውን አይነት የሚፈልጉትን መጽሀፍ ስጭልኝ….››
<<አላልኮትም ››አለችና የእሳቸውን ብር ከባንኮኒው ሰብስባ ኪሳቸው መልሳ ጨመረችላቸውና…
‹‹ሌላ ምን ምን መፃሀፍ ነው የሚፈልጉት….?››
‹‹ያው የመጽሀፍ ምርጫዎቼን ታውቂ የለ.››
…ስድስት ወይም ሰባት የሚሆኑ መጻሀፎችን መረጠችና በፔስታል አድርጋ ሰጠቻቸው
ሰውዬው ከመሄዳቸው በፊት ወደእኔ ጠጋ አሉ..ብዙ ምርቃት እንደሚያዘንቡብኝ እየጠበቅኩ ነው…‹‹እነዚህን መፃሀፎች አንብቦ ለመጨረስ ሁለት ወር ያህል ይፈጅብኛል…ለቀጣዬቹ ሁለት ወራት እንድኖር የሚያስችል ምክንያት ሰጠተኸኛል ማለት ነው..ምክንያቱም እኔ በምንም አይነት ሁኔታ እጄ ላይ ያሉ መጽሀፎቸን አንብቤ ሳልጨርስ አልሞትምና.››አሉኝ ..ምን ለማለት እንደፈለጉ አልገባኝም..ይህቺ ልጅ ግራ አጋቢ የሆነችው ከእንደዚህ አይነት ግራ አጋቢ ብኩኖች ጋር እየኖረች ነው ስል በውስጤ አሰብኩ.. ሽማግሌው ወደፌናን ዞረው ‹‹የእኔ ትንሽ መላአክ ደህና ሰንብቺልኝ..››ብለው ፊታቸውን አዙረው የመጽሀፍ መደብሩን ለቀው ወጡ
‹‹ምትገርሚ እብድ ነሽ.ለማላውቃቸው ሰው መጽሀፍ ታስገዥኛለሽ…ደግሞ ባዋርድሽስ.?››
‹‹ምን ብለህ ነው የምታዋርደኝ.?››
<<መች አልኩሽ .?››ብልሽስ
‹‹አትልማ ..ለራስህ ያለህን ግምት በደንብ አውቃለው..››
<<እንዴት ነው ምታውቂው ….?በጣም ጉረኛ ነሽ…?ዘመድሽ መስለውኝ ነው..ደግሞ ደስ የሚሉ አዛውንት ናቸው.የሚያነብ ሰው እወዳለው ለዛ ነው…›› አልኩ ቀጥሎ በመሀከላችን ለሚፈጠረው ነገር ጥሩ ስሜት እንዲፈጠር ና ንግግራችን እንዳይከር እየፈራው
‹‹ ማን መሆናቸውን ታውቃለህ?››
‹‹እኔ እንጃ .በምን አውቃለው ፡፡ካለዛሬም አይቻቸው አላውቅም..እዚህ ቦታም ስገኝ የመጀመሪያ ቀኔ ነው››
እንግዲህ እንደዛ እንድታደርግ እድሉን ስላመቻቸውልህ አመስግነኝ…ምክንያቱም ለእሷቸው መፅሀፍ መግዛት ብዙ ሰዎች ቢፈልጉም እድሉን አያገኙምና›› ብላ ማንነታቸውን ነገረቺኝ… ነዘረኝ ከሰማዩ የሚከብድ ስም ያላቸው..ለኢትዬጵያ ብዙ የሰሩ ፤ ብዙ መጽሀፍ የጻፉ ታላቅ ደራሲ ናቸው..አፍሬ አፌን ያዝኩ.ማንነታቸውን ቀድሜ ባውቅ ኖሮ መፅሀፍ ልግዛሎት ብዬ ገንዘብ ከኪሴ ለማውጣት ድፍረት ሚኖረኝ አይመስለኝም
‹‹ስማቸው እና ኪሳቸው ምነው እንዲህ ተራራቀ.››ብዬ የገረመኝን ጥያቄ ጠየቅኳት
‹‹ስማቸውን እኮ በአዕምሮቸው እንጂ በኪሳቸው አይደለም ያገኙት…እሳቸው ለቁሳዊ ሀብት ብዙም ግድ የላቸውም ..ከሚጠቀሙት በላይ ገንዘብ ኪሳቸው እዲከርም አይፈልጉም..ግን አንዳንዴ እንደዛሬ ቀን የሚፈልጉት መፃሀፍ የሚገዙበት ብር ሲጎድላቸው ይበሳጫሉ..››ብላ ልታስረዳኝ ሞከረች፡፡
‹‹ሚገርም ፅናት ነው››አልኩኝ
‹‹ አዎ ነው..አንተ ግን ምን ፈልገህ እዚህ ድረስ መጣህ .?ነው እግረመንገድህን ስታልፍ ድንገት አይተኸኝ ነው?››አለችኝ ኮስተር ብላ..ሞባይሌን ከፈትኩና ሰዓቱን አየው..አምስት ሰዓት ከሩብ ይላል
‹‹ምሳ ልጋብዝሽ ነው አመጣጤ…ምሳ ስንት ሰዓት ነው መውጣት የሚፈቀድልሽ….?››
‹‹ምሳ ምሳ...?››
‹‹አዎ ምሳ..››
ስልኳን አወጣችና ደወለች…‹‹ቶሎ ና ልወጣ ነው…››ብላ መልሳ ዘጋችው…
‹‹የሚቀበለኝ ልጅ እስኪመጣ መኪና ውስጥ ጠብቀኝ ከአስር ደቂቃ ቡኃላ መጣለው››እንዲህ በቀላሉ እሺ ትለኛች ብዬ እልጠበቅኩም ነበር…ሀሳቧን እንዳትቀይር ‹‹እሺ አመሰግናለው›› ብዬ እንደህጻን በውስጤ እየቧረቅኩ በፍጥነት ወደ መኪናዬ ተመለስኩና መሪውን ከሹፌሬ ተቀብዬ እሱ በታክሲ ወደቢሮ እንዲመለስ ልኬው እሷን መጠበቅ ጀመርኩ…ስለእሷ እያሰብኩ…ስንት ሰው እንደሆነች እያሰላው...ከሳምንት በፊት እኛ ካምፓኒ ነበር የምትሰራው…ከዛ ሹፌር ሆና ስትሰራ አገኛዋት አሁን ደግሞ የመፃሀፍት መደብር ሻጭ..ህይወቷን እንዴት እዴት ነው ጢቢ ጢቢ እየተጫወተችበት ያለው.?መስመር የሚያሲዛት ቤተሰብ የላትም ማለት ነው….?እስቲ ትምጣና ለዚህ ሁሉ ጥያቄዎቼ መልስ ትሰጠኛለች….

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ሦስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


...ሆቴል ፍለጋ ብዙም አራቅንም ..እዛው ዞር ብለን ዋቤ ሸበሌ ነበር የገባነው…እንደተቀመጥን ነው የምንበላውን በማዘዝ ወደጭቅጭቃችን የገባነው…እኔን ፍለጋ ይሄን ያህል መንገድ ይጓዛል ብዬ አልገመትኩም ነበር…እርግጥ ነገሮችን በፍጥነት እንዲህ እንዲሆኑ አድርጌ ስልኬንም፤ አድራሻዬንም አጠፋፍቼ ከመስሪያ ቤቴ የጠፋውት አውቄ ነው …ለእሱ የማሰቢያ እና የመረጋጊያ ጊዜ እንዲያገኝ በማሰብ ….እንጂማ ስራዬን እሱ ስላለ መልቀቄ አይደለም..እንደዛማ አይታሰብም…ሰው በገዛ ግዛቱ ውስጥ በታነፀ ቤተመንግስት ሊነግስበት ያሰበውን ወንበር ሌላ ተቀናቃኝ ልቀቅ ስላለው በቀላሉ ይለቃል…አይ በፍፁም ይሄ የነገስታት ባህሪ አይደለም..እሱ በንግስናው ኃይል ተማምኖ ወግጂልኝ ቢለኝ እኔ በቀላሉ ምኞቱን ላሳካለት አልችልም..ምክንያቱም እኔም ከእሱ እኩል ኃይል ያለኝ ንግስት ስለሆንኩ…
‹‹እኔን ፍለጋ እንዲህ መባከንህ አስደስቶኛል››አልኩት
‹‹ጉረኛ አትሁኚ… ስለአንቺ አንዳንድ ነገር ሳጣራ ከበፊትም ጀመሮ በካምፓኒው አንቺን በተመለከተ ያለው ነገር ትክክል ስላልመሰለኝ ያንን ለማስተካከል ነው..የአንድ አዲስ መሪ ስራ የወደፊት የካምፓኒውን አካሄድ ማስተካከል ብቻ ሳይሆን ወደኃላም ተመልሶ በባለፍት መሪዎች አላግባብ የተሰሩ ስራዎች ካሉ ለእነዛ እርማት እንዲደረግ ማሰድረግም ጭምር ነው…
‹‹ስለመሪነት ጥሩ ግንዛቤ እያገኘህ ነው››
‹‹አዎ…አስተዳደግሽ፤ የቤተሰቦችሽ ሁኔታ እና የህይወት ገጠመኞችሽ የፈጠሩብሽ ተፅዕኖ እንዳለ ሆኖ ካምፓኒያችንም ላንቺ የሰጠው ቦታ ለህይወትሽ መበላሸት አንድ አስዋፅኦ እንዳበረከተ ተሰምቶኛል..እኔም ነገሩን በደነብ ሳላጣራ በእሳቱ ላይ ቤንዚል ጨመርኩበት››አለኝ እጆቹን እያፍተለተለ…አይገርማችሁም አንዳንድ ሰው ወደ ህይታችሁ ድንገት ከመንገድ ጎራ ብሎ ይገባና ገና በሁለት እግሩ እንኳን ተስተካክሎ ሳይቆም አፍርሼ ልስራችሁ ይላል፡፡
‹‹ያው ቸኩሎ መፍረድ የአንተ ብቻ ሳይሆን…የእኛ ኢትዬጵያውያን ዋና ችግር ነው.. ለወሬ ያለን ፍቅር ለራሳችን ካለን ፍቅር በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡እንደህዝብ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ ተምረዋል በሚባሉት የህብረተሰብ ደረጃ ጨምር የ<critical thinking >ልምምድ የለንም… የሆነ ውሳኔ ላይ ከመድረሳችን በፊት የሰማነውን ወሬ ‹‹ለምን?›› ‹‹እንዴት?›› ‹‹የት?›› ‹‹ መቼ?›› ብለን በመጠየቅ የነገሩን ብልት በታትነን የማየት የምናደርገው ጥረት ለዜሮ የቀረበ ነው፡፡የሰማነውን ወሬ ወይም መረጃ በዚህ መጠን መመርመር ደግሞ የመረጃዎችን ጥራት ለመጨመር..እርግጠኝነቱን አስተማማኝ ለማድረግ እና እወነተኝነቱን በአስተማማኝ መንገድ ለማረጋገጥ ወሳኝ መንገዶች ናቸው፡፡ እኛ ግን እንደዛ አናደርግም…በዛም ምክንያት ውሳኔያችን ቡዙ ግዜ የጥድፊያና በስህተት የተሞላ ነው››አልኩት… ከገባው ብዬ
‹‹አዎ ትክክል ነሽ››አለኝ ኮራና ጀነን ብሎ
‹‹አየህ አሁንም ተሳሳትክ..ትክክል መሆኔን እንዴት በዚህ ቅፅበት ልታረጋግጥ ቻልክ….?››
ግራ ገባውና ‹‹ማለቴ….››ብሎ ሊያብራራልኝ ሲሞክር መልሼ ጣልቃ ገባውና
‹‹ግዴለም ብታስረዳኝም አታሳምነኝም..ይልቅ ህይወቴ እንደተበላሸ ስትናገር ነበር…እስቲ እንዴት እንዲያ ልታስብ እንደቻልክ አስረዳኝ..….?››
‹‹ይሄ ምን ማስረዳት ያስፈልገዋል…በዛ ነጥብ ዲግሪ ተመርቀሽ በትንሽ ደሞዝ በፀሀፊነት እየሰራሽ ነው..በቀደም አያትሽ ከሚሆን ሰው ጋር አግኝቼሻለው…ዛሬ ደግሞ ተራ የሽያጭ ሰራተኛ ሆነሽ መጽሀፍ ስትቸረችሪ ነው ያገኘውሽ…ህይወትሽ እርጋታ የሌለው ምስቅልቅሉ የወጣ ነው….ከዚህ በላይ የህይወት መበለሻሸት ከየት ይመጣል››በቃ በእሱ ቤት የእኔን ህይወት ብጥርጥር አድርጎ አጥንቶ ጨርሶል..
‹‹እውነት ግን ምንድነው ….?››ጠየቅኩት
ግራ ተጋባ‹‹….ምን አልሺኝ….?››
‹‹እውነት ምንድነው..….?››ፍጥጥ ብዬ ጥያቄዬን ደገምኩለት
‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው….….?እውነት ሀቅ ነው…በትክክል የተተገበረ ወይም የተነገረ ክንውን ነው..በቃ ይሄው ነው፡፡››
‹‹እሱ ብቻማ አይደለም…እውነት እረቂቅ ነው..እውነት ጥልቅ ነው…የሰማህው ነገር ሁሉ እውነት ሊሆን አይችልም..ለምን ይመስልሀል እኔ እና አንተ አንድ አይነት ነገር ከአንድ ሰው በእኩል ሰዓት ብንሰማ የምንረዳበት መንገድ አንድ አይነት ሊሆን አይችልም…ምክንያም ሁለታችንም በየራሳችን አዕምሮ ተጠቅመን ነው ተርጉመን ነገሩን ለመገንዘብ የምንጥረው…..ስንተረጉም ደግሞ የበፊት የህይወት ልምዳችን..የምንከተለው የሀይማኖት አይዲኦሎጂ፤ ከተወለድንበት አካባቢ ማህበረሰብ የቀሰምነው ባህል፤ የራሳችን ፍላጎት…..እነዚህና ሌሎችም በአተረጋጎማችን ላይ የየራሳቸውን ስውር ተፅዕኖ ያሳድራብናል…… የሰማነው እውነት በግማሽ ይበረዛል ማለት ነው…ያየነውም እንደዛ..፡፡ሌላ ምሳሌ ልስጥህ የአንድ ወጣት ልጃገረድ ፎቶን ሶስት ወጣት ወንዶች ቢያዩት እና ከሳዕታት ቡኃላ ምን እንዳዩ ቢጠየቁ..አንድ የተቀሰረ አስጎሚዥ ጡቶች ያላት ወጣት ይልሀል…ሌላው የሚያምረ መቀመጫ ያላት ሞዴል መሆን የምትችል ወጣት ይልሀል…ሌላው ደግሞ የሚያምር ቁንጅና ያላት ግን ልቧ በሀዘን የተሰበረ፤የእኔ ያለችውን ነገር በመጠበቅ በናፍቆ እየተሰቃየች መሆኖን አይኖቾ ውስጥ ያጋቱት እናባዋ የሚመሰክሩ ፤ ግን ደግሞ ያልሸነፍ ባይነት እና የራስን ስሜት የመቆጣጠር ጥረት በፊቷ ላይ የሚነበብባት፤ከዕድሜዋ በላይ የምታውቅ ወጣት ነች ይላል፡፡አየህ ሶስቱንም አስተያየት ሰጪዎች አንድ አይነት ስዕል ከአንድ አይነት እርቀት ላይ አይተው የተረዱት ነገር የተለያየ ነው፡፡እውነቱ የማናኛቸው ነው…….?አየህ እውነት እንደሽንኩርት ነው ሚባለው ለዛ ነው…በላጥከው ቁጥር ሌላ አዲስ ነገር..አሁንም ስትልጠው ሌላ ሚስጥር…..አንዳንዴማ ማብቂያ ሁሉ ላይኖረው ይችላል….ጲላጦስ እኮ እኔ ማውቀው አለማወቄን ነው ያለውም አንድም ለዛ ነው….ያወቀ የመሰለው ሁሉ እሱ ገና ጀማሪ ተማሪ ነው….
‹‹ወይ አንቺ ልጅ…እያወራን የነበረውን ቁም ነገር እኮ አወሳስበሽ ድራሹን አጠፋሽው….››
‹‹አይ አሁን ያወራውት ነው ትክክለኛው ቁም ነገር….አየህ የእኔ ህይወት ብልሽትሽት ማለቱን ለመወሰን በአንድ ሰምንት ውስጥ ያየሀቸው ወይም የሰማሀቸው ቅንጭብጫቢ ታሪኮች ላንተ በቂዎች መሆናቸው አስገራሚ ነው››
‹‹እኛ ካምፓኒ በፀሀፊነት እንደምትሰሪ ማንም ተናገረው ማንም እውነት ነው…..በቢዝነስ ማነጅመንት ዲግሪ እንዳለሽም አንቺ እራስሽ አትክጂም…ሹገር ዳዲሽንም በአይኔ ነው ያየውት››
በዚህ ጊዜ ምግቡ ቀርቦልን እየበላን ነበር እያወራን ያለነው..ሁሉን ነገር ጨርሶ ሳያውቅ እንደአወቀ የሚያወራው ነገር ብሽቅ አደረገኝ ‹‹ሌላውን ተወው ….ሹገር ዳዲዬ መሆኑን በምን አረጋገጥክ…….?››
‹‹አይቼሻለው አልኩሽ እኮ..አንቺም አረጋግጠሽልኛል…››
‹‹ዋሽቼህ ቢሆንስ…….?››
‹‹በምን ምክንያት ትወሺኛለሽ ….?››
‹‹ላስቀናህ ፈልጌ››
ሳቁን ለቀቀው…
‹‹ምን ያስቅሀል….?››
‹‹ለምን ብዬ ቀናለው…አፈቅሬሽ ነበር እንዴ….?››
‹‹እኔ እንጃ… ሰው አንድ ሰውን ላይ ካለምክንያት ትኩረት ካደረገና ምክንያት እየፈለገ ጥዋትና ቀን የሚነጫነጭበት ከሆነ ያው በእኔ ግምት ፍቅር ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡››
‹‹እንደ ህይወትሽ ለራስሽ ያለሽ ግምት የተዘበራረቀ ነው…አንዳዴ መሬት የሚወረድ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰማይ ላይ ልንጠልጠል የሚል…›› አለኝ …በመበሳጨትና ስሜቱን ለመቆጣጠር በሚጥር የስሜት መደበላለቅ
‹‹እሺ ተሳስቼ ይሆናል..ለምን
👍1
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_አራት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


‹‹ሁለተኛው ቢሮ በሰራተኛ አስተዳደር አንድ ኤክስፐርት ለመቅጠር ይፈልጋሉ…እዛ ቦታ እንድታመለክቺ ልመክርሽ ነው…››
‹‹እንዴ!!! በስነምግባር ጉድላት ከስራው የተባረረ ሰው እኮ መልሶ መዋዳደር እንደማይችል ይታወቃል..ለዛውም ከበፊቱ ከፋ ባለ የስራ መደብ….?››
‹‹ግድ የለሽም በማነጅመንት እናየዋለን…ያ ውሰኔ የእኔ የግሌ ነበር..እንደውም ባንቺ መባረር ማናጅመንቱ ብዙም ምቾት አልተሰማቸውም..ስለዚህ አንቺን ለመመለስ ብዙም አያንገራንግሩም..››
‹‹አንተስ.?››አልኩት በብልጣ ብልጥነቱ ተደምሜ..
‹‹እኔ ድምፀ-ተአቅቦ አደርጋለው….በእነሱ ድምጽ መልሰሽ በሚገባሽ ቦታ ትቀጠሪያለሽ..ህይወትሽ ይስተካከላል….ግን ቅድመ ሁኔታ አለው››
‹‹ምን ?የፍቅር ጥያቄ እንዳይሆን››
‹‹ቢሆንስ?››አለኝ ፊቱን ጨምድዶ
‹‹አይ እንቢ ስለማልልህ ይቅርብህ ልልህ ነው››
በግርምት አፍጥጦ ለደቂቃዎች አየኝና ‹‹እያስፈራራሺኝ ነው…….?››
ማስፈራራት አይደለም.. ለእኔ ፍቅር ማለት መላላስ እና መወሳሰብ አይደለም…ሁሌ አድቬንቸር ነው…ሁሌ ሚተረመመስ ነገር ፈልጋለው…››
‹‹ግን .ጤነኛ አዕምሮ ነው ያለሽ...?እንዴት ሰው የሚተረማመስ ነገር ያስደስተዋል.?››
‹‹አየህ የተረማመሰውን ነገር በጥበብ ሳስተካክል የሚሰማኝ የአሸናፊነት እና የውጤታማነት ደስታ ነው የፍቅር እርካታዬ…ሁል ጊዜ በፍቅር ውስጥ ጌም እንዲኖር እፈልጋለው…ላሸንፍም ልሸነፍም እችላለው..ዋናው ሁል ጊዜ ምጫወተውን ማጣት የለብኝም …ጥሩ ቁማርተኛ ካልሆንክ ከአኔ ጋር በፍቅር መዝለቅ አትችልም እና ይቅርብህ ብዬ ልመክርህ ነው፡፡››
‹‹ምን ጉድ ነሽ በፈጣሪ…እኔ ቅድመ ሁኔታ ያልኩት አንድ ከዛ ከሹገር ዳዲሽ ጋር ያለሽን ፍቅርም ሆነ የስራ ግንኙነት ታቆሚያለሽ ልልሽ ነው..ሌላው እዚህ መፃሀፍት መደብርም ያለሽን ስራ እንደዛው….
‹‹ያስቃል..››አልኩት..እውነትም ገርሞኝ
‹‹ምኑ ገረመሽ?››
‹‹በዚህ ምድር ላይ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ .. givers , takers , matcher ይባላሉ፡፡ < givers > ምንም ነገር ሲሰጡህ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ነው…ሲያፈቅሩህ የእነሱን ማፍቀር ብቻ እንጂ የእነሱን መፈቀር አለመፈቅር አያስጨንቃቸውም..ሲለግሱህም ከአንተ በመልሱ ምንም የሚጠብቁት ነገር የለም…እንደዚህ አይነት ሰዎች የአለም በጣም ደሀ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ ግን ሰማያዊ ስብዕና ያላቸው ናቸው… በተቃራኒውም የአለም በጣም ሀብታሞቹና ባለትልቅ ገቢ ባለቢቶችም እንዚሁ < givers > የሚባሉ ሰዎች ናቸው..ምክንያቱም ለአበባ ያደረጉት በእጥፍ ከሰለሞን ይደረግላቸዋል…ይሄ የተፈጥሮ ህግ ነዋ፡፡‹‹ለማታውቀው ወገንህ አንድ ስትሰጥ ከማታቀው ዘጠኝ ተጭምሮ አስር ሆኖ ይመለሰልሀል…›› የሚለው ዋና መመሪያቸው ነው..እነእየሱስ ፤ ነብዩ ሙሀመድ፤እነማዘር ትሬዛ..እነአበበች ጎበና እነሲስተር ዘቢደር፤ማህተመጋንዲ፤ማንዴላ ወዘተ …እነዚህ ዝም ብለው በነፃ ሲሰጡ በመኖራቸው ሀብታምነትን ብቻ ሳይሆን በታሪክ ማህደር ዘላለማዊነትንም የተጎናፀፈ ናቸው….
ሌላው‹‹ takers› የሚባሉት ናቸው …ከሌላው መቀበልን ብቻ ነው ዓላማ አድርገው የሚንቀሳቀሱት..ሁሌ ማትረፍን ብቻ ነው የሚያስቡት…ለእነሱ ዋናው ውጤት ነው …ምን ያህል አተርፋለው እንጂ በእኔ ማትረፍ ውስጥ እነማን ይጎዳሉ… ?የማን ቤት ይፈርሳል..?የማን ነፍስ ይነጠቃል ?አያስጨንቃቸውም..፡፡የአለም ሙሰኞች፤ ኮንትሮባንዲስቶች፤ቅጥረኛ ነፍስ ገዳዬች… ሀሺሽ ነጋዴዎች እዚህ ግሩፕ ውስጥ ይጠቃለላሉ..
ሶስተኛዎቹ ‹matcher› የሚባሉት ናቸው፡፡በሰጡት ልክ መቀበልን ይፈልጋሉ….ሁል ጊዜ በህይወት ሚዛን እየጠበቁ መጓዝ ዓላማቸው ነው…ዲፕሎማቶች ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናቸው…‹በሰጥቶ መቀበል መርህ› የሚጓዙ ናቸው… በዚህ ህግ ስትሰጥ በተሻለ መጠን እንደምትቀበል እርግጠኛ መሆን አለብህ››.እከክልኝ ልከክልህ…መመሪያቸው ነው፡፡
‹‹እና እኔ ከሶስቱ የትኛው ነኝ.?››አለኝ
‹‹እራስህን ፈልገዋ….አሁን ይብቃን እንሂድ….››
‹‹ስላልኩሽ ነገር እኮ ምንም አላልሺኝም...?››
‹‹እየሄድን መኪና ውስጥ ነገርሀለው….››
‹‹እሺ ››ብሎ ሂሳብ ሊከፍል አስተናጋጁን ደረሰኝ ሲጠይቀው..እንደተከፈለ ነገረው…
‹‹ማን ነው የከፈለው...?››አይን አይኔን እያየ ባለማመን ጠየቀኝ..የእኔም ጥያቄ ስለነበረ ልመልስለት አልቻልኩም
‹‹እዛ ጥግ ተቀምጦ የነበረው ሰውዬ ጥቁር ሱፍ ለብሶ የነበረው ..›› አስተናጋጁ አብራራልን
‹‹ማነው አውቀሺዋል….?››
‹‹አዎ፡፡ ተነስ እንሄድ በቃ…የእኔ ሰው ነው››አልኩት…
የአይኖቹ ቀለማት ሲቀየሩ ታወቀኝ
‹‹ምንድነው እንዲህ አይነት ነገር… ሰው በሰው ነገር እንዲህ ጥልቅ ሲል ሲያበሳጨኝ ..ከፈለገ ሌላ ቀን አይጋብዝሽም.?…››ይሄንን እጃችንን ታጥበን ከሆቴሉ እየወጣን በነበረበት ጊዜ ነው የሚነጫነጭብኝ..
‹‹ ምንድነው የደበረህ ….?ይክፈል…እንደውም ጥሩ ነው››
‹‹ለምን ይከፍላል .?አሁን አራት መቶ የማትሞላ ብር ከፈለ አልከፈለ ለእኔ ምኑ ነው ጥሩ…ጉረኛ በይው…››
ሁሉን ነገር ከማሸነፍና ከመሸነፍ ጋር የሚያገናኝ ምን አይነት ሰው ነው… .?አሁን አበሳጨኝ ‹‹እውነትህን ነው….እንደውም ብሩን ስጠኝ ልመልስለት…››አልኩት
ፈገግ አለ..‹‹የት ታገኚዋለሽ ወጥቷል እኮ››
‹‹አይ ያ ፊት ለፊት ያለው ብቲክ የእሱ ነው.. ስጠኝና አፍንጫው ላይ ወርውሬለት ልምጣ..ነገ ይሄንን እንደውለታ ቆጥሮ ሊለፋደድብኝ ይችላል››
ጥርስ በጥርስ ሆነ‹‹ ..በደስታ ብሩን አውጥቶ ሰጠኝ..‹‹ጠብቀኝ ››አልኩና አስፓልት ጠርዝ ላይ አቁሜው በዝብራ ተሸገርኩና ሁለት ልጆች ታቅፋ ለምትለምን ለማኝ እጆ ላይ አስጨበጥኮት ሴትዬዋ መብረቅ እንደመታት አይነት በድንጋጤ ፈዛ ለመጮህም ዳድቶት ስትርበተበት ፊቴን አዞርኩና መልሼ አስፓልቱን ተሸግሬ ወደእሱ ስሄድ እያጨበጨበ ጠበቀኝ …ሁኔታው የብሽቀት ነው…‹‹ጀግና ነሽ… ሸወድሽኝ ማለት ነው››አለኝ ለንቦጩን ጥሎ
‹‹አይ አልሸወድኩህም..አሁን ጋብዘኸኛል ማለት ነው….ስለዚህ ዘና ማለት ትችላለህ›› አልኩት
‹‹ግን ታውቂያለሽ አይደል …በጣም እብድ ልጅ ነሽ…የምትገርሚ እብድ…ነይ በይ ላድርስሽ..››
‹‹አይ.. አንተ በዚሁ ሄድ እኔ በዚች ጋ አቋራጬ መንገድ አለች …በዛ ሄዳለው.››
‹‹አረ ችግር የለም አደርስሻለው..››
‹‹ለራሴው ነው..በዚህ አቋራጭ አምስት ደቂቃ ነው የሚፈጅብኝ..አንተ ግን ገና መብራት ጠብቀህ አደባባይ ዞረህ 30 ደቂቃም አይበቃ..››
‹‹ይሁን ግን መልሱን አልነገርሺኝም እኮ...?››
‹‹እ እረሳውት ነገ 12 ሰዓት አይደል መነሻው ..እመጣለው..አንተም ባትለኝ ያ ፕሮግራም እንዲያመልጠኝ አልፈልግም››
‹‹ጥሩ ነው ስራውን ደግሞ ካዛ ስንመለስ ሰኞ ታመለክቺያለሽ..››
‹‹አይ አላመለክትም ቅዳሜ ወይም እሁድ እዛ ዝግጅቱ ላይ ሁሉም ሰራተኞች ባሉበት እኔን በተመለከተ በተሳሳተ መረጃ በማባረርህ ስህተት መስራትህን ተናግረህ ይቅርታ ትጠይቀኛለህ..ከዛ ሞራሌን በመንካትህ ለመካስ ይሄ ያልከኸውን አዲስ ቦታ በእድገት እንደሰጠኸኝ ለሁሉም ታበስራለህ….አንተ ራስህ እንደዛ ታደርጋለህ…እንደዛ ሲሆን ነው ሁሉ ነገር ተፈታ የሚባለው ከዛ እንዳልከው ስለሹገር ዳዲዬ እና ሰለ መፃሀፍ መደብሩ እናወራለን በል ቻው ››እልኩና ምንም እንዲናገር ዕድሉን ሳልሰጠው ፈዞ በደነዘዘበት ጥዬው ሄድኩ

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
.:
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_አምስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


እንዲህማ የእሷ መቀለጃ አልሆንም….እንዴ!!! ከሚገባት በላይ እኮ ፊት ሰጠዋት..አረ ፊት መስጠትም ብቻ አይደለም..ልቤንም ገልብጬ ነው የውስጥ ገበሩን ያሳየዋት….ካልጠፋ ሰው እሷን ምሳ ለመጋበዝ ጊዜዬን ማባከኔ ነው የሚቆጨኝ… መኪናዬን አስነስቼ ወደ ቢሮ እየተጎዝኩ ነው ፡፡ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰብኩ ያለውት..አሁን በቃ ይህቺን ልጅ እበቀላታለው…፡፡እንዲህ ፊጥ እንዳለችብኝ ልኳን እንድታውቅ እና ጥሩ ትምህርት እንድታገኝ አደርጋለው…፡፡አዎ የእሷን አንገት ለማስደፋት ያስችለኝ ዘንድ ዘዴዬን መቀየር አለብኝ…፡፡አዎ ምርጥ ሀሳብ መጣልኝ… ስልኬን አወጣውና ደወልኩ፡፡ ለሳምንት ስልኳን ማንሳት አሻፈረኝ ብዬ ሳበሳጫት ወደከረምኳት ፍቅረኛዬ ጋር……..
‹‹አንተ በህይወት አለህ……..?ይደብርሀል ብዬ ነው እንጂ ግራ ከመጋባቴ የተነሳ ቢሮ ሁሉ ልመጣ አስቤ ነበር…ምነው ይሄን ያለህ……..?.››ተንጣጣችብኝ
‹‹ ሳሮን…ትንሽ ስልክ የማነሳበት ሁኔታ ላይ አልነበርኩ››
‹‹እንዴ ቢያንስ ሚሴጄን አትመልስም…..?››
‹‹ይቅርታ አጥፍቼያለው..››
‹‹እንዲህ ይቅርታ በማለት ብቻማ አንላቀቅም…..››
‹‹እኮ ልክስሽ ነው…ነገ እና ተነገ ወዲያ ካምፓኒያችን የዓመታዊ በዓሉን በቢሾፍቱ ያከብራል…››
‹‹እና …..?››
‹‹እና እኔ ያው ሀለቃ እንደመሆኔ መጠን ከፍቅረኛዬ ጋር እንድገኝ እድሉ ተሰጥቶኛል..››
‹‹ከፍቅረኛህ ነው ወይስ ከባለቤትህ…..?››
‹‹ያው ሁለቱንም ቢሉ አንቺው ነሽ ሌላ ማን አለ…..?››
‹‹አስደሰትከኝ….እና ምን አድርጊ እያልከኝ ነው…..?››
‹‹እናማ ተዘጋጂ ..ነገ 1 ሰኣት መኪናዬ በራፍሽ ላይ ቆማ ትጠብቅሻለች …››
‹‹እውነትህን ነው…..?››
‹‹እውነቴን ነው..ደግሞ አሁን ትንሽ ብር በባንክ አስገባልሻለው ፤የመጨረሻ የምትይውን መዘነጥ ዘንጠሸ እንድትመጪ ነው የምፈልገው… ካልሆነ ብዙ ቆንጆዎች ሳላሉ ትነጠቂያለሽ…››
‹‹አረ እኔ ልጅት……በመዘነጥ ማን ጫፌ ደርሶ…›
ለነገሩ ጨቅጫቃ ባትሆኚ በመልክና በመዘነጥ እንኳን ማንም ስርሽ አይደርስም…በተለይ በመዘነጥ›› በውስጤ ነው ያጉረመረምኩት …ስልኩን ከመዝጋቴ በፊት ግን..ትራፊክ ያዘኝ…ስልኩን ዘግቼ አንሸራትቼ ብለቀውም ትራፊኩ አልተሸወደልኝም..ምን ነካኝ አንዲህ አይነት ቀሺም ባህሪ እኮ አልነበረኝም….
ጥዋት ሳሮን ጋር ስደርስ አንድ ሰዓት ከሩብ ነበር፡፡እውነትም በዝነጣ ማን ጫፍሽ ይደርሳል….…..?ነው ያልኩት ገና እንዳየዋት …ዓይኖች ሁሉ ዛሬ የእኔዋ ንግስት ላይ ሲንከባለሉ መዋላቸው ነው…..በተለይ ያቺ ትዕቢተኛ …እሷ እንደሆነ ለጥሩ ምላስ እንጂ ለጥሩ አለባበስ ደንታ የላትም…. በደስታ እየተፍለቀለቅኩ እሷን ይዥ ቢሮ ስደርስ አንድ ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡
እሷን እዛው መኪና ውስጥ እንድትጠብቀኝ አድርጌ ወረድኩና ወደቢሮ ግቢ ሄድኩ ….. አንድ ባስና፤ አንድ ሚኒባስ ቆሟል …ሰው ይተራማመሳል…አቶ ሰይፉ እንዳዩኝ በደስታ እየተፍለቀለቁ ወደእኔ መጡ..‹‹እንዴት ናችሁ… ሰው ሁሉ መጣ …..?›ለሰላምታ የዘረጉልኝን እጃቸውን እየጨበጥኩ ጠየቅኳቸው…
‹‹የመጡ ይመስለኛል …….አሁን ወደ መኪና እየገቡ ነው ..ለማጣራት እንዲመቸን መኪና ውስጥ ከገቡ ቡኃላ ይሻላል..ሁሉም መጥተው ከሆነ ….ከአስር ደቂቃ ቡኃላ እንነሳለን……..››
…በአምስት ደቂቃ ውስጥ ሁሉም ወደየመኪኖቹ ገብተው ቦታ ቦታ እንዲይዙ ተደረገ ..የእኔ አይን አንድ ሰው እየፈለገ ነው…. እስከአሁን አላየዋትም…ቆይ ወደባስ ውስጥ ገብታ ይሆናል …ብዬ ባስ ውስጥ ገባውና ሰራተኞችን ሰላምታ ለመስጠት በሚመስል ሁኔታ ፊት ለፊት ቆሜ እጄን ለሰላምታ እያውለበለብኩ አይኖቼን ከጥግ እስከጥግ አንከባለልኩ…. ባሱ ባዶ ነው..ማለቴ እሱማ ሙሉ ነው እሷ የለችም እንጂ …‹‹መልካም ጉዞ ››ብዬ ከባሱ ወረድኩና ወደ ሚኒባሶ ሄድኩ…ገብቼ ተመለከትኩ .. እዛም የለችም…
አቶ ሰይፉን አስጠራዋቸው…እያለከለኩ መጡ
‹‹እሺ ጨረሳችሁ…..?››
‹‹አዎ ሁሉም ተሞልተው መጥተዋል..ልንቀሳቀስ ነው››
‹‹እርግጠኛ ናችሁ…››
‹‹አዎ መዝገቡን ዘርገግተው በየስሙ ፊት ለፊት ረይት የተደረገበትን እያሰዩኝ… እይ አመስት ሰዎች ናቸው የቀሩት እነሱ ደግሞ በተለያየ ምክንያ መሄድ እንደማይችሉ ቀድመው አሳውቀዋል…››
ዙሪያ ጥምዝ መሄድን አቁሜ ‹‹ፊናንስ››
‹‹ፊናን እ..ረስቼት ነበር››
‹‹እንዴት ይረሷታል…..?››አልኳቸው …እስቲ ምን ማለቴ ነው…..?፡፡እሷ የእኔ ችግር እንጂ የእሳቸው ችግር አይደለችም፡፡
‹‹አይ ያው ስራ ለቃለች ብዬ ነዋ…. ትናንት ግን ደውዬላት ልመጣ እችላለው ብላኝ ነበር… ቆይ እስኪ ልደውልላት ›› አሉና ስልካቸውን አውጥተው ደወልሉላት…..ስልኳ አይሰራም
‹‹ታዲያ ምን ይሻላል…..?››ጠየቅኳቸው…ልክ ዝግጅቱ ሰርግ ሆኖ እሷ ደግሞ የሰርጉ ሙሽራ ሆና እንደዘገየች ነገር አንገቴን በሀዘን ሰብሬ
‹‹ረፍዶባትም ከሆነ በትራንስፖር መምጣት ትችላለች ..ስልኳን ስትከፍት እንድታየው መልዕክት ልክላታለው››ብለውኝ ወደስራቸው ሄዱ…
‹‹እኔም እያግረመረምኩ በራፉ አካባቢ በጥበቃ ስራ ላይ ወደነበረው ዘበኛ ሄድኩና የምፈልገውን ነገር ነገርኩት ..ከዛ ወደመኪናዬ አመራው፡፡እንደደረስኩ ‹‹ፍቅር ውጪ››አልኳት
‹‹ምነው..አንሄድም እንዴ…..?››
‹‹አይ ምን አንቀዠቀዠን…እነሱ ይቅደሙን… ቁርስ በልተን ቀስ ብለን እንከተላቸዋለን..››ብዬ ፊት ለፊት መንገድ ተሸግሮ ወደሚገኝ ካፌ ይዤት ገባውና ለእይታ የሚመች ቦታ መርጠን ተቀመጥን….ባሱም ሆነ ሚኒባሱ ተከታትለው ሲወጡና ሲሄዱ እያየው ነው…ቁርሱን አዘን ቢመጣም ለአመል ያህል ከመነካካት ውጭ የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም …አይኔ ቢሮችን በራፍ አካባቢ እደተሰካ ነው…..አሁን ፌናንን እየጠበቅኩ ነው ብላችሁ መቼም አትታዘቡኝም….ምን አልባት አርፍዳ ብትመጣ ወደዝግጅቱ ቦታ የምትመጣበት መኪና አጥታ እንዳትቀር ስለሰጋው….ካልመጣች እኮ እቅዴ ሁሉ በዜሮ ተባዛ ማለት ነው፡፡ ዘበኛው በነገርኩት መሰረት ከወዲህ ወዲያ እየተንጎራደደ እየጠበቃት ነው..እንደመጣች እንዲደውልልኝ ተነጋግረናል.. ቢሆንም በእሱ ላይ ብቻ እምነቴን ጥዬ ቁጭ ማለት እቻልኩም…አይኖቼ እዛው እንደተሰኩ ናቸው…
‹‹ከደቂቃዎች በፊት ፍልቅልቅ ነበርክ አሁን ደግሞ… ››አለቺኝ ሳሮን
‹‹አሁን ምን ሆንኩ…..?››
‹‹እኔ እንጃ…. ገባያ የሄደች እናቱን የሚጠብቅ ህጻን ልጅ ነው የምትመስለው..››
‹‹ትንሽ የፕሮግራሙ ቅንጅት ጥሩ ስላልመሰለኝ ነው እንጂ የምትይውን ያህል ምንም አልሆንኩም...››
‹‹ታዲዬ ምን አስጨነቀህ…..? ››
‹‹እንዴ ምን ለማለት ፈልገሽ ነው……..?አሁን ምኔ ነው የተበሳጨ የሚመስለው…››ሰዓቴን ተመለከትኩ ሁለት ከሩብ ሆኖል …አንድ ሰዓት ድረሺ የተባለች ሴት ሁለት ከሩብ ድረስ ዘግይታ ትመጣለች ብሎ ማሰብ የዋህነት መሆኑ ስለገባኝ
‹‹በይ ከጨረሽ ተነሺ እንሂድ ››አልኳት
‹‹እሺ ››አለችና ተነሳች….ተያይዘን ካፌውን ለቀቅንና ቢሮ በራፍ ላይ ወደ ቆመችው መኪናችን አመራን….. ልክ እንደደረስን ዘበኛው እየተንቀዠቀዥ ወደ እኔ ሮጦ መጣና ‹‹ጌታዬ አልመጣችም››አለኝ ….‹‹እሺ›› አልኩትና ተጨማሪ ነገር እንዳይናገር ፊትን ከስክሼበት ፈጠን ብዬ መኪና ውስጥ ገባው እና እሷም እስክትገባ ጠብቄ መኪናውን አስነሳውት …ወደቢሾፍቱ ጉዞ ጀመርን….
‹‹ማነች…..?››አመዴን ቡን አደረገችው ..
‹‹ምኗ…..?››
‹‹ስትጠብቃት የነበረችው ሴት…አሁን ዘበኛው እንዳልመጣች የነገረህ ልጅ››አቤት የሴት ደመ ነፍስ
👍2
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ስድስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


...ወደ ደብረዘይት በራሴ መኪና ለመሄድ የወሰንኩት ከነጋ ቡኃላ ነው፡፡አባቴ ሀሳቤን ተቃውሞኝ ነበር…
‹‹ህብረት የመፍጠሪያ እና ወዳጅነትን ለማጎልበት ታስቦ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ለብቻ ተገንጥሎ መሄድ ጥሩ ስሜት አይፈጥርም ››አለኝ.
‹‹እንዴ ምን ችግር አለው..?››
‹‹ችግርማ አለው… አንዳንዴ ማድረግ ስላቻልሽ ብቻ ሁሉን ነገር የግድ ማድረግ አይኖርብሽም…አንቺ በግል መኪናሽ ስትሄጅ ሌሎች የስራ ባለደረቦችሽ ላይ ምን አይነት ስሜት ነው ሊፈጥር የሚችለው….በተለይ እኔ እና አንቺ ለእንዲህ አይነት ጉራ ስንል ያለንን ነገር መጠቀም አያምርብንም››አለኝ
‹‹እንዴት አባ..? ለምን …...?ማን ይከለክለናል..?››ጥያቄዬን ደረደርኩለት
‹‹የእኛ አይደለማ ..ሰርተን የገዛነው መኪና አይደለም..የእናትሽ ላብ ነው››
‹‹እንዴ…. !!!እናቴ ታዲያ የእኔ አይደለች..?››
‹‹…እናትሽ ያንቺ ነች ማለት ንብረቷ ሁሉ ያንቺ ነው ማለት አይደለም…››
‹‹አባ አንተ ደግሞ..ደግነቱ እናቴ እንደአንተ አታስብም…›› ሀሳቡ ውስጤ ገብቶ ቢቧጥጠኝም ምክሩን ሰምቼ ግን መኪናውን ጥዬ ለመሄድ አልፈለኩም…..መኪና መያዜ ከሰውዬው ጋር ላለኝ ወሳኝ ፊልሚያ ያግዘኛል የሚል ግምት አሳድሮብኛል፡፡እና ቀድሜ ደብረዘይት በመድረስ የተቀበልኳቸው እኔ ነኝ፡፡ቡድኑ ያረፈው ቢን ኢንተርናሺናል ሆቴል ነው፡፡ለአለቅዬ ብቻ ሆቴሉ አይመጥነውም ተብሎ አሻም አፍሪካ ሆቴል ነው የተያዘለት…ሰው ሁሉ እንደ አመዳደቡ ሁለት ሁለት እየሆነ በየክፍሉ እየገባ ባለበት ሰዓት እኔ ሆቴሉ በረንዳ ላይ አረፍ ብዬ ማኪያቶ ነገር በመጠጣት ላይ ሳለው አቶ ሰይፉ ወደእኔ መጡ…..
‹‹ፌናን ላስቸግርሽ ነው..?››
‹‹ምነው ምን ቸገሮት..?››
‹‹ባክሽ ሰውዬችን መኪናዬ ተበላሽታብኝ አጉል ቦታ ቆሚያለው ብሎ ደወለልኝ ..…ሚኒባሶ መካኒክ ፍልጋ እስክትሄድ እዛ እንዳይቸገር ባንቺ መኪና ሄደሽ ብታመጪው…..መኪናውን ልጆቹ አሰርተው ያመጡለታል››
‹‹ችግር የለውም እርሶ አዘውኝ እንዴት እምቢ እላለው ››ብዬ ከመቀመጫዬ ተነሳውና መኪናዬን ወደአቆምኩበት ሄድኩ….አጋጣሚው ደስ ብሎኛል…ገቢና ከጎኔ አስቀምጬ እየነቆርኩት ይዤው መጣለው…ሀሳቤ እንደዛ ነበር..
ስደርስ ያላሰብኩት ነገር ነው የገጠመኝ… ከሰው ጋር ነው…ደስ አላለኝም..ለምን ደስ አላለኝም…..?አይ እንዲሁ ይመስለኛል..በቃ አለ አይደለ ብቻውን ነው ብዬ ሰለገመትኩ መደናገር ተፈጥሮብኝም ይሆናል…፡፡
መኪናዬ አቁሜ ወደ እነሱ እየሄድኩ ነው ያሰብኩት…ከእነሚስቱማ አልጭነውም….ይዣቸው ከመሄዴ ለመገላገል የመኪናዋን ብልሽት ቀላል ከሆነ እስኪ ልየው…እድሜ ለአባቴ የመኪና የአካል ክፍል ብትንትን አድርጌ እንዳውቅ አድረርጎኛል…ጫን ያለ ብልሽት ካልሆነ በስተቀር የእኔንም ሆነ የአባዬን መኪና ቱታዬን ለብሼ መሬት ላይ እየተንከባለልኩና በዘይት እየተጨመላለቅኩ የምጠግነው እና ሰርቢስ የማደርገው እራሴው ነኝ….
እሱ ባለበት አቅጣጫ ወደመስኮቱ ተጠጋው..እኔን በማየቱ እጅግ ደንግጦል…እንደህጻን ልጅ ነው የተረብተበተው..እንደዛ ሲርበተበት ደግሞ እኔ ውስጤ እንዲቁነጠነጥና ..መቁነጥነጤን ተከትሎ እንድሾርበት አስገደደኝ..፡፡ያው እንደከዚህ ቀደሙ.. ከዛም ትንሽ ከፍ ባለ ደረጃ ተሸቀርቅሯል…፡፡መቼስ የካምፓኒ ማናጀር ለመሆን ከመዳከር ይልቅ ፕሮፌሽናል ሞዴል ለመሆን ትንሽ ቢጥር አመት ሳይሞላ የሀገሪቱ አይኖች ሁሉ ማረፊያ ይሆን ነበር….፡፡እሷም ቆንጅዬ ነች …አዘናነጧ ግን ጭንቀት የወለደው አይነት ይመስላል…እሱን ላለማሳጣት እየጣረች በሚመስል ሁኔታ....፡፡ግን ምን ማለቴ ነው....?እየተናገርኩ ያለውት እኮ ትርጉም የሚሰጥ አይነት አይደለም..፡፡ጭንቀት ያለበት አዘናነጥ ማለት ምን ማለት ነው…..?እንደውም እኔ ስለእሷ የሰጠውት አስተያየት ይመስለኛል ከጭንቀት የተወለደው…፡፡ለማንኛውም የመኪናውን ኮፈን አስከፍቼ ስመረምረው ብልሽቱ አስቂኝ ነበር…ለማስተካከል ግማሽ ደቂቃ አልፈጀብኝም…እንደዛ በመሆኑ ደግሞ የተሰማኝ ስሜት ልነግራችሁ አልችልም…
…. አሁን ከኃላ እየተከተልኳቸው ነው…..በእስፖኪዬ ወደኃላ እያየኝ መሆኑን በደንብ አውቃለው…ከተማ ውስጥ ገብተን ጌትሼት ጋር ስደርስ ነበር ሚኒባሶ መካኒክ ይዛ ስትመጣ አግኝተን የመለስነው…..
የመጀመሪያው ፕሮግራም ከምሳ ግብዣ ነበር የሚጀምረው...እዛው ብዙሀኑ ያረፈበት ሆቴል እየተጫወትን ከበላን ቡኃላ በወጣው ፕሮግራም መሰረት በከተማዋ መታየት ያለባቸውን ቦታዎች ወደማየት ነው ያመራነው …ስምንት ሰዓት ሲሆን ተንቀሳቀስን፡፡
መቼስ ቢሾፍቱን ስትጎበኝ በዋናነት በሁሉም አዕምሮ ሚመጣው ሀይቆቾ ናቸው..ቢሾፍቱ ፤ሆራ ፤ባቦጋያ ፤ኩሪፍቱ፤ጨለቅለቃ.. መቼስ መታደል ነው…አንድ መለስተኛ ከተማ ይሄ ሁሉ ሀይቆች ባለቤት መሆን በራሱ ትልቅ ድልብ ሀብት ነው፡፡ለከተማዋ ብቻ አይደለም ለሀገሪቱም ጭምር..፡፡በዛ ለይ ከመዲናዋ 50 ኪሎ ሜትር ብቻ እርቃ መገኘቷ….ለአንድ ቀን እንኳን ለስራ ወደሀገሪቱ የመጣ ሰው ጎራ ብሎ አንድ ሁለት ሰዓት ዘና ብሎ ሊመለስባት በሚችልበት ቦታ ላይ መገኘቷ ሌላ እድል ነው…ግን ከተማዋም ሆነች ሀገሪቱ 5 ፐርሰንቱን እንኳን አልተጠቀመችበትም…አለም አቀፍ ቱሪስቶችን በልዩ ሁኔታ እንዲስብ ተደርጎ ፕሮሞሽን አልተሰራለትም… ፡፡ሌሎች ሀገሮች መሰል የተፈጥሮ ፀጋ ባለመታደላቸው አርቴፊሻል ወንዝ እና ሀይቅ በመስራት የቱሪስት ገቢያቸውን በሚያጧጡፈበት በዚህ ቴክኖሎጂ በመጠቀበት ዘመን እኛ ግን ተፈጥሮ በቸርነቷ የለገሰችንን የነፃ ችሮታ እንዲሁ ባልባሌ ሁኔታ ለዘመናት በማባከነ ስንዴ እንለምናለን…ያሳዝናል፤የእኔ ነገር ሳላስበው ወደንጭንጬ ገባው…ለዛውም በዚህ ዘና በማያ ቀኔ… ..ቅድሚያ ሆራ ሀይቅ ነው የሄድነው…ሆራ በከተማዋ ካሉት ሀይቆች በስፋት ትልቁ ነው..ዙሪያውን በተራራ የተከበበ ሲሆን ተራራው ላይ ደግሞ ዘመናዊ የሚባሉ ሎጆችና ሆቴሎች አልፎ አልፎም ቢሆንም ታንፀው ወደአካባቢው ለመዛናናት የሚመጡትን ቱሪስቶች ሆነ ሀገርኛ ቱሪስቶችን ለማስተናገድ እየሞከሩ ነው ፡፡አሪፍ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው ..አብዛኛው በጀልባ ባህሩን ሰንጥቆ በመጓዝ ተዝናንቷል....12 ሰዓት ወደየአረፍንበት ሆቴል ነው የተመለስነው..ለማታ እራት ፕሮግራም ለመዘጋጀት….የእራቱ ፕሮግራም ፕራሚድ ሆቴል ነው የሚከናወነው፡፡አንድ ሰዓት ሁሉም እዛ ተሰባስቦ መገኘት አለበት፡፡
አንድ ሰዓት ከሩብ ሲል ፕራሚድ በሚገኝ የስብሰባ አዳራሽ ሁሉም ስታፎቻችን ቦታቸውን ይዘው ለፕሮግራሙ ዝግጁ ሆነው ነበር…ልክ እንደባለፈው አመት ዘንድሮም የፕሮግራሙ መሪ እኔ ስለሆንኩ ወደ መድረኩ ወጥቼ ሁሉንም አንዴ ቃኘው…የካምፓኒው ከፍተኛ ሀላፊዎች አለቃዬንና ሚስቱን በግራና ቀኝ አጅበው የፊተኛውን ረድፋ ላይ ተደርደረረዋል፡፡
ጉሮሮዬን አፀዳዳውና ማይኩን ፈታትሼ ንግግሬን ጀመርኩ…
‹‹››የተከበሩ የድርጅታችን ስራ አስኪያጅ ፤ እኛን አክብረው በመሀከላችን የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ የተከበሩት የስራ-አስኪያጃችን እጮኛ….የተከበራችሁ የስራ መሪዎችና ድንቅና ምርጥ የካማፓኒያችን ሰራተኞች እንኳን ለዚህ አመት የካማፓኒያችን ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ …አደረሰን፡፡…››
አደራሹ በጭብጨባ ተናጋ…
ፋታ ወስጄ ንግግሬን ቀጠልኩ፡፡
…የዚህ ዓመት በዓላችን ከዚህ በፊቱ የተለየ ይሆናል ፡፡አንደኛ በዓላችን ነው..ሁለተኛ ወጣቱንና እና ካምፓኒያችንንም ሆነ የእያንዳንዱን ሰራተኛ የግል ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋሉ ብለን ሁለችንም ተስፋ
👍1
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ሰባት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍሰሀ

...ከአዳራሹ ሳይሆን ትንሽ ወደኃላ ተመልሼ ልጀምርላችሁ፡፡ እስከ አሁን አዋዋላችን በጣም ግሩም የተባለ ነበር..ከተለያዩ ሰራተኞችም ጋር በየምክንያቱ የመነጋገር ስሜታቸን ማዳመጥ፤ የመቀላለድ እና እስከዛሬ ከነበረው በተሸለ የመግባባት አጋጣሚውን ስንጠቀምበት ነበር የዋልኩት…ከፌናን ጋር ግን ከሩቁ ከመተያየት በስተቀር ፊት ለፊት የመገናኘቱ አጋጣሚ አልነበረም….ምን አልባት ሰላም ያዋልኩትም እንደዛ ስለሆነ ይሆናል..የማታውን ፕሮግራም ለመጀመር አዳራሽ ከገባን ቡኃላ ከቀኑ ከነበረው አለባበሷ በተቃራኒ በጣም ረጅም ግን ደግሞ በተመሳሳይ ውብ ያደረጋትን ደማቅ ቀይ ቀሚስ ለብሳ ወደመድረኩ ስትወጣ ነበር ያየሆት…
ምትፈልገው የሆነ ዕቃ ኖሮ እሱን ለመውሰድ ወደ መድረክ የወጣች ነበር የመሰለኝ ግን ተሳስቼ ነበር… ፊት ለፊት ቆማ …ልክ ለአመታት የመድረክ ልምድ አንዳለው ፓለቲካኛ በሙሉ በራስ መተማመን ንግግሯን ጀመረች….እኔ እራሱ ምን አይነት እንከፍ ነኝ..እስኪ ቀደም ብዬ ፕሮግራማቸውን ባየው..እርግጠኛ ነኝ ከአስር ደቂቃ ባፊት እንኳን አውቄ ቢሆን እዚህች መድረክ ላይ እንድትወጣ ፈጽሞ አልፈቅድላትም ነበር…. ከመጀመሪያው ንግግሯ ነው የነገር ጦሮን በስውር የወረወረይብኝ..እስኪ እዚህ ሁሉ ሰው መካከል አቶ ፍሰሀና እጮኛቸው ማለት ምን ማለት ነው……..?እጮኛዬ ትሁን አትሁን አልነገርኮት ከየት አባቷ አወቀች…..?አቤት ወስጤ እንደተቃጠለላችሁ ..ሰውነቴ ሁሉ ሲንቀጠቀት ይታወቀኛል…ደግሞ ይህቼ ከጎኔ የተቀመጠችው መፍለቅለቅ ምን የሚሉት ነው…?የማንም ስርዓት አልባ መድረክ ላይ ወጥታ በዘጠና ምናምን ሰዎች ፊት‹‹.. የፍሰሀ እጮኛ… ››ብላ ስለተናገረችላት የእውነት እጮኛዬ የሆነች መሰላት እንዴ..?አናደደቺኝ……..
ከዛ አስተዳዳሪው ወጣ..የካማፓኒውን ሪፖርት እያቀረበ ቢሆንም ምን እንደለ አንዱንም አልሰማው…እያብሰለሰልኩ ያለውት ስለእዛች የተረገመች ልጅ ነው…እንዴት አድርጌ ነው አንገቷን ላስደፋ የምችለው….…እግዜር ይስጠው ሽማግሌው ሪፖርቱን አላንዛዛውም…ጨርሶ አመስግኖ መድረኩን ለዛች እብድ ለቀቀላት….እሷ ማለት ያቺ የተረገመች ወጥታ ስትናገር ብዙም ቁብ አልሰጣዋትም ነበር ..ግን ሽማግሌው ያቀረበውን ሪፖርት እያብራራች እየበታተነች ሳልወድ በግድ እየመረረኝ እንድሰማውና አደረገች…
ከፍተኛ ጥቃት ነው የተፈፀመብኝ ..በእኔ ብቻ አይደለም በካማፓኒውም…..ሰራተኞቹን ጠቃሚ ከሆኑት በላይ ጠቃሚ እንደሆኑ እዲሰማቸው…በትዕቢት ልባቸው እንዲወጣጠርና ነገሮች ለእኔ ከባድ እንዲሆኑብኝ ያሴረችው ሴራ ነው በእያንዳንዱ የዋህ ሰራተኛ አዕምሮ በጥበብ የበተነችው ..አዎ ንግግሯን ሰምተው ያጨበጨብላት ሰራተኞቹ የተናገረችው ሁሉ ለእነሱ አስባ ይመስላቸዋል…የእሷን ሴራ እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው…እንደውም እሷን ማባረሬ በጣም ትክክለኛ ውሳኔ ነው..እና ይቅር ብያት እንድትመለስ የማስበውን ነገር ትቼዋለው..ለዚህችማ አይገባትም…ይህቼ ወጥ ረጋጭ ካቅሟ በላይ የምትንጠራራ… መኪና ተከራይታ ወይም ደግሞ ከሹገር ዳዲዋ ተውሳ እዚህ ይዛ በመምጣት ለመጎረር የምትጥር ከአቅም በላይ ለመኖር ስቃዬን ለምታይ ሴት ማዘን…
ወደመድረክ ስትጋብዘኝ የውስጥ ስሜቴ እየተተረማምሰ ነበር…የተዘጋጀውበትን ንግግር ሁሉ ቃላቶች ብትንትን ብለው ከአዕምሮዬ ተሰደዋል…ብቻ በደመነፍስ ወጣውና ወደጆሮዋ ጠጋ ብዬ‹‹በጣም በጣም ባለጌና መሰሪ ልጅ ነሽ ››አልኳት…ቆሽቴን እንዳሳረረቺኝ ቆሽቷን ላሳርርረው ብዬ..እሷ እቴ ምን በወጣት የመረቅኳት ይመስል ፈገግ ብላና ድምጽን ለሁሉም እንዲሰማ አድርጋ ‹‹አመሰግናለው አቶ ፍሰሀ …በእውነት ለካምፓኒዬ እና ለምወዳቸው የስራ ባለደረቦቼ ከዚህ በላይ መናገር ችዬ ብናገርና ባገለግል ደስ ይለኛል››ብላ ጭራሽ ያረረው ቆሽቴ እንዲከስል አድርገ መድረኩን ለእኔ በመልቀቅ ከኃላዬ ቆመች….

❤️ፌናን

የማታውን ፕሮግራም አትጠይቁኝ…ብዙሀኑ የተደሰቱበት እኔና ሰውዬው በየምክንያቱ በተገናኘን ቁጥር ስንጠዛጠዝና ስንነቋቆር ያሳለፍንበት ገራሚ ምሽት ነበር…በተለይ ፍቀረኛው የእኛኑ እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ስትከታተልና ስትጠብቀን ነው ያመሸችው…አራት ሰዓት ሲሆን ይዛው ትሂድ ወይም ይዟት ይሂድ አላውቅም ብቻ ተያይዘው ወጡ….ወደ ማደሪያቸው…
እኔም ከ30 ደቂቃ ቡኃላ ቡድኑን ተለይቼ ወደማደሪያዬ ሄድኩ…..ገብቼ አልጋዬ ላይ እንደተዘርርኩ ነበር እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ ያለው....ትንሽ መጠጥ የቀማመስኩ ጊዜ እንዲሁ ነው የሚያደርገኝ…ክፋቱ እንቅልፌ ቶሎ ያልቅብኛል…ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ ሙለ በሙሉ እንቅልፌን ጨርሼ ፈጠጥኩ…እዛው እየተገላበጥኩ በውስጤ የሚተረማመሰውን ሀሳብ ማመንዠግ ቀጠልኩ… በዚህ ውድቅት ለሊትም ሀሳቤ ስለእሱው ነው….ምን እየሰራው ነው…….?ከልጁ ጋር ምን እንደዚህ አይነት ጫወታው ውስጥ አሰጋባኝ..….? እሱ አልሸነፍ ባይ ስለሆነ ነው..ወይስ እኔ የማሸነፍ ሱስ ስላለብኝ….….?ነው ወይስ ቀጥታ ከአላማዬ ጋር የሚገናኝ ትግል ነው…….?እንዴት እንደዛማ አይሆንም የእኔ ዓላማ በእሱ መሸነፍ ላይ እንደማይመሰረት እርግጠኛ ነኝ..እና ምንድነው ችገሬ…….?ይሄንን ሳስብ የለበስኩትን አንሶላና ብርድልብስ ከላዬ ገፍፌ ከአልጋዬ ወረደኩ….አፍቅሬው ብቻ እንዳይሆን…….?ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ…….?ቆይ እስኪ ፍቅር እንዴት ነበር..….? አውቃለው እንዴ…….?
በሀያ አመቴ አካባቢ አንድ ሁለት የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ጋር ፍቅር ፍቅር መጫወት ጀምሬ ነበር..ግን እኩዬቼ ቢሆንም እኔ በማስበው ልክ ሊያስቡልኝ ስላልቻሉ..እኔ ፍቅርን በምተረጉምበት ልክ ሊተረጉሙልኝ ሳላልቻሉ ከአንዱ ጋር አንድ ወር ከሌለኛው ለሶስት ወራት ብቻ ነበር አብረን መዝለቅ የቻልነው…፡፡ያው ወንዶች ከሴት በእኩል ዕድሜ ሊበስሉ እንደማይችሉ ዘግይቼ ነው የተረዳውት…ማለት ያው የ18 ዓመት ሴት አንድ ቤትን እማወራት ሆና በደንብ ማስተዳደር ትችላለች አንድ የ18 ዓመት ወንድ ግን እራሱንም የማስተዳደር ብቃት ላይ አይደርስም…የድሮ አባቶቻችን እንዲሁ በዘፈቀደ አይደለም ወጣቶችን ሲያጋቡ ቢያንስ ወንዱ ከሴቷ በ5 ዓመት ቢበልጣት ጥሩ እንደሆነ የሚመክሩት እና እንደዛም እንዲሆን በተቻላቸው መጠን የሚጠነቀቁት…
የእሳትነቱን ዘመን ካለፍኩ ቡኃላ ደግሞ ፍቅርን በተመለከተ አንድ ቅድመ ሁኔታ ለራሴ አስቀመጥኩ… የማፈቅረው ሰው እኔ እንደምወደው እሱ ግን እንክትክት እስኪል ድረስ እንደሚያፈቅረኝ እርግጠኛ ስሆን ብቻ ነው እጄን ዘርግቼ ልቀበለው የምችለው፡፡ይሄን ለምን እንዳልኩ ማስረዳት አለብኝ መሰለኝ..ወንድ ልጅ በደንብ እንዳፈቀራት እርግጠኛ ሳትሆን እጇን የሰጠችና ወደጋብቻ የገባች ሴት ብዙ ጊዜ ከሳሪ ነች፡፡ምክንያቱም አብዛኛቹ ወንዶች የፍቅር ጫፍ ላይ የሚደርሱት በመጀመሪያዎቹ የፍቅር ጊዜያቶች ነው…ከዛ ወደግንኙነት ሲገቡ ፤ ከዛም አልፎ ወደ ትዳር ሲሸጋገሩ የማፍቀር መጠናቸው እየወረደ ነው የሚመጣው..ቢያንስ በግንኙነት ፍቅር ላይ የነበረ ስሜቱ ወደ ትዳር ሲገባ መውደድ ላይ አርፎ እንዲረጋጋ ከፍቅር መጀመር አለበት....ለሴት ልጅ ግን ተቃራኒው ነው ፡፡በግንኙነት እና በመላመድ ስሜቷ እያደገና እየጎለበተ ነው የሚመጣው.. ፡፡ በግንኙነት ወቅት መውደድ ከቻለች፤በትዳር ውስጥና በመላመድ ወደላይ ነው የምታሳድገው ወደፍቅር …አብዛኛዋ ሴት እንደዚህ ነች…እና እኔም የምወደውን እና እሱ ደግሞ የሚያፈቅረኝን እንዳገኘው እርግጠኛ እስክሆን ድረስ ለማንም ልቤን ከፍቼ አልሰጥም፡፡ለዚህ ፍሰሀ ለሚባለውም ቢሆን
👍31